Wednesday, October 29, 2014

ከሰማያዊ ፓርቲ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የተሰጠ መግለጫ

ሰማያዊ ፓርቲ ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ በሕብረተሰቡ ዘንድ የሚነሱ በርካታ መሰረታዊና ወቅታዊ ጥያቄዎችን ጥያቄዎቹ አድርጎ ሲንቀሳቀስ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ ባለፉት ሁለት አመታት ውስጥም ፓርቲያችን በተለያየ መልኩ የተቻለውን ሁሉ በማድረግ እየታገለ በመንግስት ላይ ጫና ለማሳደርና ችግሮች መፍትሔ የሚያገኙበት አቅጣጫ ሲያመለክት ቆይቷል፡፡ ይሁን እንጂ የሀገራችን አስተዳደራዊና ፖለቲካዊ ችግሮች ከግዜ ወደ ግዜ እየተባባሱና እየከፉ የመምጣታቸውን ያህል ገዢው ፓርቲ ቆም ብሎ ከማሰብ ይልቅ ወደ ማይወጣው አዘቅት ውስጥ ሀገሪቷን ጭምር እያንደረደራት ይገኛል፡፡ ይህም አልበቃ ብሎ ከዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ሂደት ፍፁም በማይጣጣም መለኩ ዜጎችን ለአንድ ሀሳብ ብቻ እንዲገዙ አስገዳጅ መንገዶችን ጭምር በመጠቀም አፋኛ መዋቅሩን በማናለብኝነት እያስፋፋ ይገኛል፡፡ ይህም አልበቃ ብሎ ለማናቸውም አስተዳደራዊም ይሁን ፖለቲካዊ ጥያቄዎች ሀይልን በመጠቀም ለመደፍጠጥና ለማጥፋት ቆርጦ በመነሳት ፍፁም አምባገነንነቱን ገፍቶበት የበርካቶች ህይወት ተቀጥፏል፡፡

ለዚሁ እንደማሳያም:-

ካለፈው ዓመት የክረምት ወራት መጨረሻ አንስቶ እስከ አሁን ድረስ ዜጎች በተለያየ ዘርፍ በመከፋፈል የግዳጅ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡ በዚህ አስገዳጅ ስልጠናም የምርጫ ቅስቀሳ በሚመስል መልኩ ከህወሓት/ኢህአዴግ ውጪ አማራጭ እንደሌለ ከመስበክ ባለፈም ማናቸውም የተለየ ሀሳብ የሚያራምዱ የህብረተሰብ ክፍሎችን፣ ድርጅቶችንና ግለሰቦችን ፍፁም ስነ ምግባር በጎደለው መልኩ የጥላቻ ዘመቻ በማካሄድ የሃሳብ ልዩነትን የማስተናገድ ፍላጎቱ ሙሉ ለሙሉ የተዳፈነ መሆኑን አሳይቷል፡፡ ለዚህ ህገወጥ እንቅስቃሴ እና ዓላማም ወደ 1 ቢሊየን የሚጠጋ የህዝብ ሃብት ባክኗል፤ እየባከነም ይገኛል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ እነዚህን ስልጠናዎች እጅግ በቅርበት ሲከታተላቸው የቆየ ሲሆን ከጅማሬውም ተቃውሞውን በይፋ ማሰማቱ ይታወሳል፡፡

በሌላ በኩል የሕብረተሰብ የመረጃ ክፍተት ለመሙላት እና ካለበት የፖለቲካ ድብርት ለማውጣትና ለማነቃቃት ሕገ መንግስቱን መሰረት አድርገው ሃሳባቸውን በነፃነት የገለፁ ጋዜጠኞችና የህትመት ውጤቶቻቸው ከገበያ እንዲወጡ በማተሚያ ቤቶች በኩል አስተዳደራዊ ሴራ መስራቱ ሳያንስ ሕገ መንግስቱን በሚፃረር መልኩ በሕትመት ሚዲያዎቹ ባለቤቶች፣ አዘጋጆች፣ በጋዜጠኞቹና ሰራተኞቻቸው ላይ በማስፈራራት ስነ ልቦናዊ ጫና በማሳደር በርካቶች ለስደት ሲዳረጉ ጥቂቶች ደግሞ ለእስር ተዳርገዋል፡፡ ገዢው ፓርቲ ባንድ በኩል ሀሳቡን ለመጫን የግዳጅ ስልጠና እየሰጠ በሌላ በኩል ደግሞ የተለየ ሀሳብን እንዲሁም የህዝብ ብሶትን የሚያሰሙ ጋዜጠኞች ላይ የማሳደድ ዘመቻ መክፈቱ የስርዓቱን መበስበስ እና አፋኝ አምባገነንነትን ብቸኛ አማራጭ አድርጎ መቀጠል መምረጡን ግልጽ አመላካች ነው፡፡



ከላይ ከሰፈሩት ሁነቶች እጅግ የከፋውና እየተባባሰ የመጣው ሌላው ከፍተኛ አደጋ ያዘለ ችግር ደግሞ፤ አስተዳደራዊ እና ፖለቲካዊ ጥያቄ እያነሱ ያሉ የሕብረተሰብ ክፍሎችን በሀይል ለመገዛት ቆርጦ መነሳቱ ነው፡፡ ባሳለፍናቸው ሁለት ወራት ብቻ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ዜጎች በመንግስት ሀይሎች ተገድለዋል - ቆስለዋል - ተሰደዋል፡፡ በኦጋዴን መንግስትን የተቃወሙ ዜጎች ወደ ግጭት እንዲገቡ በሚገፋፋ መልኩ ጥያቄዎቻቸውን በመግፋት በርካታ ዜጎች በመንግስት ሀይሎች ህይወታቸው መቀጠፉ ሳያንስ ሬሳቸው እንኳን ክብር በሌለው ሁኔታ መሬት ለመሬት እየተጓተተ ባደባባይ ሰብአዊ መብት ሙሉ ለሙሉ ተጥሷል፡፡ በጋምቤላም በተመሰሳይ መልኩ የህወሓት ሰዎች መሬት በሕገ-ወጥ መንገድ መቀራመታቸውን የተቃወሙ ዜጎች ወደ ግጭት የተገፉበት እና በርካታ የሰው ህይወት የተቀጠፈበት ሁነት እጅግ አሳዛኝ እና መንግስት የተያያዘው መንገድ ወደ ከፋ ሁኔታ ሀገሪቷን እየወሰዳት ለመሆኑ ማረጋገጫ ነው፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ ከላይ የተዘረዘሩትንና ከዚህ ያልተጠቀሱትን በተለያየ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚፈፀሙትን በርካታ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እና አስጊ ሁኔታዎች በቅርብ እየተከታተለ ይገኛል፡፡ በተደጋጋሚ እንደተገለፀውም አሁን ካለንበት ሀገራዊ አዘቅት እና አደጋ መውጫው መፍትሔ በቆራጥነት ሀገርን የማዳን ትግል ማካሄድ እንደሆነ ፓርቲያችን በሚገባ ይገነዘባል - ያምናል፡፡ በስልጠናዎቹ ወቅትም ተማሪዎች እና በርካታ የሕብረተሰብ ክፍሎች በብዛት ሲያነሱት የነበረውን ጥያቄና ስሞታም ከግንዛቤ በማሰገባት ጥያቄዎቹ ምላሽ የሚያገኙበትን የትግል አቅጣጫ በተጠናከረና በተጠና መልኩ አሳታፊ አድርጎ ከግብ ለማድረስ በሙሉ ቁርጠኝነት እና አቋም ላይ እንደሚገኝ ያረጋግጣል፡፡

በመሆኑም የሀገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ ከግምት በማሰስገባት መላው የሀገሪቱ ህዝብ፣ በውጪ የምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ለሀገር ተቆርቋሪ ተቋማት እንዲሁም በገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ ስር ሆናችሁ ለውጥን የምትሹ ወገኖች ሀገራችንን ወደ አደጋ እየወሰዳት ያለውን አፋኝ ስርዓት በቻላችሁት ሁሉ በመቃወምና ከስርዓቱ ጋር ባለመተባበር በብሔራዊ ደረጃ የሚደረገው ትግል አካል እንድትሆኑ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!

ጥቅምት 18 2007 ዓ.ም

ሰማያዊ ፓርቲ

አዲስ አበባ
Source ነገረ ኢትዮጵያ/Negere Ethiopia.

Sunday, October 26, 2014

ህወሃትና የጦር አበጋዞቹ እሴቶች

ህወሃት የትግሬ ተወካይ ብቻ ሳልሆን ለትግራይ ህዝብ የሚያመልከውን አምላክም ጭምር የምመርጥለት እኔ ነኝ በሚል እብሪት ውስጥ ይገኛል። በዚህ እብሪቱም እየተመራ የምታመልኩትን ልመርጥላችሁ ብሎ አጠቃላይ ሙስሊሙንም ክርስትያኑንም እያመሰው እንደሆነ እያየን ነው። እኔን የማይቀበል እጣ ፈንታው ከመታመስ በላይ የሆነ ወዮታ ነው የሚል ያልተፃፈ አዋጅም አለው። ህወሃት በትግራይ ትከሻ ላይ ተፈናጦ፤ ትግራይን ምርጫ አሳጥቶ እኔን እምኑ መንገዳችሁም ህይወታችሁም እኔ ብቻ ነኝ ብሎ ራሱን የትግራይ ጣዖት አድርጎ ሹሟል። ይሄን ጣዖት አንቀበልም፤ እኛ የራሳችን ሂሊና ያለን እንደ ሰው ማሰብ የምንችል ነን ያሉ ብዙ የኢትዮጵያ ልጆች ባልታወጀው አዋጅ መሠረት አብዮታዊ ፀሎት እየተፀለየላቸው አፈር ለብሰው ቀርተዋል።የህወሃት የእብሪቱ መጀመሪያ “እኔ ያልኩት ካልሆነ ሁሉም ገደል ይግባ” ማለቱ ነው። የትግራይ ተወካይ እኔ ብቻ ነኝ ሌላው ሁሉ የትግራይ ህዝብ ጠላት ነው የሚል እምነቱ የድርጅቱን ሥር የሰደደ መሠሪነትና እብሪት የሚያሳይ ነው።
ብዙ ኢትዮጵያዊያን ህወሃት የቆመው ለትግራይ ህዝብ ነው የሚል ዕምነት አሳድረዋል። ይሄን አስተሳሰብ መቀበል የሚጠቅመው ለህወሃት ብቻ ነው።ህወሃት ለትግራይ ህዝብ ክብርም ፍቅርም ያለው ቡድን አይደለም። ለትግራይ ህዝብ በጎ ምኞት እና ክብር ያለው ቢሆን ኑሮ የትግራይ ህዝብ የወደደውን እንዲመርጥ፤ ያልወደደውን እንዲተው ያልተሸራረፈ ነፃነት እንዲኖረው ያደርግ ነበር። እኛ እንደምናየው ግን የትግራይ ህዝብ የወደደውን ለመምረጥ፤የጠላውን ለመተው እንዲችል ነፃነትያለው ህዝብ አይደለም። የትግራይ ህዝብ ነፃነቱን በነፃነት ሥም ያጣ ህዝብ ሁኗል። ህወሃቶች የትግራይን ህዝብ ነፃነት ሸራርፈው ሸራርፈው ህዝቡን በሙሉ መያዣ አድርገውና ከወገኑ ለይተውት እየገዙት ይገኛሉ። የትግራይም ህዝብ ሳይወድ በግዱ ህወሃቶችን ተሸክሞ መከራው በዝቶ እየተገዛ ይገኛል።
ህወሃት መራሽ በሆነው መከላከያ ድህረ-ገፅ ላይ “ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ ማስረፅ” እሴታችን ነው የሚል መፈክር በጉልህ ተፅፏል። ህወሃቶች መከላከያ ኃይሉ የቆመው የህዝቡን ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲዊያ አስተሳሰብ ለመንከባከብ ነው እያሉን ነው። የህዝቡ ዲሞክራሲያዊ መብት ሳይሸራረፍ ተከብሮ ቢሆን ኑሮ ጋዜጠኛ ሚሊዮን ሹርቤ ተሰዶ ሂዶ በባዕድ አገር ባልሞተ ነበር። ህዝቡ በኑሮ ውድነት ባልተሰቃየ ነበር፤ አገሪቷ ሠላም ርቋት እዚህም እዚያም የዜጎች ደም በከንቱ ባልፈሰሰ ነበር፤ የአገሪቷ ብሄራዊ አንድነት ላልቶ ዜጎች ይሄ ክልል አገራችሁ አይደለም እየተባሉ ከኖሩበት መንደር ውጡ ባልተባሉ ነበር፤ ዜጎቿ አገር ውስጥ ከመኖር ይልቅ በባህር ውስጥ አዞ መበላትን ምርጫቸው ባላደረጉ ነበር። አገሪቷ እንዲህ ምስቅልቅሏ ወጥቶ ባለበት ሁኔታ ህወሃቶች ያልተሸራረፈ ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብን መንከባከብ የሚችል ሠራዊት ገንብተናል እያሉ እያላዘኑ ይገኛሉ። ይሄንንም ለማጠናከር ስንል የጦር አበጋዞችን መሾም አስፈልጎናል ብለው የአንደኛ ደረጃ ፊደል ቆጥረው ያልዘለቁ ሽፍቶችን ሹመት በሹት እያደረጓቸው ነው።
“ዘላለማዊ ክብር” በሰይጣን መንፈስ ሲመራ ለነበረው ለመለስ ዜናዊ ይገባል ብሎ የሚያመነው “ክርስትያኑ” ደሳለኝ ኃ/ማሪያም በመለስ ዜናዊ መንፈስ እየተመራ ስልጣኑን ከያዘ ግዜ ጀምሮ 4 ሌተናል ጄኔራሎች፤ 9 ሜጄር ጄኔራሎች፤ 28 ብርጋዴር ጄኔራሎችን ሹሟል። ብዙ ሰዎች ግን ደሳለኝ ኃ/ማሪያም በዚህ ሹመት ውስጥ የመወሰን ድምፅ የለውም ይላሉ። እንዲያውም ደሳለኝ የነብሩን ጭራ ይዞ እንዳይለቀው ጭንቅ ሆኖበት የሚኖር ብኩን ግለሰብ ነው ሲሉም ያክላሉ። ያም ሆነ ይህ ደሳለኝ ኃ/ማሪያም የመለስ ዜናዊን ራዕይ ሊያስፈፅም በትር ስልጣኑን ጨብጧልና በእርሱ ዘመን ለሚሆነው ሁሉ ኃላፊነት ይወስዳል።
ወደ ጦር አበጋዞቹ እንመለስ ከእነዚህ የጦር አበጋዞች መካከል አብዛኞቹ የህወሃት አባሎች መሆናቸው የታወቀ ነው። በዚህ ጥቅምት ወር ብቻ 3 ሌተናል ጄኔራሎች እና 3 ሜጄር ጄኔራሎች ተሹመዋል። እነዚህ የጦር አበጋዞች በየትኛው መደበኛ ጦር አውድማ ላይ ውለው ለዚህ ማዕረግ የሚያበቃቸውን ምግባር እንደፈፀሙ የሚያውቅ የለም። ሽፍቶች እና ጎሬላ ተዋጊዎች መሆናቸው ግን የሚካድ አይደለም። የሽፍትነትና የጎሬላ ውጊያ ልምድ ግን ለዚህ ማዕረግ የሚያበቃቸው ሊሆን እንደማይችል የታወቀ ነው።
ሌተናል ጄኔራል ሁነው ከተሾሙት መካከል
1ኛ. አብርሃም ወ/ማሪያም
2ኛ. አደም መሃመድ
3ኛ. ብርሃኑ ጁላ
ሲሆኑ ወደ ሜጀር ጄኔራልነት ያደጉት ደግሞ
1ኛ. ክንፈ ዳኘ
2ኛ. ተክለብርሃን ወ/አርጋይ
3ኛ. ዘውዱ እሸቴ ይባላሉ።
የእነዚህ የጦር አበጋዞች ሹመት ባላቸው የትምህርት ደረጃ፤ ለህዝባቸው ባላቸው ክብር፤ ለአገራቸው ባላቸው ፍቅር ሳይሆን ለጣዖቱ ህወሃት ያላቸው ታማኝነት ሚዛን ደፍቶ በመገኘቱ ነው።
ከስድስቱ የጦር አበጋዞች መካከል የአራቱ ሹመት ቤተሰባዊ ዝምድናን መሠረት ያደረገ ስለመሆኑ የሚከተለውን ትሥሥር እንድትመለከቱ እንጋብዛላእን።
1ኛ. በሌተናል ጄኔራልነት ማዕረግ የተሾመው አብርሃም ወ/ማሪያም የመለስ ዜናዊ የሥጋ ዘመድ ነው። የመለስ ዜናዊ ቅደመ አያት በጎን ከሌላ ሴት የወለዷቸው ሴት ልጅ ልጅ ነው።
2ኛ. ሜጄር ጄኔራል ክንፈ ዳኜ ደግሞ አባቱ አቶ ዳኜ ገ/ስላሴና የመለስ አባት የአቶ ዜናዊ እናቶች እህትማማቾች ናቸው።
3ኛ. ሜጄር ጄኔራል ዘውዱ እሸቴ ደግሞ የመለስ ዜናዊን የቅርብ ዘመድ አግብቶ በጋብቻ ተሳስሯል። ሚስቱ ደግሞ በ18 ዓመት ታንሰዋለች።
4ኛ. ሜጀር ጄኔራል ተክለብርሃን ወ/አረጋይ የመለስ ዜናዊ የአክስት ልጅ ነው።
ይህ መከላከያ ኃይል ተብሎ የአንድን ጎጠኛ ድርጅት ህልውና ለመጠበቅ የቆመውን ቡድን የሚመሩት የጦር አበጋዞች በትምህርት ደረጃቸው ከሚያዟቸው ተራ ወታደሮች የማይሻሉ፤ ከራሳቸው ወዲያ ህዝብና አገር የሚባል ነገር የማያውቁ፤ በአገኙት አጋጣሚ ሁሉ የአገሪቷን ሃብት ለመዝረፍ የሚሸቀዳደሙ እና ራሳቸውን እንደ ኢንቨሰተር የሚቆጥሩ፤ የውትድርናን ሙያ ከነፍስ ግዲያና ከጭካኔ ለይተው የማያዩ እና ርህራሄ የሌላቸው ስለመሆናቸው የህወሃት ድርሳናት ይመሰክራሉ።
ህወሃት ርህራሄን የማያውቁ ጭካኞችን የጀግንነት ማዕረግ እየሰጠ በአገሪቷ ላይ እያሰማራ ይገኛል። የህወሃቶች ስነ-ምግባርም ሆነ ስነ-ልቦና ለጀግንነት የሚያበቃቸው አይደለም። በህወሃት መንደር ጀግናና ጀግንነት አይታወቁም። ጀግና እውነትን አይፈራም። ህወሃት እውነትን ስለሚፈራ ገና ድክ ድክ የሚሉ ነፃ ሚዲያዎችን ያለ ምንም ማወላወል ሊደመስሱ የሚሸቀዳደሙትን ይሾማል። ጀግና ነፃ ሚዲያን የሚፈራበት ምንም ምክንያት አይኖረውም። ጀግና ነፍሰ ገዳይ አይደለም። ህወሃት ህፃን ነብዩን የመሰሉ እንቦቀቅላዎችን ግንባር ግንባራቸውን ብለው ለመግደል የማይራሩ ጨካኞችን ይሾማል። ጀግና ሌብነትን ከልቡ ይፀየፋል። ህወሃት ግን ሌብነትን የሚፀየፉትን ሳይሆን የድሃ ንብረት ሰርቆ ሃብት ማካበትን እንደ ብልጠት የሚቆጥሩ ደካሞችን ጄኔራል እያለ ያሰማራል።
በዚህ በጥቅምት ወር የተሾሙት 6 የጦር አበጋዞች ለሹመት ሲታጩ የትምህርት ዝግጅታቸውና ብቃታቸው፤ ለአገራቸው ያደረጉት የላቀ አስተዋፅዖ፤በውጊያ አውድማ ያሳዩት ጀግንነት ታይቶ ነው የሚል ወሬ ከህወሃት መንደር ተሰምቷል። ህወሃቶች እና ደጋፊዎቻቸው ይሄን ለማመን አይቸገሩም። የእነዚህ ቡድኖች ዋና መለያ የገዛ ውሸታቸውን እውነት ነው ብለው አምነው ጥሩ እንቅልፍ መተኛት የሚችሉ መሆናቸው ነው። የገዛ ውሸቱን እውነት ነው ብሎ የሚያምን ግለሰብ ብርቱ የሆነ የስነ-ልቦና ቀውስ ውስጥ የወደቀ መሆንኑ የስነ-አዕምሮ ተማራማሪዎች ይናገራሉ። ህወሃቶችም ብርቱ በሆነ የስነ-ልቦና ቀውስ ውስጥ እንደሚገኙ ለማየት የዕለት ተዕለት ውሸቶቻቸውን እና የሚፈፀሙትን ፀያፍ ድርጊቶች ማየት በቂ ይሆናል።
የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል በጥቂት በዘረ ሃረጋቸውና በቤተሰብ ክር በተሳሰሩ ወንበዴዎች እጅ ወድቋል። በእነዚህ ዘራፊዎች የሚመራ የሠራዊት ኃይል የህዝቡን ዲሞክራሲያዊ መብት ማስከበር አይቻለውም። የጦር አበጋዞቹ የአገሪቷን አንጡራ ሃብት እየዘረፉ ከገነቧቸው ህንፃዎች በየወሩ የሚሰበስቡትን ገንዘብ የሚጠይቅ ለህዝብ ወገንተኛ የሆነ መንግስት እንዲመሰረት ምንም ፍላጎት አይኖራቸውም። ለእነዚህ ጦር አበጋዞች ነፃነት፤ ፍትህ፤ እኩልነት እና እውነተኛ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት የሚባሉ ነገሮች ያሸብሯቸዋል። እነዚህንም ጥያቄዎች ያነሳ አሸባሪ ተብሎ የዚህን ምድር ሥቃይ እንዲያይ ይደረጋል።ይሄ ቡድን ሥልጣን ላይ እስከቆየ ድረስ ነፃነት ፤የህግ የበላይነት፤ እኩልነት የሚባሉ እሴቶች በኢትዮጵያ ይሰፍናሉ ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው።
በመጨረሻም ተራው ወታደር እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ነፃነቱን ተገፎ ለምንና ለማን እንደሚገልና እንደሚሞት ሳያውቅ በገዛ ወገኖቹ ላይ እየተኮሰና የንፁህ ደም እያፈሰሰ እንደሚኖር እያየን ነው። ተራው ወታደር ጋምቤላ ሂዶ ያገኘውን ሁሉ የሚገድለው ለምንድ ነው? ኦጋዴን ሂዶ የዘር ማጥፋት ወንጀል የሚፈፅመው ለምንድ ነው? ጉራፋርዳ ወርዶ የመዥንግሮችን ደም የሚያፈሰው በምን ምክንያት ነው? ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲን አስፍነናል ከተባለ ይሄ ሁሉ ውጊያ ምንጩ ምንድ ነው? ሠራዊቱ ለእነዚህና ለመሰል ጥያቄዎች በቂ መልስ መፈለግ ይኖርበታል።ምንም ትርጉም በሌለው ውጊያ ውስጥ እየሄደ የንፁህ ደም ማፍሰሱን ለማቆምና ነገ በወንጀል ከመጠየቅ ራስንም ለማዳን ሠራዊቱ ራሱን ከዘረኞቹና ከዘራፊዎቹ የጦር አበጋዞች መለየት ይኖርበታል።ከእርሱ በሞራልም ሆነ በትምህርት ደርጃቸው ከማይሻሉ ጄኔራል ተብየዎች ራሱን ለይቶ ለነፃነት፤ ለፍትህ እና ለእኩልነት ከሚታገሉ ኃይሎች ጎን እንዲሰለፍ ጥሪያችንን አሁንም እናስተላልፋለን።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !
Source www.ginbot7.org

