Saturday, August 31, 2013

የሼክ አል አሙዲ ኩባንያ ቤኒሻንጉል ክልል የወሰደው 20 ሺሕ ሔክታር መሬት ሊነጠቅ ነው

01 SEPTEMBER 2013 ተጻፈ በ  
ሼክ መሐመድ አል አሙዲ 80 በመቶ የባለቤትነት ድርሻ በመያዝ ለግብርና ኢንቨስትመንት የመሠረቱት ሆራይዘን ፕላንቴሽን የተባለ ኩባንያ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለለውዝ እርሻ የተረከበውን 20 ሺሕ ሔክታር መሬት ባለማልማቱ ሊነጠቅ ነው፡፡
ኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ300 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚያስወጣትን የምግብ ዘይት ግዢ በአገር ውስጥ አምርቶ ለማስቀረት ዕቅድ ይዞ ነበር የተባለው ሆራይዘን ፕላንቴሽን ኩባንያ፣ እ.ኤ.አ. በመጋቢት 2012 ለምግብ ዘይት የሚሆነውን ለውዝ ለማምረት 20 ሺሕ ሔክታር መሬት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሊዝ ተረክቧል፡፡ 
በኩባንያው ዕቅድ መሠረት 20 ሺሕ ሔክታር መሬቱ ለለውዝ እርሻ የሚውል ሲሆን፣ በአማራ ክልል ባህር ዳር ላይ ደግሞ በ600 ሚሊዮን ዶላር የዘይት ፋብሪካውን ለመገንባት ታስቧል፡፡ 
ይሁን እንጂ ኩባንያው መሬቱን ከወሰደበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ ምንም ዓይነት የልማት እንቅስቃሴ ባለማድረጉ፣ በግብርና ሚኒስቴር የግብርና ኢንቨስትመንት ድጋፍ ዳይሬክቶሬት ጉዳዩን እንዲመለከተው አስገድዷል፡፡ 
‹‹ኩባንያው መሬቱን ከወሰደበት ጊዜ አንስቶ ወደ ልማት መግባት ባለመቻሉ ማስጠንቀቂያ እንዲደርሰው አድርገናል፤›› ሲሉ የዳይሬክቶሬቱ አስተባባሪ አቶ ብዙዓለም በቀለ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ለተጻፈለት የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ምክንያቶቹ በመዘርዘር ኩባንያው ምላሽ እንደሰጠ፣ ለዚህም ምላሽ ተጨማሪ ደብዳቤ ማስጠንቀቂያውን በማፅናት እንደተጻፈለት አስተባባሪው ገልጸዋል፡፡ ነገር ግን የተለወጠ ነገር ባለመኖሩ የመሬቱ ውል እንዲቋረጥና መሬቱ እንዲመለስ ሐሳብ መቅረቡን ተናግረዋል፡፡ ኩባንያው መሬቱን ከወሰደ አንስቶ ልማት ካለመጀመሩም በላይ፣ አንድም ቀን ከግብርና ኢንቨስትመንት ዳይሬክቶሬቱ ጋር ኢንቨስትመንቱን በተመለከተ ግንኙነት እንዳልነበረው አቶ ብዙዓለም አስረድተዋል፡፡ 
ሆራይዘን ኩባንያ ለለውዝ ልማት የጠየቀው መሬት ምቹ ይሁን አይሁን ጥናት ሳያደርግ መረከቡን፣ በተረከበበትም ወቅት የተሰጠው መሬት በጣም ምቹ እንደሆነ መግለጹን የሚያስታውሱት አስተባባሪው፣ ለዓመት ከዘገየ በኋላ የሚሰጠው ምክንያት መሬቱ ምቹ እንዳልሆነለት ነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡ ይህ ኩባንያውን የሚያቀርበው ሰበብ ‹‹የበርካታ ኩባንያዎች ችግር ነው›› ሲሉ ይገልጹታል፡፡ 
የሆራይዘን ኩባንያ ኃላፊዎች ሊወሰድ የታሰበው ዕርምጃ ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት ከግብርና ሚኒስትሩ አቶ ተፈራ ደርበው ጋር እየተነጋገሩ መሆኑን ለመገንዘብ ተችሏል፡፡ 
ሼክ መሐመድ አል አሙዲ በ2005 ዓ.ም. የመጀመሪያ ወራት በኮምቦልቻ ሊገነቡት ያቀዱትን ጦሳ የብረታ ብረት ኩባንያ እንዲገነባ ከመረጡት የጣሊያን ኩባንያ ጋር ሲፈራረሙ፣ የዘይት ፋብሪካውንም ግንባታ ለመጀመር በአሥር ቀናት ጊዜ ውስጥ ከአንድ የእንግሊዝ ኩባንያ ጋር እንደሚፈራረሙ በወቅቱ ተገኝተው ለነበሩት ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትና ለምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጭምር ገልጸው ነበር፡፡ 
ይሁን እንጂ የዘይት ፋብሪካ ግንባታ ስምምነት እስካሁን አልተፈረመም፡፡ ሼክ አል አሙዲ ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ በግብርና ኢንቨስትመንት በስፋት ለመሰማራት እየሠሩ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፣ ግዙፍ የመንግሥት የእርሻ ልማቶችንም በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ከፕራይቬታይዜሽንና ከመንግሥት ልማት ድርጅቶች ኤጀንሲ መግዛታቸው ይታወሳል፡፡ ሼኩ በጨረታ ያሸነፉዋቸውን የእርሻ ልማት ድርጅቶች ለመግዛት በቢሊዮኖች የሚቆጠር ወጪ ሲያወጡ፣ ከመንግሥት የገዟቸውን ድርጅቶች 35 በመቶ ክፍያ ለመፈጸም ከዓመት በላይ እንደፈጀባቸው ያስረዳሉ፡፡ 
ጉዳዩን አስመልክቶ መረጃ እንዲሰጡ የሆራይዘን ኩባንያ ዋና ሥራ አስኪያጅን ለማግኘት የተደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡ 
ምንጭ ሪፖርተር ጋዜጣ 

ከስልጣን የተነሳው የደህንነት ሹም፣ እስር ቤት ተወረወረ!!

በዳዊት ከበደ ወየሳ
(ኢ.ኤም.ኤፍ) የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ በህይወት
በነበረበት ወቅት፤ ወልደስላሴ ወልደሚካኤል ምክትል የደህንነት ሹም ሆኖ
ይሰራ ነበር። ወልደስላሴ የህወሃት ታጋይ የነበረ ሲሆን፤ በትግላቸው
ወቅት... ወንድ እና ሴት ታጋዮችን “ፍቅር ስትሰሩ ተገኝታችኋል” በማለት
ብዙዎችን በመረሸን ይታወቃል። ኢህአዴግ አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ
በኋላ፤ የመለስ ዜናዊ ክርስትና እናት ልጅ የሆነው፤ ኢሳያስ ወልደጊዮርጊስ
የቤተ መንግስቱ ዋና ኃላፊ፣ ወልደስላሴ ደግሞ የቀድሞው ደህንነት ሃላፊ
ክንፈ ገብረመድህን ረዳት ሆኖ እንዲሰራ ተደርጎ ነበር።
እ.ኢ.አ የ1994ቱ ክንፈ ገብረመድህን ድንገተኛ ሞት ያስደነገጠው
የህወሃት ቡድን፤ የደህንነት ምክትሉን ወልደስላሴን ዋና የደህንነት ሃላፊ
አድርጎ ቦታው ላይ አላስቀመጠውም። ለዚህ ዋናው ምክንያት ወልደስላሴ
ችኩል፣ ያልተማረና ብቃት የሌለው ሰው መሆኑ ነበር። በርግጥ ሌላ
የተማረ ኢትዮጵያዊ ጠፍቶ ሳይሆን፤ ይህንን ቦታ መያዝ የሚገባው ከሌላ
ድርጅት ወይም ብሄር የተገኘ ሰው ሳይሆን፤ የህወሃት ወይም የትግራይ
ተወላጅ እንዲሆን ስለተፈለገ፤ ጌታቸው አሰፋ ለትምህርት ከተላከበት
አሜሪካ፣ ቴክሳስ ግዛት በአስቸኳይ ወደ አዲስ አበባ እንዲመጣ ታዘዘ።
ያልጠበቀው ሹመትም ተሰጠው።
ጌታቸው አሰፋ የደህንነት ሃላፊ ይሁን እንጂ፤ የቤተ መንግስቱን
ወይም የመለስ ዜናዊን ጥበቃ በተመለከተ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሁለቱ
ሹሞች ወልደስላሴ እና ኢሳያስ ሆኑ። ለምሳሌ መለስ ዜናዊ ወደ ውጭ አገር
በሚሄድበት ጊዜ መንገዱ እንዲዘጋና ጥበቃ እንዲደረግ፤ የቤተ መንግስቱ
ጥበቃ ሃላፊ ኢሳያስ ወልደጊዮርጊስ ቀጥታ ግንኙነት የሚያደርገው
ከወልደስላሴ ጋር እንጂ፤ ከዋናው ሃላፊ ጌታቸው አሰፋ ጋር አልነበረም።
በአጭር አነጋገር “መለስ መጣ” ሲባል የቦሌን መንገድ አዘግተው፤ ህዝቡን
እያስደበደቡ ከመንገድ የሚያስባርሩ አንጋች እና አጎንባሽ ሆኑ። የሁለቱ
ሹሞች የርስ በርስ መቀራረብ ብቻ ሳይሆን፤ ለመለስ ዜናዊም ቅርበት
አላቸው ስለሚባል፤ በደህንነት ሃላፊዎች ጭምር የሚፈሩ ሰዎች ነበሩ።
በዚህም ምክንያት ከታች ወደላይ ለጌታቸው አሰፋም ትዕዛዝ የሚሰጡ
ሆነው ቆይተዋል።
ያለፈው አመት የመለስ ዜናዊ ድንገተኛ ሞት ግን ይህንን ሁሉ
ምስቅልቅል እያጠራው መጣ። ጌታቸው እና ምክትሉ ወልደስላሴ
እንደተፋጠጡ የህወሃትን ጉባዔ ይጠባበቁ ጀመር። በዚህ መሃል
የወልደስላሴ ስልጣን እየኮሰመነ መጣ። ኢሳያስም ሆነ ወልደስላሴ
የሚያጅቡት መለስ ስለሌለ፤ በአዜብ መስፍን ዙሪያ ተሰበሰቡ። እናም አዜብ
መስፍን ቤተ መንግስቱን ለቅቃ እስከምትወጣ ድረስ፤ አልቃሽ እና አስለቃሽ
ሆነው ሰነበቱ። ጌታቸው አሰፋ ግን ለቅሶውን ትቶ፤ የነበረከት ስምኦንን
ቡድን ጨምሮ፤ አዲሱን ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ እና
ሌሎችንም እያስተባበረ የራሱን ኃይል ማደራጀት ጀመረ።
የቀድሞው ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ለቅሶ ሲያበቃ፤ ህወሃት/ኢህአዴግ
በሞተው እና በደከመው ምትክ አዳዲስ ሰዎችን ለመተካት እላይ እታች
ማለት ጀመረ። በዚህ መሃል ወልደስላሴ ወልደሚካኤል አጋጣሚውን
ተጠቅሞ በህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ ውስጥ ለመመረጥ የራሱን ጥረት
ማድረጉን ቀጠለ። የደህንነት ሃላፊው ጌታቸው አሰፋም — የወልደስላሴ
የመጀመሪያ እና የመጨረሻ ጠላቱ መሆኑን በዚህ ስብሰባ ላይ ግልጽ ሆኖ
ወጣ።
“ህወሃት አድርጎት በነበረው ስብሰባ ላይ ወልደስላሴ እንዲመረጥ
እጩ ሆኖ ሲቀርብ፤ የመጀመሪያ ተቃዋሚ ጌታቸው አሰፋ ነበር። ይህ
የጌታቸው አሰፋ ተቃውሞ ተሳክቶ፤ ወልደስላሴ ምርጫ ውስጥም
እንዳይገባ ተደርጎ ተሰረዘ፤ ሳይመረጥም ቀረ። የወልደስላሴ ጓደኛ እና
የመለስ ዜናው የክርስትና እናት ልጅ የሆነው ኢሳያስ ወልደጊዮርጊስ ግን
በጠባብ ሁኔታ እንደገና ተመርጦ የማዕከላዊ ኮሚቴው አባል ሆነ።
የህወሃት ስብሰባ ላይ ይደረግ የነበረው ድራማ አላበቃም። በመቀጠል
ደግሞ ጌታቸው አሰፋ ተጠቆመ። ይሄን ጊዜ ወልደስላሴ ለመናገር እጁን
አወጣና እድል ተሰጠው። እንዲህም በማለት ጌታቸው አሰፋን ኮነነው።
“ጌታቸው አሰፋ በህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ ውስጥ እንደገና መቀጠል
የለበትም። ጌታቸው ህወሃትን እያገለገለ አይደለም። ስራውንም በአግባቡ
አይወጣም። ይሄ ሰው የአላሙዲን ተላላኪ እና አሽከር ሆኗል።” በማለት
ወቀሳውን ቀጠለ። ሆኖም ይህ የወልደስላሴ ወቀሳ ተቀባይነት ሳያገኝ
ቀርቶ ጌታቸው አሰፋ ብቻ ሳይሆን፤ ወንድሙ ዳንኤል አሰፋም ጭምር
በህወሃት ማእከላዊ አባልነቱ እንዲቀጥል ተደረገ። ከዚህ የህወሃት ስብሰባ
በኋላ እነዚህ ሁለት የህወሃት ደህንነት ሃላፊዎች አብረው ሊሰሩ
የሚችሉበት ሁኔታ እየጠበበ መጣ።
ወልደስላሴ በትግራይ የሚገኙ የቀድሞ የህወሃት አባላትን
በማስተባበር፤ በጌታቸው አሰፋ ላይ ሰፊ የጥላቻ ዘመቻ ማድረጉን ቀጠለ።
ይህ ዘመቻው ግን የቆየው እስከ ሰኔ ወር አጋማሽ ነበር። ከሁለት ወራት
በፊት ወልደስላሴ ወልደሚካኤል ከሃላፊነቱ ተነስቶ፤ ከስራ ተሰናብቶ
የህወሃት አባላትን ደጅ ሲጠና ሰነበተ። አዜብ መስፍንን፣ ስብሃት ነጋን እና
ሌሎችንም በመቅረብ እጅ መንሳት ጀመረ። ሃምሌ አልፎ ነሃሴ ተተካ።
ከዚያም የአቶ መለስ ዜናዊ ሙት አመት ተከብሮ ሳያበቃ፤ አዜብ
መስፍንም ጥቁር ልብሷን ሳትቀይር ሌላ ሃዘን መጣ - ወልደስላሴ
ወልደሚካኤል ተይዞ ታሰረ።
አሁን ጌታቸው አሰፋ በፌዴራል መንግስት ደረጃ ያለውን ስልጣን
እያደራጀ የመጣ ይመስላል። ከስር ሆኖ የሚያዘው ወልደስላሴ እስር ቤት
ገብቷል። ኢሳያስ ወልደጊዮርጊስ ከቤተ መንግስት እየደወለ ትእዛዝ እና
መመሪያ አይሰጠውም። ጌታቸው አሰፋ አሁን ነጻ ሰው ነው። ይህ ነጻነቱ
የሚቆየው ግን ቀጣዩ የህወሃት/ኢህአዴግ ስብሰባ እስከሚደርስ ይሆናል።
እስከዚያው ድረስ ግን እነ ኢሳያስን በአይነ ቁራኛ መጠበቅ አለበት። አዜብ
መስፍን ከኢፈርት ስልጣንዋ ወርዳ፤ ስለመለስ ፋውንዴሽን ብቻ እያወራች
እንድትኖር እድል ሰጥቷታል። ቢሆንም ግን ህወሃት ውስጥ ሌሎች
የጌታቸው አሰፋ ጠላቶች አሉ። እስከሚቀጥለው የህወሃት ስብሰባ እና ሌላ
ውጥንቅጥ ድረስ፤ ድራማውን ከዳር ሆነን እናያለን።
ከስልጣን ተነስቶ ለሁለት ወራት ከቆየ በኋላ የታሰረው፤ ወ/ስላሌ
ከበረሃ ጀምሮ በርካታ የድርጅቱን ታጋዮች በመረሸን ይታወቃል። « ፆታዊ
ግንኙነት ስታደርጉ ተገኝታችኋል…» በሚሉና ሌሎች ተልካሻ ምክንያቶች
እንዲረሸኑ በበላይ አመራር ውሳኔ የተላለፈባቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ
የፓርቲው አባላት (ታጋዮች) ለመግደል ይጣደፉ ከነበሩት መካከል
ኢሳያስና ወ/ስላሴ ዋናዎቹ ነበሩ ሲሉ ያስረዳሉ። አቶ መለስ ሁለቱን
አባላት ወሳኝ በሆነው የደህንነት ቢሮ ቁልፍ ስልጣን የሰጧቸው
«አድርጉ» የተባሉትን ያለማመንታት ተግባራዊ እንደሚያደርጉ ጠንቅቀው
ስለሚያውቁ ነበር። ወ/ስላሴ ስልጣን በጨበጠ ማግስት በአንድ ቀን አርባ
የቢሮው አባላትን (መኮንኖች ተብለው ነው የሚጠሩት) ከስራ አባሯል።
በየጊዜው በመቶዎች የሚቆጠሩ አባላትን «ተሃድሶውን አልተቀበላችሁም፣
የቅንጅት ደጋፊዎች ናችሁ..» በሚሉና ሌሎች ምክንያቶች ከማባረር -
እስር ቤት እስከመወርወር የደረሰ እርምጃ ሲወስድ ቆይቷል። ከመለስ ጋር
በሃሳብ ያለተስማሙ ሁለት ከፍተኛ ባለስልጣናትን በገዛ መኖሪያ ቤታቸው
በገመድ በማነቅና በስለት በማረድ የጭካኔ ተግባር ያስፈፀሙት ወ/ስላሴ
እና ኢሳያስ መሆናቸው በሰፊው ይወራል። በግፍ የተገደሉት የመገናኛ ሚ/
ሩ አቶ አየነውና የቤተመንግስት የደህንነት ሹም አቶ ዘርኡ መሆናቸውን
ጠቁመዋል።
አሁን ለጊዜው ከደህንነቱ ዋና ሃላፊ አቶ ጌታቸው አሰፋ ፊት
እንዲርቅ የተፈለገው ግን ወልደስላሴ ወልደሚካኤል በመሆኑ፤ “ሃብት
በማጋበስ ወንጀል” ተብሎ በሙስና ወህኒ ተወርውሯል። የ እስሩን ዜና
የኢህአዴጉ ፋና ሬዲዮ ሲያቀርበው፤ ሌሎች የመንግስት ሚዲያዎች ግን
በደረሰባቸው ድንጋጤ ምክንያል ይመስላል - ዝምታን መርጠዋል።
ምንጭ (የኢትዮጵያ ሜዲያ መድረክ)

Thursday, August 29, 2013

የኢቲቪው ጋዜጠኛ ተመስገን በየነ ተደበደበ

በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ዜናዎችንና መንግስታዊ መግለጫዎችን በማንበብ የሚታወቀው ጋዜጠኛ ተመስገን በየነ መደብደቡን ጓደኛው ጋዜጠኛ ደመቀ ከበደ አረጋገጠ። ጋዜጠኛ ደመቀ ከበደ “ኤዲቶሪያል ፖሊሲና ዜና አንባቢ ለየቅል ናቸው – ጥቂት ስለ ተመስገን በየነ ጉዳይ” በሚል በፌስቡክ ባሰራጨው መግለጫ የጋዜጠኛውን መደብደብ ማረጋገጡን ገልጾ መደብደቡን ግን አውግዟል።
ጽሑፉ ለግንዛቤ እንዲረዳችሁ በሚል ዘ-ሐበሻ እንደወረደ እንዲህ አቅርባዋለች፦

ኤዲቶሪያል ፖሊሲና ዜና አንባቢ ለየቅል ናቸው -
ጥቂት ነገር ስለ ተመስገን በየነ ጉዳይ

(ከደመቀ ከበደ)
ከትናንት በስቲያ አንድ ወዳጄ ‹‹ተመስገን በየነ ተደበደበ የተባለው እውነት ነወይ›› ሲል ኢንቦክስ አደረገኝ፡፡ ላጣራና እነግርሀለሁ ብዬው ተለያየን፡፡
****** **** ***** *****
ተመስገንን በቅርበት አውቀዋለሁ፡፡ በጣም ሰላምተኛ፣ ትሁትና ስራውን አክባሪ ነው፡፡ ከውድነህ ክፍሌ ጋር በፋና ኤፍ ኤም 98.1 ላይ የአየር ሰአት ወስደው ይሰሩ በነበረበትና እኔም ከመልቀቄ በፊት ወደ ስቱዲዮ በመጣ ቁጥር የበዛ ትህትናውን እየለመድኩት መጣሁ፡፡ ከዚያ በኋላም ሜሮን ጌትነት፣ አንሙት አብርሀም፣ እሱ /ተመስገን/ እና ሌሎች አምባሳደር ለሆኑለት የልመና ማስወገድ ጉዳይ የተቻለውን ሲያደርግ በዘገባ ጉዳይ ብዙ ተረዳድተናል፡፡ በቃ ስራውን ያከብራል፤ የተሰጠውን ተልዕኮ ለመፈፀም ትጉህና አርአያ ነው – አሁንም ከትህትና ጋር፡፡
ሰሞኑን ስለ እሱ የሰማሁትን በሁለት መልኩ ለማጣራት ጣርኩ፡፡ አንደኛው ከእሱ ከራሱ እና ከባለቤቱ /የቀድሞ ባልደረባዬ እምርታ አስፋው / ጋር ደወልኩ፡፡ የሁለቱም ስልኮች ኦፍ ናቸው በተደጋጋሚ ብሞክርም፡፡ / እስካሁን ድረስ/
ሁለተኛው ከቅርብ ወዳጆቼ እውነቱን ለማጣራት ደወልኩ፤ /ከባለቤቱ ወዳጆችና ከ‹‹አምባሳደርነት›› ወዳጆቹ ማለት ነው፡፡ ከላይ የጠቀስኳቸው ናቸው/
‹‹ጉዳት መድረሱንና ህክምና በመከታተል ላይ›› መሆኑን ነገሩኝ፡፡
‹‹ማን እና ለምን›› ለሚለው ግን መልስ አልነበራቸውም፡፡ ሊኖራቸውም አይችልም፡፡
ከተደጋጋሚ ሙከራዬ በኋላ የባለቤቱ /ከደቂቀቃወች በፈት/ እምርታ ስልክ ጠራ – አነሳችው፡፡
‹‹አሁን በመልካም ጤነነት ላይ ይገኛል፡፡ ትንሽ ቆይተህ ደውልለትና ራሱን አናግረው፤ አሁን ደክሞት ሰለተኛ ነው እንጅ እየተሸለው ነው፡፡›› አለችኝ፡፡
‹‹ምክንያቱ ግን ምንድን ነው›› ስል ደገምኩ ጥያቄዬን፡፡
‹‹አላወቅንም፤ ጉዳዩን ፖሊስ ይዞታል፡፡ ከተጣራ በኋላ እንነግርሃለን›› ብላኝ ‹‹እግዜር ይማረው ብዬ›› ተለያየን፡፡
የሆነውን እስኪ ከሰብአዊነት ብቻ እየመዘንን ‹‹እየተወሩ ያሉ›› ምክንያቶችን እንይ፡፡ ሰብአዊነትን ሰው ከመሆን ጋር ብቻ ሚዛናችን ነው!!
‹‹ተመስገን የተደበደበው በኢቴቪ ዜና የተነሳ ነው›› – እንበል፡፡ ‹‹ማን ደበደበው›› የሚለውን ማጣራቱ ለኔ ፅሁፍ ጠቃሚ አይደለምና ብዙ አልዘላብድም፡፡ ግን ‹‹በኢቴቪ ዜና የተቆጡና የተበሳጩ አካላት ወይም ግለሰቦች ነናቸወው ከተባለ ይሀህ መታየት አለበት፡፡
በሚዲያ ህግ አንድ የሚዲያ ተቋም የሚተዳደረው ‹‹በኤዲቶሪያል ፖሊሲው›› ነው፡፡ የሚዲያ ህገ መንግስት ይባላል፡፡ ይህ ‹‹ኤዲቶሪያል›› እንደየ ሚዲያው ፍላጎት፣ እንደየ ሚዲያው ማሰራጫ አገር፣ እንደየሚዲያው ገዥዎች እሳቤና እውቀት የሚወሰን ነው፡፡ እንደኛ አገር ባሉ ታዳጊ አገራት የሚዲያዎች ኤዲቶሪያል ፖሊሲ ከአገሪቱ ህገ – መንግስት ጋር የተቆራኜ ነው፡፡ የመንግስት ጣልቃ ገብነት ይበዛበታል፡፡ ኢቴቪም ከዚህ የወጣ እንዳልሆነ መንገር ለቀባሪ ማርዳት ይሆናል ፡፡
ታዲያ በማንኛውም ሚዲያ ተቀጥሮ የሚሰራ ሁሉ / ይህ የግል ሚዲያዎችንም ይጨምራል/ ኤዲቶሪያሉን አክብረው የመስራት ግዴታ አለባቸው፡፡ በኤዲቶሪያሉ ያልተስማማ መልቀቅ ብቻ ነው ምርጫው፡፡ ጋዜጠኞች የቤቱ ኤዲቶሪያል ፈፃሚ ሲሆኑ አለቆች ደግሞ አስፈፃሚ ናቸው፡፡
ወደ ዜና አንባቢዎች ስንመጣ ደግሞ፤ ዜና አንባቢዎች የተሰፃቻን ዜናች ያላንዳች መነካካት የሚያነቡ ናቸው – ፖስተኛ ማለት ነው ዜና አንባቢነት፡፡ የተሰጠህን መቀበል ብቻ!!
የሙሉ ጊዜ ዜና አንባቢ / የሚዲያው ቋሚ ተቀጣሪ/ እና የፍሪላንስ ዜና አንባቢዎች አሉ፡፡
ተመስገን በየነ የፍሪላንስ ዜና አንባቢ ነው፡፡ የኢቴቪ ጋዜጠኞች የሰሩትን ዘገባ ከማንበብ የዘለለ ምንም ሚና የሌለው፡፡ እንደ ጋዜጠኛ ወጥቶ መረጃ ቃርሞ ወይ ኤዲት አድርጎ የማቅረብ አንዳች ተልዕኮ የለውም፡፡
ይህን ነው ‹‹ለምን›› እንድል ያደረገኝም ፤ ብዬም ወደእናንተ ያስፃፈኝም ‹‹ይኸወ የአንባቢነት እንጅ የመረጃ ቃራሚነት ወይም ሃያሲነት›› ሚና የሌለው መሆኑ ነው፡፡
አሁንም ‹‹ተደባዳቢው›› አካል ማንም ሆነ ምንም ድርጊቱ ትክክል ነው ብዬ አላምንም፡፡ ‹‹ድብደባ›› በሰው ልጅ ላይ ተገቢ አለመሆኑን የማልደግፈው ሰው በመሆኔ ብቻ ነው፡፡ ምናልባት ያነበባቸው ዜናዎች ያስቆጡት ‹‹አካል›› ወይም ‹‹ግለሰብ›. የፈፀመው ከሆነ ለኔ ‹‹አህያውን ፈርቶ ዳውላውን›› ይሆንብኛል፡፡ አሁንም እደግመዋለሁ ፤ ተመስገን በዜና አንባቢነቱ ከሆነ የተደበደበው ነውር ነው – ፖስተኛ ሳይሆን ፖስታውን የፃፈው ነው መጠየቅ ካለበት መጠየቅ ያለበት፡፡ / መደብደብ ያለበት አላልኩም/
እህስ ሌላ ጉዳይ አስደብድቦት ከሆነስ ብለን እንጨምር፤
ዘረፋ የሚፈፅሙ ማጅራት መቺዎች ከሆኑም ‹‹ህግና እግዜር›› መፍትሄ ይሰጡት ዘንድ እመኝለታለሁ፡፡
በማንኛውም ምክንያት ‹‹በቂም ተነሳስቶ›› ተፈፅሞ ከሆነም ‹‹ከድብድብና ስድብ›› ወደ ቅርርብና ፍቅር መምጣት ይቻላል ባይ ነኝ፡፡ በእኔ እምነት ሰውን ከማያግባባው የሚያግባባው ነገር ይበልጣል፡፡ ፍቅር ያሸንፋል!!
Short URL: http://www.zehabesha.com/amharic/?p=6888
Posted by 
 on Aug 29 2013

ወታደራዊ ትጥቅማ ምረቻ ፋብሪካ በቃጠሎ ጉዳት ደረሰበት

ነሃሴ ፳፫(ሃያ ሦስት ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዛሬ በተነሳ የእሳት አደጋ ቃጠሎ በመከላከያ ሚኒስትር የትጥቅና ወታደራዊ ልብስ ስፌት ፋብሪካ ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን የአይን እማኞች ለኢሳት አስታወቁ፡፡
ከአዳማ ከተማ ወደ ወንጂ በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኘው ወታደራዊ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ላይ በደረሰው የእሳት አደጋ በፋብሪካው ላይ ከፍተኛ የንብረት ጉዳት መድረሱን ለማወቅ ተችሏል፡፡
በ18 ሚሊዮን ብር ወጪ በቅርቡ የተገነባው ፋብሪካው የተለያዩ ወታደራዊ ዩኒፎርሞችን ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ የሚያቀርብ ሲሆን የደረሰው አደጋ መንስኤ ሊታወቅ አልቻለም፡፡
በፋብሪካው ላይ የደረሰውን ቃጠሎ ለማጥፋት ከአዳማ ከተማ የእሳት ማጥፊያ ባለመኖሩ ደብረ ዘይት ከሚገኘው አየር ሀይል እሳት ማጥፊያ እስከሚደርስ ድረስ የተነሳውን እሳት ማጥፋት አለመቻሉን የአይን እማኞች ተናግረዋል፡፡
ለአንድ ሰዓት ያህል በቆየው የእሳት አደጋ ግምታቸው ከፍተኛ የሆነ ማሽኖች ላይ ጉዳት እንደደረሰ የታወቀ ሲሆን ከአራት ቀናት በፊት መንግስት በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የገዛቸው ማሽኖች በፋብሪካው ገብተው እንደነበረ ታውቋል፡፡

በይዘቱ ወቅታዊ የቴሌ-ኮንፍረንስ ስብሰባ – የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት ደጋፊ ግብረ ኃይል



ጋባዥ፥ የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት የሰሜን አሜሪካ ግብረ ኃይል
ተጋባዥ፥ ኢትዮጵያውያን ሚዲያዎች በሙሉ

በስብሰባው ላይ የሚገኙት የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች፥

1) የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ – የአንድነት ፓርቲ ም/ሊቀመንበር እና የፓርላም አባል.
2) ስቶ በላይ በፍቀዱ – የአንድነት ፓርቲ ላዕላይ ምክር ቤት አባል , የፍኖተ ነፃነት ኢዲቶሪያል ቦርድ ሰብሳቢ እና የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት ግብረ ኃይል ዋና አስተባባሪ

በኢትዮጵያችን በአገር አቀፍ ደረጃ በመካሄድ ላይ በሚገኘው የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት ዘመቻ እእንዲሁም በቀጣዩ የነፃነት እና የዴሞክራሲ ትግላችን ላይ እነዚኽ የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ባልደረቦች በቴሌ-ኮንፍረንስ ከኢትዮጵያውያን ጋር ውይይት ስለሚያደርጉ የውይይቱ ተሳታፊ እንድትሆኑ የሰሜን አሜሪካ የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት ዘመቻ ግብረ ኃይል በአክብሮት ጋብዞዎታል። የአንድነት ፓርቲ መሪዎችን ጥያቄዎች መጠየቅ ይችላሉ።

በዚኽ ቴሌ-ኮንፍረንስ ከተጋበዙት ሚዲያዎች ውስጥ ጥቂቶቹ፥

1) ፓልቶክ ሚዲያዎች፥ ቃሌ፣ ሲቪሊቲ እና ከረንት አፌር
2) ሪዲዮ እና ቴሌቪዥን ስርጭቶች፥ የአሜሪካ ድምጽ (አማርኛ፣ ትግሪኛ እና ኦሮምኛ ፕሮግራሞች)፣ ኢሳት ቴሌቪዥን እና ሬዲዮ፣ የጀርመን ሬዲዮ ጣቢያ፣ የዲሲ እና ሌሎች የኢትዮጵያ ሬዲዮኖች በሰሜን አሜሪካ በሙሉ
3) ድረገጾች፥ ዘሐበሻ፣ ኢትዮሚዲያ፣ ኢትዮሚዲያ ፎረም፣ አቦጊዳ፣ ኢትዮሪቪው፣ አውራምባ ታይምስ፣ ኢካድ ፎረም እና ሌሎች

ቴሌ-ኮንፍረንሱ የሚደረገበት ቀን እና ሰዓት፥

ቀን፥ ቅዳሜ ነሐሴ 25 ቀን 2005 ዓ.ም. (Saturday, August 31, 2013) – ከሁለት ቀኖች በኋል!

ሰዓት፥ ከቀኑ 1፡00 ሰዓት (1:00 PM Estern Time)

በቴሌ-ኮንፍረንሱ ለመሳተፍ፥ (267) 507-0240 ይደውሉ እና 20-18-20 ኮድ ይጠቀሙ

ውድ የድረገጾች አስተናጋጆች፥

የጊዜ እጥረት እየተፈታተነን ነው። ስለዚኽ ይኽን ጥሪ በድረገጾቻችሁ ላይ በማውጣት የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባኛል የሚል ወገናችን ሁሉ ስለቴሌ-ኮንፍረንሱ እንዲያውቅ እንድታደርጉልን በአክብሮት ትብብራችሁን እንጠይቃለን። ለቴሌ-ኮንፍረንሱ ሁለት ቀኖች ብቻ ስለቀሩን ጥሪው እንደደረሳችሁ በድረገጾቻችሁ እንደምታሰፍሩልን ተስፋ እናደርጋለን።

እስከዚያ በአክብሮት መልካሙን እንመኛለን!

Teleconfernce

ምንጭ ፍኖተ ነፃነት

Tuesday, August 27, 2013

የአንድነቶች ሰላማዊነት ጽናት በባሌ ሮቤ እና በፍቼ ኦሮሚያ! (ግርማ ሞገስ)

ሰኞ ነሐሴ 20 ቀን 2005 ዓ.ም. (August 26, 2013)

“አንድነት ፓርቲ ሳይገድል እየሞተ ህገ-መንግስቱን የማስከበር ሰላማዊ ትግሉን አጠንክሮ ዛሬም ወደፊትም ይቀጥላል፡፡” የሚለውን መርሃቸውን አንድነቶች ካስተዋወቁን ከርመዋል። ባለፈው ሳምንት በባሌ ሮቤ እና በፍቼ ኦሮምያ የተተከሉት መረን የለቀቁ አምባገነን አስተዳደሮች እና ደህንነቶች የፈጸሙባቸውን ወደር የለሽ የአንደበት፣ የሳይኮሎጂ እና የአካል ጥቃት በፈገግታ በመቀበል እየሞቱ ሳይገድሉ በሰላማዊ ትግል ህገ-መንግስቱን ለማስከበር ያላቸውን ጽናት ደግመው አሳይተውናል አንድነቶች። አንድነቶች የሚሰብኩትን የሚፈጽሙ መሆናቸውን ኢትዮጵያ እንደገና ባለፈው ሳምንት ተመልክታለች። የባሌ ሮቤ እና የፍቼ አምባገነን አስተዳዳሪዎች እና ደህንነቶች አረመኔነት አሳፋሪ ነበር። በፍጹም የስልጣኔ አየር የነፈሰባቸው አይመስሉም። ዘመናዊ አስተሳሰብ ለአንድ ቀንም የጎበኛቸው አይመስሉም። ይባስ ብሎ የባሌ ሮቢ እና የፍቼ አስተዳዳሪዎች እና ደህንነቶች ከህጋዊ የመንግስት መዋቅር ውጪ ጸረ-ነፃነት ወረበሎች (ቦዘኔዎች) ያደራጁ ይመስላሉ። ይኽ ጉዳይ ጥናት ሊደረገበት ይገባል።

በባሌ ሮቢ ኦሮሚያ ያየነው አፈና እስከአሁን በሰሜን ኢትዮጵያ እና በደቡብ ኢትዮጵያ ካስተዋልናቸው አፈናዎች ሁሉ ዘግናኝ ነበር። የመቀሌው አፈና የተፈጸመው የድምጽ ማጉያ በመከልከል፣ የመቀስቀሻ በራሪ ወረቀቶችን በመንጠቅ፣ እና አንድነቶችን በማሰር እንደነበር እናስታውሳለን። የባሌ ሮቤ አምባገነኖች ግን ህውሃት በመቀሌ የፈጸመውን በሙሉ ቢፈጽሙም የአንድነቶችን በታጋሽነት እና በጽናት የታነጸ ሰላማዊ ትግል ሊያቆሙት አለመቻላቸውን ሲገነዘቡ ተራ ማስፈራራት ጀመሩ። ሐሙስ ነሃሴ 16 ቀን 2005 ዓ.ም. የአንድነት ፓርቲ ተወካዮች ከባሌ ሮቤ ከተማ ከንቲባ፣ ምክትል ከንቲባ፣ የፀጥታ ዘርፍ ሃላፊ እና ከከተማው ካቢኔዎች ጋር 3 ሰዓት የፈጀ ውይይት አደረጉ። በዚኽ ውይይት ላይ ነበር የባሌ ሮቢ ባለስልጣኖች “አንድነት ሰላማዊ ሰልፉን ማድረግ አይችልም፤ እኛ ከፍተኛ የሆነ የፀጥታ ስጋት አለብን፡፡ የቀድሞው ጠ/ሚር አቶ መለስ በፓርላማ እንደተናገሩት በአካባቢያችን የአልቃይዳ ክንፍ አለ” የሚል ማስፈራሪያ አዘል በማሰማት ለሰላማዊ ሰልፉ ትብብር መንፈጋቸውን የገለጹት። እሁድ በተቃረበ ቁጥር የባሌ ሮቤ አምባገነኖች ማስፈራሪያ እና ዛቻ ግለቱ እየጨመረ ቢሄድም አንድነቶችን ሊያስቆም አልቻለም። በዚኽን ጊዜ “እሁድ የገበያ ቀን ስለሆነ ሰልፍ ማድረግ አይቻልም። ሰላማዊ ሰልፍ ከተደረገ ደም ይፈሳል።” ማለት ጀመሩ የባሌ ሮቢ ባለስልጣኖች።

የአንድነቶችን ጽናት፣ ትዕግስት፣ ሰላማዊነት እና ቁርጠኛነት መስበር እና ሰልፉን ማሰናከል አለመቻላቸውን ሲገነዘቡ የባሌ ሮቤ ባለስልጣናት ቅዳሜ ምሽት ለእሁድ አጥቢያ የአንድነት ፓርቲ አመራሮች እና አባላትን ካረፉበት ሆቴል በግዳጅ አስወጥተው አገቱ። በዚኽን ጊዜ ነበር የቀሩት አንድነቶች ሰላማዊ ሰልፉ እንዳይደረግ የወሰኑት። የመጣው ይምጣ ብሎ ሰልፍ በመውጣት በመሃይም አምባገነኖች የሰለጠነ የሰላም ትግል ሰራዊት ማስመታት ስህተት ነው። ሰላማዊ ሰልፉ እንዲቀር መደረጉ ትክክለኛ ውሳኔ ነው። በድስፕሊን የታነጹ ሰላማዊ ትግል መሪዎች ገና ዘመቻውን ሲጀምሩ መቼ ማቆም እንዳለባቸውም ጭምረው ያውቃሉ። ይኽ ብስለት ያላቸው ጀግኖች የሚያደርጉት ማፈግፈግ ነው። በዚኽ አይነት ነበር እሁድ ቀን ነሐሴ 19 ቀን 2005 ዓ.ም. በባሌ ሮቤ የታቀደውን የሚሊዮኖችን ድምጽ ለነፃነት ዘመቻ የታፈነው። በዚኽ አይነት ነበር በባሌ ሮቤ አካባቢ አለ ሲሉን የነበረው ሽብርተኛ የአልቃይዳ ቅርንጫፍ እራሳቸው የባሌ ሮቤ ባለስልጣኖች መሆናቸውን ያረጋገጡልን። ይኽ ሁሉ ሲፈጸም የባሌ ሮቤ ወጣቶች ከአንድነት ፓርቲ ጎን መቆማቸውን ኢትዮጵያችን ልታውቅ ይገባል።

ፍቼ ሌላዋ ከተማ ናት። የመጀመሪያው ሁለት አባላትን ይዞ ፍቼ የገባው የሰላማዊ ሰልፍ ቅስቀሳ ቡድን በፍቼ አስተዳደር እና ደህንነት ካድሬዎች ከፍተኛ ድብደባ ተፈጸመበት። የእጅም የእግርም ጉዳቶች ደርሰባቸው ሁለቱ የዴሞክራሲ ሰራዊቶች። አንድነቶች በደረሰው ጥቃት አልተፈቱም። እንዲያውም ጊዜ ሳያባክኑ አዲስ ቡድን ወደ ፍቼ በመላክ ለነሐሴ 19 ቀን ያቀዱትን የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት ዘመቻ ለማሳካት ጎንበስ ቀና ማለት ጀመሩ። በዚኽ እርምጃቸው አንድነቶች በማይነቃነቅ ድስፕሊን የታነጹት የሰላማዊ ትግል ሐዋርያት መሆናቸውን ለፍቼ ህዝብ አሳዩ። እየሞቱ ሳይገሉ ህገ መንግስታዊ መብት ለማስከበር ያላቸውን ቁርጠኛነት አንድነቶች አስመሰከሩ። አንድነቶች የሚሉትን የሚፈጽሙ የሰብዓዊ መብቶች አስከባሪ ወታደሮች መሆናቸውን ፍቼዎች በአድናቆት አስተዋሉ። ይኽን ያስተዋሉት የፍቼ ወጣቶች ለአንድነቶች ትብብር መለገስ ጀመሩ። የፍቼ አስተዳደር እና ደህንነቶች ያሰማሩዋቸው ቦዘኔዎች በፍቼ ከተማ የሚገኘውን የአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት ለመስበር ሲሞክሩ የፍቼ ወጣቶች ድርጊቱን በመቃወም ከአንድነቶች ጎን ተሰለፉ። በፍቼ የተደረገው ሰላማዊ ሰልፍም ቢሆን በአንድነቶች እና በፍቼ ወጣቶች ሰላማዊነት እና ጽናት የተገኘ እንደነበር ኢትዮጵያ በአድናቆት አስተውላለች።

ሶስተኛው የእሁድ ነሃሴ 19 ቀን 2005 የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት ዘመቻ እቅድ በአዳማ/ናዝሬት ከተማ ማድረግ እንደነበር ይታወቃል። ይሁን እንጂ የአዳማ ከተማ አስተዳደር ከአንድነት ፓርቲ ለተጻፈለት ደብዳቤ ነሃሴ 19 በከተማው ስብሰባ መኖሩ እና የኃይል እጥረትም እንዳለበት ጠቅሶ ሰላማዊ ሰልፉን አንድነት ፓርቲ ወደ ጷጉሜ 3 ቀን 2005 ዓ.ም እንዲያዛውር ጠይቋል። አንድነት ፓርቲም የቀረበለትን ጥያቄ መቀበሉን ገልጿል። የአዳማ/ናዝሬት ከተማ አስተዳደር ህገ መንግስታዊ እውቅና ካለው አንድነት ፓርቲ ጋር በዚኽ አይነት ስልጡን እና ተራማጅ መንገድ ከስስምምነት መድረሱ ከባሌ ሮቤ እና ከፍቼ ከተማዎች አምባገነን አስተዳዳሪዎች ፍጹም የተለየ አድርጎታል። ከሁለቱ ከተሞች አስተዳደሮች የአዳማ ከተማ አስተዳደር የተሻለ መሆኑን ኢትዮጵያ ብቻ ሳትሁን አልመ አስተውሏል። በዚኽ እርምጃው የአዳማ/ናዝሬት አስተዳደር ሊመሰገን ይገባዋል። ሊኮራም ይገባዋል። ኋላቀሮቹ የባሌ ሮቤ እና የፍቼ አምባገነን አስተዳደሮች ሊያፍሩ ይገባል። የሚያስተዳድሩትን ህዝባቸውን በንቀት አፍነውታል። እነዚህን ሁለት ከተሞች ለጉብኝትም ሆነ ለንግድ የሚጓጉ ከተሞች እንዳይሆኑ አድርገዋል እነዚህ አስተዳዳሪዎች። የሚያስተዳድሩትን ህዝብ እና የቀረውን አለም ይቅርታ ሊጠይቁ ይገባል። በእነዚህ እና በመሳሰሉት ከተሞች ላይ ለዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ የሚፈሰው ገንዘብ ከምንጩ ቁጥጥር ሊደረግበት ይገባል። ከምንጩ ስል ለጋሽ አገሮችን ይጨምራል። ተዳባዳቢነት ዴሞክራሲያዊነት አይደለም! መሃይምነት ነው።

ለአንባቢያን፥

“እየሞትን ሳንገድል ህገ-መንግስት የማስከበር ሰላማዊ ትግላችንን እንቀጥላለን” የሚለው የአንድነቶች መርህ ከምራቸው እንደሆነ ባልፈው ሳምንትም አስተውለናል። ፍጹም ሰላማዊነታቸው እና የመርህ ጽናታቸው በሚፈጸምባቸው የአካል ድብደባ እንደማይነቃነቅ ፍቼ ላይ አይተናል። በዚኽ ባለፈው የፈተና ሳምንት አንድነቶች መኪና በመከራየት፣ ወረቀቶች በማሳተም፣ ለህክምና ወጪ ባማድረግ እና ለተለያዩ ጉዳዮች ብዙ ወጪዎች እንዳደረጉ መገንዘብ አያዳግትም። ትግሉ የጋራ በመሆኑ ቋሚ ተመልካች መሆን ያዳግታል። የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናል ለምንል በሙሉ የዳር ተመልካች መሆን ያዳግተናል። በባሌ ሮቤ እና በፍቼ በአንድነቶች ላይ የደረሰውን አይተን እና ሰምተን እጃችንን አጥፈን መቀመጥ ህሊናችንን ያዳግተዋል። የዜግነት ሚና መጫውት ያልጀመርን መጀመር፣ የጀመርን ደግሞ መቀጠል አለበን። ተሳትፎዋችንን ማሳደግ አለብን። አንድነቶች አንድም ክፉ ቃል ሳይሰነዝሩ እና ፈገግታ ከፊታቸው ሳይለያቸው ይኽን ሁሉ ስቃይ የሚቀበሉት ለግላቸው ብር ለማካበት እንዳልሆነ ግልጽ ነው። እየሞቱ ሳይገድሉ በአምባገነነኑ መለስ የረቀቀውን ፀረ-ሽብር ህግን ለማሰረዝ እና የኢትዮጵያችንን የፖለቲካ ትግል ባህል ለመቀየር እንደሆነ ልቦናችን ያውቀዋል። ስለዚህም አንድነቶች የጀመሩትን የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት ዘመቻ በመቀላቀል ታሪክ እንስራ። የሚከተሉትን በማድረግም አንድነቶች መሰራት የጀመሩትን ታሪክ መቀላቀል እንችላለን።

እርዳታ፥ በገንዘብ!
እርዳታ፥ በአሳብ!
እርዳታ፥ መረጃዎች በፍጥነት በማሰራጨት!
እርዳታ፥ ፊርማዎች በማሰባሰብ!
እርዳታ፥ እንደገና በገንዘብ!

