Sunday, June 30, 2013

ቅንነት እና መልካምነት ማስተዋል ቢኖርን ኖሮ?


  መልካምነት ከሁሉም በላይ በእለት እለት ኑሮችን ሊንፀባርቅ የሚገባው አባይ ጉዳይ ነው።
በአለማችን ላይ በመልካም ስራቸው የምናደንቃቸውና የምንከብራቸው የተለያዩ ግለስቦች አሉ መልካሙ ስራቸው
ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ በህይወት ካለፉ በኋላ ስማቸው እና ክብራቸው ከመቃብር በላይ ይውላል።
በአገራችን በኢትዮጵያ ብዙ ስራ እየስሩ ያሉ በርካታ ግለሰቦች ግዚያቸውን ጉልበታቸውን እንድሁም ዕውቀታቸውን
ብሎም ህይወታቸውን መስዋት በማድረግ ገንዘባቸውን ለወገናቸው የከፈሉ በርካታ ወድ የኢትዮጵያ ለጆች አሉ።
በግሌ ይህንሀስቤን ለመጻፍና ለመግለፁ ያነሳሳኝ ደከመኝ ስለችኝ ሳይል በተጠራበት ቦታና አገር ለወገኖቹ ፈጣን ምላሽ
እየስጠ ያለውን የኢትዮጵያዊነት ወግናዊነቱን ፍቅሩን አክብሮት እየገለፀ ያለው ውድ የኢትዮጵ ልጅ ሚስተር ኦባንግ ሜቶ።
       ከሁሉም በላይ ይዞየተነሳው ቅድስ አላማው የስውልጅ ሊኖርው የሚገባው ስባዊመብትና ፍትህ
   እኩልነት ዲሞክራሲ ከሚታገልለት አላማዎች ናቸው በተላያዩ የአለም ሀገሮች በትላልቅ መድርኮች በመገኝት በኢትዮጵያ
ያለውን የሰባዊ መብት ጥስትና ህገወጥ የመሪት ንጥቂያ ህዝቦችን ከነሩበት ቄዬ ወይም አገር ያላግባብ ሲፈናቃሉ የሚደርስባቸውን የስባዊ  የመብት ጥስት ሊደርስባቸው የሚችል የፖለቲካም ይሁን የኢኮኖሚ ችግር በአለም አደባባይ እየገልፀና
እያሳወቅ የሚገኝ ታላቅ ስው ነው ዘውትር የሚለው ታላቅ ቃል አለ ዘርኝነት ከሚጠላውና ከሚቃውምው ትልክ ነገር ነው
በአንድነትና በኢትዮጵዊነቱ የሚኮራ ምርጥ የዘመናችን ታላቅ ሰው ነው።
   የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶችም ቋንቋን መሰርት ያደርጉ የፖለቲካ ድርጅቶችም ይሁን ግለስቦችም ከወገናቸው
ኦባንግ ሜቶ ብዙ ቁም ነገሮችን መማር ይቻላል።
     ይህ ሁሉ ተሟልቶ ቢኖር ኖሮ የሀሳብ ልዩነቶቻችንን ችግሮቻችንን በመነጋገርና ዘመናዊ በሆነ መልኩ መፍታት
በተቻለ ነብር በመጠላለፍ እና በምወቃቀስ የትም እንደርስም የወያኔን እድሜ ከማርዘም በስተቀር።
    ዳዊት ወንድሙ።

Saturday, June 29, 2013

በድጋሚ የወጣ የአቋም መግለጫ፤ ድምጼን ከፍ አድርጌ እደግመዋለሁ!

በድጋሚ የወጣ የአቋም መግለጫ፤ ድምጼን ከፍ አድርጌ እደግመዋለሁ!
እኔ ኦሮሞ ነኝ፡፡ ኦሮሞነቴን የሰጡኝ አባቴ እና እናቴ ናቸው እንጂ ከሱፐር ማርኬት ገዝቼው አይደለም፡፡ እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ ኢትዮጵያዊነቴን ያገኘሁት ከእናት እና ከአባቴ እንጂ አንዳች አካል እላዬ ላይ ለጥፎብኝ አይደለም፡፡ በኢትዮጵያዊነቴ እንደምኮራው ሁሉ ኦሮሞነቴም ኩራቴ ነው፡፡
በኢትዮጵያ በርካታ የኦሮሚያ አካባቢዎች ተዟዙሪያለሁ፡፡ የዛን ጊዜ ከ”አካም ቡልተኒ” ውጪ ምንም ኦሮምኛ አላውቅም ነበር፡፡ ነገር ግን በየባላገሩ ያሉ ኦሮሞዎች የኔ አማርኛ ተናጋሪ መሆን፤ ወይም ኦሮምኛ ቋንቋ አለመቻል አንድም ቀን አሳስቧቸው አያውቅም፡፡ ሰው በመሆኔ ብቻ አክብረው እርጎ አቅርበውልኝ፣ እርጎ የሆነ ፈገግታ ለግሰውኝ፣ ለራቸው ከሚተኙበት የተሸለ መኝታ ሰጥውኝ በእንክብካቤ ነው የሚያስተናገዱኝ፡፡
አንዳንዶች፤ ኦሮሞ ኢትዮጵያዊ አልመሆኑን ሊነገሩኝ ታሪክ እንዳነብ፣ አዋቂ እንድይቅ፣ ጸሎት እንዳደርግ ሁላ መክረውኛል፡፡ እኔ ግን ይሄንን ሁሉ ማድረግ ሳያስፈልገኝ ከኦሮሞ የሚፎካከር ኢትዮጵያዊ እንደሌለ አሁን በቅርቡ የዞርኩባቸው የኦሮሚያ ገበሪዎች አረጋግጠውልኛል፡፡ ይህንን ነገር እኔ ብቻ ሳልሆን በቅርብ የኦሮሞን ህዝብ ጠንቅቀው የሚያውቁት እነ ጀነራል ከማል ገልቹ አረጋግጠውታል፡፡ እነ አቶ ቡልቻ ደመቅሳም መርቀውታል፡፡ ለዛም ነው ዛሬ የጀነራል ከማል ገልቹ ኦነግ በስፋት ተቀባይነት እያገኝ የመጣው፡፡ ለዛም ነው ዛሬ የኦሮሞ ልጆች በአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ያሸበረቀ የኦነግ አርማን  ከአረንጓዴ ቢጫ ቀዩ የሀገራቸው ባንዲራ ጋር ጎን ለጎን ይዘው በአደባባይ ስለ ኢትዮጵያ ልጆች የሚጮሁት!
