ሰላም ፍቅሬ / ከጀርመን
ሰሞኑን በ20/06/2013 በአሜሪካ ኮንግረስ በኮንግረስ ማን የተከበሩ ሚስተር ስሚዝ ኢትዮጵያ ከመለሰ በኋላ ፦የወደፊት ዲሞ ክራሲና የሰበአዊ መ ብት በሚ ል ርዕስ በተደረገዉ የም ስክርነት ቃል ላይ የተከበሩ አም ባሳደር ያማ ማ ቶ በተቃዋሚ ዎች ዙሪያ ሲናገሩ በራሳቸዉ ስለማይተማ መኑና ስለሚፈሩ ነዉ ብለዉ መናገራቸዉን አድምጠናል።
በዚህ ጉዳይ ብዙ ማለት ይቻላል ፤ ይሁንና ለዛሬ በቅርብ የሆኑትንና በተወሰኑ ጉዳዮች ላይ ብቻ ላተኩር።
እዉነት አምባሳደር ያማማቶ እንዳሉት ፍርሃት ያለዉ በተቀዋሚ ጎራ ነዉ ፤ በህወሃት አካባቢ ነዉ ፤ ወይስ አሜሪካ የኢትዮጵያ ጉዳይ እያስፈራት መጣ?ጉዳዩን ለፖለቲካ ጠበብቶች እተወዋለሁ ።
እድሜ ለሰማያዊ ፓርቲ አምባሳደር ያማማቶ ከመናገራቸዉ በፊት ቀደማቸዉ እንጂ ሁሉንም ፈርታችሁ ነዉ ይሉ ነበር። አንድ ነገር አምባሳደር ያማማቶን ልጠይቃቸዉ ለመሆኑ ፍርሃት ዝም ብሎ ይመጣል? ከ1997 ዓ.ም ምርጫ በኋላ ኢትዮጵያ ውስጥ ህዝቡ ግንባር ግንባሩን እየተባለ ሲገደል ባያዩ እንኳን አልሰሙም ?ታዲያ አሁንስ ህወሃት ጥቅሞቹ እንዳይነኩበት ለ39 ዓመታት ያከማቸዉን የጭካኔ ልምድ የሰማና ያየ ለምን አይፈራ ?
ግን እኮ አምባሳደር ያማማቶ እዉነታቸዉን ነዉ፤ ከፍርሃት ዉጡና ታገሉ ማለታቸዉ እንደሆነስ? ካለ ትግል ድል የለምና ከፍርሃት ወጥቶ መ ታገል የድል መሰረት በመሆኑ ጥቆማቸዉ ዋናና ጠቃሚ ጉዳይ ነዉና በጥሩ ጎኑ ብናየዉስ?
የኢትዮጵያ መንግስት ለ8ዓመታት በግዳጅና በማስፈራራት ይዞት የቆየዉን የሰላማዊ ሠልፍ ፍቃድ ክልከላ ሳይወድ በግድ መፍቀዱን መንግስትና ሰማያዊ ፓርቲ ባሳዩት እንቅስቃሴ ለማወቅ ችያለሁ።
ሠማያዊ ፓርቲ የተከበሩ አምባሳደር ያማማቶ በዚሁ የምስክርነት ቃል ላይ የተናገሩትን አስቀድሞ ያወቀ ይመስላል። ምክንያቱም ፓርቲዉ ምንም ፍርሃት ሳይገባዉ ህወሃት/ ኢህአደግን ብቻ እያስፈራራ ሰላማዊ ሰልፉን አድርጓል። ከሰልፉም ፍርሃቱ የቱጋ እንዳለ አሳይቷል።
ህወሃት/ ኢህአደግ ግን ይፈራል?።አዎ ይፈራል። ህወሃት ለምን ይፈራል? የስንቶች የንጹሃን ደም በእጁ አለ፣ሰንቶችን አስለቅሷል፣ ስንቶችን አሳብዷል፣ ስንቶችን የአልጋ ቁራኛ አድርጓል፣ ስንቶችን ንጹሃን ከመቃብር በታች አድርጓል። ስንቶችን በዘር መሰረታቸዉ አሳድዷል ፣ ከቦታቸዉ አፈናቅሏል፣ንብረታቸዉን ነጥቋል፣አለጥፋታቸዉ አስሯል። ስንት በኢትዮያውያን ህዝብ ስም የመጣ ሃብትና ንብረት ተበዝብዟል፤በዚህም ሰንቶች ህወሃቶች ሃብት አጋብሰዋል።እነዚህ ብቻ አይደሉም ህወሃት የሰራቸዉ ሃጥያቶችና ወንጀሎች ብዙ ናቸዉ ።
ሌላ ህወሃት የሚፈራበት ነገር አለ ወይ? አዎ። ምን?ይህ ዘመን አምባገነኖችን ያንቀተቀጠ ዘመ ን መሆኑና አምባገነኖችን እረፍት መንሳቱ አንድ ቀን ለእነሱም እንደማይቀር ስለገባቸዉ ፤ በአረቡ አለም የወደቁት አምባገነኖች የነበራቸዉ ትጥቅ ከህወሃት ትጥቅ በላይ መሆኑና ያላዳናቸዉ መሁኑን ህወሃት ጠንቅቆ ስለተረዳ፤ በሌሎችም አገሮች ለምሳሌ በአሁኑ ወቅት በብራዚል እና በቱርክ ህዝብ ምን ሊያመጣ እንደሚችል ስለሚያስረዳቸዉና የህዝብን ብሶት መሳሪያ እንደማይገድበዉ ህወሃት ስለተማረ።
ታዲያ ምን ያስፈረዋል? ለምን አያስፈራ? ህዝቡ ትግሉን ወደ ከፍተኛ ደረጃ ካደረሰዉ ለህወሃት ትልቅ አደጋ ስለሆነ ነዉ ።
ህወሃትን አሁን የሚያስፈራዉ የኢትዮጵያ መኖር አለ መኖር ሳይሆን ፤ የዘረፉት ንብረት ፣ በፓርቲያቸዉ ስር ያለዉ ግዙፍ የንግድ እንቅስቃሴና ሌሎች ሊያስጠብቋቸዉ የፈለጋቸዉን ፤ስዉር ዓላማዎቻቸዉን ሁሉ የሚጠራርግ ማዕበል እየመጣ መሆኑ ስለገባቸዉ ለምን አይፈሩም?
