Monday, July 15, 2013

የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች ሕዝበ ክርስቲያኑ ከጎናቸው እንዲቆም ጠየቁ


የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች አመጽ እንደቀጠለ ነው። ደቀመዛሙርርቱ (ተማሪዎቹ) ሕዝበ ክርስቲያኑ ከጎናቸው እንዲቆም በመጠየቅ በዛሬው የሥላሴ ክብረ በዓል ላይ የሚከተሉትን መፈክሮች አሰምተዋል።
የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅን መዝጋት ታሪክን ማጥፋት/ማበላሸት ነው!
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ችግራችንን ይመልከት!
ልጆቹን የማይጠይቅ አባት አለን?
ሙስናንና ኑፋቄን የሚያደቅ ክንድ አለን!
የምንማረው በምእመናን ብር ነው፡፡ ሌቦች ሆይ፣ እጃችኹ ይሰብሰብ!
ጢሞቴዎስ ሆይ፣ አደራህን ጠብቅ፡፡ (፩ኛጢሞ. ፬÷፳)
ችግራችንን የሚሰማንና መፍትሔ የሚሰጠን አባት ዐጣን!
የቅ/ሲኖዶሱ አባላት ትኩረት ይስጡን!
ሙስናን በቃል ሳይኾን በተግባር እንዋጋ!
ተማሪዎች ሙስናን በመዋጋታቸው ሊበረታታቱ እንጂ ሊባረሩ አይገባም!
ከአየህጉረ ስብከቱ ቤተ ክርስቲያንን አምነን ወጥተን ለረኀብ ተጋለጥን፡፡
ኮሌጁ በመዘጋቱ ከተመገብን ሰባተኛ ቀናችን ነው፡፡
አቤቱ የኾነብንን አስብ፡፡
ኮሌጁን የሚዘጋው የከፈተው ሲኖዶስ ነው፡፡
ኮሌጁ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንጂ የግለሰቦች አይደለም!
እውነትን ሙስና አይደለም መቃብር አያሸንፈውም!
ጌታ ሆይ፣ ከመቅደሳችን ውስጥ የሙስናን እሾኽ ንቀል!
እየሞትንና እየተራብን ሙስናንና ዘረኝነትን እንቃወማለን!
ሙስና ከቤተ ክርስቲያናችን ይወገድ!
ከሓላፊነት መሸሽ በራሱ ሙስና ነው!
ሐራ ተዋሕዶ ድረ ገጽ እንደዘገበው በነገው ዕለት በመንበረ ፓትርያሪኩ በሚያካሂዱት ከፍተኛ የተቃውሞ ትዕይንት ምእመኑ ከጎናቸው እንዲሰለፍ ጥሪያቸውን አቅርበዋል
አቡነ ጢሞቴዎስ ደቀ መዛሙርቱን በፖሊቲከኝነት መወንጀል ጀምረዋል
የተማሪዎች መማክርት የኮሌጁን አስተዳደር በሕግ ለመጠየቅ እየተዘጋጀ ነው
St Trinity College Disciples demonstrating at the gate of the Patriarchate
ደቀ መዛሙርቱ በመንበረ ፓትርያሪኩ ቅጽር በተቃውሞ ትዕይንት ላይ
ምእመናን ቤተ ክርስቲያን ከመሳለምና ገንዘብ ከመስጠት/ከመመጽወት ባሻገር ስለ ቤተ ክርስቲያናቸው ጉዳይ በመጠየቅ ቀጥተኛ ተሳታፊ መኾን እንደሚገባቸው የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት አሳሰቡ፡፡
ደቀ መዛሙርቱ ማሳሰቢያውን ያስተላለፉት፣ በዛሬው የቅድስት ሥላሴ ክብረ በዓል አጋጣሚ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ለተገኘው ምእመን የኮሌጁ አስተዳደር በትምህርት አመራሩና በአካዳሚያዊ መብቶቻቸው ላይ ስለሚፈጸመው በደል በገለጹበት ወቅት ነው፡፡
አንጋፋው የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ÷ ሊቃነ ጳጳሳትን፣ የመምሪያ ሓላፊዎችን፣ የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎችን፣ የዩኒቨርስቲ መምህራንን፣ ተመራማሪዎችን፣ በመንግሥትና መንግሥታዊ ባልኾኑ ድርጅቶች በከፍተኛ ሓላፊነት ላይ የሚገኙ ቀደምት ምሩቃንን ያፈራ መኾኑን ደቀ መዛሙርቱ ለምእመናኑ አስታውሰዋል፡፡
ኮሌጁ አገልግሎቱን የሚያከናውነው ‹‹በእናንተው ገንዘብ ነው›› ያሉት ደቀ መዛሙርቱ፣ ‹‹የምእመኑ ሥራ ገንዘብ መስጠት ብቻ አይኹን፤ ስለ ቤተ ክርስቲያናችኹ ጠይቁ፤ ይህ ኮሌጅ የሕዝብ ነው፤ ነገር ግን የገጠር አብያተ ክርስቲያን እየተዘጉ፣ መናፍቃን እንደ አሸን ፈልተው ቤተ ክርስቲያኒቱን እንደ ቅርጫ ሥጋ ሊከፋፍሏት ባሰፈሰፉበት ወቅት በግለሰቦች እየተዘጋ ነው›› በማለት ከአስተዳደሩ ጋራ ሙስናን፣ ኑፋቄንና ብልሹ አሠራርን በመቃወም የገቡበትን ውዝግብ በሰፊው አብራርተዋል፡፡
ወደ መንበረ ፓትርያሪኩ ከዐሥር ጊዜያት በላይ በጋራና በተወካዮቻቸው በመመላለስ ጥያቄዎቻቸውን ሲያቀርቡ መቆየታቸውን የገለጹት ደቀ መዛሙርቱ በጥበቃ እየተገፈተሩ ያለውጤት ከመንገላታት በቀር ያገኙት ነገር ባለመኖሩ ምእመኑን፣ ‹‹በየብሔረሰቡ በተለያየ ቋንቋ ቤተ ክርስቲያንን የምናገለግል ልጆቻችኹ ነን፤ ሙሰኞቹ ኀያላን ናቸውና ርዱን! ነገ በጠቅላይ ቤተ ክህነት በሁለት ሰዓት በምናደርገው እንቅስቃሴ አብራችኹን ቁሙ!!›› ሲሉ በከፍተኛ አጽንዖት ተማፅነዋል፡፡
Short URL: http://www.zehabesha.com/amharic/?p=5271

No comments:

Post a Comment