Sunday, April 26, 2015

በጨካኞች ሰማእታት በመሆን ሕይወታቸውን ላጡት ወገኖቻችን የተላያዩ ዝግጅቶችን በማቅረብ በስቮልቫር ከተማ ተደረገ!!!

በህወሓት   አገዛዝ  የአንድ ብሄር  የበላይነት  በሚንፀባረቅበት  ሰዎች  በዕውቀታቸው  ደረጃ  በዜግነታቸው  ሳይሆን  ለወያኔ ሎሊ  ወይም  አገልጋይ  ካልሆኑ  የስራም  ሆነ  የመኖር  መበታቸው  በማይረጋገጥበት   አገር  መኖር ስይችሉ  ሲቀሩ  ሰደትን እንደአማራጭ  በመጠቀም  የትም  በርሃ  ሲቀሩ  እናያለን  ከሁሉም  በላይ  የከፋው  የአለምን  ቀልብ  የሳበው    30 ንፁሀን ወግኖቻችን ላይ  በአይሲስ  የተወሰደባቸው  የጨካኔ  ግድያ  ለዚሁሉ  ጥፋት  በመጀመሪያ  ደርጃ  ተጠያቂው  የወያኔ  ስርአት ነው። የወንድሞቻችን  ደም  ያለአግባብ  መፍሰሱ  የተቆጨን  ህዝቦች  ሁሉ ሀዘናችንን  በተለያየ  መልኩ  እየገለፅነው፣፣

 ኤፕሪል 25/4/2015  ፍፁም ሰባዓዊነት  በጎደለው  መልኩ  ባአሰቃቂነት  ለተሰውት  ወገኖቻችን  በማሰብ  የሻማ  ማብራት  እና በቤተክርስቲያን  የተለያዩ  ዝግጅቶችን  በማቅረብ  በስቮልቫር  ከተማ  የምንኖር  የኢትዮጵያ  ስደተኞች  ከኤርትራ  እህቶቻችን ወንድሞቻችን  በጋራ በመተባበር  ሀዘናችን  በመግለፅ  ፍሳቸውን  ይማር  በማለት  አስበናቸው  ውለናል።
በፕሮግራሙላይ  በስቮልቫር  ከተማ ነዎሪዎች  የሆኑ ኖርዌያኖች  የተወሰነ ቁጥር  ያላቸው ጥሪያችንን  በማክበር  እና ታወቂያውን  በማየት   የፕሮግራሙ  ተካፋይ በመሆን  አጋርነታቸውን  አሳይተዋል  በተለይም  ወደቤተክርስቲያን  ድረስ አብረውን  በመጓዝ  እስከመጨረሻ  ድረስ  የተሳተፉትን  ከልብ  አናመስገናለን።


ከአበባ  ማስቀመጡ  እና  ከሻማ  ማብራቱ  በተጎዳኝ  በግፍ  የትገደሉ  ወገኖቻችን  የሚገልፅ  ምሰልና  ገዳዮቻችው  ተሽፋፍነው የሚያሳየውን  ፎቶ  አይሲስ  የልቀቁትን  ፎቶ  በማያዝና   የምስሉ  ገላጨ  የሆነ  ፅሁፍ  በመፃፍ  ለማህብረሰቡ  አምፊ (AMF) የገቢያ አደራሽ  በር  ላይ  በመቆም  የደርሰባቸውን  መከራ ሰቃይ  በገላጨ  ፎቶው  ለማሰየት  ሞክረናል  ትልቁ  ትኩረት  ሊሰጠው የሚገባው  አብይጉ  አይሲሰ  እንወክለዋልን  በለው  የሚያምኑትን  የእስለምና  ሀይማኖትን  የማይወክሉና  ትልኮቸው  ፍፁም ደቢሎሳዊ  ሰለሆነ  የአለም  ህዝብ  በጋራ  በመቆም  በተለይም  አሜሪካና  የተቀረው  የምዕራቡ  ዓለም  ትኩረት  ሰጥተው ማጥፋታ  አለባቸው  ይህንንም  መልእክት  ለኖርዌይ  ማህበረሰብ  አስተላልፈናል።


ከአንድ  ስዓት  ቆይታ  በኃላ  በመቀጠልም  በተያዘው  ፕሮግራም  መሰረት  ወደ  ሁለተኛው  ፕሮግራም  የያዝነውን ምስል  ወይም ፎቶ  በመያዝ  ዋናውን  ከትማ  በምዞር  በህብረት  ጉዞ  ወደ  ቤተክሪስቲያን  እዛም  ስንደርስ  ፕሮገራሙን  የያዙልን  ቄስ  እንኳን ደህና መጣቹሁ  በማለት  በመንፈሳዊ  መዙሙር  ኦርጋን  በመጫውት  በፈገግታ  ተቀብለውናል  ከዛም  በመቀጠል  ብደጋሚ ቄስ ጉናኣር  አንደርሰን (Gunnar Andersen)  እንኳን  ደህና  መጣችሁ  በማለት  አጭር  የምግቢያ  ንግግር  ካደረጉ  በሆላ  በደጋሚ የምስጋና  መዝሙር  ጋብዘውናል  ከዛም  በመቀጠል  የፕሮግራሙ  መሪ  ወንድማችን  ሳምሶን  ወደመድርክ  በኤርትሪያ   የኦርቶዶክስ ተዋህዶ  አማኝ  እህቶቻችን  ወንድሞቻችን  በመጋበዝ  ለእለቱ የሆናል  በለው  የተዘጋጁበትን  3 መንፈሳዊ  መዝሙሮችን   በተከታታይ  አቅርበዋል  በማስከተልም   አንድ  ውንደማችን  ኤርትራዊ  ግጥም  አዘጋጅቶ  አቅርቦልናል  በመጨረሻም  የፕሮግራሙ  መሪ  በራሱ  የተዘጋጀውን   የስደትን  አስከፊነት  የሚገልፅ  በወንድሞቻችንላይ  የደረሰው  አሰቃቂ  መከራና  ግድያ  በእያንዳንዳችን  ቢደርስብን  ምንሊሰማን  እንደሚችል  የሚያሳስብ  ግጥም  በማቅረብ  ገልጿል  በስተመጨረሻ  ሻይ  ብና  በማ ፕሮግራሙ  በታያዘለት  ስዓትና  ደቂቃ  በሰላም  ተጠናቋል


በሰተመጨረሻ  ምስጋና  ለዝግጅቱ  መሳካት  ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትሉ  በእውቀታቹሁ ፣ በጉልበታቹሁ ፣በመልካም ሀሳባቹህ ለተባበራችሁን  የሻማ ማብሪያ  ቦታ ለፈቀዱልን  ለአምፊ  (AMF)የግቢያ  አዳራሽ ፣ፎቶውን ከለር  ፕሪንት  በማደርግ  ለትባበችን  የትምህርት  ቤቱ  ሰራ  አስኪያጅ  ለቄስ ጉናኣር  አንደርሰን (Gunnar Andersen)  ላደርጉልን  መልካምና  በጎ ሀሳብ  እርዳታ  ከልብ  እና መሰግናለን።

በግፍ በጨካኞች የተገደሉትን ወገኖቻችን ወንድሞቻችንን ነፍስ የማርልን !!!!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!
Dawit Wondimu
SVOLVÆR  25/4/2015


No comments:

Post a Comment