Monday, September 30, 2013

በኖርዌይ ለግንቦት 7 ህዝባዊ ኃይል የተደርገ የገቢ ማሰባሰቢያ በደማቅና ባሸበረቁ በተለያዩ ዝግጅቶች በድል ተጠናቀቀ!!!!

በሴፕቴምበር 28 በኦስሎ ኖርዌይ ለግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል የገቢ ማሰባሰቢያ በደማቅና ባሸበረቁ በተለያዩ ፕሮግራሞች
ታጅቦ በድል መጠናቀቁ ይታወቃል ህዝባዊ አላማ ያነገበው ዝግጅት ከጅምሩ ለማጨናገፍ የተለያዩ የስም ማጥፋት
ፕሮፓጋንዳዎችን በማስራጨት የአሸባሪ ድርጅት ለመርዳት የገቢ ማሰባስቢያ ፕሮግራም ማካሄጃ ትፈቅዳላቹሁ በማለት ለኖርዌይን
የተዛባ ኢንፎርሜሽን በማስተላለፍ የታቀደውን ፕሮግራም ለማምከን የታሰበው፡ እውነት በመያዝ ስለእውነት የቆመ
ኃይል ምንግዜም አሸናፊ ነው እና የታሰበው ፕሮግራም በታቀደለት ስነስርዓት በድል ተጠናቋል።


    በኖርዌይ የምንኖር ኢትዮጵያዊያን ለግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል ወገናዊነት እና አጋር በመሆን በተግባር ቁርጠኝነታችንን
አሳይተናል ከዚህም የተናሳ በገቢ ማሰባሰቢያው ላይ በስጦታ እና ጨርታ ብቻ እስካሁን ባለኝ መርጃ 408,633.85
የኖሮዌጅያን ክሮነር ሲሆን ይህ ገቢ ከመግቢያ ትኬት፣ ከምግብ ሺያጭ አና የመሳሰሉትን ሳይጨምር ነው።
   ይህ በንዲ እንዳለ አብዛኛውን ታዳሚውን ቀልብ የሳበው የግንቦት 7 የፍት ህ የነፃነት የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሃፊ
አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በፎቶ ግራፍ የተደገፈ ስእላዊ መግለጫና የህዝባዊ ግንባር የእለት ተእለት የሚያደርጉት
የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን በማስረዳት በተጨማሪ ከ አሜሪካን፣ከአውሮፓ ወደ ትገሉ አንደተቀላቀሉ፣ የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል
ከተለያዩ ብሄር ብሔርስቦች የተወጣጡ እንደሆኑ በገለፃቸው አስርድተዋል።
 ኮማንደር አሰፋ ማሩ በተመሳሳይ መልኩ ንግ ግ ር ያደርገ ሲሆን በታዳሚው ለቀረበለት ጥያቄዎች
ተገቢውን መላሽ በመስጠት ገለፃ አድርጓል።
  በዚ አጋጣሚ ሳልጠቅስ የማላልፈው የ ኢትዮጵያዊነት ፍቅር ግድ ብላቹሁ ከ እንግሊዝ ፣ከ ሲዊዝ፣ከ ሲዊዲን
እንዲሁም ከተለያዩ አገሮች የታደማቹሁትን እንግዶቻችን በሙሉ እናመስግናለን።

ሞት ለወያኔና ለሆድ አደሮቹ!!!!!

ድል ለኢትዮጵያ ሰፊ ህዝብ !!!!!

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!!!!!

ከ ዳዊት ወንድሙ.

Wednesday, September 25, 2013

ደጃች ውቤ ሠፈር ሊፈርስ ነው

ተጻፈ በ  
‹‹በቅርስነት ሊጠበቅ ሲገባው በድንገት ሊፈርስ ነው መባላችን አሳዝኖናል›› የአካባቢው ነዋሪዎች
‹‹በችኮላ የሚሆን ሳይሆን ተማሪዎችን ታሳቢ ያደረገ ዕቅድ ነው›› የአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር
ከአዲስ አበባ ከተማ ምሥረታ ጋር ተያይዞ በቀደምትነት ከተመሠረቱ አካባቢዎች ቀዳሚነቱ የሚነገርለትና በተለምዶ ‹‹ውቤ በረሃ›› በሚል መጠሪያ የሚታወቀው ደጃች ውቤ ሠፈር፣ በከፊል የሚፈርስ መሆኑ ለነዋሪዎች ተነገራቸው፡፡ 
በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ አምስት ንዑስ ቀበሌ 05 ከጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት ወደ አፍንጮ በር በሚወስደው መንገድ በቀኝ በኩል በ11.6 ሔክታር ቦታ ላይ ያሉ ነዋሪዎች እንደሚነሱና ከ100 ዓመታት በላይ ያስቆጠረው ሠፈር እንደሚፈርስ ለነዋሪዎቹ የተነገራቸው፣ መስከረም 11 ቀን 2006 ዓ.ም. በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ለግማሽ ቀን በተደረገ ውይይት ነው፡፡
ከራስ መኮንን ድልድይ ወደ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በስተቀኝ በኩል በሚያስወጣው አስፓልት እስከ አደባባዩ ድረስ የተገነቡ የመኖሪያ ቤቶች፣ የንግድ ቤቶችና የተለያዩ ቢሮዎች፣ ሆቴሎችና ምግብ ቤቶችን ጨምሮ እስከ አፍንጮ በር ድልድይ መዳረሻ ድረስ እንዲፈርሱ ምክንያት የሆነው፣ የባቡር ተርሚናልና ኃይል መስጫ ጣቢያ ሊገነባበት በመሆኑ እንደሆነ በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት በተደረገው የግማሽ ቀን ስብሰባ እንደተነገራቸው ነዋሪዎቹ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ 
ነዋሪዎቹ እንደገለጹት፣ በጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አደባባይ ፊት ለፊት ከሚገኙት ንግድ ቤቶች ጀምሮ ከሦስት ሔክታር በማይበልጥ ቦታ ላይ ያሉ ነዋሪዎች እንደሚነሱ ቀድመው ተነግሯቸዋል፡፡ መስከረም 11 ቀን አስቸኳይና ድንገተኛ ስብሰባ እንዳለና ማንም ቢቀር ኃላፊነቱ የራሱ እንደሆነ በማስጠንቀቅ ነዋሪዎች እንዲገኙ ከተደረገ በኋላ፣ በሰሙት ጉዳይ እጅግ በጣም መደንገጣቸውንና ማዘናቸውን አስረድተዋል፡፡
የባቡር ተርሚናልና ኃይል መስጫ ጣቢያ ግንባታ በሚል በዳር ያሉት እንደሚነሱ በቅድሚያ ከተነገራቸው በኋላ በድንገት ‹‹የሚያስፈልገው ስምንት ሔክታር ነው፡፡ የሚቀረው 3.6 ሔክታር ተቆርጦ መቀጠል ስለሌለበት ለመልሶ ማልማት መፍረስ አለበት፡፡ ይኼ ደግሞ ተወስኖ አብቅቷል፤›› መባላቸው ተገቢ አለመሆኑንና ኅብረተሰቡን መናቅ እንደሆነ ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡
በቅርስነት ተጠብቆ መኖር ሲገባው እንደ መርዶ ነጋሪ በድንገት እንደሚፈርስ መወሰኑን ለነዋሪዎች ማርዳት ማን አለብኝነት ነው የሚሉት ነዋሪዎቹ፣ ከወረዳ እስከ ማዕከል ድረስ መረጃ በመጠየቅ በሁለትና በአራት ሚሊዮን ብር በቅርቡ ከሚፈርሱት ቤቶች ውስጥ የመኖሪያ ቤትና የንግድ ቤቶችን የገዙትን ለመጉዳት ሆን ተብሎ የተደረገ እንደሚያስመስለውም ጠቁመዋል፡፡
ነዋሪዎቹ እንደተነገራቸው ከሆነ፣ አስተዳደሩ ሁለት አማራጮችን አስቀምጦላቸዋል፡፡ የመጀመሪያው 20 በመቶ ቅድሚያ ክፍያ በመፈጸም የጋራ መኖሪያ ቤት ማግኘት ሲሆን፣ ሁለተኛው አማራጭ የቀበሌ ወይም የኪራይ ቤቶች ተዘጋጅተውላቸው ወደዚያ መግባት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አስተዳደሩ አስቀምጦላችኋል የተባሉትን አማራጭ ነዋሪዎቹ ተቃውመዋል፡፡ ምክንያታቸውም መንግሥት አቅማቸውን በማወቅ 20 በመቶ ቅድሚያ ክፍያ ፈጽመው የኮንዶሚኒየም ቤት ባለቤት ለመሆን አምስት ዓመታትን መጠበቅ ግድ እንደሚላቸው ነግሯቸው፣ ተመዝግበው እየቆጠቡና እየጠበቁ መሆናቸውን ነው፡፡ ይኼ ሆኖ ሳለ በድንገት 20 በመቶ ክፍያ እንዲፈጽሙ መጠየቅ ተገቢ አለመሆኑን አውስተዋል፡፡
ደርግ እንኳን ‹‹ሠፈራ›› በማለት ነዋሪዎችን ከቀያቸው ሲያስነሳ ባለአንድ ፎቅ ሕንፃ ገንብቶ በማስረከብ እንደነበር የሚናገሩት ነዋሪዎቹ፣ ‹‹ምን ያመጣሉ›› በማለት ከአራት ወር በኋላ በጥር ወር ውስጥ ለዘመናት የኖሩበት ቤት እንደሚፈርስ ማሳወቅ ተገቢ ባለመሆኑ፣ መንግሥትም ሆነ የሚመለከተው አካል ለነዋሪዎች ክብር በመስጠት ነገሩን እንዲያጤነው ጠይቀዋል፡፡
የነዋሪዎቹን ቅሬታ በመግለጽ ማብራሪያ እንዲሰጡን ያነጋገርናቸው በአራዳ ክፍለ ከተማ የመሬት ልማት ማኔጅመንት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ ሙሉጌታ፣ ‹‹አስተዳደሩ ወይም መንግሥት ማንንም መጉዳትና መበደል አይፈልጉም፡፡ የደጃች ውቤ ሠፈር ነዋሪዎች ወደ ሌላ አካባቢ እንደሚዛወሩ የነገርናቸው ተማሪዎችን ታሳቢ ባደረገ መንገድ ዕቅዳችንን ነው፤›› ብለዋል፡፡
ነዋሪዎቹ በዋናነት እንዲነሱ የተነገራቸው መንግሥት እያስገነባው ላለው የቀላል ባቡር ፕሮጀክት ከሚያስፈልጉት አራት ተርሚናሎች መካከል አንዱ ፒያሳ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት በቀኝ በኩል እስከ ደጃች ውቤ ሠፈር ስምንት ሔክታር ቦታ ላይ መሆኑን አቶ ግርማ ገልጸዋል፡፡ ጫፍ ላይ ላሉ ነዋሪዎች ቀደም ብሎ የተነገራቸውና ያወቁ ቢሆንም፣ ቀሪዎቹን ማወያየትና ማሳወቅ አስፈላጊ በመሆኑ መስከረም 11 ቀን 2006 ዓ.ም. ማወያየታቸውን የገለጹት ኃላፊው፣ መንግሥት ድርጊቱን እየፈጸመ ያለው ቅርስን ካለመፈለግና ነዋሪዎችን ከማፈናቀል አኳያ መታየት እንደሌለበት አስገንዝበዋል፡፡ 
ቅርስም ሆነ ሌላ ነገር ከባቡር ተርሚናሉ ጋር የሚገናኝ ከሆነ መፍረሱ የማይቀር መሆኑን የገለጹት ኃላፊው፣ እንዲፈርስ ውሳኔ የተላፈበት ቦታ 11.6 ሔክታር መሆኑንና ለተርሚናልና ለኃይል መሙያ ስምንት ሔክታር ተወስዶ ቀሪው 3.6 ሔክታር ለመልሶ ማልማት እንደሚውል አቶ ግርማ ገልጸዋል፡፡ ከባቡር ተርሚናል የሚተርፈው 3.6 ሔክታር ቦታ የግል ይዞታ ከሆነና በፕላኑ መሠረት ለመኖሪያ ቤት ወይም ለድርጅት የሚጋብዝ ከሆነ፣ ባለይዞታዎቹ እንዲያለሙት ቅድሚያ እንደሚሰጣቸው አቶ ግርማ ጠቁመዋል፡፡ 
‹‹ማንም ነዋሪ እንዲንገላታ አንፈልግም፡፡ በፌዴራል አዋጅ ቁጥር 455/97 መሠረት ለልማት ለሚነሱ ነዋሪዎች ሁለት አማራጮችን እናቀርብላቸዋለን፤›› ያሉት አቶ ግርማ፣ አንደኛው በቀበሌ ወይም በኪራይ ቤት የሚኖሩ ከሆነ ከስቱዲዮ እስከ ሁለት መኝታ ቤት የጋራ መኖሪያ ቤት እንዲያገኙና 20 በመቶ ቅድሚያ ክፍያ እንዲፈጽሙ ማድረግ ነው፡፡ ሁለተኛው አማራጭ ደግሞ በሌላ ቦታ የቀበሌ ወይም የኪራይ ቤት እንዲያገኙ ማድረግ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ ነዋሪዎቹ የኮንዶሚኒየሙን ቅድሚያ ክፍያ መንግሥት እንዲከፍልላቸው መጠየቃቸውን የገለጹት ኃላፊው፣ ጥያቄያቸው አግባብነት የሌለውና አሁን የሚኖሩት በትንሽ ክፍያ የነፃ ያህል መሆኑን፣ ቦታውና ቤቱም የመንግሥት በመሆኑ አቅም ከሌላቸው በመመርያው መሠረት በቀበሌ ቤት እንዲኖሩ እንደሚደረግ ገልጸዋል፡፡ ወደፊት በጋራ ሕንፃ ላይ መኖራቸው ስለማይቀር ያለዕጣ የማግኘት ዕድላቸውን እንዲጠቀሙ መክረዋል፡፡
የግል ይዞታ ያላቸው ነዋሪዎችን ለመለየትና ለማወቅ ትክክለኛው መረጃ ገና በመሰባሰብ ላይ ቢሆንም ከ105 በላይ እንደሚሆኑ የገለጹት ኃላፊው፣ እነሱም በአዋጅና በመመርያ ቁጥር 3/2002 መሠረት ሁለት አማራጮች እንደተዘጋጁላቸው ተናግረዋል፡፡ አንደኛ አማራጭ በመንግሥት መሬት ላይ የሠሩት ቤት ካሳ ተከፍሏቸው ኮንዶሚኒየም ቤት በቅድሚያ እንዲያገኙ ማድረግ ሲሆን፣ በሁለተኛ ደረጃ ካሳ ተከፍሏቸው በመሀል ከተማ ቦታ እንደሚሰጣቸው ወይም በማስፋፊያ አካባቢ እንዲመርጡ ማድረግ መሆኑን አቶ ግርማ አብራርተዋል፡፡ ነዋሪዎቹ በዚህ ዓመት መጨረሻ ሊነሱ እንደሚችሉ የጠቆሙት ኃላፊው፣ ምናልባት ነገሮች ከተመቻቹ በጥር ወር ሊያሸጋግሯቸው እንደሚችሉ በስብሰባ ላይ እንደነገሯቸው አስረድተዋል፡፡
ከቅርስ አጠባበቅ ጋር በተያያዘ ለተነሳላቸው ጥያቄ አቶ ግርማ በሰጡት ምላሽ፣ ‹‹አንዳንዶቹን ከቅርስ አኳያ የምናያቸው አሉ፡፡ በመመርያው መሠረት የሚሆነው ይሆናል፡፡ ለምሳሌ ያህል ዶሮ ማነቂያ አካባቢ እየተለዩ ነው፡፡ የባቡር ተርሚናሉና ኃይል መሙያው የሚሠራበት ከሆነ ግን ለድርድር አይቀርብም፡፡ ይፈርሳል፡፡ መታሰብ ያለበት ነገር ቢኖር ጊዜያዊውን ችግር ብቻ ሳይሆን ኅብረተሰቡ ወደተሻለ ሕይወት ማለፍ ስለሚኖርበት ነው፤›› ሲሉ አቶ ግርማ ገልጸዋል፡፡ 
በደጃች ውቤ (ውቤ በረሃ) ሠፈር ከሚፈርሱት ቤቶች መካከል የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ዩኒቨርሲቲ ሲማሩ ይኖሩበት የነበረውና ከራስ መኮንን ድልድይ በስተቀኝ በኩል የሚገኘው ዓድዋ ሆስቴል፣ የታዋቂው አኮርዲዮን ተጨዋች አቶ ፍሬው ኃይሉ ቤት፣ የኢትዮጵያ ባለውለታ የነበሩትና በዳግማዊ ምኒልክ ዘመን ከቱርክ መሣሪያ በመግዛት ለኢትዮጵያ ያመጡ የነበሩት አርመናዊው ሚስተር ቴራዚያን ቤተሰቦች መኖሪያ ቤት፣ በቀይ ሽብር ቤተሰቦቻቸው የተገደሉባቸው አፈ ንጉሥ ተክሌ ቤት፣ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን የነበሩት የጄነራል መልኬ ቤት፣ በደርግ ዘመን የዘመቻ መምርያ ኃላፊ የነበሩት ከበደ ስመኝ ቤት፣ በደርግ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የነበሩት አቶ ቢልልኝ ማንደፍሮ ቤት፣ የመጀመሪያው ስፖርት ቤት መሥራች ሙሉ ስፖርት ቤት፣ የመጀመሪያው የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ በረኛ አቶ ታደሰ ጌጤ ቤት፣ የቡድኑ መሥራችና ተጨዋች የነበሩት አቶ አየለ አትናሸ ቤት ጥቂቶቹ ሲሆኑ፣ በአጠቃላይ ከ775 በላይ ቤቶች እንደሚፈርሱ ታውቋል፡፡  
 ምንጭ ሪፖርተር ጋዜጣ

Tuesday, September 24, 2013

15 የሚሆኑ የአንድነት ፓርቲ አባለት ዛሬ ህገወጥ እስር ተፈፀመባቸው የተቀሩት ስኬታማ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ ናቸው

አንድነት ፓርቲ በመጪው እሁድ መስከረም 19 ከ33ቱ ፓርቲዎች ጋር ለሚያደርገው ሰላማዊ ሰልፍ የመኪና ላይ ቅስቀሳ ሲያደርጉ የነበሩ 15 አባላቱ ህገወጥ እስር ተፈፀመባቸው፡፡ አባላቱ ከስድስት ኪሎ ወደ አራት ኪሎ በሚወስደው ጎዳና በመኪና ላይ እየቀሰቀሱ ባለበት ወቅት ሚኒሊክ ት/ቤት ፊትለፊት የፖሊስና የደህንነት ኃይሎች የሚተላለፈውን መኪና መንገድ በመዝጋት ቅስቀሳውን አደናቅፈዋል፡፡
በስፍራው የነበሩ በርካታ ሰዎች “ቀስቃሾቹ ህጋዊ ወረቀት ይዘዋል፤ልቀቋቸው” በማለት ተቃውሞ አሰምተዋል ከአንድነት ፓርቲ ጎን እንደሚቆሙም ተናግረዋል፡፡ ፖሊስ 15 የሚሆኑትን የቅስቀሳ ቡድን አባላት ወደ ሁለተኛ ፖሊስ ጣቢያ ወስደዋቸዋል፡፡ የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች አባላቱ ወደ ታሰሩበት 2ኛ ፖሊስ ጣቢያ በመሄድ ረ/ኢ መንግስቱ ለማ የተባሉትን የፖሊስ ጣቢያው ኃላፊ የታሰሩት አባላት እንዲለቀቁ ጠይቀዋል፡፡ ኃላፊውም “ህጋዊ ሰልፍ እንደምታደርጉ እናውቃለን ይቀስቅሱ የሚል መመሪያ አልደረሰንም ብለዋል፡፡ አመራሮቹ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነርንና የከተማዋን መስተዳድር ሃላፊዎች ለማነጋገር ተንቀሳቅሰዋል፡፡
በተለያየ አቅጣጫ የተሰማሩት ሌሎቹ የአንድነት ፓርቲ ቅስቀሳ ቡድን አባላት ስኬታማ የመኪና ላይ ቅስቀሳ በማደረግ ላይ ናቸው፡፡ #millonsofvoicesforfreedom #Ethiopia#UDJ

Monday, September 23, 2013

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ለሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት የበይነ መረብ ዘመቻ መግለጫ

