Thursday, May 29, 2014

ግንቦት 20 ስናስበው!!!!!

  ዳዊት ወንድሙ
 በአብዛኞቻችን ኢትዮጵያን ዘንድ ላንረሳው ልንዘነጋው የማይቻሉ በርካታ ክስተቶች አልፈዋል ወያኔ እስልጣን ዙፋን ላይ
ከተቀመጡበት ግዜ ጀምሮ ህዝብን በእስራት፣ለስደት፣ለረሀብ ከዛም አልፎ በመግደል በማሰቃየት በብሄር እና በጎሳ፣በመንደር
በማደራጀት በመከፋፈል ሌሎችም ያልገለፅኳቸው በርካታ መጠነ ሰፊ ችግሮችን አይተናል ።
   ሁሌም ከህሊናችን ከአእምሮችን የማንረሳው ውድ ወንድማችን በደቡብ ክልል ዳውሮ ዞን የኔሰው ገብሬ  በሙያው መምህር የነበር እሱን
የመሰሉ ብዙ ኢትዮጵያን በእውቀት የሚያፈራ የነበር የህዝቦችን ስቃይ ፍትህና ህግ በተግባር በማይታይበት በማይወሰንበት
ሀገር ከመኖር ይልቅ እራሴን በእሳት አቃጥዬ በሞት ይሻለኛል ብሎ እራሱን ለፍትህ ለነፃነት ብሎ የሰዋው እኔ እራሴን
በመሰዋት ያቀጣጠልኩትን ትገል እዳር እና እውጤት አድርሱ ብሎ  ለኛትቶ አልፏል።
   እንደው እንደምሳሌ አድርጌ የኔሰው ገብሬን ጠቀስኩ እንጂ በወያኔ ስርዓት ስንቱን በዝርዝር ገልፆ መጨረስ አይቻልም
ከሁሉም በላይ ደግሞ ልንረሳው የማንችለው በወያኔ ኣጋዚን አልሞ ተኳሽ በምርጫ 1997 በሰላማዊ መንገድ የተሰረቀው
ድምፃችን ይመለስ በማለት በ አዲስ አበባ በተለያዩ ቦታዎች የተቃውሞ ድምፁን ያስማ የነበረውን ህዝብ ምንም እራሱን የሚከላከልበት
እንኳን ምንም አይነት መሳሪያ የሌለው ሰላማዊና ፍት ህ ፈላጊ ባደባባይ ድምጹን ለማሰማት የወጣውን ህዝብ በ አጠፋው
በምላሹ የጥይት እሩምታ ፍጹም በራስ ወገን ሊደርግ አይደለም ሊታስብ የማይገባውን ፋሽስታዊ ጭካኔ በገዛወገናቸው ላይ
ፈፅመዋል በዚህ ምክንያት መቼም ማንረሳቸው ዘውትር ምንዘክራቸው 200 ወግኖቻችን አጥተናል በሁላችን ልብ ዘወትር
የሚያስለቅሰን እንደ አብሮ አደግ ጓዶኞቹ በሰላም ወደትምህርት ቤት ደብተሩን እንደያዘ እናቱን ስሞ ልጄ በሰላም ተመለስ
በላ መርቃ ልጄ ተምሮ አድጎ እራሱን እኔንም ከዛም አልፎ አገሩን ወገኑን የጠቅማል ብላ እናት ስለልጆ የወደፊት ብሩ ተስፋ
እያለመች እና እያሰበች ሽኘችው ይህ ሁሉ ሳይሆን ቀርቶ በወያኔ ኣጋዚን እናት እንዳሰበችው ሳይሆን በነሱ ጥይት ህፃን ነብዩ
ደብተሩን እንደያዘ ተዘርሮ ከመንገድ ባጭሩ ቀርቶል መግደላቸው ሳያንሳቸው የ 12(14) ዓመት ህፃን ባንክ ሊዘርፍ ሲል ነው
የተገደለው በማለት የአለምን ህዝብ  ለሚዲያ ለማሳሳት ሞክርዋል እንኳን ባንክ ሊዘርፍ ቀርቶ የባንክ ቤትን በር መግቢያ
የማያቅ ልጅ እንዲሁ የትምህርት ደፈተሩን እንደያዘ ከአስፋልት ተዘርሮ ቀርቶል።
   እህታችን ሽብሬንም አንረሳትም አረስንቱን እንዘርዝር ቤት ይቁጠረው አንጂ።
       ግንቦት 20 ስናስበው ምናልባት የትወሰኑ ክፍሎች፣ቡድኖች፣ግለሰቦች የነፃነት ቀናችን ብለው ሊያስቡ ወይም ሊደሰቱ
ይችሉ ይሆናል እነሱም እንደሚሉት ልማታዊ መንግስት 11% ኢኮነሚያችን አደገ የህዝባችን የኑሮ ሁኔታ ተሻሸሎል ማይቀበጣጥሮት የለም እውነተውና ሀቁ እሱ አይደልም ከ አንደነት የልቅ በጎጥ መነፅር የምንተያይበት በተለያዩ አግሮች
በመሰደድ መከራና ስቃይ በተለይም በየ አረብ ሀገር የእህቶቻችን የወንድሞቻችን መከራና ስቃይ ሞት የምንሰማበት የምናይበት እንዲሁም በታሪካችን ተስምቶ ያማይታውቅ ብሔራዊ ውርደታችን ያየንበት ነው።
 
አባቶቻችን እናቶቻችን ለአገራቸውና ለባንዲራቸው ክብር ብለው የሞቱለትን ታሪክ ዛሬ እረስተን በጠላትና በወራሪዎች
አንገዛም አንበርከክም ብለው ለመላው የጥቁር ህዝብ ነፃነትን ጎሕ ያጎናፀፉትን በደማቸው በአጥንታቸው ደማቅ ታሪክ የሰሩትን
ትተን መቼም የማይፋቅና የማይረሳ ከትውልድ ወደ ተውልድ የሚተላለፈውን የ አደዋ ደልን እና ገድል።
  እስከ አፍጢሙ ታጥቆ የመጣውን የጣሊያን ጦር በቂ የመከላከያ ዘመናዊ መሳሪያ ሳይኖራቸው በፍቅር እና በአንድ ልብ
በመሆን አሳፍረው የመለሱበት ታሪክ እና ባንዲራ(ሰንደቅአላማ)ዛሬ ወያኔ የስልጣን እድሜውን ለማራዘም ሰሞኑን ደግሞ
እንደሚሉን እስከ 40 ዓመት የመግዛት የቁም ቅዠት ሀሳብ እንዳላቸው እንሰማለን ለዚህም ነው ክልል በለው ከለለውን
በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያን ደም የፈሰሰበትን ብሄራዊ ባንዲራ እያለን እርስ በርሳችን እንድንተላለቅ
ክልል እያለ የተለያዩ የትግል አርማ ይሁን የመለያ ምልከት ወይም ማስታውቂያ እየተከሉ ልንወጣው የማንችለው ብጥብጥ ውስጥ ለመክተት ከቅደመ አያቱ ጣሊያን በተማረው ባንዳ የባንዳ ልጅ እነሱ ቀደመው ሲመኙት የነበረውን ኢትዮጵያኖችን
የመከፋፈል እና በዘር የመለያየት እቅድ ተሸንፈው የተዋረዱበትን ታሪክ ዛሬ ሊያስፈፅም ቀና ደፋ ይላል ይህን መሰሪ ሴራቸውን
መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጠንቅቆ ተርድቶታል ምክንያቱም በሀይማኖት ለማበጣበጥ ኢስላማዊ ሃራካት አኬልዳማ የሚል ደራማ ዎችን አሳይን ሙስሊሙ ማህበረስብ በረጅም ግዜ ታሪኩ ከክርስቲያን ወገኖቻቸው በተለያዩ ማሀበራዊ ህይወቶች የተሳሰሩናቸው።
መቼም ቢሆን እንደማይሳካ ተርዱት የበለጠ እንዲተሳሰቡ እንዲፈቃቀሩ ነው ሁለቱንም ያረጋቸው ምክንያቱም ዋናው ጠላታቸው ማንእንደሆነ ጠንቅቀው ሰለሚያውቁ ።
 አሁን ደግሞ ትልቁን የኢትዮጵያን ስርና ግንድ የሆነውን  የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪውን ስፊውን ህዝብ ከወገኑ ከአማርኛ
ቋንቋ ተናጋሪ ኢትዮጵያዊ ወንድሙ ጋራ በማጋጨት የመጨረሻውን ካርድ እየሳበነው ወያኔ እንደሚያስበው ኢትዮጵያ እንደ
ሩዋንዳ ህዝብ ሁቱና ቱሲ ተባብለን አንጨፋጨፍም የተለያዩ ብሄርና ብሔርስቦች በመከባብር እና በመፈቃቀድ በመስማማት
የምንኖርበትን አገር ነው መገንባት የምንፈልገው ብዙ ግዜ እንደሚባለው ልዩነታችን ወበታችን ነው ባህላችን ደግሞ መገለጫችን ነው በልዩነታችን ውስጥ መከባበር መተሳሰብ ካለ ሁሉንም ችግራችን በመነጋገር በሰለጠነ በዘመናዊ መንገድ
እንፈታዋለን ይኀውም በቅን ልቦና በማሰብና በንፁ ልብ በመነጋገር።
ኢትዮጵያ ለዘላለም በክብር ትኑር!!!

Tuesday, May 27, 2014

40 – 23 የኢህአዴግ የጎሳና የመጥበብ ሰረገላ ሐዲዱ ላይ ነውን? “ኢትዮጵያን በጎሳ ሳጥን ቆልፎ የሚጓዘው ህወሃትና ድግሱ”

ህወሃት በነጻ አውጪ ስም ታግሎ ኢትዮጵያን መግዛት የጀመረበትን 23ኛ ዓመት በዓሉን እያከበረ ነው። ወዳጆቹና መሪዎቹ ባስቀመጡት እቅድ መሰረት ኢትዮጵያን “በመተካካትና በተሃድሶ” ስም ራሱን እያገላበጠ ለመግዛት የቆረጠው ጊዜ በትንሹ 40 ዓመታት እንደሆነ ይታወቃል። አሁን ባለው የሰረገላው ጉዞ ኢህአዴግ ከ40 – 23 ከመቀነሱ ውጪ አሰበበት ስለመድረሱ መገመት የሚያስችል ምልክት የለም። እንደውም ስጋት እንጂ።
ሲጀመር “የገበሬ ተሟጋች” ነኝ በማለት ራሱን የአርሶ አደሩ ወኪል አድርጎ የተነሳው ህወሃት፣ ኢህአዴግ ሆኖ አገር መግዛት ሲጀምር ያስቀደመው የብሄር ብሄረሰቦችን የመብት ጥያቄ እንደ ውዳሴ ጸሎት በመደጋገም ነበር። በዚሁ በጎሳ ላይ ተመስርቶ በቋንቋ የተቆለፈው የአገዛዝ ስልት ሲጀመር ማስጠንቀቂያ የሰጡ፣ ለመታገል የሞከሩ፣ የታገሉ፣ ያስተባበሩ፣ ያደራጁ የህወሃት የ40 ዓመት ጉዞ ጸር ተደርገው ተወሰዱ። ስለ ኢትዮጵያ ጥቅምና ኢትዮጵያዊነት ያሳሰቡ ጠላት ተደርገው ተፈረጁ። በስውር በአፈና፣ በግልጽ ህግ እየተጠቀሰባቸው ከጫወታና ከመኖር ተገለሉ። ብዙዎች እንደሚሉት “የጉዳቱን መጠን ህወሃትና የተጎዱት ቤተሰቦች ይቁጠሩት”!
ግንቦት ሃያ “የህዝብ የድል ክቡር ቀን ነው” በሚሉና “የህዝብና የአገር ውድቀት የታወጀበት የክፉ ቀኖች ሁሉ ድምር” ሲሉ በሚሰይሙት መካከል ሰፊ መከራከሪያ አለ። የመንገድ ግንባታ፣ የህንጻ ግንባታ፣ የኮሌጅና የትምህርት ቤቶች ግንባታ፣ የግድቦች ግንባታና የአባይ ወንዝ ልማት ወዘተ ጉዳዮች የግንቦት 20 ጣፋጭ ፍሬዎች ስለመሆናቸው “የቀኑ ወዳጆች” ይከራከራሉ። የቀኑ “ባሮችም” ይህንኑ ውዳሴ በማቀንቀን ታማኝነታቸውን ይገልጻሉ። በጥቅም የተደለሉ ሎሌዎች ስለሆኑ ይህንን ድል ለማስጠበቅ በግልጽና በህቡዕ አድርጉ የተባሉትን ያደርጋሉ።
በተጠቀሱት የልማት ስራዎች ላይ ተቃውሞ የማያነሱ የቀኑ “ሰለባዎች” ሰላምና መረጋጋት እንዳለ የሚሰብክ አስተዳደር ልማትን ከመስራት ሌላ ተግባር እንደሌለው ይገልጻሉ። አያይዘውም ጣሊያንም በ5 ዓመት ጊዜ ውስጥ በርካታ መንገድና ድልድዮችን መገንባቱን ያጣቅሳሉ። ከሁሉም በላይ ግን ኢህአዴግ በሚገዛት አገርና ሕዝብ ስም የተበደረውን የገንዘብ መጠን “ከተዘረፈው ውጪ” በማለት ከፍተኛ እንደሆነ ይናገራሉ። በሌላ በኩል ደግሞ “መንገድ መስራትና ህንጻ ማቆም የመብት ጥያቄን በጥይት ለመመለስና በደም ለመጨማለቅ ዋስትና ሊሆን አይችልም” በማለት ስርዓቱን አጥብቀው ይኮንኑታል።
በሌላም ወገን የተሰሩትን ህንጻዎች፣ የንግድ ተቋማት፣ የገንዘብ ተቋማት፣ ከፍተኛ ኢንቨስትመንቶች በማንሳት “የግንቦት 20 ፍሬዎች” ሲሉ ይሰይሟቸዋል። ሲያብራሩም “የነዚህ ሁሉ ሃብቶች መነሻና ባለቤቶች ህወሃትና ህወሃት ዙሪያ የሚሽከረከሩ ባለሟሎች ናቸው። የህዝብ አይደሉም። ሕዝብም አያምንባቸውም” በማለት ጥርስ ይነክሱባቸዋል። በዝርፊያ ሃብት የሚያግበሰብሰውን ኤፈርት ኢትዮጵያን “ንብረቶችሽን ባደራ ላስቀምጥ” የሚል እስከሚመስል የንግድ ኢምፓየሩን ማስፋቱን አብዝተው ይኮንናሉ።
የግንቦት 20፣ የቀኑ ወዳጆች ኤፈርት ላይ የሚቀርበውን ጥያቄ አያስተባብሉትም። ይልቁኑም ድርጅቱ ጓዳና ካዝናው የተለጎመ መሆኑ ያብከነክናቸዋል። አለው የሚባለው ሃብት ሁሉ የትኛው ቋት እንደሚቀበር ስለማይረዱ “የተሸውደናል” ስሜት አላቸው። ለዚህም ይመስላል የህወሃት ወዳጆች “ኤፈርትን ያየህ ወዲህ በለኝ” ሲሉ የሚደመጡት። በግልጽ አነጋገር ኤፈርት ፊት ለፊት ከሚያሳየው ሃብቱ ይልቅ፣ የማይታው ጉዱ ስለሚያመዝን በህወሃት ወዳጆች ሳይቀር አልሞ ተኳሽ (ስናይፐር) የተደቀነበት ነው።
አፈናው፣ ግድያው፣ እስሩ፣ ዝርፊያው፣ ከላይ ከተገለጸው በተቃራኒ አርሶ አደሩ ላይ የሚፈጸመው የመሬት ቅሚያ ሌላው የግንቦት 20 የጨነገፈ ፍሬ ተደርጎ ይወሰዳል የሚሉ አሉ። በተለይም ራሱ ህወሃት ሁሉንም በራሱ ደረጃ ለማሳነስ ሲል ያዋቀረው የቋንቋና ጎሳን ተገን ያደረገ የአገዛዝ ስልት ዛሬ ግንቦት 20ን እድሜውን ወደ ማሳጠር እያደረሱት ነው ሲሉ ያክላሉ። በዚህ አስተሳሰብ ላይ የሚተቹ ሰሞኑን አጠንክረው እንደገለጸት “የግንቦት 20 ወዳጆች ኢትዮጵያዊነት ከውስጣቸው እንዲወልቅ ተደርጎ በተዘጋጀላቸው የትምህርት እቅድ፣ ሥርዓተ ትምህርት፣ … መሰረት ወደ ጎሳ እየጠበቡ የግንቦት 20 ድል ‘ሰረገላው’ መድረስ የፈለገበት ቦታ ሳደርስ ሃዲዱን ሊያወላልቀው ይችላል”፡፡
40 – 23 ዓመት ላይ ያለው ኢህአዴግ ህወሃትን እያጀበና እየሞሸረ ወደ “መንገሻው” ለማድረስ የተሰሩበት የጎሳ ኬሚስትሪ እንደሚከለክላቸው የሚናገሩ ክፍሎች “የግንቦት 20 ድል እየተከበረ 40 ዓመት መዝለቅ ምናልባትም ከተረትም የወረደ ሟርት ነው” ባይ ናቸው። ህወሃት ለጊዜው ብሎ የዘራው የበቀል ዘርና በጎሳ ሳጥን ውስጥ ከቶ ያሳደጋቸው ወዳጆቹና በጊዜ የታሰረ ቦንብ እንደሚሆኑበት ምልክቶቹ ከበቂ በላይ እንደሆኑም ይናገራሉ። እነዚህ ወገኖች እንደሚሉት “ህወሃትን የሚበሉት ራሱ ያመረታቸው ፈንጂዎቹ ናቸው” በመሆኑም የዘንድሮው ግንቦት 20 አንጸባራቂ ጥቅስ “ለመጥበብ ብሎ ህወሃት የወጠነው የጎሳ መዋቅርና አስተምህሮት የህወሃት ፉርጎ የሚሄድበትን ሃዲድ እያወላለቀው ነው” የሚለው ይሆናል – “ጉድጓድ የሚምስ ራሱ ይወቅድበታልና”፡፡
ምንጭ www.goolgule.com

