Thursday, September 5, 2013

በደቡብ ኮርያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በዛሬው እለት ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ በ ሰውል ኣካሄዱ።

ሰልፈኞቹ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የማያባራ የሰብዓዊ መብት ጥሰት በመቃወም በደቡብ ኮርያ ፕሬዚደንት ጽ/ ቤት ፊት ለፊት ፕሬስ ኮንፈረንስ በማድረግ የኮርያ መንግስት በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ጫና እንዲፈጥር ተማጽነዋል። ለ ደቡብ ኮርያ ፕሬዚደንት ፓርክ  ግን-ሄ ደብዳቤም ኣስገብተዋል።
ሰልፈኞቹ  ለደቡብ ኮርያ  UNHCR  ተወካይና የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ደብዳቤዎችን ያስገቡ ሲሆን በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ጫና እንዲፈጥሩ ተማጽነዋል።
ከሰልፈኞቹ መሃል ኣብዛኛዎቹ የዘማች ልጆች ሲሆኑ ባለፈው ጊዜ ለስልጠና መጥተው ገዢውን መንግስት በመቃወም ጥገኝነት መጠየቃቸው ኣይዘነጋም።
Short URL: http://www.zehabesha.com/amharic/?p=7077

No comments:

Post a Comment