Saturday, October 25, 2014

U.K. authorities accused of ‘dodging obligations’ in the abduction of Andargachew Tsige

THE INDEPENDENT
The partner of a British father-of-three being held on death row after he was spirited into Ethiopia has accused the Government of “dodging its obligations” by insisting it has no grounds for demanding his release.
Andargachew ‘Andy’ Tsege
Andargachew ‘Andy’ Tsege
Andargachew “Andy” Tsege, 59, was arrested at an airport in Yemen in June, and vanished for a fortnight until he reappeared in Ethiopian detention facing a death sentence imposed five years ago after a trial held in his absence.
The Foreign Office is now facing legal action after it classified Mr Tsege’s arbitrary disappearance and removal to Ethiopia as “questionable but not a criminal matter” and said that despite the risk of torture and the ultimate sanction hanging over him it did not feel “entitled” to demand he be returned home to London.
Yemi Hailemariam, Mr Tsege’s partner and the mother of their three children, told The Independent she was deeply concerned that Britain was soft-pedalling on his case to preserve its relationship with an increasingly important ally in east Africa.
Mr Tsege, who came to Britain as a political refugee in 1979 and is a prominent dissident campaigning against the Ethiopian regime, is feared by Ms Hailemariam and the legal charity Reprieve to be at extreme risk of torture. Electrocution, beatings and abuse, which includes tying bottles of water to men’s testicles, have been reported by detainees, and Mr Tsege’s whereabouts has not been revealed by the Ethiopian authorities.
Ms Hailemariam said: “For anyone reading what has happened, it must be clear that Andy is the victim of a crime. He was kidnapped to Ethiopia and faces the death sentence from a trial where he wasn’t even represented. He is a political prisoner.
“The Foreign Office is dodging its obligations and it is hard to see any other reason than it is to preserve Britain’s wider relationship with Ethiopia. It is now 117 days that he has been in detention and Britain must now say enough is enough.”
Reprieve, which has taken up Mr Tsege’s case, said it was starting legal action against the Government, potentially leading to a judicial review, to force it to press for the Briton’s immediate release and repatriation.
Maya Foa, director of the Reprieve’s death penalty team, said: “Andy Tsege is now well into his fourth month of detention and, incredibly, we are no closer to knowing where he is or even whether the Ethiopians plan to execute him. The UK Government’s unwillingness to take action is simply unacceptable.”
The father-of-three was en route to Eritrea when he was arrested during a two-hour stop over in the Yemeni capital, Sana’a, at the apparent request of the Ethiopian authorities, who seem to have had foreknowledge of Mr Tsege’s travel arrangements.
The Yemeni authorities have claimed the arrest and subsequent transfer of the Briton to Ethiopia – without any opportunity to challenge the move – took place on the basis of a security agreement between the two countries.
In a letter to lawyers for Ms Hailemariam, seen by The Independent, the FCO said it accepted “due process” did not appear to have been followed in the case but said his disappearance did not amount to a “kidnapping”.
It added that it required evidence that a British national was not being treated “in line with internationally accepted standards” before it could consider approaching local authorities. The letter said: “On the information presently available, the Foreign Secretary does not consider that the United Kingdom is entitled to demand Mr Tsege’s release or his return.”
Ms Hailemariam said: “Andy has been abducted and placed on death row on the basis of a politically motivated trial. It is difficult to think of circumstances that would fall further below ‘internationally-accepted standards’. What will it take for Britain to demand the return of one of its citizens?”
A FCO spokesman said: “The British Embassy in Ethiopia remains in contact with the Ethiopian authorities about regular consular access to Mr Tsege in the future so we’re able to continue to monitor his welfare. We also continue to press for reassurances that the death penalty imposed in absentia will not be carried out.”
The Independent revealed earlier this month that public money is being used to train security forces in Ethiopia under a £2m programme run by the Department for International Development (DfID) to fund masters degrees for 75 Ethiopian officials on improving the accountability of security services.
Material on the DfID website explaining the scheme has since been removed, prompting Reprieve to write to International Development Secretary Justine Greening asking whether the policy is under review or has been erased “to avoid embarrassment”.
DfID admitted it had cancelled the masters courses due to “concerns about risk and value for money”. A source said the decision was not linked to the case of Mr Tsege.
Source www.zehabesha.com

Friday, October 24, 2014

ባነሰ ወጪ ድልን መቀዳጃ አመቺ ጊዜ ላይ ነን – እንጠቀምበት!

October 23,2014
በአለፈው አንድ ወር ጊዜ ውስጥ በምንም የማይገናኙ እና የተመሰቃቀሉ የሚመስሉ፤ በጥልቀት ላያቸው ግን የተያያዙና የተደጋገፉ ከመሆናቸው አልፎ እንደከዋክብት ፈለግ አቅጣጫን የሚያመላክቱ በርካታ ክስተቶች ተስተውለዋል። የጊዜ ቅደም ተከተላቸውን ሳንጠብቅ አንዳንዱን ለአብነት ያህል እናንሳ።
በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የዘነበው የዘለፋና የዛቻ ውርጅብኝ ህወሓት በቀጥታ በማይቆጣጠራቸው ማኅበራት ላይ ሁሉ ሲደርስ የቆየው ነፃ ማኅበራትን የማፍረስ ዘመቻ አካል መሆኑን መገንዘብ ቀላል ነው። ህወሓት የእስልምና እምነት ተከታዮችን ነፃ ማኅበርን በቁጥጥሩ ውስጥ ካስገባ በኋላ ፊቱን ወደ ክርስትና በተለይም ወደ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ማዞሩ የተረጋገጠ ነገር ሆኗል። ወያኔ በሥልጣን ላይ እስካለ ድረስ ማንም ከጥቃት እንደማያመልጥ፤ ለምንም ጉዳይ ይቋቋም ወያኔ የማይቆጣጠረው ማኅበር እንዲኖር የማይፈልግ መሆኑ ከዚህ በፊት የሚታወቅ ቢሆን በድጋሚ ማረጋገጫ የሰጠበት አጋጣሚ ሆኗል።
በመዠንግር ከአስራ አምስት በላይ የሥርዓቱ ታጣቂዎች ከነመሣሪያዎቻቸው አገዛዙን ክደው ጠፍተዋል። የጠፉትን ለማደን የመጡ ወታደሮች ደግሞ ከሕዝቡ ጋር በፈጠሩት ግጭት በርካቶች ሕይወታቸውን አጥተዋል። በዚህ ግጭት ብቻ ከ40 በላይ ወታደሮች መገደላቸው ይነገራል። በጋምቤላ እና በቤንሻንጉልና ጉሙዝ ወረዳዎች ውጥረት ሰፍኗል። ከመሃል አገር ሄደው ኑሮዓቸውን እዚያው ያደረጉ ዜጎች ላይ ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚደርስባቸው አፈናና እንግልት ጨምሯል። ግድብ እየተሠራበት ነው በሚባለው አካባቢም ከአሁኑ የፀጥታ ችግር እየደረሰ መሆኑ መረጃዎች ይጠቅማሉ። ወያኔ በምሥራቅ ኢትዮጵያ ኦጋዴን ውስጥ የገባበት ዓይነት ማጥ በምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያም እየመጣ መሆኑ አመላካች ነው። የመከላከያ ሠራዊት አባላት መፍለስና የነፃነት ታጋዮችን መቀላቀል የእለት ለእለት ትዕይንት እየሆነ ነው። ወያኔ በመሃል አገር በሙስሊም እና በክርስቲያን ወገኖቻችን የእምነት ማኅበራት ላይ በከፈተው ግንባር “ጠብ ያለሽ በዳቦ” ሲል ዳር ዳሩን ሠራዊቱና ሕዝቡ ለማይቀረው ፍልሚያ እየተዘጋጁ ነው።
በርካታ ጋዜጠኞችና አሳታሚዎች ለስደት ከተዳረጉ ጥቂት ሣምታት በኋላ “የሚመጣውን ሁሉ አገሬ ውስጥ ሆኜ እቀበላለሁ” ያለውን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሣለኝ አሳዛኝም አስቂኝም በሆኑ ክሶች ጥፋተኛ ተብሎ ወደ ወህኒ ተግዟል። በጋዜጠኞች ሕይወትና ሞት ወያኔ የፓለቲካ ቁማር መጫወቱ አጠናክሮ ቀጥሏል። በአንፃሩ ደግሞ በውጭ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያን አምርረዋል። የወያኔ ሹማምንት በአሜሪካ እና አውሮፓ የሚዘዋወሩት በሰቀቀን ሆኗል፤ በየደረሱበት ውግዘትና ውርደት ይጠብቋቸዋል። የወያኔ ሹማምንት በኢትዮጵያዊያን የተጠሉና የረከሱ ተደርገዋል።
የዩ.ኤስ. አሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ከኢትዮጵያ ቴሌቬዥን ባላነሰ ወያኔን በልማት አምጭነት አሞካሽተዋል። የአውሮፓ መንግሥታት በሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ወያኔን እየተቹም ቢሆን ወያኔ በሚሰጣቸው ቁጥር እየማለሉ “እውነትም ልማት እየተፋጠነ ነው” በሚል ተስፋ ማበረታቻ እየሰጡት ነው። በዚህ ደስታ አቅሉን ያጣው ኃይለማርያም ደሣለኝ የውሸት ቁጥሮችን የመፈብረክ ሥራ ከስታትስቲክስ ጽ/ቤት ነጥቆ የራሱ የሥራ ድርሻ አድርጎታል። በዚህ አዲሱ ሥራውም ውጤት እያስመዘገበ ነው። ሁለት መቶ አምሳ (250) ሚሊዮን ኩንታል ሰብል አመረትን ባለ በሶስት ወሩ ሶስት መቶ (300) ሚሊዮን ኩንታል አመረትን በማለት በሶስት ወራት ውስጥ ብቻ የ20 በመቶ የግብርና ምርቶች የውሸት እድገት ፈጥሯል።
የውሸት ቁጥሮች ፈጠራ እንዲህ ቢፋፋምም፤ ቁጥሮቹን የሰሙ ኦባማ፣ የአውሮፓ መንግሥታት ሆነ ዓለም ባንክ ቢያወድሱትም አገር ውስጥ ያለው ሀቅ አልቀየረም። ስኳር፣ ዘይት፣ እንቁላልና ሌሎች የምግብ ግብዓቶች የደረሱት የሚያውቅ ጠፍቷል። ውሃ የለም፤ መብራት የለም፤ ኔት ዎርክ የለም። የአዲስ አበባ ጎዳናዎች በመቸውም በባሰ መጠን በነዳያን እና በቤት አልባ በረንዳ አዳሪ ዜጎች ተጥለቅልቀዋል። ድህነት ከጎጆዎች ወጥቶ ጎዳናዎች ላይ ፈሷል። የገንዘብ ዋጋ ወርዶ ወርዶ ብር ቁራጭ ወረቀትን ማከል አቅቶታል። በጥቂት በዝርፊያ በደለቡ የህወሓት ሹሞችና በብዙሃኑ ኢትዮጵያዊ መካከል ያለው የኑሮ ልዩነት ማነፃፀር እንኳን እንዳይቻል ሆኖ ተራርቋል።
የመከላከያ ሠራዊት አባላት በኑሮም በዘረኝነትም እየተማረሩ ነው፤ አለቆቻቸው ግን አሁንም በዝምድና እየተፈላለጉ እየተሿሿሙ ነው። አሁንም በዝምድና እየተፈላለጉ እርስ በራሳቸው እየተሿሿሙ ጄኔራሎች ሁሉ ዘመዳሞች ሆኑ፤ በሥራቸው ያለውን ኢትዮጵያዊውን ወታደር ግን እንደ ግል አሽከራቸው እንኳን ማየት ተጠይፈዋል። በጄኔራሎችና በሠራዊቱ መካከል ያለው ግኑኝነት ከጌታና ሎሌም የባሰም ሆኗል።
እነዚህ ምስቅልቅል ያሉ ሁኔታዎች ምንን ያመለክታሉ?
እነዚህንና እነዚህን የመሳሰሉ ምስቅልቅል ያሉ ሁኔታዎችን በጥንቃቄ የተነተነ ሰው በምስቅልቅነታቸው ፋንታ ሥርዓት የያዙ ፈለጎችን ያገኛል። ከእነዚህ ፈለጎች አንዱ የሚያመላክተው መጪዎቹ ጥቂት ወራት ለኢትዮጵያ ወሳኝ ጊዜያት እንደሚሆኑ ነው። እንደ እውነቱ ከሆነ ምስቅልቅል ውስጥ ያለው ወያኔ ነው። ወያኔ፣ በድንገት አዕምሮዉን እንደሳተ ሰው ይይዘው ይጨብጠው ጠፍቶታል። በዚህ ምስቅልቅል ወቅት ውስጥ በቢሊዮን የሚገመት የሕዝብ ሀብት አውጥቶ፤ የማይረቡ ድርሳናትን ጽፎ የአገሪቱን ዜጋ በሙሉ ካላሰለጠንኩ ሞቼ እገኛለሁ ማለቱ ራሱ የውስጡን መመሰቃቀል ማሳያ ነው። ስልጠናውን ሰልጣኞች ብቻ ሳይሆን አሰልጣኞችም ጭምር የጠሉት ቢሆንም ፋታ የሚሰጠው መስሎት ገፍቶበታል። የነፃነት ኃይሎች በሚቀጥሉት ጥቂት ወራት ውስጥ ኃይላችንን አሰባስበን ከገጠምነው ባነሰ ወጪ ድልን መቀዳጃ አመቺ ጊዜ ይሆናል።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ያለንበት ወቅት ወሳኝነት በመገንዘብ ከመሰል ድርጅቶች ጋር ውህደት በመፍጠር፤ ከሌሎቹ ጋር በጥምረት ትግሉን ለማፋጠን ቆርጦ ተነስቷል። የኢትዮጵያ ሕዝብ የወቅቱን ልዩ ባህሪ በመገንዘብ በአንድ ልብ ለትግል እንዲነሳ ግንቦት 7 ጥሪ ያቀርባል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!
Source www. ginbot7.org