ለብቻ መኖር የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ ቢሆን ኖሮ እንደ ኦሮሞ ህዝብ ጀግንነት እና ብዛት፤ ጮክ ብዬ እደግመዋለሁ እንደ ኦሮሞ ህዝብ ጀግነነት እና ብዛት፤  አርባ አመት ፈጅቶ አይኮላሽም ነበር፡፡
በአሁኑ ጊዜ የኦሮሞ ህዝብ እየተበደለ እንደሆነ ምንም ጥያቄ የለውም፡፡ በርካታ ወዳጆቼ ኦሮምኛ ተናጋሪ ስለሆኑ ብቻ ኦነግ ናችሁ ተብለው ከዩንቨርስቲ ወጥተው እስር ቤት ገብተዋል፡፡ ከስራቸው ተባረው ለስደት ተዳርገዋል፡፡ ወዘተ ተደርገው ወዘተ ሆነዋል፡፡ ልክ እንደዛ ሁሉ ግን በደሉ ሌሎችም ዘንድ አለ፡፡ አማራውም ትግሬውም አዲሳቤውም ሁሉም ቁስል አለበት፡፡
አብሮ ታክሞ አብሮ መኖር ለሁሉም ይበጃል!!!

Friday, June 28, 2013

ይድረስ ለኢትዮጵያው ሥውር መንግሥት

ይነጋል በላቸው

ከአቶ መለስ ዜናዊ ሞት በኋላ ኢትዮጵያን ማን እየገዛ እንደሆነ ከግምት ያለፈ ዕውቀት የለኝም፡፡ በመለስ ጊዜም ቢሆን ሀገሪቱ በዕውር ድንብርና በነሲብ ነበር የየሚገርም አጋጣሚ ነው፡፡ በደቡብ አፍሪካ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ምዕመናንና በዚያ የሚገኙ የቤተ ክርስቲያናችን ኃላፊዎች ጸሎት በቶሎ እንዲድኑ ሲጸልዩላቸው የሀገሪቱ የሃይማኖት ታዋቂ አባትና ተከታይ ምዕመኖቻቸው ግን በሰላም እንዲያርፉ ነው ጸሎት እየተደረገ ያለው – ለኔልሰን ማንዴላ፡፡ ይህ ነገር የሥልጣኔ ልዩነት ይሁን የባህል አልገባኝም፡፡ ይህን የዜና ሽፋን ከውጪ ወደ ሀገር ውስጥ በሚሰራጭ አንድ የተቃውሞው ጎራ ቴሌቪዥን አማካይነት እየተከታተልኩ ነኝ – ልክ አሁን፡፡ በመሠረቱ ከ94 ዓመታት ምድራዊ የሥጋ ለባሽ ሕይወት በኋላ አንድ ብዙ የሕይወት ውጣ ውረድ ያሳለፈና በእሥርም ብዙ የተሰቃዬ ሰው ዕድሜ እንዲረዝም መመኘት ከፍቅር ብዛት የሚመነጭ የዋህነት ይመስለኛል፡፡ በጀመርኩት ሃሳብ ትንሽ ልቆይና ወረድ ብዬ በዚህ ላይ እንደመጠቅለያነት እመለስበታለሁ፡፡
… በመለስ ጊዜም ቢሆን ሀገሪቱ በዕውር ድንበርና በነሲብ ነበር እስትንፋሷ ውሎ እሚያድረው፡፡ ሰውዬው የሚፈልገው ሁሉ እዛው ባለበት እየቀረበለትና እንደአንበሣ በብረት አጥር ውስጥ እየኖረ በስልክና በደብዳቤ ሲገዛንና ሲሸጠን ኖረ፤ ፈጣሪ በወደደው ሰዓት ያን የእፉኝት ልጅ ወሰደ፡፡ ጦስ ጥንቡሱ ግን አሁንም እንደገነነ አለ፤ መቃብር ውስጥ ሆኖ በመግዛት መለስ አንደኛ ሣይሆን አይቀርም፡፡ ይቺ ራዕይ የሚሏት ሀገርን የማጥፋት ተልእኮ በየወያኔው ጭንቅላት ውስጥ ሠርፃ ገብታ እነሱንም እኛንም ዕረፍት ነስታለች፡፡ አዳሜ እየተነሣ “ከመለስ ራዕይ ጋር ወደፊት!” ይላል፡፡ “ራዕያቸው ምን ነበር?”ተብሎ ሲጠየቅ በቅጡ የሚመልስ የለም፡፡ የፈረደበት የአባይ የሚሌኒየም ይሁን የሕዳሴ ግድብ አለ፡፡ እሱው መሰለኝ ትልቁ ራዕይ፡፡ በሌሎች ሀገሮች እዚህና እዚያ የተትረፈረፈ የወንዝና የኩሬ ግድብ እኛ ሀገር ሲደርስ ብርቅ ሆኖ ሰውን በመዋጮና በተስፋ ቁንጣን እየገደለ ነው፡፡ ራዕዩ ይሄው ነው፡፡ በተረፈ በሚሊዮኖች ላብና ደም ጥቂት ቅንጡ ሀብታሞችን የመፍጠር ራዕይ ካልሆነ በስተቀር፣ ለብዙ አሠርት ዓመታት ተከፍሎ በማያልቅ ብድር መንገድና ሕንጻ መሥራት ራዕይ ካልሆነ በስተቀር፣ ይበልጡን ለፖለቲካ ፍጆታ በሚመስል መልኩ የሀገርን ሀብት ለተወሰኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች በማዋል በአነስተኛና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞችና በኮብል ስቶን ሥራ አደራጅቶ ዜጎችን በጥቅም መከፋፈል ራዕይ ካልሆነ በስተቀር፣ ለዕይታ ሳይቀር የሚዘገንን የኔቢጤ (ለማኝ)፣ ወፈፌና ሰካራም፣ ብስጩና ግልፍተኛ፣ በረንዳ አዳሪና የዐዋቂና ሕጻናት ሴተኛ አዳሪዎችን በየዋና ዋና ከተሞች በብዛትና በስፋት ማምረት በልዩ ራዕይነት ካልተመዘገበ በስተቀር የመለስ ራዕይ ብሎ ነገር የሚጨበጥ ነገር አላየሁም – በዋና ራዕይነት እንዲመዘገብለት ከተፈለገ ዋናው የመለስ ራዕይ የተከፋፈለችና የደከመች፣ ለኤርትራ በምንም መንገድ የማታሰጋ ጥንጥዬ ኢትዮጵያን በሂደት መፍጠር ነው – ይሄ የሚታየው