ላለፉት ሶስት ወራት ስኬታማ ህዝባዊ ንቅናቄ ሲያደርግ የቆየው አንድነት ፓርቲ የመጀመሪያውን ዙር ለሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ህዝባዊ ንቅናቄ መስከረም 19 ቀን 2006 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ከሰላሳ ሶስቱ ፓርቲዎች ጋር በሚያደርገው ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ያጠናቅቃል፡፡ የህዝባዊ ንቅናቄው አካል የሆነው የበይነ መረብ ዘመቻ(online social media campaign) ከመስከረም 14-18 ቀን 2006 ዓ.ም ይደረጋል፡፡ ዘመቻው ትኩረት የሚያደርገው የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ህዝባዊ ንቅናቄ ቀዳሚ አጀንዳ በሆነውና የፀረ ሽብር ህጉ እንዲሰረዝ በሚጠይቀው የትኩረት ነጥብ ላይ ነው፡፡
ለአምስት ቀናት የሚቆየው የበይነ መረብ ዘመቻ አንድነት ፓርቲ የጸረ ሽብር ህጉ እንዲሰረዝ የጠየቀባቸውን ጉልህ ህገ መንግስታዊ መሰረታዊያን በማብራራት ህዝባዊ ንቅናቄውን በበይነ መረብ (online social media campaign) የሚያቀጣጥል ነው፡፡ የበይነ መረብ ዘመቻው የፖለቲካ አስተሳሰብ ልዩነቶችን ወደ ጎን በመተው መሰረታዊ ህገ መንግስታዊ መብቶችን የሚደፈጥጠው የፀረ ሽብር ህግ እንዲሰረዝና መንግስት ህገ መንግስቱን እንዲያከብር የሚጠይቅ ነው፡፡
በዚህ ዘመቻ የተለያየ ርዕዮተ አለም የሚከተሉ ሆኖም ህገ መንግስቱ እንዲከበር የሚጠይቁ የዴሞክራሲያዊ ኃይሎች አባላት፣ ነፃ የሲቪክ ማህበረሰብ አባላት፣ የሀገሬ ጉዳይ ይመለከተኛል ለሚሉ ዜጎች፣ የመብት አራማጆች(አክቲቪስቶች) እና ህገ መንግስቱ እንዳይሸራረፍ የሚፈልጉ የኢህአዴግ አባላት እንደሚሳተፉበት ይጠበቃል፡፡
ለበይነ መረብ ዘመቻው የተዘጋጁ የፕሮፋይል ምስሎችና የከቨር ምስሎችን በመቀየር እንዲሁም#millionsofvoices የሚለውን ሀሽ ታግ በመጠቀም የሚተላለፉ መልዕክቶቻችንን በማሰራጨት ለህገ መንግስት የበላይነት እንዲቆሙ በአክብሮት ይጠየቃሉ፡፡
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ
ለሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት
ግብረ ኃይል

Sunday, September 22, 2013

አባይ ወልዱና ደብረጽዮን ሽጉጥ ተማዘው ነበር – የአባይ ቡድን በሁለት ተከፈለ (አብርሃም ደስታ – ከመቀሌ)

ህወሓት በአባይ ወልዱና ደብረፅዮን ቡድኖች በሁለት መከፈሉ ይታወቃል። ባለፈው የህወሓት የማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ የአባይና የደብረፅዮን ጠብ በጣም በመክረሩ የተነሳ ሽጉጥ መማዘዛቸው ተሰምቷል። ሃይለማርያም ደሳለኝና በረከት ስምዖን ለማስታረቅ የሞከሩ ሲሆን ዉጤቱ አልታወቅም።
ትንቅንቅ
ይህ በንዲህ እንዳለ የአባይ ቡድንም ሰሞኑ በሁለት ተከፍሏል፤ የአባይ ወልዱና የበየነ መክሩ። ከህወሓት ስብሰባ በኋላ የስልጣን ሽግሽግ ለማድረግ የተሞከረ ቢሆንም በየነ መክሩና ኪሮስ ቢተው ከስልጣናቸው ለመውረድ (ሓላፊነት ለመቀየር) ፍቃደኛ ባለመሆናቸው ከአባይ ወልዱ ጋር ከፍተኛ አምባጓሮ ተፈጥሯል።
ኪሮስ ቢተው የግብርና ቢሮ ሓላፊና የኢንተርፕራይዞች የቦርድ ሰብሳቢ ነበር። አባይ ወደ ሌላ ቢሮ ሊቀይሮው አስቦ ፍቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል። የኢንተርፕራይዞች (ብዙ በጀት የሚመደብበት) ስልጣን ግን ቀምቶ ለአለም ገብረዋህድ ሰጥቶታል። ግብርና ቢሮም ለወደ አዳል ታስቦ ነበር። ግን ጠብ ስለተነሳ አልተሳካም። በየነ መክሩም የንግድና ኢንዱስትሪ (የከተማ ልማት ጨምሮ) ስልጣን በእጁ ሲሆን አባይ ቢሮው ለሌላ ሊሰጠው ፈልጎ ፍቃደኛ ባለመሆኑ ግን እስካሁን ውዝግብ ላይ ናቸው። በየነ መክሩ ወደ ሀገሩ (እስራኤል) የመሄድ ሓሳብ ይዟል።
የአባይ ቡድን በሁለት መከፈሉ (አባይና በየነ የሚመሩት) ማሳያ በትግራይ ክልል የዉሃ ሃብት ቢሮ አመራር አባላት የሁለቱ ቡድኖች ደጋፊዎች ተጣልተው እንደተደባደቡና አከባቢው እስካሁን በፌደራል ፖሊስ እየተጠበቀ መሆኑ ተረጋግጧል።
ስርዓት ሲበሰብስ እንዲህ ነው። ለማንኛውም ቸር ያሰማን።
It is so!!!

Short URL: http://www.zehabesha.com/amharic/?p=7629

ቀጣዩ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ማን ሊሆን ይችላል?

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ርዕሰ ብሔር በመሆን በሁለት ዙር ለ12 ዓመታት ያገለገሉት ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ፤ የስልጣን ዘመናቸው ሊያበቃ የቀራቸው ጥቂት ቀናት ብቻ ነው። ይሄም ሆኖ ግን ቀጣዩ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ማን ሊሆን እንደሚችል አሁንም ድረስ ፍንጭ አልተገኘም። የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ ናፍቆት ዮሴፍ በፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ የስልጣን ዘመን የስራ ክንውኖች ዙሪያ የተለያዩ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችን ባለስልጣናትንና ምሁራንን አስተያየቶች አሰባስባለች፡፡ የ90 ዓመቱ የዕድሜ ባለፀጋ ፕሬዚዳንት ግርማ ምን ተሳካላቸው፣ ምንስ ከሸፈባቸው? እሳቸውን የሚተካው አዲሱ ፕሬዚዳንትስ ማን ይሆን? አስተያየቶቹ እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡
=============
“የመምረጥ እድል ቢሰጠኝ ወ/ሮ ሙሉ ሰለሞንን እመርጣለሁ” ዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማሪያም ፕሬዚዳንት ግርማ እስካሁን በስልጣን ላይ ሲቆዩ ይህን ሰሩ፣ ይህን አደረጉ የምለው አንድም ወደ አዕምሮዬ የሚመጣ ነገር የለም። አንድም ጊዜ አቋም ወስደው በአገር ፖሊሲ ላይ ጫና ሲፈጥሩ አይቼም ሰምቼም አላውቅም። እንደውም እውነቱን ለመናገር ከነመኖራቸውም ትዝ አይሉኝም፡፡ አንድ ጊዜ እንደውም “አሰብ የኤርትራ አንጡራ ሀብትና ግዛት ናት” ሲሉ በጆሮዬ ሰምቼ እጅግ አዝኜባቸዋለሁ፡፡ ይህን በቴሌቪዥን ነው የተናገሩት፡፡ ቦታው ለምልክትነት ካልሆነ ብዙ የሚሰራበት አይደለም በሚለውም አልስማማም፡፡ ፕሬዚዳንቱ ሊያከናውኗቸው የሚችሏቸው የተለያዩ ተግባራት አሉ፡፡ በግልፅ የተቀመጡትን እንግዳ መቀበል፣ ፓርላማ መክፈት እና የመሳሰሉትን ትተን፣ በርካታ ስራዎችን መከወን ይችሉ ነበር፡፡ ለምሳሌ አንዳንድ የበጐ አድራጐት ስራዎችን መምራት፣ የተለያዩ ማህበራትን ማጠናከር፣ ህዝቡን ለስራ ማደፋፈር፣እስረኞችንና ህሙማንንን መጐብኘትና ያሉበትን ሁኔታ መከታተልና የመሳሰሉትን ሊሰሩ ይችሉ ነበር፡፡
ከዚህም ባለፈ የውጭ ግንኙነት ላይ የዲፕሎማሲ ስራዎች ሞልተዋል፡፡ ነገር ግን እኔ አንዱም ላይ ሲንቀሳቀሱ አላየሁም፡፡ ስለዚህ በዚህች አገር ፕሬዚዳንትነት ላይ ብዙም የሚታወሱ አይደሉም ማለት እችላለሁ፡፡ የተለያዩ የአለምና የአፍሪካ ፕሬዚዳንቶች በርካታ ስራዎችን ይሰራሉ፣ የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ግን እንቅስቃሴያቸው በጣም ደካማ ነው፡፡ በቀጣይ ማን ፕሬዚዳንት ይሁን በሚለው ላይ የመምረጥ እድል ቢሰጠኝ አንድ ዕጩ አለኝ በውስጤ፡፡ የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ሙሉ ሰለሞን ፕሬዚዳንት ሆነው ቢመረጡ በጣም ደስ ይለኛል፡፡ ይህ በተለይ ለኢትዮጵያ ሴቶች ትልቅ አቅም ይፈጥራል። አሁን ባሉበትም ብዙ እየሰሩ ነው፣ ወደፊትም ብዙ ለመስራት አቅም እንዳላቸው ይሰማኛል፡፡ በመሆኑም እጩ ምረጥ ብባል ለወ/ሮ ሙሉ ሰላምን ቅድሚያ እሰጣለሁ፡፡ “ፕሬዚዳንቱ ለሁለተኛ ጊዜ መመረጣቸው ፈፅሞ ስህተት ነበር” አቶ ሙሼ ሰሙ (የኢዴፓ ሊቀመንበር) እኔ እስካሁን በኖሩበት የፕሬዚዳንት ዘመናቸው አንድም የማስታውሰው ስኬት የላቸውም፡፡
ይህን የምልበት ምክንያት አንደኛ፣ ጤነኛ ሆነው አመቱን ሙሉ የሰሩበትን ጊዜ አላስታውስም፡፡ ሁለተኛ፣ የሰውነት አቋማቸው በንቃት እንዲንቀሳቀሱ የሚያደርጋቸው አልነበረም፡፡ በሶስተኛ ደረጃ፣ ባሉበትም ሁኔታ ይህን ሰሩ ብዬ በግልፅ የምጠቅሰው ነገር የለኝም፡፡ በዚህች አገር ጉዳይ ላይ፣ ይህችን አገር ወደፊት ያራመደ ጠንካራም ሆነ ደካማ የማስታውሰውም የማውቀውም ነገር የለም። እኔ ፕሬዚዳንት ግርማን የማውቃቸው በአገር ምልክትነታቸውና መገለጫነታቸው ብቻ ነው፡፡ ፕሬዚዳንቱ ህገ-መንግስቱ ሰፍሮ ከሰጣቸው ስልጣን ባለፈ በፕሬዚዳንትነታቸው ሊሰሯቸው የሚችሏቸው ሥራዎች ሞልተዋል፡፡ ለምሳሌ የፕሬዚዳንቱ ቦታ የዲፕሎማቲክ ስራዎችን እንዲሰሩ ያደርጋቸዋል፡፡ ብዙ ማህበራዊ እንቅስቃሴዎችም አሉ፡፡ ምናልባት አንድ ወቅት ላይ በእርሳቸው ተጀምሮ የከሸፈ ወይም የት እንደደረሰ የማላውቀው የአገሪቷ የደንና የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ነበር።
አሁን በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ አላውቅም፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ሊሰራባቸው የሚገቡ ነገሮች አሉ፡፡ ለምሳሌ ከጤና፣ ከአረጋዊያን፣ ከህፃናትና ከሴቶች፣ ከህፃናት ጥቃትና መሰል ጉዳዮች ጋር የተገናኙ ሥራዎች ሞልተዋል፡፡ በፖለቲካውም ማህበራትን በማቋቋምና በማጠናከር፣ እንዲሁም በት/ቤቶች ዙሪያ ሊሰሩ የሚችሉ እጅግ በርካታ ነገሮች አሉ፡፡ ይህቺ አገር የሚያስፈልጓት ስራዎች ማለቴ ነው፡፡ እናም እርሳቸው የሀገሪቱ ምልክት እንደመሆናቸው ከተለያዩ አገራት መንግስታት ጋር እየተገናኙ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ፋውንዴሽኖችን ማቋቋምና ማጠናከር ይችሉ ነበር፡፡ የሌሎች አገሮች ፕሬዚዳንቶች ይህንን ያደርጋሉ። በሴቶችና በህፃናት ጥቃት ጉዳይ፣ በህፃናት የትምህርት ጉዳይ፣ በጤናና በበርካታ ሚሊዮን ጉዳዮች ዙሪያ ሊንቀሳቀሱና ሊሰሩ ይችሉ ነበር፡፡ ይህቺ አገር ያለባት ማህበራዊ ችግር ሠፊና ጥልቅ መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡
ይህ ከማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ነው፡፡ በፖለቲካው ረገድ ብትወስጂው እዚህ አገር እጅግ በርካታ ችግሮች አሉ፡፡ ለምሳሌ በፖለቲካ፣ በወንጀል እና በተያያዥ ጉዳዮች ወህኒ ቤት የሚገኙ እስረኞች አሉ፡፡ የእነዚህ እስረኞች ጉዳይ መፍትሄ አግኝቶ በቀላሉ የሚፈቱበትን ሁኔታ ለማመቻቸት በሠፊው መስራት ነበረባቸው፡፡ አንዳንዱ ሰው እኮ እስር ቤት የቆየበትን ምክንያት እንኳን አያውቀውም፡፡ ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ ከኦነግ ጋር፣ ከኦብነግ ጋርና ከተለያዩ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ጋር በተያያዘ እስር ቤት ገብተው እስካሁን ያልተፈቱ ሰዎች አሉ፡፡ ይህ ጉዳይ አንድ ማህበራዊ ተቋም ተመስርቶ፣ ተጣርቶና መፍትሄ አግኝቶ መስተካከል ነበረበት፡፡ ይህን መስራት ያልቻሉት በጤናና በአቅም ሁኔታ ይመስለኛል፡፡ ከዚህ በፊት በነበረው መንግስት በርካታ ተጠቃሽ ስራዎችን ሰርተዋል፡፡ ቀላል የማይባሉ ተቋማትን በማጠናከር ረገድም ብዙ ስራዎችን አከናውነዋል፡፡ ሰውየው የብቃት ችግር አለባቸው ብዬ አላምንም፡፡ አሁን ግን የእድሜ፣ የጤናና የሰውነት አቋም ችግሮች ተደማምረው በፕሬዚዳንትነታቸው መስራት የሚገባቸውን እንዳይሰሩ አድርጓቸዋል፡፡ ይህ መቼም ግልፅና ብዙም የማያወዛግብ ጉዳይ ነው፡፡
በተለይ ሁለተኛው ተርማቸው ፈፅሞ መደረግ ያልነበረበት ነው። አሁን ኢትዮጵያ ወደፊት ለመራመድ ከምትፈልገው አቅጣጫ አኳያ ጠቃሚ ያልሆነ ውሳኔ ነበር፡፡ ኢትዮጵያ አሁን ልማት፣ እድገትና ብልፅግና ማምጣት የምትፈልግ አገር ነች፡፡ የዚያ መገለጫ የሚሆን ፕሬዚዳንት ነው የሚያስፈልጋት፡፡ ለእኔ ያንን መገለጫ የሚያሳዩ ፕሬዚዳንት አልነበሩም፡፡ እንዳልኩሽ ኢትዮጵያ ራዕይ አላት፡፡ ራዕይ ስልሽ የኢህአዴግ ራዕይ አይደለም፣ የዜጐች ራዕይ ማለቴ ነው፡፡ ያ ራዕይ ደግሞ ዜጐች ከድህነት ወጥተው፣ የተረጋጋ የኢኮኖሚና በተረጋጋ አገር ውስጥ የመኖር ራዕይ አላቸው፡፡ ይህንን ለማምጣት ደግሞ አቅምና ብቃት ያለው ገለልተኛ ፕሬዚዳንት ያስፈልጋል፡፡ ገለልተኛ ሲሆን የፖለቲካ ተቃርኖዎችን በማስታረቅና መፍትሄ በመስጠት እንዲሁም አቅጣጫ በማሳየት፣ እነዚህን ሁሉ ስራዎች ወደ ውጤት መቀየር የሚችል መሪ ይሆናል፡፡ ከላይ የተጠቀሱትን የዜጐች ራዕይ ማን ያሳካል ለሚለው፣ እከሌ ማለት ምኞት ብቻ ነው የሚሆነው። አንደኛ፣ ኢህአዴግ ይህን እድል ለማንም አይሰጥም። ሁለተኛ የራሱን ሰው መርጧል፡፡ ሲመርጥ ደግሞ በራሱ መስፈርት ነው፡፡ ከብሄር፣ ከሀይማኖትና ከመሰል ጉዳዮች አኳያ እንደሚመርጥ ነው የሚገመተው፡፡ ከዚህ በፊት በውስጤ ያሉ ሰዎች ነበሩ፡፡ አሁን ግን ከኢህአዴግ አኳያ አቅጣጫውን ሳየው፣ እከሌ ወይም እንትና ማለት ጥቅም የለውም፡፡
ስለዚህ አስፈላጊ አይደለም። ምክንያቱም ኢህአዴግ እንዲህ አይነት እድል የሚሰጥ ባህሪ የለውም፡፡ የሰዎችን ባህሪና ስነ-ልቦና አዳምጦ፣ ጠቃሚ የሆነን ሰው ወደዚያ ቦታ ለማምጣት ተነሳሽነት ያለው ድርጅት አይደለም፡፡ ስለዚህ አሁን አስተያየት መስጠት ዝም ብሎ ምኞት ብቻ ነው የሚሆነው፡፡ እኔ ደግሞ የምኞት ሰው ሳልሆን የተግባር ሰው ነኝ፡፡ “እንኳን አቶ ግርማ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳስ ምን ሰራና ነው” ፕ/ር መስፍን ወ/ማሪያም ለመሆኑ አቶ ግርማ ምን ሰርቶ ነው ስኬት ነበረው ውድቀት ነበረው የምትይው? አሁን ይሄን ጥያቄ ብለሽ ነው የምትጠይቂው ወይስ ጠፍቶሽ ነው? በመጀመሪያ ደረጃ ምን ሀላፊነት ተሰጠውና ነው ስኬት ውድቀት የምትለኪበት? የፕሬዚዳንቱ ስራ ዝም ብሎ ቁጭ ማለት ነው፡፡ ወደ 12 ዓመት ገደማ ቁጭ ብሏል ይወጣል፣ በቃ አለቀ፡፡ የምን ስኬት ነው? ምንስ ስራ ተብሎ ነው ስኬቱ የሚለካው? በመሰረቱ ህጉ ራሱ ምንም ሀላፊነት እና ሥራ አይሰጠውም፡፡ በህጉ ላይ የተወሰኑ ነገሮች አሉ፡፡ ሰዎችን መቀበል፣ እንግዶችን ማስተናገድ፣ አምባሳደሮችን መቀበልና መሸኘት፣ ይቅርታ መስጠት፣ “ይሙት በቃ” የተፈረደባቸውን ሰዎች ፈርሞ ማፅደቅ የመሳሰሉትን ያከናውናል፡፡ ይህንንም ቢሆን የሚፈፅመው ግን ከላይ ያሉት ሲፈቅዱለት ነው፡፡ ይህን ጉዳይ እናንተ ጋዜጠኞቹም ታውቁታላችሁ፣ ዝም ብላችሁ ነው የምታደርቁን፡፡
እኔ የምለው--- ከእርሱ በፊት የነበረው ፕሬዚዳንት ነጋሶ ጊዳዳስ ምን ሰራ? እንኳን አቶ ግርማ? ዝም ብሎ ተቀምጦ ኖሮ ጊዜው ሲደርስ ወጣ፣ በቃ ይሄው ነው፡፡ አንድ ሰው ስኬቱና ውድቀቱ የሚለካው ይህን ይህን ይሰራል ተብሎ በጉልህ የተቀመጠ እና ሊያሰራ የሚችል ሁኔታ ላይ ሲሆን ነው፡፡ ይሄ በሌለበት ስኬት ውድቀት የሚባለው ነገር አይገባኝም፡፡ አዲሱ ፕሬዚዳንት ማን ይሁን? ምን ይስራ? ለሚባለው የማውቀው ነገር የለኝም፡፡ እኔን ተይኝማ ጐሽ! “ፕሬዚዳንት የሚሆኑ ሰዎች ጤናማና ቀልጣፋ ቢሆኑ እመርጣለሁ” ኢ/ር ይልቃል ጌትነት (የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር) ፕሬዚዳንቱ ስኬታቸው ውድቀታቸው ምንድነው የሚለው ጥያቄ ከባድና የሚገርም ጥያቄ ነው፡፡ እኔ እንደውም ባልናገር ይሻለኛል፡፡ እንዴ! እርሳቸው ቤተ-መንግስት ገብተው ሲጦሩና ሲታከሙ ኖሩ እንጂ ምን የሰሩት ስራ አለና ነው እንደ ጥያቄ የሚነሳውስ፡፡ እናንተም ቢሆን እንዴት አንድ ነገር ሳንፅፍ ይሰናበታሉ በሚል ለወጉ ነው እንጂ ያነሳችሁት ምንም አለመስራታቸውን ሳታውቁት ቀርታችሁ አይደለም፡፡ በግላቸው በተፈጥሮ ሳይንሱና በአካባቢ ጥበቃ ላይ ፍላጐት እንዳላቸው በተደጋጋሚ ሲናገሩ እሰማለሁ፡፡ ነገር ግን ያ ጉዳይ ወደ ተግባር ተለውጦ ማየት ነበረብን፡፡
እኔ በበኩሌ ይሄ ነው የሚባል ነገር አላየሁም፡፡ እርሳቸው ርዕሰ መንግስት ሳይሆኑ ርዕሰ ብሄር ናቸው፣ ስለዚህ እሳቸው ሊሰሩ ይገባ የነበረው ይቅርታን የመስበክ፣ ሁሉንም ፓርቲዎች እኩል የማየት፣ በሀይማኖት ጉዳይ ችግር ሲከሰት የራሳቸውን አስተዋፅኦ ማድረግ ነበር፡፡ ነገር ግን እርሳቸው ጤናቸውም፣ እድሜያቸውም ምክንያት ሆኖ የስራ እንቅስቃሴያቸው ትክክለኛ ፕሬዚዳንት ሊያደርገው የሚችለው አይነት አልነበረም፡፡ በሁለተኛ ደረጃ፣ እርሳቸው ኢህአዴግን ከማመን ውጭ በራሳቸው ተንቀሳቅሰው ይህን አደረጉ የሚባልላቸው ነገር የለም፡፡ በሶስተኛ ደረጃ፣ ቦታውም ሆን ተብሎ በህገ-መንግስቱ ሲፀድቅ ባዶ ከመሆን የማይሻል ተደርጐ ስለሆነ እኔ እንደ አንድ የፖለቲካ ቁምነገር ለማየት እቸገራለሁ፡፡ በነገራችን ላይ ህገ-መንግስቱ ላይ ባይቀመጥም ፕሬዚዳንቱ ብዙ ሊሰሯቸው የሚገቡ ነገሮች አሉ፡፡ እርሳቸው ግን ምንም አላደረጉም፡፡ ለምሳሌ በሀይማኖቶች አካባቢ ያለውን እንመልከት፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለሁለት ተከፍሎ ችግር ላይ ነበር፡፡ በአንድ ወቅት እነዛም ከውጭ ይምጡና ይወዳደሩ የሚል ሀሳብ ካቀረቡ በኋላ፣ ፖለቲከኞቹ ሲቆጧቸው ሀሳቡን አንስቻለሁ አሉ። በእስልምና እምነት ተከታዮች መካከል ይህ ሁሉ ችግር ሲፈጠር፣ እንደ ርዕሰ-ብሄርነታቸው መንግስት ከዚህ ጨዋታ እንዲወጣና ችግሮቹ መልክ እንዲይዙ ማድረግ ይችሉ ነበር፡፡ በምርጫው ጊዜ በፓርቲዎች መካከል አለመግባባት ሲፈጠር ወደ እርቅ፣ ወደ መቻቻልና ወደ ሰላም እንዲመጡ የራሳቸውን አስተያየትና ሀሳብ መስጠት ይችላሉ፡፡
እንደርዕሰ ብሄርነታቸው ጐላ ባለ መልኩ ሊሰሯቸው የሚችሏቸው በርካታ ነገሮች ነበሩ፣ ነገር ግን እንደነገርኩሽ ዕድሜያቸውም ሆነ ጤናቸው እንዲሁም አጠቃላይ ሁኔታቸው ያንን እንዲከውኑ አላደረጋቸውም። በዘመኑ ቋንቋ “ከደረጃ በታች ተጫውተዋል” ነው የእኔ አስተያየት፡፡ በትምህርት ዝግጅት፣ በዲፕሎማሲ በአጠቃላይ ሁኔታዎች እከሌ ቢመረጥ የምትለው አለ ወይ ለተባልኩት እኔ በእውነቱ ምንም እከሌ የምለው ሰው የለኝም፡፡ አንደኛ የሚመረጠው ሰው በኢህአዴግ ኮረጆ ውስጥ ገብቶ ነው የሚሰራው፡፡ ሁለተኛ ቦታውም እዚህ ግባ የሚባል ስልጣን በህገ-መንግስቱ አልተሰጠውም፡፡ የሚወዳደሩትም ሰዎች በብዛት እዚያ ሲስተም ውስጥ የሚገቡት በዚህ ታሪክ ውስጥ ስማችን ተመዝግቦ እናልፋለን ብለው እንጂ ቦታውን አሁን ባለው ሁኔታ ቁም ነገር እንሰራበታለን ብለው አይደለም፡፡ ስለዚህ ለእኔ ማንም ተመረጠ ማን ለውጥ አያመጣም፡፡ ነገር ግን ጨቋኞች ቢሆኑም የአገር ምልክት ናቸውና ጤነኛ፣ የተማረ፣ ተነጋግሮ በቋንቋ የሚግባባ ሰው፣ በተቀላጠፈ ሁኔታ የሚንቀሳቀስና ያሉትንም ውስን ስራዎች የሚያከናውን ቢሆንና አገር ባይዋረድ እመርጣለሁ፡፡
ከዚህ ባለፈ በስራ ደረጃ ፕሬዚዳንቱ ይህን ሰርቶ፣ ይህን አድርጐ ለውጥ ያመጣል በሚል የምጠብቀው ምንም ነገር የለም፡፡ “ፕሬዚዳንት በህገ-መንግስቱ የተቀመጠላቸውን ሀላፊነት በአግባቡ ተወጥተዋል” ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ ፕሬዚዳንቱ ይህን ሰሩ ወይም አልሰሩም ለማለትም በህገ-መንግስቱ የተቀመጠላቸውን አቅጣጫ ማየት ግድ ይላል፡፡ በህገ-መንግስቱ የተቀመጠና የተሰጣቸው የስራ ሀላፊነት አለ፣ ያንን ከመወጣት አኳያ በተገቢው መንገድ ተወጥተዋል የሚል እምነት አለኝ፡፡ ከዚህ ውጭ በግላቸውም በተለይ አካባቢንና ተፈጥሮን ከመንከባከብ አኳያ የጀመሩት ስራ በጥሩ ሁኔታ ተከናውኗል የሚል እምነት አለኝ፡፡ የእኛ አገር አካሄድ በአብዛኛው ፓርላሜንታሪ ነው፡፡ በፓላሜንታሪ አገር ደግሞ ብዙውን ስራና ሀላፊነት የሚጥለው በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ ስለሆነ ባልተሰጣቸው ሀላፊነት ስራ አልሰሩም ተብሎ የሚወቀሱበት ሁኔታ ያለ አይመስለኝም። ህገ መንግስቱ የፈቀደላቸውን ግን በአግባቡ ተወጥተዋል ባይ ነኝ፡፡ ይቅርታ በማድረግ፣ አምባሳደሮችን በመሾም እና በመሰል ጉዳዮች ላይ ሰርተዋል ወይ ከተባለ፣ አዎ ሰርተዋል። ሹመቶቹንም ቢሆን ቀጥታ መሾም ሳይሆን በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት ነው የሚሾሙት፣ ስለዚህ ስራቸውን ተወጥተዋል፡፡ ስለወደፊቱ ፕሬዚዳንት አመራረጥ መነሻው ህገ-መንግስቱ ነው፡፡
በህገ መንግስቱ መሰረት ለገዢው ፓርቲ የተሰጠ ስልጣን አለ፡፡ ገዢው ፓርቲ ነው ፕሬዚዳንቱን የሚያቀርበው፣ ስለዚህ ስለ ቀጣዩ ፕሬዚዳንት ከዚህ በላይ ማለት አልችልም፡፡ “ፕሬዚዳንት ግርማ ስኬታማም እድለኛም መሪ ናቸው” “የቀጣዩን ፕሬዚዳንት ማንነት መተንበይ አልችልም” አቶ አሰፋ ከሲቶ የፕሬዚዳንቱ አማካሪ የፕሬዚዳንት ግርማ ዋናው ስኬት ለሁለት ጊዜ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዴሞክራሲያዊ መንገድ የመረጣቸው መሆኑ ነው፡፡ ከዴሞክራሲ ሂደቱ አንፃር ይሄ ትልቅ ስኬት ነው፡፡ ከዚህ ባለፈ በራሳቸው ለህዝብ አርአያ የሚሆን በርካታ ስራዎችን ላለፉት 12 ዓመታት ሲያከናውኑ ነው የቆዩት፡፡ የህዝብ አገልጋይነትን ስሜት ይዘው ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ህዝብ ማገልገል መቻላቸው በጣም አስደሳች ነው፡፡ ለምሳሌ የተቸገረ ሰው ወደ እርሳው አቤቱታ ባቀረበ ጊዜ ችግሩ እንዲፈታ ያደርጋሉ፡፡ የቅርብ አማካሪ እንደመሆኔ የእርሳቸውን ውሳኔና ድጋፍ ሊያገኝ የመጣ ሰው የእርሳቸውን ድጋፍና ምክር አግኝቶ የሚሄድበት ሁኔታ እንደነበር አውቃለሁ በአጠቃላይ ዜጐችን የማገልገል እምነታቸውና ፍላጐታቸው ጠንካራ መሆኑን ለማስተዋል ችያለሁ፡፡ በሌላ በኩል እውቀታቸው ከምንምና ከማንም ጋር ተወዳዳሪነት የሌለው ነው።
ለምሳሌ የቋንቋ ችሎታቸው በጣም ሰፊ በመሆኑ ከማንኛውም አገር መሪና ኤምባሲዎች ጋር በመገናኘት በፈለጉት ቋንቋ ሀሳባቸውን የመግለፅ ብቃታቸው ወደር የለውም፡፡ እንግሊዝኛ፣ ፈረንሳኛ፣ ጣሊያንኛና ሌሎችንም ቋንቋዎች አቀላጥፈው መናገር የሚችሉ በመሆናቸው ስለ አገሪቱ ጠቅላላ ሁኔታ በእድገት ጉዞና በተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ የአገርን ገፅታ ግንባታ በመስበክ ስኬታማ መሪ ናቸው፡፡ በጣም አንባቢ ናቸው፡፡ የማስታወስ ችሎታቸው ፍፁም የሚደነቅና ወደር የለሽ ነው፡፡ በዚህ ለሌሎች አርአያ መሆን የሚችሉ ናቸው፡፡ ሌላው ማረሚያ ቤት ገብተው የታረሙ ሰዎች ይቅርታ አግኝተው እንዲወጡ ከፍተኛ ክትትል ያደርጋሉ። አንድ ሰው ወንጀል ፈፅሞ በፍ/ቤት ፍርድ ተሰጥቶ ማረሚያ ቤት የገባ ሰው መታረሙ ከተረጋገጠ ማረሚያ ቤት እንዲቆይ አይፈልጉም፡፡ ታራሚው ከማረሚያ ከወጣ በኋላ ችግር የማይፈጥር መሆኑን እንደ ይቅርታ መስፈርት ይወስዱታል፡፡ እንደውም በአንድ ወቅት የነገሩኝን ባነሳ ደስ ይለኛል፡፡ በ1950ዎቹ ኢሉባቡር ጐሬ ውስጥ ለስራ በሄዱ ጊዜ 15 ሰዎች መንገድ ላይ ቆመው ያገኛሉ። ከመኪና ወርደው “ምንድናችሁ?” ብለው ሲጠይቁ፣ እስረኞች እንደሆኑ መለሱላቸው ከመሀላቸው አንዱ ጠብመንጃ ይዟል፡፡
“አንተስ ጠብመንጃ የያዝከው ምንድነህ?” ብለው ይጠይቁታል፡፡ “ወደ መቱ አጅቦን የሚሄደው ፖሊስ ሊፀዳዳ ወደ ጫካ ገብቶ ጠብመንጃውን ያዝ ብሎኝ ነው” አላቸው፡፡ እርሳቸውም በጣም ተገርመው በወቅቱ መቱ ጠቅላይ ግዛት ሀላፊ ለነበሩት ሰው ደብዳቤ ፅፈው እንዲፈቱ አድርገው ወደ አዲስ አበባ መመለሳቸውን አጫውተውኛል፡፡ እናም የታረሙ ሰዎች እስር ቤት እንዲቆዩ አይፈልጉም፡፡ እድለኛ ናቸው የምለው ደግሞ በእርሳቸው ዘመን ታላቁ የህዳሴ ግድብ በመጀመሩ ነው፡፡ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድም ውጤታማ በሆነ መንገድ ተፈፃሚ እየሆነ ያለበት ወቅት በመሆኑም ስኬታማም እድለኛም ናቸው እላለሁ፡፡ እስካሁን እንደ ርዕሰ ብሄርነታቸው በህገ-መንግስቱ አንቀፅ 11 መሰረት የተሰጣቸውን ስልጣንና ተግባር ሙሉ ለሙሉ በአግባቡ እንደተወጡ አምናለሁ፡፡ በአስፈፃሚ አካል ስልጣንና ሃላፊነት ጣልቃ አይገቡም፡፡ ጠንካራና ታታሪ ሰራተኛ ናቸው፡፡ ለምሳ የማይወጡበትቅ ጊዜ ይበዛል፡፡ ሀላፊነታቸውንና ተግባራቸውን በአግባቡ ተወጥተዋል፡፡ እርሳቸውን ተክቶ የሚሰራውን ሰው መገመት አልችልም፡፡ በህገ መንግስቱ በተቀመጠው መሰረት ቀጣዩ ፕሬዚዳንትም በህዝብ በተወካዮች ም/ቤት እና በፌዴሬሽን ም/ቤት ስብሰባ ተደርጐ በውይይት ተመርጦ ነው የሚቀርበው፡፡ በመሆኑም የቀጣዩን ፕሬዚዳንት ማንነት መተንበይ አልችልም፡፡ የማውቀውም ነገር የለም፡፡
(ምንጭ አዲስ አድማስ)

