በድጋሚ የወጣ የአቋም መግለጫ፤ ድምጼን ከፍ አድርጌ እደግመዋለሁ!
እኔ ኦሮሞ ነኝ፡፡ ኦሮሞነቴን የሰጡኝ አባቴ እና እናቴ ናቸው እንጂ ከሱፐር ማርኬት ገዝቼው አይደለም፡፡ እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ ኢትዮጵያዊነቴን ያገኘሁት ከእናት እና ከአባቴ እንጂ አንዳች አካል እላዬ ላይ ለጥፎብኝ አይደለም፡፡ በኢትዮጵያዊነቴ እንደምኮራው ሁሉ ኦሮሞነቴም ኩራቴ ነው፡፡
በኢትዮጵያ በርካታ የኦሮሚያ አካባቢዎች ተዟዙሪያለሁ፡፡ የዛን ጊዜ ከ”አካም ቡልተኒ” ውጪ ምንም ኦሮምኛ አላውቅም ነበር፡፡ ነገር ግን በየባላገሩ ያሉ ኦሮሞዎች የኔ አማርኛ ተናጋሪ መሆን፤ ወይም ኦሮምኛ ቋንቋ አለመቻል አንድም ቀን አሳስቧቸው አያውቅም፡፡ ሰው በመሆኔ ብቻ አክብረው እርጎ አቅርበውልኝ፣ እርጎ የሆነ ፈገግታ ለግሰውኝ፣ ለራቸው ከሚተኙበት የተሸለ መኝታ ሰጥውኝ በእንክብካቤ ነው የሚያስተናገዱኝ፡፡
አንዳንዶች፤ ኦሮሞ ኢትዮጵያዊ አልመሆኑን ሊነገሩኝ ታሪክ እንዳነብ፣ አዋቂ እንድይቅ፣ ጸሎት እንዳደርግ ሁላ መክረውኛል፡፡ እኔ ግን ይሄንን ሁሉ ማድረግ ሳያስፈልገኝ ከኦሮሞ የሚፎካከር ኢትዮጵያዊ እንደሌለ አሁን በቅርቡ የዞርኩባቸው የኦሮሚያ ገበሪዎች አረጋግጠውልኛል፡፡ ይህንን ነገር እኔ ብቻ ሳልሆን በቅርብ የኦሮሞን ህዝብ ጠንቅቀው የሚያውቁት እነ ጀነራል ከማል ገልቹ አረጋግጠውታል፡፡ እነ አቶ ቡልቻ ደመቅሳም መርቀውታል፡፡ ለዛም ነው ዛሬ የጀነራል ከማል ገልቹ ኦነግ በስፋት ተቀባይነት እያገኝ የመጣው፡፡ ለዛም ነው ዛሬ የኦሮሞ ልጆች በአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ያሸበረቀ የኦነግ አርማን ከአረንጓዴ ቢጫ ቀዩ የሀገራቸው ባንዲራ ጋር ጎን ለጎን ይዘው በአደባባይ ስለ ኢትዮጵያ ልጆች የሚጮሁት!
ለብቻ መኖር የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ ቢሆን ኖሮ እንደ ኦሮሞ ህዝብ ጀግንነት እና ብዛት፤ ጮክ ብዬ እደግመዋለሁ እንደ ኦሮሞ ህዝብ ጀግነነት እና ብዛት፤ አርባ አመት ፈጅቶ አይኮላሽም ነበር፡፡
በአሁኑ ጊዜ የኦሮሞ ህዝብ እየተበደለ እንደሆነ ምንም ጥያቄ የለውም፡፡ በርካታ ወዳጆቼ ኦሮምኛ ተናጋሪ ስለሆኑ ብቻ ኦነግ ናችሁ ተብለው ከዩንቨርስቲ ወጥተው እስር ቤት ገብተዋል፡፡ ከስራቸው ተባረው ለስደት ተዳርገዋል፡፡ ወዘተ ተደርገው ወዘተ ሆነዋል፡፡ ልክ እንደዛ ሁሉ ግን በደሉ ሌሎችም ዘንድ አለ፡፡ አማራውም ትግሬውም አዲሳቤውም ሁሉም ቁስል አለበት፡፡
አብሮ ታክሞ አብሮ መኖር ለሁሉም ይበጃል!!!
No comments:
Post a Comment