ብልጭልጭ ነገርና የዕድገት እመርታ የሚመስል የፎቅና የአስፋልት ወይም ሌላ የመሠረተ ልማት ዝርጋታ ሁሉ መለስ ሳይወድ በግዱ በሥሩ ባሉ ጥቂት ሀገር ወዳድ ወያኔዎች አማካይነት የተከሠተ – ‹ከሬዲቱ› ለርሱ ብቻ የሚሄድ ሳይሆን ለማለት ነው- በመለስ የጥፋት ራዕይና በአፈጻጸሙ መካከል እንደሳይድ ኢፌክ ሊቆጠር የሚችል አጋጣሚ ነው፡፡ ምን ማለቴ ነው – መለስ ኢትዮጵያን በማጥፋት ሂደት ተጠምዶ ሳለ ያን ሂደት ተዓማኒነት እንዲኖረው ለማድረግ ኢትዮጵያዊ መስሎ መታየት ወይም ማታለል ስላለበት ለዚያም ሲባል አንዳንድ የሚታዩና የሚጨበጡ ነገሮችን ማድረግ ስለነበረበት በኢትዮጵያዊ ስብዕና ዓለም አቀፍ አመኔታን ለማግኘት ሲል ባልጠበቀው ሁኔታ ከእጁ ሾልከው ክፉ ገጽታውን በጥሩ ቅባት ያዋዙለት አጋጣሚዎች ነበሩ ወይም ናቸው(ለዚህም ይመስላል ብዙ ኢትዮጵያውያን በዚህ ሰው ‹ምትሃት› ተወናብደው የወያኔን ትክክለኛ ተፈጥሮ እንዳያውቁ የተደረገውና ዐይናቸው በወያኔ ጥፋት ላይ እንዳያማትር እንዲያውም በሀገር ውስጥም ከሀገር ውጪም የርሱ ነገረ ፈጅ እስከመሆን እንዲደርሱ የተሞከረውና አሁን አሁን ደግሞ እየቆጫቸው መምጣቱን እየተገነዘብን ያለነው…) ፡- በሕክምና አነጋገር ለጉበት የወሰድከው መድሓኒት ኩላሊትህን ሊጎዳ ይችላል – ኔጌቲቭ ሳይድ ኢፌክት፡፡ ለራስ ምታት የወሰድከው መድሓኒት ከጨጓራ ህመምህ ሊፈውስህ ይችላል – ፖዚቲቭ ሳይድኢፌክት፡፡ የመለስም የአባይ ግድብና ሌላው ግርግር ሁሉ ከዚህ መሠረታዊ እውነት ያለፈ አይደለም፡፡ እውነተኛ የሕዝብ ፍቅርና የሀገር መውደድ ስሜት ቢኖረው ኖሮ… ታውቁት የለ – ምን ወደዚያ ውስጥ ከተተኝ … ፡፡ ይቅርታ – በዋናው የሃሳብ መስመሬ ላይ እንደአረብ ጣቢያ ጣልቃ እየገባ ኳርት የሚለዋውጥብኝና እንድዘባርቅ የሚያደርገኝ ዘርፈ ብዙው የሀገራችን ችግር በመሆኑ ታገሱኝ፡፡
ኢትዮጵያን በአሁኑ ወቅት እያስተዳደረ ያለው ማን ነው? የት ተቀምጦ? በስምና በአካል ይታወቃል ወይ? ብለን እንጠይቅ፡፡
እኔ በግል እንደምታዘበው ኢትዮጵያን በአሁኑ ወቅት እያስተዳደራት የሚገኘው ሰው አይመስለኝም፤ መንፈስ ነው፡፡ ይህ መንፈስ ግማሹ ቅዱስ ነው፤ ግማሹ ደግሞ እርኩስ ነው – አሁንም በኔ ዕይታ፤ ዕይታየ ትክክል ነው ትክክል አይደለም የኔ ጉዳይና የናንተ የኅሊና ፍርድ ነው፡፡
ቅዱስ ያልኩት በተከመሩብን ሁለንተናዊ የፖለቲካና ማኅረሰብአዊ ችግሮች የተነሣ እርስ በርስ ተበላልተን እንዳናልቅ እየረዳን ያለ አንዳች ኃይል መኖሩን ከመገመት ባለፈ ስለማምን ነው፡፡ ይህ ኃይል ባይኖር ኖሮ በሀገሪቱ እንደሚታየው ጭቆናና የኑሮ ውድነት አንድም ሰው በአንጻራዊ ሰላም ከቤት ወጥቶ ወደቤት በሰላም ባልገባ ነበር – እውነቴን ነው የምለው ይህን ዓይነት ደግ መንፈስ ባይጠብቀን ኖሮ ተበላልተን ለማለቅ የሚፈጅብን ጊዜ ሰዓታትን ብቻ በወሰደ ነበር(ሦርያንና ሊቢያን… ያዬ ይፍረድ – ሊያውም ከኛ በእጅጉ ያነሰ ጭቆናና እንግልት ደርሶባቸው!) ፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠረው በረንዳ አዳሪ፣ ሥራ አጥና ቤት አልባውም በ”ሰላም” ካደረበት ከየቱቦውና ከየላስቲክ ቤቱ ወጥቶ በቀጣዩ ቀን በየአደባባዩ ባላየነው ነበር፡፡ ካለአንዳች አለሁህ ባይ የመንግሥት መዋቅር በራሱ ኃይልና እንዲሁ በኪነ ጥበቡ ርሀብና ችግሩን ችሎ የሚኖር ሕዝብ ማየት የሚገርምም የሚሰቀጥጥም በድንቃ ድንቅ መዝገብ ሊመዘገብ የሚገባውም የሚሌኒየሙ ተዓምር ነው፡፡ አንድም ሥራና አንድም ደመወዝ የሌለው በሚሊየን የሚገመት ዜጋ ቀኑን አለበቂ ምክንያት እዚህና እዚያ ሲንከራተትና ሲንገላወድ ውሎ አሁንም ልድገመውና በየሥርቻውና በየሥርጓጉጡ በ”ሰላም” አድሮ የቀጣይዋን ዕለት ጀምበር ለማየት እባቡር መንገዱ ላይ ተሰጥቶ መታየቱ የትንግርትን እንጂ የመንግሥትን ኅልውና አያመላክትም፡፡ በዚህ ምክንያት የሀገራችንን በትረ ሥልጣን ከያዙ ሥውር ኃይሎች ውስጥ የተወሰነውን ‹የፓርላማ ወንበር› የተቆናጠጠው አንዳች የተቀደሰ ነገር መሆን አለበት ብዬ አምለሁ፡፡ እንዲያ ባይሆንማ ማን እየተዘባነነ ማንስ በችግር አለንጋ እየተገረፈ በርሀብና በጥም እየተሰቃዬ ይኖር ነበር? ሀሰት ነው?