ፊርማ ለማስቀመጥም ሆነ ገንዘብ ለመላክ ይኽን የአንድነቶች ድረ ገጽ ይጎብኙ፥ www.andinet.org

Sunday, August 25, 2013

መንግስት የሙት ዓመትና ተዝካር ማሇት ትቶ ትኩረቱን ሇሀገራዊ መግባባት ቢሰጥ ግርማ ሠይፉ ማሩ

ግርማ ሠይፉ ማሩ
ሙት ዓመትና ተዝካር የሚያወጣ መንግሰት ያየሁት የኛው ጉዴ የሆነው በስሌጣን ሊይ ያሇው ፓርቲ መሆኑን መጠራጠር ያሇብን
አይመስሇኝም፡፡ ፋውንዳሽኑ እንጂ የመንግሰት አይዯሇም የሚሌ ማምታቻ እንዯማይሰራ ከዚሁ ማሰጨበጥ ያስፈሌጋሌ፡፡ ሌክ ነው
የአንዯኛ ዓመት መታሰቢያ በአንዴ አዲራሽ ቢታሰብ ክፋቱ አይታየኝም፡፡ ነገር ግን ሁለም የመንግስት መዋቅር የ”ሕዝብ” ተወካዮች
ምክር ቤቱን ሰራተኞቹን ጨምሮ የሙት ዓመት ሇማክበር የመንግሰት ሰራ አቋርጠው ችግኝ ተከሊ ወይም የሻማ ማብራት ሰነ ስርዓት
ሊይ መገኘት ተገቢም ትክክሌም አይመስሇኝም፡፡ ከሁለም የሚገርመው በሙት ዓመት ሊይ ሇመገኘት ወዯ ሀገራችን የመጡት መሪ
ተብዬዎች እና ተወካዮች ናቸው፡፡ እርግጥ ነው የሱዲኑ ፕሬዝዲንት ከሸሪክ አንባገነን ሀገሮች ውጭ መሄዴ ስሇማይችለ የእርሳቸው ጉዞ
በእውነቱ አጋጣሚውን ተጠቅሞ ወጣ ሇማሇት ብሇን በቅንነት ሌንወስዯው እንችሊሇን፡፡ የሚያሳዝነው ይህን ጉዲይ ብሇው የመጡ
መሪዎችን ሇመቀበሌና ሇመሸኘት በሚዯረግ ሸብ-እረብ ዜጋው የገጠመው ሰቃይ ነው፡፡ ሁለም እንዯሚረዲው የአዱሰ አበባ ከተማ
በአጭሩ ሉቃሇሌ በማይችሌ የትራንስፖርት አገሌግልት ቅርቃር ውስጥ ትገኛሇች፣ በዚህም ሊይ በተሇያየ የመንገዴና የባቡር ግንባታ
ምክንያት ከፍተኛ የትራፊክ ፍሰት ችግር አሇ፡፡ እዚህ ሊይ ነው እንግዱህ ሰራ ፈት መሪዎች ሙት ዓመት ብሇው መጥተው ከተማዋ ሊይ
ጫና ፈጥረው በእንቅርት ሊይ ጆሮ ዯግፍ ያሰኙን፡፡
በነገራችን ሊይ የሙት ዓመቱ ፕሮግራም በባሇቤትነት የሚመራው “የመሇስ ፋውንዳሽን” የሚባሇው ሲሆን ይህ ፋውንዳሽን ሲቋቋም
በግሌፅ ያራዴኩት አቋም “በፋውንዳሽኑ ምስረታ የመንግሰት እጅ መኖሩ ተገቢ እንዲሌሆነ” ነበር፡፡ ይህ ፋውንዳሽን አሁንም ቢሆን
እጁ ረጅም እንዯሆነ የሚያመሊክተው ሁለም ክሌልች፣ ሁለም የመንግሰት መዋቅሮች፣ በእርግጥ ጥቃቅኖችን ጨምሮ ሰራቸውን
አቁመው በሙት ዓመት በዓሌ ሊይ ሽርጉዴ ሲለ ነበር፡፡ ይህ የፋውንዳሽኑ ቦርዴ ስብሳቢ የቀዴሞዋ ቀዲማዊት እመቤት በመግሇጫ
እንዯነገሩን በፈቃዯኝነት ሊይ ተመስርቶ ብቻ እንዲሌሆነ ያሳብቃሌ፡፡ ከወር በፊት ስሇ በዓለ አከባበር መግሇጫ ሲሰጡ በፈቃዯኝነት
ተመስርቶ ሲለ ሇማመን ፈሌጌ ነበር፤ በቀበር ስነስርዓት ወቅት በተፈጠረው ትርምስ ቅር ተሰኝተው ትምዕርት ወስዯው ይሆናሌም
በሚሌ ታሳቢ ማሇት ነው፡፡ ነገር ግን ጉዲዩ ውስጠ ወይራ ኖሮዋሌ፡፡ ጦጢት አንበሳን “አሌበሊምን ምን አመጣው” እንዲሇቸው፤
በፈቃዯኝነት ሊይ ተመስርቶ ስንባሌ፣ “ፈቃዯኝነት” የሚሇውን ምን አመጣው ማሇት ነበረብን፡፡
የመንግሰት አገሌግልት ሰጪ ተቋማት ኔት ወርክ የሇም በሚሌ የሚያቋርጡት አገሌግልት ትዕግሰታችንን እየተፈታተነው ባሇበት ወቅት፣
ሇሙት ዓመት ችግኝ ተከሊ እና ሻማ ማብራት አገሌግልት ማቋረጥ ይህ ሙት ዓመት ሇማይመሇከተን ዜጎች ምንዴነው ማካካሸው?
ብሇን ጠይቀን ማሇፍ ተገቢ ነው፡፡ መሌስ ሰጪ ባይኖርም፡፡ ይህ ብቻም አይዯሇም የመንግሰት ተቀጣሪ ሠራተኞች የፓርቲ አባሊት
በመሆናቸው የተነሳ በስራ ሰዓት የፓርቲን ተግባር ሇማከናወን እና የፓርቲውን ስሌጠና ሇመውሰዴ ከህግ ውጭ በስራ ገበታቸው ሊይ
እንዯማይገኙ ተጨባጭ መረጃዎች አለን፡፡ መንግሰትና ፓርቲ ተቀሊቅሇው ማሇያየቱ ችግር ሆኖ ባሇበት ወቅት ሶስተኛ ተዯራቢ
“ፋውንዳሽን” የሚባሌ ነገር መጥቶ ላሊ ዝብርቅርቅ እየፈጠረ ነው፡፡
የሰሞኑ ችግኝ ተከሊ በየዓመቱ በሀገራችን ክረምት ሲገባ የሚዯረገውን ዘመቻ (ሰኔ መጨረሻ አካባቢ ጀምሮ) ተክቶ ከሙት ዓመት በዓለ
ጋር እንዱገናኝ በማሇት ወዯ ነሐሴ አጋማሽ ተገፍቶ መምጣቱን ሊስተዋሇ፣ ይህ የችግኝ ተከሊ ጊዜ መዘግየት በችግኙ መፅዯቅ ሊይ
የሚያመጣው ጫና ባሇሞያዎች ሉያዩት ይችሊለ፡፡ ነገር ግን ዝናቡ መውጫው ስሇተቃረበ ሰር ያሌያዙት ችግኞች የመዴረቅ ዕዴሊቸው
ሰፊ መሆኑን ሇማወቅ ባሇሞያ መሆን የሚጠይቅ አይመስሇኝም፡፡ ዝናብ በወጣበት የሚዘራው ምስርና ሽንብራ የመሳሰለት ናቸው፡፡
እዚህ ሊይ በኢቲቪ የችግኝ ተከሊው ሊይ የተገኙት ሰዎች በሙለ እንዯወትሮ ተመሊሌሰን እንክብካቤ እናዯርጋሇን ሲለ የተዯመጡ ሲሆን
አንደ አስተያየት ሰጪ “በራሴም ትራንስፖርት መጥቼም ቢሆን የተከሌኩትን ችግኝ አየዋሇሁ” የሚሌ አሰተያየት ሲሰጥ ከጎኔ ቁጭ ብል
የነበረ አንዴ ሰው “እንኳን ይሄን ችግኝ ሌትከታተሌ የታመመ ዘመዴህንም ተመሊሌሰህ አትጠይቅም” ብል እውነትነት ያሇው ሃሳብ
ሲሰነዝር ፈገግ ማሇታችን አሌቀረም፡፡ በዚሁ አጋጣሚ አንዴ የእግረ መንገዴ ጥያቄ ትተን እንሇፍ፡፡ ተመሊሌሰው ችግኝ ሇመንከባከበው
ያቀደት ችግኝ ተካዮች ወዯ ችግኙ ሲሄደ ውሃ በጀሪካን፣ ማዲበሪያ ነገር/ፍግም ሉሆን ይችሊሌ/ በኪስ ወረቀት፣ወዘተ ይዘው ነው
ወይስ እንዳት ነው ክትትሌ የሚያዯርጉት?
በሀገራችን የተተከለት በብዙ ሚሉዮን ችግኞች በእንክብካቤ እጦት መፅዯቅ ሳይችለ የቀሩ ቢሆንም በዚሁ አጋጣሚ ሇቀዴሞ
ጠቅሊያችን ተብል እንክብካቤ ማዴረግ ከተቻሇ በእውነቱ ከዚህ በኋሊ የሚተከለት በሙለ በእርሳቸው ስም ቢተከሌ እኔም ወጥቼ
ሌተክሌ እችሊሇሁ፡፡ ሇማነኛውም በቅርቡ በዚሁ አጋጣሚ የሰማሁት የዯን ሽፋናችን ወዯ አሰራ አንዴ በመቶ መዴረሱን ስሰማ በእውነቱ
ዯስ ያሇኝ ሲሆን የአስራ አንዴ በመቶ ግጥምጥሞሽ ግን ግርምታን ፈጥሮብኛሌ፡፡ በክሌሌ አስራ አንዴ የሚመራው ነገር ሁለ አስራ አንዴ
በመቶ የአኬር ቁጥሩ ሳይሆን አይቀርም፡፡ (ሀገሪቱን በዘጠኝ ክሌሌ እና ሁሇት ከተማ አስተዲዯር በዴምሩ በአስራ አንዴ ማዋቀሩ
አጋጣሚ ይሆን ወይስ ይህ አኬር ያሌነው ነገር ነው)፡፡ በዯናችን አስራ አንዴ በመቶ የተገረምኩት ነብስ ካወቅሁ ጀምሮ በሁሇትና ሶስት
በመቶ ተገትሮ የነበረው የዯን ሽፋናችን መሃሌ ሊይ ቁጥር እንዯላሇ ዘል አስራ አንዴ በመቶ በመዴረሱ ነው፡፡ ፈረንጆች አስራ ሦስትን
አይወደም ይባሊሌ፣ እኛ ዯግሞ አስራ አንዴን እንወዲሇን፡፡ከዚሁ ርዕስ ሳንወጣ ክቡር ጠቅሊይ ሚኒስትራችን አቶ ኃይሇማሪያም ዯሳሇኝ ትንሽ ጋብ ብል የነበረውን የታሊቁ መሪ ላጋሲ ዴንገት
ባገረሸ መሌኩ በሙት ዓመት ሊይ ሇማንሳት ሞክረዋሌ በዚህ ንግግር መሃሌ ያስገረመኝ ነገር ቢኖር ኢህአዳግ ፓርቲያቸው በውስጡ
ምንም መንገራገጭ እንዯላሇበት አዴርገው የነገሩን ነገር ነው፡፡ እዚህም ጋ የዚያች ጦጣ “አሌበሊሽምን ምን አመጣው” ትዝ ብልኛሌ፡፡
ኢህአዳግ ውስጥ “ችግር የሇምን ምን አመጣው” ማሇት ይኖርብናሌ፡፡ ችግርማ አሇ የላሇው ችግሩን መፍቻ ጥበቡ ነው ማሇት ያሇብን
ይመስሇኛሌ፡፡ በእውነቱ ኢህአዳግ ስሇማያምነን ነው እንጂ ኢህአዳግ ችግር ውስጥ እንዱገባ ፍሊጎት የሇንም፡፡ ምክንያቱም ጦሱ
ሇሀገራችን ዜጎች ስሇሚተረፍ፡፡ ይህ እንዲይሆን ግን ሀገራችን ኢትዮጵያ ሇእኛም ሀገራችን መሆኗን ተረዴቶ ተመካክረን የምንሰራበት
መንገዴ ማሰብ ይኖርበታሌ፡፡ እንመካከር ስንሌ ሁሇት ነገር ማሇታችን አይዯሇም፡፡ ሙት ዓመት ሇማክበር አብረን እንሁን እና ስሌጣን
አጋሩን ማሇታቸን አይዯሇም፡፡ የእኛ ጥያቄ አጭርና ግሌፅ ነው፡፡ ያሇንን አማራጭ ሇህዝብ ሇማቅረብ እንዴንችሌ የዘረጋችሁትን የአፈና
እና የካዴሬ ስርዓት አዯብ አስገዙሌን፡፡ አማራጫችን በህዝብ ውዴቅ ከተዯረገ እና የአብዮታዊ ዱሞክራሲ መስመር በህዝቡ ይሁንታ
ካገኘ (በካዴሬዎች ማሇት አይዯሇም) ሇመቶ ዓመት መግዛት ትችሊሊችሁ ነው የምንሊችሁ፡፡
በኢህአዳግ ችግር ውስጥ መግባት ዯስተኞች እንዲሌሆንን መረዲት ያሇበት ማነኛውም የኢህአዳግ ባሇስሌጣን አንዴ ነገር እንዱያዯርግ
ጥያቄዬን አቀርባሇሁ፡፡ የአንዴነት ፓርቲ ስሇ ሰሊማዊ ትግሌ ሇአባሊቱ መግሇጫ ሲሰጥ አቅራቢ ሆኖ የቀረበው ጋዜጠኛ እስክንዴር ነጋ
ሲሆን የመዴረክ መሪው ዯግሞ የፓርቲው ምክትሌ ሉቀመንበር አንደዓሇም አራጌ ነው፡፡ የዚህ ፕሮግራም ሲዱ ቅጅ ሇህዝብ እንዱዯርስ
ተዘጋጅቶ በፓርቲያችን እጅ ይገኛሌ፡፡ አቃቢ ህግም ቅጅው አሇው፡፡ የማቀርበው ጥያቄም ሲዱውን ከመጀመሪያ እስከመጨረሻ
እንዴትመሇከቱት ነው፡፡ በዚህ ፕሮግራም ሊይ የተራመዯው ሃሳብ እና የተዯረሰበት ዴምዲሜ ሲጠቃሇሌ እንዱህ የሚሌ ነበር፡፡
“ኢትዮጵያ ሀገራችን ሃምሳ ዓመት ባሌሞሊ ጊዜ ውስጥ ሇሶስተኛ ጊዜ አብዮት ማስተናገዴ አትችሌም፤ መንግሰት ይህ እንዲይመጣ
የማሻሻያ እርምጃ በመውስዴ ሀገራዊ መግባባት ይፍጠር” የሚሌ ነበር፡፡ አሁን ግብፅ ያሇችበት ሁኔታ ሲታይ እነዚህ ወጣቶች ነብይ
ነበሩ ማሇት ይቻሊሌ፡፡ በሀገራችን ባሇው የሌዩነት ብዛት የግብፅ ዓይነት አብዮት ጦሱ የታያቸው፡፡ ይሁን እንጂ ሰሊም ሲሰብኩ ሁሇቱም
ያሇስማቸው ስም ተሰጥቶዋቸው “አሸባሪ” ተብሇው አሁን በእስር ቤት ይገኛለ፡፡ የተረጋገጠ ማስረጃ በእጄ ባይኖርም እነርሱን “አሸባሪ”
ተብሇው እንዱታሰሩ ክስ ሲመሰርቱ ከነበሩት አቃቢ ህጎች አንደ ሀገር ጥል መሰዯደን ሰምቻሇሁ፡፡ ይህ እውነት ከሆነ ብዙ ማስረጃ
እንዯምናገኝ ተሰፋ አዯርጋሇሁ፡፡
ሟች ጠቅሊይ ሚኒስትር መሇስ ዜናዊ በመጨረሻ ባነሳሁት በእነ አንደዓም ጉዲይ እንዱሁም ሀገራችን ሇራቃት ሀገራዊ መግባባት
ዋነኛው ተጠያቂ ቢሆኑም፣ መግቢያዬ ሊይ ያነሳሁትን የሙት ዓመትና የተዝካር እሼሼ ገዲሜን ሇአፍታ ከመቃብር ቀና ብሇው ቢያዩ
በጓድቻቸው እጅግ እንዯሚያዝኑ፣ እንዯሚያፍሩም አሌጠራጠርም፡፡ ይህን እንዴሌ ያዯረገኝ ሰሇ ጠቅሊይ ሚኒስትር፣ ምክትሌ ጠቅሊይ
ሚኒስትር፣ ፕሬዝዲንት፣ እና ላልች ሹማምንትን ስርዓተ ቀበር አስመሌክቶ በእርሳቸው ሰርወ መንግሰት የወጣው ህግ በምንም ዓይነት
ይህን አያመሊክትም፡፡ ይሌቁንም የሞተ ሞቶዋሌ ወዯ ሰራ የሚሌ ዓይነት ነው፡፡ መሌካም አዱስ ዓመት የሰሊም፣ የጤና እንዱሁም
ሀገራዊ መግባባት ሇመፍጠር እረሾ የምናኖርበት ዓመት እንዱሆን ከሌቤ እመኛሇሁ፡፡ ሀገራዊ መግባባት እና መተማመን ከአሸባሪነት ህጉ
በተሻሇ ሇህዝቡ ሰሊም ይሰጣሌ የሚሌ እምነት አሇኝ፡፡ ቸር ይግጠመን፡፡
Source http://www.zehabesha.com Amharic.

