Friday, April 17, 2015

እስከመቼ ነው የወገኖቻችን ስቃይና መከራ በማየት በማዘን እና በመቆጨት ብቻ የምንገልፀው?

ከመቼውም በከፋ መልኩ ኢትዮጵያዊ የተዋረደበት እና አንገቱን የደፋበት ዘመን ቢኖር ወያኔ ሕወሓት መንግስት አገሪቶን ተቆጣጥረው ያለአቅማቸው እና በጠባብ አመለካከታቸው አገርእንመራለን ህዝብ እናስተዳደራልን ብለው ስልጣን በያዙበት ማግስት ነው ።ዛሬ ኢትዮጵያዊ በገዛ አገሩላይ በነፃት መኖር እየፈለገ ይህንመብት በማጣቱ ስደትን እንደጊዜዊ አማራጭ በመጠቀም በተለያዩ አገራት ሲሰደድ እየተመለከትን ነው ሆኖም ግን በተቃራኒው የምንሰማው እና የምናየው መከራውን ፣ፍዳውን፣ስቃዩን፣እንግልቱን፣መታሰሩን ከዛም አልፎ በህይወት እያለ በእሳት እየተቃጠሉ እየሞቱበት ያሉበትን ሁኔታ እየተመለከትን ነው። መቼም ልንረሳው የማንችለው የቅርብ ግዜ ትዝታ የንበረው በሳዑዲ አረቢያ ይኖሩ የነበሩ ኢትዮጵያን ወገኖቻችን ላይ የደረሰው መከራና ሞት የእናት ሀገሩን ሰንደቅ ዓላማ(ባንዲራ)አንገቱላይ እንዳደረገ የሞተውን በየአስፋልት መንገዱላይ እንደውሻ የተጎተተውን ወንድማችን በሴት እህቶች ላይ የደርሰባቸው የፆታጥቃት ብዙ ተዘርዝረው የማያልቁ ስቃያቸውን አይተናል የወግኑ ያለአግባብ መሰቃየት የተሰማው ኢትዮጵያዊ በሚኖርበታ አገር ድምፅ ለሌለው ወገኑ ድምፅ በመሆን የሳዑዲ አረቢያ ኤምባሲ በሚገኝበት አገር ድምፁን ሲያሰማ አስተውለናል ይህቅዱስ ሀሳብ የሚደገፈና የሚበረታታ ነው።
በየመን ሰሞኑን በሳዑዲ መሪነት በሁቲ አማጽያን ላይ በተውሰድው ጥቃት የተለያዩ አገርዜጎች መንግስታቸው ደርሶላቸው በትለያዩ መንገዶች ዜጎቻቸውን ሲያትርፉ መንግስት አልባው ኢትዮጵያዊ የስልክ ቁጥር ብቻ ነበር ቀደሞ የሚነገረው በስደተኛ ጣቢያ የአለምአቀፍ የተባበሩት መንግስታት ምልክት ባለብት ዱንካኑውስጥ ተጠልለው ሳሉ በአየር ድብደባ ምክንያት ህይወታቸው የለፈው ኢትዮጵያዊያን የሚደርስላቸው መንግስት በማጣት።
ከሰሞኑ ደግሞ የምንሰማውና በጣም የሚያሳዝነው ከወደ ደቡብ አፍሪካ በደርባን ከተማ በአንድ ትንሽ ሱቅ ኮንቴና ውስጥ በሁለት ወንድማማቾች እሳት የለቀቁባቸው በዚህ ምክንያት የአንዱ ኢትዮጵያዊ ህይወቱ ሲያልፍ አንደኛው ህይወቱ ተርፎ በሆስፒታል ውሰጥ እርዳታ እየተደረገለት የገኛል ዛሬ ኢትዮጵያዊ የማይንገላታበት አገር የለም በአውሮፓም ጭምር።
ለዚሁሉ መከራና ሰቃይ ያደረገን የወያኔ ዘረኛ አገዛዝ ስለሆን ዛሬ መናልባት አንዳንድ ሰዎች ችገሩ የግል በራቸውን ካላንኳኳው የወገናቸው መከራና ስቃይ ላይታያቸው ይችል ይሆናል በወንድሜ፣በእህቴ በወገኔ ላይ የሚደርሰው ጉዳት የኔ ነው በማለት ከመቼውም በበለጠ ኢትዮጵያዊ እና ወገናዊ መሆናችንን በተገባር አቅማችን በፈቀደው ደረጃ የምናሳይበት እና የምንገልፅበት ወሳኝ ወቅት ነው ስለዚህም በሚደረገው በማናቸው የትግል ስልት ያዋጣናል በለው የተደራጁ የፖለቲካ ድርጅቶችም ሆነ የሚንቀሳቀሱ ሃይሎችን በመቀላቀል አባል ወይም ደጋፊ ሆኖ በመንቀሳቀስ ወቅቱ የሚጠይቀው የውዴታ ግዴታ ነው ።
ዳርሆኖ መመልከት ወይም ከንፈር መምጠጥ፣መቆጨት ነፃነትን አያሰገኝም ወይም በሌላመልኩ ከወያኔ ጋራ እንደመተባበር ያሰቆጥራል ሁሉም በሚችለው አቅምና ችሎታ የዜግነት ገዴታውን ይወጣ ባለበት አገርም ሆን አካባቢ።
ኢትዮጵያ ለዘላለም እንደቀደምት አባቶቻችን እናቶቻችን በክብር ትኑር 
Dawit Woundimu 

No comments:

Post a Comment