Saturday, September 21, 2013

አዬ … ተመከተ …. ቀደሞ ተነበዬ …. ትንቢቱም … ዕውን ይሆናል። ከ ሥርጉተ ሥላሴ

ሥርጉተ ሥላሴ 17.09.2013
ከዬት እንደምጀምር ሳላውቅ ጀመርኩት። ይሁን። መቼም አጅሬዋ እንደማታሳፍረኝ በማመን እሷኑ ተከትዬ ልንጎድ።
ቀና …. ቀናውን እያሳለሁ። ቀኝ … ቀኜን …. እየተመኘሁ …..፤ ተስፋን ሰንቄ መጭ ልበል …. ግን አንጀቴ እርር ብሎ፤
ማህጸኔም ኩርምት ጭብጥ ብሎ /// ሱባኤ ገብቷል። ለነፍሷ፤ ለእስትንፋሷ ከሞላው ብርታት አባ መስጠት መዳህኒቴ
መንፈሱን እንዲልክላት በመማጸን ….
አንቺ ህብር …. ግብር
የወጣት አብነት ተግባር።
የመሆን መቻል ንብ
የብዕር ፍጹም ዘብ።
የነፃነት አውራ … ትንግርት
የሴት አብነት የትንቢት።
የቆረጥሽ እመቤት - የጽናት
የፍቅር ምላዕት ውፅፍት።
ቀድመሽ አይተሽ ተናገርሽ ….
ለነገ እራስሽን ሰጥተሽ ተቃጠልሽ ….
ነደሽ ቀልጥሽ፤ …. በአንቺ መከራ እኛን አበራታሽ ….
በዘረኞች ቋሳ … ተቀቀልሽ፤
እንደከሰመ አይቀር ይበቅል
መስዋዕትነትሽ ያዘምር፤
ትናነትን ዘክሮ ነገን ያሳምር
የተፈጠርሽ ለታምር
ሰብል ያነባብር!
ዛሬ ወደ ቀንጮዋ ወጣት አናብስት አሰኝቶኝ ትንሽ ስንኝ
መቋጠር ወደድኩኝ። በዚህ ዕድሜ፤ በሴትነት አቅም፤ „እኔ ብሞትም ሚሊዮን ርዕዮቶች …“ አለችን ያቺ የትናትናዋ
እንቡጥ በዕድሜ ከሁላችንም ያነሰች የመሆን መቻል ንግሥት መምህርት ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ። በቀዬፋ የመቅጫ ቦታ
ቀራኒዎ ላይ ሁና በተስፋ እኛን ታነጥረናለች። በአረመኔዎች እጅ ወድቃ አዲስ የሰለጠነ ራዕይ ታውጃለች፤ በበለኃሰቦች
ክርኒ ሥር ሆና፤ መከራውን ሁሉን ችላና ታግሳ የአይዟችሁን መናን ትመግበናላች። አሁን ደግሞ ሰው የማይችለውን
ለመቻል ወስናና ቆርጣ እኛ አዲስ ብለን ባደገደግንለት፤ ከቅዱስ የኋንስ ጀምሮ እሷና ቤተሰቦቿ ኮሶ ቆርጥመው ዋሉ
አደሩ …. አሁንም እሷ ቀጥላለች። መከረኛዋ ከእህል ከእውኃ ታዕቅባ እንደ ቅዱሱ ተክልዬ ሥጋዋን እዬቀጣችው …
ነው። መ-ረ-ራታ! በቀሉ አዬለባታ፤ በአጋም ታጠረች …. በፍዳዋ ቤት እንኳን ድቅድቅ እንሆ ተሸለመች …. አወጁ ዘረኞች
ከቃሊቲም በበቀል ሊደቁሷት …. ዶለቱ ….
የኛ ዕንቡጥ፤ የኛ ለጋ፤ የኛ ሰማዕት ለሴት ልጆች ከፍተኛ የመንፈስ ድቀት በሚፈጥረው በጡት ህመም እዬተሰቃዬች፤
ዘለፋውን፤ እርግጫውን ችላ በካቴናው ማሳ ትንፋሽ አጥሯት ታፍና፤ ተወጥራ፤ በፋሽስቶች ትንገበገባላች። ይህ ዘመን
ከዬትኛው ዘመን ጋር ሊመደብ እንደሚችል መግለጽ ባልችልም፤ የኦሾቲዝምን ሚስጢር ያነበባችሁ ወገኖቼ ከዛ ጋር
ታገናዝቡት ዘንድ በአክብሮት እጠይቃችኋላሁ።
የርዕዮት እስትንፋስ፤ በዬሰከንዷ አፋፍ ላይ ነው። እኛን በአጽህኖት ይማጸነናል። በተደሞ ውስጣችን ይመረምራል።
በትዝብት ያጠናናል፤ ከራሳችን ጋር ስለሞሆናችንም መንፈሳችነን በተደሞ ይረምራል። ሥቃዮዋ እዬተጣራ ነው።
ድረሱልኝ እያለ ነው። መልዕክቱን ዕውነትን ታጥቆ ልኮልናል። ለመሆኑ ጆሮ አለን? ማድመጥ እንችላለን?!~
አይመስለኝም በሰባራ ሰንጣረው አቲካራ ገጥመን አካሎቻችን የዘነጋን ይመስለኛል። ያማ ባይሆን ኖሮ የሚቀድመውን
ለማስቀደም ባልተሳነን ነበር። ምን ያቅታል? ውስጥን በቅንነት አጥቦ …. ለተግባር መትጋት …. የነፃነት አርበኞቻችን እኮ
ከህልፈት ጋር ግብግብ ገጥመዋል …. ሩኃቸው መፈናፈኛ አጥቶ ጨለማ ታውጆበታል …
እጅግ የማከብራችሁ የጹሑፌ ታዳሚዎች … ሴት እህት፤ ሴት እናት፤ ሴት አክስት፤ ሴት የማህበራዊ ኑሮ ጓደኛ፤ ሴት
የትዳር ጓደኛ፤ ሴት፤ ሴት ልጅ ያለችሁ ሁሉ ይህን ስቃይ፤ ይህን መከራ፤ ይህን ከሞት ጋር መፋጠጥ መራራ ገጠመኝ
እንዴት ትተረጉሙት ይሆን?! እንዴትስ ታመሳጥሩት ይሆን?! ለመሆኑ ይህን ሰቆቃ ቸል የሚል አንጀትስ መንፈስ ይኖራችሁ ይሆን?! እንደ እኔ ህማማተ ~~~ ርዕዮት የተራራው የመዳህኒታችን የቀራኒዎ፤ የጎለጎታ ስብከት ሆኖ ነው
ያገኘሁት።