ሕወሐት በአዜብ ጉዳይ ተወጥሯል (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

ለስድስት አመት ኤፈርትን ሲመሩ የቆዩት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ከሃላፊነት መነሳት ተከትሎ በሕወሐት ውስጥ ውጥረት መንገሱን ምንጮች አመለከቱ። የኤፈርት ቦርድ ሰብሳቢ በነበሩት ባለቤታቸው አቶ መለስ አማካይነት ዳይሬክተር ተደርገው አዜብ መሾማቸውን ያስታወሱት ምንጮች፣ ከመለስ ሕልፈት በኋላ ቦታውን የተረከቡት ኤርትራዊው ቴዎድሮስ ሃጎስ መሆናቸውን፣ እንዲሁም ዳይሬክተር የመሾምና የመሻር ስልጣኑ የቦርዱ መሆኑን ያስረዳሉ። አዜብ ከኤፈርት እንዲወገዱ የተደረገው ግን በነቴዎድሮስ ሃጎስ ሳይሆን ስብሃት ነጋ ባቀነባበሩት ጣልቃ ገብ ውሳኔ መሆኑን ምንጮቹ ገልፀዋል። በኤፈርት የተለያዩ ተቋማት የሚሰሩ ሰራተኞች አዜብ በመባረራቸው ደስታቸውን እየገለፁ መሆኑን የጠቆሙት ምንጮች፣ አያይዘውም ደስታቸውን በስብሰባ ጭምር ከመግለፅ ባለፈ፥ « አዜብ ከኤፈርት ጀምሮ ለፈፀሟቸው የሙስና ወንጀሎች በሕግ መጠየቅ አለባቸው» በማለት አቋም እስከ መያዝ መድረሳቸውን አስታውቀዋል። ከዚህ በስተጀርባ በበቀለኝነታቸውና የጥፋት ሴራ በማቀነባበር የሚታወቁት ስብሃት ነጋ እንዳሉበትና ከኤፈርት ስልጣናቸው ያስነሷቸውን አዜብ ከጨዋታ ውጭ ከማድረግ ባለፈ በሙስና እንዲጠየቁ በየአቅጣጫው ጫና እያሳደሩ መሆኑን ምንጮቹ አስረድተዋል። በአዜብ ተፈፀሙ ተብለው ከተነሱት የሙስና ወንጀሎች በኤፈርት ስም 200 ከባድ ተሽከርካሪዎች አቶ ነጋ ገ/እግዚያብሄር ቀረጥ ሳይከፍሉ እንዲያስገቡ ማድረጋቸውን፣ በሚሊዮን የሚገመት ቀረጥ ሊከፈልባቸው የሚገቡ የተለያዩ የሕክምና መሳሪያዎች፣ በኤፈርት ገንዘብ ሶስት መርከብ ስሚንቶ የፍራንኮ ቫሉታን ሕግ በመተላለፍ ቀረጥ ሳይከፈልበት አገር ውስጥ መግባቱ፣ ክሶች እንዲቋረጡ ትእዛዝ በመስጠት..የሚሉት በዋነኛነት መነሳታቸውን ምንጮቹ አመልክተዋል። ( አዜብ ከኤፈርት እንደሚነሱ ከዚህ ቀደም በወጡ ዘገባዎች ምንጮችን በመንተራስ መገለፁ ይታወሳል)
 azeb Mrs. corruption
 ይህ በእንዲህ እንዳለ – በአዜብ ቦታ የተተኩት ብርሃነ ኪ/ማርያም (በቅፅል ስማቸው ብርሃነ “ማረት”) ሲሆኑ፣ ከመለስ በፊት የአዜብ ፍቅረኛ የነበሩና ከሱዳን ተያይዘው በመምጣት ሕወሐትን እንደተቀላቀሉ ምንጮች አስታውሰዋል። ድርጅቱን ከተቀላቀሉ ከጥቂት ወራት በኋላ ሁለቱ (አዜብና ብርሃነ) የፍቅር ግንኙነታቸውን እንዲያቋርጡ ከበላይ አመራር መወሰኑን፣ አዜብ ከመለስ ጋር ግንኙነት መቀጠላቸውን ይገልፃሉ። ፓርቲው ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ ብርሃነ በመቀሌ ማዘጋጃ ቤት ተመድበው ሲሰሩ «ለመንገድ ስራ ከተመደበ ገንዘብ አምስት ሚሊዮን ብር ተዘርፏል» በሚል በሙስና እንዲባረሩ መደረጉን ምንጮች ጠቁመዋል። አዲስ አበባ የመጡት ብርሃነ ብዙ ጥረት አድርገው አዜብ ዘንድ (ቤተ መንግስት) የመግባት አጋጣሚ ያገኛሉ። ባቀረቡት አቤቱታና ተማፅኖ መሰረት ሲቪል ሰርቪስ እንዲገቡ አዜብ ትእዛዝ ያስተላልፋሉ። ከኰሌጁ እንደወጡ የማ.ረ.ት. ሃላፊ ተደርገው በመለስ የተሾሙት ብርሃነ፣ በተለይ ከ1993ዓ.ም በኋላ የመለስ ቀኝ እጅ በመሆን በአውሮፓና አሜሪካ ያለውን የፓርቲውን መዋቅርና ስለላ በመምራት፣ አምባሳደሮችን በማስፈራራት፣ በማዘዝና ፈላጭ ቆራጭ ውሳኔ በማሳለፍ ታማኝ አገልጋይ ሆነው እንደቆዩ ያስታወሱት ምንጮች፣ ከመለስ ሞት በኋላ ግን የስብሃት ነጋ ተከታይና አስፈፃሚ በመሆን አሰላለፋቸውን ቀይረው እንደቀጠሉ አያይዘው ገልፀዋል። ስብሃትና ብርሃነ ዝምድና እንዳላቸው የጠቆሙት ምንጮች፣ አዜብን በማስነሳት ብርሃነ እንዲቀመጡ ያደረጉት ስብሃት መሆናቸውን አመልክተዋል።
ምንጭ የኢትዮጵያ ሜዲያ ሙድረክ

Saturday, August 24, 2013

ሰማያዊ ፓርቲ በመብራት ሀይል ሊያካሂድ የነበረውን ስብሰባ በጽ/ቤቱ ሊያደርግ ነው

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
“አዳራሽ መፍቀድ ያለበት ባለቤቱ እንጂ መስተዳድሩ አይደለም” 
ሰማያዊ ፓርቲ ነገ መብራት ሀይል አዳራሽ ሊያካሂድ የነበረውን ህዝባዊ ስብሰባ በፅህፈት ቤቱ ለማድረግ ወሠነ፡፡ ፓርቲው በአዳራሹ ህዝባዊ ስብሰባ እንዳላካሂድ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስብሰባና ሠላማዊ ሠልፍ ማሳወቂያ ክፍል እንቅፋት ሆኖብኛል ብሏል፡፡ 
የመስተዳድሩ የስብሰባና ሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያ ክፍል ሀላፊ አቶ ማርቆስ ብዙነህ በበኩላቸው፤ የመሰብሰቢያ አዳራሽ የመፍቀድ መብት የባለ አዳራሹ እንጂ የመስተዳድሩ አይደለም ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ 
ፓርቲው “የግጭት አፈታት በኢትዮጵያ” በሚል ርዕሰ-ጉዳይ ላይ የመነሻ ሀሳብ እንዲያቀርቡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሳይንስ ፋካልቲ የሳይንስና ቴክኖሎጂ መምህር የሆኑትን ዶ/ር በቃሉ አጥናፉን መጋበዙን ገልፆ፣ አዳራሽ ለመከራየት ሲሄዱ ከአዲስ አበባ አስተዳደር ለስብሰባ ያስፈቀዳችሁበትን ደብዳቤ ካላመጣችሁ አናከራይም መባላቸውን የፓርቲው ፕሬዚዳንት ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ተናግረዋል፡፡ ከምኒልክ ት/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽም ተመሳሳይ ምላሽ ማግኘታቸውን ኢ/ሩ ጨምረው ገልፀዋል፡፡ 
“አዳራሽ ተከለከልን ብለን ፕሮግራማችንን አናስተጓጉልም” ያሉት ኢ/ር ይልቃል፤ ህዝባዊ ስብሰባውን በፓርቲው ጽ/ቤት ለማካሄድ መወሰናቸውን ተናግረዋል፡፡ 
ከዚህ ቀደም ለሌሎች ፓርቲዎች የመስተዳድሩ ማሳወቂያ ክፍል ደብዳቤ ፅፎላቸው ስብሰባቸውን ማከናቸናቸውን የገለፁት የፓርቲው ፕሬዚዳንት፤ ለእኛ ጊዜ መስተዳድሩ ደብዳቤ አለመፃፉ ሆን ተብሎ የፓርቲውን እንቅስቃሴ ለመግታት የተደረገ ነው ሲሉ አማረዋል። 
የመስተዳድሩ የስብስብና ሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያ ክፍል ሀላፊ ግን በሰዎች አዳራሽ አያገባንም፤ ለአዳራሽ የከፈላችሁበትን ደረሰኝ አምጡ ማለታችን ትክክለኛ የአሰራር አካሄድ ነው ብለዋል፡፡ 
ስማቸውን መግለፅ ያልፈለጉ የመብራት ሀይል አዳራሽ የስራ ሀላፊ ግን በእስከዛሬው አሰራራቸው ከመስተዳድሩ ህጋዊ ስብሰባ ማካሄጃ ፈቃድ ሲያገኙ ብቻ አዳራሹን እንደሚያከራዩ ገልፀው፤ ሰማያዊ ፓርቲ ይህን ደብዳቤ ሊያቀርብ ባለመቻሉ አዳራሹን ለማከራየት መቸገራቸውን ተናግረዋል፡፡ 
በተያያዘ ዜና፤ ሰማያዊ ፓርቲ ነሀሴ 26 የሚያካሂደውን ሁለተኛውን ሰላማዊ ሰልፍ ለመስተዳድሩ የስብሰባና ሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያ ክፍል ማሳወቂያውን ካስገባ በኋላ በምን ዙሪያ፣ የትና እነማን ሰልፉን እንደሚያካሂዱት በደብዳቤ እንዲገልፅ ተጠይቆ በደብዳቤ ምላሽ መስጠቱን ገልጿል፡፡
ምንጭ አዲስ አድማስ

የኢህአዴግ ባለስልጣኖችና ደጋፊዎች ከየትኛውም ዜጋ በላይ ዋስትና እንደሚፈልጉ በመግለጽ ዶ/ር ተጋ ለንዳዶ ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ተናገሩ። በአገራቸው ጉዳይ …

“አገራችንን በእርቅ እንታደጋት” ዶ/ር ተጋ "ዋስትና የናፈቃቸው ባለስልጣናት አሉ"