Wednesday, May 21, 2014

የአሜሪካ የሸፍጥ ዲፕሎማሲ “አስቂኝ የመድረክ ትወና” – ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

የ አሜሪካ የ ሸፍጥ ዲፕሎማሲ “አስቂኝ የ መድረክ ትወና”


ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

የኦባማ አስተዳደር የሰብአዊ መብት አያያዝ ፖሊሲ “አስቂኝ የመድረክ ትወና ነውን”?

የዩናይትድ ስቴትስ የመንግስት መምሪያ ጸሐፊ የሆኑት ጆን ኬሪ ባለፈው ሳምንት የሶሪያን ፕሬዚዳንት ባሽር አላሳድን “አሸባሪ” ወንጀለኛ ናቸው
ብለው ከፈረጁ በኋላ የአላሳድ የቀጣዩ ዓመት የምርጫ ዕቅድም “አስቂኝ የመድረክ ትወና” ነው ብለው ተችተው ነበር፡፡ ኬሪ በመቀጠልም እንዲህ
በማለት ሀሳባቸውን አጠናክረው ነበር፣ “አሳድ ከአሸባሪ ኃይሎች ጋር ህብረትን ፈጥረዋል፣ አሸባሪዎችንም እያቀረቡ እና እየረዱ ነው፣ እናም
በእራሳቸው ህዝብ ላይ አሸባሪነትን በመፈጸም ዕኩይ ተግባራት ላይ ተዘፍቀው ይገኛሉ፡፡“ እንዲሁም ኬሪ የሚከተለውን ነገር አጽንኦ በመስጠት
ተናግረዋል፣ “የአሳድ ፕሬዚዳንታዊ የምርጫ ዕቅዶች ለታዕይታ የተዘጋጁ አስቂኝ የመድረክ ትወናዎች ናቸው፡፡ በዚህ መልኩ ለመተግበር
የሚደረጉ ምርጫዎችም በህዝብ ላይ የሚካሄዱ ዘለፋዎች ናቸው፣ እንደዚህ ዓይነቶቹ ዕኩይ የምርጫ ዕቅዶች በሶሪያ እና በዓለም ህዝቦች
ዴሞክራሲ ላይ የሚቃጡ ሸፍጦች ናቸው፣“ ብለው ነበር፡፡

አሳድ በ21ኛው ክፍለ ዘመን የሶሪያን ህዝብ አሳር ፍዳውን በማሳየት ላይ የሚገኙ እና በዘመኑ የሰውን ልጅ ከሚያሰቃዩ አምስት የመጀመሪያዎቹ
ወሮበላ ወንጀለኞች ምድብ ውስጥ እንደሚካተቱ ምንም ዓይነት ጥርጣሬ የለኝም፡፡ እ.ኤ.አ ሜይ 2007 በተደረገው ምርጫ ባሽር 97.6 በመቶ
ድምጽ በማግኘት ለሰባት ዓመታት ለሁለተኛ ጊዜ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ፡፡ በዚያን ጊዜ የአሜሪካን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል
አቀባይ የነበሩት ማኮርማክ እንዲህ የሚል መልዕክት አስተላልፈው ነበር፣ “በሶሪያ ያለው ገዥ አካል ዕጩ ተወዳዳሪዎች እንደልብ በህዝቡ ውስጥ
ተንቀሳቅሰው ሀሳባቸውን በመግለጽ መመረጥ እንዳይችሉ ለማድረግ በህዝቡ ላይ እየፈጸመ ባለው ማስፈራራት እና በሰላማዊ የፖለቲካ
ተቀናቃኞቻቸው ላይ የሚያራምዱት ግፍ የተሞላበት ጭቆና ላይ የቀረበው ዘገባ ዩናይትድ ስቴትስን ያሳስባታል፡፡ የሶሪያ ህዝብ ተማዕኒነት ያለው
ግልጽ እና በህዝቡ ሙሉ ተሳትፎ ላይ የተመሰረተ ፖለቲካዊ ድባብን በመፍጠር ፍትሀዊ ምርጫ የማድረግ እና የሚወክሉትን ዕጩዎች መምረጥ
እንዳይችል ባሽር አላሳድ መብቱን ቀምተውታል“ በማለት ሀሳባቸውን አጠቃለዋል፡፡ ስለአሳድ “አስቂኝ የምርጫዎች ትወና መድረክ” ማውሳት
አዲስ ነገር አይደለም፡፡

እ.ኤ.አ ማርች 2011 የቀድሞ የየአሜሪካን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ሂላሪ ክሊንተን ደም ለተጠሙት ባሽር አላሳድ (በሺዎች የሚቆጠሩ
የሶሪያ ሰላማዊ ህዝቦችን ካለፈው ኦክቶበር ጀምሮ ቢያንስ 14 ጊዜ በኬሚካላዊ መሳሪያ ለጨፈጨፉት) መልካም ስብዕና ጥብቅና ቆመው
ተስተውለዋል፡፡ እንዲህ በማለትም ሀሳባቸውን አጠናክረው ነበር፣ “በአሁኑ ጊዜ በሶሪያ ለየት ያለ መሪ አለ፡፡ ባለፉት ጥቂት ወራት ወደ ሶሪያ
በመሄድ ጉብኝት አድርገው የተመለሱት በርካታ የሁለቱም ፓርቲዎች (ዴሞክራቶች እና ሬፐብሊካኖች) የኮንግረስ አባላት አላሳድ የለውጥ
አራማጅ ሀዋርያ በመሆናቸው ላይ እምነት እንዳላቸው ገልጸው ነበር “ ብለዋል፡፡ ይህ ሁኔታ በአንድ ጊዜ ተቀይሮ ከሶስት ዓመታት ባነሰ ጊዜ ውስጥ
አሳድ “የለውጥ አራማጅ ሀዋርያ” መሆናቸው ቀርቶ ወደለየለት “አሸባሪነት” እና የዘር ማጥፋት ወንጀል ተዋናይነት ተቀይረው ተገኙ፡፡ እንደ ሂላሪ
አባባል የት ይደርስ የተባለ ወይፈን አጎንብሶ ሲጠባ ተገኘ መሆኑ ነውን?

በእኔ የአዕምሮ ዕይታ ኬሪ በአላሳድ ላይ እያሰሟቸው ያሏቸው የውግዘት ቃላት ተመሳሳይ ጥያቄዎችን እንዳነሳ ያስገድዱኛል፡፡ የኦባማ አስተዳደር
የሰብአዊ መብት አያያዝ ፖሊሲ “ለአስቂኝ የመድረክ ትወና” የዲፕሎማሲ አካሄድ ነው ብሎ በእርግጠኝነት መናገር ይቻላልን? በዓለም ላይ
“ሸፍጥ” ለመስራት የተቀነባበረ ተንኮል ነውን? ይህ ሁኔታ ሆን ተብሎ ህዝብን እና የሰብአዊ መብት ጥበቃን ለመዘለፍ እና ለማዋረድ የሚደረግ
ደባ ነውን? የኦባማ አስተዳደር የሰብአዊ መብት አያያዝ ዲፕሎማሲን በአስመሳይነት ወይም ደግሞ “በዲፕሎክራሲ” (የዓለም አቀፍ የሰብአዊ
መብት አያያዝ ፖሊሲውን አስመሳይነት ለመግለጽ የተጠቀምኩበት ትርጉም ነው) ሰበብ ተጨባጭነት በሌለው መልኩ ለይስሙላ እየተጠቀመበት
ነውን? ማንም ቢሆን አመልካች ጣቱን በሌሎች ሰዎች ላይ ሲቀስር ሶስቱ ጣቶቹ ተቀስረው ወደ እራሱ እንደሚያመለክቱ በጥንቃቄ መገንዘብ
ይኖርበታል፡፡

እ.ኤ.አ ኤፕሪል 2013 የመንግስት መምሪያ ቃል አቀባይ የነበሩት ኬሪ ኒኮላስ ማዱሮ በቤንዙዌላ በምርጫ አሸንፈው የአገሪቱ ፕሬዚዳንት
መሆናቸውን እውቅና እንደማይሰጡ እና እንደማይቀበሉ አሳወቁ፡፡ ማዱሮ ያንን ምርጫ በጣም በጠበበ ሁኔታ 50.66 በመቶ ድምጽ በማግኘት
አሸንፈው ነበር፡፡ የተቃዋሚው ፓርቲ መሪ የነበሩት ሄንሪክ ካፕሪልስ ስለምርጫው ነጻ እና ፍትሀዊ አለመሆን ጉዳይ አስመልክቶ ዝርዝር ታሪኩን
ከተናገሩ በኋላ ኬሪም የእርሳቸውን ሀሳብ በመቀበል የሀሳባቸው ተጋሪ በመሆን እንዲህ ብለው ነበር፣ “ስለምርጫው ዝርዝር ማብራሪያ መሰጠት
የነበረበት መሆኑን እናምናለን…በግልጽ ለመናገር ከፍተኛ የሆኑ የምርጫ ግድፈቶች ተከስተው ከሆነ ስለሚመሰረተው የማዱሮ መንግስት ቅቡልነት
በርካታ ጠንካራ ጥያቄዎችን የምናነሳ ይሆናል“ ብለው ነበር፡፡ በተጨማሪም የኋይት ሀውስ ቤተ መንግስት ቃል አቀባይ የሆኑት ጃይ ካርኔይ
በተመሳሳይ መልኩ ስለምርጫው አፈጻጸም ዝርዝር ማብራሪያ መቅረብ እንዳለበት በመግለጽ መግለጫ አወጡ፡፡
 ዚምባብዌ እ.ኤ.አ ኦገስት 2013 ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ባካሄደችበት ወቅት ኬሪ እንዲህ ብለው ነበር፣ “በግልጥ በማያሳስት መልክ እንየው፣ በአገር
ውስጥ እና በአህጉራዊ የምርጫ ታዛቢዎች በቀረበው ዘገባ መሰረት በርካታ ግድፈቶች የተንጸባረቁበት ምርጫ መሆኑን የገለጹ ቢሆንም ዩናይትድ
ስቴትስ በዛሬው ዕለት ይፋ የሆነው የምርጫ ውጤት የዚምባብዌን ህዝብ ፍላጎት የሚያሟላ ነው የሚል እምነት የላትም…የቀረበው ማስረጃ
እንደሚያረጋግጠው የዛሬው የምርጫ ውጤት የረቀቀ እና ጥልቅ የሆነ የምርጫ ማጭበርበር ሂደት ማክተሙን ያረጋገጠ ነው “ ብለው ነበር፡፡ ያም
ሆነ ይህ ሙጋቤ በዚያን ጊዜ በተካሄደው ምርጫ 61 በመቶ ድምጽ በማግኘት ነገር ያሸነፉት፡፡

እ.ኤ.አ ሜይ 2010 በኢትዮጵያ በተካሄደው ፓርላሜንታዊ ምርጫ በቅርቡ ያረፉት አቶ መለስ ዜናዊ 99.6 በመቶ ድምጽ በማግኘት አሸንፊያለሁ
ብለው ሲያውጁ ዩናይትድ ስቴትስ ሁኔታው “የሚያሳስበን እና በጉዳዩም ላይ ያለንን ጥልቅ ስጋት እንገልጻለን” በማለት የተለመዱ እና አሰልች
የግዴታ አይነት የቃላት መግለጫዎችን ከመስጠት በዘለለ ስለምርጫ ዘረፋው ህገወጥነት በተጨባጭ በመሬት ላይ የሚታይ ያደረጉት አንድም
ድርጊት አልነበረም፡፡ የኋይት ሀውስ ብሄራዊ ደህንነት ቃል አቀባይ የሆኑት ሚክ ሀመር እንዲህ ብለው ነበር፣ “ዓለም አቀፍ የምርጫ ታዛቢዎች
ቡድን የምርጫ ሂደቱን ከታዘበ በኋላ ባወጣው መግለጫ መሰረት ምርጫው ዓለም አቀፍ የምርጫ መስፈርትን አያሟላም፣ ስለሆነም በዚህ ጉዳይ
ላይ ያለንን ስጋት እንገልጻለን፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ባለስልጣኖች በምርጫው ዕለት ከአገሪቱ ርዕሰ መዲና ወጣ በማለት በየአቅጣጫው
ተዘዋውረው የምርጫውን ሂደት ለመታዘብ ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት ያልተሰጠው በመሆኑ የተሰማንን ቅሬታ እንገልጻለን፡፡ ነጻ የሆነ የምርጫ
ታዛቢ ያለማግኘት እና ባሉት የነጻ ሜዲያ ተወካይ ታዛቢዎች ላይ የሚደረገው የማሸማቀቅ ስራ ለችግሩ መፍትሄ ከመስጠት ይልቅ በጣም
የተወሳሰበ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ ከምርጫው ዕለት በፊት እንኳ ነጻ እና ፍትሀዊ የምርጫ ከባቢ አልነበረም… ለነገሩ እ.ኤ.አ በ2010 በኢትዮጵያ
የተካሄደው “ፓርላሜንታዊ ምርጫ” አስቂኝ የምርጫ ትወና መድረክ ነበርን? የዚህ ዓይነት መሰሪ እና ዕኩይ ተግባራት በኢትዮጵያ ህዝብ እና
በዓለም ላይ የሚካሄድ ዘለፋ እና በዴሞክራሲ ላይ የሚደረግ ሸፍጥ ነውን?“

በዝንጀሮ ቆንጆዎች መካከል የቀንጅና ውድድር አይካሄድም ሆኖም ግን ዩናይትድ ስቴትስ ባሽር አላሳድ 97.6 በመቶ ድምጽ በማምጣት
ፕሬዚዳንታዊ ምርጫውን አሸንፈዋል በማለት ስታወግዝ በኢትዮጵያ በተደረገው ፓርላሜንታዊ “የብዙሀን ፓርቲ” ተብዬ ምርጫ አቶ መለስ
ዜናዊ 99.6 በመቶ ድምጽ በማግኘት አሸነፍኩ ብለው ድንፋታ ሲያሰሙ ዩናይትድ ስቴትስ አልሰማሁም፣ አላየሁም በማለት ጆሮ ዳባ ልበስ
ብላለች፡፡

የኦባማን የሰብአዊ መብት መርህ መገንዘብ፣

የኦባማ የሰብአዊ መብት አያያዝ መርህ ግልጽ እና ቀጥተኛ ይመስላል፡፡ የሰብአዊ መብት አያያዝ ፖሊሲ የማውጣት ስራ በዋናነት ከሁለት
ሰይጣኖች መካከል የትኛው የተሻለ ምርጫ ሊሆን ይችላል እንደማለት ነው፡፡ ዓለም እንደ እነ አሳድ፣ ሙጋቤ እና ማዱሮ ባሉ በሰው ልጆች ላይ
ወንጀልን የሚፈጽሙ የተጠሉ “ሰው በላ ጭራቆች” የተሞላች ናት፡፡ እንዲሁም እንደ የግብጹ ኢል ሲሲ ፣ የኡጋንዳው ሙሴቤኒ፣ የሩዋንዳው
ካጋሜ እና በቅርቡ በህይወት የተለዩት የኢትዮጵያው አቶ መለስ ዜናዊ በሰው ልጆች ላይ ተመሳሳይ የወንጀል ድርጊቶችን የፈጸሙ እና አሁንም
በመፈጸም ላይ ያሉ የተሻሉ ““ሰው በላ ጭራቆች” ናቸው፡፡ በሁለቱ ጭራቆች መካከል ያለው ልዩነት የኋለኞቹ የእኛው “ሰው በላ ጭራቆች”
መሆናቸው ነው፡፡ የእራሳችንን ስራ ይሰሩልናል፡፡ ትዛዛችን ይቀበላሉ:: ለዚህ ውለታቸው ደግሞ ነጻ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ ይፈቀድላቸዋል፡፡
በየዓመቱ በምጽዋት ስም በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ የአሜሪካ ዶላሮች እንሰጣቸዋለን፡፡” በማለት ዩናይትድ ስቴትስ ሀሳቧን አጠቃላለች፡፡

እ.ኤ.አ በ2008 ዕጩ ተመራጭ ኦባማ በማያቋርጥ ሁኔታ በየጊዜው በዋሽንግተን በሚወጡት “እምነት የማይጣልባቸው” “የውጭ ፖሊሲ
መርሆዎች” ላይ የተሰማቸውን ቅሬታ ገልጸው ነበር፡፡ ይህንን ጉዳይ በማስመልከት እንዲህ ብለው ነበር፣ “ልንታገላቸው ከሚገቡን ጠላቶች
መካከል በእርግጠኝነት አንዱ አሸባሪነት ብቻ አይደለም… ይልቁንም እምነት የለሽ መሆንም አንዱ እና ዋናው ነው፡፡ “በስድስት ዓመታት
የፕሬዚዳንትነት ዘመናቸው የኦባማ የሰብአዊ መብት ጥበቃ አያያዝ ፖሊሲ ደጋፊዎቻቸው ኦባማን ወደ ታማኝ የለሽነት አውቶብስ ጎማ ስር ውስጥ
ወርዉረዋቸዋል፡፡ የሂዩማን ራይትስ ዎች ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ኬን ሮዝ በቅርቡ የሚከተለውን ምልከታ አድርገው ነበር፣ “ፕሬዚዳንት ኦባማ
የሰብአዊ መብት ጉዳዮችን ቀዳሚ የትኩረት አጀንዳ አድርገው ባለመያዛቸው ምክንያት በርካቶችን አሳዝነዋል፡፡“ ወሳኝ በሆኑ የሰብአዊ መብት
ጉዳዮች ላይ ለመደራደር የሚያሳዩት ዝግጁነት ለሰብአዊ መብት ጥበቃ መርሆዎች ያላቸውን ቁርጠኝነት አናሳ መሆን የሚያመላክት አስተሳሰብን
ይፈጥራል፡፡ “በዓለም ላይ ያሉ ህዝቦች ሁሉ ለነጻነታቸው እና ለመብቶቻቸው መጠበቅ የጋራ የሆነ ፍላጎት ያላቸው መሆናቸውን“ ኦባማ የረሱት
ይመስላል፡፡

እ.ኤ.አ በ2008 ፕሬዚዳንት ኦባማ በጋና አክራን ሲጎበኙ ለአፍሪካ ወጣቶች ባደረጉት ንግግር ላይ የሚከተለውን መልዕክት አስተላልፈው ነበር፣
“ታሪክ ከጀግኖቹ አፍሪካውያን/ት ጎን ነው“ በማለት ማረጋገጫ ከሰጡ በኋላ እንዲህ ብለው ነበር፣ “መሪዎቻችሁ ለሚሰሯቸው ማናቸውም
ስራዎች ሁሉ በህዝቡ ዘንድ ተጠያቂዎች እንዲሆኑ የማድረግ ስልጣኑ አላችሁ፣ እናም ህዝቡን ሊያገለግሉ የሚችሉ ተቋማትን መገንባት እና
ማጠናከር አለባችሁ፡፡“ በቅርቡ ኦባማ ከእነዚያ ወጣት እና ጀግና ኢትዮጵያዊውያን/ት አፍሪካውያን/ት ወጣቶች እርሳቸው “እምነት ማጣት”
እያሉ በሚጠሩት ከፍተኛ ዋጋ ሰጥተውት በነበረው ጉዳይ ላይ በድንገት ትልቅ ፈተና ገጥሟቸው ተስተውለዋል፡፡ በካሊፎርኒያ ግዛት በሳን ጆሴ
የገንዘብ ማሰባሰቢያ መድረክ ላይ በትውልድ ኢትዮጵያዊ የሆነው ጋዜጠኛ እና የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ አበበ ገላው በኋይት ሀውስ ድረገጽ ላይ
እንደተለቀቀው ከፕሬዚዳንት ኦባማ ጋር የሚከተሉትን የሃሳብ ልውውጦች አድርጓል፣
 አበበ ገላው (የስብሰባው ታዳሚ አባል)፡ ፕሬዚዳንት ኦባማ! ለኢትዮጵያ ነጻነት! ነጻነት! ነጻነት ለኢትዮጵያ ጌታዬ!
ፕሬዚዳንት፡ ለትንሽ ጊዜ ቆይ፡፡ በምትለው ጉዳይ ላይ እስማማለሁ ሆኖም ግን ስጨርስ ኋላ ለምን አላነጋግርህም፣ ምክንያቱም ለመጨረስ
እየተቃረብኩ ነው (የመሳቅ ዓይነት አዝማሚያ እያሳዩ)፡፡ እኔ እና አንተ ስለጉዳዩ እንነጋገራለን፡፡ ወደዚያው አካባቢ እየመጣሁ ነው፡፡
አበበ ገላው (የስብሰባው ታዳሚ አባል)፡ (አይሰማም)--
ፕሬዚዳንት፡ እዚያ ሂድ
አበበ ገላው (የስብሰባው ታዳሚ አባል)፡ (አይሰማም)--
ፕሬዚዳንት፡ በምትለው ጉዳይ ላይ አስማማለሁ፡፡
አበበ ገላው (የስብሰባው ታዳሚ አባል)፡ (አይሰማም፡፡)
ፕሬዚዳንት፡ ከአንተ ለመስማት እፈልጋለሁ፡፡
አበበ ገላው (የስብሰባው ታዳሚ አባል)፡ እንወድዎታለን!
ፕሬዚዳንት፡ እኔም እወዳችኋለሁ፡፡ ብቻ የንግግሬን መጨረሻ አበላሸህብኝ፡፡ ቢሆንም ምንም አይደለም፡፡ (ሳቅ እና የድጋፍ ጭብጨባ ከታዳሚው
አስተጋባ፡፡) እሺ፡፡ ይህች አገር የመናገር ነጻነት የተከበረባት ናት-- (የድጋፍ ጭብጨባ እንደገና አስተጋባ)-- ይህም ታላቅ ነገር ነው፡፡

ለአምላክ/አላህ ምስጋና ይግባውና በአሜሪካ የመናገር ነጻነት አለን፡፡ አንድ ተራ ጋዜጠኛ እና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ግለሰብ በቁጥጥር ስር
እውላለሁ ብሎ ሳይፈራ፣ እታሰራለሁ ብሎ ሳይሰጋ፣ ድብደባ ወይም ደግሞ ስቃይ ይደርስብኛል ብሎ ሳያስብ ለዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ
ፕሬዚዳንት ቀጥ ብሎ ቆሞ በነጻነት መናገር ይችላል፡፡ ፕሬዚዳንት ኦባማ እና አበበ በአንድ ዓይነት ስሜት ሆነው ነው የተነጋገሩት፡፡ ፕሬዚዳንት
ኦባማ ጋዜጠኛ አበበ የንግግራቸውን መጨረሻ እንዳበላሸባቸው በቀልድ መልክ ተናግረዋል፡፡ አበበ ግን የኦባማ የሰብአዊ መብት አያያዝ ፖሊሲ
የትውልድ ሀገሩን እያበላሻት እንደሆነ በቁም ነገር ተናግሯል፡፡
ከዚህ ክስተት ልንማረው የምንችለው ታላቅ ቁም ነገር በዓለም ላይ ታላቅ ስልጣን እና ኃይል ያለው ሰው እና አንድ ተራ ዜጋ በዓለም መድረክ
በአንድ ላይ መቆማቸው ነው፡፡ ምክንያቱም ሁለቱም በነጻነት ላይ በተለይም በመናገር ነጻነት ላይ እምነት አላቸው፡፡ በተቃራኒው ደግሞ አበበ
ገላው በሳን ጆሴ ከተማ በመገኘት ድምጻቸውን ያሰማላቸው በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን/ት የመናገር ነጻነት ወይም እምነትን በነጻ
የማራመድ ነጻነት ወይም ደግሞ የመሰብሰብ ወይም ለሚፈጸሙባቸው በደሎች ቅሬታ የማቅረብ ነጻነት የላቸውም፡፡ ለዚህም ነው አበበ ገላው
ድምጹን ከፍ አድርጎ ለኢትዮጵያውያን/ት ወገኖቹ ነጻነት ሲል “ፕሬዚዳነት ኦባማ! ነጻነት ለኢትዮጵያ!“ እያለ የጮኸው፡፡

ፕሬዚዳንት ኦባማ በኢትዮጵያ እና በሌሎች የአፍሪካ አገሮች የመናገር ነጻነት እና ሌሎች ነጻነቶች እንዲኖሩ እምነት ያላቸው በመሆኑ ጉዳይ ላይ
ጥርጣሬ የለኝም፡፡ ጥያቄው ተያያዥነት በሌላቸው ባዶ የተስፋ ቃላትን በማነብነብ የተግባር ኮስማና እና ድሁር የመሆናቸው እና የአፍሪካን ወሮበላ
አምባገነኖች በጽናት የመደገፋቸው ጉዳይ ነው፡፡ ኦባማ በኢትዮጵያ ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ላይ በእርግጠኝነት እምነት ያላቸው ከሆነ
ለምንድን ነው እርሳቸው ወይም (የእርሳቸው የመንግስት መምሪያ ጸሐፊ፣ አምባሳደሮች እና ተወካዮቻቸው) የእርሳቸውን የመናገር ነጻነት እና
በኢትዮጵያ በእስር ቤት የሚማቅቁትን ጋዜጠኞች እና ጦማሪስቶች እንደ እስክንድር ነጋ፣ ርዕዮት ዓለሙ፣ ውብሸት ታዬ፣ አስማማው ኃ/ጊዮርጊስ፣
ተስፋለም ወልደየስ፣ ኤዶም ካሳዬ፣ አቤል ዋቤላ፣ አጥናፍ ብርሀኔ፣ ማህሌት ፋንታሁን፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ ዘላለም ክብረት እና በፈቃዱ ኃይሉ
ከብዙዎቹ ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያህል እንዲፈቱ ጥረት ሲያደርጉ የማይታዩት፡፡

ነጻነት በነጻ የማይገኝ መሆኑን ፕሬዚዳንት ኦባማ በእርግጠኝነት ማወቅ አለባቸው፡፡ ተግባርን አግልሎ በረዥሙ ምላሳቸው ስለይስሙላ ነጻነት
ብቻ ማውራት ርካሽ ንግግር ነው፡፡ በተደጋጋሚ እየተደረጉ ያሉት በጣም በርካታ ሆኖም ግን እርባናየለሽ ንግግሮች ናቸው፡፡ እናም በኢትዮጵያ
ነጻነት እጅግ ውድ የሆነ ዋጋ ተከፍሎበት የሚመጣ ጉዳይ ነው፡፡ እስክንድር ነጋ፣ ርዕዮት ዓለሙ፣ ውብሸት ታዬ እና ሌሎቸም የእራሳቸውን ድሎት
ሰውተው ለነጻነት የሚከፈለውን ክቡር ዋጋ በመክፈል ላያ ናቸው፡፡ ለሰው ልጆች የነጻነት ክብር ሲሉ በእስር ቤት ውስጥ በመማቀቅ ላይ ይገኛሉ፡፡
የእነዚህ ትንታንግ የነጻነት ታጋዮች የመኖር ሚስጥሩ በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙትን ወንጀሎች ለመታገል ነው፡፡

እ.ኤ.አ በ2005 ወደ 200 አካባቢ የሚጠጉ ምንም ዓይነት የጦር መሳሪያ ያልታጠቁ ሰላማዊ የነጻነት ታጋዮች ለነጻነት ሲሉ ክቡር ህይወታቸውን
መስዋዕት አድርገዋል፡፡ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሀን ዜጎች ሩብ ምዕተ ዓመታትን ባስቆጠረው የአምባገነኖች የአገዛዝ ስርዓት ለነጻነት ሲሉ
ውድ ህይወታቸውን ገብረዋል፡፡ የእነዚህ ንጹሀን ዜጎች ገዳዮች በአሁኑ ጊዜ በአገሪቱ በከፍተኛው የስልጣን ወንበር ላይ እንደ መዥገር ተጣብቀው
እና ያለምንም ተጠያቂነት ደረታቸውን ነፍተው በአውራ መንገዶች እንደ ነጻ ሰው ሁሉ ሰው መስለው በወንጀል ባህር ውስጥ ሲዋኙ እንዳልቆዩ እና
አሁንም እየዋኙ እያሉ መሆናቸው እየታወቀ ነጻ እና ከወንጀል የጸዱ በመምሰል ደረታቸውን ገልብጠው ሲንገዋለሉ እና ሲኮፈሱ ይታያሉ፣ የቁርጥ
ቀን የማይመጣ መስሏቸው፡፡ ኦባማ አነዚህን ወሮበላ አምባገነኖች በየዓመቱ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ የአሜሪካ ዶላሮች በመለገስ በስልጣኖቻቸው
ላይ ተጣብቀው ህዝብን ሲያሰቃዩ እንዲኖሩ ያደርጓቸዋል ብሎ መናገር ማጋነን አይሆንም፡፡ ተዋቂዋ የአፍሪካ የኢኮኖሚክስ ምሁር የሆኑት እና
“የበከተ እርዳታ/Dead Aid” የሚለው መጽሐፍ ደራሲ የሆኑት ዳምቢሳ ሞዮ እንደዘገቡት “በኢትዮጵያ በጣም ግዙፍ የሆነው በጀት 97 በመቶ
የሚሆነው የመንግስት በጀት የሚመጣው ከውጭ እርዳታ ነው፡፡“ ብለዋል፡፡ ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ በኢትዮጵያ ያለዜጎች ይሁንታ በጉልበት
በስልጣን ላይ ተፈናጥጦ ለሚገኘው ወሮበላ ገዥ አካል ሽማግሌ አናትም አባትም ናት! በአሁኑ ጊዜ 90 ሚሊዮን የሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ
ክብሩን እያጣ እየተሰቃየ፣ ኢፍትሀዊነት ድርጊት እየተፈጸመበት እና መብቱ በወሮበላዎች እና በሙስና በበከቱ ደንቆሮ መሪዎች ነን ባዮች መዳፍ
ስር ወድቆ አሳር ፍዳውን በመቀበል ላይ ይገኛል፡፡

የኦባማን የሰብአዊ መብት አያያዝ ፖሊሲዎች እና መርሆዎች ከሚናገሯቸው ባዶ የሰብአዊ መብት ንግግሮች ለመለየት አይቻልም፡፡ ለአሳድ
በምናባቸው “ቀይ መስመር” በማስመር የሶሪያን ህዝብ ሊጭርስ የሚችል ኬሚካላዊ መሳሪያ መጠቀም እንዳይችሉ የተሰመረውን ቀዩን መስመር እንዳያልፉ ያስጠነቅቋቸዋል፡፡ ባለፉት በርካታ ወራት አሳድ ይህንን ኬሚካላዊ መሳሪያ በመጠቀም ቢያንስ 14 ጊዜ ተግብረውታል፡፡ ለአፍሪካ
ወሮበላ አምባገነኖች ኦባማ ቀጥሉ የሚል አረንጓዴ መብራት በማሳየት በቀዩ መብራት የሰብአዊ መብት ወንጀሎች እንዲፈጸሙ ትዕዛዝ
ሰጥተዋል፡፡

የአቦማ አስተዳደር የሰብአዊ መብት መርሆዎች እንዲከበሩ ከልብ ተነሳሽነቱን የማያሳይ ከሆነ በተስፋ የሚያስሞሉ እና የዜጎችን ቀልቦች የሚገዙ
ታላላቅ መግለጫዎችን እና ንግግሮችን በሚሊዮኞች ለሚቆጠሩ ለዓለም ዓቀፉ የማህበረሰብ አባላት በተደጋጋሚ ማሰማቱ ፋይዳው ምንድን ነው?
የኦባማ አስተዳደር ይህን አሰልች እና አደንቋሪ የውሸት የሰብአዊ መብት አጠባበቅ መዝሙር ሲያሰማ ህዝቡ በሚደሰኮረው ዲስኩር እና
በተጨባጭ ምንም የተደረገ ነገር ያለመኖሩን ሊያገናዝብ የሚችል አዕምሮ የሌለው ደደብ እና ደንቆሮ አድርገው ሊቆጥሩት ይሞክራሉን? ለምንድን
ነው አቦማ በተደጋጋሚ በተግባር ሲያውሏቸው የማይታዩ የአስመሳይነት እና እምነተቢስነት ንግግሮችን እንደበቀቀን እየደጋገሙ ሲናገሩ
የሚደመጡት? ፕሬዚዳንት ኦባማ! እስቲ ቆም ብለው ያስተውሉ፣ የአፍሪካ ወሮበላ አምባገነኖች በጊዜ ሂደት የሰብአዊ መብት ጥበቃን የሚያራምዱ
እና መርሆዎቻቸው አድርገው ለመተግበር እንደገና ሊበራል ዴሞክራቶች ሆነው ይወለዳሉ ብለው ያስባሉን? የአረም አበባዎች አድገው ጽጌረዳ
ይሆናሉን?

ላሜሪካ የሰብአዊ መብትን የሚተካ የኢሰብአዊ ፖሊሲ የቀረበ ሀሳብ፣

ኦባማ በውጭ ግንኙነት ፖሊሲ የሰብአዊ መብትን በኢሰብአዊ ፖሊሲ መቀየሩ ይበጃል፡፡ የእርሳቸው ስልታዊ የሆኑ ብሄራዊ የሀገር ጥቅሞችን ብቻ
በሚያስገኙ ተግባራዊ የፖለቲካ ተግባራት ላይ ብቻ ማተኮራቸው የሞራል ሰብዕናን እና ትክክል ያልሆኑ የፖለቲካ እሴቶችን እንዲያሽቆለቁሉ
አድርጓቸዋል፡፡ በሌላ አባባል ስለሰብአዊ መብት ጥሩ እና ጥሩ ያልሆኑ ንግግሮችን ይናገራሉ፡፡ አምባገነናዊ ስርዓት ስለሚያከትምበት እና
ዴሞክራሲ በዓለም ላይ ስለሚያብበት ሁኔታ ይናገራሉ ሆኖም ግን የአሜሪካንን የአጭር ጊዜም እንኳ ቢሆን ብሄራዊ ጥቅሟን ከሚነካ አካሄድ ጋር
ለሰከንድ እንኳ በፍጹም የሚታሰብ ጉዳይ አይደለም፡፡

እንደ ትክክለኛው አካሄድ ኦባማ የዩናይትድ ስቴትስን “የተሳሳተ የኢሰብአዊ ፖሊሲ” ቢያንስ በአፍሪካ አህጉር ውስጥ በመርህ ደረጃ በመመስረት
እና በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያላቸው የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በአፍሪካ ሲፈጸሙ ዩናይትድ ስቴትስ ተመልክታ ጆሮ አልባ መሆኗን ማሳወቅ
አለባት፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ የኢሰብአዊ ፖሊሲ መብት መርሆዎች በሚከተሉት ቀላል ሀሳቦች ላይ የተመሰረቱ ይሆናሉ፡

አፍሪካ በምዕራቡ ዓለም እንደሚታሰበው ወይም ደግሞ በተግባር እንደሚስተዋለው የሰብአዊ መብት ጥበቃ አስፈላጊዋ አይደለም፡፡ “ሰላም እና
መረጋጋት” ዩናይትድ ስቴትስ በአፍሪካ ላይ የምታራምደው ትልቁ እና ጠቃሚዋ የፖሊሲ አካሄድ መሳሪዋ ነው፡፡ በአፍሪካ አምባገነን መሪዎች
የሚፈጸሙ ሰብአዊ ወንጀሎች ሌሎች አለመረጋጋቶችን እና ግጭቶችን ይወልዳሉ ከሚል የተሳሳተ እምነት አንጻር ዩናይትድ ስቴትስ አይታ
እንዳላየ፣ ሰምታ እንዳልሰማ ጆሮ ዳባ ልበስ በማለት ታልፈዋለች፡፡ (ለምሳሌ ያህል በደቡብ ሱዳን ሳልቫኪር እና ሬክ ማቻር በሚያደርጉት
ሰይጣናዊ ድርጊት ሰበብ ለፈጸሙት ግድያ፣ እልቂት፣ ዘር ማጥፋት፣ ህዝብን በኃይል ከሚኖርበት ቀየ ማፈናቀል፣ እስራት፣ ስቃይ አስገድዶ መድፈር
እና የጎሳ ዘር ማጥፋት ወንጀሎች ከተጣያቂነት ነጻ ነው የሚሆኑት፡፡)

የዩናይትድ ስቴትስን ዓለም አቀፋዊ እና አህጉራዊ ጥቅሞች እስካከበሩ እና ዩናይትድ ስቴትስ በአሸባሪነት ላይ የከፈተችውን ጦርነት
እስካልተቃወሙ ድረስ የአፍሪካ ወሮበላ አምባገነኖች በአፍሪካ አህጉር ላይ በጠራራ ጸሐይ ኮሮጆ ገልብጠው ምርጫ ሲዘርፉ እና ስልጣናቸውን
ከህግ አግባብ ውጭ እየተጠቀሙ በአፍሪካውያን/ት ዜጎች ላይ የቁማር ጨዋታ ሲጫወቱ አሜሪካ ጸጥ በማለት በትዕግስት የምትመለከተው
ደንታም የማይሰጣት የዕለት ከዕለት ጉዳዩዋ ሆኗል፡፡

የፍራንክሊን ዲ.ሩዝቬልት “በየትኛውም የዓለም ክፍል” እንዲተገበሩ የሚገባቸው አራቱ አስፈላጊ የሰው ልጆች ነጻነቶች በአፍሪካ ላይ ግን
ተግባራዊ አይሆኑም፡፡ ዩናይትድ ስቴትስ ጨለማ የተንሰራፋበትን የአምባገነኖች አገዛዝ በማንኮታኮት እራሷን ከጀግና የነጻ የዓለም ህዝቦች ጋር
ለማስተሳሰር የሩዝቬልትን ራዕይ አትከተልም፡፡ “አራት አስፈላጊ የሆኑ የሰው ልጅ ነጻነቶች የሚገለጹባት ዓለምን ዕውን ሆና ማየት እንፈልጋለን፡፡”
በማለት ሩዝቬልት የተናገሩትን ወደ ተግባር ለአፍሪቃ አያስፈለግም፡፡የመጀመሪያው የመናገር እና ሀሳብን በነጻ የመግለጽ መብት - (ከአፍሪካ
አህጉር በስተቀር በዓለም ላይ ሁሉ)፡፡ ሁለተኛው ማንም ሰው በራሱ መንገድ አምላኩን የማምለክ እና የፈለገውን እምነት በመያዝ የእራሱን እምነት
የማራመድ መብት - (ከአፍሪካ አህጉር በስተቀር)፡፡ ሶስተኛው የፍላጎት ነጻነት መብት - ከዓለም አቀፍ ሁኔታ አንጻር ሲተረጎም ይህ ማለት
የእያንዳንዱን አገር ጤናማ የሰላም ጊዜ የማስፈን እና የእያንዳንዱን ዜጋ ፍላጎት - በየትኛውም የዓለም ክፍል ማሟላት (ከአፍሪካ በስተቀር)፡፡
አራተኛው ከፍርሀት ነጻ የመሆን መብት… ከዚህ አንጻር ማንም ጠብ አጫሪ አገር ተነስቶ በጎረቤቱ ላይ የኃይል እርምጃ በመውሰድ ጥቃት
አይፈጽምም፡፡ እንደዚሁም በዓለም ላይ ጥቃት ለመፈጸም አይቻለውም (ከአፍሪካ በስተቀር)፡፡ የሩዝቬልት ዓለም አቀፍ የሰብአዊ ድንጋጌ እና
ሌሎችም በድንጋጌው እየተፈተሉ የሚገኙት ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ስምምነቶች በየትኛውም የዓለም ክፍል ላይ ተግባራዊ ይደረጋሉ
(ከአፍሪካ በስተቀር)፡፡

በዩናይትድ ስቴትስ ትክክለኛ እና “በተግባር ተኮር ፖለቲካ” ፖሊሲ ላይ እራሱን ብቁ ያደረገ በሚከተሉት የዩናይትድ ስቴትስ ፖሊሲ የሰብአዊ
መብት ፖሊሲ ግድፈቶችን ግልጽ በሆነ መልኩ ያካትታል የሚል እምነት አለኝ፡፡ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እና የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች
በአፍሪካ ላይ ዩናይትድ ስቴትስ ስላሏት እሴቶች፣ መርሆዎች እና ፖሊሲዎች ግልጽ የሆነ ግንዛቤ ይኖራቸዋል የሚል እምነት አለኝ፡፡ ዩናይትድ ስቴትስ በአፍሪካ ላይ ስላሏት ዝንባሌዎች እና ዓላማዎች እንዲሁም አለመግባባቶች እና ግንዛቤ ያለመኖር ችግሮች አይኖሩም፡፡ የሰብአዊ መብት
ተሟጋቾች ዩናይትድ ስቴትስ ስለሚኖራት የሰብአዊ መብት ስህተቶች የሚናገሩት በጣም ጥቂት ነገር ብቻ ይሆናል፡፡ ከንፈሮቻቸውን ይነክሳሉ፡፡
አብዛኞቹ የአፍሪካ አምባገነኖች ለሰሩት ታማኘነት ላለው እና መልካም ስራ ትክክለኛ ምስጋና ያገኛሉ፡፡ ዩናይትድ ሰቴትስ ወዲያውኑ እነዚህን
አምባገነኖች እንዳላየች አድርጋ የመሄድ አስመሳይነቷን ታቆማለች፡፡

 ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
ግንቦት 12 ቀን 2006 ዓ.ም
ምንጭ የኢትዮጵያ ሜዲያ መድረክ

Monday, May 19, 2014

በአባይ ጉዳይ ኃያላኑ በግብጽ ላይ ጫና እየፈጠሩ ነው የጫናው መነሻ አነጋገሪ ሆኗል

ምዕራባውያን ሃያላን አገሮች ግብጽ በአባይ ዙሪያ የድርድር ጠረጴዛ ላይ እንድትቀመጥ ጫና እያደረጉ መሆኑ ተሰማ፡፡ ዜናውን የዘገበው አልአህራም ቃል በቃል ግብጽ ላይ ጫና ተፈጠረ ብሎ ባይጽፍም ከዜናው ለመረዳት እንደተቻለው ግብጽ ላይ ጫና እየተደረገባት ነው፡፡ ሃያላኑ ግብጽ ላይ እያሳደሩት ያለው ጫና መነጋገሪያ ሆኗል፡፡
እንደ ጋዜጣው ዘገባ ያለፈው ቅዳሜ የግብጹ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ከኢትዮጵያ ጋር በአባይ ጉዳይ ለመደራደር አገራቸው ፈቃደኛ መሆኗን ማሳወቃቸውን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ ይህንን መግለጫ ከመስጠታቸው በፊት የግብጹ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር መ/ቤት የውሃ ሃብት ልዩ አስተባባሪ ከሆኑት አሮን ሳልዝበርግ እንዲሁም ከአውሮጳ ኅብረት ልዩ ልዑክ አልክሳንደር ሮንዶስ ጋር ውይይት ማድረጋቸው ታውቋል፡፡
በተለይ የአሜሪካው ተወካይ ሳልዝበርግ ወደ ግብጽ ከመሄዳቸው በፊት አዲስ አበባ ላይ ቆይታ አድርገው ከኢህአዴግ ባለሥልጣናት ጋር ግድቡን በተመለከተ ውይይት ማድረጋቸው አብሮ ተዘግቧል፡፡ ሆኖም ኢህአዴግ በምን ነጥቦች ላይ እንደተደራደረ የተገለጸ ነገር ባይኖርም የአሜሪካው ባለሥልጣን ወዲያው ወደ ግብጽ እንደበረሩ ግብጽ ድርድር መፈለጓ መገለጹ የበርካታዎችን ትኩረት የሳበ ጉዳይ ሆኗል፡፡
idan ofer
ኢዳን ኦፈር – ፎቶ ሪፖርተር
በተያያዘ ዜና ሪፖርተር እሁድ ባስነበበው ጋዜጣ ላይ እስራኤል በኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጨት ሥራ የመሰማራት ዕቅድ እንዳላት ዘግቧል፡፡ እስካሁን ድረስ እስራኤል በኃይል ማመንጨት ሥራ ውስጥ የመሳተፍ ፍላጎት እንዳለት ሲጠቀስ የቆየ ቢሆንም ከዚሁ ጋር ተያይዞ በርካታ ጥያቄዎች ሲነሱ ቆይተዋል፡፡ ሆኖም እንደ ሪፖርተር ዘገባ ከሆነ በኢትዮጵያ የፖታሽ ፕሮጀክት 30በመቶ ባለድርሻ የሆኑትን የሚስተር ኢዳን ኦፈር ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ዘርፍ የመሰማራት ዕቅድ እንዳላቸው ጠቅሷል፡፡
እንደ ዜናው ከሆነ እስራኤል የምትሰማራበት የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ “የውኃ፣ የጂኦተርማል ወይም የንፋስ መሆኑን” በግልጽ እንዳላሳወቀች ነገር ግን ጥናቱ በኩባንያው ቴክኒክ ቡድን በኩል እንደሚካሄድ የኩባንያው ባለቤት መናገራቸውን ጨምሮ ዘግቧል፡፡ ሚስተር ኦፈር የሚመሩት ኢዝራኤሊ ኬሚካልስ የተባለው ኩባንያ በማዳበሪያና መሰል ምርቶች ላይ የተሠማራ ሲሆን የማዕድን ማውጣት ተግባሩን በእስራኤል፣ በአሜሪካ፣ በአውሮጳና ቻይን ያካሂዳል፡፡ ከኩባንያው አክሲዮን ሁለተኛው ከፍተኛ ባለድርሻ የካናዳው የፖታሽ ኮርፖሬሽን እንደሆነ ይታወቃል፡፡
የእስራኤል በኢትዮጵያ በኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ተግባር የመሰማራቷ ዜና ምናልባትም ከአባይ ግድብ ጀርባ የሃያላኑ አገራት ድጋፍና ጥበቃ እንዲሁም ቀጥተኛ ወይም ተዘዋዋሪ የሆነ ጥቅም የማስከበር ፍላጎት እንዳለ የሚሰነዘረውን ሃሳብ ያጠነክረዋል፡፡ አንዳንዶች እንደሚሉት የጫናው መነሻ ይህ የጡንቸኞቹ የጥቅም ጉዳይ እንደሆነ ያስረግጣል ይላሉ፡፡
በዚህና በተለያዩ ምክንያቶች በአባይ ግድብ ዙሪያ የሚነሱት መላምቶች ወይም መከራከሪያዎች ከሃያላኑ ጫና ጋር ተዳምረው መነጋገሪያ ርዕስ ሆኗል፡፡ግብጽ ጫናውን አስመልክቶ በይፋ የገለጸችው ተቃውሞ ወይም ቅሬታ የለም፡፡ ይሁን እንጂ በግብጽ የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዘመቻ ላይ ያሉትና የምዕራባውያን ቀጥተኛ ድጋፍ ያላቸው ፊልድ ማርሻል አል-ሲሲ “የውሃ ነገር” ለግብጽ “የህይወትና የሞት ጉዳይ” መሆኑን መግለጻቸውንና  ከኢትዮጵያ ጋር በመሆን መፍትሔ መፈለጉ “የግድ” እንደሆነ ማስታወቃቸውን ጎልጉል ዘግቦ ነበር፡፡
በዜናው መሠረት አል-ሲሲ “የሌሎችን ፍላጎትና ጥቅም የምንረዳ መሆናችንን ማሳየት ይገባናል፤ (የዚያኑ ያህልም) የራሳችንን ጥቅም ለማስጠበቅ ጽኑ መሆን አለብን፤ (ምክንያቱም) ውሃ ማለት ለእኛ የህይወትና የሞት ጉዳይ ነው” ማለታቸውን ጎልጉል ጨምሮ በማስታወቅ እጩው ፕሬዚዳንት ከዚህ በፊት ያልታየ መለሳለስ በማሳየት “ለኢትዮጵያና ለሌሎች አፍሪካ ወንድሞቻችን ተገቢውን ጥረት አለማድረጋችንን ማመን አለብን፤ በዚህ ዓይነቱ ጉዳይ ለመተባበርና መፍትሔ ለማግኘት ድርድርና የጋራ መግባባት ቁልፍ ናቸው” ማለታቸውን ጭምሮ ዘግቦ እንደ ነበር ይታወሳል፡፡
የአባይ ጉዳይ ኢትዮጵያንና ግብጽን ለዘመናት በተለያዩ እሰጥ አገባ ውስጥ የከተታቸው ነው፡፡ በአባይ ከሚፈሰው 90በመቶ የሚሆነው ውሃ የሚመነጨው እንዲሁም በአባይ ተጠርጎ ከሚወሰደው ለም አፈር 96በመቶ የሚሆነው የሚሄደው ከኢትዮጵያ ደጋማ ክፍል እንደሆነ ይታወቃል፡፡ የአባይ ወንዝን አጠቃቀም በተመለከተ የሚያስተዳድሩት ሕጎች እኤአ በ1929 እና በ1959 በግብጽና በሱዳን እንዲሁም በግብጽና በብሪታኒያ በቅኝ ግዛት ዘመን በተፈረሙ ውሎች ሲሆን በውሉ መሠረት ግብጽና ሱዳን ከአባይ ወንዝ ኃብት በድምሩ 90በመቶ የሚሆነውን የመጠቀም መብት አላቸው (ይህም በየዓመቱ 55.5 ሜትር ኩብ የሚሆነው ለግብጽ 18.5 የሚሆነው ደግሞ ለሱዳን ማለት ነው)፡፡
ይህ ኢትዮጵያን የሚጎዳ ውልና አሠራር እንዳለ ሆኖ የዛሬ አራት ዓመት አካባቢ በታህሳስ ወር አቶ መለስ ይህንኑ የቅኝ ግዛት ዘመን ውል እንደገና በመቀበል ግብጽ በአባይ ወንዝ ላይ የተፈቀደላትን የድርሻ ኮታ ማግኘት ይገባታል በማለት ስምምነት መፈረማቸውን አልአህራም በወቅቱ ዘግቦ እንደነበር አይዘነጋም፡፡
ከጥቂት ቀናት በፊት ደግሞ ኢነርጂ ቢዝነስ ሪቪውን በመጥቀስ ሪፖርተር ለንባብ ባበቃው ዜና ላይ “በምሥራቃዊ ሱዳን በኩል ከከሰላ ግዛት ተነስቶ ወደ ኤርትራ በሚዘረጋ የ45 ኪሎ ሜትር የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር” በኩል ሱዳን ከኢትዮጵያ የምትገዛውን የኤሌክትሪክ ኃይል ለኤርትራ ለመሸጥ እንቅስቃሴ ላይ መሆኗን ዘግቧል፡፡ ሱዳን ከዚሁ የአባይ ግድብ በርካሽ የምትገዛውን የኤሌክትሪክ ኃይል ምን ያህሉን በምን ያህል ትርፍ ለኤርትራ ለመሸጥ እንዳሰበች እስካሁን አለመታወቁን ጋዜጣው ጭምሮ አስታውቋል፡፡
አቶ መለስ ሥልጣን ላይ በነበሩበት ዓመታት ኤርትራ ከኢትዮጵያ ያለቀረጥ ክፍያ በነጻ ያህል ከኢትዮጵያ የምትወስደውን ቡና በዓለም ገበያ ላይ በመሸጥ ከቡና አምራችና ሻጭ አገራት ውስጥ ተመዝግባ እንደነበር አይዘነጋም፡፡ ከዚህ ልምድ በመነሳት አሁንም ኤርትራ ከሱዳን የምትገዛውን ከአባይ ግድብ የሚመነጨውን የኤሌክትሪክ ኃይል በአቅራቢያዋ ለሚገኘው አጎራባቿ የሰሜን ኢትዮጵያ ክልል መልሳ በትርፍ ትሸጥ ይሆናል የሚለው አስተያየት ስላቃዊ ቢሆንም አነጋጋሪ እየሆነ መጥቷል፡፡
ምንጭ www.goolgule.com

Sunday, May 18, 2014

ግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል ላለፉት ሶስት ወራት ያሰለጠናቸውን የአራተኛ ዙር ታጋዮችን አስመረቀ

የኢትዮጵያዊያንን ስቃይና መከራ ሊያቅብና እንባቸውን ሊየብስ፤ ሀገራችን ኢትዮጵያ በጎጠኛው ሕወሃት የደረሰባትንና እየደረሰባት ያለውን ውርደት ወደ ክብር ለመለወጥና የናቋትና ያዋረዷት በፍትህ ሚዛን ላይ እንዲቀመጡና ፍርዳቸውን እንዲያገኙ ለማድረግ ዓላማየ ብሎ ምሎ ዱሩ ቤቴ ካለ ገና ሁለት ዓመት እንኳ ያልሞላው ግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል በቃሉ መሰረት አራተኛውን ዙር የታጋዮች የምረቃ በአል ሚያዚያ 26 2006 ዓ/ም ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች በተገኙበት ማክበሩን አስታወቀ። ይህ የአራተኛው ዙር ስልጠና በሰልጣኞች ቁጥርም ሆነ በስልጠናው ጥንካሬ ካለፉት ሶስት ዙሮች በእጅጉ የተለየ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን በአሁኑ ሰአት ያለውን የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበና ወቅቱ የሚፈልገውን ቴክኖሎጅ በመጠቀም መረጃን መቀበልና ማስተላለፍን የጨመረም እንደነበር ተያይዞ ተጠቅሷል።
በሀገር ውስጥ ፋሽስት ወያኔ እያደረሰው ባለው መረን የወጣ ግፍ የተበሳጩና ሁሉም ልክ እንዳለው ለማሳየት ቆርጠው የተሰለፉት እነዚህ ምሩቅ ታጋዮች ከወታደራዊው ስልጠና በተጨማሪ የፖለቲካ፣ መረጃና ደህንነት እንዲሁም ሌሎችንም ተያያዥ ክህሎቶችን በበቂ ሁኔታ እንደቀሰሙም ተጠቁሟል። ስልጠናው ታጋዮቹ ወደፊት

ከሚያጋጥማቸው ጠንካራ ፈተናና ከሚሰለፉበት ጥብቅ ግዳጅ አንጻር በቀላሉ ተስፋ እንዳይቆርጡ ለማድረግ በአካልም ሆነ በመንፈስ ዝግጁ እንደሚያደርጋቸው የተገለጸ ሲሆን የተጀመረው ሕዝባዊ ትግል በግለሰብ ደረጃ ሳይሆን በጋራና በተቀነባበረ ሃይል ለድል እንደሚበቃና ይህን የጋራ ሃይል በጠነካራ እጆች ላይ ላመስቀመጥም የተሰጠው ስልጠና ከበቂ በላይ ነበር ተብሏል።
ግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል በሀገር ውስጥ እንደማእበል እየገነፈለ ያለውን የአታግሉን የሕዝብ ጣያቄ በተደራጀና በተቀነባበረ መንገድ በተገቢው መልኩ ለማስተናገድ እንዲችል እንደ ድርጅት ከመቼው በላይ ራሱን እያደራጀና እያጠነከረ እንደሚገኝና ምቹ አታጋይ ተቋም ሆኖ ለመውጣት ሌት ተቀን እየደከመ መሆኑም ተያይዞ ተጠቅሷል። በታጋዮች ስልጠና ወቅት የተገኙ አንዳንድ የክብር እንግዶች እንደጠቆሙትም ”ባሁኑ ሰአት በሀገር ውስጥ ያለው ሁኔታ ከመቼውም በላይ የተመቻቸ ነው” ካሉ በሗላ ”ሕወሃት የሚተማመንበት ወታደሩ እንኳ ቁጥሩ ካልሆነ በቀር ልቡም ሆነ መንፈሱ ከሕዝብ ጋር ነው፤ በሁሉም የሀገሪቱ አቅጣጫዎች እየሆነ ያለው ወያኔ በእርጅና ዘምኑ ማብቂያ ላይ መሆኑን ነው የሚያመለክተው። ስለሆነም በመረጃ መንቀሳቀስና በትብብር መስራት ባጭሩ ለድል ያበቃል። ለዚህ ደግሞ የዛሬ ምሩቅ ታጋዮች ያገኙት ስልጠና ለታሰበው ስኬት የሚያበቃቸው ነው” በማለት ትዝብታቸውን አጠቃለዋል።
በምረቃው ማብቂያ ላይ ራሱን ግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል ብሎ ከሰየመበት ጊዜ ጀምሮ ለፋሽስት ወያኔ ከፍተኛ ስጋት እንደሆነ በማስረገጥ የጠቆሙት የሕዝባዊ ሃይሉ ሃላፊዎች፤ ከዚህ በፊት ፋሽስት ወያኔ በከፍተኛ ወጭና ጥንቃቄ ሕዝባዊ ሃይሉን ለማፈራረስና ለማትፋት በከፍተኛ ሁኔታ የሰራ ቢሆንም በሕዝባዊ ሃይሉ መረጃና ደህንነት ክፍል መክሸፉን አስታውሰው፤ ዓላማችንን ከዳር ለማድረስና የሕዝባችንን አርነት ለመመለስ ሀገራችንንም ከወያኔ አገዛዝ ነጻ ለማውጣት በምናደርገው ትግል የኢትዮጵያ ሕዝብ ከመቼውም ጊዜ በላይ ከጎናቸው እንዲቆም ጥሪ አስተላለፈዋል። ይህን ታሪካዊ ጥሪ ለመመለስና የሀገርና የትውልድ ጠላት የሆነውን ወያኔ ሕወሃትን ለማስወገድ አብረን እንቁም ሕዝባዊ ሃይላችንንም ተቀላቀሉ ሲሉም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
ምንጭ www.ginbot7.org

Friday, May 16, 2014

ሰሚ ያጣ ጩክት ከሱዳን /ካርቱም (አጥናፉ መሸሻ)

በአባት አያቶቻችን ክቡር ደም ተከብራ የኖረችው ኢትዩጵያ አሁን በኛ ዘመን ልጆቾ ለደረሰባት ውርደት ዝቅጠት ሰደትን እንደመፍትሄ
አድርገን መውሰድ ከመጀመራችን በፊት በአለም አቀፍ ደረጃ ስደተኛን በማስተናግድ ቀዳመዊ ነበረች። ለዚህም እስራኤሎቾን፤ አረቦችን፤
አርመኖችና ግሪኮች ምስክር ቢሆኑንም በዋናነት ግን የታሪኳ ቁንጮ ሆኖ የተመዘገበው ነብዩ መሀመድ እምነታቸውን ለማስፋፋት ችግር
በገጠማቸው ግዜ ተከታዮቻቸውንና ቤተሰባቸውን ወደ ሀበሻ የሰላም ምድር፤ እምነቶች በ እኩልነት የሚስተዳደሩባት ፍርዱ ትክክል የሆነ
መሪ ያለባት ሀገር እንዲሄዱ ቤተሰቦቻቸውን ሸንተው ተከታዮቻቸውን በክብር ተቀብላ ጥላ ከላላ፤ የመከራ ግዜ መጠጊያ ሆና የኖረች
በገናና ታሪኮ እንደ ሰለሞን ጌጥ ጥበብ አለም ያደነቃት ያካበራት የምንኮራባት ሀገራችን ኢትዩጽያ ናት።፡እነሆ የነዚያ ደጋግና ቆራጥ ልጅ
ልጆቾ እስልምና እምነት ተከታይ በሆነቸው ጎረቤተ ሀገር ሱዳን በስደት ተጠለልን በምንኖርበት ምድር ግፍ እየተፈፀምብን ይገኛል።

በእርግጥ ሱዳኖች ለወያኔ ታላቅ ባለውለታ እንደመሆናቸው መጠን አይናችን እያየ የዮሀንስ ከተማ መታማ ና በበርካታ በክርሰ ምድሮ
የደለበ ማእድናት ና ድንግል መሬት ባላቤት ሆነዋል በዚህም አላበቃም ዛሬ ሀገራችን በ እንቨስትመንት ስም ከቻይና ቀጥሎ በሁለተኛነት
ኢትዮጽያን የተቀራመቶት ከቅጥረኛው ወያኔ ባለስጣናት ጋር በመሰሪ ተግባራቸው በመመሳጠር በሱዳን ከበርቴዋች ስም በርካታ
እንቨስትመንት ባለቤት ሆነዋል በዚህ ተግባር አዜብ ከሱዳኖች ከበርቴ ጋር በስውር ሸርክና እንዳላት ለዚህ አንዱ ማሳያ ሆነ እንጅ ሁሉም
ቅጥረኛው ዘራፊ የወያኔ ባለስልጣናት እንዳሉበት አሳምረን አናውቃለን ፤ ዛሬ ከ ከሁለት መቶ ሀምሳ በላይ ሱዳናዊያን ከበርቴዎች
በግብርና፤ በከፍተኛ የመንገድስራ ኮንስትራክሸን ባለቤት ና ወደ አርብ ሀገራት በቀን አስከ አምስ ሸህ የበግና የፍየል ስጋ በመላክ የተሰማሩ
የናጠጡ ከበርቴዎች ሆነዋል እኛ ግን እዚህ ሰርተን ጥረን ግረን በምንኖር ስደተኞች ከሌሎች ዜጎች በተለየ በወያኔ አቀነባባሪነት ቁም
ስቅላችን እናያለን።

ሱዳን ሀገር ውስጥ ለበርካታ አመታት በስደተኝነት የተሻለ ቀን እስኪመጣ ድረሰ ትክክለኛ አሀዙ የማይታወቅ ኢትዩጵያዊ የጉልበት ስራ
እየሰራ ቤተሰቡን እያስተዳደረ የሀገሪቱን ሕግ አክብሮ ይኖራል ካለፈው ወር ጀምሮ ወያኔና የሱዳን መንግስት ይፋዊ ባልሆነ መልኩ
ያደረጉት ድብቅ ስምምነት መሰረት በተቀናጀ መልኩ የሱዳን ደህንነት፤ የልዩ የፖሊስ፤ እንዲሁም ከወታደሩ ክፍል የተወጣጣ ሰራዊት ዩኒ
ፎርም የለበሱና ያለበሱ የስደታኛውን ማህበረሰብ ቤት ለቤት በመግባት ፤ በየ አውራ መንገድ ሀበሻው በሚኖርበት አካባቢ እየተዘዋወሩ
የስደተኛ መታወቂያ የያዘውንና እንዲሁም ወያኔና የሱዳን መንግስት ያዘጋጁት ለስድስት ወር የሚቆይ ጊዜያዊ ማታወቂያ ያለውንና
ያልያዘውን መታወቂያ በመጠየቅ በመንጠቅ አስገድደው መኪና ላይ በመጫን ካርቱም ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ እስርቤቶች በስሀፋ
ዘለጥ፤ በሰሀፋ ሸሪ ፤ በዴም ፤በጅሬፍ፤ ባርኬዌት፤ በሶባ፤ ባህሪ፤ በ እንዱሩማን በከደሮ በሀጅ የሱፍ ግፍ እየተፋፀመባቸው ይገኛል።

እንደሚታወቀው ወያኔ በትግል ዘመኑ ይሁን ስልጣን ከጨበጠ አንስቶ በ በጎንደር ክ/ሀገር ለምና ወርቅ ምድር ከሆነው የፀለምትንና
ሁመራ ወልቃይት ጠጌዴን ገበሬዎችን በሽህዎች የሚቆጠሩ ቅድመ አያቶቻቸው ተወልደው ድረው የኮሉበትን ባድማ፤ ለዘመናት
ማእረግና ክብር ባዩበት ምድር በግፍ እንዲሰደዱ አድርጎ የዘር ማፅዳት ወንጅል ካከናወኑ በሓላ በምትኩ የወያኔን የትግል ዘመኑን
ሰራዊትና የራሱን ሰዎች አስፍሮበት ፤ ለህሊና ማመን የሚከብደው ግፍ ከተፈፀመባቸው በሓላ አሁን በስደት የሚገኘው ማህበረሰብን
በሚሰራበት የስራ ቦታ ፤ በመንገድ ልጆቹ እዚህ ካርቱም ተወልደው ለመታወቂያ ያልደረሱ ተማሪዎች በግፍ ከነ ቤተሰባቸው ታስረዋል፤
ከሁሉም በላይ ልጆቻቸውን ክርስትና አስነስተው አስጠምቀው ከቤተክርስትያን በሕዝብ ትራንስፖርት ወደ ቤተቻው በመመለስ ላይ
የነበሩትን አውርደው አስረዋቸዋል ፤ ከወለደች አንድ ወር የሆነች አራስ እህት ከቤቶ አውጥተው በመታወቂያ ስም ከነ እርጥብ ጨቅላ
ልጆዋ የሙቀት ደረጃው 50℅በሚደርስበት ሰአት ታስራለች ፤ ሌላው በወያኔ ደላላ በቀን አንድ ሸህ ዶላር ይከፈላችሁል እየተባሉ ከሞቀ
ቤታቸው ሴት ህፃናትን ከት/ቤት እያታለሉ ከሀድያ አካባቢ ከወላይታ፤ ከጅማና ከ አሩሲ ገጠራማው ለም ምድር ሆን ተብሎ እያሰፈለሱ
በሸህ የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ካርቱም በሚገኙ የተላያዩ እስር ቤቶች ውስጥ ኢትዮጽያዊያን ግፍ እየተፈፀመባቸው ይገኛል; ባሳለፍነው
እሁድ ከደሮ በሚገኘው እስር ቤት ኦሮምኛ የሚናገሩ ወንድሞቻችን ተመርጠው ተነጥለው ወደ አልታወቀ ቦታም ተወስደዋል።

ከሁሉም በላይ ይህ ሁል በደል በ ኢትዩጽያዊያን ስደተኞች ላየ ሲፈፀም ዩ ኔ ኤች ሲ አር UNHCR / ከ አቅማችን በላይ ነው የሚል መልስ
መስጠቱ ያሳፍራል ባሳለፍነው ሳምንት አቶ ኢሳያስ ወደ ሱዳን ሲመጡ እጅ መንሻ ዳረንጎት ይሆን ዘንድ 30 ኤርትራዊያን ስደተኛ
ወገኖቻችን ለኤርትራ ተላለፈው ሲሰጡ አለም አቀፍ የሰባአዊ መብት ተቆርቐሪ ጮኸት ማሰማታቸው ቢያስደስተንም ይህ ሁሉ በደል በኛ
ላይ እየተፈፀመ በየ ቀኑ እንደወንጀለኛ አንድ መቶ ሀምሳ የሚገመትና አራት መቶ ሸህ የሱዳን ፓውንድ እየተቀጡ ንብረታቸውን ሳይዙ
ኢትዮጽያዊያን ሲባረሩ አንዳንችም አለምማቀፍ የሰባአዊ መብት ተሞጎች ካው ቦይስ ትንፍሸ አለማለታቸው ከልብ ያሳዝናል;; ትናትና
13/5/2014 ሁዳ እየተባለ ከሚጠራው ከ እንዱርማን ውጭ በርሀ ውስጥ በሚገኘው እስር ቤት ውስጥ ከ አቶ ኢሳያስ ጉብኝት መመለሰ
ጋር በተያያዘ ይሁን አይሁን ባይታወቅም 300 ኤርትራዊያን እስረኞች በነፃ ሲለቀቁ ከ300 በላይ ኢትዮጽያዊያን ሲኖሩ እነዚህም
ለበርካታ አመታት ጠያቂ የለላቸው እስረኞችም የመከራን ሕይወት እየገፉ ይገኙበታል። ሌላው አስገራሚው ድራማ ግን 150
ኢትዮጽያዊያን በዛሬው እለት 14/5/2014 ወደ መተማ ይባረራሉ፤ ከነዚህ እስረኞች መሀል በትናትናው እለት የመሸኛ ወረቀት ሊሴ ፓሴ
ሲያዘጋጁ አንዱ እስራኛ ወያኔ ኢንባሲ ውስጥ አምልጧቸው ለሊቱን ሙሉ የቀሩትን ሲደበድቧቸው እንዳደደሩ አይን እማኞች
ተናግረዋል።
ለወገን ደራሸ ምንግዜም ኢትዮጵያዊው ወገን ነውና ሰውዲ አረቢያ በነበሩ ወገኖቻችን ሰብአዊነት የጎደለው ግፍ ሲፈጸም ፈጥኖ በመደረስ
ይደረስ የነበረውን ውርደት ግፍ አለምአቀፋዊ ጩኸት በማሰማታችሁ ሊቆም ችሏል። አሁንም እኛ ይህንን ሁሉ ሰቆቃ እንደ ራሄል እንባ
በማንባት በመንበረ ፅብዐቱ እሰኪ ዘልቅ የግፍአን እንባና ጮኸታቸን በየቤቱ ሁሉም እያሰማን ብንገኝም ከ እለት እለት ተዘርዝሮ
የማያልቅ በደል ሰሚ የለለው በኛ ምንዱባን ላይ በወያኔ ልዩ ቅንብር ስለሚፈፀምብን በመላው አለም የምትገኙ ወገኖቻችን ከምንግዜው
በበለጠ ትደርሱልን ዘንድ እንማፀናለን;; ይህንን የግፍአን ድምፅ ልሳን ትሆን ዘንድ እያቃተትን እንማፀናለን። አዎ ! ይህንን ሁሉ በደል
ከደንበሩ ጋር ስለምናያይዘው የሱዳን መንግስት አለም አቀፍ ስምምነቶችን አክብሮ ሰብአዊነታችንን እንዲያከብር እንዲሁም ዩ ኤን ኤች ሲ
አር UNHCR ጉዳያችን ቅድምያ ሰጥቶ ዝምታውን ሰብሮ ይህንን ሁሉ ግፍ በ አስቸኳይ እንዲያስቆም በአንድ ድምፅ ታሰሙለን ዘንድ
እንማፀናለን።

አጥናፉ መሸሻ


ምንጭ ኢትዮሚድያ - Ethiomedia.com
May 14, 2014

Thursday, May 15, 2014

ጁነዲን ሰዶ አሜሪካ አትላንታ ገቡ

“ይሄ ፋሽስት መንግሥት!” ማለት ጀምረዋል!

5/14/2014- አገር ለቀው የኮበለሉትና የኦሮምያ ፕሬዚዳንትነትን ጨምሮ በተለያዩ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች በሚኒስትርነት ማዕረግ ያገለገሉት እንዲሁም የኦህዴድና የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት አቶ ጁነዲን ሰዶ አሜሪካ ገብተዋል። ኬንያ ለአንድ ዓመት ያህል በስደተኝነት ተቀምጠው የአሳይለም ወረቀታቸውን አግኝተው አትላንታ ከገቡ ሁለት ወራት እንደሆናቸውም የዘኢትዮጵያ ጋዜጣ ምንጮች ገልጸዋል።

አቶ ጁነዲን በአባ ዱላ ገመዳ እስኪተኩ ድረስ ከኦክቶበር 28/2001 እስከ ኦክቶበር 6 /2005 የኦሮምያ ክልል ፕሬዚዳንት ነበሩ። ከዚያም የትራንስፖርትና መገናኛ ሚኒስትር በመሆን እስከ ኦክቶበር 2008 አገልግለዋል። በመቀጠልም በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትርነት ከሠሩ በኋላ በመጨረሻም በ2010 የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር በመሆን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊን መንግሥት አገልግለዋል። የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲም የቦርድ ሊቀመንበር ነበሩ። መንግሥታቸው ብዙ ዓመት ከኖሩበት የሚኒስትሮች ካቢኔ ያሰነባታቸው የአቶ ኃይለማርያም የጠቅላይ ሚኒስትርነት ዘመን ሲጀመር ነው።

የስደት ኑሯቸውን ማቃናት የያዙት አቶ ጁነዲን ከወዳጆቻቸው ጋር ሲያወጉ “ይሄ ፋሽስት መንግሥት እኮ የሚያደርገውን አያውቅም” በሚል መገረም ሲናገሩ መደመጣቸውን ምንጮቻችን ገልጸዋል። ባለቤታቸው ወ/ሮ ሀቢባ መሀመድ “በሽብር ተግባር ተጠርጥረዋል፣  ከሳዑዲ ኤምባሲ ገንዘብና መጽሐፍት ይዘው ሲወጡ ሐምሌ 9 ቀን 2004 እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል” በሚል ተዘውታሪ ሰበብ በእስር መቆየታቸው ይታወሳል። ከሥልጣናቸው በመስመጥ ላይ ለነበሩት አቶ ጁኒዲም ይህ የባለቤታቸው እስር ተጨምሮ ከአገር ለመኮብለል መንስኤ መሆኑ ሲዘገብ መሰንበቱ ይታወቃል። ባለቤታቸውና ልጃቸው አሁንም በኢትዮጵያ የሚገኙ በመሆኑ አቶ ጁኒዲን በይፋ ምንም አስተያየት ሳይሰጡ ተቆጠበው መቀመጡን መምረጣቸው ተነግሯል።  ሰሞኑን በኦሮምያ ክልል ተማሪዎች ላይ እየደረሰው ያለው ግድያና ሁከት በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ የሚመለከታቸው ቢሆንም፣ እንደ ተራ ሰው “ይሄ ፋሽስት መንግሥት ምን እያደረገ ነው” ብለው መገረማቸው መልሶ ማሰገረሙን ምጮቻችን ገልጸውልናል። የኦሮምያ ክልል ፕሬዘዳንት ከነበሩት ውስጥ ሀገር ጥለው የኮበለሉ ፕሬዘዳንቶች ከአቶ ሀሰን ዓሊ ጋር አቶ ጁነዲን ሲደመሩ ሁለተኛ መሆናቸው ነው። ሁለቱም አትላንታ መሆናቸው ሲገለጽ አቶ ጁነዲን በአንድ ዩኒቨርስቲ መምርህነት ሥራ ለማግኘት ማመልከቻ ማስገባታቸውም ተነግሯል።ምንጭ (ዘኢትዮጵያ)

Wednesday, May 14, 2014

“አማራንና አማርኛን ማጥፋት የህወሃት ፕሮግራም ነው”

አማርኛ ተናጋሪዎችን የማመናመን፣ የማደህየት፣ የማራቆትና ክልላቸውን እያሳነሱ የማጥፋት እቅድ በህወሃት መርሃግብር ውስጥ የተካተተ ዋና ተግባር እንደሆነ ተገለጸ። አማርኛ ቋንቋንም ማሽመድመድ የዚሁ እቅድ አካል መሆኑ ተዘግቧል።
አቶ ገ/መድህን አርአያ ከኢሳት ሬዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ በህወሃት ፕሮግራም ገጽ 18 አካባቢ “አማራ የትግራይና የኤርትራ ህዝብ ጠላት እንደሆነ ተመልክቷል” ብለዋል፡፡ አያይዘውም አማራ ማጥፋት የቅስቀሳው ዋና መሳሪያ ቢሆንም የትግራይ ህዝብ አልተቀበለም ብለዋል። ቅስቀሳውን አንቀበልም ያሉ “የትግራይ ሸዋ” ተብለው መገደላቸውን ይፋ አድርገዋል።
በተለይ የድርጊቱ ዋና አስተባባሪ በማለት የጠቀሷቸው አቶ መለስ ዜናዊ፣ አቶ ስብሃት፣ አቶ ስዩም መስፍን፣ አቶ አባይ ጸሐዬን የጠቀሱት አቶ ገ/መድህን፣ በ1972 በሰሜን ጎንደር የዘር ማጥፋት ወንጀል መፈጸሙን አጋልጠዋል። በወቅቱ የተካሄደው ጭፍጨፋ ከፍተኛ የዘር ማጥፋት ወንጀል እንደሆነም አመልክተዋል። “በሰላም እጃቸውን የሚሰጡ ወታደሮች እንኳ አማርኛ የሚናገሩ ከሆነ ይረሸኑ ነበር” ሲሉ እነ መለስ ያለቸውን በዘር ላይ የተመሰረተ ቆሻሻ አመለካከት አጋልጠዋል።
“ኢትዮጵያ የምትበተነው አማራ ሲጠፋ ነው” በሚለው የነመለስ ሃሳብ መተግበር የጀመረው ህወሃት አዲስ አበባ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ መሆኑንን ያወሱት አቶ ገ/መድህን፣ ህወሃት ያሰማራቸው ከ350ሺህ በላይ ካድሬዎች ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ አማራዎች በተለያዩ ምክንያቶች እንዲጨፈጨፉ ማድረጋቸውን አመልክተዋል።
ብአዴንን “አማራን ለማጥፋት የተፈጠረ፣ ጸረ አማራ ድርጀት” ሲሉ የሰየሙት አቶ ገ/መድህን፣ አመራሮቹ የኤርትራና የትግራይ ተወላጆች መሆናቸውን በርግጠኛነት ተናግረዋል። የትግራይ ህዝብ የተወከለው “በባንዳ ልጆችና የኤርትራ ተወላጆች ነው” ሲሉም ህዝቡ አደጋ ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል። የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ አባይ ወልዱን “የባሻ ወልዱ ልጅ ነው” በማለት የትግራይ ህዝብ በባንዳ ኤርትራዊ ልጅ እንደሚመራ ያመለከቱት አቶ ገ/መድህን፤ ብርሀነ ገብረክርስቶስ፣ ቴድሮስ ሃጎስ፣ ቴድሮስ አድሃኖም፣ በማለት በመዘርዘር የባንዳ ልጆች መሆናቸውን ይፋ አድርገዋል።
“አማራው የሚኖርበትን መሬት በመውሰድ መሬቱን ያጠቡበታል፣ ከሌላው ክልል በማባረር የሚኖርበትን ክልል ያጠቡታል” ያሉት አቶ ገ/መድህን፣ ይህ የሚደረገው ከመጀመሪያው እንዲጠፋ የተወሰነበትን ህዝብ አጥብቦ በማፈን በችግር ለመግረፍና ለመቆጣጠር ተብሎ እንደሆነ ገልጸዋል።
ዘር የማጥራት የህወሃት የቀደመ ድርጅታዊ መዋቅር እንደሆነ በማመልከት መለስን የጠቀሱት አቶ ገ/መድህን፣ “አማራውን ዝም ካልነው አያስቀምጠንም” የሚለው የመለስ መፈክር አካል የሆነው የቤኒሻንጉል ክልል ርምጃ የህወሃት ቤት ስራ እንደሆነ አረጋግጠዋል። አማራውን ፋታ ማሳጣት፣ ማንገላታት፣ ስነልቦናውን መግፈፍ ህወሃት በፕሮግራም ደረጃ የያዘው እቅድ ስለሆነ ወደፊትም እንደሚቀጥል አቶ ገ/መድህን ተናግረዋል።
“ሞት መፍራት አያስፈልግም። የተቀደሰ ሞት መሞት ክብር ነው” ሲሉ በቃለ ምልልሳቸው መጨረሻ የተናገሩት የቀድሞው የህወሃት የፋይናንስ ሃላፊ ህዝቡ ተባብሮ ህወሃትን ማስወገድ ካልቻለ ማፈናቀሉና መሰደዱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስጠንቅቀዋል።
ምንጭ www.goolgule.com

ቦኮ ሐራም የተጠለፉ ሴት ተማሪዎችን የእስረኛ ልውውጥ መሣሪያ ሊያደርጋቸው ነው

ሴቶችን በተለይም ታዳጊዎችን ጠልፎና አግቶ የሚፈልጉትን ለማግኘት በመደራደሪያነት መያዝ የተለመደ አይደለም፡፡ ዓለምም እንደዚህ ዓይነቱን ክስተት እምብዛም አስተናግዳ አታውቅም፡፡
ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም በቀውስ ውስጥ የሚገኙ አገሮችን ቀድሞ የሚረዳው ሴቶችና ሕፃናትን ነው፡፡ ከየትኛውም አስቸጋሪ ሁኔታም ለመውጣት ትኩረት የሚያገኙት ቀድመው ነው፡፡
ናይጄሪያ ግን ሰሞኑን ዓለምን ያነጋገረ ክስተት አስተናግዳለች፡፡ ላለፉት 12 ዓመታት የናይጄሪያ መንግሥትን ለመጣል ሲዋጉ የከረሙት የጽንፈኛው የቦኮ ሐራም ታጣቂዎች ከወር በፊት ያገቷቸውን ከ300 የማያንሱ ሴት ተማሪዎችን በመንግሥት ለታሰሩባቸው አባላቶቻቸው ልዋጭ ድርድር አቅርበዋቸዋል፡፡ 
በክርስትናም ይሆን በእስልምና አስተምርሆ ሴትን ማሰቃየትም ሆነ ማጉላላት የተከለከለ ነው፡፡ እስልምናን በናይጄሪያ አስፋፋለሁ፣ እስላማዊ መንግሥትም እመሠርታለሁ ለሚለው ቦኮ ሐራም ግን ይህ በተግባር አልታየም፡፡ ይልቁንም ሴት ተማሪዎችንና እናቶችን እየጠለፈ ለእስረኛ ልዋጭ እየተደራደረባቸው መገኘቱ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችንና ኃያላን መንግሥታትን አስቆጥቷል፡፡ 
ቦኮ ሐራም ከዚህ ቀደም በሽምቅ ውጊያ የናይጄሪያን መንግሥት ሲፈታተን ቢቆይም፣ አሁን ሥልቱን በመቀየር ሴቶችን ማደን ተያይዞታል፡፡ ከአንድ ወር በፊት ከአዳሪ ትምህርት ቤት የጠለፋቸውን 276 ሴት ተማሪዎች ‹‹ለባርነት እሸጣቸዋለሁ›› ብሎ ዓለምን ያስደመመው ቦኮ ሐራም፣ በያዝነው ሳምንት ባሰራጨው የቪዲዮ መልዕክት ‹‹ተማሪዎቹን አስልሜያቸዋለሁ›› ብሏል፡፡ አብዛኞቹ ክርስቲያን ተማሪዎች እንደነበሩ፣ ከተጠለፉ በኋላ በተሰጣቸው የእስልምና ትምህርትም ወደ እስልምና እንደተቀየሩም የቦኮ ሐራም መሪ አቡበከር ሽካው ተናግሯል፡፡ 
አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ባሰራጨው የቦኮ ሐራም የቪዲዮ መልዕክት ተማሪዎቹ ሥፍራው በግልጽ በማይታወቅ አረንጓዴ ቦታ ላይ በሂጃብ ተሸፋፍነው ታይተዋል፡፡ አምላካቸውን በዓረብኛ ቋንቋ ሲያመሠግኑም ተሰምተዋል፡፡ 17 ደቂቃዎች በሚፈጀውና በሐውሳና በዓረብኛ ቋንቋዎች የቪዲዮ መልዕክት የቦኮ ሐራም መሪ ላለፉት አምስት ዓመታት በእስር ቤት ውስጥ የሚገኙት አባላቶቹ ከተለቀቁ ሴቶቹን እንደሚለቅ አስታውቋል፡፡ 
የሴቶችን መማርና የምዕራባውያንን ትምህርት የማይቀበለው ቦኮ ሐራም በትምህርት ቤት የሚገኙ ሴቶችን ከመጥለፍ ባለፈም፣ በገጠር የሚገኙ እናቶችንም እየጠለፈ መሆኑ ተነግሯል፡፡ 276 ሴት ተማሪዎችን ከወር በፊት ከጠለፈ በኋላ በቡርኖ ከተማ የሚገኙ 11 ሴቶችን በድጋሚ ጠልፏል፡፡ አሁንም ሴቶችን የሚጠልፍ መሆኑንም በይፋ አሳውቋል፡፡ 
ቦኮ ሐራም ትምህርት ቤት የሚሄዱ ሴቶችን እንደሚጠልፍ ካስጠነቀቀ በኋላ፣ የዋራብ ነዋሪ የሆኑት አብዱላሂ ሳኒ መሣሪያ የታጠቁ የቦኮ ሐራም ሸማቂዎች ሴቶችን ፍለጋ ቤት ለቤት እንደሚያስሱ ተናግረዋል፡፡ 
‹‹በአካባቢያችን ምንም ጥበቃ የለም፡፡ መሣርያ የታጠቁት ሸማቂዎች ሴቶቻችንን ሊወስዱ ሲመጡ መስጠት ነው፡፡ የሚያስቆማቸው የለም፤›› ብለዋል፡፡ 
በ12 እና በ15 ዓመት ዕድሜ ውስጥ የሚገኙ ሴቶችን ከአካባቢው የጠለፉ ሲሆን በጠለፋው ወቅት ግን እንዳልተኮሱና ማንንም እንዳልገደሉም እማኞች ተናግረዋል፡፡ ዓላማቸውም ሴቶችን ጠልፈው መሄድ ብቻ መሆኑ ተነግሯል፡፡ በናይጄሪያ ጦር ከይዞታቸው ያፈገፈጉት የቦኮ ሐራም አባላት ሌሎችን ሳይጎዱ ሴቶችን ብቻ እየጠለፉ መሄዳቸው ሥልት በመቀየር ትኩረት ለመሳብ መሆኑም ተነግሯል፡፡ 
ቦኮ ሐራም በሴት ተማሪዎችና በእናቶች ላይ የሚያደርገው ጠለፋና በደል በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እየተወገዘ ነው፡፡ ኃያላን መንግሥታትም ናይጄሪያ የቦኮ ሐራምን ድርጊት እንድትገታ ድጋፍ መስጠት ጀምረዋል፡፡ 
የሴት ተማሪዎችን መጠለፍ ‹‹ልብ የሚሰብር›› በማለት ለኤቢሲ መግለጫ የሰጡት የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ፣ ጊዜው ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ተባብሮ ተማሪዎቹንና ናይጄሪያን ከችግር የሚያላቅቅበት ነው ብለዋል፡፡ 
የአሜሪካ መንግሥት የተጠለፉትን ናይጄሪያውያት ለመታደግ ባለሙያዎቹን ከመላኩ በላይ፣ ከናይጄሪያ መንግሥት ባገኘው ፈቃድ መሠረት ቦኮ ሐራም ሴቶቹን ያግትባቸዋል የሚባሉ ሥፍራዎችን በሙሉ በሳተላይት በመታገዝ ቅኝት እያደረገ ይገኛል፡፡ 
አሜሪካ ከጦር ኃይሏ፣ ከሕግ አስከባሪዎችና ከተለያዩ ኤጀንሲዎች የተውጣጣውን ቡድን ወደ ናይጄሪያ የላከች ሲሆን፣ የቡድኑ አባላት ሴቶቹን ለማግኘትና ዕርዳታ ለመስጠት ሁኔታዎችን ያመቻቻሉም ተብሏል፡፡ 
በአስፀያፊ ድርጊቱ የዓለም አቀፍ ሚዲያ መነጋገሪያ የሆነው ቦኮ ሐራም በሰው ልጆች ላይ አስፀያፊ ወንጀል ሠርቷል ሲል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታውቋል፡፡ የፖለቲካ ተንታኞችም በሴቶች ላይ የተቃጣ ከባድ በደል ብለውታል፡፡ 
ከ300 ያላነሱ ሴቶችን የጠለፈው ቦኮ ሐራም ባሰራጨው የቪዲዮ መልዕክት ሴቶቹ ተረጋግተው የሚታዩ እንዲመስሉ ተደርጓል፡፡ እንዲያውም አንዷ በሸማቂዎቹ ምንም ጉዳት እንዳልደረሰባቸው ተናግራለች፡፡ ባለፈው ሳምንት የወጡ ሪፖርቶች የሚያሳዩት ግን የተወሰኑት ታጋቾች ጠላፊዎቻቸውን እንዲያገቡ መገደዳቸውን ነው፡፡  
የናይጄሪያ መንግሥት ሴቶቹ ከትምህርት ቤት ሲጠለፉ አፋጣኝ ዕርምጃ ባለመውሰዱ እየተወቀሰ ነው፡፡ ትንሽ እንቅስቃሴ ማድረግ የጀመረውም የቦኮ ሐራም የመጀመርያው የቪዲዮ መልዕክት ከተለቀቀና ሸማቂዎቹ ‹‹ሴቶቹን በገበያ ቦታ እሸጣለሁ›› ካለ በኋላ ነው፡፡ 
ይህንን ተከትሎ አሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ፣ ቻይናና እስራኤል የፕሬዚዳንት ጉድላክ ጆናታንን መንግሥት ለመርዳትና ታጋቾቹን ለማስለቀቅ ድጋፍ ማድረግ ጀምረዋል፡፡
አገሮቹ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን ተጠቅመው ታጋቾቹ የሚገኙበትን ለማወቅ እያሰሱ ናቸው፡፡ ቦኮ ሐራም በበኩሉ፣ ‹‹ሴቶቹን የምታገኙት የናይጄሪያ መንግሥት ያሰረብንን አባላት በሙሉ ሲለቅ ነው፤›› ብሏል፡፡ የናይጄሪያ መንግሥት ደግሞ የቦኮ ሐራምን ጥያቄ ሲያጣጥለው፣ አሜሪካም ‹‹ወንጀለኞች ለሚፈጽሙት ድርጊት ማካካሻ የለም›› ስትል ተደምጣለች፡፡ ፕሬዚዳንት ጉድላክ ጆናታን ግን በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ ጫናው በርትቶባቸዋል፡፡ ቦኮ ሐራም እንዴት ሊንሰራፋ ቻለ በማለት፡፡ 
ምንጭ www.ethiopianreporter.com

Sunday, May 11, 2014

የወያኔ ጥላቻ ፍሬ "ወንጀል በዘር አይተላለፍም"

