Wednesday, September 11, 2013

የዓመቱ የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች ምርጥ ሰው – የሕይወት ገድል


በ1997 ዓ.ም ኢዴፓ /ቅንጅትን ወክሎ በተወለደበት ክ/ሀገር ፋርጣ ወረዳ ለተወካዮች ም/ቤት ተወዳድሯል:፡ በምርጫው ውጤት ቅንጅት ቢያሽንፍም ከፍተኛ አመራሩና አባላቱ በተለያዩ እስርቤቶች ሲታሰሩ እሱም አብሮ ቃሊቲ እስር ቤት ለሁለት ዓመታት ቆይቷል፡: በሁለት ዓመት ቆይታውም የብረት ግድግዳ በመሆን ፅናቱን አስመስክሯል:፡ ከእስር ቢለቀቅም ከፖለቲካው ወደ ኋላ አላፈገፈገም፡ አንድነት ፓርቲን በመቀላቀል የብሔራዊ ም/ቤትና የሥራ አሥፈፃሚ አባል በመሆን ለዋና ጸሐፊነት ተመርጦ ላንድ ዓመት በቆራጥነት አገልግሏል፡: ብቃቱን በማስመስከሩም በም/ሊቀመንበርነት የሕዝብ ግንኙነት ሐላፊ ሆኖ ተመርጦ በማገልገል ላይ እንዳለ፤ በተጨማሪም የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር እንዲሆን ብዙዎች እየቀሰቀሱ ባለበት ወቅት ነው ርምጃው ያልጣመው ገዥው ፓርቲ ከግንቦት 7 ጋር በማገናኘት የሽብርተኝነት ጥላሸት በመቀባት መስከረም 3 ቀን10 ሰዓት ላይ ከመንገድ የታጠቁ ኃይሎች ከመኪና አስወርደው ይዘውት በመሄድ አሁን እድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበት በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ይገኛል።



አንዱዓለም አራጌ ማነው? ለሚለው ጥያቄ ለአንባቢያንና ለውጥ ለማምጣት ለሚታገልለት የኢትዮጵያ ሕዝብ ከሕይወት ታሪኩ ትንሽ ጨለፍ አድርገን ለመፈንጠቅ እንሞክራለን።
የትውልድ አካባቢና የልጅነት ጊዜ አቶ አንዱዓለም አራጌ በጎንደር ክ/ሀገር በደብረታቦር አውራጃ በፋርጣ ወረዳ ጉና ተራራ ሥር ወይንም ግርጌ ክምር ድንጋይ ከተባለ ቦታ በ65 ዓ.ም ጥቅምት25 ቀን ተወለደ፡፡ የኢትዮጵያ አብዮት ሊፈነዳ ሁለት ዓመት ሲቀረው በምጥ ዋዜማ ማለት ነው፡፡ “ሰው አካባቢውን ይመስላል” እንደሚባለው አንዱዓለም አራጌ በክ/ሀገሩ ከራስ ዳሽን ተራራ ቀጥሎ በሁለተኛደረጃነት ከሚጠቀሰው ጉና ተራራ ስር በመወለዱ ለኢሕአዴግ እንደ ጉና ተራራ ኮርቶና ከብዶ ታይቶታል፡፡ እናም አስሮ በሽብርተኝነት በመወንጀል አሞቱን ያፈሰሰ መስሎታል፡፡ አንዱዓለም አራጌ ግን እንዲህ በቀላሉ የሚፈታ አይደለም፡፡ ለምንም ነገር የማይበገር፣ ችግር የማይፈታው፣ ለቆመለት ዓላማ ወደ ኋላ የማይል፣ ከሁሉም በላይ ቅጥፈትንና እብለትን አጥብቆ ይጠየፋል፡፡ባጭሩ ትክለ ሰውነቱ ወይንም nስብእናው በቁም ነገር የታነፀ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ለቆመለት ዓላማና ላመነበት ነገር ያላንዳች ይሉኝታና ፍርሃት ሽንጡን ገትሮ ይከራከራል፡፡
በዚህ አቋሙና ፅናቱም ነው ገና በለጋ እድሜው ሩጦ ሳይጠግብ፣ ሠርቶ ሣይደክም በተደጋጋሚ የእሥር ሰለባ ለመሆን የበቃው፡፡
አ ን ዱ ዓ ለ ም አራጌ አሥራ አንድ ዓመት እስከሚሞላው ድረስ ክምር ድንጋይ ከወላጆቹ ጋር ቆይቷል፡፡ አባቱ የቤተ ክህነት ሰው በመሆናቸው ልጃቸው በፅኑ የግብረገብ ሥነ ምግባርኮትኩተውና ገርተው ከማሣደጋቸውም በላይ የቤተክህነት ትምህርት እንዲማርላቸው በመሻት ካንድ ከታወቁ መርጌታ ልከውት በተመላላሽነት እየተማረ እንዳለ አዲስ አበባ የሚኖሩ አያቱ ክምርድንጋይ ይሄዳሉ፡፡ እሳቸውም የቤተክህነት ሰው ነበሩና ንቃቱን፣ ጨዋነቱን፣ ትህትናውንና አርቆ አስተዋይነቱን በዚያች አጭር ጊዜ ቆይታቸውአስተዋሉና “ይኸ ልጅ ዘመናዊ ትምህርት መማርአለበት” ብለው ወደ አዲስ አበባ ይዘውትይመጣሉ፡፡ሕይወት በአዲስ አበባአንዱዓለም አራጌ ካያቱ ጋር አዲስ አበባ ከመጣ በኋላ መስከረም መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በመግባት ከ1-8ኛክፍል ድረስ ሁለት ጊዜ ደብል ወይንም አጥፎ በማለፍ በ6 ዓመት ውስጥ ስምንተኛ ክፍልን አጠናቀቀ፡፡