August 24, 2013 03:00 am By  
የኢህአዴግ ባለስልጣኖችና ደጋፊዎች ከየትኛውም ዜጋ በላይ ዋስትና እንደሚፈልጉ በመግለጽ ዶ/ር ተጋ ለንዳዶ ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ተናገሩ። በአገራቸው ጉዳይ ላይ በተለይም በዕርቅ ዙሪያ በርካታ ጽሁፎችን ሲያቀርቡና ሲንቀሳቀሱ የቆዩት ዶ/ር ተጋ ለንዳዶ በኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ዙሪያ በኃላፊነት ሲሰሩ የቆዩ ሲሆን ከአገራቸው ውጪም በኬንያ፣ በሞዛምቢክ፣ በስዊትዘርላንድና በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች በከፍተና ኃላፊነት ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡ በተለይም በዎርልድ ቪዥን፣ በተባበሩት መንግሥታ፣ በዓለምአቀፍ አብያተክርስቲያናት ካውንስል፣ … የሰጡት የዓመታት አገልግሎት ተጠቃሽ ነው፡፡ በአገር ውስጥና በውጪ አገራት የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ከፍተኛ ትምህርታቸውን የተከታተሉት ዶ/ር ተጋ በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው የዕርቅ፣ የሰላምና የፍትሕ ሒደት ውስጥ የተጫወቱት መጠነኛ ሚና በአገራቸው ተግባራዊ ሆኖ ለማየት የሚመኙና ለዚያም የሚቻላቸውን ጥረት ሁሉ ሲያደርጉ መቆየታቸው እስካሁን የሠሩት ሥራ ምስክር ነው፡፡ ከዚህም ሌላ ዶ/ር ተጋ ለንዳዶ የአገር ውስጥና የውጭ ስድስት ቋንቋዎችን አቀላጥፈው የሚናገሩ ናቸው፡፡
“እውነተኛ እርቅ የሚያስፈልግበት ወቅት ላይ ነን” የሚሉት ዶ/ር ተጋ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በመረዳት አገራችን ከምትገኝበት አደጋ መታደግ የሁሉም ዜጋ ግዴታ እንደሆነ አመልክተዋል። በማያያዝም በደል ሲበዛ ህዝብ እንደሚያምጽ በመጠቀስ ሳይረፍድ ሁሉም ወገኖች ለእርቅ ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ጠይቀዋል።
እርቅና ሰላም ለማውረድ የሚችሉ ዜጎች አድፍጠው መቀመጣቸውን የጠቆሙት ዶ/ር ተጋ “የፖለቲካ መናኞች” ያሉዋቸውን እነዚህ ዜጎች ከተደበቁበት በመውጣት ባገራቸው ጉዳይ ተሳታፊ ሊሆኑ እንደሚገባ አሳስበዋል።
እውነተኛ እርቅ ቢጀመርና፣ ለማስታረቅ የሚመጥን ስብእና ያላቸው ወገኖች የሚካተቱበት አስታራቂ ቢሰየም ህዝብ እውቅና ለመስጠት እንደማይቸገር ያስታወቁት ዶ/ር ተጋ “ከኢህአዴግ ወገን እርቅ የሚፈልጉና ለልቡናቸው የቀረቡ ሰዎች አሉ። እነሱም ሰው ናቸውና ሰላም ይፈለልጋሉ። ራሳችሁን መናኝ ያደረጋችሁ ከተደበቃችሁበት ውጡና ኢትዮጵያን እናድን” ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል። ሙሉ ቃለ ምልልሳቸው እንደሚከተለው ተቀናብሯል።
ጎልጉል፦ በተደጋጋሚ ስለ እርቅ ይናገራሉ። በርግጥ መፍትሔ ይኖረዋል?
ዶ/ር ተጋ፦ ከእርቅ ውጪ ምንም አማራጭ የለም። አለ?
ጎልጉል፦ አሁን ኢህአዴግ ከያዘው አቋም አንጻር “እርቅ ዋጋ የለውም” የሚሉ አሉ፤
ዶ/ር ተጋ፦ ስለነዚህ ወገኖች በተለይ የምለው ነገር የለም። በኔ እምነት እርቅ፣ ትክክለኛው የእርቅ መንገድ ተሞክሯል የሚል እምነት የለኝም። ስለዚህ ትክክለኛው እርቅ፣ እውነተኛው አርቅ መሞከር አለበት። እኔ እንደምረዳው ከሁሉም ወገን ትክክለኛ እርቅ ከቀረበ ተቀባይ የማይሆንበት ምክንያት የለም።
ጎልጉል፦ትክክለኛ እርቅ ሲሉ ምን ማለትዎ ነው?
ዶ/ር ተጋ፦ ከፍቅርና የሚመነጭ ፍርሃት ሰዎች አምነው እንዲገዙ ያደርጋቸዋል። ፍርሃት ስል አምነው ለሰየሙት መንግሥት ክብር መስጠትና መገዛትን ነው። በሌላ በኩል ደግሞ መሳሪያ ያላቸውና ህግ ያረቀቁ ክፍሎችም ህዝብን መግዛት ይችላሉ። እነዚህ ክፍሎች እኔን ምሰል። እኔ የምልህን አድርግ። አንተ ቦታ የለህም። የአንተ ድርሻ መገዛትና መገበር ብቻ ነው። አንተ ዝም ብለህ ከመገዛት ውጪ ሌላ ተግባርና ድርሻ የለህም በማለት በጉልበት ይገዛሉ። ልክ አሁን እንደሚደረገው ማለት ነው። በሌላ ወገን “አማራጭ ነን”  ብለው በጉልበት እየገዛ ያለውን ለመገልበጥ የሚታገሉ አሉ። ገለልተኛ ሆነው የሚኖሩና የሸሹ ወገኖች አሉ። እነዚህ የሸሹ ሰዎች “የፖለቲካ መናኞች” ናቸው፡፡ እነዚህ ሁሉ ሌሎችንም አካትቶ ለመታረቅ ሲስማሙ ትክክለኛው እርቅ ይመጣል። ሳይሞከር አይሳካም ማለት አይቻልምና እንሞክረው።
ጎልጉል፦ ያልተቻለው እኮ እነዚህን ወገኖች ማሰባሰብ ነው? በተለይም ኢህአዴግን ወደ እርቅ የሚገፋው ጉዳይ የለም የሚሉም ወገኖች አሉ። ኢህአዴግ ምን አስፈርቶት ወደ እርቅ ይመጣል? የሚሉ አሉ፤
ዶ/ር ተጋ፦ ለጊዜው ሃይል አለኝ ብሎ ከተራራ ላይ አልወርድም። መሳሪያ አለኝና እርቅ አይበጀኝም። ጡንቻ አለኝና ሰላም አያሻኝም በማለት ኢህአዴግ የሚያከር ከሆነ የተጎዱ፣ የተረገጡ፣ የተገፉ፣ የከፋቸው፣ የባሰባቸው ቀኑ ሲደርስ “አታስፈልግም” ብለው ይነሳሉ። ዓለም ብዙ አሳይታናለች። የህዝብ ቁጣ ሲነሳ የሚደርሰው አደጋ የከፋ ነው። እኔን ዘወትር የሚያስጨንቀኝ ይህ ነው። የኢህአዴግ ሰዎችም ቢሆኑ ሰዎች ናቸውና ከደጋፊዎቻቸው ጭምር ይህንን ሳያስቡት ውለው ያድራሉ ብዬ አላስብም። ደግሞም ያስባሉ። እንደውም ከማንኛቸውም በላይ የኢህአዴግ ደጋፊዎች እውነተኛ እርቅ የሚመኙበት ወቅት ላይ ለመሆናቸው ጥርጥር የለውም። ዋናው ጉዳይ ግን እንዴት …
tegga
ዶ/ር ተጋ ለንዳዶ
ጎልጉል፦ ኢህአዴግ እርቅ ይፈልጋል እያሉ ነው?
ዶ/ር ተጋ፦ በሚገባ። የኢህአዴግ አመራሮችና ደጋፊዎች እኮ ሰዎች ናቸው። አሁን አገሪቱ ላይ ያለው አደጋ ያሰጋቸዋል። ከሁሉም በላይ ሰላም ለነሱም ያስፈልጋቸዋል። ያለ ስጋት ተራ ሰው ሆነው መኖር የሚፈልጉ አሉ። የግፍና የጭቆና መጠን ሲያልፍ ህዝብ እንደሚነሳ ጠንቅቀው ያውቃሉ። የግፈኛ መሪዎች መጨረሻ ምን እንደሚመስል ይረዳሉ። ችግሩ ያለው እነሱና ደጋፊዎቻቸው ወደ እርቅ እንዲመጡ የሚኬድበት መስመር አግባብ ያለው መሆኑ ላይ ነው። የመተማመን ችግር አለ።
ጎልጉል፦ እርቅ የጀመሩና አሁንም እየሰሩ ያሉ አሉ?
ዶ/ር ተጋ፦ ካሉ ጥሩ ነው። እኔ ግን የማወራው ሌሎች ስለጀመሩት እርቅ አይደለም። እኔ የምናገረው የእውነተኛው እርቅ መንገድ ለገባቸው፣ የእርቅ ሃሳብ ላላቸው፣ ያልተነካኩና ለእርቅ ተግባር ቢነሱ የህዝብ ይሁንታና አመኔታ ማግኘት ለሚችሉ፣ ኢህአዴግም አክብሮ ሊያነጋግራቸው ፈቃደኛ ይሆናል ብዬ ለማምንባቸው ክፍሎች ነው። እርቅ ጀመሩ የሚባሉትን እነዚህን ሰዎችም ሆኑ ክፍሎች አላውቃቸውም። የምናገረው ቢጀምሩት ይሳካላቸዋል ብዬ ለማምንባቸው ሰዎች ለህሊናቸው ነው። የአገራችን ጉዳይ ያገባናል ለሚሉ ጨዋ ስብዕና ላላቸው ወገኖች ነው። እንግዲህ ይህንን ስል ከሁሉም ወገን ኢህአዴግን ጨምሮ ነው። አሁን አገራችን ያለችበት አሳሳቢ ወቅት ጤና ለነሳቸው፣ የወደፊቱ ትውልድ እድልና እጣ ፈንታ ግራ ላጋባቸው የኢትዮጵያ ልጆች ነው።
ጎልጉል፦ እውነተኛ እርቅ ምንድ ነው?
ዶ/ር ተጋ፦ ስለ አቀራረቡ መናገሩ የሚሻል ይመስለኛል። ከላይ የጠቀስኳቸው ክፍሎች ውስጥ አገራችንን ሊታደጉ የሚችሉ፣ የመጪውን ትውልድ መከራ ሊገፉ የሚችሉ ነገር ግን ዝምታን የመረጡ የተከበረ ስብእና ያላቸው ወገኖች አሉ። እነዚህ ዝምታን የመረጡ ወገኖች ዝምታን የመረጡበት በርካታ ምክንያቶች ይኖራቸዋል። የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከውስጥም ሆነ ከውጪ ስድድብ ነው። አንዳንዴ ቃላት እንኳ አይመረጥም። ሰው በስድብ ፖለቲካና ባለመከባበር የሚደረገው አተካሮ የሰለቸው ይመስለኛል። አንግዲህ እንዲህ ያለው መንገድ አልመች ብሏቸው ዝም ያሉትን ከተሸሸጉበት እንዲነሳሱ ማድረግ የመጀመሪያው ስራ ነው። ሌላው እርቅ የምትጠይቀውን ክፍል ማክበር ነው። እየዘለፍክና እያዋረድክ እርቅ መጠየቅ በባህላችንም ቢሆን አያስኬድም። በመከባበር ልዩነትን ማሳየትና ተቃውሞን መግለጽ የሚቻልበት መንገድ ሲፈጠር አድማጭ ማግኘት ይቻላል። በዚህ መልኩ መነጋገር ይጀመራል። እውነተኛ እርቅ የሚጀመረው የእርቁ አጀማመር ክብር የተሞላበት ሲሆን ነው። ሲጀመር መከባበርና የህዝብን ይሁንታ ማግኘት ከተቻለ የቀረው ጉዳይ ሂደት ነው የሚሆነው። ራሳቸውን ያከበሩና የጸዳ ማንነት ያላቸው ወገኖች ከየትኛውም ወገን ድጋፍ አላቸው። ከበሬታም አይነፈጉም። ኢህአዴግ ራሱም ቢሆን ሊገፋቸው አይችልም። አላማቸውና መሰረታቸው እርቅ ማውረድ መሆኑ ከተረጋገጠ ሊገፉ ወይም እምቢ ሊባሉ የሚችሉበት መንገድ የለም። ሁሉም ነገር የሚመነጨው ከስብዕናቸው ነውና ስብዕናቸው ያማረ ሰዎች ተሰባስበው እርቅ ላይ ቢሰሩ የሁሉም ስጋት ተቀረፈ ማለት ነው። ሌላ ትርጉም ካልተሰተው በቀር እርቅ አሁን ላለችው ኢትዮጵያ ፈውሷ ነው።
ጎልጉል፦ የሐይማኖት መሪዎች ሚና ምን ሊሆን ይችላል?
ዶ/ር ተጋ፦ የሐይማኖት መሪዎች ነው ያልከው? እንደው ለመሆኑ እዛ ደረጃ የደረሱ አሉ? ካሉ ጥሩ ነው። እኔ ግን እስካሁን አላየሁም። የራሳቸው የግል አመለካከት ቢኖራቸውም ለጊዜው እሱን ወደ ጎን አድርገው ለእርቅ ቢሰሩ ደግ ነው። ግን …
ጎልጉል፦ ቄስ ገመቺስና ቄስ ኢተፋ ጎበና የጀመሩት እርቅ ነበር፤
ዶ/ር ተጋ፦ ለትግል መንስዔ የሆኑ ሰዎች የእርቅ አፋላላጊ መሆን የሚችሉ አይመስለኝም። ከጅምሩ የህዝብን ይሁንታ ማግኘትና አለመነካካት ያልኩት እዚህ ጋር ይመጣል። ከቤተክርስቲያን ሃላፊነት በላይ በእርቅና በሰላም ፍልስፍና ማመን ይቀድማል። ራሳቸውን ለሰላምና ለእርቅ ፍልስፍና ያስገዙ ሰዎች የእርቅን ሂደትና የሚያስከፍለውን ዋጋ ስለሚረዱ እንዲህ አይነት ሰዎች ቢሆኑ ይመረጣሉ ባይ ነኝ። አሁን የጠቀስካቸው ወገኖች የጀመሩት ስራ ድጋፍ የሚያሻው ደረጃ ከደረሰም ማገዝ ነው።
ጎልጉል፦ በአንድነት ያምናሉ?
ዶ/ር ተጋ፦ አንድነት የተሰጠን ነው። እምነት ነው። በፍጹም ሊፋቅ አይችልም። አንድነት ውስጥ ልዩነት፣ በልዩነት ውስጥ ደግሞ አንድነት አለ። የምናምረው በልዩነታችን ነው። በልዩነታችን ውስጥ የሚፈጠረው አንድነት ደግሞ ያደምቀናል። ልዩነት በየጊዜው የሚያድግ፣ ወደፊትና ወደኋላ የሚለጠጥ የላስቲክ ይዘት ያለው ነው። ስለዚህ ይህንን እንደ ላስቲክ የሚለጠጥ ልዩነት ስንይዘው፣ “ያንተ ማንነት እኔን አይረብሸኝም” የሚለው እሳቤ ውስጥ ሁልጊዜም መኖር እንችላለን። ያንተ ቋንቋ፣ ማንነት፣ አስተሳሰብ፣ አያስፈልገኝም የሚል ጉዳይ ከተነሳ የላስቲክ ይዘት ያለውን ልዩነት ባህሪውን ወደሚሰበርና የሚቀነጠስ ቁስ ይቀይረዋል። እንዲህ ያለው እርምጃ አደጋ አለው። እኔ እንግዲህ እንዲህ ያለውን አስተሳሰብ ከሚቃወሙ የአንድነት አማኞች ውስጥ ነኝ …
ጎልጉል፦ ስለ እርቅ እንመለስና የውጪ ሃይሎች /መንግስታት/ ካልገቡበት አይሆንም የሚሉ አሉ፤ በተለይም ተጽዕኖ ፈጣሪ አገሮች፤
ዶ/ር ተጋ፦ እስከማውቀው ሕዝብ እውቅና የሰጠው እርቅ ስለመከናወኑ አልተሰማም። እኔ በግል ህዝብ እውቅና የሰጠው እርቅ ስለመኖሩ መረጃ የለኝም። በመጀመሪያ እርቅ በጓዳ ሲሆን ክብር የለውም። እርቅ በግልጽና ባደባባይ መሆን አለበት። ከላይ የገለጽኳቸው ወገኖች ከተሸፈኑበት መጋረጃ ከወጡና ለእርቅ ከሰሩ ብዙ ርምጃ መራመድ ይቻላል። የውጪ ሃይሎችን ማካተት ተገቢ የሚሆንበት አግባብ ብዙ ነው። እንደውም በገሃድ እርቁ ሲጀመር ለእርቁ ስራ የሚተባበሩ አገራትም አብረው መገለጽ አለባቸው። ለምሳሌ በኤርትራ ጉዳይ ላይ ኖርዌይ ብዙ ሚና ተጫውታለች። በወቅቱ ሚናዋ ደስተኛ ባልሆንም አስፈላጊ የሆኑ አገሮች እንዲካተቱ ማድረግ ተገቢ ይመስለኛል።
ጎልጉል፦ በተደጋጋሚ ዝምታን የመረጡ እንዲነሱ ይጠይቃሉ። በውል ስም ጠርተው ለዚህ ተግባር ተነሱ የሚሏቸው ወገኖች ካሉ?
ዶ/ር ተጋ፦ ብዙ ታሪክ መለወጥ የሚችሉ ወገኖች አሉ። ራሳቸውን ከአገራቸው ፖለቲካ አግልለው የመነኑ አሉ። ራሳቸውን የፖለቲካ ባህታዊ ያደረጉ አሉ። እነዚህ ባህታዊ ፖለቲከኞች እንዴት እንዲቀሳቀሱ ማድረግ እንደሚቻል ያሳስበኛል። ብዙ እርቅ ላይ መስራት የሚችሉ ወገኖች አሉ። እነዚህም ወገኖች ከሸፈቱበት የ”አያገባኝም” መንገድ ተመልሰው ማየት እፈልጋለሁ። ስለዚህ ድንገት ቢሰሙኝ ብዬ ነው ደጋግሜ የጠቀስኳቸው።
ጎልጉል፦ ፖለቲከኛ ነበሩ? አሁንስ?
ዶ/ር ተጋ፦ ፖለቲከኛ አይደለሁም። አጥብቄ የምጠየፈው ነገር ነው። አንዴ እዚህ፣ አንዴ እዚያ የመርገጥ ባህሪ የለኝም። የመገለባበጥ ነገር አይገባኝም። አቋራጭ ብሎ ነገር አላውቅም።
ጎልጉል፦ ግን በቂ ልምድ ያለዎት ይመስላል፤
ዶ/ር ተጋ፦ (ሳቅ ብለው) … ልምድ!! ስለ አገራችን ፖለቲካ አንድ ነገር ልበል። የእኛ ህዝብ ቦይ ነው። መንገድ ካሳየኸው ዝም ብሎ ይጎርፋል። አሁን ታዲያ ቦዩ በዛ። ቦዮቹ ደግሞ ትንንሽ ሆኑ። ትንንሽ ስም ያላቸው ሆኑና እንደ ስማቸው ትንሽ፣ ትንሽ ሰዎችን ይዘው ቀሩ። እነዚህ ትንንሽ ቦዮች የጥቂት ብልጣብልጦች መጠቀሚያ ሆኑ። ባህሪያቸውና ተፈጥሯቸው ትንሽ በመሆኑ ጥቂቶች አትራፊ ሆኑና አብዛኞች ከሰሩ። ይህ አካሄድ ያላስደሰታቸው አብዛኞች ራሳቸውን አቀቡ። አድፋጮች በዙና /silent majority/ ተባሉ። ከስማቸው እንደምንረዳው እነሱ ይበዛሉ። አሁን ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት እነዚህ ዝምተኛ፣ ባህታዊ ፖለቲከኞች፣ የመነኑ ዜጎች ተመልሰው ለእርቅና ለሰላም እንዲሰሩ ማሳሰብ የሁሉም ቀና ዜጋ ተግባር ሊሆን ይገባል። እኔ እንግዲህ እንደዚህ አስባለሁ። የተደበቁ ተመራማሪዎች አሉ። ሌሎች አገራትን የሚጠቅሙ ክቡር ዜጎች አሉን። አገራቸውን የሚወዱ ህዝብን የሚፈሩ አሉ። ከሁሉም በላይ ለህሊናቸው የሚኖሩ ዜጎች አሉ። ኢትዮጵያ የልጆች ደሃ አይደለችም። እነዚህ ዜጎች ለህዝብ ሲሉ፣ አገራቸው ሰላምና እርቅ እንዲወርድላት ሲሉ ከተደበቁበት ሊወጡ ይገባል።
ጎልጉል፦ ከህወሃት ሰዎች ጋር ይተዋወቃሉ?
ዶ/ር ተጋ፦ የቀድሞውን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ስዩም መስፍንን አውቃቸዋለሁ፤ አብረን ተምረናል። ባለስልጣን ከሆኑ በኋላ ተገናኝተንም ነበር። በግል በእርቅ ዙሪያ ላነጋግራቸው እችላለሁ። ሌሎችም ሰዎች አሉ። ኢህአዴግ ውስጥ ቀና ሰዎች እንዳሉ መታመን አለበት። ቀና የትግራይ ልጆች አሉ። የወደፊቱ ችግር የሚያሳስባቸው ጥቂት አይደሉም። ደጋግሜ እንደነገርኩህ ዋስትና የሚናፍቁ ባለስልጣኖች ብዙ ናቸው። ሰላም የሚመኙ ብዙ ናቸው። መንገዳቸውን መመርመር የሚፈልጉ ጥቂት አይደሉም። ግን በስድብና በጥላቻ ሊሆን አይችልም። በመከባበር የሚመሰረት መቀራረብ ወደ አንድ የእርቅ ሃሳብ ያመጣል። ጊዜ ቢወስድም መጀመር አለበት። ሲጀመር ግን በክብር መሆን አለበት። ህዝብም እውቅና የሚሰጠው ሊሆን ይገባል።
ጎልጉል፦ እርስዎ የሚያምኑበት እርቅ በዋናነት ምን መያዝ አለበት?
ዶ/ር ተጋ፦ እርቅና ሰላም ከፍትህ ጋር። ፍትህ የሌለበት እርቅ ዋጋ የለውም። ሰላምም አያመጣም። ግብጽ ጥሩ ምሳሌ ናት። አሁን የተነሳውን የፕሬዚዳንት ሙርሲን ደጋፊ ምን ታደርገዋለህ። ፍትህ ካላገኘ ለመሞት ተነስቷል። በሌላ በኩል ሙርሲን አውርደው የተቀመጡ አሉ። ለሙርሲ ደጋፊዎች ምላሽ ቢሰጥ አውርደው የተቀመጡትና የፈለጉትን ለመምረጥ ጊዜ ገደብ የተቀመጠላቸው ይነሳሉ። ሲጀመር ፍትህና እርቅ ተጣምረው ባለመከናወናቸው ችግሩ እየተባበሰ ሄደ። ስውር ጉዳዮች እንዳሉ ሆነው ማለቴ ነው። ስለዚህ እርቅና ፍትህ የሚለያዩ ነገሮች አይደሉም። ፍትህ ያለበት እርቅ እንዲሰፍን ተግተን መስራት አለብን። አገራችን ያለችበት ሁኔታ ቸል የሚባልበት አይደለም። በኋላ ሁላችንንም ይቆጨናል። እርቅ ላይ ትኩረት ማድረግ ግድ ነው። የፖለቲካ ለውጥ እንኳን ቢኖር የተዘራውን ክፉ ዘር ለማክሰም እርቅ ግድ ነው።
ምንጭ ጎልጉል