Thursday, October 23, 2014

አቡነ ማትያስ በጥቅምት/2007 ዓም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉአባኤ መክፈቻ ንግግራቸውም ከቤተ ክርስቲያን ዋና ዋና ችግሮች ላይ ከማተኮር ይልቅ የቤተ ክርስቲያኒቱን ልጆች በመግፋት ምድራዊውን መንግስትን ማስደሰት ቀጥለዋል

(ጉዳያችን)
tuafየቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጥቅምት 11/2007 ዓም ከቀትር በኃላ  በምህላ እና በፀሎት መጀመሩ ይታወቃል።በማግስቱ ጥቅምት 12/2007 ዓም ፓትራርኩ አቡነ ማትያስ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ምእመናንን እና የቤተክርስቲያን አባቶችን ያሳዘኑ ንግግሮችን ተናግረዋል።ፓትራርኩ በንግግራቸው አብዛኛውን ክፍል የያዘው የገዢውን ምድራዊ መንግስት ያስደስታል፣ በአጠገባቸው በሙስና እና የቤተ ክርስቲያንን አይን የወጉ ሙሰኞች፣እበላ ባይ አድር ባዮች እና ”የጨለማው ቡድን” ተብለው የሚታወቁትን ታጣቂ ካድሬዎች ያስደስትልኛል ያሉትን ቃላት እየመረጡ ማኅበረ ቅዱሳን ላይ ጣታቸውን መቀሰር መርጠዋል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ዘርፈ ብዙ የአስተዳደር ችግሮች እና የእምነቷ ቀሳጮች ከመቼውም ጊዜ በላይ በከበቧት በእዚህ ፈታኝ ወቅት ማኅበረ ቅዱሳንን የሚያህል ለቤተ ክርስቲያን እና ለአብቶች የሚታዘዙ፣በእውቀታቸው፣በጉልበታቸው እና በገንዘባቸው ቤተ ክርስቲያንን በነፃ የሚያገለግሉ አባላት ማኅበርን ማፍረስ እንደትልቅ የቅዱስ ሲኖዶሱ ቀዳሚ ተግባር አድርገው ማቅረባቸው በቀጥታ የምያስፈፅሙት አካል ተልኮ እንዳላቸው አመላካች ነው የሚሉ ወገኖች  ተበራክተዋል።
ፓትራርኩ በዛሬው ንግግራቸው ”እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመበት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ” ሐዋርያት ሥራ 20፣28  የሚለው ቃል እና ”ለሁሉም እኩል አባት እሆናለሁ” ያሉትን እረስተው ለቤተክርስቲያን ልጆች ከለላ መሆኑ ቀርቶ ”ሽብርተኞች” እያሉ የምነቅፉትን አይዟችሁ ባይ ብቻ ሳይሆን በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መክፈቻ ላይ  ማኅበረ ቅዱሳንን ”በቤተ ክርስቲያን የማይታወቅ ሀብት የሚሰበስብ እና ቤተክርስቲያን ወደ ሁለት የመክፈል አዝማምያ ያለው እና የቤተ ክርስቲያንን መመርያ ለመቀበል ፈቃደኛ ያልሆነ” የሚል ስም ለጥፈውበታል።
እርሳቸው ይህንን ይበሉ እንጂ የማኅበሩ ሥራ አመራር እና ሥራ አስፈፃሚ አባላት ማኅበረ ቅዱሳን  በቤተ ክርስቲያን መዋቅር ስር ያለ ማኅበር እንደመሆኑ እና መተዳደርያ ደንቡንም እራሱ ያፀደቀው ሳይሆን ከቅዱስ ሲኖዶስ ተረቆ፣ተሰፍሮ፣ ተቆጥሮ እና በራሱ በቅዱስ ሲኖዶሱ ምልዓተ ጉባኤ ፀድቆ እና ተፈርሞ በተሰጠው ሕግ መሰረት የሚተዳደር መሆኑ ይታወቃል።
ይህም በመሆኑ የማኅበሩ ሥራ አመራር እና ሥራ አስፈፃሚ በተደጋጋሚ ከርሳቸው የስራ መመርያ ለመቀበልም ሆነ በሚያነሷቸው ጥያቄዎች ላይ ለመመካከር በፅሁፍም ሆነ በቃል በተደጋጋሚ እንዲያናግሯቸው ጠይቀው  አንድ ጊዜም ሳያናግሯቸው በአደባባይ ለዋልጌ አባት ነን ባይ ካድሬዎች ተቀምጠው ሲያሰድቡ እና እርሳቸውም ሲወቅሱ መሰንበታቸው ከፍተኛ ትዝብት ላይ ብቻ ሳይሆን የቤተ ክርስቲያኒቱን ክብር በእዚህ ደረጃ ማውረዳቸው ብዙ ምዕመናንን አሳዝኗል ።በወጣቶች ዘንድ ደግሞ ከፍተኛ ቁጣ ቀስቅሷል።
አንድ  የቤተ ክርስቲያኒቱ  አገልጋይ ፓትራርኩ  ጥቅምት ወር መጀመርያ ላይ ለቤተ ክህነቱ ሥራ አስኪያጅ ሳይነግሩ በጠሩት ህገ ወጥ ስብሰባ ላይ ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ደፋ ቀና የሚሉ፣በእዚህም አገልግሎት አገልጋዮቹ በጎርፍ አደጋ፣በመኪና አደጋ እና ለብዙ ጤና መታወክ የተዳረጉ እውነተኛ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ያሉበትን ማኅበረ ቅዱሳንን ”አልሸባብ፣አሸባሪ፣የቤተ ክርስቲያን ንብረት የሰበሰቡ፣ ወዘተ” እያሉ የግፍ ምላሳቸውን ያስረዘሙባትን ግፉአን  ላይ አስተያየቱን ሲሰጥ ”በሕይወቴ በእዚህን አይነት ደረጃ ሐሰት ነግሳ ስትፎክር፣ ሰው የሚባል ፍጡርም ሕዝብ የሚያውቀውን እውነት በአደባባይ በድፍረት በሐሰት ምላሱ ሲለበልባት አልተመለከትኩም ወደፊትም የምመለከት አይመስለኝም ” ሲል ተሰምቷል።
 ሐሰት ማረፍያ ምላስ አገኘች።ሀገር ያወቃቸው ቀማኞች ”አባታችን” በሚል የማቆላመጫ ቃል ፓትራርኩ ፊት ንፁሃንን ባልሰሩት ወንጀል ከሰሷቸው።ፓትራርኩም  ቅንድባቸውን አንድ ጊዜ ወደላይ ሌላ ጊዜ ወደታች እያደረጉ አዳነቁላቸው።በእዚህ ብቻ አላበቁም ጠርተው በአንድነት መመካከር፣ቤታቸንን እንዴት እናስተካክል ብለው መምከር ቅሬታቸውንም በግልፅ ጠርተው መግለፅ ያልፈለጉት ፓትራሪክ ከውስጥ ያሉትን እየገፉ ስለውጭው የተጨነቁ መስለው መናገራቸው ሚዛን አልደፋ ያለበት ምዕመን በቀጣዩ ጊዜ ስለሚወስደው የእራሱ እርምጃ የማሰላሰያ ጊዜው መሆኑን ያመነበት ይመስላል።
ከውስጥ ያሉትን የቤተክርስቲያን ነገር ያንገበገባቸውን ”አተላ እና ዘኬ ጋር የሚውሉ” ተብለው ሲሰደቡ ”ተዉ እንዲህ አይባልም” ብለው ከመምከር ይልቅ እንደ ተራ የመንደር ሙግተኛ ስድቡን ለማድነቃቸው ከፊታቸው ላይ መደበቅ አልቻሉም።”እድምያችንን’ ሸውደን’ እንድኖራለን” የሚሉ ‘የዶሮ ማነቅያ’ ሰፈር ቃላትን እንጂ የቤተ ክህነቱ ሽታ የሌላቸው ቀሚስ ለባሾች የተከበረውን የቅዱሳን መታሰብያ ”ዝክርን” ”ዘኬ” በሚል ፀያፍ ቃል ሲጠቀሙም አሁንም ፓትርያሪኩ ቅር አላላቸውም።
ይህንን የሰሙ ሌላ የጉባኤው ተሳታፊ አባት ከግፉአኑ ጉባኤ ከወጡ በኃላ እንባ ባቀረረ ፊታቸው ”በዓለማዊው ትምህርት መግፋታቸው፣ሱፍ መልበሳቸው የማኅበሩን አባላት ከዝክር ማራቅ ነበረበት? ሱፋቸውን አቧራ እንዳይነካው ”እፍ እፍ” እያሉ እንዲኖሩ ነበር ምኞታቸው? አልጋቸውን ትተው የማኅበረ ቅዱሳን ቢሮ መሬቱ ላይ ሰሌን አንጥፈው ተኝተው መስራታቸው ነው አሸባሪ ያስባላቸው?” ሲሉ ጠይቀዋል።
ለማጠቃለል አቡነ ማትያስ ከሰማያዊው አምላክ ይልቅ ለምድራውያኑ ገዢዎች ማድላታቸው የአደባባይ ምስጢር ሆኗል።በአንድ ወቅት ”ይህ ማኅበር የሚሰራውን አውቃለሁ ወጣቶች ናችሁ በርቱ” ባሉበት አንደበት መንበረ ፕትርክናውን ሲይዙ እነ አባይ ፀሐዬ እና መሰሎቻቸው ለሚሏቸው የሚታዘዙ፣ ሐሰት ሲነገር የማያርሙ አባት መሆናቸውን አስመስክረዋል።በውስጥ ያሉትን ልጆቻቸውን እንዳይወጡ መጠበቅ ሲገባቸው ለመግፋት እና ለማስገፋት አለ የተባለውን የምድራችንን ያሰቅልልኛል ያሉትን  ክስ አንጠፍጥፈው ያርከፈከፉትን በማድነቅ  በልጆቻቸው ደረት ላይ በጭካኔ ሰክተውባቸዋል፣ አሰክተውባቸዋል።
እግዚአብሔር እረኞች ጳጳሳትን፣ካህናትን እና አገልጋዮችን  ከውጭ ያሉትን በጎች በፍቅር እና በትምህርት  ወደ ቤቴ አላመጣችሁም ብሎ የሚወቅስ እና የሚቀጣ ከሆነ ከውስጥ ያሉትን በጎች በሐሰት ፍርድ  ወደውጭ እንዲወጡ (አይወጡም እንጂ ) የሚገፉትንማ በምን አይነት ፍርድ ይቀጣቸው? ለነገሩ ስንዝር ያክል ከቤተ ክርስቲያን የምያፈገፍግ የለም።ይልቁን ክንድ ያህል የበለጠ እንቀርባለን።የበለጠ የቤተ ክርስቲያንን ንብረት መተዳደርያቸው ያደረጉትን በግድም በውድም ይነቀሳሉ።በፊውዳል አስተሳሰብ  ውስጥ እየዳከሩ ፈላጭ ቆራጭ ሆኖ መኖርን እና ለምድራውያን ገዢዎች እየሰገዱ መኖርን ቤተ ክርስቲያን አላስተማረችንም።
 ”እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመበት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ” ሐዋርያት ሥራ 20፣28
ጉዳያችን
ጥቅምት 13/2007 ዓም (ኦክቶበር 23/2014)
ምንጭ ዘ-ሐበሻ

Wednesday, October 22, 2014

የፓርቲዎች ትብብር ስምምነቱን ላልፈረሙት ጥሪ አቀረበ

• ኢትዮጵያውያንም የዜግነት ግዴታቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል
ዘጠኝ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ትናንት ጥቅምት 11 ቀን 2007 ዓ.ም በጋራ ለመስራት የትብብር ስምምነት መፈረማቸውን በማስመልከት ዛሬ ጥቅምት 12/2007 ዓ.ም በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ትብብሩን የፈረሙት ፓርቲዎች ትብብሩን ያልፈረሙት ሌሎች ፓርቲዎች ስምምነቱን እንዲፈርሙ በይፋ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ፓርቲዎቹ በመግለጫቸው፣ ‹‹በሂደቱ ከጅምሩ እስከ መጨረሻው ተሳትፋችሁ በተለያየ ምክንያት በትናንትናው ቀን የስምምነቱን ሰነድ ያልፈረማችሁም ሆነ የአገርና ህዝብን ጉዳይ ከፓርቲ ጥቅምና ዓላማ አብልጣችሁ የምትመለከቱና ለዚህም በጋራ ለመስራት ዝግጅቱና ቁርጠኝነቱ ያላችሁ ሌሎች ሰላማዊ የተቃውሞ ፖለቲካ ፓርቲዎች ከጋራ ትግሉ እንድትቀላቀሉ ጥሪያችንን እናቀርባለን›› በማለት ፈራሚዎቹ ፓርቲዎች ይፋዊ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡
በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የተገኙት የትብብሩ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነትና ዋና ጸሐፊው አቶ ግርማ በቀለ እንደገለጹት ትብብሩ ያለፉትን ድክመቶች የፈተሸና ወደፊት እንዴት እንጓዝ የሚለውን አቅጣጫ ያስቀመጠ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
ፓርቲዎቹ ለትብብሩ መነሻ የሆናቸውን ምክንያት ሲያብራሩም፣ ‹‹በገዢው ፓርቲ/መንግስት የሚፈጸሙ ኢ-ህገ-መንግስታዊ እና ኢ-ዴሞክራሲያዊ ተግባራት በአገራችን የመድብለ ስርዓትን እውን ለማድረግ ከማያስችሉበት ደረጃ በመድረሱ የተፈጠረውን ምስቅልቀስል ለመሸከምም ሆነ ተመጣጣኝ መፍትሄ መስጠት በማስፈለጉ መሆኑ ነው›› ብለዋል፡፡
በመሆኑም ዘጠኙ ትብብሩን የፈረሙ ፓርቲዎች የትብብር ስምምነት ያስፈለገበት ምክንያት፣ ‹‹ነጻ፣ አሳታፊና ታአማኒ ምርጫ እንዲካሄድ በትብብር ለመስራት፣ የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋትና የዜጎችን ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች እንዲከበሩ በጋራ ለመታገል›› መሆኑን አመልክተዋል፡፡
የትብብሩ ፈራሚ ፓርቲዎች ሰማያዊ ፓርቲ፣ መኢዴፓ፣ መዐህድ፣ መኢአድ፣ ሶጎህዲድ፣ ኢብአፓ፣ ኦህዲህ፣ ከህኮ እና ጌህዴድ መሆናቸው ታውቅል፡፡
በተመሳሳይ ‹‹ከዓላማችን ለሚያደርሱን ተግባራት ተፈጻሚነት በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ የምትገኙ ኢትዮጵያውያን ተሳትፎ አስተዋጽኦ ያለው ድርሻ ከፍተኛ ስለሆነ ከጎናችን በመቆምና በንቃት በመሳተፍ የዜግነት ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ›› ሲሉ ለህዝቡ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡
Source Negere Ethiopia