በሌላ በኩል የሚታየውን መቋጫ የሌለው የግፍ አገዛዝና የዘረኝነት ቱማታ ስንቃኝ ከነዚህም ጋር የሚቆራኘውን አጠቃላይ የድቀት ሕይወት ስንታዘብ በተለይ በፖለቲካውና በሃይማኖቱ አመራር ረገድ የእርኩሱ መንፈስ ምን ያህል የበረታ እንደሆነ መረዳት አይቸግርም፡፡ ስለዚያም ምክንያት ይመስለኛል ይህ በመለስ የሙት መንፈስ የሚነዳ የአጋንንት መንጋ አንዳች ሥፍራ ተደብቆ ደህና ሰው ወደ አመራር ዝር እንዳይል እነአዜብንና በረከትን እየተመሰለ በላያችን ላይ የሚያንዣብብብን፡፡ እንደሚወራው አዜብ ወደ አዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ምክትል ሆና አይደለም ጽዳትና ዘበኛም ሆና ብትመጣ እንኳን ምን ሊፈጠር እንደሚችል አስቡት፡፡ በሌላ ቦታ እያለች የማዘጋጃ ቤት ሹሞችን በስልክ እያስፈራራችና በአካል እያስጠራች ስንትና ስንት ግፍና በደል መፈጸሟ እየታወቀ አንድያውን በዚያ ቢሮ ስትገኝማ ከተማዋን ብቻ ሣይሆን እኛን ነዋሪዎቹን በጅምላና በችርቻሮ ባወጣንበት ዋጋ ቸብችባ በጥቂት ወራት ውስጥ ትጨርሰናለች፡፡ አዜብ – ዮዲት ጉዲት – እንኳንስ ማዘጋጃ ቤት ገብታ በሩቅ እያለችም – ለብልግናየ ይቅርታና – ለውሽማዋም ይሁን ለምትፈልገው ማንኛውም ሰው ቦታ ለማሰጠት፣ መብራት ለማሰጠት፣ የንግድ ፈቃድ ለማሰጠት፣ (እንዳስፈላጊነቱ ተመላሽ ሊደረግ ወይ ላይደረግ የሚችል) የባንክ ብድር ለማሰጠት፣ በመንግሥት ወጪ ረጃጅም የስልክና የውኃ መስመር ለማዘርጋት፣ የፈለገችውን ለማሾም ወይም ለማሻር፣ ንጹሕን ሰው ካለበደልና ጥፋቱ ዘብጥያ ለማስወረድ፣ በጥፋቱ የታሠረን በቅጽበታዊ ጣልቃ ገብነት ለማስለቀቅ፣ የዜጎችን ሀብትና ንብረት በሕግ ሽፋን ለማዘረፍና ለራሷ ካምፓኒዎች ወይም ለመሰላት ለማሰጠት፣ በነባርና አዳዲስ የአክሲዮን ካምፓኒዎች ራሷን በአባልነትና በቦርድ ሰብሳቢነት ለማስገባት፣ ወዘተ. ታደርገው የነበረውና አሁንም ከማድረግ የማትመለሰው አቅል ያጣ ሩጫ በሕዝብ ዘንድ የታወቀ ነው፡፡ ሴትዮዋ ለገንዘብና ለእንትን ሲሏት ገደል እንደምትገባ የሚያውቋት ይመሰክራሉ – አጉል ተፈጥሮ፤ ከምን ዓይነት ሥጋና ደም ተፈጥራ ይሆን ወገኖቼ? በዚህ ዓይነቱ ለከት የሌለው የገንዘብና የሀብት ፍቅሯ ነው እንግዲህ ሰውዬውን ቤተ መንግሥት ውስጥ እንደውሻ አሥራ በርሱ ስምና በርሷ ድፍረት ባጠራቀመችው ንዋይ ከዓለም መሪዎች መለስን በሀብት የሚበልጠው እንዳይገኝ ከፍተኛ ጥረት ላይ የነበረችው – በየባንኩ ብዙ ገንዘብ ታቁር የነበረችው፣ በየዓለም ማዕዘናት ብዙ ቤቶችንና የንግድ ተቋማትን ትመሠርት የነበረችው፣ በፍቅረ ንዋይ መታወሯ እንዳንዳች እያደረጋት እንዲያ ዐይን ባወጣ መንገድ ትዝብት ላይ ወድቃ የነበረችው፡፡ ይህች በገንዘብና በእንትን ፍቅር ያበደች የድብቁ ቢግ ብራዘር ተወዳዳሪ ሴት አዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ብትገባ ምን ተዓምር ልትሠራ እንደምትችል ገምቱ – የምን መገመት ነው – ፍንትው ብሎ እየታዬ! የስንቱን ቤት እንደምታፈናቅልና ባወጣ እንደምትሸጥ፣ ስንቱን የኪስ ቦታ እንደምትቸበችብ፣ እንደ አንደኛው ባሏ ‹የዐይናችሁ ቀለም አስጠላኝ› እያለች ስንቱን ምሥኪን ሰው ከሥራና ከደመወዝ እንደምታግድ፣ እንደምታሳስርና ደብዛ እንደምታስጠፋ፣ ስንትና ስንት የሀገር ማፈሪያ ወንጀልና የቁጭ በሉ አሣፋሪ ድርጊቶችን እንደምትሠራ፣ ስንቱን ኮበሌ ካልተኛኸኝ እያለች ከትዳሩና ከጤናማ ኑሮው እንደምታፈናቅል (“አሮጊት ለምኔ! ገንዘብና ሥልጣን ባፍንጫየ ይውጣ!” ብሎ አሻፈረኝ የሚልን መቀመቅ እንደምታወርድ)፣ … በበኩሌ ቁልጭ ብሎ ይታየኛል – እባካችሁን ‹ህልም እልም› ብለን ሁላችን እናማትብበት፡፡ አዜብ ብሎ ከንቲባ? ወያኔ ይህን ካደረገ በርግጥም ራሱን ለማጥፋት ከምንጊዜውም በላይ ቁርጠኛ አቋም ላይ ደርሷል ማለት ነው፡፡ ይህችን የአጋንንት ውላጅ የባንዳ ልጅ ማሳረፍ ይገባል – በሰላም፡፡ በቃ – በመለስ ቀብር እንዳለችው ልጆቿን በማሳደግ ፈተና ላይ ብቻ ታተኩርና በዚያው ትታይ፡፡