Saturday, September 21, 2013

ለፕሬዚዳንት ግርማ በወር በ530 ሺሕ ብር ቤት ለመከራየት የተፈረመው ውል ፈረሰ

22 SEPTEMBER 2013 ተጻፈ በ  
የፕሬዚዳንትነት ቆይታቸውን በማጠናቀቅ ላለፉት 12 ዓመታት የቆዩበትን ብሔራዊ ቤተ መንግሥት ለአዲሱ ፕሬዚዳንት እንደሚያስረክቡ ለሚጠበቁት ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ መኖሪያ እንዲሆን በወር 530 ሺሕ ብር የሚከፈልበት ቤት ለመከራየት የተገባው ውል ተሰረዘ፡፡
ምንጮች እንደገለጹት፣ ፕሬዚዳንት ግርማ በቅርቡ ከቤተ መንግሥት ሲለቁ ከነቤተሰቦቻቸው እስከ ሕይወት ፍፃሜያቸው ይኖሩበታል ተብሎ የተመረጠውና በወር 530 ሺሕ ብር ለመክፈል ከቤቱ ባለቤት ጋር የተደረገው ስምምነት፣ የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽሕፈት ቤት ቀርቦ ውል ታስሮበት ነበር፡፡ ሆኖም የኪራይ ስምምነቱ ውል ከተፈረመ ከሁለት ሳምንታት በኋላ የፕሬዚዳንቱ ጽሕፈት ቤት ውሉ እንዲቋረጥ መወሰኑን አስታውቋል፡፡ 
አዲስ አበባ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ውስጥ የሚገኘውን ለፕሬዚዳንት ግርማ መኖሪያ የተመረጠውን ቤት ለመከራየት ከአከራዩ ጋር የኪራይ ውል ስምምነት ያደረገው  የፕሬዚዳንቱ ጽሕፈት ቤት ነበር፡፡ ቀድሞም ቢሆን ስምምነቱ የተጋነነና ለG+1 መኖሪያ ቤት ይህን ያህል ዋጋ ይከፈላል የሚል ሙግት ቀርቦ እንደነበር ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ስምምነቱ በይፋ ከተፈረመ በኋላ ግን የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጭምር ኪራይ ተገቢ አይደለም በማለት ውሳኔ በማስተላለፋቸው፣ የፕሬዚዳንቱ ጽሕፈት ቤት በውሉ ውስጥ የተካተቱትንና ውሉን ለማፍረስ ያስችሉኛል ያላቸውን አንቀጾች በመጥቀስ እንዲሰረዝ አድርጓል፡፡ ይህንንም የመኖሪያ ቤቱን ለማከራየት ውል ለገቡት ባለንብረት በደብዳቤ ማስታወቁንም ምንጮች ገልጸዋል፡፡ የኪራይ ስምምነቱን የመዘገበው የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽሕፈት ቤትም ውሉ መሰረዙን እንዲያውቅ የፕሬዚዳንቱ ጽሕፈት ቤት ደብዳቤ ጽፏል ተብሏል፡፡ 
ሕጋዊ የውል ስምምነት ስለመደረጉ ማረጋገጫ የሰጠውና ምዝገባ ያካሄደው የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽሕፈት ቤት፣ ለፕሬዚዳንቱ መኖሪያ ተብሎ የኪራይ ስምምነት የተደረገበት ውል እንዲሰርዘው በደብዳቤ ተገልፆለታል ተብሏል፡፡ 
ተጋነነ የተባለው የቤት ኪራይ ውል የተፈጸመው በአገሪቱ ሕግ መሠረት ሥልጣናቸውን ለለቀቁት ፕሬዚዳንት ቀሪ ሕይወታቸውን በተሟላ ሁኔታ እንዲያሳልፉ አስፈላጊው ጥቅማ ጥቅም መጠበቅ ስላለበት ቢሆንም በዚህን ያህል ዋጋ ቤት መከራየት ተገቢ አለመሆኑን የሚገልጹም አሉ፡፡ 
እንደ ምንጮች ገለጻ ከሆነ ፕሬዚዳንቱ ከቤተ መንግሥት ሲወጡ ሊኖሩበት የሚችለውን ቤት ለማዘጋጀት የቤተ መንግሥት ጽሕፈት ቤት አምስት የተያዩ ቤቶችን በመምረጥ የተሻለ ነው ተብሎ የተመረጠው አሁን ውሉ እንዲቋረጥበት የተደረገው ቤት ነው ተብሏል፡፡ 
ከኃላፊነት የተነሱት የአገርና የመንግሥት መሪዎች፣ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች፣ የምክር ቤት አባላትና ዳኞች የሚያገኙዋቸውን መብቶችና ጥቅሞች ለመወሰን የወጣው አዋጅ እንደሚደነግገውም ለተሰናባቹ ፕሬዚዳንት ቤት እንደሚዘጋጅ ይጠቅሳል፡፡ 
በዚህ አዋጅ አንቀጽ 4 መሠረት የመኖሪያ ቤት አገልግሎትን በተመለከተ የተጠቀሰው ከኃላፊነት የተነሳ ፕሬዚዳንት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ወይም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ለራሱና ለቤተሰቡ መኖሪያነት የሚያገለግል የሠራተኞች ደመወዝን ጨምሮ በመንግሥት ወጪ የሚተዳደር ከአራት እስከ አምስት መኝታ ክፍሎች ያሉት መኖሪያ ቤት የሚሰጠው መሆኑን ነው፡፡ 
ከሚሰጣቸው መኖሪያ ቤት ባሻገር ደረጃቸውን የጠበቁ ሦስት ለመጓጓዣ የሚያገለግሉ የመንግሥት ተሽከርካሪዎችም ይመደቡላቸዋል፡፡ ለተሽከርካሪው ሹፌር ደመወዝ፣ የነዳጅና የጥገና እንዲሁም ሌላ ወጪ በመንግሥት የሚሸፈን መሆኑንም ያመለክታል፡፡ 
ከኃላፊነቱ የሚነሱ ሦስት ከፍተኛ ኃላፊዎች በተለያዩ የሕዝባዊ አገልግሎቶች ላይ ከተሰማራ መኖሪያ ቤቱ በሚገኝበት ከተማ የቢሮ አገልግሎት እንደሚሰጠው የሚደነግግ ሲሆን፣ ባለመብቶቹ የሚመርጧቸውና መንግሥት ደመወዛቸውን የሚከፍላቸው አንድ ጸሐፊና አንድ ባለሙያ ጭምር ይኖራቸዋል፡፡ 
በዚሁ አዋጅ ድንጋጌ መሠረት ከኃላፊነት የተነሳ ፕሬዚዳንት ጠቅላይ ሚኒስትር በሞት ሲለይ ጥቅማ ጥቅሙ ለቤተሰቦቻቸው ይተላለፋል፡፡ በዚሁ መሠረት በሞት ሲለዩ የግል ወጪ አበል ለባለቤቱ መክፈሉ የሚቀጥል ሲሆን፣ የባለመብቱ ባቤትም ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩም የመኖሪያ ቤት፣ የሕክምና ክፍያ የግል ደኅንነት ጥበቃ አገልግሎቶች እንደማይቋረጡበትም ይደነግጋል፡፡ 
ፕሬዚዳንት ግርማ የ12 ዓመታት የፕሬዚዳንት ዘመን መጠናቀቅን ተከትሎ በአዋጁ መሠረት መንግሥት የሚያዘጋጅላቸው ቤት አዲሱ ፕሬዚዳንት ማንነት ይፋ ከመሆኑ በፊት ይዘጋጃል ተብሎ እየተጠበቀ ነው፡፡  
 (ምንጭ ሪፖርተር ጋዜጣ)