እንደ እኔ ርዕዮት አሁን መምህርም፤ ጋዜጠኛም ብቻ አይደለችም። የነፃነት ብቁ ሐዋርያና ሰማዕትም ናት። እመ ብዙኃን
ናት። ጉልላትና ማማ ናት፤ በታሰረ ሰንሰለት ሞትን ፈቅዶ በስቃይ ለመቀበል በቀንበጥነት መወሰንና መቁረጥ! ምን
ዓይነት የቅኔ ጉባኤ ነው። ምን ዓይነት የታሪክ መጽሐፍ ነው?! … ይህ በዬትኛውም ዘመን ያልታዬ የኛ የሆነ፤ የዛሬ ብርቅ
ታሪክ የነገ መወድሳዊ ትውፈታችን ነው። ድርሳናችን ነው። እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ ለሃይማኖቷ ቅድስና
አገኘች። ርዕዮት ደግሞ ለነፃነት ቅድትና ድንግል ናት። በዚህ ዘመን የተፈጠሩ ወጣት አንስት የነፃነት ጎሆቻችን ናቸው።
የእናት ሀገራችን ታሪክ ሙሉዑ ያደረጉ የታሪክ ዘብ አደሮች።
አብሶ እጅግ መጥቀው፤ ቀድመው በሚወጡ ብልህ አንስት የነፃነት አርበኞቻችን፤ ግፈኛው ወያኔ የሚፈጽመው
አረመኔያዊ እኩይ ተግባር ፍጹም የተለዬና ታይቶም ተሰምቶም የማይታወቅ ጭካኔ ነው። ጋዜጠኛ ሰርኬ … በኽረ ልጇን
እስር ቤት ሆና አርግዛ ወልዳ ከአራስ ልጇ ጋር ሳትገናኝ፤ የአራስ ወጓ …. እስር ቤት፤ …. አራስ ህፃንም ከጡት ተለይቶ
በሀገሩ ባይታዋርነት ታውጆበት ገና ከጥንሰሱ ጀምሮ በጭካኔ እንዳይወለድ፤ ከተወለደም እንዳያድግ የተፈረደበት
በታምሩ ግን ያደገ የነገ ዓይነታዊ መዘክራችን ነው።