ዘጠንኛና አሥርኛ ክፍልን የተማረው ኮከበ ጽባህ ሲሆን የደረጃ ተማሪ ስለነበር 11ኛና 12ኛ ክፍልን የተማረውና ከፍተኛ ውጤት አምጥቶ ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለመግባት የበቃው በሳንጅዮሴፍ ት/ቤት በመማር ነበር፡፡ አንዱዓለም አራጌ በከፍተኛ ውጤት አ.አ.ዩ በመግባት በታሪክ የመጀመሪያ ዲግሪውን አግኝቷል፡፡በዩኒቨርስቲ ቆይታውም በተለያዩ ክበባት በመግባት በኃላፊነትም ሆነ በአባልነት ካንድ ንቁ ተማሪየሚጠበቅበትን ግዴታ ተወጥቷል፡፡ በዩኒቨርስቲው ውስጥ በአራት ዓመት ቆይታው የት/ቤት ጓደኞቹ በሚያደርጋቸው ክርክሮችና በአቋሙ ፅናት እጅግ አድርገው ያደንቁት እንደነበር ዛሬ በቅርብየሚያውቁት ይናገራሉ፡፡
አንዱዓለም አራጌ ከሚታወቅባቸው ቁም ነገሮች መሀከል ባገራችን ገና የሰላማዊ ትግል ፅንስ ሐሳብ በቅጡ ባልታወቀበት ወቅት እሱ ሰለሰላማዊ ትግል ይሰብክ ነበር፡፡ ይህንንም ሲያደርግ የአንጋፋሰላማዊ ታጋዮችን አርማ በማንሳትና መርሃቸውን እንደ ምርኩዝ በመጠቀም ነው፡፡ ማርቲን ኪንግ፣ ማንዴላ፣ ማኅተመ ጋንዲን ታሪካቸውን በማጥናትና የሄዱበትን መንገድ በመከተል በዩኒቨርስቲቆይታው መርሃቸውን መርሁ በማድረግ የትግል ብቃቱን እንዳዳበረ በቅርብ የሚያውቁት በአጽንኦት ይናገራሉ፡፡ የአንዱዓለም አራጌ ልዩ ባህሪውና ተሰጥኦው ወይንም ትክለ ሰውነት ከላይ ለመጥቀስእንደሞከርነው በሰላማዊ ትግል ገና ከወጣትነቱ ዕድሜው ጀምሮ ቆርቦ እያለ ገዥው ፓርቲ “ሽብር አራማጅ” ብሎ በመወንጀል ጥላሸት ሲቀባው ማየትና መስማት ያለንበትን ዘመንና ሥርዓት ምንያህል አስጨናቂና አስከፊ እንደሆነ መገመቱ ከባድ አይሆንም፡፡ እያንዳንዳችንም ውለን ስለመግባታችን ዋስትና የለንም፡፡ ሁላችንም የሱ እጣ እንደሚጠብቀንና ጥላሸት እንደምንቀባም በርግጠኝነትመናገር እንችላለን፡፡
የሥራ ዓለምአንዱዓለም አራጌ ከአ.አ.ዩ ትምህርቱን ጨርሶ ከወጣ በኋላ በተለያዩ ድርጅቶች ውስጥ እየተቀጠረ ሠርቷል፡፡ ከነዚህ ውስጥ የዓለም ባንክና የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ባለሙያዎች መኅበርበግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
የፖለቲካ ሕይወቱ
አቶ አንዱዓለም አራጌ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቆይታው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የፖለቲካ ሀሁን ከመቁጠር ጀምሮ በማዳበር ብስለቱን ያስመስከረ ቢሆንም በድርጅትውስጥ ታቅፎ መታገል የጀመረው ግን በ1992 ዓ.ም የኢዴፓ መሥራች አባል በመሆን ነበር፡፡ በኢዴፓ ውስጥ በቆየባቸው ዓመታትም ከቋሚ ኮሚቴ አባልነት ጀምሮ ደረጃ በደረጃ አድጎ ም/ዋናጸሐፊ በመሆን በከፍተኛ ኃላፊነት ሠርቷል፡፡ በመሆኑም በ1997 ዓ.ም ኢዴፓ /ቅንጅትን ወክሎ በተወለደበት ክ/ሀገር ፋርጣ ወረዳለተወካዮች ም/ቤት ተወዳድሯል። በምርጫው ውጤት ቅንጅት ቢያሽንፍም ከፍተኛ አመራሩና አባላቱ በተለያዩ እስር ቤቶች ሲታሰሩ እሱም አብሮ ቃልቲ እስር ቤት ለሁለት ዓመታት ቆይቷል፡፡ በሁለት ዓመት ቆይታውም የብረትግድግዳ በመሆን ፅናቱን አስመስክሯል፡፡ ከእስር ቢለቀቅም ከፖለቲካው ወደ ኋላ አላፈገፈገም፡፡ አንድነት ፓርቲን በመቀላቀል የብሔራዊ ም/ቤትና የሥራ አሥፈፃሚ አባል በመሆን ለዋና ጸሐፊነት ተመርጦ ላንድ ዓመት በቆራጥነት አገልግሏል፡፡
ብቃቱን በማስመስከሩም በም/ሊቀመንበርነት የሕዝብ ግንኙነት ሐላፊ ሆኖ ተመርጦ በማገልገል ላይ እንዳለ ነው ርምጃው ያልጣመው ገዥው ፓርቲ ከግንቦት 7 ጋር በማገናኘት የሽብርተኝነት ጥላሸት በመቀባት መስከረም 3 ቀን 10 ሰዓት ላይ ከመንገድ የታጠቁ ኃይሎች ከመኪና አስወርደው ይዘውት የሄዱት፡፡