አዬ … ተመከተ …. ቀደሞ ተነበዬ …. ትንቢቱም … ዕውን ይሆናል። ከ ሥርጉተ ሥላሴ

ሥርጉተ ሥላሴ 17.09.2013
ከዬት እንደምጀምር ሳላውቅ ጀመርኩት። ይሁን። መቼም አጅሬዋ እንደማታሳፍረኝ በማመን እሷኑ ተከትዬ ልንጎድ።
ቀና …. ቀናውን እያሳለሁ። ቀኝ … ቀኜን …. እየተመኘሁ …..፤ ተስፋን ሰንቄ መጭ ልበል …. ግን አንጀቴ እርር ብሎ፤
ማህጸኔም ኩርምት ጭብጥ ብሎ /// ሱባኤ ገብቷል። ለነፍሷ፤ ለእስትንፋሷ ከሞላው ብርታት አባ መስጠት መዳህኒቴ
መንፈሱን እንዲልክላት በመማጸን ….
አንቺ ህብር …. ግብር
የወጣት አብነት ተግባር።
የመሆን መቻል ንብ
የብዕር ፍጹም ዘብ።
የነፃነት አውራ … ትንግርት
የሴት አብነት የትንቢት።
የቆረጥሽ እመቤት - የጽናት
የፍቅር ምላዕት ውፅፍት።
ቀድመሽ አይተሽ ተናገርሽ ….
ለነገ እራስሽን ሰጥተሽ ተቃጠልሽ ….
ነደሽ ቀልጥሽ፤ …. በአንቺ መከራ እኛን አበራታሽ ….
በዘረኞች ቋሳ … ተቀቀልሽ፤
እንደከሰመ አይቀር ይበቅል
መስዋዕትነትሽ ያዘምር፤
ትናነትን ዘክሮ ነገን ያሳምር
የተፈጠርሽ ለታምር
ሰብል ያነባብር!
ዛሬ ወደ ቀንጮዋ ወጣት አናብስት አሰኝቶኝ ትንሽ ስንኝ
መቋጠር ወደድኩኝ። በዚህ ዕድሜ፤ በሴትነት አቅም፤ „እኔ ብሞትም ሚሊዮን ርዕዮቶች …“ አለችን ያቺ የትናትናዋ
እንቡጥ በዕድሜ ከሁላችንም ያነሰች የመሆን መቻል ንግሥት መምህርት ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ። በቀዬፋ የመቅጫ ቦታ
ቀራኒዎ ላይ ሁና በተስፋ እኛን ታነጥረናለች። በአረመኔዎች እጅ ወድቃ አዲስ የሰለጠነ ራዕይ ታውጃለች፤ በበለኃሰቦች
ክርኒ ሥር ሆና፤ መከራውን ሁሉን ችላና ታግሳ የአይዟችሁን መናን ትመግበናላች። አሁን ደግሞ ሰው የማይችለውን
ለመቻል ወስናና ቆርጣ እኛ አዲስ ብለን ባደገደግንለት፤ ከቅዱስ የኋንስ ጀምሮ እሷና ቤተሰቦቿ ኮሶ ቆርጥመው ዋሉ
አደሩ …. አሁንም እሷ ቀጥላለች። መከረኛዋ ከእህል ከእውኃ ታዕቅባ እንደ ቅዱሱ ተክልዬ ሥጋዋን እዬቀጣችው …
ነው። መ-ረ-ራታ! በቀሉ አዬለባታ፤ በአጋም ታጠረች …. በፍዳዋ ቤት እንኳን ድቅድቅ እንሆ ተሸለመች …. አወጁ ዘረኞች
ከቃሊቲም በበቀል ሊደቁሷት …. ዶለቱ ….
የኛ ዕንቡጥ፤ የኛ ለጋ፤ የኛ ሰማዕት ለሴት ልጆች ከፍተኛ የመንፈስ ድቀት በሚፈጥረው በጡት ህመም እዬተሰቃዬች፤
ዘለፋውን፤ እርግጫውን ችላ በካቴናው ማሳ ትንፋሽ አጥሯት ታፍና፤ ተወጥራ፤ በፋሽስቶች ትንገበገባላች። ይህ ዘመን
ከዬትኛው ዘመን ጋር ሊመደብ እንደሚችል መግለጽ ባልችልም፤ የኦሾቲዝምን ሚስጢር ያነበባችሁ ወገኖቼ ከዛ ጋር
ታገናዝቡት ዘንድ በአክብሮት እጠይቃችኋላሁ።
የርዕዮት እስትንፋስ፤ በዬሰከንዷ አፋፍ ላይ ነው። እኛን በአጽህኖት ይማጸነናል። በተደሞ ውስጣችን ይመረምራል።
በትዝብት ያጠናናል፤ ከራሳችን ጋር ስለሞሆናችንም መንፈሳችነን በተደሞ ይረምራል። ሥቃዮዋ እዬተጣራ ነው።
ድረሱልኝ እያለ ነው። መልዕክቱን ዕውነትን ታጥቆ ልኮልናል። ለመሆኑ ጆሮ አለን? ማድመጥ እንችላለን?!~
አይመስለኝም በሰባራ ሰንጣረው አቲካራ ገጥመን አካሎቻችን የዘነጋን ይመስለኛል። ያማ ባይሆን ኖሮ የሚቀድመውን
ለማስቀደም ባልተሳነን ነበር። ምን ያቅታል? ውስጥን በቅንነት አጥቦ …. ለተግባር መትጋት …. የነፃነት አርበኞቻችን እኮ
ከህልፈት ጋር ግብግብ ገጥመዋል …. ሩኃቸው መፈናፈኛ አጥቶ ጨለማ ታውጆበታል …
እጅግ የማከብራችሁ የጹሑፌ ታዳሚዎች … ሴት እህት፤ ሴት እናት፤ ሴት አክስት፤ ሴት የማህበራዊ ኑሮ ጓደኛ፤ ሴት
የትዳር ጓደኛ፤ ሴት፤ ሴት ልጅ ያለችሁ ሁሉ ይህን ስቃይ፤ ይህን መከራ፤ ይህን ከሞት ጋር መፋጠጥ መራራ ገጠመኝ
እንዴት ትተረጉሙት ይሆን?! እንዴትስ ታመሳጥሩት ይሆን?! ለመሆኑ ይህን ሰቆቃ ቸል የሚል አንጀትስ መንፈስ ይኖራችሁ ይሆን?! እንደ እኔ ህማማተ ~~~ ርዕዮት የተራራው የመዳህኒታችን የቀራኒዎ፤ የጎለጎታ ስብከት ሆኖ ነው
ያገኘሁት።

እንደ እኔ ርዕዮት አሁን መምህርም፤ ጋዜጠኛም ብቻ አይደለችም። የነፃነት ብቁ ሐዋርያና ሰማዕትም ናት። እመ ብዙኃን
ናት። ጉልላትና ማማ ናት፤ በታሰረ ሰንሰለት ሞትን ፈቅዶ በስቃይ ለመቀበል በቀንበጥነት መወሰንና መቁረጥ! ምን
ዓይነት የቅኔ ጉባኤ ነው። ምን ዓይነት የታሪክ መጽሐፍ ነው?! … ይህ በዬትኛውም ዘመን ያልታዬ የኛ የሆነ፤ የዛሬ ብርቅ
ታሪክ የነገ መወድሳዊ ትውፈታችን ነው። ድርሳናችን ነው። እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ ለሃይማኖቷ ቅድስና
አገኘች። ርዕዮት ደግሞ ለነፃነት ቅድትና ድንግል ናት። በዚህ ዘመን የተፈጠሩ ወጣት አንስት የነፃነት ጎሆቻችን ናቸው።
የእናት ሀገራችን ታሪክ ሙሉዑ ያደረጉ የታሪክ ዘብ አደሮች።
አብሶ እጅግ መጥቀው፤ ቀድመው በሚወጡ ብልህ አንስት የነፃነት አርበኞቻችን፤ ግፈኛው ወያኔ የሚፈጽመው
አረመኔያዊ እኩይ ተግባር ፍጹም የተለዬና ታይቶም ተሰምቶም የማይታወቅ ጭካኔ ነው። ጋዜጠኛ ሰርኬ … በኽረ ልጇን
እስር ቤት ሆና አርግዛ ወልዳ ከአራስ ልጇ ጋር ሳትገናኝ፤ የአራስ ወጓ …. እስር ቤት፤ …. አራስ ህፃንም ከጡት ተለይቶ
በሀገሩ ባይታዋርነት ታውጆበት ገና ከጥንሰሱ ጀምሮ በጭካኔ እንዳይወለድ፤ ከተወለደም እንዳያድግ የተፈረደበት
በታምሩ ግን ያደገ የነገ ዓይነታዊ መዘክራችን ነው።

ክብርት ዳኛ ብርቱካን ሜዴቅሳም ለሁለት ጊዜ እስር ቤት ስትገባ ሃልዬ እናት አልባ ሆና ዘወትር ሰንበትን፤ ልደቷን፤
ዓውደ-ዓመታትን፤ የጨዋታ ጊዜዋን፤ የእረፍት ጊዜዋን፤ የህጻንነት ወቅቷን ሁሉ ቃሊቲ ላይ ሰንሰለት እያዬች፤
የአረመኔውን ሰራዊት ግፋና በደል በማስተዋል እዬተሸማቀቀች እንድታድግ ተበይኖባት ነበር። እናቷን ሲገፏት
ሲያንገላቷት እዬተመለከተች፤ ደካማ አያቷን ሲገላምጡ እዬተመለከተች …. በፍርኃት ተሸማቃ የማይችለው ቀንበጥ
መንፈሷ ጎብጦ እንዲያድግ ተዘመተባት …..
ይህ የሄሮድ አስተዳደር፤ ራዕይ መቼ እንዲያው መቼ ይሆን የሚነቀለው? ይህን ሁሉ ስቃይ የሚያዬውስ ወገን እንዴትና
እንዴት ብሎ ነው ይህን ፍትህን የሚቀጠቅጥ፤ ርትህን አጋድሞ የሚያርድ፤ ነፃነትን የሰቀለ ፋሽስታዊ አስተዳደር
ለማስወገድ የገፋ ተግባር የሚፈጽመው …. ? ? ?
መቼ ይሆን እራሳችን በራሳችን ካዘጋጀነው፤ እንደ ጉም ሽንት ከሚጎትተን ትብትብ ነገር ሁሉ ተፋተን በውስጣችን
እውነተኛ ለውጥ በማምጣት እንዲህ በፈላ በቀል የሚቀቀሉ ወጎኖቻችን ጥሪ እድምተኛ ቤተኛ በፍቅር የምንሆነው …. ፧
ምንው ባልተፈጠርኩ። ከተፈጠርኩም ቀድሜ አፈር ብሆን ምንኛ መልካም በሆነ …. ትንፋሽ ያሳጥራል …
አቅምሽ --- መዳህኒትሽ
ፈውስሽም --- አምላክሽ
እውነትም ---- ትራስሽ
የሆ /// ን//// ሽ!
ነፃነትም --- መሪሽ
መሰዋትም ----- ፈርሽ
ለሰላም ~~~~ የቆረብሽ
መሆን መቻል ፈውስሽ!
መቅለጥ ሆነ ፈርጥሽ
እርኃብ ሆነ ሰርግሽ!
ዓላማሽም --------------------------ሩቅ
የመከራ ምሩቅ፤
የአንስትም ነሽ ልዑቅ
የእኩልነት መረቅ፤
እ///ር///ቅ!
የብዕር ማህለቅ
የብራና ወርቅ - ልቅ።
ታናሼ ድምቀቴ
ታናሼ ድህነቴ
ሰንደቅ ቀለበቴ!
ልቦና ይሰጠን! ፈጣሪያችን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
(source addis voice)

የሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ ዝግጅት ተጠናክሮ ቀጥሏል

ሰማያዊ ፓርቲ እሁድ መስከረም12 ለሚያካሂደው ሰላማዊ ሰልፍ የአዲስ አበባ አስተዳደር ፓርቲው የሰልፉን ቦታ እንዲቀይር የጠየቀ ቢሆንም ፓርቲው ሰልፉን በመስቀል አደባባይ እንደሚያካሂድ በአፅንኦት በመግለፅ ዛሬ ደብዳቤውን ለአስተዳደሩ የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊና ምክትል ኃላፊ በተገኙበት ለሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል ኦፊሰር አቶ ማርቆስ ብዙነህ አስፈርመው አስረክበዋል:: ይህ በእንዲህ እንዳለ በፓርቲው በኩል የሰልፉ ዝግጅት ተጠናክሮ ቀጥሏል::
የፓርቲውን ደብዳቤ ሙሉ ቃ ለማንበብ  እዚህ ላይ ይጫኑ           (ምንጭ የኢትዮጵያ ሜዲያ መድረክ)         
semayawi sep 20

Thursday, September 19, 2013

የኢትዮጵያ ወታደሮች ብሶትና የመንግሥት ምላሽ፣

በሶማልያ የሚገኙ የኢትዮጵያ ወታደሮች በበላይ አለቆቻችን እየተበደልን ነው አሉ። አንዳንድ የሠራዊቱ አባላት፤ በ SMS መልእክት አማካኝነት ለ DW እንደገለጹት ከሆነ የውስጥ ነጻነታቸውን እየተነፈጉ ነው። የህክምና ፈቀድ በተለይ እንደነርሱ አገላለጽ
A picture taken on March 2, 2012 shows Ethiopian troops standing on an army tank at an air base in the city of Baido, which was taken over from Shebab rebels on February 22. Truckloads of Ethiopian and Somali troops on February 22 captured the strategic Somali city of Baidoa from Al-Qaeda-allied Shebab insurgents, who vowed to avenge their biggest loss in several months. Baidoa, 250 kilometres (155 miles) northwest of the capital Mogadishu, was the seat of Somalia's transitional parliament until the hardline Shebab captured it in 2009. Ethiopia says it is in the country to support Somalia?s transitional government to stamp out Shebab insurgents, but says it does not plan to remain in the country for the long term. AFP PHOTO / JENNY VAUGHAN (Photo credit should read JENNY VAUGHAN/AFP/Getty Images)
የኢትዮጵያ ወታደሮች-ባዶዎ
በጉቦ ሆኗል።
የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ፤ «ቅሬታውን ለዶቸ ቨለ የሚልክ ወታደር የለኝም » ሲል አስተባብሏል።
ጃፈር ዓሊ ዝርዝር ዘገባ አለው።
ጃፈር ዓሊ
ተክሌ የኋላ
ነጋሽ መሐመድ

AUDIOS AND VIDEOS ON THE TOPIC

  • ቀን 19.09.2013

Wednesday, September 18, 2013

የቤተመንግስት ደህንነት ሃላፊ ተነሱ (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

የነአዜብ ቡድን እየተመታ ነው!!
የቤተ-መንግስት የደህንነት ጥበቃ ዋና ሃላፊ ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት የሕወሐት አባል አቶ ጌታቸው ተፈሪ ከስልጣናቸው መነሳታቸውን ምንጮች አስታወቁ። አቶ ጌታቸው ቀደም ሲል በክልል 14 ፖሊስ ኮሚሽን የደሕንነት ልዩ ተወርዋሪ ሃይል ሃላፊ ተደርገው ሲያገለግሉ መቆየታቸውን የጠቆሙት ምንጮች፣ ከዚያም ወደ ቤተ መንግስት ተዛውረው መመደባቸውንና በተጨማሪ የአገር ውስጥ ደህንነት ምክትል ሃላፊ በመሆን ከአቶ ወ/ስላሴ ወ/ሚካኤል ጋር ሲሰሩ መቆየታቸውን አስረድተዋል። የአቶ መለስና ወ/ሮ አዜብ የቅርብ ሰው የሆኑት አቶ ጌታቸው ተፈሪ በነበራቸው ታማኝነት የቤተመንግስት የደህንነት ሃላፊ ተደርገው በአቶ መለስ ተመርጠው እንደተሾሙ ያስታወሱት ምንጮች፣ በማያያዝም እስከ 1994ዓ.ም የቤተመንግስት የደህንነት ጥበቃ በሃላፊነት ሲመሩ የቆዩት አቶ ዘርኡ መለስ በወቅቱ ከአቶ መለስ ጋር በፈጠሩት የፖለቲካ ልይነት ምክንያት ካዛንቺስ አካባቢ በሚገኘው የቀድሞ “ኮከብ ሬስቶራንት” የአሁኑ “ሚልክ ሃውስ” መኖሪያ ሕንፃ አንደኛ ፎቅ ቤታቸው ውስጥ አንገታቸው በስለት ታርዶና በድናቸው ተበላሽቶ መገኘቱን አመልክተዋል። ይህን አሰቃቂ ግድያ ያከናወነው አሁን በእስር ቤት የሚገኘው የቀድሞ አገር ውስጥ ደህንነት ሃላፊና የአቶ መለስ ቀኝ እጅ ወ/ስላሴ ወ/ሚካኤል መሆኑን ምንጮቹ አጋልጠዋል።
የነ አዜብ ቡድን እየተመታ ነው!
የነ አዜብ ቡድን እየተመታ ነው!
አቶ ጌታቸው ተፈሪ ከስልጣን እንዲነሱ የተደረገው በደህንነት ዋና ሹም አቶ ጌታቸው አሰፋ ትእዛዝ መሆኑን ያመለከቱት ምንጮች፣ በአሁኑ ወቅት በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ እንደማይታወቅ ጠቁመዋል። አቶ ጌታቸው ተፈሪ — የወ/ስላሴ መታሰር ቅር ሳያሰኛቸው እንዳልቀረና በተጨማሪም የነአዜብ ቡድን ደጋፊ መሆናቸውን ምንጮቹ አመልክተዋል።
በሌላ በኩል የኢ.ኤም.ኤፍ ምንጮች ቀደም ብለው እንደገለጹት፤ ባለፈው አመት የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ከሞቱ በኋላ “ቤተ መንግስቱን አንጠብቅም” ብለው ንዝህላልነት ካሳዩት መሃል እኚሁ የቤተ መንግስት ጥበቃ ሃላፊ ጌታቸው ተፈሪ አንዱ ነበሩ። በተለይም አዲሱ ጠ/ሚንስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ከገቡ በኋላ የቤተ መንግስቱ ጥበቃ እንዲላላ ከማድረግ አልፈው፤ ለአዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር አክብሮት የማይሰጡ ሰው እንደነበሩ ይታወቃል።
ምንጭ የኢትዮጵያ ሜዲያ መድረክ

Tuesday, September 17, 2013

ሰማያዊ ፓርቲ እሁድ ያስመረቀውን ቲያትር በቪሲዲ ለህዝብ ሊያደርስ ነው

ኢ/ር ይልቃል ጌትነት
ሰማያዊ ፓርቲ እሁድ ያስመረቀውን ቲያትር በቪሲዲ ለህዝብ ሊያደርስ ነው
“ታዋቂ አርቲስቶች አንሳተፍም ማለታቸው አሳዛኝ ነው” ኢ/ር ይልቃል ጌትነት
የመንግስት ሲኒማ ቤቶች ትያትሩን ለማሳየት ፈቃደኛ አልሆኑም
ሰማያዊ ፓርቲ ባለፈው እሁድ ያስመረቀውን “የነፃነት ፈለግ” የተሰኘ ቲያትር በቪሲዲ ለህዝብ ሊያቀርብ እንደሆነ የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ገለፁ፡፡
እሁድ እለት በጣሊያን የባህል ተቋም የተመረቀው ትያትሩ፤ በፕሮፌሽናል ካሜራ መቀረፁንና በቅርቡ ኤዲቲንጉ አልቆ በቪሲዲ ለህዝብ እንደሚደርስ የጠቆሙት ኢ/ር ይልቃል፤ ትያትሩን በመንግስት ሲኒማ ቤት ለማሳየት ሲኒማ ቤቶች ፈቃደኛ ባለመሆናቸው በቪሲዲ ለማውጣት ተገደናል ብለዋል፡፡
የ70 ደቂቃ ርዝመት ያለው ትያትሩ በአገሪቱ ወቅታዊ የፖለቲካና ማህበራዊ ችግሮች ላይ የሚያተኩር መሆኑንና የፓርቲው አባል በሆነው ወጣት ዳዊት ፀጋዬ እንደተፃፈ የተናገሩት ኢ/ር ይልቃል፤ ታዋቂ አርቲስቶች በትያትሩ ላይ ለመሳተፍ ለሶስት ወራት ሲለማመዱ መቆየታቸውን ጠቁመው፤ በኋላ ግን መንግስትን በመፍራት ጥለው እንደወጡና በዚህም እርሳቸውና ሌሎች የፓርቲው አባላት እንዳዘኑ ገልፀዋል፡፡ “ታዋቂ አርቲስቶች ሙያቸውን በመጠቀምና ለእውነት በመቆም ህዝቡን ማገልገል አለባቸው” ያሉት ኢ/ር ይልቃል፤ ታዋቂ የትያትር አዘጋጅና አስተማሪ የሆነው ግለሰብ “ሀላፊነት አልወስድም” ብሎ ዝግጅቱን አቋርጦ ከአገር መውጣቱንም ገልፀዋል። “አዘጋጁ ሀላፊነት አልወስድም” ያለው በተለይ ግንቦት ላይ ሰላማዊ ሰልፍ በማድረጋችንና ጉዳዩ መነጋገሪያ በመሆኑ ነው” ብለዋል፡፡
“ተዋንያኑም አዘጋጁን አምነን ነው ስራውን የጀመርነው፤ እርሱ ሀላፊነቱን ካልወሰደ እኛም አንፈልግም” በማለት ከሶስት ወር በኋላ ጥለው መበተናቸውንና እንደ አዲስ ሌሎች ወጣት ተዋንያንና አዘጋጅ ተፈልገው ልምምዱ መጀመሩን የገለፁት የፓርቲው ሊቀመንበር፤ በዚህ ምክንያት ቴያትሩን ለእይታ ለማብቃት ከስድስት ወር በላይ መፍጀቱን ገልፀዋል። ትያትሩ ትርፍን ማዕከል ባላደረገ መልኩ የተዋንያን እና የደራሲውን ወጪ ለመሸፈን በመጠነኛ ዋጋ ለህዝብ ይደርሳል ያሉት ሊቀመንበሩ፤ ፓርቲዎች ለአጭር ጊዜ ገቢ ማስገኛ ስራዎችን የመስራትና ለገበያ የማቅረብ መብት እንዳላቸው አዋጁ እንደሚደነግግ ገልፀው፤ ቪሲዲውን በቅርቡ ለማከፋፈል ዝግጅት እየተጠናቀቀ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡ ትያትሩ በተመረቀ እለት ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያምን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ተገኝተው አድናቆታቸውን መግለፃቸውን የተናገሩት ኢ/ር ይልቃል፤ ሥራው በተቃዋሚ ፓርቲ ደረጃ የመጀመሪያና አስተማሪ መሆኑን ፕሮፌሰሩ መናገራቸውን አውስተዋል፡፡
ፓርቲው ትያትሩን በመንግስት ሲኒማ ቤት ለማሳየት ፈልጎ ይሁንታ በማጣቱ በጣሊያን የባህል ተቋም ካስመረቀ በኋላ ተቋሙ ለትያትሩ ደራሲ “አገባባችሁ ትክክል አይደለም፣አታላችሁናል፣ አዳራሹም ለፖለቲካ ስራ ውሏል” የሚል ይዘት ያለው ደብዳቤ መፃፉን የተናገሩት ኢ/ር ይልቃል፤ በዚህም ማዘናቸውን ገልፀዋል፡፡