አዜብ በሌብነቷ አይደለም ሹም አትሁን እያልኩ የምከራከረው፤ በሌብነቷ ከሆነ መብቷ ነው፡፡ ዓለማችን በሌቦችና አጭበርባሪዎች የተሞላች በመሆኗ የርሷ ሌባ መሆን እንግዳ ነገር አይደለም – በአመራርም ሆነ በተራ ዜጋነት ሌባና አጭበርባሪ ሀገር ምድሩን ሞልቶታል፡፡ አዜብ በተፈጥሯዊ ደመ ሞቃትነቷና ያንንም ተከትሎ በጉልህ ስለሚንጸባረቅባት የሴሰኝነት ጠባይዋ አይደለም ሹም እንዳትሆን የምመኘው፡፡ ያም መብቷ ነው – ካልሰለቻት እንኳንስ ነባር ታጋዮችን አዳዲሶቹንና እምቦቀቅላ ታጋዮችንም ታነባብራቸው፡፡ አዜብም ሆነች ቤቲ በተፈጥሮ የተሰጣቸውን መብት እስከፑንት (ላንድ) ቢጠቀሙበት የነሱ ጉዳይ እንጂ የማንም ራስ ምታት ሊሆን አይገባም፡፡ እኔን ክፉኛ የሚያሳስበኝ ድንበር የማያውቀው ውሸቷ ነው፡፡ በተራ ቃል ‹ውሸታም› መባል በፍጹም አይመጥናትም፡፡
በባህር ዳሩ የወያኔ ስብሰባ የተናገረችው ውሸት ስለሷ ባሰብኩ ቁጥር ስለእውነት በጣም ያመኛል፡፡ በዚያ ስብሰባ ‹መለስ ከዓለም መሪዎች በደመወዙ ብቻ ቤተሰቡን እያሰቃየ የኖረ ብቸኛው መሪ ነው፤ ከስድስት ሺ ብር ደመወዝ ለኢሕአዲግ ተቆርጣ በምትደርሰው አራት ሺህ ምናምን ብር ወርን ከወር እየጣጣፍን በመከራ ሲያኖረን የነበረና አእምሮውን ብቻ ይዞ የተወለደ… ይህ ሊሠመርበት ይገባል ፤ ሰው የሚለው አይደለም – እርሱ በዚያች ትንሽ ደመወዝ ብቻ ኖሮ ያለፈ የተለዬ መሪ ነው…› እያለች የቀላመደች ዕለት ስለርሷ ጨረስኩ፡፡ ስለርሷ ብቻም አይደለም፡- ስለወያኔ/ኢሕአዴግም ያኔውን ጨረስኩ፡፡ አንድ አንጋፋ ድርጅት ያን የመሰለ በሬ ወለደ ዓይነት ነጭ ውሸት ሰምቶ እርምጃ አለመውሰዱ ገርሞኛል – የዚያን ድርጅት የለዬለት ባዶነትም አረጋግጫለሁ፤ የሴትዮዋ ንግግር እውነትነት ቢኖረውም እንኳን የሀገርንና የድርጅትን ምስል በማጠየም ረገድ ቀልማዲት ያደረገችው ነገር እጅግ ሰቅጣጭ በመሆኑ በሕይወት የመኖርን መብት ሳይጨምር ከብዙ ነገር ልትታገድ በተገባት ነበር፡፡ ሕዝብ በሆነ ምክንያት በይሁንታ አፉን ቢለጉም እውነት እንዳይመስላቸው፡፡ ሕዝቡ በዕውቀት ከነሱ ስለሚበልጥ በዚያን ሰሞን ይህን የአዜብን የድህነት ወሬ የቡና ማጣጣሚያ ነው ያደረገው – ሳይጠማን እየጠጣን ብዙ ቡና ፈጅተንበታል – ጊዜው ሲደርስ ይህንን ኪሣራችንንም ታወራርዳለች፡፡ የዚህች ቀልማዳ ሴት ንግግር በአሣፋሪነቱና አጸያፊነቱ በሺዎች ዓመታት አንዴ እንደሚያጋጥም እጅግ ነውረኛ አነጋገር ሊወሰድ ይችላል፡፡ የርሷ ስህተት እንደግለሰባዊ ስህተት ተቆጥሮ በዝምታ ሊታለፍ ይችላል፡፡ የወያኔው ድርጅት በፍርሀት ይሁን በሌለው ይሉኝታ እርሷን በዝምታ ማለፉ ግን ይቅር የማይባል ታሪካዊ ህፀፅ ነው፡፡ ለነገሩ አሁንም ብዙም አልረፈደምና የሴትዮዋን ተፈጥሮ የምታውቁ ወያኔዎች እባካችሁን አንድ ነገር አድርጉ – ለናንተው ስትሉ፡፡ እኛ ሁሉንም ለምደነዋልና ስለኛ ብላችሁ እንደማትጨነቁ እናውቃለን፡፡ ሀፍረቱ ይበልጡን ለእናንተው ስለሆነ አዜብን ግዴላችሁም ተዋት፡፡