የቤተሰብ ሁኔታ
ወጣቱ ፖለቲካኛ አንዱዓለም አራጌ ባለትዳርና የሁለት ህፃናት አባት ነው፡፡ አንዱዓለም አራጌ ትዳር የመሠረተው ከእስር ከተፈታ በኋላ በ2000ዓ.ም ከዶ/ር ሰላም አስቻለው ጋር በሥርዓተ ተክሊልነው፡፡
አንዱ ዓለም ለኢትዮጵያ ሕዝብ ባደረገው የነፃነት ትግል ወህኒ ተወርውሮ ጠባብ ክፍል ውስጥ ቢቀመጥም በፍርድ ቤት የሚከተለውን ተናግሮ ነበር፦
“መንግሥት ለኢትዮጵያ ሕዝብ የአፋና ሥራ እየሠራ ነው፡፡ እኔም አንዱ የዚህ ሰለባ ነኝ፡፡ ፍ/ቤት ነፃ ሆኖ የራሱን ሂደት ያያል የሚል እምነት ስለሌለኝ እስከመጨረሻው የሞት ፍርድ ድረስ ቢደርስብኝም ከመቀበል ሌላ የምከራከረውም ሆነ የምናገረው ነገር የለኝም”
አንዱዓለም አራጌ መስከረም 4 ቀን2004ዓ.ም፡፡
የሕሊና እስረኛው አንዷለም አራጌ የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች የ2005 ዓ.ም ምርጡ ሰው ተብሎ ተመርጧል።
Short URL: http://www.zehabesha.com/amharic/?p=7230

No comments:

Post a Comment