ትንሹ መለስ በሲቪል ሰርቪስ ዩንቨርስቲ

Tuesday october 21,2014
ተሻለ መንግሥቱ (ከአዲስ አበባ)
mocis_tig_homeኢትዮጵያ እጅግ ድሃና ኋላ ቀር ከሚባሉ የዓለም ሀገሮች ተርታ የምትሰለፍ መሆንዋን የተለያዩ ዓለም አቀፍ ጥናቶች ያረዳሉ – እኛም በዘግናኙ ኑሯችን ይህንኑ መራራ እውነት እያረጋገጥነው እንገኛለን፡፡ በሰብኣዊ መብት አያያዝ፣ በኢኮኖሚ፣ በሥልጣኔና በመሳሰሉ የሀገርና የሕዝብ ጤናማ ዕድገት መለኪያዎች ከሁሉም ሀገሮች ግርጌ ሆኖ መገኘት ለገዢዎቻችን ምን ያህል የደስታ ስሜት እንደሚፈጥርላቸው ማወቅ ባንችልም እኛ ዜጎቿ ግን በየምንሄድባቸው ሀገራት ሁሉ በዚህ የ“ፊተኞች ኋለኞች ይሆናሉ” እውናዊ ክስተት በግልጽ የሚንጸባረቅበት ውራነታችን እያፈርንና እየተሳቀቅን በዚህ ዘመን ኢትዮጵያዊ ሆኖ መፈጠር የሚያሸክመው ቀምበር ምን ያህል ከባድ እንደሆነም ከጊዜ ወደ ጊዜ ይበልጥ እየተረዳን መጥተናል፡፡ በልማድ “ሳታጣ ያጣች” እያልን የምናንቆለጳጵሳት ሀገራችን በወያኔ ትግሬ የራሷ መዥገሮች ተወርራ ላሚቷ በመክሳቷ ለጥቂቶች ታልባ የማትነጥፍ ጥገት ስትሆን ለሚሊዮኖች ግን ድርቅ መትቷት ይሄውና ብዙዎቻችን የምንልሰውንና የምንቀምሰውን እያጣን በርሀብ አለንጋ እየተገረፍን እንገኛለን፡፡ ብልጭልጩ የአስፋልት መንገድና እዚያና እዚህ ሕይወት አልባ ሆነው የተገተሩት የሙሰኛ ዜጎች ቤቶችና ሕንፃዎች እንዲሁም ኢንዱስትሪና ፋብሪካዎች በሚሰጡን የተንሻፈፈ ምስል ሕዝቡ እንዳለፈለት በተለይ በገዢው የትግሬ ዘረኛ መንግሥት ሚዲያዎች ነጋ ጠባ ቢለፈፍም እውነቱ ግን በእጅጉ ተቃራኒና ለመግለጽም አስቸጋሪ ሆኗል፤ ብናነገር የማንታመን መሆናችን በራሱ የሚያስከትለው ጭንቀት ደግሞ ከበደሎች ሁሉ የከፋ በደል ሆኖብናል፡፡ የፍትህ ዕጦት የሚያሰቃየውን በዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንደተምበሸበሸ፣ የራበውን በልቶ እንደጠገበ፣ የተጠማውን ጠጥቶ እንደረካ፣ የታረዘውን ሡፍና ሀር ለብሶ እንዳማረበትና እንደሞቀው … ተደርጎ እንዲታይ በተለይ በዓለማቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ የውሸት ምስል ለመፍጠር የሚጥር መንግሥታዊ የፕሮፓጋንዳ ማሽን በመኖሩ የምሥኪኖች ዋይታና ልቅሶ እስካሁን ሰሚ ሊያገኝ አልቻለም፡፡ ሰውና እግዜር ተባብረው የጨከኑባት ሀገር – ኢትዮጵያ!
ድህነታችን አጥንትን ዘልቆ የገባና ሀገሪቱንና ሕዝቧን ጥልቅ ገደል ውስጥ የከተተ ሆኖ ሳለ የመንግሥት ሥልጣን የተቆጣጠሩት ወያኔዎች እየዘረፉት ያለው የሀገሪቱ ውሱን ሀብት እንዲህ በቀላሉ ሊገለጽ የማይችል መሆኑን አንድ አብነት ጠቅሰን በዚች ጽሑፍ ውስጥ ወረድ ብለን እንመለከታለን፡፡ እንዲህ የምናደርገው ለታሪክ መዝገብ ፍጆታ እንዲሆን እንጂ በአሁኑ ወቅት አድማጭ ተገኝቶ መፍትሔ ይኖራል ብለን እንዳልሆነ ሊታወቅ ይገባል – ያን ያህል ሞኝነት በአሁኑ ወቅት የለም፡፡ እንናገራለን – ሰሚ ቢጠፋ የኢትዮጵያ ዐፈርና ዛፍ ቅጠል ሰምቶ በታሪካዊ መዝገብነት ቀረፆ ያኖረዋል፤ መጪው ትውልድም ይፋረዳል፤ ይማርበታልም፡፡ እንጂ አፄ ቴዎድሮስ ካህናት አናደውት ሲገስጽ “አንድሽ አንባቢ አንድሽ ተርጓሚ” እንዳለው እነዚህ በሙስና የበከቱ ወያኔዎች አንዳቸው ሌላኛቸውን አደብ ለማስገዛትና ሥርዓት ለማስያዝ የሚያስችል የሞራል ብቃት አላቸው ተብሎ አይታሰብምና ከነሱ ምንም አንጠብቅም –  በዚያ ላይ “አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ” ወይም “የመጥረቢያ ልጅ መዘለፊያ” እንዲሉ በመሆናቸውና ለሀገርም ሆነ ለወገን የሚቆረቆር አንዳችም ስሜት የሌላቸው ግዑዝ ፍጡሮች በመሆናቸው ከነሱ አንዲት ቅንጣት በጎ ነገር መጠበቅ በሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ ራስን ማቂያቂያል ይመስለኛል፡፡ በሙስና ስም ሲካሰሱና ሲተሳሰሩ የምናያቸው ለሽፋን እንጂ እውነተኛ ምክንያቱ የሥልጣን ሽኩቻ ወይም ከጥቅም ጋር የተያያዘ የግል ጠብ ነው፡፡ በሙስና የተዘፈቀ ሰው በሙስና የተዘፈቀን ሰው እንዴት በፍትህ አደባባይ ሊያቆም ይችላል? ብዔል ዘቡል ብዔል ዘቡልን ሊያወጣስ ይቻለዋልን? ፈጽሞ የሚታሰብ አይደለም፡፡
ባለታሪካችን የወያኔ ጎምቱ ካድሬ የሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ የዕድሜ ይፍታህ ፕሬዚደንት የሆነው ዶክተር ኃይለ ሚካኤል ማንትስ ይባላል፡፡ ኢትዮጵያ በዘመነ መሣፍንት የአገዛዝ ቅኝት ሥር እንደምትገኝ አንዱ ተጨባጭ ማስረጃ የሚሆነን የዚህ ሰውዬ ሃይ ባይ የሌለው ጋጠወጥ አድራጎት ሲታይና በእግረ መንገድም ሀገራችን የገባችበት አዘቅት ምን ያህል ጥልቀት እንዳለው ስንረዳ ነው፡፡ በዚህ ላይ መማር አለመማር በወያኔ መንደር ምንም ማለት እንዳልሆነ እንገነዘባለን፡፡ አንድ ሰው ዶክተርም ሆነ ማስተርስም ኖረው ዘረኝነቱና ሆዱ ከዕውቀት እንደሚበልጥበት በነዚህ ዶክተር ተብዬ የወያኔ አንጋፋ ካድሬዎች አስነዋሪ ተግባራት እንረዳለን፡፡ እነዶክተር ቴዎድሮስ፣ እነዶክተር ገ/አብ ባርናባስ፣ እነ“ፕሮፌሰር” ክንፈ፣ እነዶክተር ሶሎሞን ዕንቋይ፣ እነዶክተር ሐጎስ፣ እነዶክተር አርከበ ዕቁባይ፣ እነዶክተር አብረኸት፣ እነዶክተር አምለሰት፣ እነዶክተር ፍትዊ፣ እነዶክተር ዘርዑ፣ እነዶክተር መዓሾ፣ ያሉትም የሞቱትም … የሚሠሩትን የዘረኝነትና የምዝበራ ወንጀል ሁሉ ተመልክተን “መማር ባፍንጫችን ይውጣ!” ብንል ሊፈረድብን አይገባም፡፡ አዲዮስ ትምህርት! (በአንድ ሆቴል ውስጥ አንዱ ጣሊያን አንዱ ሀበሻ የቀረበለትን ፓስታ በግሩም ሁኔታ በሹካ እየጠቀለለ ሲያወራርደው ባጠገቡ ተቀምጦ ይመለከታል አሉ፡፡ አበላሉ ሥልጡንና አንዲትም የፓስታ ክር ወደጠረጴዛው ወይም ደረቱ ላይ ወዳንጠለጠላት የገበታ ናፕኪን ጠብ ሳትልበት ጥንቅቅ አድርጎ ስለጨረሰ ፈረንጁ ታዛቢ ደስ ይለዋል፡፡  ግን ምን ዋጋ አለው – ያ ሀበሻ ሲያቀብጠው አንድ አቦሬ ውኃ አንስቶ ግጥም አድርጎ ይጠጣና ፓስታውን ያወራርድበታል፡፡ ያኔ ነው “አዲዮስ ፓስታ!” በማለት ጣሊያኑ የፓስታዋን በጎርፍ መወሰድ በጩኸት የገለጸው – እነሱ ወይን ነዋ የሚጠጡት፡፡ የኛም “ምሁራን” ዶክትሬታቸውን በዕውቀት ሣይሆን በዘረኝነት ለወሱት፤ በሙስና አጨቀዩት፤ ብኩርናቸውንም ለግል ጥቅምና ብልጽግና ሲሉ በርካሹ ሸጡት፡፡)
እያንዳንዱን የመንግሥት መሥሪያ ቤት ስናይ የሙስናው ነገር ያስደነግጣል፡፡ የወያኔ ነገረ ሥራ ሁሉ ሱቅ ውስጥ የገባ ሕጻን ነው፡፡ ሕጻኑ ሕጻን ስለሆነ ያንንም ይህንንም ግዙልኝ ቢልና ዐይን ዐዋጅ ቢሆንበት ሕጻን ስለሆነ አንፈርድበትም፡፡ ወያኔዎች ግን ሀፍረታቸውን ባወጣ ሸጠው የሀገሪቱን ሀብት በግላጭና ካለንዳች ይሉኝታ እየተቃረጡት ናቸው፡፡ የሌላውን ነገድ ባይተዋር አባላት በመጠኑ ስኳር እያስላሱ እነሱ ዋናውን ማር በአካፋና በጎላ ይዝቁታል፡፡ እነሱ ባለመብቶች ሌሎች መፃተኛ እንደሆኑ ስለሚቆጥሩም ከነሱ ፈቃድና ይሁንታ ውጪ የተፈጸመች ማንኛዋም የሌሎች ዜጎች ደቂቅ የሙስና ተግባር በሙስና ወደ እስር የምታስግዝ ናት፤ በዚያ ላይ ትንሽ ፖለቲካዊ ጣጣ ካለችባት ክሱ ወደሽርተኝነትም ሊለወጥ ይችላል፡፡ እንደነሱ በሙስና ለመብከትም ቅድመ ሁኔታ ያለው መሆኑን እንግዲህ ልብ ይሏል፡፡ እነሱ ለመብከት ያላቸው ሙስናዊ መብት ሌላው የለውም – በገዛ ሀገሩ ባይተዋርና የበይ ተመልካች ነዋ! እንደዜጋ አይቆጠርማ! ሌላው ዜጋ ቀበጥ አድርጎት ከነሱ እጅግ ባነሰ ሁኔታ እንኳን ሲሞስን ቢገኝ “ድምበር ዘለልክ! ቀስ ብለህ እደግ! ያደረችዋ ባቄላ… እናንተ ፊት ሲያሳዩዋችሁ፣ የዱሮው ይበቃችኋል …” በሚል አደብ እንዲገዛ ያደርጉታል፤ ትግሬ ወያኔ ግን ወያኔ ያልሆነን ሺህ ዜጋ ቢገድል፣ በቢሊዮን የሚገመት ገንዘብ ቢዘርፍ ጠያቂ የለውም – የድርሻውን እንደገደለና የድርሻውን የደም ካሣ እንደወሰደ ይቆጠርለትና እንዲያውም የሚመሰገን ይመስለኛል (በኤርምያስ ለገሠ መጽሐፍ የተገለጸችውንና የሚጣል የበግ ቆዳ ለአንዲት ምሥኪን ጠላ ሻጭ በመስጠቷ ምክንያት ከሥራ የተባረረችውን ሴት እዚህ ላይ ያስታውሷል፤ ያቺ ሴት ትግሬ ብትሆን ኖሮ – በግልጽ እንነጋገርና – አይደለም አንድ ወይ ሁለት የበግ ቆዳ መቶ ሺህ ለዕርድ የተዘጋጁ በጎችን ለፈለገቺው ሰው ብትሰጥ ግፋ ቢል “ምን ነካሽ አንች ልጅ? ዕረፊ እንጂ!” ተብላ በ‹ድርጅቱ› ትገሰጽ እንደሆነ እንጂ ዝምቧን እሽ የሚለው አይኖርም – ምክንያት፡- የአብዮቱ ዋና አንቀሳቃሽ ከሆነው የጠራ ዘር – ምናልባትም ከ“እሽ አትበሉኝ የሹም ዶሮ ነኝ” ምርጥ የዐድዋ ዘር የተገኘች ናታ!)፡፡ እዚህ ላይ የሚታየውን ዐይን ያወጣ ልዩነት ለመግለጽ ያህል እንጂ ለሙሰኞች አቦካቶ መሆን ቃጥቶኝ እንዳልሆነ ማስታወስ እፈልጋለሁ፡፡ ሙሰኛ ሙሰኛ ነው፡፡ የየትኛውም ጎሣ አባል ይሁን፣ በትንሹም ይሞስን በብዙው፣ ሙስና ያው ሙስና (ጥፋት) በመሆኑ በፍጹም ወገንተኝነት ሊያሳዩበት አይገባም፤ ነውርም፣ ኃጢኣትም፣ ወንጀልም ነው፡፡ በፍትህ ሚዛን ጥፋት ሁሉ እኩል የሚለካና እንደየጥፋቱ ቅለትና ክብደት ተገቢውን አንቀጻዊና ኅሊናዊ ፍርድ ማግኘት የሚገባው እንጂ በዘርና በነገድ፣ በትውውቅና በዘመድ አዝማድ እንዲሁም በጉቦና በመማለጃ ገጸ በረከት(በዓይነትም ይሁን በገንዘብ) ፍርድ የሚያዛቡበት ሊሆን አይገባም፡፡ ግን ግን ትግሬ ወያኔ ብቻ የፈለገውን ይዝረፍ ሌላው ግን የተንጠባጠበችዋን እንኳን ሳትቀር መሬት ላይ አግኝቶ ቢልስ ዘብጥያ ይውረድ የሚል ጭፍን ያለ “ፍትህ” ሲበየን እንደ አንድ ሀገር የጋራ ዜግነት ክፉኛ ያማል – የህመሙ ቃንዛ አጥንትን ሰርስሮ መቅኒ ውስጥ እስኪገባ ድረስ፡፡ ለፍርድና ለንግግር ያስቸገረ ሁኔታ እኮ ነው የገጠመን፡፡ ምን ይሻለን ይሆን አሁንስ? ወደፊትስ ይህን ጉዳችንን እንዴት ነው ለሰው የምናወራው? በጣም እኮ ነው የሚያሣፍር! በዚህ የ21ኛው መቶ የ‹IT› ዘመን እንዲህ ያለ ሀገራዊ ውርደት ይግጠመን? እግዜሩን እግዜር ይይለት! ኃጢያታችን ምን ከሰው ቢከፋ እንዴት በዚህ ዓይነት ለወሬ እንኳን በማይመች አሸማቃቂ ቅጣት ይቀጣናል?
እዚህ ላይ አንድ ቁጭት እናንሳ፡፡ የዚህች ሀገር ሀብት በሙስና እንዲህ እየተዛቀ ባይዘረፍ ኖሮ ስንትና ስንት የልማት ሥራ ይሠራ ነበር? ስደትና ሥራ አጥነት በስንት ደረጃ ይቀንስልን ነበር? ከላይ እስከታች ያለው የወያኔ ባለሥልጣን በሚያገኘው አጋጣሚ ሁሉ፣ ራሱም አጋጣሚውን እየፈጠረ የጋራ ሀብታችንን እንዲህ ከቋት ከቋቱ ባይሞጨልፍብን ኖሮ አንድ የአባይ ግድብ አይደለም መቶና ሁለት መቶ ትላልቅ የልማት ዕቅድ አይጠናቀቅም ነበር ወይ? ቁርሱን እንደነገሩ ቀምሶ የምሣና የእራቱ  ነገር ህልም ከሚሆንበት ሲቪል ሰርቫንት (የመንግሥትና የግል ተቀጣሪ ሠራተኛ?) ለአባይ ግድብ ደመወዙን በግዳጅ ከሚቆረጥ በሰፊ ቧምቧ ወደ ግለሰብ ኪስ የሚንዶለዶለው የሀገር ሀብት ቢገደብ የአንድ የአምስት ስድስት ባለሥልጣናት ገንዘብ ብቻ ግደቡን አያሠራም ነበር ወይ? መከላከያን ወደቢዝነስ በመለወጥ በንግድ ስም የሚካሄደው ስርቆት፣ በባለሥልጣናትና ዘመዶቻቸው እንዲሁም በጥገኛ መዥገሮች በሙስና እየተወሰደ የሚቸበቸበው መሬታችንና ሀብታችን፣ በጦርና በፖሊስ ከፍተኛና መካከለኛ መኮንኖች የሚካሄደው ለከት ያጣ ዘረፋ፣ በመሣሪያ ግዢ ሰበብ፣ በስንቅና ትጥቅ፣ ለወንበር ጥበቃ ለተሠለፈው የመከላከያ፣ የደኅንነትና ፀጥታ ተቋማትና አባላት በከንቱ የሚፈሰው የሀገር ሀብት፣ በወያኔው የኢንዳውመንት ተብዬዎቹ የንግድ ድርጅቶች፣ ወዘተ. የሚመዘበረው ከግምት በላይ የሆነ የሀገር ገንዘብ ድህነትን ከኢትዮጵያ በስንት ማይል ያባርር ነበር?  በመለስ ስም – ሊያውም ሳይበላው ለሞተው – ስንት ቢሊዮን ዶላር አለ? ባለሥልጣናት ስንትና ስንት ተንቀሳቃሽና የማይንቀሳቀስ ሀብት በሀገር ውስጥና በውጪ አካብተዋል? በመለስ ልጅ በሰምሃል ስም ተቀምጧል የተባለው ከአምስት ቢሊዮን የሚበልጥ ዶላር  ስንት ግድብና ስንት ዘመናዊ ሆስፒታል ያሠራ ነበር? በየምሽት ክበቡ ለምታስታውክበትና ጎረምሣ ለምትቀልብበት ለዚህች አሳዳጊ ለበደላት የመርገምት ውጤት የኢትዮጵያ ሕዝብ ገንዘብ እንደቅቤ በከንቱ የሚቀልጠው የምን ፍርጃ ይሆን? ስንቶቻችን ነን በቀላ ሊድኑ በሚችሉ ጥቃቅን በሽታዎች በየቀኑ እንደቅጠል የምንረግፍ? ስንቶቻችን ነን በርሀብ አለንጋ የምንገረፍ? ለመሆኑ በዚያች ማሕጸን ውስጥ ውኃ ብትሆን በሚሻላት አዜብ በሚሏት መበለት ስም ስንት ዶላር አለ? በእያንዳንዱ ባለሥልጣንና ዘመድ አዝማዶቹ ስም ስንት ገንዘብ በየባንኩ አለምንም ሥራ ታጉሯል? በግለሰቦች እንደተመዘበረ ከተደረሰበትና ውጪ እንደኮበለለ ወይም ወዳገር ሳይገባ በዚያው እንደቀረ ከተነገረው የ8.5 ቢሊዮን ዶላር የአንድ ወቅት ሪፖርት በተጨማሪ በየጊዜው በድብቅ እየወጣ የሚጠፋው ዶላርና ወርቅ ስንት ይሆን? ያ ጋጠወጥ ቀልበ-ቢስ ቱጃርና መሰሎቹ ልበ-ሥውራን ሀብታሞች አለመላው የሚጫወቱበት የሀገር አንጡራ ሀብት በስንት ቢሊዮን ይገመታል? ታዲያ ኢትዮጵያና ሕዝቧ በአጥንታቸው መሄድ ይነሳቸው? የግፋቸው ግፍ ደግሞ ከዚችው ከልደታ እስከባታ እንኳን መድረስ ከማትችለው ደሞዝ ተብዬ አነስተኛ ምንዳ ላይ ከዓለም ሀገሮች በከፍተኛነቱ እጅግ በሚለየው የሥራ ግብርን(income tax) ጨምሮ በፈለጉት ሰበብ መዝረፋቸው ነው( ይገርማችኋል- በዓመት አምስት መቶ ሺህ የተጣራ ገቢ ሊያገኝ የሚችል ነጋዴ አጭበርብሮና ከግብር አስከፋይ ኃላፊዎች ጋር በጥቅም ተሞዳምዶ በዓመት ከአምስት ሺህ ያልበለጠ የገቢ ግብር ሲከፍል እንደኔ ዓይነቱ ደመወዙ ላይ አንድም ድምፅ የሌለው ምሥኪን ሠራተኛ ቫትን ጨምሮ ከደመወዙ 50 በመቶ አካባቢ ይቆረጥበታል፤ ፍትህ የት አለች? ሰሚም ባይኖር አብረን እንጠይቅ፡፡) ዳሩ እነሱ ደሞዛቸውን አያውቁት፤ ዳሩ እነሱ ምን ገደዳቸው በደሞዛቸው አይኖሩ፤ እነሱ ደሞዝን ለስም እንጂ መች ሲጠቀሙበት ፡፡ ይብላኝ ለኛ እንጂ፡፡ እግዜሩ፣ ጨካኙን መንግሥቱ ኃ/ማርያምን ወስዶ እነዚህን አረመኔ ገዢዎች የሰጠን ምን ያህል ክፉ ብንሆንበት ይሆን? ለመልስ ዳተኛ ቢሆንም እሱንም እንጠይቀው፡፡
ሁሉን ቢያወሩት ራስን ከማሳመም ውጪ ትርፍ የለውምና ስለዶክተር ተብዬው የወያኔ አንዱ መሥፍን ትንሽ እናውጋ፡፡ ነገር እየተጎተተብኝ አንዱን ጀምሬ በቅጡ ሳልቋጭ ሌላውን ማንሳቴን አውቃለሁና ይቅርታችሁን – ወድጄ እንዳይመስላችሁ፡፡
ይህ ሰው ሲቪል ሰርቪስን እንዲመራ ከተመደበ 20 ዓመት ሊሞላው ጥቂት ጊዜ ነው የሚቀረው፡፡ ያን ግቢ እንደፈለገው ያሽከረክረዋል፤ አስፈሪና አስጨናቂ ንጉሥ ነው፡፡ የእናት አባቱ ርስተ ጉልት ይመስል በወያኔ ካድሬነቱ በመኮፈስና ከማንጠልጠያዎቹ ጋር ባለው የጥቅም ትስስር ምክንያት ማንም ምንም ሊያደርገው እንደማይችል በመረዳት መምህራንና ሠራተኞችን ሲያንገላታ አንድም ጠያቂ የለውም፡፡ በድንጋይ ማምረቻነት የሚታወቀውን ይህን ዩኒቨርስቲ ልክ እንደ አንድ ኪንደር ጋርተን (ሙኣለ ሕጻናት) በመቁጠር እንደፈለገው ይዘባነንበታል፡፡ በሰሞኑ የወያኔ የዩንቨርስቲ መምህራን ሥልጠና ግና በስብሰባው መጨረሻ ላይ በተከፈተች አንዲት ጠባብ “የተቋማችሁን ችግሮች አስረዱ” የምትል መድረክ ምክንያት የዚህ ሰውዬ ገመና ተፍረጥርጦ ሊነገር ችሏል፡፡ ደፋር አይጥፋ፡፡ እስከዶቃ ማሰሪያው ነው የነገሩት፡፡ ከሰማሁት በጥቂቱ ላካፍላችሁ እችላለሁ፡፡ የሰውዬው ገመና በተለይ ይህን ተቋም ለሚያውቅ የአደባባይ ምሥጢር ስለሆነ አዲስ ነገር አልናገርም፡፡ (በነገራችን ላይ ዩኒቨርስቲው ካባ (ድንጋይ ማምረቻ) እየተባለ የሚጠራው በመምህራኑ ዕውቀትና ችሎታ ማነስ ሣይሆን በፖለቲካው ቅኝት ተመርጠው የሚገቡት ተማሪዎች “ሀ” ቢሏቸው “ሁ” የማይሉ ደናቁርት በመሆናቸው ነው፡፡ በወያኔ ቡድን ከወረቀትና ከታማኝነት ባለፈ የትምህርት ጥራትና ብቁ የዲግሪ ትምህርት አያስፈልግም፡፡ ስለሆነም እምነት የሚጣልበት ቅን ታዛዥ ይሁን እንጂ ከስምንተኛ ክፍልም ቢሆን ተመልምሎ የሚላክ ካድሬ የላከው ድርጅት የፈለገው ድግሪ በተቋሙ እንዲሰጠው የወያኔ ያልተጻፈ ህግ ያስገድዳል – ዐይኑን ሳያሽ የታዘዘውን የሚፈጽም ሙሰኛ አለቃም ስላለ  ድንጋይ ለማምረት አደናቃፊ ነገር አይኖርም፡፡ የድንጋዮች መጨረሻ አምሮ እንደማያውቅ ብጠቁም ግን ደስ ይለኛል፡፡)
  1. ሰውዬው ፍጹም አምባገነን ነው፡፡ በግቢው ውስጥ ያሉ ትላልቅና ንዑሳን የሥራ ክፍል ኃላፊዎች በፕሬዝደንቱ በኩል ሳያልፍ ከማንም ጋር ምንም ዓይነት መደበኛም ይሁን ኢ-መደበኛ ግንኙነት እንዲያደርጉ አይፈቀድላቸውም፡፡ ለዚህም ሳይሆን አይቀርም ምንም ደብዳቤ መጻፍና መላላክ እንዳይችሉ አንዳቸውም ቢሮ የሥራ ክፍሉ ማኅተምና የኃላፊው ቲተር እንዳይኖር የተደረገው፡፡ እንኳንስ በአንድ ትልቅ ዩኒቨርስቲ በአንዲት ትንሽ ተቋም እንኳን፣ ልዩ ልዩ የሥራ ክፍሎች እዚህ የተጠቀሱት የመደበኛ ደብዳቤ መላኪያ ማኅተምና ቲተር ያስፈልጋቸዋል፡፡ ይህ አፄ መለስ ዳግማዊ ግን ይህን አልፈቀደም፡፡ ሁሉንም በርሱ ሥር ማሳለፍና መቆጣጠር ይፈልጋል፡፡ ተቋሙ የግሉ ንብረት እንደሆነ ያህል ስለሚሰማው በንብረቱም ሆነ በገንዘቡ ያሻውን ያደርጋል፤ እንደብዙዎቹ ወያኔዊ የመንግሥት ተቋማት ሁሉ በዚህ ግቢም ቁጥጥር ብሎ ነገር የለም፡፡ ሠራተኞችንና መምህራንንም አባቱ የቀጠሩለት የዱሮ ዘመን ባሪያዎች የሆኑ ያህል ሳይቆጥራቸው አልቀረም፡፡ የሚገርም ‹ዶክተር› ነው እባካችሁ!
  2. ሠራተኞችንና መምህራንን ደስ ባለው ጊዜ እየተነሣ ከሥራ ያባርራል – ይህም ጠባይ ሀገሪቱን እንደግል ርስት የያዙ የሚመስላቸው የብዙ መንግሥታዊ መሥሪያ ቤቶች የሥራ ኃላፊዎች የሚጋሩት ነው፤ ወያኔን አይንኩ እንጂ በሌላው ጎሣና ነገድ ላይ እንደዐይጥ እንዲጫወቱበት ዘረኛ ሥርዓቱ ይፈቅድላቸዋል – በትግሬ ላይ ቢያደርጉት ግን የአለቃ ገ/ሃናን “እዚያም ቤ እሳት አለ!” የሚለውን ብሂል ሊያስታውሱ የግድ ነው (መለስ ስለሚስቱ ሲናገር እሳት የሚተፋ ምን ነበር አላት ያለው?) ፡፡ ሰውዬው – ዶፍተሩ – ከመጠን በላይ አሉቧልታና ሀሜት እንደሚወድ ይነገርለታል፤ በትንሹም በትልቁም እያኮረፈ ታዲያን ሠራተኞችን ከሕግ ውጪ ከሥራ ያግዳል፤ ያባርራል፡፡ ባለፈ አንድ ወቅት አንዳችም መሠረታዊ አሳማኝ ምክንያት ሳይኖረው ስምንት መምህራንን አባርሮ እንደነበርና ኋላ ላይ ግን ብዙዎቹ በፍርድ ቤት ተከራክረው መመለሳቸው ታውቋል፤ ይህም በስብሰባው ላይ ተገልጾኣል፡፡ አምባገነን ግለሰብ ከአምባገነን የመንግሥት ሥርዓት ጋር ሲጎዳኝ የዜጎች የመኖር ዋስትና እንዴት እንደሚጨፈለቅ ከዚህ ሰውዬ ነውረኛ ድርጊት መገንዘብ ይቻላል – ተምሮ ያልተማረ ማይም፡፡ በአንድ የምረቃ መጽሔት የመጨረሻ ቃል ማስፈሪያ የፎቶዋ ግርጌ ላይ አንዲት ተመራቂ “ሣይማሩ ላስተማሩኝ መምህሮቼ ምሥጋና ይድረሳቸው” የሚል አስደንጋጭ ሐረግ ማስቀመጧን አሁን ሳስበው የዚህ ‹ዶክተር› ትምህርትም ውኃ እንደበላው ገባኝ፡፡ ግን ግን ሞኝ አትበሉኝና መማር ለመደደብ በር ከፋች ዘበኛ(doorman) ይሆን እንዴ?
  3. አምስት መቶ ሺህ ብር እንኳን በማትፈጅ ትንሽዬ ድልድይ ስምንት ሚሊዮን ብር እንደፈጀ አድርጎ ማወራረዱ ተሰብሳቢን በሣቅ ባፈነዳ ሁኔታ ጉባኤው ላይ በግልጽ ተነግሯል፡፡ በዚህ ትንሽ ሰው ይህን ያህል የሀገር ሀብት ከተዘረፈ እሱን መሰሎች በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ የወያኔ ካድሬዎች ምን ያህል የሀገር ሀብት ሊመዘብሩ እንደሚችሉ ይታያችሁ፡፡ አሁንም ከፍ ሲል የጠቀስኩትን እዚህ ልድገመው – እናም እኛ ኢትዮጵያውያን በችጋርና በችግር ያላከክን ማን ሊያክ ኖሯል? ድልድይቱን እኔም በዐይኔ በብረቱ አይቻታለሁ፡፡ ዩኒቨርስቲውን በስተጀርባ በኩል ካለው መንገድ የምታገናኝ በጣም ትንሽ ድልድይ ናት፡፡ የሚገርመው “ስምንት ሚሊዮን”ም ፈጅታ ከተሠራች ስድስት ወር ሳይሆናት ተሰነጣጥቃለች፡፡ ምን ይታወቃል – ለማሳደስ በሚል ሰበብ ደግሞ አንድ አሥር ሚሊዮን ብር ወጪ ይደረግባት ይሆናል፡፡ የተዓምራት መገለጫ በሆነች ሀገራችን ምን የማንሰማው ድንቅ ነገር አለ?
  4. ይቺኛዋ ታሪክ ደግሞ ትንሽ ቆየት ያለች እውነተኛ ዘገባ ናት፡፡ አንድ ጊዜ ነው – ብዙ የሕዝብ ማመላለሻ የቻይና ሃይገር አውቶቡሶች ወደዩኒቨርስቲው ይመጣሉ፡፡ ሹፌሮቹም አቶ ማንን ነው እቴ – ዶክተር እንጂ፣ ዶክተር ኃይሌን ጥሩልን ይላሉ፡፡ ዶክተሩ ተጠርቶ ሲመጣ ሾፌሮቹንና መኪኖቹን ባዬ ጊዜ በድንጋጤ ተውጦ “ለምን እዚህ መጣችሁ? ለምን በስልክ አታናግሩኝም?” በማለት ይጮህባቸዋል፡፡ እነሱ ደግሞ የገጠማቸውን ችግር ያስረዳሉ – የመጡት ከመኪና መሳደሪያ ሒሳብ ጋር በተያያዘ በገጠማቸው እሰጥ አገባ ምክንያት የደረሰባቸውን ጊዜ የማይሰጥ ችግር ለማስረዳትና በወቅቱ መፍትሔ ለማግኘት ነበር፡፡ ለካንስ እነዚያ መኪኖች የዶክተሩ የግል ንብረቶች ናቸው! አንድ የዩንቨርስቲ ፕሬዚደንት ይህን ያህል ሀብትና ንብረት ማፍራት እንዴት ይችላል? አዎ፣ የኛ ሀገር የወያኔ ካድሬዎች የሆኑ “ምሁራን” ሙስና እንደማይዘወተርበት በሚታመነው የትምህርቱ መስክ ሣይቀር ይህን የመሰለ ዘረፋ ያካሂዳሉ – በሌሎች መስኮች የሚገኙትማ እንዴቱን ያህል አይዝቁት፤ የየባለሥልጣኑ ሆድ እንዴት ነው እንዲህ እንደፊኛ እየተለጠጠ የሀገርን ሀብት የሚያግበሰብሰው ጃል! ታዲያ እኛ ያልከሳን ያልጠቆርን ማን ይክሳ፣ ማንስ ይክሰል? አክስቴ ማንጠግቦሽ አሥሯን አሥራ አምስት አደርጋለሁ ብላ በየጉሊቱ የሃምሣ ብር ቃሪያና ሽንኩርት በአንድ ብርና በሁለት ብር ትቸረችራለች – እነወያኔ ደግሞ በየቀኑ በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ከድሃዋ ኢትዮጵያ በሰበብ አስባቡ ይዘርፋሉ፤ እነሱ እየዛቁ ወደግል ካዝናቸው ሲከቱ ሀገሪቱ ለደሞዝ መክፈያ እንኳን እጅ እያጠራት ከቀን ወደ ቀን እየደኸየች ትሄዳለች፤ የነዚህን ወያኔዎች ቀዳዳ ሆድ ለመሙላትም ብሔራዊ ባንክ በየቀኑ የወረቀት ግፋፎ እያተመ ገበያውን ያጨናንቀዋል፡፡ ሠራተኛው በዚህ መሀል ጭዳ ይሆናል – ግራሟ(ክብደቷ) የአንድ ጆሮ ጌጥ ለምታህል አንዲት ጉርሻ ፎርኖ አንድ ብር ከሠላሣ ሣንቲም እየገዛን ልጆቻችንን ቁርስ ማቅመስ አቅቶን ባዶ ሆዳቸውን ትምህርት ቤት የምንልክ ብዙ ነን – ሊያውም ለዚህም የታደልን እንጂ ዩኒፎርምና ደብተር መግዛት እያቃተው ስንቱ ወላጅ መሰላችሁ ልጆቹ በረንዳ ሲያሞቁ ውለው ማታ ሲገቡ ወይም በየጎዳናው ሲርመሰመሱ እያዬ አንጀቱ የሚቃጠለው፡፡ በዓይነቱ የተለዬ ዕንቆቅልሽ ገጥሞናል፡፡ ፈጣሪ ይሁነን እንጂ በዚህ ከቀጠልን በጥቂት ዓመታት ውስጥ ስሊያችንን አንቀው እንደተራበ ነብር ደማችንን በጠራራ ፀሐይ ሳይመጡት አይቀሩም፡፡ እነዚህ መዥገሮች ቀላል እንዳይመስሏችሁ፡፡
  5. አንድ መምህር ለትምህርት ወደ ውጭ ሀገር ይሄዳል፡፡ ባለቤቱና ሕጻን ልጁ በግቢው በተሰጣቸው ቤት ይኖራሉ፡፡ ይህ ዶክተር ሕጻን ይመስል ከመምህሩ ጋር በተጋባው እልህ ምክንያት ሴትዮዋን ከቤቱ ውጪ ይላታል፡፡ ቤት አፈላልጋ ልትወጣ ወደግቢው ስትገባ ዘበኞቹ አትገቢም ይሏታል፡፡ የሚገርመው በፊት ስትወጣም አትወጪም ተብላ በመከራ ነው የወጣችው፤ አትወጪም – አትገቢም፡፡ የወያኔ ነገር “ያውጡብሽ እምቢ፣ ያግቡብሽ እምቢ” መሆኑ አይገርምም? ምን ዓይነት ትዕዛዝ ነው? ከዛም የምታደርገውን ስታጣ ፖሊስ ይዛ መጣችና የምታጠባው ሕጻን ልጅ ስለነበረ እንድትገባ ተደረገ፡፡ ሰውዬው – ዶክተሩ – ግራ የሚያጋባ ስብዕና ባለቤት ነው – እንደብዙዎቹ ወያኔዎች፡፡ ወያኔዎች ሥራቸው ሲታይ የሕጻንነት ጊዜያቸውን ሳይጨርሱ ይመስለኛል ትልቅ የሚሆኑት፡፡ እልሃቸው ይገርማል፤ ቂም በቀልን የሚወጡበት ሥልት ይገርማል፤ የሚጠሉትን ለማጥቃት የሚሄዱበት አስቂኝ መንገድ ሁሉ ይገርማል፡፡ አሁን እስኪ ይታያችሁ “ከስምንት ዓመት በፊት የገዛሃት መኪና የቀረጥ ችግር ነበረባት” ብሎ ከተሸጠችና ከተረሳች ዘመን ያለፋትን መኪና ታሪክ – ችግሩ እውነት ነው ብለን ብናምንላቸውም እንኳን – ከመቃብር አውጥቶ ሰውን መክሰስ ሕጻንነት እንበለው ወይንስ መጃጃል? በርግጥም ለሀገር የሚቆረቆሩ ከሆነ እስኪ የዶክተር ኃይሌን ድልድይ ወጪ ያጣሩና ከዚያች መኪና የበለጠ ገንዘብ ለ“መንግሥት” ለማስገባት ይሞክሩ፡፡ እንዴ! ምንድናቸው እነዚህ “ሰዎች”?