ምንጭ(ዘ-ሐበሻ)

አሁንስ በዛ …. ገለማኝም! ከሥርጉተ ሥላሴ

ከሥርጉተ ሥላሴ
በጣም ብዙ ታገስኩኝ። በጣም ብዙ ብእሬን ኮረኮምኳት። የሚባለውን አነባለሁ። እያደንኩ አያለሁ። ዝም ያልኩት ግን
መማር ይቻል እንደሆን ብዬ ነበር። ከዚህም ሌላ በድርጀቱ በአባልነት ሆነ በአካልነት ያሉ ወንድምና እህቶቼም
ብዕራቸውን ሊያነሱ ይችላሉ ብዬም ጠበቅሁ። አሁን ግን እኔ ነፃ ሴት ስለሆንኩ ውስጤ የቆሰለበትን ነፃ አስተሳሰቤን
ላጋራችሁ ወደድኩ።
ለማን እንደሚጠቅም አላውቅም። ለማን ይመቸው ተብሎ እንደሚደረግም አይገባኝም። ለነገሩ እንዲገባኝም
አልፈልግም። ጠናና ዕይታና ቅንነት የነጠፈበት የምቀኝነት ቋሳ ----፤ ሽፍታው ድርጅት ወያኔ የሚፈጥረው መጠራቅቅ
አልበቃ ብሎ የነፃነት ትግሉ ቤተሰቦች ከሆኑት ስህተቶች እዬተፈለጉ፤ ስንጥርና ስንጥቅ እዬተፈተሽ በግንቦት ሰባት ላይ
ጦር የሚመዘዝበት ነገር አይገባኝም።
ድርጅት የሰዎች ስብስብ ነው። ስብስቡ ደግሞ እንደ ሰው ሊፈጽመው የሚችል ስህተት ሊኖር ይችላል። በግንቦት ሰባት
ግን ሁሉ ነገር ብርቅና ድንቅ ነው። አሉ የሚባሉትን ስህተቶች ለድርጅቱ መላክ ይቻላል። ቀጠሮ ይዞም ቁጭ ብሎ ፊት
ለፊት ቀርቦ ለመነጋጋርም መሪዎቹ ዕድሉን የሚነፍጉ አይመስለኝም፤ - ከቅንነት የመነጨ ከሆነ። ወያኔ የሚፈራውን፤
የሚርበደበትን ነገር የበለጠ ጥንካሬ መስጠት ሲጋባ ከጠላት ያልተለዬ ዱላ ይመዘዝበታል ግንቦት ሰባት። ይቀጠቀጣል
በመዶሻ፤ ከዚህም ባላፈ እንዘምትበታለን የሚል ጹሑፍም አንብቤያለሁ። ለመሆኑ ማንን እያገዝን ነው? ማንንስ
ይድላው ብለን ነው ይህን መሰል እርምጃ የምንወስደው? እስኪ ህሊናችሁን መርምሩት የነፃነት ትግሉ ቤተኞች።
በሌላ በኩል መወጮ ሰበሰበ ተብሎ ግንቦት ይተቻል። የድርጅት ህግ እኮ ነው። ፈቅደው አባል ከሚሆኑ አባሎቹ ገንዘብ
ንቅናቄው መሰብሰቡ። ደርግ እንደ መንግሰት ተደራጅቶ ኢሰፓ ከሚባል ፓርቲው ከአባላቱ በዬወሩ እንደ ገቢያቸው
መጠን መዋጮ ይሰበስብ ነበር። ይህ ደግሞ አንድ ድርጅት ሲፈጠር በሚያጸድቀው ደንቡ ላይ የአባላት መብትና ግዴታ
ላይ የሚደነገግና በአባላት ጉባኤ የሚጸድቅ መርህ ነው። አባላቱ ድርጅታችን ነው ሲሉ አይደለም ገንዘባቸውን ደንቡን
የህይወታችን መመሪያ ብለው ፈቅደውና ወደው ነው የሚቀበሉት። እስኪ እባካችሁ ወገኖቼ ስለ ፓርቲ አደረጃጃትና
አመራር ቀደምት ልምድ ያካበቱ ሀገሮችን ተመክሮ እስኪ አንብቡት። ውጪ ሀገር ደግሞ ግዴታ የለበትም ሰው ወዶና
ፈቅዶ አምኖበትም ነው አባል የሚሆነው። ስለሆነም ለወሰነው ውሳኔ እራሱን በነፃነት ማስገዛቱ የተገባ ነው።
ሌላው ጎልቶ ሲነገር የምሰማው ግንቦት 7 አልሰራም የሚለው ነው። ለድልም ተሎ በፍጥነት አልበቃም የሚሉም አሉ።
ድል ገቢያ ተሂዶ የሚገዛ ሸቀጥ ይመስል? ነባራዊ ሁኔታ እንደ ፍሬቻ በሰው እጅ የሚገራ እንደሆነ … አዬ! ለማንኛውም
ንቅናቄው ሲወጠን ከነበሩት ሁኔታዎች ተነስቼ ለምን እንዳሰበው አልተጓዘም ለሚለው … የግል ዕይታና የደረስኩበትን
መደምደሚያ ለመነሻ እንደሚከተለው አቀርባለሁ ….
1. በወቅቱ ፈርታይል ወይንም የለሙ ሁኔታዎች ነበሩ። እንቅስቃሴው ይፋ ተግባሩን ሲጀምር፤ ነገር ግን ጦርነቱ
የእርስ በርስ ነውና በቀንበጡ ተስፋ ላይ ጫና ገጠመው። ሚስጢር ማሸነፍ ነውና። ሚስጢር ከፈሰሰ ጠላት
እጅ ከገባ ብዙ ነገሮችን ይበክላል። ለቀጠይ እርምጃ ደግሞ እንደ ገና ከ“ሀ“ ይጀመራል። አዲስ ስልት ቅዬሳ
ሽርሽር አይደለምና ….
2. የሽፍታው አስተዳደር ያወጣው የሽብር ህግም ሌላው በንቅናቄው ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳደረው ጉዳይ ነው።
3. የከፍተኛ አመራሩ የአኗኗር ዘይቤ በተለያዩ አኽጉሮች መሆን፤ ለተግባሩ ፍጥነት እንቅፋት እንደሆንበት
አስባለሁ።
4. ዓለምዓቀፋዊ፤ አህጉራዊና ሀገራዊ ሁኔታዎችም የራሳቸው አሉታዊ ጫና አድርገውበታል፤
5. በመሪ አካላቱ ላይ ሽፍታው አስተዳደር የወሰደው ከዕድሜ ልክ እስራት እስከ ሞት ድረስ ህገ ወጥ ዳኝነት
ሌሎችን እንዲሸማቀቁ አድርጓቸዋል፤
6. የፋይናንስ አቅሙ ራሱን ያልቻለ፤ በአባላቱ ጥገኛ መሆኑ እንደ ፍላጎቱ እንዳይራመድ እንቅፋት ሆኖታል።
7. ሁሎችም ማለት ይቻላል አመራሩ በቋሚነት ሳይሆን በትርፍ ጊዜያቸው ብቻ እንዲሰሩ መገደዳቸው። ይህም
የእንቅስቃሴው የኢኮኖሚ አቋም፤ አቅም ከድርጅቱ ትውልዳዊ ራዕይ ጋር የማይመጣጠን በመሆኑ ለተልእኮው
መጠራቅቅ እንደፈጠረበት እገምታለሁ።
8. ድጋፍ በመስጠት እረግድ ምቀኝቱ በገፍ፤ ቅንነቱ ደግሞ በመቁንን የትውልዱ ዕጣ ፋንታ መሆኑ፤ ፈቃድ
የሰጠነው መሰናክል …. ነው፤
9. የትጥቅ ትግሉን ለመምራት አስተማማኝ፤ እርግጠኛ ቦታ፤ ወይንም መቀመጫ፤ ወይንም ኮማንድ ፖስት ሀገር
ለማግኘት የነበረው አቀበታማ ጉዞ፤ የተገኘው ቦታም ራሱን የቻለ የዲፕሎማሲዊ ጥረትና ተግባር፤ ሰፊ ጊዜና
ትእግስትን ይጠይቅ ስለነበር ….
ከዚህም በገዘፉ ፈተናውች ውስጥ የጮርቃ ድርጅት ኃላፊነቱና የልጅነቱ አቅሙ ማገራዊ አጥንት ከሚችለው በላይ
ሸክም ነበረበት። ይህም ሆኖ 1. ለድርጅቱ የተግባር መሰረት የሚሆኑ መመሪያዎችንና ሰነዶችን በማዘጋጀት፤
2. አመራሩን በመምረጥና በመመደብ፤ መደበኛ ጉባኤዎችና አስቸኳይ ስብሰባዎችን በማካሄድ፤
3. በተከታታይ ዓላማውንና ተግባሩን ለማስተዋወቅ የተደረጃ ህዝበዊ ስብሰባዎችን በአውሮፓ፤ በአሜሪካና
በአውስትረልያ በማካሄድ የተበተነው መንፈስ ለመሰብሰብ ያደረገው ጥረት ጉልበታም ነበር፤
4. በምስረታው ወቅት መዋቅራዊ ድርጅቱንም በመዘርጋት የሚመጥን ሰው ከማግኘት ጋር የነበረው ፈተናና
መጠራቅቅ ሰፊ እንደሚሆን እገምታለሁ፤ ግን የገጠመውን ፈተና ተቋቁሞ ተግባረዊ ማድረግ መቻሉ ደግሞ
የጥናካሬው አካል ነው።
5. የራዲዮ ፕሮግራሙ ሌላው የመረጃ ፍሰቱን መሰረት አስጥሏል፤
6. ድህረ ገጹን በመምራት፤ በማስተዳደርና ተልእኮውን እንዲወጣ በማድረግ እረግድ የበሰለ ተግባር ነው
እዬተከወነበት ያለው …
7. የዲፕሎማሲያዊ ተግባራቱ ደግሞ ከሁሉም የገዘፈው ኃላፊነቱ እንደሚሆን እስባለሁ።
8. ለስንት ዘመን ለዜና ለመዘገብ ፈቃደኛ ያልነበረውን የኦሮሞ ነጻ አውጪ ግንባርን ማንፌስቶ እስከማስቀዬር
የደረስ እጅግ ድንቅ ተግባር ሲሆን፤ የዘመናችን ምርጥ ክንውን ሊባል የሚያስችለውም ይመስለኛል።
9. በተወሰነ ደረጃም ቢሆን የጥምረት መፈጠርና ለነፃነት ትግሉ የበኩሉን ድርሻ ለማበርከት መንገድ መከፈቱ፤
10. ሰራዊት ለመመልምል፤ ለማደራጀትና፤ ለማሰልጠን ያደረገው ጥረት ….
11. በህዝባዊ ስብሰባዎች ላይ ያለውን የውክልና ፍላጎት በማሟላት እረግድም ጊዜና ጉልበት የሚጠይቅ የድርጊቱ
አካል እንደ ሆነ ይሰማኛል።
12. ተጨማሪ አባላትን በመልምልና በማሰማራት፤ አዳዲስ ውክል አካላትን በመሰዬምና መዋቅር በመዘርጋትም
ተከታታይ ተግባራትን ከውኗል ብዬ አስባለሁ። ዕለታዊ መተንፈሻ ተግባሩ ነውና ወዘተ … ከዚህ ሌላ ህዝብ
ዳኝነት ለመስጠት የማይችላቸው፤ ማለትም ለሚዲያ ይፋ ያልሆኑ ረቂቅ ስውር ሥራዎችንም እንደ ከወነ
ይገባኛል። ሁለገብ ትግልን የመረጠ ድርጅት ሁሉ ተግባሩን ይፋ እንዲያደርግ የአደረጃጃት ባህሪው
አይፈቅድለትም። ይህ እንግዲህ እኔ ውጭ ሆኜ የማያቸው ተግባራት ከሞላ ጎደል ለናሙና አነሳሰሁ።
እናንተ እንደምትሉት ደግሞ ኢሳት የግንቦት 7 ከሆነ በአፍሪካ የነፃነት ትግል ታሪክ ውስጥ በስደት አዲስ የፈጠራ፤
የብቃት ምዕራፍ ነው። አደረጃጀቱ፣ አመራሩ፣ ተግባሩ፣ ብቃቱ፣ ጥራቱ፤ አስተማሪነቱ ፍጥነቱ፤ መዘከርነቱና
አሸናፊነቱ ከልጅነቱ ጋር ኢሳት ሲመዘን ከባለ ግራጫው ከኢትዮጵያ ቴሌቪዢን ጋር ሲገመገም እርቀቱን እናንተው
ገምግሙት … ከሁሉ በላይ እርምት ለመቀበል ያለው ዝግጁነትና ቅንነቱ ፍቅርን ካለ ገድብ እንዲሸምት አድርጎታል።
ከዚህ በተረፈ በዬመድረኩ፤ በዬሩሙ፤ የግንቦት ነገር ሲነሳ ጆሯችሁን ቀጥ ለምታደርጉ ስህተት ቆፋሪዎች
የምነግራችሁ ከእላፊ ነገር ተቆጠቡና በሩ ክፍት ነው። አባል ሁኑ፤ ግዴታችሁን እዬተወጣችሁ እንዳሻችሁ
በመብታችሁ እራሳችሁን ተቹት፤ ተግባሩንም ገምግሙት፤ በዕለታዊ ድሉም ታደሙ! የማከብራችሁ ፍጽማናን
ከሰው ልጅ የምትጠብቁ ወገኖቼ ሁሉ የግንቦት አባል ሁኑና ግዴታችሁን እዬተወጣችሁ የመብታችሁን አፄ ለመሆን
ቁረጡ! ወስኑ!። አልመሸም …. መልካም ጉዞ …. ለአዲስ ዓመት ዋዜማ
ደግሞ! እስኪ ይሁን አልሰራም ከተባለም ብለን ጸጥ አለነ። አሁን በቅርቡ ክቡር አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ያለውን
ተጨባጭ ሁኔታ ሲገልጹ ደግሞ ወያኔ ካበደው በላነሰ የነፃነት ፈላጊው ቤተሰብ ያሰማው ጩኽት በእውነት
የጆሮዬን ታንቡር ነው የበጠረቀው። ምን ይሁን ነው የምትሉት?!!! ምንድን ነው የምንፈልገው? ለመሆኑ
ከፍላጎታችን ጋር እንተዋወቃለን ….?! የሚፈልግ በሰላም፤ የሚፈልግ በመሳሪያ በቀለኛውን ወንበዴ ለመስወገድ
ወስኖ መታገል መብት አለው።
አሁን ሳዬው ግንቦት የድርጅቱን ነጻነትም እዬተጋፋነው ነው። በስልቱ ላይ ትችት አለን። በስትራቴጁ ላይ ትችት
አለን። ምን ችግር አለው የሚመጥነውን ድርጅት ፈጥሮ መንቀሳቀስ ነው። ከቶ ማን ያዘን …. ጀምሩት እና ሞክሩት
… ከበሮ በሰው ሲይዙሽ እኮ ነው … ። ልናከብረውም ልናደንቀውም ሲገባ ጅማታችን እስኪገታተር ድረስ
እንወርድበታለን። ምን እንዲሆን ይሆን የምንፈልገው …. ስለተንገላታ በርኃ በበርኃ ስለተከላተመ …
ለምን ኤርትራ ተመረጠች የሚለውም ሌላው የጦርነት ግንባር ነው …. ይህም በሌሎች ድርጅቶች እኮ አይነሳም።
ቁጭ ብዬ ስታዘባችሁ። ከህሊናችሁ ጋር ስለመኖራችሁ እጠራጠራለሁ። የት ይሂድ …. የጁቡቲ መንግስት ማነን ይዛ
እንደሰረከበ ታውቃላችሁ። ሱዳን ሻ/ አጣናው ዋሴን ይዞ ነው የሰጠው። ኬኒያ በቅርቡ እንኳን ኢንጂነር ተስፋዬ
ጨመዳን ይዞ እስረክቧል። ሻ/አጣናው ዋሴና ኢንጂነር ተስፋዬም ነፃነት እንደ ራባቸው አልፈዋል። እኛ
የማናውቃቸው ታፍነው የተገደሉ፤ የታረዱ፤ የታሰሩ ሺ ናቸው። እዬሰሙ በጩቤም የተዘለዘሉም። ሄሮድስ መለስ
እኮ ከራሳቸው ውጪ ለማንም ምህረት የማይሰጡ ሳጥናኤል እኮ ነው የነበሩት። በቀል ነበር አንጎላቸው ገባችሁ!
ለመሆኑ የት ተሂዶ ትግል ይደረግ? ኤርትራ አካላችን ናት፤ ተገነጠለች ስንል አልነበረም? አሁን ጥግ ስትሆነን
ለምንድነው የሚጎረብጠን። አንድ ወገና በወያኔ ጦር ቆስሎ ህክማና ሳያገኝ መሞቱ ነውን ደስታ የሚፈጥርልን ይሆን
ግራዎች እስኪ መልሱልኝ? … እኔ በርቀትም ኡጋንዳ ላይ ኮማንድ ፖስቱን ያደረገ ድርጅት አውቃለሁ። ከተጨባጩ በጣም የራቀ ስለሆነ ፍላጎቱ ሆነ ራዕዩ ባክኖ ነው የቀረው። ስለሆነም ለአርበኞቻችን ጥግና ቤት የሆነውን አካላችነን
የሆነውን የኤርትራ መንግስት ከልብ አመሰግናለሁ እኔ ሥርጉተ ሥላሴ! ። ለሎጅስቲክስ ሆነ ለትግል ከ ኤርትራ
የተሻለ ለ እኛ የለም። ወዛችን እኮ ናቸው! የሚገርመው „የብሄረሰቦች ነፃነት እሰከ መገንጠል“ እያሉ ስንት ህዝብ
ያስጨረሱ ድርጅቶች አሁን ደግሞ ኮናኞች መሆናቸው ግርንቢጥ ነው …. ጎርባጣ!
እንደ ማሳረጊያ አንድ ነገር ላንሳ እና …. ልሰናበት። ግንቦት ገንዘቡን የት አገኘው? የሚልም እድምታ አለ። ከዬትም
ይሁን። ጥገኛ እንዳይሆን ከተፈለገ ወጪውን ሁሉ የመሸፈን ግዴታ አለብን። እኛ ግን እንኳንስ ወጪውን ሁሉ
የዓመት የስልክ ወጪ የመሸፈን አቅሙ የሌለን በማለት ብቻ የዘለብን የተግባር ድሆች ነን። ለመሆኑ ከልመና ውጪ
የሆነ አቅም ያለው የፈጠርነው ድርጅት ወይንም ተቋም ለናሙና፤ ለምልክት አንድ ነገር አለን?~~~~ አዬ -
ትብትባችን መጠኑ ስፋቱ ቀመቱም ርዝመቱ …. በስንት ጉድ እኮ ነው የምንታመሰው። …. ይደክማል፤
መከረኛው ግንቦት 7 … እንደ ሰው የድርጅቱ አካላት ነፃነትም እንደተነፈገ ይሰማኛል። እኛ በዬቤታችን ስንት
እንላለን? ስንቱን ስናብጠለጥል ውለን እናድራለን? ደግሞ ለዚህም አመራሩ የእኛን ነፃነት የመስጠት ፈቃድ ይጠይቅ
…. አይደል? ስንገርም?! እግዚኦ! እኛ ብንችል አንደበታቸውን በዚፕ እንዘጋው ነበር። …. ሁላችንም የተሰደድነው
ነጻነት ፈልገን ነው። ሞተውም ደምተው ተቃጥለውም ያስጠጉን ሀገሮች ለሰጡን ነፃነቱንም ካልተሰረ ብለን ኡኡታ
እናሰማለን … አዝናለሁ። እራሳቸውን አሳልፈው ለመስጠት የቆረጡትን … የግል ህይወታቸው፤ ፖለቲካዊ
ኑራቸውን፤ ሙያዊ ሥነ ምግባራቸው ሁሉ ስነብጠለጥል መሽቶ ይነጋል። ነግቶ ይመሻል። ይህ ለእኔ ሥራ ፈትነት
ይመስለኛል።
ድል ከተፈለገ የመብታችና የግዴታችን ጣራና ግድግዳ አውቀን እንራመድ!
ማሰተዋል እንደ ተሰጠን እንፈጽመው ዘንድ እግዚአብሄርን በሱባኤ እንጠይቀው!
ቅንነትን ለማዳ እናድርገው!
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
source addisvoice.

Friday, September 13, 2013

የርዕዮት ደህንነት አደጋ ላይ ነው!

(ሰርካለም አለሙ)
” እኔ ባልፍም እንኩዋን ሺህ ርዕዮቶች ስላሉ በርቱ አትደናገጡ “
* የርዕዮት ደህንነት አደጋ ላይ መሆኑን እንድታዉቁት ስል ነዉ ይህንን በብዙ ሀዘን ዉስጥ ሆኜ የጻፍኩላችሁ ትላንትና እንደሁል ጊዜዉ ስንቅ ይዤላት ወደ ቃሊቲ ሔድኩ በር ላይ ያለዉ ፖሊስ “የርዕዮት እህት ነሽ አይደል እሱዋን መጠየቅ አትችይም በአስተዳደር በኩል ሔደሽ ጠይቂ” አለኝ፡፡ እንዳዘዘኝ በአስተዳደር በር በኩል ሔድኩ ወደ ዉስጥ በስንት ትግል ከስለሺ (የርዕዮት እጮኛ) ጋር ገባን፡፡
Reeyot Alemu
Reeyot Alemu
ከብዙ ጥበቃ በሁዋላ በብዙ ፖሊሶች ታጅባ መጣች ፊትዋ ተለዋዉጦ ስለነበር ምን እንደሆነች ስጠይቃት ከእናት፡ አባት እና ንስሃ አባት ዉጪ ማንም ሊጠይቃት እንደማይችል እና የእነሱን ስም እንድትሰጥ እንደተጠየቀች እና አሚናዘር የሚትባል የሴቶች ክፍል ሀላፊ አልጋዋ ድረስ በመምጣት እንደሰደበቻትና እንደዛተችባት እየነገረችኝ እያለ አሚናዘር የተባለችዉ ሃላፊ ወደኛ በመምጣት ርዕዮትን በማመናጨቅና በመስደብ ከኛ ልትወስዳት ስትሞክር ለምን እንደሆነ ስጠይቃት “ከዛሬ ወዲህ ዐይኑዋን አታዩትም ማንም እኔን ሊያዝ አይችልም የእናንተ ጋዜጣና ሚዲያ ምን እንደሚያመጣ እናያለን ” በማለት ርዕዮትን በማዋከብ እና በመጎተት እየሰደቡ ወሰዱዋት፡፡ ምድር ላይያሉ ሰቅጣጭ እና ለህሊና የሚከብዱ ስድቦችን አወረዱብን በዚህ መሀል ርዕዮት ድምጹዋን ከፍ አርጋ “የማልጨርሰዉን ነገር አልጀምርም እኔን ለማንበርከክ እና ለማሸማቀቅ ክሆነ መቼም አላረገዉም ትገይኝም ከሆነ ነይ ተኩሺ ” ስትል ጎትተዉ ወሰዱዋት፡፡ እኛንም ከጊቢዉ አዋክበዉ አስወጡን፡፡
ዛሬ በዐል ስለሆነ ምን አልባት ሊያስገቡን ይችላሉ ብለን ነበር ሁላችንም ወደ ቃሊቲ የሔድነዉ፡፡ የሆነዉ ግን በጣም አሳዛኝ ነበር፡፡ በር ላይ ደርሰን ስንጠይቅ (ቤተሰቦችዋና ጓደኞችዋ) አሚናዘር ላስፈቅድ ብላ በር ላይ ያለችዉ ፖሊስ ወደ ዉሰጥ ገባች ትንሽ ቆየት ብላ ተመለሰችና አባትና እናት ብቻ ነዉ የሚገቡት ያልችዉ አሚናዘር ብላ እኔና ስለሺ ጓደኞችዋንም ጨምሮ መግባት እንደማንችል ተነገረን። የዚህን ጊዜ አባታችን “የእነሱን ህገወጥ ስራ እንደማይተባበር እና እኛ ተከልክለን እሱ እንደማይገባ ነገራቸዉ” እናታችን እንድትገባና ሁኔታዋን አይታ እንድትነግረን የያዝነዉን ምግብ ይዛ ገባች፡፡ በጣም በሀዘን የያዘችዉን ምግብ ይዛ ተመለሰች ” ምነዉ?” ስንላት ርዕዮት የርሃብ አድማ እንዳደረገች እና ቤተሰብ የማይገባላት ከሆነ አድማዉን እንደምትቀጥል እንደነገረቻት እናም በጣም ያስደነገጠንን ዜና ነገረችን “አጠገቡዋ ኮ/ል ሐይማኖት (የ ገብሩዋድ ባለቤት) እንዳመጡዋትና የርዕዮትን አልጋ በማስጠጋት እሱዋነ ከጎንዋ አድረገዋት እሱዋም ሙሉ ለሊት እየሰደበቻትና እየዛተች እንዳሳደረቻት ህይወትዋ አደጋ ላይ መሆኑን አንድ ነገር ቢፈጠር በህመም እንዳልሆነ እንድታዉቁት እኔ ባልፍም እንኩዋን ሺህ ርዕዮቶች ስላሉ በርቱ አትደናገጡ” የሚል መልእክት ነገረችን፡፡
አስረዉ ሲያበቁ እንኳን ምነዉ ቢተዋት? በዚህ ከቀጠለ እህቴን ነገ ለማግኘቴ ምን ያህል እርግጠኛ እንደምሆን አላዉቅም!!
የኢትዮጵያ ሜዲያ መድረክ.

Thursday, September 12, 2013

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጀግናዬና ሽልማቴ ናቸው( ሥርጉተ ሥላሴ )

ሥርጉተ ሥላሴ 10.09.2013
መቼም እኛ መላ ያጣን፤ ስንፈጠር ያዬነውን ነገር ለማድነቅ ያልተደልን ፤ በእጃችን ያለውን ኃብታችን ለማመሰገን
ያልተባረክን መሆናችን፤ አንጀት
የሚቆርጥ መቀስ ነው። ከብክበን
ያሳደገነው አብሮ አደግ ኮሳሳ
ባህሪያችን ቅናት ነው። እኛ የሌላ
ሀገር ጀግኖችን በትውስት
ስናሞጋግስ ይመቸናል። የተገለበጠ
ጉድ። በዚህ ዕድሜ የተመቸና
ሰላም የሰፈነው የለንደን ኑሯቸውን
ረስተው፤ ቤተሰቦቸውንም
ትተው፤ ልጆቻቸውንም አባት
አልባ አድርገው እንደ ገና ጫካ
ለጫካ ለነፃነት የሚተጉትን ክቡር
አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ለእኔ
ጀግናዬ ናቸው። ለሰማዕትነት
እራስን ፈቅዶ ከመስጠት ባላይ
ምን ትርጉም ያለው ጀግነንነት
አለና!
አቶ አንዳርጋቸው ጥሩ ተናጋሪ - አንደበተ ርዕቱ፤ ብቁ አስተማሪ፤ ጥሩ አደራጅ ከመሆናቸውም በላይ ጥሩ አድማጭም
ናቸው። እኔ በሁለት አጋጣሚ ከእሳቸው ጋር ተገናኝቼ በነበረበት ወቅት ውስጣቸውን ያዬሁት፤ በጥልቀት የመረመርኩት
ጉዳይ እራሳቸው የድርጅት ተቋም መሆናቸውን ነበር። አንዳንድ ተፈጥሮዎች አሉ እንዲዚህ ልዩ ጸጋና በረከት
የተመረቀለት። ያጌጠ መክሊት! እኔ ከፖለቲካ ተግባራት ጋር በጽኑ በተቆራኜው የህይወት ዘመኔ ሁሉ በታሪክ ታድዬ
ከሁለት ተፈጥሯቸውን እግዚአብሄር አምላኬ ለድርጅት ከመረጠው ወገኖቼ ጋር ተገናኝቻለሁ።
በአንድ ወቅት አብሬው እሰራው የነበረውና በአግባቡ ሰብዕናዬን የቀረጸው የድርጅት የተግባር መምህሬና አሁን ደግሞ
ለሁለተኛ ጊዜ የገጠሙኝ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ናቸው። ስለሆነም ይህን ተፈጥሮን እንዳከብረው፤ እንዳደንቀውና
እንድምሰክርለት ግድ አለኝና ብዕሬን እነሆ አነሳሁ።
አንድ የፖለቲካ ድርጅት የህይወቱ አናት ለድርጅት ጉዳይ ልዩ ተፈጥሮ ያላቸው፤ ሰብዕናቸው ለዚህ የተመረጠ፤ የተረጋጋ
የመንፈስ ቅምጥ ሃብት ያላቸው፤ የህዝብን ውስጣዊ ስሜት እዬረመሩ የሚፈውሱ ወገኖችን ማግኘት እጅግ አስቸጋሪና
መንገዱም አድካሚ ነው። ዘርፉ የአንድ የፖለቲካ ድርጅት ውድቀትም ሆነ እድገት መሰረታዊ ሩህ ጉዳይ ነውና። የአንድ
የፖለቲካ ድርጅት አካላዊ አቋሙ፤ ህልውና፤ የአፈጣጠሩን ሥነ ምግባር አሟልቶ ኃይል ሊሆን የሚችለው ለድርጅት
ተፈጥሮው ሥነ ምግባሩን ያሟሉ፣ ትክክሉና ግጣሙን ያሟሉ ዜጎችን ሲያገኝ ብቻ ነው። በዚህ ስሌት ስንሄድ ለአንድ
የፖለቲካ ድርጅት ወይንም ግንባር ወይንም ንቅናቄ ምንም ዓይነት የመዋቅር ጋጋታ፤ የማንፌስቶ መሽሞንሞን፤ የፖሊሲ
ጥራት አስተዋጾ እንጂ ወሳኝ ሚና የላቸውም።
አንድ የፖለቲካ ድርጅት የወሳኝነት ሚና የሚጫወተው የድርጅት ብቃቱ ምንጭ የሆነ፤ አቅምን ፈጥሮ አቅምን
በአግባቡ ተግባር ላይ ሊያውል የሚችል ብቁ ተፈጥሮ ያለው ሰው ዘርፉን የመምራት አጋጣሚ ከተገኘ ልዩ ሽልማት
ነው። „ሽልማታችን“ በሚልም በዬካቲት ወር መጨረሻ በ2009 የጻፍኩት መጣጥፍ ይህን የብቃት መሰረት መነሻ ያደረገ
ነበር።
ሰው እንደ ሰው የሚያድርጉት አካላቱና የነቃው ህሊናው ሙሉዕነት ነው። ለአንድ የፖለቲካ ድርጅት የሰው ሰውነቱ
ደግሞ የድርጅት ጉዳይ ነው። ይህ ከተገኘ መሰረቱ ሆነ መድረሻ እርካቡ ሙሉዕ ይሆናል። የዛ ድርጀት …. የጉዞ
እርግጠኝነት ይለፍም ይኖረዋል ። እርግጥ ነው ብዙ የፖለቲካ ድርጀቶች በዚህ ተፈጥሮ የታደሉ ሰዎችን በመምረጥና
በማሰማራት በአቅም ማነስ፤ ወይንም ጨርሶም ይህ ልዩ ተፍጥሮ ያላቸውን ካለማግኘት፤ ወይንም ለዘርፉ ብቁ ትኩረት
ካለመስጠትም ሊሆን ይችላል የድርጀቱ ሆድ ዕቃ የሆነውን የዘርፉን ጸጋዎች ለባለ ጸጋዎች ስለማያገናኙት ቀጭጨው
ዕድሜ ዘመናቸውን ሁሉ ካለ ሐሴት እንዲያልፉ ይገደዳሉ። እንዲህ የሰመረ ግንኙነት ሲኖር ግን ፈተናውን በማለፍ
ለውጤት የመብቃቱ አጋጣሚ አብዛኛውን እጁን ይይዛል። ለአንድ የፖለቲካ ፓርቲ የድርጅት ዘርፍ ኃላፊው አንጎሉና ማዕከላዊ የደም ማማንጫ እንብርቱ እንዲሁም መተንፈሻ
ቧንቧውም ነው። ከክቡር አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ተፈጥሮ ስነሳ በዚህ ግንቦት 7 ከሁሉም የተቃዋሚ ፓርቲዎች
የበለጠውን ዕድል አግኝቷል ብዬ አምናለሁ። ግንቦት ሰባት የዚህ ዕድል ባለድርሻ በመሆኑም ከምንም ነገር በላይ
የመንፈስ ዲታ ነው።
ምክንያቱም የድርጀቱ መዋቅራዊ ነባቢተ ነፍስ መደወሪያ ይህ ዘርፍ ነው። በድርጀት ዘርፍ ተግባር ከሁሉም በላይ ረጅም
ጊዜ ሳይሰለቹ መቀመጥን ይጠይቃል። ፍላጎትን ጠቅልሎ በተገቢው ሰዓት - ለተገቢው ኃይል በአግባቡ ማከፋፈልን
ይሻል። እንደ ገናም ያሰማራቸውን ተግባሮች ሰብስቦና ገምግሞ ለቀጣይ ስምሪት ድክመቶችን በማረም እንዲሁም
ፈተናዎችን በማረቅ ተከታይ የስምሪት ተግባር እዬከወነ ለውጤቱ ድልድይ ያበጅለታል። ለዚህ ደግሞ ለግንቦት 7 ብቻ
አይደለም ለትውልዱ ክቡር አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የግንቦት 7 ጸሐፊ ተፈጥረዋል። ስጦታም ናቸው።
እርምጃውን እራሱ ቁጭ ብዬ ሳስተውለው ይህ እርምጃ በዚህ ዘመን ይታሰባልን? ይህ ውሳኔ በዚህ ዘመን ይታለማልን?
ለዛውም ከአውሮፓ ወደ ሳልህ በረኃ … በማለት እኔ እና እኔን ስብሰባ አስቀምጬ ፍርድ ስጥ ብዬ ህሊናዬን ሳፋጠው
መልስ አልነበረው። ህሊናዬ ከበደው። እኔ ሥርጉተ ሥላሴ ክቡር አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ፍጹም ሊገለጽ የማይችል
የመስዋዕትነት የተግባር አብነት ሆኖ ነው ያገኘኋቸው። ተግባሩ ሥነ ጸጋ፤ ከሥነ - መስዋዕትነት ጋር ሲጋባ የነፃነት
ስዋሰዋዊ ህግ ሆኖ ነው ያገኘሁት።

የማይሆነው ሲሆን፤ ያልተሰበው ሲከውን በዓይን ላይ ዕውነት ቁሞ ሲመሰከር ማዬትን ላልታደሉት ስውሮች
መዳህኒዓለም አባቴ ዓይናቸውን በተለይም ህሊናቸውን እንዲበራላቸውና የቀበሩትን ቅንነት ይጠቀሙበት ዘንድ
እንዲረዳቸው እዬተመኘሁ …. የእናታችነን ጥቃት ለማውጣት በዱር በገደሉ ለሚከላተሙት የነፃነት ደቀ መዝሙር
የ2006 ምርጥ ሰው ክቡር አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን እግዚአብሄር አምላክ እንዲጠብቃቸው ድንግልም ጥላ ከላላ
ትሆናቸው ዘንድ እማጸናለሁ። ድካማቸውን ለፍሬ ይበቃ ዘንድም ከልብ እመኛላቸዋለሁ። ለአርበኞቻችንም
ከማያልቀው የኤደን ገነት ኃይልና ብርታት ድልና ሰብል ዕለታዊ ስንቃቸው እንዲሆንላቸው ከልቤ እመኛለሁ።
ድል ለአርበኞቻችን!
የትውልዱን ባለውለታዎች የምናከብርበት ንጹህ ልቦና አምላካችን ይፍጠርልን!
አሜን!
source Addis Voice.