Thursday, August 22, 2013

ለእምነት ነፃነት የምናደርገውን ትግል ለሰብዓዊ መብቶች መከበር፣ ለዜግነት ክብር እና ለሀገር ነፃነት ከምናደርገው ትግል ጋር እናቀናጅ!!!

ትንሽነቱ በፈጠረበት ስጋት ምክንያት ሁሉንም ነገር ካልተቆጣጠረ በጉልበት የያዘውን ሥልጣን የሚያጣ የሚመስለው እና በዚህም ሳቢያ ሁሉም ነገር ውስጥ እጁን የሚነክረው ወያኔ ራሱን በገዢነት ከሾመበት እለት ጀምሮ የሃይማኖት ተቋማትን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር እንደተጋ ነው። በእኛ በኢትዮጵያዊነት ዳተኝነት ታግዞም ትጋቱ ውጤት እያስገኘለት ነው።
ወያኔ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክህነትን ከፓትሪያርክ ጀምሮ እስከ ደብር አለቆች ድረስ ያለው መንፈሳዊ ሹመት ተቆጣጥሯል። አሁን የቀየረው የቤተክርስቲያኒቷን ሃይማኖታዊ ቀኖናን መቀየር ነው። ወያኔ በሥልጣን ላይ ከቆየ ይህንንም ከማድረግ የማይመለስ መሆኑን በእስልምና እምነት ላይ ተግባራዊ እያደረገ ካለው መገንዘብ ይቻላል።
ልክ እንደ ክርስትናው ሁሉ ወያኔ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትን (መጅሊስ) በራሱ ካድሬዎች ሞልቶት ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮታል። እስልምና ላይ ግን የሃይማኖት ተቋማትን ከመቆጣጠር አልፎ በቀኖና ጉዳይ በመግባት የራሱን “ምርጥ እስልምና” እያስተዋወቀ ነው። ዛሬ በሙስሊሞች ላይ የመጣው ነገ በክርስቲያኖችም ላይ የሚመጣውን አመላካች ነው።
እርግጥ ነው ክርስቲያኖችና ሙስሊሞች የወያኔን ጥቃት በፀጋ አልተቀበሉትም። ሁሉም በየራሳቸው መንገድ የወያኔን ሁሉን-ጠቅላይ አገዛዝ እየተቃወሙትና እየታገሉት ነው። ዛሬ የወያኔ ጥቃት የደረሰበት ደረጃ ግን የሁለቱን ሃይማኖቶች አማኖችን ኅብረት የሚጠይቅ ሆኗል። ወያኔ ደግሞ በበኩሉ ይህ መከባበርና መተባበር እንዳይኖር ጥረት እያደረገ ነው።
የሁለቱም ትላልቅ ሃይማኖቶች ምዕመናን ለእምነታቸውና ለእምነት ተቋሞቻቸው ነፃነት በሚታገሉበት በአሁኑ ሰዓት “ጅራፍ እራሱ ገርፎ ራሱ ይጮህ” እንዲሉ ወያኔ ድምፃቸውን ቀምቶ በደሉን ለማጠናከር እየተጠቀመበት ነው። እፍረት ያልፈጠረባቸው የወያኔ ሹማምንት “መንግሥት በእምነታችን ጉዳይ ጣልቃ አይግባብን” እያሉ አቤት የሚሉትን ምዕመናንን “በፓለቲካ ጉዳይ ጣልቃ ገባችሁ፤ ይህ ደግሞ በኛ ሕግ ክልክል ነው” እያለ ይከሳቸዋል።
“ሃይማኖት በመንግሥት፤ መንግሥትም በሃይማኖት ጉዳዮች ጣልቃ አይገቡም” የሚለውን ሰፊ ተቀባይነት ያለው መርህ ወያኔ መሠሪ በሆነ ተንኮሉ “ሃይማኖት በፓለቲካ፤ ፓለቲካም በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገቡም” ወደሚል እጅግ አደገኛ መርህ እየቀየረው ነው።
“በሃይማኖትና መንግሥት” እና “በሃይማኖትና ፓለቲካ” መካከል ያለው ግዙፍ ልዩነት ለአብዛኛው ምዕመን ግልጽ አይደለም በሚል ግብዝነት ነገሮችን በማጣመም ምዕመናንን በማደናገር ለፍረጃ ያመቻቻቸዋል።
አዎ ሃይማኖትና መንግሥት መለያየት አለባቸው። ኢትዮጵያዊ ክርስቲያኖችና ሙስሊሞች እየጠየቁ ያለውም ወያኔ ይህንን መርህ እንዲያከብር ነው። “ወያኔ ሆይ!!! በሃይማኖታችን ጉዳይ ጣልቃ አትግባብን!” እያሉት ነው።
ሃይማኖትና ፓለቲካ ግን በብዙ ክሮች የተቆላለፉ ነገሮች ናቸው። ለሃይማኖት ነፃነት መከራከር ራሱ ፓለቲካ ነው። ለሰብዓዊ መብቶች መከበር መከራከርም ትልቅ ፓለቲካ ነው። የሁለቱ ሃይማኖቶች አማኞች ይከባበሩ፤ ይተባበሩ ማለትም ፓለቲካ ነው። ይህ እንዳይፈጠር ነው ወያኔ ሃይማኖትና ፓለቲካ እሳትና ጭድ አድርጎ ሊስላቸው የሚዳዳው።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ኢትዮጵያዊያን ምዕመናን በሃይማኖትና ፓለቲካ አንድነትና ልዩነት ላይ የጠራ አቋም መያዛቸው ትግላችን ያግዛል ብሎ ያምናል።
ሃይማኖትና መንግሥት መለያየታቸው ተገቢ ነው። ሃይማኖትና ፓለቲካ ግን አንድ ባይሆኑም በብዙ መንገዶች የሚደጋገፉ ናቸው። ሃይማኖቶች ለእምነት ነፃነት፣ ለሰብዓዊ መብቶች መከበር፣ ለዜግነት ክብር፣ ለሀገር ነፃነት እና መሰል ጉዳዮች በግንባር ቀደም መታገል ይኖርባቸዋል። በታሪካችን ውስጥ ታቦቶች ጦር ሜዳዎች ዘምተው አርበኞችን አበረታተዋል። ይህ ዛሬም ሊደረግ የሚገባው የተቀደሰ ተግባር ነው።
በዛሬ የአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ሃይማኖትና የሃይማኖት ተቋማትን ከወያኔ መዳፍ ማውጣት ሀገርን ከወያኔ መዳፍ ከማዳን ጋር በጥብቅ የተሳሰረ ጉዳይ ሆኗል። ስለሆነም ለሃይማኖት ነፃነት የምናደርገው ትግል ለሀገራችንም የምናደርገው ትግል አካል ነው።
ወያኔ በሃይማኖቶቻችን፣ በሀገራችን ብሎ በራሳችን ላይ የመጣ እኩይ ኃይል ነው።
ስለሆነም፣ ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ለሃይማኖት ነፃነት የምናደርገውን ትግል ለሰብዓዊ መብቶች መከበር፣ ለዜግነት ክብር እና ለሀገር ነፃነት ከምናደርገው ትግል ጋር እንድናቀናጅ ወገናዊ ጥሪ ያደርጋል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!