ክብርት ዳኛ ብርቱካን ሜዴቅሳም ለሁለት ጊዜ እስር ቤት ስትገባ ሃልዬ እናት አልባ ሆና ዘወትር ሰንበትን፤ ልደቷን፤
ዓውደ-ዓመታትን፤ የጨዋታ ጊዜዋን፤ የእረፍት ጊዜዋን፤ የህጻንነት ወቅቷን ሁሉ ቃሊቲ ላይ ሰንሰለት እያዬች፤
የአረመኔውን ሰራዊት ግፋና በደል በማስተዋል እዬተሸማቀቀች እንድታድግ ተበይኖባት ነበር። እናቷን ሲገፏት
ሲያንገላቷት እዬተመለከተች፤ ደካማ አያቷን ሲገላምጡ እዬተመለከተች …. በፍርኃት ተሸማቃ የማይችለው ቀንበጥ
መንፈሷ ጎብጦ እንዲያድግ ተዘመተባት …..
ይህ የሄሮድ አስተዳደር፤ ራዕይ መቼ እንዲያው መቼ ይሆን የሚነቀለው? ይህን ሁሉ ስቃይ የሚያዬውስ ወገን እንዴትና
እንዴት ብሎ ነው ይህን ፍትህን የሚቀጠቅጥ፤ ርትህን አጋድሞ የሚያርድ፤ ነፃነትን የሰቀለ ፋሽስታዊ አስተዳደር
ለማስወገድ የገፋ ተግባር የሚፈጽመው …. ? ? ?
መቼ ይሆን እራሳችን በራሳችን ካዘጋጀነው፤ እንደ ጉም ሽንት ከሚጎትተን ትብትብ ነገር ሁሉ ተፋተን በውስጣችን
እውነተኛ ለውጥ በማምጣት እንዲህ በፈላ በቀል የሚቀቀሉ ወጎኖቻችን ጥሪ እድምተኛ ቤተኛ በፍቅር የምንሆነው …. ፧
ምንው ባልተፈጠርኩ። ከተፈጠርኩም ቀድሜ አፈር ብሆን ምንኛ መልካም በሆነ …. ትንፋሽ ያሳጥራል …
አቅምሽ --- መዳህኒትሽ
ፈውስሽም --- አምላክሽ
እውነትም ---- ትራስሽ
የሆ /// ን//// ሽ!
ነፃነትም --- መሪሽ
መሰዋትም ----- ፈርሽ
ለሰላም ~~~~ የቆረብሽ
መሆን መቻል ፈውስሽ!
መቅለጥ ሆነ ፈርጥሽ
እርኃብ ሆነ ሰርግሽ!
ዓላማሽም --------------------------ሩቅ
የመከራ ምሩቅ፤
የአንስትም ነሽ ልዑቅ
የእኩልነት መረቅ፤
እ///ር///ቅ!
የብዕር ማህለቅ
የብራና ወርቅ - ልቅ።
ታናሼ ድምቀቴ
ታናሼ ድህነቴ
ሰንደቅ ቀለበቴ!
ልቦና ይሰጠን! ፈጣሪያችን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
(source addis voice)

No comments:

Post a Comment