ቁጭ ብዬ በእርጋታ ሳስበው ሕዝብንና የታሪክ ፍርድን ንቆ ይህችን ሴት ባለሥልጣን ማድረግ የኋላ ኋላ ኢሕአዴግን ትልቅ ዋጋ የሚያስከፍለው ይመስለኛል፡፡ እናም ኢሕአዴግ ለክብሩ ሲል – ክብር ካለው ነው ለዚያውም – አለበለዚያም ውርደቱን ቅጥየለሽ ላለማድረግ ሲል ይህችን ሴት ከማዘጋጃ ቤት ሹምነት የዕጩ መዝገብ ይፋቃት፡፡ እኔ ውርድ ከራስ ብያለሁ፡፡ ሰውን መናቅ ፈጣሪን መናቅ እንደሆነ ለሃይማኖት የለሹ ወያኔ መጠቆም እፈልጋለሁ፡፡ እርግጥ ነው – በአምባገነኖች ዘንድ ማይምንና እንደጤናማ ሰው ማሰብ የማይችልን አጋሰስ መሾም የተለመደ ነው፡፡ ሲበዛ ግን ያንገሸግሻል፡፡ ሕዝብ ስቆ ቢያልፈው የውሻን ደም መና የማያስቀረው ፈጣሪ፣ አይደለም ይህችን በሰው ቋንቋ ከመናገሯ ውጪ ከውሻ ብዙም የማትለየው ሴት ትቅርና ሂትለርንና ሙሶሊንን የመሰሉ ለሰማይ ለምድር የከበዱ አምባገነኖችን አይቀጡ ቅጣት አከናንቦ በጭቁኖች መሃል አዋርዷቸዋል፡፡ ይህች መናኛ ሴትም ከወያኔ ጋር የምትዋረድበት ዘመን እየመጣ ቢሆንም ማምሻም ዕድሜ ነውና ማሰብ ያልተሳናችሁ በጣት የምትቆጠሩ ወያኔዎች ካላችሁ የዛሬን ማሩን፤ ቀድሜ እንደገለጽኩት ውርደቱ የጋራችን ነው፡፡ ይበልጡን ግን – ልድገምላችሁ – የእናንተው ነው፡፡ ሴትዮዋን መሾማችሁ የግድ ከሆነ ብትፈልጉ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጓት፡፡ ያ ቦታ ከሕዝብ የራቀ በመሆኑ አንገናኝምና እንደፍጥርጥራችሁ፡፡ አዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ግን ሺዎችን በየቀኑ የሚያስተናግድ የሕዝብ መናኸሪያ በመሆኑ ባለሥልጣናቱ የሕዝብን ቀልብ እንደነገሩም ቢሆን የሚስቡ መሆን አለባቸው፡፡ ይህች ሴት እኮ አርከበ ዕቁባይ ለሕዝብ ጥሩ ሠራ በመባሉና ሕዝብም በተወሰነ ደረጃና በግል አበርክቶው ስለወደደው በዚያ ቀንታበት ኤች አይ ቪ ሲመረመር የሚያሳየውን ቢልቦርድ በተሰቀለ በጥቂት ቀናት ውስጥ እንዲወገድና ከዕይታ እንዲሠወር አድርጋለች፡፡ የባል ተብዬው የመለስና የሚስት ተብዬዋ የአዜብ የክፋት ደረጃ እንግዲህ እስከዚህ የወረደና ከአንድ ተራ ዜጋ እንኳን የማይጠበቅ ነው – ለቅጣት መምጣታቸውን በበኩሌ አምናለሁ፡፡ ተራ ዜጋ ምቀኛና ቀናተኛ ቢሆን ምንም አይደለም፡፡ የአንድን ሀገር በትረ ሥልጣን የጨበጠ ቁንጮ ያገር መሪና ሚስቱ ግን እንዲህ ያለ በራሱ በመለስ ወራዳ የቋንቋ አጠቃቀም ለመግለጽ እንዲህ ያለ ወራዳና ልክስክስ ጠባይ ሲያሳዩ የሀገርን አጠቃላይ ውድቀት ነው በጉልህ የሚያስረዳን፡፡ ያልዘሩት መቼም አይበቅልም፡፡ የዘራነውን እያጨድን ነን፡፡
ለማንኛውም አዜብን በከንቲባነት መሾም – ምክትልም ሆነች ዋና ለውጥ የለውም – የሚያስከትለው አደጋና ውርደት ታስቦበት በጊዜ አንድ ነገር እንዲደረግ የዜግነት ጥሪየን ማስተላለፍ እፈልጋለሁ፡፡
በሌላም በኩል ይሄ ለይምሰል ያህል በብሔረሰብ ተዋጽዖ አንጻር የሚደረገው ሹመት ይቁም፡፡ ምክንያቱም አንደኛ ማንም አያምንም – ይህን ያረጀ ያፈጀ ሥልት አንቀልባ ውስጥ ያለ ጡት ያልጣለ ሕጻንም ያውቀዋልና፡፡ እኔ ለምሳሌ በደመቀ መኮንን መሾም ምክንያት አልተደሰትኩም፡፡ አንደኛውና ትልቁ ነገር እንደውሻ አጥንትና ደም አላነፈንፍም፡፡ በብቃትና በችሎታ ከሆነ ሁሉም የሚኒስትር ካቢኔ ከኮንሶና ከሙርሲ ቢሆን ሃሳቡ አይበላኝም፤ ወያኔንም የጠላሁት በመጥፎ ድርጊቱ እንጂ በተሹዋሚዎች የዘር ሐረግ አይደለም – በጭራሽ፡፡ ሁለተኛ የደመቀ መሾም ስሜትን በማይነካ የቃላት አጠቃቀም ለየዋሃን አማሮች ካልሆነ በስተቀር መሬት ላይ የፈጠጠውን ኢትዮጵያዊ እውነት ለሚረዳ ሰው ‹አማራ ተሾመልኝ!