  6. አንድ ወቅት ለሰባት መምህራን ቤት ሊሰጥ ከሃያ መምህራን መካከል በተቀመጡ መሥፈርት አማካይነት የማጣራት ሥራ ይካሄዳል፡፡ ከሃያዎቹ መካከልም ሰባቱ ነጥረው ይወጡና ከአንድ እስከ ሰባት በደረጃ ይቀመጣሉ፡፡ ሰውዬው ይህን ሲመለከት ከሰባቱ ውስጥ በተለይ አንደኛና ሁለተኛ የወጡትን ሁለት ግለሰቦች አይወዳቸውም ነበርና ውጤቱን ለመገለባበጥ አዲስ መስፈርት ይጨምራል፡፡ ያም መመሪያ የአስተዳደር ግምገማ ከ20 በመቶ እንዲያዝ የሚል አዲስ ትዕዛዝ ነው፡፡ በአዲሱ “መመዘኛ” መሠረት ሰውዬው የሚፈልጋቸው በፊተኛው የማጣራት ሂደት የወደቁ ሁለቱ ግለሰቦች አንደኛና ሁለተኛ እንዲወጡ ሆኖ የፊተኞቹ አንደኛና ሁለተኛ የወጡ መምህራን ፎሪ ይደረጋሉ፡፡ የሚገርመው ዝርዝሩ ብዙ ስለሆነ እዚህ ላይ መጥቀሱ ይከብደኛል እንጂ በአዲሱ መመዘኛም እነዚያ ቤት እንዳገኙ የተደረጉ ሁለት መምህራን እነዚህኞቹን በውጤት በልጠዋቸዋል፤ ግን ሞኝ እንዴት ያሸንፋል ቢሉ እምቢ ብሎ እንዲሉ ሆኖ በድርቅና ብቻ እንዲያሸንፉ ተደረገ፡፡ ይህን ዐይን ያወጣ የመድሎ ሥራ ሁሉም የግቢው ሰው ያውቀዋል፡፡ ነገር ግን ዘረኝነት ያሳወረውን ሰው መጋፈጥ ለበለጠ ጥቃት ማጋለጥ በመሆኑ ገፍቶ የሄደበት ሰው የለም፡፡ በቀደም ዕለት ግን ይህ አስነዋሪ ተግባር በአደባባይ በስብሰባው ወቅት ተጋለጠና ሰውዬው የሀፍረት ጃኖ ለበሰ፤ ግን ማፈርስ ሲያውቅበት አይደል?
  7. በዚህች የመጨረሻ ድሃ ሀገር ይህ ሰውዬ ለመሥሪያ ቤት ሥራ የሚጠቀምባቸው መኪኖች ቁጥር አራት ናቸው፡፡ “ሁሉ አማረሽን ገበያ አታውጧት” እንደምንለው ወያኔዎች ካሉባቸው መጥፎ ጠባዮች አንዱ ሁሉንም ነገር የመቆጣጠር አባዜ ነው፡፡ በአንዲት ድሃ ሀገር የአንድ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ኃላፊ አንድ ዐይን የማይገባ መኪና ቢጠቀም የትኛው ክብሩ ይቀነስበታል? የዚህ ሰውዬ መኪኖች ዋጋ ደግሞ ሰማይ ነው፡፡ እንደሚባለው ድምር ዋጋቸው ከአምስት ሚሊዮን አያንስም፡፡ የመኪኖቹ ዋጋ ራሱ በአንድ መንደር አንድ አነስተኛ ክሊኒክ ሊያሠራ ይችላል፡፡ የአንድ ሀገር ባለሥልጣን የሚያስተዳድረውን ሀገር ሕዝብ ኢኮኖሚያዊ አቅምና የአገሩን የዕድገት ደረጃ ካላወቀ ዓለም እስክትታዘበው ድረስ ትልቅ ችግር ይፈጠራል፡፡ ለምሳሌ በሚከፈለው ደሞዝ የወር ቀለቡን መሸፈን ሳይችል በርሀብ የሚንጠራወዝ የመንግሥት ሠራተኛን በሥሩ ያቀፈ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር ሚኒስትር ለፕሮቶኮሉ ሣይሆን ለደኅንነቱ ሲባል በእግሩ እንዲመላለስ ባይጠበቅበትም በአምስትና ስድስት ሚሊዮን ብር በሚገዛ ተሸከርካሪ እንዲጓዝ ኅሊናው ሊፈቅድለት አይገባም፡፡ አእምሮ የተፈጠረው አዙሮ ለማየት ነውና የሚያስተዳድሩትን ሕዝብ ኑሮና አጠቃላይ ሁኔታ ወረድ ብሎ ማየትና ባጭር ታጥቆ የሕዝብን ችግር ለመጋፈጥ መነሣት ከአንድ ሀገር ወዳድ ባለሥልጣን የሚጠበቅ ነው – እንደወያኔ የድሆችን ገንዘብ እየመዘመዙ በድሃ ላይ መንቀባረር ሳይሆን “እንዲህ ከምቀናጣ ለሕዝቤ ስል ይህን ይህን ነገር ልተው” ማለት ይገባል – “ሆድ” ደግሞ “እንዳሳዩት ነው” ይባላል፡፡ በመሠረቱ ሀገርን ለማስተዳደር በቅድሚያ ሀገራዊና ብሔራዊ ስሜት ያስፈልጋል፡፡ አሁን የምንጮኸው ጅብንና ዓሣማን እንደሰው አስቡ የማለት ያህል ነው፡፡ ከንቱ የቁራ ጩኸት፡፡ ምን ይሻለን ይሆን ግን?
ወያኔ ጋር ለመሥራት ኅሊና ስለማያስፈልግ እነሱን ተጠግቶ ሀገሪቱን ባለ በሌለ አቅሙ የሚግጠው የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ዜጋ ብዙ ነው – ያ የእግር ኳስ አሰልጣኝ እንኳ ግብ በገፍ የሚያስተናግድ ልፍስፍስ ቡድናችንን ለ“ማሠልጠን” የስንትና ስንት ሠራተኛ ደመወዝ ጭማሪ ቢሆን የብዙ ሕጻናትን ወስፋት ይሸነግል የነበረ 500,000.00 ሺህ ብር አይደል በየወሩ የሚከፈለው? በሞኝ ደጃፍ ሞፈር እንደተቆረጠ በኢትዮጵያ ግዛት ፀሐይ ሳትወጣ እስከመቼ እንደምንዘልቅ ሳስበው ግርም ይለኛል – ለዚህ ለዚህማ ሰውነት ቢሻው እንደለመዳቸው እያሰለጠናቸው ደህና ደሞዝ ቢከፈለው ምን ነበረበት? ለምን በቆዳ ይታመናል? ራስን እየናቁና የራስን እያጣጣሉ የት ይደረሳል? ይህን የምለው በሁሉም ዘርፍ ስላለው የጭቡ ሥራ ሁሉ እንጂ የስፖርቱን ብቻ አይደለም፡፡ ለአብነት በትምህርቱ ዘርፍ ዶክትሬት ይኑረው አይኑረው፣ ዶክትሬቱ ሊያስተምር በተቀጠረበት የትምህርት ዓይነት ይሁን አይሁን ሳይታወቅ እንዲሁ በቀለምና በዘር የማምለክ ጠባያችንና ምናልባትም በሙስናዋ ደንዝዘን ለአንድ የሕንድ ዶክተር ተብዬ መምህር ብዙ ሺህ ብር ስንከፍል እሱን ለሚበልጠው ኢትዮጵያዊ ምሁር ግን አንድ አሥረኛውን እንኳን አንከፍለውም፤ ለምንከፍለው አነስተኛ ገንዘብም እንቆጫለን – ወጉ አይቀርምና ሲሉም ተሰምቷልና በሚዲያችን ላይ “brain drain” እያልን እናላዝናለን – የውሸታችንን፡፡ ለመሆኑ በአሁኑ ወቅት ስለሀገር የሚጨነቅ አንድ ባለሥልጣን አለ? ለተማራና ለሠለጠነ የሀገር ልጅ ቅድሚያስ የሚሰጥ ተቋም አለ? የለም፣ ምክንያቱም ብዙዎቻችን የምቀኝነትና የማይምነት ልክፍት ሰለባዎች ነና፤ ፈረንጁ ሲልጠን ደስ ይለናል፤ የኛው ሲያገኝ ግን ይከፋናል፤ ብዙዎቻችንን የተጠናወተንን ጠማማ አስተሳሰብና አመለካከት በአወንታዊ የቀናነት ቅባት ካላሸነው ከዚህ በበለጠ ገና እንጠፋለን፤ ምቀኝነትና ቅናት ፈዋሽ ጠበል ካልፈለቀላቸው ሀገርን የሚያጠፉ አደገኛ መርዞ ናቸው፡፡ እንዲያው ባጭሩ ግን ብዙዎቻችን ፈረንጅ አምላኪዎች ነን – የማንረባ! ስንቱ ጉዳችን ተነግሮ ይዘለቃል እባካችሁ(በተማሪ መግቢያና መውጫ ሰዓት ነጭ ገዋን አልብሰው ባገሩ አትክልተኛ የነበረ ማይም ፈረንጅ በግቢያቸው የሚገትሩ  የግል ትምህርት ቤት ባለቤቶች እንዳሉ ሰምታችኋል? ወላጅ ልጁ በፈረንጅ ሲማርለት እየታየው የተጠየቀውን ገንዘብ ይከፍላላ! መቼ ይሆን ሰው የምንሆነው?)፡፡ እውነቱን ያ ብላቴና “ባለቤት የሌላት ከተማ” ያላት አዲስ አበባን፡፡ ሀገሪቱም ሕዝቧም እንደጠፍ አህያ ማንም እንደፈለው የሚጭነን ባለቤት አልባዎች ሆነናል፡፡(እዚች ላይ ባጭሩ ሳልጠቅሳት ማለፍ የማልፈልጋት የምቀኝነትን ባህላዊ ትክልነት የምትጠቁም ነገር አለችኝ፡፡ በወቅቱ አንድ መጣጥፍ ልጽፍባት አስቤ እየዘነጋሁትና ንዴቴ እየበረደ ሄዶ ተውኩት፤ ቆይቶ ደግሞ ያናደደኝ አንድ በጣም የምወደው ጋዜጠኛ ወገኔ ወደእስር ስለወረደ መጻፌን በገምቢነት አላየሁትም፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡- በስም የማልጠቅሰው ጋዜጠኛ በኤርምያስ ለገሠ መጽሐፍ ላይ ትችት ሲያቀርብ ኤርምያስ እያገኘ ያለውን ዝናና ታዋቂነት መሠረት ያደረገ በሚመስል የምቀኝነት ሊለቀን ያልቻለ አባዜ የወጣቱን ልጅ ሀገራዊ አስተዋፅዖ – ምናልባትም ሳይታወቀው – አንኳስሶ ሲጽፍበት በውነቱ አፍሬያለሁ፤ እንደዚያ ያለ ለጠላት በር የሚከፍት ነገር በወዳጅ ጋዜጠኛ ብዕር ተጽፎ ሳነብ የተሰማኝ የመከፋት ስሜት ወደር አልነበረውም፡፡ … አንድ ሰው የሚኖረው ዝና የኛን ስብዕናና ታዋቂነት የሚሻማብን እየመሰለን አንዳንዶቻችን የምናሳየው ያልተለመደ የመቅበጥበጥና የመወራጨት ባሕርይ ትዝብት ውስጥ ይጥለናልና ጠንቀቅ ማለቱ ደግ ነው፡፡ የጻፍነውን ነገርም ደግመን ማየቱና ‹ኤዲት› ማድረጉ ብዙዎችን ከማስከፋት ያድነናል፡፡ በዚህ ብቻ ልለፈው፡፡ እሱም በአሁኑ ሰዓት እየተሰቃዬ ስለሆነ ፈጣሪ ከርሱና ከመሰሎቹ ጋር ይሁን፡፡)
ወደጀመርኩት አለፍኩ፡፡ በነዳጅ ስም፣ በአበል ስም፣ በወንበር ስም፣ በቤት አበል፣ በትምህርት አበል፣ በግልጽ በሚታወቅም በማይታወቅም ልዩ ልዩ ጥቅማጥቅም ስም በየቢሮው የሚዘረፈውን ገንዘብ ታሪክ ያስላው ከማለት ውጪ የምናውቀውና የምንለውም የለም፡፡ የሚገርመው ሌላ ነገር በርዕሳችን የተገለጠውን ዶክተር ተብዬ ጨምሮ እነዚህ የወያኔ ባለሥልጣናት አለን የምንለውን ትንሽ ሀብት እንዲህ ሲዘባነኑበት ሕዝቡ ግን መንገድ የለው፣ መብራት የለው፣ ውኃ የለው፣ ስልክ የለው፣ ህክምና የለው፣ ዴሞክራሲ የለው፣ ትምህርት (ቤት) የለው፣ የመኖሪያ ቤት የለው፣ ሠራተኛው ከወር ወር ቀርቶ ለሦስት ቀናት የሚበቃ ደሞዝ እንኳን አይከፈለው…. ኧረ ምን ይሻለናል ገበዝ? በአንድ በኩል የባለሥልጣናቱንና አጃቢዎቻቸው የሆኑ የነጋዴዎችን ኑሮ ስታዩት፣ በሌላ በኩል የአብዛኛውን ሕዝብ የከፋ የድህነት ኑሮና ጉስቁልና እንዲሁም የታህታይና ላዕላይ መዋቅሮች በበቂና ደረጃቸውን በጠበቀ ሁኔታ አለመዘርጋት ስታዩ ወዴት እየሄድን እንደሆነ ግራ በመጋባት ሁሉም ነገር ጨልሞባችሁ ጭንቅላታችሁ ይዞርባችኋል፡፡( የአሁኑ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ብፃይ ቴዎድሮስ አንደሆም አንድ የሐኪሞች ስብሰባ ላይ ለተጠየቀ የጥራት ጥያቄ ምን አለ አሉ – “እኛ የምናሰለጥናችሁ ለዚህ ሀገር ሕዝብ የሚበቃችሁን ያህል መጠነኛ ዕውቀት እንጂ ለዓለም አቀፍ ገበያ የምትሸጡት ከፍ ያለ የሕክምና ዕውቀት አይደለም”፡፡ አሃ! ኢትዮጵያውያንን ለማከም አስፕሪንና ፓናዶል ማዘዝ ብቻ የሚችል ዶክተር ነዋ የሚያስፈልገን! ለዚች ለዚችማ ዳማከሴና አርማጉሳ፣ ሐረግሬሣና ጤናዳም የት ሄደው? ለነገሩ “ራቁቱን ለተወለደ እርቦ ምን አነሰው” ይባል የለም? ጊዜያቸው ነውና ግዴለም እነብፃይ ይጫወቱብን፡፡ “ይደልዎሙ” ይላል ግዕዙ “ይገባቸዋል” ሊል ሲፈልግ፤ እኛም “ይደልዎነ” እንበላ “We deserve!” ለማለት፡፡ አዎ፣ ከችግራችን ለመውጣት የምንጓደድ ከሆነ ችግራችን ድሎታችን እንደሆነ በመቁጠር ተስማምተን ተቀብለናል ማለት ነውና ቢረግጡን ሊከፋን አይገባም፡፡…)
እኛና ፖለቲከኞቻችን እንግዲህ እንዲህ ነን፡፡ ሙስናና ንቅዘት የሌለበት ሀገራዊ ተቋም በፍጹም አይገኝም፡፡ ለአንድ ፕሮጀክት ከሚመደብ በጀት ውስጥ በግምት ከሃምሣና ስልሣ በመቶ በላይ በባለሥልጣናት ይመነተፋል፡፡ በቀሪዋ በጀት ሥራውን እናስጨርሳለን ብለው ሲሞክሩ ደግሞ የሥራው ጥራት ይበላሽና ለምሳሌ ቤት ከሆነ ገና ሥራ ሳይጀምር በባህር ዛፍና በጥድ አጣና የሚደገፍ ወይም ስብርብሩ ወጥቶ ከናካቴው የሚገነደስ ይሆናል፤ መንገድም ከሆነ አንድ ክረምት ሳያልፍ ምናልባትም ርክክቡ ሳይፈጸምና በወጉ ሳይመረቅ ፍርክስክሱ ወጥቶ ወይ አስፋልት ወይ የጠጠር የገጠር መንገድ ሳይሆን የሸማኔ ጉድጓድ እንደሆነ መኪኖችን ሲያረትም ይገኛል – ባለመኪኖችን ለተወደደ የተሸከርካሪ መለዋወጫ ሊያጋፍጥ፡፡ በመጨረሻም…
በመጨረሻም ፈገግ ልታሰኛችሁ ብትችል  አንዲት  ሙስና ቀመስ ቀልድ ልንገራችሁና እንሰነባበት – ዛሬ መቼስ አሰለቸኋችሁ፡፡ ከአንድ ከፍተኛ ተቋም በምህንድስና ሙያ የተመረቁ ሁለት ጓደኛሞች ዘወትር እየተገናኙ ይጨዋወታሉ፡፡ ከሁለቱ አንደኛው በአጭር ጊዜ ውስጥ እያለፈለት ሲሄድ ሌላኛው ግን እግረኛና የሚቀይረውም ልብስ የሌለው ናቸው፡፡ በኑሮው ያለፈለት መሃንዲስ መኪና እንደሸሚዝ ይቀያይራል፤ አለባበሱና አመጋገቡ እንዲሁም ቆነጃጅትን አለዋወጡም ሌልኛ ነው፡፡ ይህን የታዘበው ጓደኛው “ደሞዛችን ተመሳሳይ ነው፤ አንተ ግን በኑሮህ በጣም እየተለወጥክ ነው፤ ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ?” ብሎ ይጠይቀዋል፡፡ እንዴት እንዳለፈልኝ ልንገርህ? ይለውና አዎንታውን ሲያገኝ እንዲህ ያጫውተዋል፡፡ በተውኔት መልክ እናቅርበው መሰለኝ፡፡ ስማቸውንም ወደሌላ ቅኔ ውስጥ ሳንገባ እንዲሁ በዘፈቀዳዊ አሰያየም ያለፈለትን መሃንዲስ አበበ፣ ያላለፈለትን ደግሞ ደበበ እንበላቸው፤