Wednesday, September 11, 2013

መነበብ የሚገባው! የሙስና ነገር (ክፍል ሁለት) – በዳዊት ከበደ ወየሳ

የሙስና ነገር (ክፍል ሁለት)
በዳዊት ከበደ ወየሳ
እውነት የማይመስሉ ግን እውነት የሆኑ የሙስና ታሪኮች - በኢትዮጵያ።
አሁን በኢትዮጵያ አቆጣጠር ወደ 2006 ተሻግረናል። ከአመት ወደ አመት ስንሸጋገር ደግሞ ያለፈውን አመት
የሙስና ነገር በገደምዳሜ ዳሰስ አድርገን ብናልፍ ክፋት የለውም። በመሆኑም የስራ ባልደረባዬ ክንፉ አሰፋ “ክፍል አንድ”
ብሎ በጀመረው የሙስና ጉዳይ… “ክፍል ሁለት” ብዬ እኔ ቀጠልኩበት፤ አንብቡት።
የጉምሩክ ከፍተኛ ሃላፊዎች ሲታሰሩ፤ በየፊናው የነበሩ ጉምቱ ባለስልጣናት መደንገጣቸው አልቀረም። “እገሌስ
መቼ ነው የሚታሰረው ወይም የምትታሰረው?” የሚለው ሹክሹክታም ከቢሮ አልፎ በአደባባይ የህዝቡ መነጋገሪያ ሆኖ
ሰንብቷል። በዚያኑ ሰሞን ከኢትዮጵያ የመጣ አንድ ዘመዴ ጋር ቁጭ ብለውን ስናወራ፤ “ገብረዋህድ የሚባለውንስ እንኳንም
አሰሩት።” አለኝ።
“ምነው?” አልኩት።
“በጣም መጥፎ ሰው ነው” ብሎ ጀመረልኝ - ፊቱን አጨፍግጎ። “መጥፎ ሰው ነው። አንዳንዴ እንደተራ ሰው ሻይ
ቤት እና ቡና ቤት ገብቶ፤ የሆነ ነገር አዝዞ ይቀመጣል። ከዚያም አንዱ ተስተናጋጅ፤ ሂሳቡን ከፍሎ ሲወጣ፤ ድንገት ደረሰኝ
ይዞ ካልወጣ… ከመቀመጫው ተነስቶ፤ ‘ሌቦች አጭበርባሪዎች’ ብሎ ይሳደብና ፖሊስ ወዲያው ጠርቶ የንግድ ቤቱን
ያሳሽጋል።” (ደረሰኝ ለደንበኛ አለመስጠት ሙስና መሆኑን እዚህ ላይ ጠቅሰን እንለፍ)… እናም ይህ የጉምሩኩ ምክትል
ሰውዬ ያላስለቀሰው ነጋዴ የለም።
ደግሞም በነጋዴዎቹ ቢበቃው ጥሩ ነበር። የመስሪያ ቤቱን ሰራተኞች በሙስና እየወነጀለ ያላሳሰረው ሰራተኛ
እንዳልነበር፤ የቅርብ ሰዎች ያወራሉ። እዚህ ላይ አንድ አስቂኝ ነገር አለ። ይሄ ለሰማይና ለመሬት ከብዶ ህዝቡን ሲያስለቅስ
የነበረ ሰውዬ በመጨረሻ የሱም ቀን ደረሰና ሊታሰር ሆነ። እናም በቁጥጥር ስር በዋለበት ቀን፤ ሁለት የፌዴራል ፖሊስ
አባላት ወደ ቢሮው ገብተው በቁጥጥር ስር ሊያውሉት ሲሉ ይደነፋል።
“ማን እንደሆንኩ ታውቃለህ?” ይላል።
“አዎ እናውቃለን!” አሉት። አንድ ሁለት ቃል ከተለዋወጡ በኋላ፤ ልክ እንደ ነጋ ገብረእግዚአብሄር - አንቱ
ወደተባሉ ከፍተኛ የህወሃት አባላት ስልክ መደወል ይጀምራል። ከባለስልጣናቱ የሚሰማው ነገር ያልጠበቀው ነበር። በመሃል
ፌዴራል ፖሊሶቹ ከቢሮው እንዲወጡ ያደርግና ከውስጥ በኩል የቢሮውን በር ይቆልፈዋል። ፖሊሶቹ ቢያንኳኩ -
ቢያንኳኩ የሚከፍት ሰው ጠፋ። የጉምሩክ መስሪያ ቤት ተጨነቀ። በቢሮ አካባቢ ያሉት “በቃ ይሄ ሰውዬ እንደ አጼ
ቴዎድሮስ የራሱን ህይወት ሊያጠፋ ነው” ብለው በመስጋት፤ ከአሁን አሁን የተኩስ ድምጽ በጉጉት ይጠባበቃሉ። ሌሎች
የግቢው ጥበቃ ሰራተኞች ደግሞ፤ ‘ከፎቅ ላይ ራሱን ወርውሮ ይገድላል’ በሚል ስጋት አንገታቸውን ወደ ፎቁ አንጋጠው፤
ድንገት ከፎቅ ላይ ሲወድቅ ሮጠው እንደኳስ ሊቀልቡት ተዘጋጅተዋል። ይሄ ሁሉ ሲሆን፤ ሰውየው ቢሮውን ቆልፎ
ከህወሃት ባለስልጣናት እስከ ጠቅላይ ሚንስትሩ ቢሮ ድረስ ስልክ እየደወለ ነበር።
የደወለላቸው ባለስልጣናት በሙሉ ለራሳቸው በመስጋት የተለያየ ምክንያት እየሰጡ ስልኩን ጆሮው ላይ ዘጉበት።
በዚህች ቀውጢ ወቅት በመከላከያ ውስጥ የኮሎኔል ማዕረግ የተሰጣት፤ እጩ ጄነራል ሚስቱም ልታድነው አልቻለችም።
ፌዴራሎቹ ጉዳዩን አስመልክተው ወደ አለቆቻቸው ደወሉ። “ሰውየው እራሱን እንዳያጠፋ ስለሰጋን ነው” አሉ።
ከአለቆቻቸው የተሰጣቸው መልስ አጭር ነበር። “እራሱን አያጠፋም። ተጨማሪ ትዕዛዝ እስከሚሰጥ ድረስ እዚያው ቆዩ”።
የሙስና ነገር (ክፍል ሁለት) በዳዊት ከበደ ወየሳ ገጽ1“ሰራተኛ ሲወጣ፤ እሱ ከቢሮ ካልወጣ ሰብራችሁ ትገባላችሁ” ተባሉ። ፖሊሶቹም ሰራተኛው ከስራ እስኪወጣ
መጠባበቅ ጀመሩ። ሰራተኛው ከወጣ በኋላ፤ ፌዴራሎቹ በር የሚሰብሩበትን መሳሪያ እያፈላለጉ ሳለ ገብረዋህድ
ከተደበቀበት ቢሮ ሹክክ ብሎ ወጣ።
“ምነው ብዙ የምታስጠብቀን?” ብለው ጠየቁት ፌዴራሎቹ።
“በሰራተኛው ፊት ታስሬ መሄድ ስላልፈለኩ ነው” አላቸው።
ገብረዋህድ በማግስቱ የፈራው ደረሰበት። ለፖሊስ ቃሉን ከሰጠ በኋላ፤ በሚቀጥለው ቀን የመንግስት ንብረት
እንዲያስረክብ ወደ ጉምሩክ ሲወሰድ፤ በሰራተኞቹ ፊት ሁለት እጁን ተጠንጎና በፌዴራል ፖሊሶች እየተጎነተለ መጣ። “ከዚህ
በላይ ውርደት?” ብለን ቃሉን አለመጨረሹ ይሻለናል።
ሌላም የሚገርም ነገር አለ። ይሄ ሰው ከመታሰሩ አንድ ወር በፊት በመላው አገሪቱ የሚገኙ የጉምሩክ
ባለስልጣናትን በኮንፈረንስ ስብሰባ አድርጎ ነበር። የፈረደበትን የሟቹን ጠቅላይ ሚንስትር ፎቶ በመለጠፍም “በሙስና
ለምትጨማለቁት እንደደርግ ጥይት አናጎርሳችሁም፤ እናስራችኋለን።” እያለ ስለመለስ ራዕይ ሲያወራ ነበር። በንግግሩም
መጨረሻ፤ (ያን ሰሞን የመለስ ሚስት የምኒልክን ቤተ መንግስት ለቅቃ ነበርና…) “በአሁኗ ደቂቃ የመለስ ዜናዊ ልጆች
መኖሪያ ቤት እንኳን የላቸውም። ሜዳ ላይ ነው የቀሩት።” ሲል የዋሆቹ ሲያለቅሱ፤ ነገሩን የሚያውቁ ግን ስቅስቅ ብለው
ይስቁ ነበር።
ገብረዋህድ ከታሰረ በኋላ በስሙ የአርሲን ቆዳ ስፋት የሚያህሉ የቤት ካርታዎች ሲገኙ፤ “ምናለበት አንዱን ቤት
ሜዳ ላይ ለወደቁት ለመለስ ዜናዊ ልጆች ቢሰጣቸው ኖሮ?” መባሉ አልቀረም።
ወደ አዲስ አበባ ከተማ ሲገቡ፤ ቦሌ መንገድ ላይ ያሉትን ህንጻዎች ከተመለከቱ፤ ህዝቡ ራሱ እንደጎበዝ አስጎብኚ
ይነግርዎታል። “ይሄ ህንጻ የጄነራል ጻድቃን ነው። ይሄኛው የጄነራል እገሌ ነው እያሉ፤ መድሃኔአለም ቤተ ክርስቲያን ፊት
ለፊት ከሚገኘው ኤድናሞል ህንጻ ጋ ሲደርሱ ደግሞ “ከጎኑ ያለው የሚያምር ህንጻ የጄነራል አባ ዱላ ነበር።” ይሏችኋል።
“አሁንስ የማነው?” ካሉ አስጎብኚዎ የሙስናን ነገር እያጣቀሰ ወሬውን ሊቀጥል ይችላል። እኛም እንንገርዎ - የነ አባ
ዱላን ነገር። አባ ዱላ ገመዳ አሁን የፓርላማው አፈ ጉባዔ ነው። ከዚያ በፊት የኦሮሚያ ፕሬዘዳንት፡ ከዚያም በፊት
የመከላከያ ሚንስትር፡ ከዚያ በፊት በሻዕቢያ የተማረከ የደርግ ወታደር ነበር… መቼም አንድ ወታደር ለሻዕቢያ እጅ ሰጥቶ
ከተማረከ ከዚያ በፊት ምን ነበር? ተብሎ አይጠየቅም። እናም አባዱላ እና በሙስና ስለተሰራው ትልቅ ቤተ መንግስት
የመሰለ ቤታቸው ከማውራታችን በፊት፤ ሰውየው ሌሎቹን ጄነራሎች ጭምር እንዴት በሙስና እንዳነካኩ ላጫውታችሁ።
በአንድ ወቅት ለጄነራሎቹ (ያው ከአባ ዱላ በቀር ብዙዎቹ ህወሃቶች ናቸው) አዲስ አበባ ውስጥ መኖሪያ እንዲሰሩ
መሬት ተሰጣቸው። የሲሚንቶ እና የሌላ ሌላው ነገር ዋጋ መጨመርን ተከትሎ የብዙዎቹ አቅም የሚችለው አልሆነም።
እናም የኦሮሚያ ፕሬዘዳንት የነበሩት አባ ዱላ ገመዳ ከሌሎቹ ጄነራሎች ጋር በመመሳጠር በኦሮሚያ የሚገኙ መሬቶች፤
እየተሸነሸኑ ለጄነራሎቹ በስጦታ መልክ እንዲሰጣቸው አደረጉ። ይህ የተደረገው ያለ ምክንያት አይደለም። በኋላ ላይ
ጄነራሎቹ በኦሮሚያ ባለስልጣናት የተሰጣቸውን መሬት እየሸጡ፤ አዲስ አበባ ላይ በተሰጣቸው መሬት ላይ ህንጻ
ከቢሾፍቱ እስከ አዳማ፤ አልፎም እስከ ሻሸመኔ ድረስ ያሉ መሬቶች በዚህ አይነት የሙስና ቅብብሎሽ ለጄነራሎቹ
ታደሉ። አባ ዱላ ገመዳ ይሄንን ሁሉ ሲያደርግ፤ ለሱም ትንሽ ጉርሻ ይሰጠው ነበር። ያቺ በጉቦም በ እጅ መንሻም ያገኛትን
ገንዘብ ሰብስቦ ቦሌ መድሃኔአለም ፊት ለፊት የተንጣለለ ህንጻ መገንባት ጀመረ።
እንግዲህ ልብ በሉ። በቦሌ መንገድ እርስዎ ብቻ አይደሉም የሚሄዱት- ሟቹ ጠቅላይ ሚንትርም በዚያ መንገድ
ብዙ ጊዜ ተመላልሰው ነበር - ያውም መንገድ እየተዘጋ። እናም አስጎብኚው ለርስዎ እንደሚነግርዎ ለመለስ ዜናዊም፤ “ይሄ
የእገሌ ነው። ይሄኛው የጓደኛችን እገሌ ነው።” መባሉ አልቀረም። ነገር ግን ሟቹ ጠቅላይ ሚንስትርም ቢሆኑ፤ የስርአቱ
ዋነኛ መገለጫ የሆነውን የሙስና አደጋ በዝምታ ሲያልፉት ነበር። የኢህአዴግ ሰዎች ሙስናን እንደጥፋት የሚያዩት ከዚያ
ሰውዬ ጋር እስከሚጣሉ ድረስ ነው። እናም ከአባ ዱላ ጋር እስከሚጣሉና የጄነራልነት ማዕረጉን እስከሚገፈፍ ድረስ ምንም
አላሉም። በኋላ ላይ ግን… አባ ዱላ ከህወሃት ሰዎች ጋር ሳይሆን ከራሱ ሰዎች ጋር መጋጨት ጀመረ። በተለይም በኦህዴድ
የሙስና ነገር (ክፍል ሁለት) በዳዊት ከበደ ወየሳ ገጽ2ውስጥ ካለው ከነ ግርማ ብሩ ቡድን ጋር ክፉኛ ተጋጨ - የቁርጡ ቀን ሲመጣም በመታሰር፣ ክብርን በማጣት እና ንብረቱን
በመስጠት መካከል ዋዠቀ።
በመጨረሻ አባ ዱላ ገመዳ ያሰራውን እና ሊኖርበት የነበረው በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ የወጣበት ባለ
ትልቅ ግቢ ቪላ ጥያቄ ውስጥ ገባ። ጸቡ እየከረረ ሲመጣ፤ በመጀመሪያ ደረጃ ያሰራው ትልቅ ህንጻ በሙስና መሆኑን ነገሩት።
መጀመሪያ ሊከራከር ፈለገ። በኋላ ላይ ግን ደሞዙና የወጣው ወጪ እንደማይመጣጠን ሂሳቡን ሰርተው ሲያሳዩት፤ “አይ እኔ
እንኳን Surprise ላደርጋችሁ ብዬ ነው” አለ።
ኦህዴዶቹም በመገረም፤ “ምንድነው Surprise የምታደርገን?” ሲሉ ጠየቁት።
“ይሄንን ቤተመንግስት የመሰለ ቪላ የሰራሁት ለኔ ሳይሆን፤ ለድርጅታችን ነው።” ብሎ የቤቱን ቁልፍ ሲያስረክብ፤
አጨብጭበው ዝም አሉት። አሁን በቦሌ በኩል ስታልፉ፤ “ይሄኛው የጄነራል አባ ዱላ ነበር” ይሏችኋል። ከርክክቡ በኋላ
ግን የኦህዴድ ዋና ጽህፈት ቤት ሆኗል - እውነት የማይመስል የአገራችንን ታሪክ ነው እያወጋናችሁ ያለነው።
ባለስልጣናቱ “Surprise” ከመባላቸው በፊት፤ እዚያው ቤት ምሳም እራት ተጋብዘው በልተዋል። የቤት ምርቃቱ
ጊዜ፤ ስጦታ ይዘው መጥተዋል። ጸቡ ሲመጣ ዝምድናው ወደ ሙስና ተቀይሮ፤ አባ ዱላ ገመዳ ቪላ ቤቱን ከነ ሙሉ እቃው
የኦሮሚያ ቤተ መንግስት እንዲሆን ሰጥቶ ከመታሰር አመለጠ። የጄነራልነት ማዕረጉን ከመቀማት ግን አልዳነም። ከመከላከያ
ሚንስትርነትም ሆነ ከኦሮሚያ ፕሬዘዳንትነት በጥፋት ተወንጅሎ ከተነሳ በኋላ ይህንን ታማኝ ሰው ሙስና የሌለበት ቦታ
ሊመድቡት ፈልገው ክፍት የስራ ቦታ ፓርላማ ውስጥ ተገኘ። እናም የፓርላማው አፈ ጉባኤ በመሆን፤ ኢህአዴግን
በማገልገል ላይ ይገኛል - አባ ዱላ (ምናሴ ገብረማርያም )።
እንግዲህ ይህ ሙስና የምንለው ነገር… ዋናዎቹን ሰዎች እስካላስከፋ ድረስ፤ በኢህአዴጎች ዘንድ እንደባህል
የሚቆጠር ነውር ያልሆነ ተግባር ነው። የሙስና ነገር አውርተን… የኢህአዴግ ሙስና እመቤት ስለሆነችው ወ/ሮ አዜብ
መስፍን ሳንጨዋወት ብንቀር እሳቸውም ቅር ይላቸዋልና ስለ ወይዘሮዋ ትንሽ እንዙር።
በአንድ ወቅት ለጄነራሎቹ መሬት ሲታደል ወይዘሮዋ ቦታ አምልጧቸው ኖሮ ተናደዋል። ወደ አዳማም ሆነ
ቢሾፍቱ ደውለው ቢጠይቁ፤ “መሬት ተወዲ’ዩ” አሏቸው። ቆይተው ግን በኦሮሚያ ሰበታ ከተማ መሬት መሰጠት መጀመሩን
ሰምተው፤ እንዲሰጣቸው ጠየቁና ተሰጣቸው። ከዚያም የሚያውቋቸውን ሰዎች እየላኩ መሬት ያሳድሉ ጀመር። በኋላ ላይ…
የሰበታ ከተማ አስተዳዳሪዎች ሁኔታው ሲበዛባቸው፤ በወ/ሮ አዜብ አማካኝነት የሚላኩትን ሰዎች መሬት ከለከሏቸው።
በዚህን ጊዜ ወ/ሮ አዜብ መስፍን እሳት ለብሰው፣ እሳት ጎርሰው ለከተማው አስተዳዳሪ ደወሉና ከፍ ዝቅ አድርገው
ተናገሩት። በመጨረሻ የሆነው ነገር ነው የሚገርመው… ወይዘሮዋ ዛቻ ቢጤ አሰሙ። እንዲህ ሲሉ።
“እንዲያውም በሰበታ አካባቢ ሙስና አብዝታችኋል ማለት ነው! ሙስና ስላበዛችሁ ግምገማ መደረግ አለበት።”
ወ/ሮ አዜብ እንዳሉትም በህወሃት ሰዎች ታጅበው ሰበታ ከተማ በመገኘት የመንግስት ሃላፊዎችን ከላይ እስከታች
አተረማመሷቸው። ለሳቸው መሬት የሰጧቸው ሰዎች ሳይቀር፤ በሙስና ተወንጅለው እየተለቀሙ ታሰሩ። መሃንዲሱ እና
መሬት ፈቃጆቹ ሁሉ ተቀፈደዱ። ከዚያም የራሳቸውን ታማኞች ሹመው ሰበታ ከተማን ለቀው ተመለሱ። ባለፈው አመት
ኢቲቪ ስመለከት እነዚያ በሰበታ ከተማ “ሙስና ውስጥ አላችሁበት” የተባሉ ሰዎች እያንዳንዳቸው ከአስር አመት በላይ
እንደተፈረደባቸው ሰማሁ። በርግጥ ሰዎቹ ሙስና ውስጥ ነበሩበት። ቢሆንም ግን ለወ/ሮ አዜብ መስፍን እና ለሌሎች መሬት
ሲሰጡ፤ ሙስና አልተባለም… የአዜብን “ትዕዛዝ አንቀበልም” ሲሉ ግን የጨዋታው ህግ ተቀይሮ፤ ሰዎቹ በሙስና ወንጀል
እየተለቀሙ ወህኒ ወረዱ።
መቼም የወ/ሮ አዜብ መስፍን ታሪክ ማለቂያ የለውም። ባለፈው ሰሞን ደሞ፤ አቶ አያሌው የተባሉ ትልቅ ባለሃብት
ፍርድ ቤት ቀርበው ሲናገሩ፤ “ክቡር ፍርድ ቤት እኔ ምንም ጥፋት እንደሌለብኝ አቃቤ ህጉም ያውቀዋል። የኔ ጥፋት ከወ/ሮ
አዜብ መስፍን ጋር በሽርካነት እንድሰራ ተጠይቄ እምቢ ማለቴ ነው።” ብለው ነበር። አቶ አያሌው በተከበሩበት አገር አስራ
ስድስት አመት ተፈርዶባቸው ወደ እስር ቤት መወርወራቸውን ከጥቂት ወራት በፊት ስንሰማ ማዘናችን አልቀረም። እንግዲህ
አቶ አያሌው በደርግ የሶሻሊዝም ዘመን ሳይቀር በንግድ ሙያ ውስጥ የቆዩ ናቸው። የደርግ ዘመን አልፎ በዘመነ - ነጻ ገበያ
ሲታሰሩ ያልገረመው ሰው የለም።
የሙስና ነገር (ክፍል ሁለት) በዳዊት ከበደ ወየሳ ገጽ3እዚህ ላይ የምናወራው ላይ ላዩን የምናውቀውን… እውነት የማይመስል፤ ነገር ግን እውነት የሆኑ የሙስና ታሪኮችን
ነው። ውስጥ ውስጡን የማናውቀው ብዙ ነገር ሊኖር እንደሚችል ምንም አያጠያይቅም። ሌላ ነገር ትውስ አለኝ። የዛሬ 12
አመት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ወደ አሜሪካ ሲመላለሱ፤ ብዙም አይን የሚገቡ ሰው አልነበሩም። ሃብታቸውም ሰማይ
አልደረሰም ነበርና ብዙዎች ትኩረት አንሰጣቸውም ኖሯል። ሆኖም እዚሁ አሜሪካ ኮሎምበስ ኦሃዮ ለምትገኘው እህታቸው፤
250 ሺህ ዶላር ካሽ ከፍለው ቪላ ቤት ሲገዙ ብዙዎቻችን ማመን አቃተን። እናም ‘አዜብ ሙስና ውስጥ የለችበትም’ እያለ
ለሚጨቀጭቀኝ ዘመዷ ስልክ ደወልኩና ጠየኩት።
“የምንሰማው እውነት ነወይ?” አልኩት።
“ምኑ?” አለኝ።
“ዘመድህ ካሽ ከፍላ ለእህቷ ቪላ ቤት የመግዛቷ ነገር…” ብዬ ሳልጨርስ፤ የነገሩን እውነተኛነት አረጋግጦ በትህትና
ሊያስረዳኝ ሞከረ።
“እሷም ሆኑ ልጆቿ ሲመጡ የሚያርፉበት ቤት ያስፈልጋቸዋል። ... ታዲያ ይህን ማድረጓ ምን ያስደንቃል?" የሚል
አይነት ምላሽ ሰጠኝ። ለነገሩ ከደጃዝማች ጎላ የሚወለዱ፤ የነአዜብ መስፍን የቅርብ ዘመዶች ብዙ ናቸው። ድርጊቷን
የሚደግፉ እንዳሉ ሁሉ፤ በግልጽ የሚቃወሟትም አሉ። ለገንዘብ ሳይሆን ለህሊናቸው ላደሩ ዘመዶቿ አክብሮት እንዳለኝ
በዚህ አጋጣሚ ጠቅሼ የውጪ ሃብት ግዢውን ነገር እዚህ ላይ ገታ ላድርገው።
የ"ደቡብ ክልል" ፕሬዚዳንት የነበሩት የአቶ አባተ ኪሾ ጉዳይም አለ። አባተ ኪሾ ከወያኔ ሳይጣሉ ከደቡብ በጀት
ተመላሽ የሆነ ሰባ ሚሊዮን ብር (70.000.000) ለመንግስት ተመላሽ ሊያደርጉ ሲሉ "ወዲህ በል!የምን መንግስት ነው?"
በማለት ወ/ሮ አዜብ ተቀብለው ወስደዋል። ብሩ ወደ አዜብ ካዝና ይግባ እንጂ የፖለቲካ ቂም የተቋጠረባቸው አቶ አባተ
ወደ ወህኒ ከመወርወር አልዳኑም። አቶ አባተ ኪሾ ይህንን ጉዳይ በፍ/ቤትም ጭምር ምስክር ሰጥተውበት ነበር።
የወ/ሮ አዜብን ጉዳይ ጨርሼ ወደሌሎቹ መሄድ ብፈልግም። ብዙ እውነት የማይመስሉ፤ ነገር ግን እውነት የሆኑ
አስገራሚ ነገሮች ታወሱኝ። ስለሁሉም ነገር ምንም ማለት ስለማልችል ጥቂት ነገር ብዬ የሴትዮዋን ነገር ልቋጭ። በኢትዮጵያ
የፀረ ሙስና ኮሚሽን ሲቋቋም በዋናነት እንዲሰራ ከታዘዙት ነገሮች አንዱ፤ የመንግስት ባለስልጣናት ሃብታቸውን
እንዲያስመዘግቡ ማስደረግ ነው። ይህ ስራ እንደተጀመረ… “አሻፈረኝ አላስመዘግብም” ካሉት ውስጥ ወ/ሮ አዜብ እና
የህወሃት ጄነራሎች መሆናቸውን ከዚህ በፊት በሌላ ጉዳይ ላይ ጠቅሼው ነበር። አሁንም ልድገመው። እናም የወ/ሮ አዜብ
መስፍን የሃብት መጠንም ሆነ ምንጭ እስካሁን ድረስ በመንግስት ደረጃ አልተመዘገበም። አሁንማ ሴትዮዋ ጥቁር ሲለብሱ፤
ጥቁር ለብሰው የሚያጅቧቸው፤ ሲያስነጥሳቸው መሀረብ የሚያቀብሉ አሽከሮች አላቸው። ሴትዮዋ ከመለስ ዜናዊ ሞት በኋላ
እንደጎማ ተንፈስ ብለዋል። ሜጋ ሚሊዮን ዶላር ከሚያንቀሳቅሰው የህወሃት ኤፈርት ሊቀመንበርነት ተነስተው፤ የመለስ
ዜናዊ ፋውንዴሽን ዛፍ አስተካይ ከመሆን ያለፈ ስልጣን እንደሌላቸው እየስማን ነው።
በሌሎች ላይ የሚደረገውን የሙስና ክስ አመሰራረት እያየን… “የሙስና እመቤቷ ወ/ሮ አዜብ እና ሌሎች
የኢህአዴግ ሰዎችስ ተራ መቼ ይሆን?” ማለታችን አልቀረም። ደግሞም “የጉምሩክ ባለስልጣናት ሲታሰሩ ዋነኛውን ሃላፊ አቶ
መላኩ ፈንታን ወንጀል አግኝተውበት ይመስላችኋል?” አይደለም። ነገሩ የህወሃቱን ገብረዋህድ ብቻውን ቢያስሩት በህወሃት
አካባቢ ከፍተኛ ጫጫታ መምጣቱ አይቀርም። ስለዚህ ከብአዴንም “የአማራ ድርጅት አባል አስረናል” በማለት ነገሩን
ለማብረድ የተጠቀሙበት ነው የሚመስለው።
ባለፈው አመት ብቻ ምን ያህል ሙስና እንደተፈጸመ እናውጋ እና እንለያይ። ባለፈው አመት (እ.ኢ.አ 2005) ከ1
ሺህ 500 በላይ ጥቆማዎች ለፀረ ሙስና ኮሚሽን ደርሰው በ200 ያህሉ ላይ ክትትል አድርጓል። የሚገርመው ግን ከሁለት
ሺህ በላይ ጥቆማዎች ደግሞ፤ ከስልጣኔ በላይ ነው በማለት ባሉበት ትቷቸዋል። (ይህንን መረጃ ያገኘነው ከራሱ ከፀረ ሙስና
መስሪያ ቤት ነው።) እነዚህ ከፀረ ሙስና ኮሚሽን አቅም በላይ የሆኑት እንግዲህ፤ የጄነራሎቹ፣ የነአዜብ እና የህወሃት
ከፍተኛ ንብረት እና የመከላከያ ጉዳይ መሆኑ ነው።
የሙስና ነገር (ክፍል ሁለት) በዳዊት ከበደ ወየሳ ገጽ4ለመሆኑ መከላከያ ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ በሙስና ተወዳዳሪ ያልተገኘለት፤ ከፌዴራል መንግስት ውጪ የራሱ ባለ
አምስት ሆቴል እና ሌሎች የንግድ ስራዎችና ገቢዎች እንዳለው ያውቃሉ? የምናወራው እውነት ስለማይመስሎት፤ የሙስና
ታሪካችን ስለሆነ አብረውን ይቆዩ።
ፀረ ሙስና ኮሚሽኑ ከስልጣኑ ውጪ ያሉትን ሙስናዎች አይከታተልም። እናም ከዚህ በታች ያሉት ኮሚሽኑ
እርምጃ ስለወሰደባቸው ጉዳዮች ነው።
ባለፉት ሁለት አመታት ከአንድ ሺህ በላይ የሙስና ክሶች ተከፍተው፤ ጉዳያቸው በፍርድ ቤት ታይቷል ወይም
እየታየ ነው። እውነት ከማይመስሉ መካከል አንዳንዶቹን እንጥቀስ። በየሰፈሩ ወጣቶችን ሳያደራጁ፤ ያደራጁ አስመስለው
መሬት የወሰዱ የኢህአዴግ አባላት ብዙ ናቸው። የሃሰት የማህበራት ማደራጃ ሰነድ በማዘጋጀት ግምቱ 25 ሚሊዮን ብር
የሆነ መሬት በነዚህ ሰዎች እንደአባት ውርስ ። ከሰላሳ ሚሊዮን ግምት በላይ ያለው 4ሺህ ካሬ መሬትም በ’ነዚህ የኢህአዴግ
ሰዎች ያለአግባብ ወደ ግል ይዞታነት ተቀይረዋል ወይም ካርታ ወጥቶባቸዋል፤ አልፎ ተርፎም የገንዘብ ብድር
ተወስዶባቸዋል። ግምቱ 842 ሚሊዮን ብር የሆነ መሬትም ያለአግባብ በግለሰቦች እጅ ገብቶ፤ የፀረ ሙስና ኮሚሽኑ
የሚያደርገው ጠፍቶት፤ ግራ እንደተጋባ 2006 ዓ.ም. ገብቷል።
የኢህአዴግ አባላትና ሹመኞች በመሬት ቅርምት ብቻ አያበቁም። ጉምሩክ መስሪያ ቤት ዋነኛ የገቢ ምንጫቸው
ነበር። በኮንትርባንድ የተያዘን ለዋስትና የተያዘን ቦንድ ሰነድ በማጥፋት ገንዘቡን ቅርጥፍ አድርገው ይበሉታል። የኢህአዴግ
ወዳጆች ወይም ጉቦ የሚሰጡትን አነስተኛ የታክስ መጠን በማስከፈል ከመቶ ሚሊዮን ብር በላይ ወደ ግለሰቦች ኪስ ገቢ
ሆኗል።
በመንግስት መስሪያ ቤቶች ትላልቅ ግዥና ሽያጭ ሲደረግ ያለው ማጭበርበር ደግሞ አይን ያወጣ ነው። የአፋር
መስተዳድር ቻይናዎች መንገድ እንዲሰሩ ከተዋዋሉ በኋላ የፌዴራሉ መንግስት የሰጣቸውን 10.7 ሚሊዮን ብር እጃቸው
አስገብተው ከመብላታቸው በፊት ተይዘዋል። እንዲህ አይነት ብዙ ታሪክ መዘርዘር ይቻላል። ባለፈው አመት ብቻ ልዩ ልዩ
የመንግስት መስሪያ ቤቶች ባወጧቸው ጨረታዎች እና የሃራጅ ሽያጮች 3 መቶ ሚሊዮን ብር ተጨበርብሮ የተያዙም
የተፈቱም ሰዎች አሉ።
ከፊንጫ ስኳር ፋብሪካ 75 ሚሊዮን ብር መሰረቁን እንንገርዎና በየመስሪያ ቤቱ እንዲህ ያለው ማጭበርበር ምን
ያህል ሊሆን እንደሚችል እርስዎ ይገምቱ።
“በኢትዮጵያ አየር መንገድ በኩል የሚመጡ ተጓዦች ንብረት መጥፋቱንስ ሰምተው ይሆን?” አዎ ባለፈው አመት
ብቻ፤ ከሰባት ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው ንብረቶች እና ሻንጣዎች ጠፍተዋል።
“ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም” ነው የሚባለው… እንዲህ እንዲህ እያልን፤ የዳኛውንም፣ የጉቦኛውንም ታሪክ
እያወራን ከቀጠልን ጊዜና ምሽቱ ላይበቃን ነው። ስለዚህ የሰማነውን በልቦናችን ያሳድርልን በማለት ልንለያቹህ ነው። ጊዜ
አግኝተን እንደገና ከተጨዋወትን ከአጼ ምኒልክ ቤተመንግስት ስለተሰረቁት የወርቅ ሹካ እና ማንኪያዎች ጭምር
እናወጋለን። እንደገና ከተገናኘን የአጼ ኃይለስላሴ የወርቅ ቀለበት ስርቆት እንጨዋወታለን። አረ ሌላም አለ። የአጼ ምኒልክን
ሽጉጥ ሰርቆ፤ መጠጥ ቤት ሲፎልል የነበረን አንድ የኢህአዴግ ኮሎኔል ኢትዮጵያ ውስጥ በሚታተመው ጋዜጣዬ ላይ
አጋልጠነው ነበር። በአገራችን የሚፈጸመው እውነት የማይመስለን የኢህአዴግ ሙስና ማብቂያ ያለው አይመስልም። በዚሁ
እንሰነባበት… መልካም አዲስ አመት።
የሙስና ነገር (ክፍል ሁለት) በዳዊት ከበደ ወየሳ ገጽ5
ምንጭ የኢትዮጵያ ሚዲያ መድረክ

