Friday, July 5, 2013
መቼ ይሆን የኢትዮጵያ የጦር ሀይል ይህዝብ አጋር የሚሆነው?
የግብፅ ህዝብ መብቱን እና ነፃነቱን ለማስጠበቅ በአንድነት በመቆም በሁለት አመት ውስጥ ሁለት መንግስት ለመግልበጥ
ቆራጥነቱን በማሳየት በአደባባይ በህብረት እየገለፀ ይታያል በተለይም በታህሪር አደባባይ ቀደመው አምባገነኑን ሁሴን ሙባረክ
የውረድልን በማለት ለረጅም ወራት እየዋሉ እዛውእያደሩ ህዝባዊ አመፃቸው ለድል አብቅቷቸዋል ይሁሉ ሲሆን ያለመሳዋትነት
ደል የለምና ህያው ህይወታቸውን የከፈሉ በርካታ ግብፃዊያን ናቸው አሁን ደግሞ በእስላማዊ ብራዘርሁድ ደጋፊ የሚመራአው
የሙርሲ መንግስት ለህዝቡ ቃል የገባውን በአግባቡ ባለመፈፀሙ ለህዝብ ተቃውሞ ተዳርጓል በዚህም የተነሳ ኩሁሉም በላይ
የሚያስደስተው የግብፅ ህዝብን ሊያኮሯው ይችለው አብይ ጉዳይ ከህዝብ አብራክ የተገኘው የጦር ሀይሉ ህዝባዊ ወገናዊነቱን
በማሳየቱነው።
ምናልባትም ወንድሙ ወይም እህቱ በአደባባይ ወጥተው ሲቃወሙ ወታደሩ እንዴት ከቤተስቡ አካል ላይ ቃታ ይስባል፣
ይህን ለማለት ያስቻለኝ ከአገራችን ወቅታዊ ሁኔታ ጋራ ለማገናኘት ፈልጌ ነው ይህዉም በሁላችንም አምሮውስጥ ትልቅ ጠባሳ
ጥሎ ያለፈውን የምርጫ 97 ትውስታ በአካለም ተግኝቼ ሁኔታውን ስላይው ነው ትዝታዬን ቀስቅሶት ነው የትጨበረበረውን
የተሰረቀውን ድምጻችንን ይመለስልን ብለን በአደባባይ ለተቃውሞ የወጣነውን ስላማዊ ህዝብ በወርሃ ጥቅምት 22,1989
ከአንድ ጎጥና ብሔር የተወጣጣው በፋሽስቱ መለስ የሚመራው የአጋዚን ልዩ ጦር በንፁሀን ኢትዮጵያኖች ላይ የፈፀመው
ኢሰባዊ ግድያ ከሁላችንም ህሊና መቼም ቢሆን አይረሳነም። ከአንድ ብሄር የወጣው የአጋዚን ወታደር የኢትዮጵያ ደም
ሰለሌው ነው እንደግብፅ ወታደር ለህዝብ የቆም ስላልሆነ ንው ለአንባገነኖቻ።
እኛ ኢትዮጵያኖች ከግብፅ ህዝብ ልንማር የምንችለው ቁምነገሮች አሉ ለውጥ ሊመጣ የሚቺለው በትግል መሆኑን ሁላችንም
ጠንቅቀን እናውቃለን ከቀደምት አባቶቻችን እና እናቶቻችን ታሪክ የሚያስተምሩን አንዳንድ ጥቃቅን ችግሮች እንኳን
ቢኖራቸው በአገርህልውናላይ በአንድነት ነው የሚቆሙት ከኢትዮጵያ አልፈው ለጥቁር ህዝቦች ሁሉ ደማቅ ታሪክ ስርተው
ያለፉት የህም ትውልድ የአባቶቹን እና የ እናቶቹን አደራ በጎሳወይም በብሄር ሳይከፋፈል በመከባበርና እና በመቻቻል
ልዩነታችንን ወደ ጎን ትተን ለአንዲት ከማነም አገር በፊት ቀደምት ታሪክ ላላት ወድ ሀገራችን ለኢትዮጵያችን በጋራና በህብረት
እንደ ግብፅ ህዝቦች መቆም አለብን።
የመከላከያም ተቋምም ይሁን የፖሊስ ሰራዊት እንዲሁም የህዝብ ደንነት ከህዝብ አካል ስለተገኛ ህዝባዊ አጋርነቱን
ማሳየት አለበት እድሜልኩን ለአባገነኖች ለዘረኞች ማገልገል የለበትም ከግብፅ ወታደር ብዙ ቁም ነገርቹን መማር አለብት
በቃ በሎ ከህዝብ ጎን መቆም ይኖርበታል።
ኢትዮጵያ በቆራጥ ልጆቿ ለዘላለም ትኑር!!!!!!
ዳዊት ወንድሙ!!!!!
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment