(ዘ-ሐበሻ) የአረና ለትግራይ ፓርቲ በትግራይ ክልል የተለያዩ ከተሞች ሕዝብን የማነቃቃስ ስብሰባዎችን በመጥራትና በማወያየት ላይ የሚገኝ ሲሆን በሚያደረጋቸው ሰላማዊ እንስቃሴዎች በሕወሓት ካድሬዎች ፈተና እየገጠመው ይገኛል። ዛሬ ከወደ አዲግራት የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው በፌስቡክ፣ በትዊትር እና በተለያዩ ድረገጾች ላይ “አብርሃ ደስታ ከመቀሌ” እያለ የሚዘግበው መምህር ድብደባ ተፈጽሞበታል።
አረና ፓርቲ ነገ እሁድ ጁላይ 26 ቀን 2014 በአዲግራት ከተማ የጠራውን ሕዝባዊ ስብሰባ ለሕዝብ ለማስተዋወቅ በከተማዋ በሚንቀሳቀሱበት ወቅት በሕወሓት ካድሬዎች በተደራጁ በተባሉ ወጣቶች “ሕዝብ መቀስቅሳችሁን አቁሙ” በሚል ጥቃት የተፈጸመባቸው አሰገደ ገብረ ሥላሴ፣ አምዶም ገብረስላሴና አብርሃ ደስታ ላይ ሲሆን በአብርሃ የደረሰው ድብደባ ከፍተኛ ጉዳት ባያደርስም አቶ አሰገደ እና አንዶም ወደ ሃኪም ቤት ተወስደው ህክምና እንደተደረገላቸው ለዘ-ሐበሻ የደረሱት መረጃዎች አመልክተዋል።
በተያያዘ ዜና በተጨማሪ የአዲግራቱን ስብሰባ ለማስተጓጎል ሕወሓት ወታደሮችን በማሰማራት የአረና ሰዎችን በማሳሰር ላይ እንደሚገኝ የደረሰን ዜና አመልክቶ ለማሰር የቀረበው ምክንያትም “ሕዝብ በስብሰባ እንዲሳተፍ ቀስቅሳችኋል” በሚል ነው።
ከዚህ ቀደም የአረና አባላት በተንቤይን ሕዝባዊ ስብሰባ ጠርተው የነበረ ስሂን እዚያም እስር እና እንግልት እንደደረሰባቸው ዘ-ሐበሻ በወቅቱ መዘገቧ አይዘነጋም።
No comments:
Post a Comment