› በሚል የሚያስፈነጥዝ አይደለም፡፡ ራሱን ከጥቃት የማያድን አማራ፣ የራሱ ናቸው የተባሉ ወገኖችን ጥቃትና እንግልት ለማስቆም አንዳችም ተሰሚነት የሌለው በድንና ገልቱ ሰውዬ ተሾመልኝ ብዬ ጮቤ የምረግጥ ሞኝና ተላላ መስዬ ከታየኋቸው – አዝናለሁ – ሞኞቹ እነሱ እንጂ እኔ አይደለሁም፡፡ ደመቀን መሣይ ከረፈፍ ሆዳሞች በሥርዓቱ ውስጥ ወይነው ገብተው ሀገሪቱን ምን ያህል እየጎዱ እንደሆነ ማስታወስም ተገቢ ነው፡፡ በጣም የምወደው ኦባንግ ሜቶ ቅድም ሲናገር እንደሰማሁት ሁልጊዜም እኔ ራሴ እንደምለው ወያኔ ማለት በዘርና በቋንቋ ተወስኖ ወይም ተቀንብቦ የተቀመጠ አለመሆኑንም መረዳት ይገባል፡፡ መነሻውና አስኳል አመራሩ ከትግራይ ይሁን እንጂ ለዚህ የወያኔ ሥርዓት ማበብና ማፍራት ዋና ተባባሪዎቹ ትግሬ ያልሆኑ የተጋቦት ወያኔዎች መሆናቸውን እናውቃለን፡፡ ግን ግን “የምታሸንፈውን ምታ ቢሉት ወደ ሚስቱ ዞረ” እንዲሉ ሆኖብን አንዴ የፈረደበትን የትግራይ ሕዝብ ብዙዎቻችን እንወርድበታለን፡፡ በበኩሌ አሁን እየሆነ ባለው ነገር ሁሉ የእያንዳንዳችን ልብ ሳይሰበር ነገ ይቅርታ እንደምንባባልና አብሮነታችን ካለሣንካ እንደሚቀጥል በሙሉ ልብ አምናለሁ፡፡ ንዴትና ብስጭት የማይፈጥረው አእምሮኣዊ ምስል ባለመኖሩ ደመናው ሲጠራና እውነት ስታሸንፍ አሁን ችግር የሚመስሉን ብዙ ነገሮች ከላያችን ላይ ተገፍፈው ይጠፋሉ፤ ያለ ነገር ነው – በዚህን መሰሉ ጊዜ የሚያጋጥም ብዙ ነገር አለ፡፡ መምሰልና መሆን ስለሚለያዩ የደፈረሰው ሲጠራና የሰላም አየር በሀገራችን ሰማይ ሲያረብብ የግጭትና የሁከት እርኩሳን መናፍስት ተጠራርገው ይወገዳሉና ስለነገው ከመጠን በላይ አንጨነቅ፡፡ የወቅት ንፋስ የሚፈጥራቸው ብዙ አላፊ ክስተቶች አሉ – በኛ ብቻ ሳይሆን በየሀገሩ፡፡ ሁሉም እንደሚያልፍ መረዳትና ለዚያ በርትቶ መታገል እንደሚገባ ተረድተን በወንድማማችነትና በእህትማማችነት ተባብረን ይህን የለያየንን ቆሻሻ ሥርዓት ለማስወገድ አብረን መታል ብቻ ነው የሚያዋታን፡፡ አለጥርጥር ሥርዓቱ ይወድቃል – ችግሩ በጣም ብዙ ምናልባትም ከእስካሁኑ የከፋ ቨስጠሊታ የታሪክ ጠባሳ ሳይተው የሚወድቀው እንዴት ነው? የሚለው ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ የሁሉም ምክክር፣ ትብብርና ስምምነት ያስፈልጋል፡፡ እውነት ምን ጊዜም ከእውነት መንገድ ለማትወጣው ነገር በመለያየት አዲስ ግን በወያኔያዊ ትልምና ዐቅድ የተለወሰና በፀረ-ኢትዮጵያነት የተመረዘ ታሪክ ለማስመዝገብ የምንቻኮል ሰዎች ካለን ቆም ብለን እንድናስብ በእገረ መንገድ ጠቆም ባደርግ ደስ ይለኛል – ከወያኔ ብዙ ነገሮችን መማር እንችላለን፡፡ የሕዝቡ ችግረና ፍላጎት ይግባን፡፡ ‹ሕዝቡ ምን ይላል? ምንስ ይፈልጋል ?› ብለን እንራመድ እንጂ በየግል ፍላጎታችን የተጓዝን ተሳስተን አናሳስት፤ ታሪክም ይቅር አይለንም፡፡ መደማመጥ ለመልካም የጋራ ስኬት ጠቃሚ መሆኑን እየዘነጋን ለየህልማችን እውን መሆን በተናጠል ስንሮጥ የዓለም ፍጻሜ ተቃረበ፡፡
ማንዴላ እጅ ሆነዋል፡፡ ምናልባትም ይህች ጽሑፍ በአንዱ ድረ ገፅ ከመለጠፏ በፊት አንዳች ነገር ሊከሰት ይችላል፤ ወይም በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት ውስጥ ዜና ዕረፍታቸውን እንሰማ ይሆናል – ለነገሩ ‹እግረ ቀጭን እያለ እግረ ወፍራም ይሞታል› እንዲሉ ከማንዴላ በፊት ለምሳሌ እኔ ራሴ ልቀድም እችላለሁ፡፡ የወደፊቱን ያለማወቃችን ምሥጢር ነው ሕይወትን ትርጉም ያላት እንድትሆን ያደረጋት፡፡ ተስፋ ባትኖር ሁሉም በቁም እንደሞተ ያህል ነው – ጧት ከቤቱ በሰላም የወጣ ሰው ማታ ሬሣው ወደቤቱ ሊመለስ እንደሚችል ቢያውቅ ማንም የመኖር ጉጉት አያድርበትም – የእግዜሩም እንበለው የተፈጥሮ ጥበብ መገለጫም ይሄው ነው – ስለወደፊቱ አለማወቅ፡፡ በዚህም አለ በዚያ በማንዴላ ሁኔታ ዓለም በጭንቀት ላይ የምትገኝ ትመስላለች፡፡ ጭንቀቷ ግን ለማንዴላ ለራሱ እንዳይመስላችሁ፡፡ ምሥጢሩ ወዲህ ነው፡፡(በነገራችን ላይ ‹ድኅረ ገፅ› የምንል ሰዎች ‹ድረ ገፅ› ማለትን ብንለምድ ደስ ይለኛል፡፡ ‹ድኅረ› ማለት ‹በኋላ›(post) ማለት እንደሆነና ‹ድረ› የሚለው ቃል ግን ‹ድር› ከሚለው የአማርኛ ቃል ተወስዶና ከ‹ገፅ› ጋር ተጋምዶ ‹website› የሚለውን የእንግሊዝኛ ቃል እንዲተካ መደረጉን ምሁራን ይገልጻሉ፡፡ ዕውቀት አይናቅምና በተለይ ድረ-ገፆች እባካችሁን ይቺን ነጥብ አትናቋት፡፡ መናደድ ሲያምረኝ ከምናደድባቸው ነገሮች አንደኛዋ ይህች ነች፡፡ )