አንዳንድ ተቀዋሚ ፓርቲዎች ሰማያዊ ፓርቲ አብረን ሰላማዊ ሰልፍ እንውጣ ባለ ጊዜ ምክንያት እየደረደሩ አስቸግረዉ ነበር ይባላል።ይሁንና አሁን ከሰልፉ በኋላ ፦ይህም አለ እንዴ ? ያሉ ይመስላል።አሁንም ትግሉን መደገፋቸዉና መጀመራቸዉ ይበል የሚያሰኝ ጅምር በመሆኑሊበረታታ ይገባል።መነሻዉ የትም ይሁን የት መጀመሩ በራሱ አበረታች ነዉ ።ከፍርሃት ወጥተዋል ማለት ነዉ።
አንድነት ፓርቲ የሚሊዬኖችን ድምጽ ለማስጠበቅ በሚል መነሳታቸዉን እየሰማን ሲሆን ይህም ማነዉ ፈሪዉ የሚለዉን ለማወቅ ጊዜዉ እየደረሰ መ ሆኑንና ሰላማዊ ትግሉ ሊቀጥል እንደሆነ ይታያል። እንግዲህ ህዝቡ ወደ ጨዋታዉ ሜዳ በመጠጋት ድጋፉን እንደሚሰጥ የሚጠበቅ ሲሆን፤መሪ አጣን ለሚሉም ቀጥተኛ መልስ መገኘቱ ታዉቋል።
ትግሉን ከግብ ለማድረስ ከፍርሃት ዉጭ ሆኖ ስራን መፈጸም ይጠይቃልና ከሰማያዊ ፓርቲ ትምህርት መዉሰድ የበታችነት ሳይሆን ብልህነት ነዉ።ትምህርት ትልቅ ጉልበት ይፈጥራል፤ተጨማሪም የሞራል ዝግጅት ማድረግ ያስችላልና፤በዚህ ዙሪያ ቆራጥነትንና ሌሎች የልምድ ግብአቶችን መጋራት ጠቃሚ ነዉ እላለሁ።
ለራሳችን መ ፍትሔ የምናመጣዉ በእርግጥ እራሳችን ነን፤ አንድ ትልቅ ነገር ለተቀዋሚ ዎች እመክራለሁ ። እርሱም ከየዋህነት እንድንወጣ ። በየዋህነት ህወሃትን ማሸነፍ አይቻልም ። የህወሃትን የክፋት መጠን የሚመጥን እና የሚቋቋም የትግል ስልትና አቋም ይዞ መነሳት ህወሃትንም ላይቀርለት ወደ ፍጻሜ ያቀርበዋል።
የኢትዮጵያ ህዝብም ፤ በአገር ዉስጥም ሆነ ከሃገር ዉጭ ያሉ ሁሉ ተገቢዉን ድጋፍ ለትክክለኛና ለእዉነተኛ ተቃዋሚዎች በመ ስጠት ህወሃትን ከጫንቃችን ላይ እናዉርድ ፤በዚህም የእፎይታ ዘመናችንን እናፋጥን ። ካልሆነ ግን መንግስትም የራሱን ጥላ ባየ ቁጥር ሰዉ ከሚገልና ቃሊቲ ከሚወረዉር፤ተቃዋሚም ፈርቶ በመንግስት ከሚያላክክ ፤ ህዝብም ፈርቶ የሚመራን አጣን እያለ ከሚያዝን፤ ትግሉ ይጀምር፣ይቀጥል፥ ለጥያቄዉ መ ልስ ይገኝ። ሁሉም ከፍርሃት ይዉጣ ።
ኢትዮጵያ የነጻነት ፣የዲሞክራሲና የብልጽግና አገር ትሁን።ለራሳችንና ለትዉልዳችን ጥቅም ሲባል ቢያንስ ተቃዋሚዉ ከፍርሃት ይውጣ ። በመጨረሻም ፈሪዉ ማን እንደሆነ ይታወቅ።
አም ላክ ኢትዮጵያን ይባርክ !
No comments:
Post a Comment