    ግብፅን ሁለት ቦታ የከፈለው ብጥብጥ ወደ እርስ በርስ ጦርነት ሊቀየር ይችላል

    21 AUGUST 2013 ተጻፈ በ  
    ለ30 ዓመታት ግብፅን የመሩት ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክ በሕዝባዊ አብዮት ሥልጣናቸውን ከለቀቁበት እ.ኤ.አ. ከ2011 ወዲህ ግብፅ ከፍተኛ የሆነ ደም አፋሳሽ ግጭት ያስመዘገበችው ካለፈው ሳምንት ረቡዕ ወዲህ ነው፡፡
    የቀድሞው የግብፅ ፕሬዚዳንት ሙባረክ በሕዝብ ንቅናቄ ከሥልጣን ከወረዱ በኋላ በዲሞክራሲያዊ መንገድ ለመጀመርያ ጊዜ የተመረጡት ፕሬዚዳንት መሐመድ ሙርሲ፣ በምርጫ ያገኙትን የአራት ዓመት የሥልጣን ዘመን ለመምራት በለስ አልቀናቸውም፡፡ አገሪቷን መምራት በጀመሩ በዓመታቸው የተለያዩ ሚዲያዎች ‹‹አብዛኛው ሕዝብ›› እያሉ በሚዘግቡት ግብፃውያን ተቃውሞ ሳቢያ የአገሪቱ ጦር ኃይል ከሥልጣን አውርዷቸዋል፡፡
    የአገሪቱ ጦር ኃይል ፕሬዚዳንት ሙርሲን ከሥልጣን ካወረደበት እ.ኤ.አ ከሰኔ 26 ቀን ጀምሮ ግን ግብፅ ሰላም አላገኘችም፡፡ ፕሬዚዳንት ሙርሲ ከሥልጣን ይውረዱ በማለት ለተቃውሞ ወጥተዋል የተባሉት 23 ሚሊዮን የሚጠጉ ግብፃውያን ከጐዳና ወደቤታቸው ሲገቡ፣ የሙርሲ ደጋፊ የሆኑት 14 ሚሊዮን ይጠጋሉ የተባሉ የሙስሊም ብራዘርሁድ አባላት ለተቃውሞ ጐዳና ወጥተዋል፡፡
    ‹‹የሽግግር መንግሥቱን አንደግፍም፣ ፕሬዚዳንት ሙርሲ ይፈቱ፣ መሪያችን ፕሬዚዳንት ሙርሲ ናቸው፣ የወታደሩን ጣልቃ ገብነት እንቃወማለን፣ በግብፅ ታይቶ የነበረው ዴሞክራሲ ተረግጧል፣ ወዘተ›› በማለት በየጐዳናው መጠለያ በመሥራት ከሳምንታት በላይ ውሎና አዳራቸውን ውጭ ያደረጉት የፕሬዚዳንት ሙርሲ ደጋፊዎች፣ ከጐዳና ወደቤታቸው እንዲገቡ ቢጠየቁም ፈቃደኛ ሊሆኑ አልቻሉም፡፡ የፕሬዚዳንት ሙርሲ ደጋፊዎችን የጐዳና ላይ ተቃውሞ መታገስ ያልቻለው ጦር ኃይሉ ባለፈው ሳምንት በወሰደው የመበተንና መጠለያዎችን የማፍረስ ዕርምጃ የሙስሊም ብራዘርሁድ ደጋፊዎችን አስቆጥቷል፡፡ 
    በግብፅ ለደረሰው ሕይወት መጥፋትና ንብረት መውደም ምክንያት ሆኗል፡፡ ከዚህ በከረረ በክርስቲያኖችና በሙስሊሞች፣ በሙርሲ ደጋፊዎችና በተቃዋሚዎች መካከል ልዩነት ተፈጥሯል፡፡ ግብፃውያንን ለሁለት ከፍሏል፡፡ ግብፃውያን ፕሬዚዳንት ሙርሲን የሚደግፍና የማይደግፍ በመባባል መገዳደል ጀምረዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያናትም እየተቃጠሉ ነው፡፡ መስቀል አንገታቸው ላይ ያንጠለጠሉ እየተገደሉ ነው፡፡ ግብፃውያን ወደ እርስ በርስ ጦርነት ሊያስገባቸው በሚችል ሁኔታ ተበጣብጠዋል፡፡ የተፈጠረው ግጭት በቀላሉና በአጭር ጊዜ ሊበርድ እንደማይችልም የፖለቲካ ተንታኞች እየገለጹ ነው፡፡ 
    በእስር ላይ የሚገኙት መሐመድ ሙርሲ የሙስሊም ብራዘርሁድ ደጋፊዎችና የሽግግር መንግሥቱን እየጠበቀ ያለው ጦር ኃይሉ በአንድነት ተወቃሽ በሆኑበትና ባለፈው ረቡዕ ነሐሴ 8 ቀን 2005 ዓ.ም. በተጀመረው ግጭት ብቻ 638 ግብፃውያን ተገድለዋል፡፡ በዚህ ቀን ለሞቱት ሰዎች ምክንያቱ የሙስሊም ብራዘርሁድ ደጋፊዎች ቀድመው በፖሊሶች ላይ በመተኮሳቸው ነው ቢባልም፣ ሁለቱም ወገኖች እየተወቀሱ ነው፡፡ 
    የ638 ሰዎችን መሞት ተከትሎ ሐሙስ ነሐሴ 9 ቀን 2005 ዓ.ም. የመንግሥት ተቋማትን ከሙርሲ ደጋፊዎች ጥቃት ለመጠበቅ ፖሊስ መሣሪያ እንዲጠቀም መፈቀዱ በግብፅ ግድያው እንዲጨምር፣ ግጭቱ እንዲባባስና አቅጣጫ እንዲቀይር አድርጐታል፡፡ በረቡዕ ዕለት የተከሰተውን ግድያ በመቃወም ዓርብ ነሐሴ 10 ቀን 2005 ዓ.ም. በካይሮ ራማሲስ አደባባይ በወጡ የሙርሲ ደጋፊዎችና ፖሊስ መካከል በተፈጠረ ግጭት 117 ሰዎች ተገድለዋል፡፡ 
    በፖሊስና በሙርሲ ደጋፊዎች መካከል የተፈጠረው ግጭት አቅጣጫውን በመሳቁ፣ የሙርሲ ደጋፊዎች ብሶታቸውን ሕንፃዎችን በማቃጠል ገልጸዋል፡፡ ከዚህ ባለፈም ክርስቲያኖችን መግደል መጀመራቸው ተዘግቧል፡፡ 
    እስልምናን ለማስፋፋትና በግብፅ እስላማዊ መንግሥት ለማስፈን ዓላማ አድርጐ መነሳቱ የሚነገርለት በምርጫ በርካታ የፓርላማ መቀመጫዎችን በማግኘትና በኋላም አገሪቱን ለመምራት መብቃቱ የሚነገርለት የሙስሊም ብራዘርሁድ ደጋፊዎች፣ ማክሰኞ ምሽት ለሕትመት እስከገባንበት ጊዜ ድረስ 37 አብያተ ክርስቲያናትን ማቃጠላቸው በተለያዩ ሚዲያዎች ተዘግቧል፡፡ 
    ፖሊስ 36 የሙርሲ ደጋፊዎችን ከካይሮ ወደ ሌላ እስር ቤት ሲያዘዋውር ለማምለጥ ባደረጉት ጥረት አስለቃሽ ጭስ በመተኮሱ በጭስ ታፍነው ሞተዋል፡፡ 25 የፖሊስ አባላት በሙስሊም ታጣቂዎች መገደላቸው የተሰማውም ባለፉት ሰባት ቀናት ውስጥ ነው፡፡ 
    በግብፅ ግድያና እስር አይሏል፡፡ ትክክለኛው ቁጥር ግልጽ ባይወጣም አንድ ሺሕ የሚደርሱ የሙርሲ ደጋፊዎችና የፖሊስ አባላት መገደላቸው በመንግሥት ተረጋግጧል፡፡ የሙርሲ ደጋፊዎች የሟቾችን ቁጥር 2,600 አድርሰውታል፡፡
    የሙስሊም ብራዘርሁድ አቅጣጫ ያላማረው የሽግግሩ መንግሥት ድርጅቱ በሕጋዊ መንገድ እንዲፈርስ ጥያቄ አቅርቧል፡፡ የሙስሊም ብራዘርሁድ መፍረስ ወይም አለመፍረስ ለግብፅ ሰላምን ያመጣል ወይ? የሚለው ለብዙ ግብፃውያን ጥያቄ ሆኗል፡፡ ግብፃውያን ዛሬ ላይ ሆነው ግራ ተጋብተዋል፡፡ ያጠፋው ማነው? ትክክለኛውና የተሳሳተው ማን ነው? በሚለው ውዥንብር ውስጥ ሆነው ሞትን ያስተናግዳሉ፡፡ 
    የመካከለኛው ምሥራቅ የፖለቲካ ተንታኞች ግብፃውያን አሁን ባሉበት ሁኔታ ማንን መደገፍ እንዳለባቸው ግራ መጋባታቸውን እየገለጹ ነው፡፡ የመንግሥትና የግሉ ሚዲያ ዘገባ ደግሞ የበለጠ ግራ እያጋባቸው ነው፡፡ 
    የአገሪቱ ሚዲያዎች ወታደራዊ ክፍሉ ዕርምጃ እየወሰደ የሚገኘው የፖለቲካ ልዩነት ባላቸው የሙስሊም ብራዘርሁድ ደጋፊዎች ላይ ሳይሆን በአሸባሪዎች ላይ ነው ቢሉም፣ ግብፃውያን ማንን መደገፍ፣ ማንን ማመንና መውቀስ እንዳለባቸው ግራ ተጋብተዋል፡፡
    ኤንቢሲ ኒውስ እንደዘገበው፣ ግብፅ ውስጥ በተፈጠረው ግጭት ማን ተወቃሽ ማን ወቃሽ እንደሆነ የማይለይበት ደረጃ ተደርሷል፡፡ የሳቢያን ሴንተር ፎር ሚድል ኢስት ፖሊሲ አባል ካሊድ ኢልጊንዲ፣ ‹‹ሁሉም ወገኖች ከሚገባው በላይ በመሄዳቸው ሕዝቡ በከፍተኛ ፍርኃት ተውጧል፡፡ ፖለቲካዊ መፍትሔ የማያዋጣ ሊሆን ይችላል፡፡ ግብፅ በከባድ አለመረጋጋት ውስጥ ገብታለች፤›› ብለዋል፡፡ 
    ግብፅ በብጥብጥ ማዕበል ውስጥ ባለችበት በአሁኑ ወቅት ሪፐብሊካንና ዲሞክራት የአሜሪካ ሕግ አውጭዎች አሜሪካ ለግብፅ በየዓመቱ የምትሰጠውን የ1.5 ቢሊዮን ዶላር ዕርዳታ ቢያንስ ብጥብጡ እስኪቆም እንድታቆም የፕሬዚዳንት ኦባማ አስተዳደርን ጠይቀዋል፡፡ 
    በአሜሪካ ሕግ መፈንቅለ መንግሥት ለተካሄደበት አገር ዕርዳታ እንዳይሰጥ የሚያግድ ቢሆንም፣ አሜሪካ እስካሁን በፕሬዚዳንት ሙርሲ ላይ መፈንቅለ መንግሥት ተካሂዷል ከማለት መቆጠብን መርጣለች፡፡ ሆኖም አሜሪካ ለግብፅ ለመሸጥ ተስማምታ የነበሩትን አፓቼ ሔሊኮፕተሮች ለጊዜው አዘግይታለች፡፡ ከግብፅ ጋር ያላትን ጥምር ወታደራዊ ልምምድም ማቆሟን አስታውቃለች፡፡
    ይህ ግን የእስራኤል ባሥልጣናትን ዓይን አስፈጥጧል፡፡ እስራኤል በሲናይ በረሃ የእስላም አክራሪነት እንዲለዝብ ትፈልጋለች፡፡ ለዚህም አሜሪካ ለግብፅ ጦር ኃይል የምታደርገው ድጋፍ መቋረጥ የለበትም የሚል አቋም አላት፡፡ በመሆኑም እስራኤል የፕሬዚዳንት ኦባማ አስተዳደር ለግብፅ ጦር ኃይል የሚያደርገውን ዕርዳታ እንዳያቆም እንደምትወተውት ከወዲሁ እየተነገረ ነው፡፡ 
    በግብፅ ማህሙድ ባድኤን ጨምሮ ከፍተኛ የሙስሊም ብራዘርሁድ ባለሥልጣናት ታስረዋል፡፡ አልቃይዳ ደግሞ የሙስሊም ብራዘርሁድ አባላት መታሰርና መገደልን ከበፊት ጀምሮ ለያሁው የእስልምና አክራሪነት ዓላማ ማራመጃ እየተጠቀመበት ነው፡፡     
    አሶሼትድ ፕሬስና ሮይተርስ እንደዘገቡት፣ የአልቃይዳ የምሥራቅ አፍሪካ ብንፍ የሆነው አልሸባብ በግብፅ ያለውን ነውጥ አስመልክቶ ‹‹አልቃይዳን ለመደገፍ ጊዜ አሁን ነው፡፡ በግብፅ የአልቃይዳን ባንዲራ ማውለብለብ ቅድሚያ የሚሰጠው ነው፤›› ብሏል፡፡ 
    ሚስተር ኢሊጊንዲ የግብፅ ጦር ኃይል፣ ሙስሊም ብራዘርሁድና አልቃይዳ አሁን ባሉበት ሁኔታ ከቀጠሉ አስቸጋሪ ነው ይላሉ፡፡ በተለይ የግብፅ ወታደሮች በሙስሊም ብራዘርሁድ ላይ ከፍተኛ ዕርምጃ መውሰድ ከጀመሩ፣ የሙስሊም ብራዘርሁድ ካድሬዎች ወደ ጂሃዲስትነት ሊቀየሩ ይችላሉ ሲሉ ሥጋታቸውን ገልጸዋል፡፡ ይህ ማለት ደግሞ በግብፅ የእርስ በርስ ጦርነት እንዲነሳ ምክንያት ከመሆኑም በላይ በአካባቢው ከፍተኛ ውጥረት ያነግሳል፡፡ 
    ምንጭ ሪፖርተር ጋዜጣ

    Wednesday, August 21, 2013

    Letter from prison / Reeyot Alemu, Ethiopia

    Anti-Terrorism Decree | Born from Power Thirst
    AUGUST 21, 2013
    2012 Courage in Journalism Award winner Reeyot Alemuwas arrested on June 21, 2011.
    Today is her 793th day in prison.by Reeyot Alemu, Ethiopia
    Many questions cross my mind when I look at the "'Anti-Terrorism Decree" and its application. Why does this decree have paragraphs that violate human rights? Why does it prosecute innocent citizens who have no ties to terrorism or terrorist organizations? I ask myself. In order to answer these questions one needs to look at the reasons behind the creation of such a decree, and so I did.
    Why was the anti-terrorism decree written? One needn't look too far to realize that the ruling party, EPRDF, didn't create these anti-terrorism laws because it faced a real threat. You only need to look at the individuals who are either facing such charges, or have already been found guilty under this decree. Members of the opposition party who have denounced human rights violations and have peacefully called for the replacement of the current regime by a more democratic one, freethinkers who dared ask stern questions to officials at locally organized discussion forums, leaders of the Muslim community who refused to dilute and redraft their religious beliefs to appease the government's stance on religion, and ourselves, members of the free press who performed their duty as voices of the people have been the main victims of this anti-terrorist decree. 
    This proves that the real purpose of this decree is to enable the current regime to comfortably rule without any criticism, opposition, or competition. These actions are not creations of the EPRDF, instead they are old tried and true methods copied from other brutal regimes. It is very well known that colonial regimes of the past found it convenient to label the freedom fighters that refused to kneel as "terrorists." And today, the EPRDF travels this same colonial path by stuffing its prisons with its own citizens and punishing those of us who have refused to give up our human and citizenship dignity. 
    What is to be done? Stopping the gross human rights violations that the EPRDF is committing under the guise of the anti-terrorism decree requires a lot of work. The current anti-terrorism decree will have to be replaced by a more appropriate one. Even with such changes, as long as the judicial system leans in favor of the EPRDF such arrests will continue. For, those of us who are currently imprisoned would have been found "not guilty" had we been judged fairly, even under the current anti-terrorism decree. As such, demonstrations and movements aimed at this decree, and more importantly at the ruling EPRDF who seeks to illegally use it, shall be strengthened and continued.
    The reason I strongly believe that these protests should primarily be aimed at the ruling party is because it is the source of the wrongful application of this law and other innumerable Ethiopian problems. We have observed with disgust the length this regime will travel to protect its grip on power, and its rule. In other words, the actions of the EPRDF are based on motives that are tied to ethnicity, power hunger, and unjust prosperity among others. In Arthur Gordon's words “If one's motives are wrong, nothing can be right.” Because of this, nothing good can be expected from the EPRDF. 
    Therefore our only option for change remains a modern and peaceful struggle wherein we should be prepared to provide the needed sacrifices. As we embark on this journey to transform the system, there are many related issues that we should consider. We should deeply consider all the challenges set forth by the ruling party whether they are the ethnic, religious, ideological, or the interest based divisive elements it nourishes. We shall learn how to unite our many fronts of struggle into one. 
    Looking forward, it is the role of any responsible citizen, and especially that of the opposition parties and related groups, to think of and discuss  the nature of the system that shall proceed the current one. For as long as we accomplish these required duties, and stay  firm in our convictions, a Bright Day will not be too far.

    The author, a columnist for the now-defunct Ethiopian newspaper Feteh, is currently serving a 5-year prison sentence in Addis Ababa on bogus terrorism charges. The International Women's Media Foundation honored Alemu with its 2012 Courage in Journalism Award last year, and in May 2013, the UNESCO recognized her "commitment to freedom of expression" with its Guillermo Cano World Press Freedom Prize.
    The article has been translated from the Amharic original exclusively for the IWMF.
    Source The Global Network for Women in the News Media.