ወያኔ ለትግራይ ሕዝብ ሀብትንና ብልጽግናን አመጣ ብለው የሚያምኑ ሰዎች ብዙ ናቸው፤ ወያኔ የሥልጣን ወንበሩ ላይ በመውጣቱ ትግሬዎች ሁሉ አልፎላቸዋል ተብሎ ይታመናል፤ በተለይ በአውሮፓና በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በዚህ ላይ የጠነከረ እምነት አላቸው፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ከኢትዮጵያ ውጭ ብዙ ውይይትም ይሁን ንትርክ ይደረጋል፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ግን የተፈራ ርእስ ነው፤ ውስጥ-ውስጡን እንጂ አደባባይ አይወጣም፤ ይህንን ጉዳይ በኢትዮጵያ ውስጥ አደባባይ ለማውጣት ጊዜው የደረሰ ይመስለኛል፤ አረጋዊ በርሄ፣ ገብረ መድኅን አርአያ፣ አስገደ ገብረ ሥላሴ፣ አብርሃ ደስታ (አሥር ቢሞሉልኝ ደስ ይለኝ ነበር!) እየደጋገሙ ቢያነሡትም ሌሎች በቁም-ነገር የተቀበሉት አይመስልም፤ ሕዝቡ ግን በራሱ መንገድ እየተናገረና ምስክርነቱን እየሰጠ ነው፤ በመቀሌ የተሠራውን የመኳንንት መንደር ሕዝቡ አፓርቴይድ ብሎ ሲሰይመው፣ በአዲስ አበባ የተሠራውን መንደር መቀሌ ብሎ ሲሰይመው እየመሰከረ ነው፤ “የለሁበትም!” እያለ ነው።
የትግራይ ሕዝብ መደህየቱ አልበቃ ብሎት ሲለምንም እየተሳቀቀ ነው፤ የሚለምነው ትግሬ ለብዙ ሰዎች ትግሬና ወያኔ አንድ መስሎ እንደሚታየው ያውቃል፤ አብዛኛው ሰው በወያኔ ላይ ያለውን ስሜት ያውቃል፤ ስለዚህም ሲለምን ሰዎች በወያኔ ላይ ያላቸውን ስሜት ስለሚያራግፉበት እየተሸማቀቀ ነው፤ አንድ የትግራይ ቄስ ከአርሲ ነኝ አሉኝና ለምን እውነቱን አይናገሩም ስላቸው እውነቱን ስናገር የማገኘው ስድብ ብቻ ነው አሉኝ፤ እኒህ ሰው ምን በወጣቸው የወያኔን ኃጢአት ተሸካሚ ይሆናሉ፤ በሌላ በኩል ደግሞ በትግሬነቱ የተጠቀመ አለ፤ እኔ የማውቀው የደርግ ወታደር የነበረ ትግሬ ቆስሎ ከውትድርና ወጣና በአንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤት የጥበቃ ሥራ ላይ ነበር፤ በጣም ይቸግረው ነበር፤ ሚስቱ ሕመምተኛ ነበረች፤ የቤት ኪራይ መክፈል ይቸገር ነበር፤ ዛሬ ግን የሚለብሰው ልብስ ሌላ ነው፤ ከኑሮውም ተርፎ ለሲጃራና ለጫት እያወጣ ነው፤ ወይም ሌሎች እያወጡለት ነው፤ ትግሬነታቸው ብቻ እንዲህ የደላቸው በጣም፣ በጣም ጥቂቶች ናቸው፤ ስለዚህም በወያኔ አገዛዝ ትግሬ ሁሉ ተጠቅሞአል ማለት ከጉልሁ እውነት ጋር የሚጋጭ ስሕተት ነው፤ አብርሃ ሰዎች ትግሬ ሁሉ ተጠቃሚ ሆኗል ሲሉ ‹‹ያመኛል›› ማለቱ ይገባኛል።
ወያኔ ትግሬ በመሆኑ ብቻ ትግሬ ሁሉ ዕዳ አለበት ማለት እንደወያኔ ማሰብ ነው፤ ወንጀል በዘር አይተላለፍም፤ እያንዳንዱ ሰው ለሠራው ሥራ ሁሉ ኃላፊነትን ይወስዳል፤ ጊዜው ሲደርስ ውጤቱንም ለመቀበል ይገደዳል፤ ይህ የሚሆነው ሰው ሁሉ በመንፈሳዊ ኃይል በጎ መንፈስ አድሮበት፣ አእምሮው በትምህርት ተገርቶ በትክክል ማሰብ ሲችል ነው፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ አሁን በአለበት ሁኔታ በጎ መንፈስ የራቀው ይመስላል፤ አእምሮም ጭራሹኑ በእኩይ መንፈስና በጥላቻ እየዛገ ነው፤ ስለዚህ ያስፈራል፤ በደቡብ ሱዳን ሁለት መቶ ሰዎች በዘር ተለይተው ታረዱ ሲባል ያስፈራል፤ በናይጂርያ፣ በኮንጎ የሚካሄደውን የዘርና የሃይማኖት እልቂት ስንሰማ ያስፈራል፤ በ1997 ዓ.ም. መለስ ዜናዊና አዲሱ ለገሰ እንዳስታወሱን የሩዋንዳ የጎሣ እልቂት በብዙ ሰዎች አእምሮ ውስጥ አለ፤ የቅርብ ተኳሽ የሆነው የአግዓዚ ጦርም አድፍጦ መጠበቅ ያስፈራል፤ ሌላውም ይህንን አውቆ አድፍጦ መጠበቁ ያስፈራል፤ ሰማይ ጠቀስ የሠሩት፣ የሥልጣን ኃላፊነትን ችላ ብለው በሥልጣን የሚነግዱና የሚከብሩት፣ የማይኖሩበትን ሕንጻ የሚክቡት፣ ከሕዝብ ጋር ያላቸው የአይጥና የድመት ኑሮ ያስፈራል፤ አቶ አስገደ ወያኔ መደንገጡን ይነግረናል፤ መደንገጥ የማይቆጣጠሩት ፍርሃት ነውና አደጋ ያመጣል፤ አደጋው አደጋን ይጠራል፤ ይህም ያስፈራል።
በትግራይ ዙሪያ ያለው ምንድን ነው? የትግራይ ሕዝብ በየትኛው አቅጣጫ ነው አንደልቡ እየተዘዋወረ ለመሥራትና ለመኖር የሚችለው? ወያኔ የትግራይን ሕዝብ ከሰሜን ከወገኑ ከኤርትራ ሕዝብ ጋር ደም አቃብቶታል፤ በደቡብ-ምሥራቅ ከወሎ መሬት ቆርሶ የወሎን ሕዝብ ቂም አስቋጥሯል፤ በደቡብ-ምዕራብ ከጎንደር መሬት ቆርሶ የጎንደርን ሕዝብ ቂም አስቋጥሯል፤ የራስን ወገኖች አስቀይሞ ሱዳንን በመሬት ለመደለል የሚደረገው ጥረት ሁሉ ፋይዳ የለውም፤ ሱዳን ለራሱም ያልበጀ አገር መሆኑ እየታየ ነው፤ ወደፊት ደግሞ ይበልጥ ይታያል፤ በትግራይ ውስጥ ደግሞ ወያኔ የፈጠረው አፓርቴይድ የወያኔን የኑሮ ደረጃ ወደሰማይ ሲያስጠጋው፣ የቀረውን ወደአንጦርጦስ የደሀነት ገደል ውስጥ ከቶታል፤ በዚህም ምክንያት በአዲስ አበባ ከተማ ከነልጆቻቸው እየተዘዋወሩ የሚለምኑ ሞልተዋል፤ ይህ ልመናም ለወያኔ ለመገበር ነው፤ ብዙዎቹ እንደሚናገሩት የሚለምኑት የማዳበሪያ ዕዳቸውን ለወያኔ ለመክፈል ነው።
ወያኔ ከሀያ ዓመታት በላይ አፍንጫ እየያዘ ያስከፈለውን የሚመልስበት ጊዜ እየተቃረበ ነው፤ ጥያቄው ወያኔ እንዲመልስ የሚገደደው እንዴት ነው? የሚል ነው፤ጥላቻ ወደንዴት፣ ንዴት ወደቁጣ ተለውጦ ሲገነፍል ምጽዓት ደረሰ ማለት ነው፤ ሁሉም ሰው ራቁቱን ይሆናል፤አንደአውሬ ከጥፍሩና ከጥርሱ በቀር ሌላ መሣሪያ አይኖረውም፤ ሰው ሁሉ በክፋት ወደአውሬነት ይለወጣል፤ ጠመንጃና ቦምብ አያገለግሉም፤ ሕንጻው ምሽግ አይሆንም፤ መኪናው፣ ባቡሩ፣ ታንኩ ከቆመበት አይነቃነቅም፤ የትም አያደርስም፤ ጭፍራ ሁሉ በየራሱ ፍዳ ታንቆ እንኳን ለሌላ ሊተርፍ ለራሱም የማይበቃ ይሆናል፤ ለነገሩ ጌታና ሎሌም የለም፤ ሁሉም በአውሬ እኩልነት የተፋጠጠ ነው፤ ርኅራኄ ተሟጦ፣ መግል ያዘለ ልብ ፈርጦ፣ ውይይትና ክርክር አብቅቶ፣ ጥርሱን ያገጠጠና ጥፍሩን የሳለ መንጋ በደም የሚራጭበት ሁኔታ ነው።
ሌላ አገር እንዲህ አልሆነም፤ እዚያ አገር እንዲህ አልሆነም፤ የሚባል ነገር የለም፤ እኛ ዘንድ ሌላ ነው፤ የኢትዮጵያ ደሀዎች እንባ የእግዚአብሔርን ሰማይ አጨቀየው!
“ክፋት እንደእሳት ይቃጠላል፤ ኵርንችቱንና እሾሁን ይበላል፤ ጭፍቅ የሆነውንም ዱር ያቃጥላል፤ ጢሱም ተትጐልጕሎ እንደዓምድ ይወጣል፤ በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ቁጣ ምድር ተቃጥላለች፤ ሕዝቡም እሳት እንደሚበላው እንጨት ሆኖአል፤ ሰውም ለወንድሙ አይራራም፤ ሰው በቀኙ በኩል ይነቅላል፤ ይራብማል፤ በግራም በኩል ይበላል፤ አይጠግብምም፤ እያንዳንዱም የክንዱን ሥጋ ይበላል፤ ምናሴ ኤፍሬምን፣ ኤፍሬምም ምናሴን ይበላል፤…” ኢሳይያስ 9/18-21
ፕ/ር መስፍን ወልደ-ማርያም፤ ሚያዝያ 2006
ምንጭ www.goolgule.com

Saturday, May 10, 2014

የሲዊዘርላንድ መንግሥት ረዳት አብራሪውን ለኢትዮጵያ አሳልፎ እንደማይሰጥ አስታወቀ Switzerland rejects Ethiopia's gov't request to extradite co-pilot Hailemedhin Abera

የኢትዮጵያ መንግሥት ከሦስት ወራት በፊት አውሮፕላን በመጥለፍ ጄኔቭ ያሳረፈው ኃይለመድህን አበራ ተላልፎ እንዲሰጠው ያቀረበውን ጥያቄ የሲዊዘርላንድ መንግሥት እንዳልተቀበለው ተጠቆመ።
ቪኦኤ የስዊዘርላንድ የፍትህ ሚኒስቴር ቃል አቀባይን ጠቅሶ ሰሞኑን እንደዘገበው የኃይለመድህን ጉዳይ በሕግ ሂደት ላይ መሆኑን ጠቅሶ ረዳት አብራሪውን ለኢትዮጵያ አሳልፎ ለመስጠት የቀረበለትን ጥያቄ የስዊዝ መንግሥት አልተቀበለውም። ቃልአቀባዩ ለዚህ የሰጡት መልስ ስዊዘርላንድ እና ኢትዮጵያ ወንጀለኞችን አሳልፎ ለመስጠት የሚያስችል ስምምነት አለማድረጋቸውን ነው።
በየካቲት ወር 2006 ዓ.ም አጋማሽ የበረራ ቁጥር ET702 የተመዘገበና ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነው ቦይንግ 767 አውሮፕላን በ31 ዓመት ወጣት ረዳት አብራሪው ኃይለመድህን አበራ ተጠልፎ የጉዞ መስመሩን በመቀየር ጄኔቭ ኤርፖርት ካረፈ በኋላ ጉዳዩ በዓለም አቀፍ ደረጃ መነጋገሪያ ሆኖ መቆየቱ የሚታወስ ነው።
በወቅቱ ስለሁኔታው መግለጫ የሰጡት የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትር አቶ ሬድዋን ሁሴን ረዳት አብራሪ ኃይለመድህን አበራ ለኢትዮጵያ ተላልፎ እንዲሰጥ የሲዊዘርላንድ መንግሥትን ለመጠየቅ መንግሥታቸው ማቀዱን መጥቀሳቸው የሚታወስ ነው።
ረዳት ፓይለት ኃይለመድህን አበራ በሌለበት በአገር ውስጥ ክስ የተመሠረተበት መሆኑም አይዘነጋም።
Source sodere.com

Monday, May 5, 2014

በደቡብ ኮሪያ የሚኖሩ የኢትዮጵያውያን መልእክት ያምማል! አፍንጫን ሲመቱት ዓይን ያለቅሳልና!

እኛ የኦጋዴን፣ የኣማራ፣የኦሮሞ፣የትግራይና የደቡብ ብሄር ተወላጆች ኣዲስ ኣበባን ለማስፋፋት በሚል ሽፋን በኣዲስ ኣበባ ዙሪያ
የሚገኙ ድሃ የኦሮሞና ሌሎች ገበሬዎችን ግፍ በጥብቅ የምናወግዝ ሲሆን በቅርቡ በሃረማያ፣ በኣምቦ እና በሌሎች ኣካባቢዎች
የሚኖሩ የኦሮሞ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ላይ የኢትዮጵያ መንግስት የወሰደውን ግድያና በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን
ሊገልጹ በወጡ ተማሪዎች ላይ እየተወሰደ ያለውን የድብደባና የማጉላላት ዘመቻ በጥብቅ እናወግዘዋለን። ገዳዮቹም የጊዜ ጉዳይ
እንጂ በፍትህ ፊት ቀርበው የእጃቸውን እንደሚያገኙ ኣንጠራጠርም።

እኛ ኢትዮጵያዊያን ልብ ልንል የሚገባው ጉዳይ ባለፉት ዘመናት እንደታዘብነው የኢህዓዴግ መንግስት ሲያሻው ብሄር እየለየ
ሲያሻው በጅምላ ሰላማዊና ለውጥ ፈላጊ ዜጎችን ሲያሰቃይ ሲገድል ቆይቱኣል። ኣንዴ ኦሮሞን፣ ኣንዴ ደቡብ ሲዳማን፣ ኣንዴ
ኣማራን፣ ኣንዴ ኦጋዴንን፣ኣንዴ ጋምቤላን ወዘተ ሲያጠቃ ተላላ ሆነን የተጠቃው ቡድን ብቻ ለብቻው ትንሽ ጮሆ ዝም ስለሚል
የግፉ ጊዜ ሊረዝምብን ችሏል። ኣሁን ግን የኢትዮጵያ ህዝብ የመንግስትን የከፋፍለህ ግዛው ዘዴ ሊነቃበትና ኣፍንጫን ሲመቱት
ኣይን ያለቅሳል እንደሚባለው ኣንዱ ሲጠቃ ሌላውም ሆ! ብሎ በመነሳት ይህንን ኣስከፊና በዓለም የሌለ ብሄርተኛ ኣገዛዝ
ኣሽቀንጥሮ መጣል ይገባዋል።በሌላ በኩል የኦሮሞ ወገኖቻችን ያነሱትን የፍትህ ጥያቄ ለማጣመምና ብሄርን ከብሄር ለማጋጨት
የኢህዓዴግ ካድሬዎች ሊሯሯጡ እንደሚችሉ እየተገነዘብን ይህንን ጉዳይ የኦሮሞ ተማሪዎች ይስቱታል ብለን ኣናምንም። መንግስት
በተለይ በኣሁኑ ሰዓት የቀለም ዓብዮት ሊነሳብኝ ይችላል የሚል ትልቅ ስጋት ስላለበት ህዝቡን በሃይማኖትና በብሄር በመከፋፈልና
ከፍተኛ የሆኑ የፍትህና የዴሞክራሲ ጥያቄዎች በጋራ እንዳይነሱ ስለሚፈልግ ብሄርተኝነትንና ጠባብነትን ለብሶ እንደለመደው
እያጋጨ በስልጣን ለመቆየት መፍጨርጨሩ ኣይቀርምና በማናቸውም ተቃውሞዎቻችን ውስጥ ለወያኔ እድል ፈንታ መስጠት
የለብንም።

በሌላ በኩል ለውጥ ለማምጣት የሚታገሉ ዴሞክራት የፖለቲካ ፓርቲዎችም ቢሆኑ ኣንድ ብሄር ተለይቶ ሲጠቃ ሁሉን
የማንቀሳቀስና ለጋራ ትግል ቆራጥ የጥሪ ደወል የማሰማት ሃላፊነት ኣለባቸው ብለን በጽናት እናምናለን።

የጀግናው ብእረኛ እስክንድር ነጋ ነገር፣ በቅርቡ ደግሞ ወደ ዘብጥ የወረዱት የዞን ዘጠኝ ጦማሪያንና ጋዜጠኞች ጉዳይ እንቅልፍ
የነሳን ጉዳይ ነው። እነዚህ ወጣት የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን በሰፊው እስር ቤት የሚገኘውን የኢትዮጵያን ህዝብ የነጻነት እጦት ኑሮ
ተምሳሊት ኣድርገው ይንቀሳቀሱ የነበሩ ለጋ ወጣቶች ወደ እስር ቤት መውረዳቸው ከሰፊው እስር ቤት ወደ ጠባቡ መግባታቸውን
ከማሳየቱም በላይ የታሰሩት ግለሰቦቹ ብቻ ሳይሆኑ ኣላማቸው በመሆኑ ሌላው የዞን ዘጠኝ እስረኛ የሆነው ኢትዮጵያዊ ሁሉ
መንግስት የነጻነት ጥያቄውን ወደ ወህኒ መወርወሩን የሚያሳይ በመሆኑ ምን ያህል መንግስት በጭካኔ ስራው ሊቀጥል እንደ ወሰነ
ያሳያል። በመሆኑም የነዚህ ወገኖች መታሰር፣ የፖለቲካው ምህዳር ምን ያህል እየጠበበ መምጣቱን፣ መንግስት ለህዝቡ ያለው
ንቀት ጫፍ መርገጡን ያሳያል። በመሆኑም ሁሉም ኢትዮጵያዊ በብሄርና በሃይማኖት ሳይከፋፈል የኦሮሞ ወገኖቻችንን ወቅታዊ
ጥያቄና የጋዜጠኖቹን እስር ጉዳይ ወደ ኣጠቃላይ ፍትህና ዴሞክራሲ ጥያቄ ከፍ ኣርገን በያለንበት እንነሳ :: ዴሞክራሲና ፍትህ
ሲሰፍን ጥያቄዎቻችን ሊፈቱ ይችላሉና ኢትዮጵያዊያን በጋራ ለለውጥ እንድንነሳ ወገናዊና ወንድማዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ!
የማትከፋፈል ኢትዮጵያን ለትውልድ እናሳልፋለን!
በደቡብ ኮርያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ድምጽ



ኢትዮሚድያ - Ethiomedia.com
May 4, 2014