አበበ፤ ያን ድልድይ ታየዋለህ?

ደበበ፤ እዚያ ወዲያ ያለው?

አበበ፤ አዎ፣ እሱ፡፡ እሱን ሳሠራ ለርሱ ከተመደበው በጀት 30 በመቶውን ለራሴ ውስድ፡፡

ደበበ፤ እሺ …
አበበ፤ ያ እዚያ ጋ የተገተረው ሕንፃስ ይታይሃል?

ደበበ፤ በሁለቱ ቪላ ቤቶች መሃል ያለው?

አበበ፤ እህሳ! ከርሱ በጀት ደግሞ 35 በመቶውን ቅርጥፍ!
(ከጥቂት ወራት በኋላ ደቤ ጀግናው ፕራዶ ሚካናውን ይዞ ሱፉን ከነሚያምር ክራቫቱ ገጭ አድርጎ ሲሄድ                            መብራት ያቆመውና አቤን ያገኘዋል፡፡ መብራ ተለቅቆ ዳር ይዘው ከቆሙ በኋላ …)

አበበ፤ እንዴ! በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ምን አግኝተህ እንዲህ ተለወጥክ?

ደበበ፤ ዕድሜ ላንተ፡፡

አበበ፤ እኔ ደግሞ ምን አደረግሁልህ?

ደበበ፤ ይልቁናስ እንዴት እንዳለፈለኝ እንዳሳይህ ና ተከተለኝ፡፡ (ምንም ቤትና መንገድ እንዲሁም ሕንፃና ድልድይ                                      ወደሌለበት  ገላጣ የከተማ ዳርቻ ሥፍራ ይወስደዋል – ደበበ አበበን፡፡)

ደበበ፤ ያ ድልድይ ይታይሃል ?

አበበ፤ የትኛው ድልድይ? ( ምንም ነገር ወደሌለበት ባዶ ጫካ እየተመለከተ)


ደበበ፤ ባይታይህ አይፈረድብህም፤ ብቻ ለሱ ሥራ የተመደበውን በጀት 100 ፐርሰን ልቅሙጭ!

አበበ፤ እሺ…

ደበበ፤ ያ እዚያ ታች ከዛፎቹ መሃል የተገተረው ሕንፃ ይታይሃል?

አበበ፤ የቱ ሕንፃ? (አሁንም ከዛፍና ቁጥቋጦ ውጭ አንዳችም የቤት ዘር ወደሌለበት ደን እየተመለከተ)

ደበበ፤ ባይታይህ አይፈርድብህም፤ ብቻ የርሱንም በጀት መቶ ፐርሰነት ልቅሙጭ!

ማብራሪያ የሚያስፈልግ አይመስለኝም፡፡ ትምህርት ማለት እንዲህ ነው፡፡ ከራሱ የሚበልጥ ተማሪ የማያፈራ አስተማሪ እንዳስተማረ አይቆጠርም ይሉ ነበር ግሪካውያን የጥንት ፈላስማዎች በዘመነ አሪስጣጣሊስ ወአፍላጦን፡፡ ግሩም ሀገር ገምቢ ወጣትና ጎልማሣ በብዛት እያፈራን ነው፡፡ ለሀገርና ለወገን ተቆርቋሪ ቴክኖራት በገፍ እያመረትን መላ የወያኔ ኢትዮጵያን እያጥለቀለቅናት ነው፡፡ ኢትዮጵያ ሆይ ደስ ይበልሽ፤ በጥራትም በብዛትም እጅግ የላቁ የተማሩ ልጆች ሕዝብሽን ወደታላቅ የሥልጣኔ ማማ ሊያደርሱት ቀን ከሌት እየተጉልሽ ናቸው፡፡ አዲዮስ ፓስታ ነበር ያለው ያ ጣሊያን? አዲዮስ ሀገር! አዲዮስ ሕዝብ! አዲዮስ ዕውቀት! አዲዮስ ትምህርት! አዲዮስ ኅሊና!… ራስ ብቻ ጤና፡፡
ምንጭ ዘ-ሐበሻ

Monday, October 20, 2014

በአፋር ክልል በተለያዩ ሞያዎች ሲሰሩ የነበሩ የአማራ ተወላጆች ወደ ክልላቸው እንዲመለሱ ታዘዘ

አኩ ኢብን ከአፋር ለዘ-ሐበሻ እንደዘገበው፦
ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የአማራ ተወላጆች ላለፉት 20 አመታት በአፋር ክልል በተለያዩ ሞያዎች ሲያገለግሉ ቆይተዋል። አሁን ከአፋር ክልል ሾልከው የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከሆነ እነዚህ የአማራ ተወላጆች በአስቸኳይ ወደ ክልላቸው እንዲመለሱ በአማራ ክልላዊ መንግስት ታዘዋል። በጉዳዩ ላይ የአማራ ክልልና የአፋር ክልልን መንግስታት የተስማሙ ሲሆን «ይህ ውሳኔ በህወሓት ሆን ተብሎ በአፋር ክልል ለኢህአዴግ ታማኝ የሆኑ የወያኔ ደጋፊ ትግሬዎች ተወላጆችን ለመተካት የተደረገ ነው» ሲሉም ምንጮቻች ያስረዳሉ።
(አፋር ክልል)
(አፋር ክልል)

ወያኔ በተለይ በሶማሌ ክልልና በአፋር ክልል የሚሰሩ የአማራ ተወላጆችን «ከተቃዋሚዎች ጋር ይተባበራሉ» የሚል ስጋት እንዳለውና ከመጪው ምርጫ በፊት ከአፋር ክልል የአማራ ተወላጆችን አስወግደው በወያኔ ቤተሰብ እንዲተኩ አስቧል። በአፋር ክልል ብዙ በተለያዩ ሞያዎች በመጀመሪያ ዲግሪና በሁለተኛ ዲግሪ የተመረቁ ምሁራን ስራ የማያገኙበት ሁኔታ እያለ ክልላችን የህወሓት መጫወቻ መሆኑን የአፋር ወጣቶችን ሞራል የሚነካ ተግባር ነው ሲሉ አንዳንድ አስተያየት ሰጭዎች ይናገራሉ። በንግድም ቢሆን የአፋር ክልልን የወያኔ ደጋፊ ትግሬዎች ተወላጆች ብቻ እንዲቆጣጠሩ እየተደረገ ሲሆን በአሁን ወቅት ይሄ ሁሉ ሴራ የሚያሴሩት በተንዳሆ ሱኳር ፋብረካ እያሰሩ የሚገኙት የቀድሞው የህወሓት ታጋይ አቶ ሚካኤል ናቸው።
አቶ ሚካኤል በየእሁድ በአፋር ክልል ለሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች በሎግያ ከተማ ስብሰባ የሚያደርጉ መሆኑንና የስብሰባ ቦታቸውም ናዝሬት ሆቴል ቁጥር 1 የሚባለው ሲሆን የናዝሬት ሆቴል ባለቤት በንግድ የአፋር ክልልን የወያኔ ደጋፊ ትግሬዎች ብቻ እንቆጣጠሩ የሚለፉ የትግራይ ሀብታም ናቸው። አሁን ለአቶ ሚካኤል ይህ የመንግስት ሰራተኞችን የማባረር ሴራ ከተሳካላቸው የአፋር ክልል መሉ በሙሉ በወያነ ቤተሰቦች ይያዛል ማለት ነው፣ የአፋር ህዝብም ቢሆን ከከተማ እያስወጡ ወደ ገጠር እየመለሷቸው ነው። ይህ ደግሞ ለወደፊት ከጀቡቲ ታኮሪ ወደ መቀሌ ለሚሰራው የባቡር ሀዲድ ዝርጋታና ወደ ፊትም የትግራይ ክልል የኢንዱስትሪ ዞን የማድረግ አላማ ስላላቸው የአፋር ክልልን በቀላሉ ለመቆጣጠር ነው።
ምንጭ ዘ-ሐበሻ

Sunday, October 19, 2014

ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ፡ በአሜሪካ ሲያትል ዋሽንግተን ዉስጥ የተሳካ ህዝባዊ ስብሰባ አካሄደ

october 18.2014
የግንቦት 7 ንቅናቄ ቅዳሜ ኦክቶበር 11 ቀን 2014 አ.ም በአሜሪካ ሲያትል ከተማ ደማቅ ህዝባዊ ስብሰባ ማካሄዱን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በዚህ ህዝባዊ ስብሰባ ላይ በሲያትልና አጎራባች ከተሞች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በነቂስ በመውጣት የታደሙበት እንደነበር ያደረሰን ዘጋቢያችን አገር ወዳድ ኢትዮጵያኑ በስብሰባው ላይ በክብር እንግድነት ከተገኙት የንቅናቄው ሊቀመንበር ከዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ጋር ሰፊ አገራዊ ውይይት ማካሄዳቸውን ለማወቅ ተችሏል። በሲያትል የተካሄደው ይህ ህዝባዊ ስብሰባ ኢትዮጵያውያን በዘር በሃይማኖት በጎሳ ሳይለያዩ በአንድነት በመሰባሰብ በአገራቸው ጉዳይ ላይ በሰፊው የመከሩበት፤ ኢትዮጵያዊነት እጅግ አምሮና አሸብርቆ የታየበት እንደነበርም ተመልክቷል።
በህዝባዊ ስብሰባው ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት ዶ/ር ብርሀኑ ለስብሰባው ታዳሚዎች ባደረጉት ንግግር “የምንገኝበት ወቅት ጊዜያችንን እንደ ከዚህ ቀደሙ መቋጫ በሌለው ውይይትና ጭቅጭቅ የምናጠፋበት ሳይሆን፤ ስለ ነፃነቴ እታገላለሁ የሚል ወደ ተግባራዊው ትግል የሚቀላቀልበት፤ በአንድም ሆነ በሌላ ምክንያት ትግሉን መቀላቀል የፈራ ዝም ሊል የሚገባበት ወቅት መሆኑን በአንክሮ በማስገንዘብ በተጨማሪ የነፃነት ትግሉን በከፍተኛ ደረጃ እየጎዳ የሚገኘውን የእርስ በርስ ጥልና ሽኩቻ በአስቸኳይ ቆሞ ሁላችንም በአንድነት በመነሳት በዋናው አላማችን ላይ ማለትም የጉጅሌው ወያኔን አገዛዝ ለማስወገድ መዝመት ይገባናል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል። በተለይ የነፃነት ትግሉ ለመቀላቀል እስካሁን እድሉን ላላገኙና በትግሉ ላይ የራሳቸው የታሪክ አሻራ ማሳረፍ ለሚሹ ወገኖችም የተቀላቀሉን ጥር ማቅረባቸውን ለማወቅ ተችሏል። የቀረበላቸውን ጥሪ በመጠቀም ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ኢትዮጵያውያን በአባልነት እንዲሁም በደጋፊነት በመመዝገብ ግንቦት 7 ትን መቀላቀል መቻላቸው ታውቋል። ትግሉ አሁን ላይ የደረሰበትን ደረጃ አስመልክቶ ለታዳሚዎች በስፋት ያብራሩት ዶ/ር ብርሃኑ ተሰብሳቢዎቹ እንዲሁም መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ግንቦት 7 ለነደፋቸው የትግል ስልቶች ማለትም ለሕዝባዊ ተቃውሞ፣ ሕዝባዊ እምቢተኝነት እና ሕዝባዊ አመጽ ዛሬ ነገ ሳይባል ምላሽ መስጠት መጀመር እንዳለበት ማሳሰብያ ማቅረቡ ታውቋል። በተለይ እነዚህን ስልቶች በአገር ውስጥ እና ከአገር ውጭ በተቀናጀ ሁኔታ መተገበር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ቆም ብሎ ሊያስብና ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ሊገባ የሚገባበት ሰአት አሁን ነው ያሉት ዶ/ር ብርሃኑ ይህንን በተሳካ ሁኔታ መተግበር ስንችል ጉጅሌዎቹን ከአገራችንንና ከህዝባችን ጫንቃ ማውረድ እንችላለን ሲሉ ተናግረዋል።
ዶ/ር ብርሃኑ ከተሰብሳቢው ለቀረበላቸው በርካታ ጥያቄዎችም አጥጋቢ ምላሽ ሰጥተዋል። በተለይ በኤርትራ በኩል እየተደረገ ያለውን ትግል አስመልክቶ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሰፊ ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት በተሰብሳቢዎች ዘንድ የነበረውን ብዥታ ማጥራት መቻላቸውንና ተሰብሳቢዎቹ እየተደረገ ላለው ትግል በጭብጨባ ድጋፍ መስጠታቸውን ከስፍረሰው የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
በመጨረሻም በስብሰባው ላይ በጠላት እጅ ወድቀው የሚገኙት የንቅናቄያችን ዋና ፀሐፊ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ሥራዎች በስፋት መወሳታቸውን ለማውቅ የተቻለ ሲሆን ኢትዮጵያውያኑ የአቶ አንዳርጋቸው ስራዎች ሲቀርቡ አብዛኞቹ በሐዘን እና በቁጭት ሲያነቡ እንደነበርም የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በስብሰባው መገባደጃ ላይ ለጨረታ የቀረበው የነፃነት አርበኛው የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ፎቶግራፍም በከፍተኛ ገንዘብ መሸጡ ታውቋል። ኢትዮጵያውያኑ በጋራ እጅ ለእጅ በመያያዝ እየተደረገ ያለውን የነፃነት ትግል ከዳር ለማድረስ ከመቼውም ጊዜ በላይ በቁርጠኝነት መነሳታቸውን በቃለ መሐላ ካረጋገጡ በኋላ ስብሰባው መፈጸሙም ታውቋል።
source www.ginbot7.org

Wednesday, October 15, 2014

ማኅበረ ቅዱሳን ተካሔደብኝ ባለው የስም ማጥፋት ዘመቻ ቅ/ሲኖዶስ ውሳኔ እንዲሰጠው ጠየቀ

·ኑፋቄአቸውና ሕገ ወጥ ጥቅማቸው እንዳይጋለጥ የሚሰጉ አካላት ያስተባበሩት ነው
· የብፁዓን አባቶች ስም እየተጠቀሰ የወረደው የስድብ ናዳ በእጅጉ አሳዝኖናል
· በፈቃዳችን በነፃ የምንፈጽመውን የአገልግሎት መብታችንን የሚፃረር ነው
· ግለሰቦቹ በስም ማጥፋት ዘመቻቸው ከቀጠሉ ማኅበሩ በሕግ ይጠይቃቸዋል
(በሰንደቅ ጋዜጣ ሪፖርተር)
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥር አገልግሎቱን የሚፈጽመው ማኅበረ ቅዱሳን፣ ፓትርያርኩ በተገኙባቸው ስብሰባዎችና ስለ ስብሰባዎቹ በሚዘግቡ ሚዲያዎች ላይ የማኅበሩ ስም እየተጠቀሰ የሚካሔድበትን የስም ማጥፋት ዘመቻ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ እንዲሰጥበት መጠየቁ ተገለጸ፡፡
Mhbere Kidusan
ማኅበሩ ጥያቄውን ያቀረበው ‹‹በሚዲያና በተለያዩ ስብሰባዎች የተከፈተው የስም ማጥፋት ዘመቻ አግባብ አለመኾኑን ስለመጠየቅ›› በሚል ርእስ ጥቅምት 1 ቀን 2007 ዓ.ም. በአድራሻ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በግልባጭ ደግሞ ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት፣ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ለኾኑት ለኹሉም ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ባሰራጨው ደብዳቤ ነው፡፡
ላለፉት 23 ዓመታት በቅዱስ ሲኖዶስ በወጣለትና በተፈቀደለት ሕግና ደንብ መሠረት በቤተ ክርስቲያን ሥር ተዋቅሮ ኹለንተናዊ አገልግሎቷን ለመደገፍና ለማጠናከር የድርሻውን እየተወጣ እንደሚገኝ የገለጸው ማኅበሩ÷ በማያውቀው፣ ጥፋትም ካለ ተጠርቶ ባልተጠየቀበትና መልስ ባልሰጠበት ኹኔታ ፓትርያርኩ ባሉባቸውና በተለያዩ ጊዜያት በተጠሩ ስብሰባዎች የተፈጸምበት የስም ማጥፋት ዘመቻ መደጋገም ደብዳቤውን ለመጻፍ እንዳስገደደው ገልጧል፡፡
ማኅበሩ በደብዳቤው፣ በየስብሰባዎቹ የሕዝብ መገናኛ አውታሮች እየተጠሩ በማኅበሩ አገልግሎት ምክንያት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የኾኑ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በስም እየተጠቀሱ ተራ የስድብ ናዳ እንደወረደባቸው ገልጦ፣ ‹‹የስም ማጥፋት ዘመቻው እኛንም ኾነ እውነተኛ የቤተ ክርስቲያን አባቶችንና ምእመናንን በእጅጉ አሳዝኖናል፤›› ብሏል፡፡ ስብሰባው የተቀረፀበትንና ‹‹አስነዋሪ›› ሲል የገለጸውን ቪዲዮ፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሕጋዊ ድረ ገጽ ላይ በኢንተርኔት መለቀቁ፣ የቤተ ክርስቲያን አካላት ነን ከሚሉ ሰዎች የማይጠበቅና ‹‹ቤተ ክርስቲያንን ለጠላት መሳለቂያ ለማድረግ›› በጥፋት መልእክተኞች የተቀናበረ እንደኾነ አመልክቷል፡፡
ትውልዱ በእምነትና በዕውቀት ታንፆ በሞያው፣ በገንዘቡና በጉልበቱ ቤተ ክርስቲያኑን እንዲያገልግልና ሐዋርያዊ ተልእኮዋ እንዲፋጠን ማኅበሩ ያበረከተው አገልግሎትና ስኬት አኹን ላለበት ደረጃ የደረሰው በብፁዓን አባቶችና በሊቃውንት ምክርና ጸሎት ተደግፎ እንደኾነ ደብዳቤው አስታውሷል፡፡ የቤተ ክርስቲያን እምነቷና ሥርዓቷ ሳይበረዝና ሳይከለስ ተጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ ጥብቅና በመቆሙ፣ ከዚኽም አንጻር ‹‹አፅራረ ቤተ ክርስቲያን›› ናቸው ካላቸው አካላት የሚሰነዘሩ ‹‹የተሐድሶ ሽምቅ ደባዎች››ን ለቅ/ሲኖዶስ በማስረጃ አስደግፎ በማጋለጡና ማስረጃው ተጠንቶና ተረጋግጦ በመወገዛቸው ምክንያት በአገልግሎቱ ላይ ግልጽና ስውር ፈተናዎች እየተፈጠሩ መቆየታቸውን አስረድቷል፡፡
ማኅበሩ ‹‹አስነዋሪ›› ያለውና በተጠቀሰው መምሪያ ሕጋዊ ድረ ገጽ ላይ የተለቀቀው ቪዲዮ መስከረም 27 ቀን 2007 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አዳራሽ ‹‹የቤተ ክርስቲያንን አስተዳደራዊ አስተሳሰብ ማበልጸግ›› በሚል ርእስ የተካሔደውን የግማሽ ቀን ስብሰባ የሚያሳይ መኾኑ ታውቋል፡፡ ፓትርያርኩ አቡነ ማትያስ በጽሑፍ የተደገፈ ገለጻ የሰጡበትና በልዩ ጸሐፊያቸው የተመራው ይኸው ስብሰባ፣ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችና ጸሐፊዎች የተካፈሉበት ሲኾን የማኅበረ ቅዱሳንን ስም በመጥቀስ ማኅበሩ ‹‹ለአባቶች አይታዘዝም፤ መዋቅር ጠብቆ አይሠራም፤ ሒሳቡን አያስመረምርም፤ ዐሥራት ይሰበስባል፤ የፖሊቲካ ዓላማ አለው፤ አክራሪና አሸባሪ ነው…ወዘተ›› በሚሉ ሐሳቦች ዙሪያ ያተኮሩ የስም ማጥፋት ዘመቻ እንደተፈጸመበት ደብዳቤው ዘርዝሯል፡፡
mahibere-kidusan
ማኅበሩ በስብሰባው ላይ ‹‹ስም ማጥፋት›› የተባለውን ድርጊት የፈጸሙበት ግለሰቦች ማንነት እንደየ ምክንያታቸው ሊለያይ እንደሚችል በተለያዩ ጊዜያት ያካሔዳቸውን ጥናቶች መነሻ በማድረግ አመልክቷል፡፡ እኒኽም ራሳቸውን ደብቀው የምንፍቅና ዓላማን ያነገቡና ማኅበሩ ለዓላማቸው መሳካት ዕንቅፋት እንደኾነባቸው የሚያምኑ፤ የቤተ ክርስቲያንን ንብረት በመጠቀም የግል ሀብት የሚያካብቱና ማኅበሩ ሊያጋልጠን አልያም ምቹ ኹኔታ ፈጥሮልን የኖረውን የሒሳብና ሌሎች አሠራሮች ክፍተት ሊደፍንብን ይችላል በሚል የሚፈሩ፤ የቤተ ክርስቲያንን መዋቅር በተማረ ኃይል በመሙላት ቦታ ያሳጣናል በሚል የሚሰጉ፤ ማኅበሩን በመቃወም ማኅበሩን ከሚጠሉ አካላት ጥቅም ለማግኘት ወይም በተሳሳተ መረጃ የማኅበሩን አገልግሎት ጥቅም ባለመረዳት የሚቃወሙ እንደኾኑ ነው ያስረዳው፡፡
የማኅበሩ አገልግሎት ችግር ይኖርበታል ተብሎ ቢታሰብ እንኳ ትክክለኛው አካሔድ ማኅበሩ በጉዳዩ ተጠርቶ፣ ተጠይቆና ችግሩ ተረጋግጦ እንዲያርም ማድረግ ነው ያለው ማኅበረ ቅዱሳን፣ የስብሰባው አካሔድ ‹‹ድብቅ ዓላማ አንግቦ የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ለማደናቀፍ የተቀናጀ ሤራ ነው›› የሚያሰኝ ጥያቄ ሊያሥነሳ እንደሚችል ገልጧል፡፡ ‹‹ቅዱስነትዎም ይህ ኹሉ ሲኾን የማኅበሩን አመራር አካላት አንድም ቀን ጠርተው አለመጠየቅዎ እንደ ልጅነታችን አሳዝኖናል›› በማለትም ከስብሰባው ቀደም ሲል ከፓትርያርኩ ጋራ የውይይት መርሐ ግብር እንዲያዝለት በተደጋጋሚ ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት ባላገኘበት ኹኔታ መሠረት በሌላቸውና ከእውነትነት በራቁ የሐሰት ክሦች ‹‹የስም ማጥፋት ዘመቻ›› እንዲከፈትበት በመደረጉ ቅር መሰኘቱን አስታውቋል፡፡
በደብዳቤው እንደተብራራው፣ ማኅበረ ቅዱሳን ለቤተ ክርስቲያኒቱን ኹለንተናዊ አገልግሎት የሚያበረክተው፣ ከዋናው ማእከል አንሥቶ በሀገር ውስጥና በውጭ አህጉረ ስብከት በተዘረጋው መዋቅሩ ሲኾን ይኸውም ከየሀገረ ስብከቱ ሊቃነ ጳጳሳት ጋራ በመመካከርና መመሪያ በመቀበል የሚከናወን ነው፡፡ በየጊዜው ዕቅዱን በማሳወቅ በየስድስት ወሩ የዕቅድ አፈጻጸምና የሒሳብ ሪፖርት ለጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ያቀርባል፡፡ ሒሳቡን በየጊዜው በውስጥ ኦዲተር የሚያስመረምር ሲኾን በየዓመቱ ደግሞ ዓለም አቀፍ ዕውቅና ባለው ሕጋዊ የውጭ ኦዲተር አስመርምሮ ለሚመለከታቸው የቤተ ክህነቱ አካላት እያቀረበ ይገኛል፡፡ በዚኽም ከየትኛውም አካል ጥያቄ፣ ነቀፌታ ይኹን እርማት ቀርቦበት ባያውቅም ባቀረባቸው ሪፖርቶች የሚሰጠውን መመሪያ ተከትሎ አገልግሎቱን እያከናወነ ኻያ ሦስተኛ ዓመቱን ማስቆጠሩን በደብዳቤው ተመልክቷል፡፡
ማኅበሩ ‹‹እንኳን የራሱን የሒሳብ አያያዝ የቤተ ክርስቲያንዋ የሒሳብ አሠራር በሙሉ ዘመናዊና ለኦዲት የሚመች እንዲኾን የሚያግዝ ነው፤›› ያለው ደብዳቤው፣ ማኅበረ ቅዱሳን ዘመናዊና የኹለትዮሽ የሒሳብ አያያዝ ሥርዐት (double entry accounting system) የሚከተል በመኾኑ የቤተ ክህነቱን የነጠላ የሒሳብ አያያዝ ሥርዐት ለመከተል እንደተቸገረ አልሸሸገም፡፡ ይኹንና የቤተ ክህነቱ የቁጥጥር አገልግሎት ባስፈለገው ጊዜ ማኅበሩ በውስጥ ይኹን በውጭ ኦዲተር ያስመረመረውን ሒሳብ ማየት፣ በአካልም ተገኝቶ ማረጋገጥ እንደሚችል ለጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ማስታወቁን አውስቷል፡፡ ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን ወዶ ፈቅዶ አባቶችን ለማገልገል፣ የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት በፈቃደኝነት ለመደገፍ የተቋቋመ በመኾኑ የመታዘዝ ይኹን በሞያ የተደገፍ የሒሳብ አያያዝ የመተግበር ችግር የለበትም፤›› በማለት ለመዋቅሩ ያለውን ታማኝነት አጽንቷል፡፡
ማኅበሩ ‹‹ከምእመናን የዐሥራት በኵራት ገቢ ይሰበስባል›› በሚል በስብሰባው ላይ የተሰነዘረበትን ‹‹ስም ማጥፋት›› ፍጹም ሐሰት በማለት አጣጥሎታል፡፡ በሰጠው ምላሽም ማኅበረ ቅዱሳን አገልግሎቱን የሚያከናውነው ከአባላቱ ገቢ በሚሰበስበው የኹለት በመቶ ወርኃዊ አስተዋፅኦ እንደኾነ፣ ለቅዱሳት መካናትና ለስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ ፕሮግራሞች ደግሞ ፕሮጀክቶችን በመቅረፅ ከገባሬ ሠናይ ምእመናን ድጋፍ እንደሚያፈላልግ ገልጧል፡፡ አገልግሎቱ የበጎ ፈቃድና የትሩፋት መኾኑን በተደጋጋሚ የገለጸው ማኅበሩ ከአባላቱ የሚሰበሰበው የኹለት በመቶ ወርኃዊ አስተዋፅኦ፣ እያንዳንዳቸው ለየሰበካቸው የሚጠበቅባቸውን ዐሥራት ወይም የሰበካ ክፍያ ከፈጸሙ በኋላ የሚያበረክቱት እንደኾነ አረጋግጧል፡፡
ማኅበሩ ረብ የለሽ ሲል ውድቅ ካደረጋቸው የአንዳንድ ተሰብሳቢዎች ክሦች ውስጥ ግንባታውን የተጠናቀቀውንና የሚገለገልበትን የጽ/ቤት ሕንፃ የሚመለከት ይገኝበታል፡፡ ሕንፃው ያረፈበት ቦታ የተገዛው የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የወቅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ በሰጡት ውክልና መኾኑን ማኅበሩ በደብዳቤው ገልጦ፣ አባላቱ የወር ደመወዛቸውን በተደጋጋሚ በማዋጣት የገነቡትና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማኅበረ ቅዱሳን ስም በሕግ ተመዝግቦ የሚገኘውንና በማኅበሩ የሒሳብ ሪፖርትም በቋሚ ንብረትነት ተይዞ በየወቅቱ የሚገለጸውን ሕንፃ አመራሩ ይኹን አባላቱ የመጠበቅና የመገልገል እንጂ ለሦስተኛ ወገን አሳልፎ የመስጠት ይኹን የመሸጥ ፍላጎት እንደሌላቸው አስታውቋል፡፡
በቅዱስ ሲኖዶስ በጸደቀውና እየተመራበት በሚገኘው መተዳደርያ ደንቡ መሠረት ማኅበሩ በማንኛውም የፖሊቲካ አመለካከት ጣልቃ እንደማይገባና አገልግሎቱ ሰማያዊ እንጂ ምድራዊ እንዳልኾነ ያረጋገጠው ማኅበሩ፣ የፖሊቲካ ዓላማ እንዳለው ለተሰነዘረው ውንጀላ መረጃው ቀርቦ በሚመለከተው አካል ሊታይና ሊጣራ እየቻለ የማይመለከታቸው አካላት ከሜዳ ተነሥተው ስም ለማጥፋት ሊጠቀሙበት እንደማይገባ አሳስቧል፡፡ ማኅበሩ ‹‹አክራሪ ነው፤ አሸባሪ ነው›› ማለትም ‹‹ውንጀላን ከማዳመቅ›› ያላለፈ ፋይዳ የሌለው መሠረተ ቢስ ክሥ ነው ብሏል፡፡
ማንም ግለሰብ ይኹን ኅብረተሰብ የፈለገውን እምነት ሊከተል እንደሚችል እምነቱ እንዳለውና የማንንም ሰብአዊና ሕገ መንግሥታዊ መብት እንደማይነካ በአጽንዖት የገለጸው ማኅበሩ፣ ማንም የራሱን እምነት ከማራመድ አልፎ በሌላው እምነት ጣልቃ መግባት ስለሌለበት፣ ‹‹በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዐት ጣልቃ ገብተው የሚያውኩትን የተሐድሶ መናፍቃን የመከላከልና ቤተ ክርስቲያንን የመጠበቅ ተልእኮዬን አጠናክሬ እቀጥላለኹ፤›› ብሏል፤ ‹‹እናቱን አውሬ ሲበላት ቆሞ የሚሥቅ ልጅ የለም›› ሲልም አቋሙን አስረግጧል፡፡
ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በተጣለባቸው ታላቅ የቤተ ክርስቲያን ሓላፊነትና አባትነት በማኅበሩ ላይ የሚካሔደውን የስም ማጥፋት ዘመቻውን በአጽንዖትና በተረጋጋ መንፈስ እንዲመለከቱ ማኅበረ ቅዱሳን በአቤቱታው ተማፅኗል፡፡ ግለሰቦቹን በሕግ ለመጠየቅ ሊገደድ እንደሚችል ያስታወቀው ማኅበሩ ‹‹አስነዋሪና የቤተ ክርስቲያን ነን ከሚሉ አካላት የማይጠበቅ ነው›› ያለው ድርጊት ‹‹በቤተ ክርስቲያን ልጅነታችን በፈቃዳችን ገንዘባችንን፣ ጉልበታችንንና ጊዜአችንን አስተባብረን የምናደርገውን ነፃና የፈቃድ አገልግሎት መብታችንን የሚፃረር ነው፤›› ሲል አስገንዝቧል፡፡ ኹኔታው በተመሳሳይ መልኩ ከቀጠለ ቤተ ክርስቲያንን እርስ በርሷ የማትናበብ፣ ማእከላዊ አሠራር የሌላት የሚያስመስልና ለአገልግሎቷ ዕንቅፋት የሚፈጥር በመኾኑ ቅዱስ ሲኖዶስ ጉዳዪን በጥንቃቄ መርምሮና አጣርቶ አስቸኳይ ውሳኔ እንዲሰጥበት ጠይቋል፡፡
ምንጭ ዘ-ሐበሻ