የዓመቱ የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች ምርጥ ሰው – የሕይወት ገድል


በ1997 ዓ.ም ኢዴፓ /ቅንጅትን ወክሎ በተወለደበት ክ/ሀገር ፋርጣ ወረዳ ለተወካዮች ም/ቤት ተወዳድሯል:፡ በምርጫው ውጤት ቅንጅት ቢያሽንፍም ከፍተኛ አመራሩና አባላቱ በተለያዩ እስርቤቶች ሲታሰሩ እሱም አብሮ ቃሊቲ እስር ቤት ለሁለት ዓመታት ቆይቷል፡: በሁለት ዓመት ቆይታውም የብረት ግድግዳ በመሆን ፅናቱን አስመስክሯል:፡ ከእስር ቢለቀቅም ከፖለቲካው ወደ ኋላ አላፈገፈገም፡ አንድነት ፓርቲን በመቀላቀል የብሔራዊ ም/ቤትና የሥራ አሥፈፃሚ አባል በመሆን ለዋና ጸሐፊነት ተመርጦ ላንድ ዓመት በቆራጥነት አገልግሏል፡: ብቃቱን በማስመስከሩም በም/ሊቀመንበርነት የሕዝብ ግንኙነት ሐላፊ ሆኖ ተመርጦ በማገልገል ላይ እንዳለ፤ በተጨማሪም የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር እንዲሆን ብዙዎች እየቀሰቀሱ ባለበት ወቅት ነው ርምጃው ያልጣመው ገዥው ፓርቲ ከግንቦት 7 ጋር በማገናኘት የሽብርተኝነት ጥላሸት በመቀባት መስከረም 3 ቀን10 ሰዓት ላይ ከመንገድ የታጠቁ ኃይሎች ከመኪና አስወርደው ይዘውት በመሄድ አሁን እድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበት በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ይገኛል።



አንዱዓለም አራጌ ማነው? ለሚለው ጥያቄ ለአንባቢያንና ለውጥ ለማምጣት ለሚታገልለት የኢትዮጵያ ሕዝብ ከሕይወት ታሪኩ ትንሽ ጨለፍ አድርገን ለመፈንጠቅ እንሞክራለን።
የትውልድ አካባቢና የልጅነት ጊዜ አቶ አንዱዓለም አራጌ በጎንደር ክ/ሀገር በደብረታቦር አውራጃ በፋርጣ ወረዳ ጉና ተራራ ሥር ወይንም ግርጌ ክምር ድንጋይ ከተባለ ቦታ በ65 ዓ.ም ጥቅምት25 ቀን ተወለደ፡፡ የኢትዮጵያ አብዮት ሊፈነዳ ሁለት ዓመት ሲቀረው በምጥ ዋዜማ ማለት ነው፡፡ “ሰው አካባቢውን ይመስላል” እንደሚባለው አንዱዓለም አራጌ በክ/ሀገሩ ከራስ ዳሽን ተራራ ቀጥሎ በሁለተኛደረጃነት ከሚጠቀሰው ጉና ተራራ ስር በመወለዱ ለኢሕአዴግ እንደ ጉና ተራራ ኮርቶና ከብዶ ታይቶታል፡፡ እናም አስሮ በሽብርተኝነት በመወንጀል አሞቱን ያፈሰሰ መስሎታል፡፡ አንዱዓለም አራጌ ግን እንዲህ በቀላሉ የሚፈታ አይደለም፡፡ ለምንም ነገር የማይበገር፣ ችግር የማይፈታው፣ ለቆመለት ዓላማ ወደ ኋላ የማይል፣ ከሁሉም በላይ ቅጥፈትንና እብለትን አጥብቆ ይጠየፋል፡፡ባጭሩ ትክለ ሰውነቱ ወይንም nስብእናው በቁም ነገር የታነፀ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ለቆመለት ዓላማና ላመነበት ነገር ያላንዳች ይሉኝታና ፍርሃት ሽንጡን ገትሮ ይከራከራል፡፡
በዚህ አቋሙና ፅናቱም ነው ገና በለጋ እድሜው ሩጦ ሳይጠግብ፣ ሠርቶ ሣይደክም በተደጋጋሚ የእሥር ሰለባ ለመሆን የበቃው፡፡
አ ን ዱ ዓ ለ ም አራጌ አሥራ አንድ ዓመት እስከሚሞላው ድረስ ክምር ድንጋይ ከወላጆቹ ጋር ቆይቷል፡፡ አባቱ የቤተ ክህነት ሰው በመሆናቸው ልጃቸው በፅኑ የግብረገብ ሥነ ምግባርኮትኩተውና ገርተው ከማሣደጋቸውም በላይ የቤተክህነት ትምህርት እንዲማርላቸው በመሻት ካንድ ከታወቁ መርጌታ ልከውት በተመላላሽነት እየተማረ እንዳለ አዲስ አበባ የሚኖሩ አያቱ ክምርድንጋይ ይሄዳሉ፡፡ እሳቸውም የቤተክህነት ሰው ነበሩና ንቃቱን፣ ጨዋነቱን፣ ትህትናውንና አርቆ አስተዋይነቱን በዚያች አጭር ጊዜ ቆይታቸውአስተዋሉና “ይኸ ልጅ ዘመናዊ ትምህርት መማርአለበት” ብለው ወደ አዲስ አበባ ይዘውትይመጣሉ፡፡ሕይወት በአዲስ አበባአንዱዓለም አራጌ ካያቱ ጋር አዲስ አበባ ከመጣ በኋላ መስከረም መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በመግባት ከ1-8ኛክፍል ድረስ ሁለት ጊዜ ደብል ወይንም አጥፎ በማለፍ በ6 ዓመት ውስጥ ስምንተኛ ክፍልን አጠናቀቀ፡፡

ዘጠንኛና አሥርኛ ክፍልን የተማረው ኮከበ ጽባህ ሲሆን የደረጃ ተማሪ ስለነበር 11ኛና 12ኛ ክፍልን የተማረውና ከፍተኛ ውጤት አምጥቶ ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለመግባት የበቃው በሳንጅዮሴፍ ት/ቤት በመማር ነበር፡፡ አንዱዓለም አራጌ በከፍተኛ ውጤት አ.አ.ዩ በመግባት በታሪክ የመጀመሪያ ዲግሪውን አግኝቷል፡፡በዩኒቨርስቲ ቆይታውም በተለያዩ ክበባት በመግባት በኃላፊነትም ሆነ በአባልነት ካንድ ንቁ ተማሪየሚጠበቅበትን ግዴታ ተወጥቷል፡፡ በዩኒቨርስቲው ውስጥ በአራት ዓመት ቆይታው የት/ቤት ጓደኞቹ በሚያደርጋቸው ክርክሮችና በአቋሙ ፅናት እጅግ አድርገው ያደንቁት እንደነበር ዛሬ በቅርብየሚያውቁት ይናገራሉ፡፡
አንዱዓለም አራጌ ከሚታወቅባቸው ቁም ነገሮች መሀከል ባገራችን ገና የሰላማዊ ትግል ፅንስ ሐሳብ በቅጡ ባልታወቀበት ወቅት እሱ ሰለሰላማዊ ትግል ይሰብክ ነበር፡፡ ይህንንም ሲያደርግ የአንጋፋሰላማዊ ታጋዮችን አርማ በማንሳትና መርሃቸውን እንደ ምርኩዝ በመጠቀም ነው፡፡ ማርቲን ኪንግ፣ ማንዴላ፣ ማኅተመ ጋንዲን ታሪካቸውን በማጥናትና የሄዱበትን መንገድ በመከተል በዩኒቨርስቲቆይታው መርሃቸውን መርሁ በማድረግ የትግል ብቃቱን እንዳዳበረ በቅርብ የሚያውቁት በአጽንኦት ይናገራሉ፡፡ የአንዱዓለም አራጌ ልዩ ባህሪውና ተሰጥኦው ወይንም ትክለ ሰውነት ከላይ ለመጥቀስእንደሞከርነው በሰላማዊ ትግል ገና ከወጣትነቱ ዕድሜው ጀምሮ ቆርቦ እያለ ገዥው ፓርቲ “ሽብር አራማጅ” ብሎ በመወንጀል ጥላሸት ሲቀባው ማየትና መስማት ያለንበትን ዘመንና ሥርዓት ምንያህል አስጨናቂና አስከፊ እንደሆነ መገመቱ ከባድ አይሆንም፡፡ እያንዳንዳችንም ውለን ስለመግባታችን ዋስትና የለንም፡፡ ሁላችንም የሱ እጣ እንደሚጠብቀንና ጥላሸት እንደምንቀባም በርግጠኝነትመናገር እንችላለን፡፡
የሥራ ዓለምአንዱዓለም አራጌ ከአ.አ.ዩ ትምህርቱን ጨርሶ ከወጣ በኋላ በተለያዩ ድርጅቶች ውስጥ እየተቀጠረ ሠርቷል፡፡ ከነዚህ ውስጥ የዓለም ባንክና የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ባለሙያዎች መኅበርበግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
የፖለቲካ ሕይወቱ
አቶ አንዱዓለም አራጌ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቆይታው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የፖለቲካ ሀሁን ከመቁጠር ጀምሮ በማዳበር ብስለቱን ያስመስከረ ቢሆንም በድርጅትውስጥ ታቅፎ መታገል የጀመረው ግን በ1992 ዓ.ም የኢዴፓ መሥራች አባል በመሆን ነበር፡፡ በኢዴፓ ውስጥ በቆየባቸው ዓመታትም ከቋሚ ኮሚቴ አባልነት ጀምሮ ደረጃ በደረጃ አድጎ ም/ዋናጸሐፊ በመሆን በከፍተኛ ኃላፊነት ሠርቷል፡፡ በመሆኑም በ1997 ዓ.ም ኢዴፓ /ቅንጅትን ወክሎ በተወለደበት ክ/ሀገር ፋርጣ ወረዳለተወካዮች ም/ቤት ተወዳድሯል። በምርጫው ውጤት ቅንጅት ቢያሽንፍም ከፍተኛ አመራሩና አባላቱ በተለያዩ እስር ቤቶች ሲታሰሩ እሱም አብሮ ቃልቲ እስር ቤት ለሁለት ዓመታት ቆይቷል፡፡ በሁለት ዓመት ቆይታውም የብረትግድግዳ በመሆን ፅናቱን አስመስክሯል፡፡ ከእስር ቢለቀቅም ከፖለቲካው ወደ ኋላ አላፈገፈገም፡፡ አንድነት ፓርቲን በመቀላቀል የብሔራዊ ም/ቤትና የሥራ አሥፈፃሚ አባል በመሆን ለዋና ጸሐፊነት ተመርጦ ላንድ ዓመት በቆራጥነት አገልግሏል፡፡
ብቃቱን በማስመስከሩም በም/ሊቀመንበርነት የሕዝብ ግንኙነት ሐላፊ ሆኖ ተመርጦ በማገልገል ላይ እንዳለ ነው ርምጃው ያልጣመው ገዥው ፓርቲ ከግንቦት 7 ጋር በማገናኘት የሽብርተኝነት ጥላሸት በመቀባት መስከረም 3 ቀን 10 ሰዓት ላይ ከመንገድ የታጠቁ ኃይሎች ከመኪና አስወርደው ይዘውት የሄዱት፡፡


የቤተሰብ ሁኔታ
ወጣቱ ፖለቲካኛ አንዱዓለም አራጌ ባለትዳርና የሁለት ህፃናት አባት ነው፡፡ አንዱዓለም አራጌ ትዳር የመሠረተው ከእስር ከተፈታ በኋላ በ2000ዓ.ም ከዶ/ር ሰላም አስቻለው ጋር በሥርዓተ ተክሊልነው፡፡
አንዱ ዓለም ለኢትዮጵያ ሕዝብ ባደረገው የነፃነት ትግል ወህኒ ተወርውሮ ጠባብ ክፍል ውስጥ ቢቀመጥም በፍርድ ቤት የሚከተለውን ተናግሮ ነበር፦
“መንግሥት ለኢትዮጵያ ሕዝብ የአፋና ሥራ እየሠራ ነው፡፡ እኔም አንዱ የዚህ ሰለባ ነኝ፡፡ ፍ/ቤት ነፃ ሆኖ የራሱን ሂደት ያያል የሚል እምነት ስለሌለኝ እስከመጨረሻው የሞት ፍርድ ድረስ ቢደርስብኝም ከመቀበል ሌላ የምከራከረውም ሆነ የምናገረው ነገር የለኝም”
አንዱዓለም አራጌ መስከረም 4 ቀን2004ዓ.ም፡፡
የሕሊና እስረኛው አንዷለም አራጌ የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች የ2005 ዓ.ም ምርጡ ሰው ተብሎ ተመርጧል።
Short URL: http://www.zehabesha.com/amharic/?p=7230