የዓለም ሕዝብ አንድ አባሉ ከ94 ዓመታት በላይ በመሬት ላይ እየኖረ እንዲሰቃይ የሚፈልግ አይደለም፡፡ ይህ ዓይነቱ ሰዎች እስከዘላለሙ እንዲኖሩ የሚፈለግበት ምኞት – ከልብ ስለመሆኑ ማወቅ ቢያስቸግርም – በብዛት የሚታየው በኛይቷ ሀገር በኢትዮጵያ ነው፡፡ የመቶ ሃያ ዓመት ሽማግሌ ሲሞት ፊት የሚነጨው በሌላ ሀገር አይደለም – በኢትዮጵያ ነው – ሊያውም ይበልጡን በአማራው አካባቢ፡፡ ባህላችን ከኛ ወቅታዊ ግንዛቤ በልጦ የሚገኝበትን ሁኔታዎች አንዳንዴ እንታዘባለን፤ ከአንዳንዴም በላይ እንዲያውም፡፡ ለዚህም ነው በዛሬዋ ውሎየ እንኳ ሁለት ተቃራኒ ጸሎቶችን የታዘብኩት – አንድ ከኢትዮጵያውያን፣ አንድ ከደቡብ አፍሪካውያን፡፡ መቼም እኛ ከነሱ በልጠን እግዜሩ ለማንዴላ የማቱሳላን ዕድሜ እንዲሰጥልን ልንጸልይ እንደማንችል ቢያንስ ኅሊናችን ያውቃል – እውነቱን እንነጋገር ከተባለ፡፡ ይህ ምን ያሳያል? ፊት ለፊት የሚታየው ባህላችን ለሰው መጥፎ የማይመኝ መሆኑንና በብዙ ነገር ከሌሎች የምንለይ ሕዝብ መሆናችንን ነው ለዓለም እያስመሰከርን የምንገኘው – ምነው እውነተኛና በምንም ዓይነት ማዕበል የማይናወጥ አቋም ባደረገልን!
ማንዴላ እንዳይሞት የምንፈልግበት ምክንያት ግልጥ ነው፡፡ ዓለማችን በሰው እጦት ምች ስለተመታች ጥሩ ሰው ስናገኝ እንደብርቅ እናየዋለን፤ ሞት እንዳይነጥቀንም እንሳሳለታለን፤ እስከወዲያውም አብሮን እንዲኖር እንመኛለን – ትውልድ ቢያልፍም ከቀጣዩ ትውልድ ጋር፡፡ ብዙ ደጋግ ሰዎች ቢኖሩን ኖሮ የዓለም ሕዝቦች ትኩረት በአሁኑ ሰዓት ያለቪዛና የትራንስፖርት ወጪ ደቡብ አፍሪካ ሄዶ ፕሪቶሪያ ሆስፒታል ዙሪያ ባልከተመ ነበር፡፡ ጥሩ ሰው ብርቅ በሆነበት ዘመን መፈጠር እንዴት መታደል ነው! መለስም እንዲያ የተንጫጫንለት እኮ የርሱን አእምሮ ይዞ የሚወለድ – እንደአዜብ አነጋገር በዓለም የአንጎል ገበያ ተመራጭ ጭንቅላት ይዞ በሺዎች ዓመታት አንዴ የሚወለድ ዐዋቂና ታዋቂ በመሆኑ ነው፡፡ እኔ ለመለስ የነጨሁት ፊት እስካሁን አላገገመም፤ የምለብሰውም ማቅ ከላየ ላይ አልወረደም፡፡ እርግጥ ነው – ይበልጡን ለክፋት ቢጠቀምበትም መለስን በዕውቀቱ መቀጣጠብ አይቻልም፤ ሰይጣን ለዘዴው ከመጽሐፍ ቅዱስ ይጠቅሳል እንደሚባል መለስም የነበረው ሁለገብ ዕውቀትና ብልጣብልጥ ተፈጥሮ ከብዙዎች መሪዎች ቢበልጥ እንጂ አያንስም፡፡ የኔነህ ሳይለኝ ቢሞትም የኔነው ማለት ወጪ የለውምና ሳልወድ በግዴ የኔነው ብዬ ብቀበለው ከሚኮሰኩሰው ኢትዮጵያዊነቱ አንጻር ብቻም ሳይሆን ከአጠቃላይ ስብዕናው የሚፈልቁ ብዙ የሚደነቁ ሰብኣዊ ተሰጥዖዎች እንደነበሩት አልክድም – አጭበርባሪው፣ አስመሳዩና መልቲው መለስ ዜናዊ፡፡ ግን ተሰጥዖዎቹን ለተንኮልና እንደሥራየ ቤት ነገርን በመጠምዘዝ ሕይወቱን ጨርሶ ዕውቀቱን ሳይጠቀምበት ሞተና ዐርፎ ዐሣረፈን፡፡ በሚስቱ ሲንገበገብ የነበረ አንድ ፈላስፋ መቃብሯ ላይ እንዲህ የሚል ጽሑፍ አስፍሯል አሉ፡- My wife lies here; let her rest in peace, so do I.
አትታዘቡኝ፡፡ በበኩሌ ማንዴላ እንዲያርፍ እጸልያለሁ – በሰላም ማረፍ ለኔ አይገባኝም – ሰው እየሞተ ምን ሰላም አለና፤ ማንዴላ በ‹ሰላም› እንዲያርፍም በ‹ሰላም› እንዲድንም ከጸሎት ጀምሮ ሁሉም ነገር ቢደረግም እስከዚች ሰዓት ድረስ አልዳነም ወይም አላረፈም፤ የዚህን ደብዳቤ የመጀመሪያ ረቂቅ ስጽፍ – አሁን ሰዓቱ ከሌሊቱ ስምንት ገደማ መሆኑን ልብ ይሏል – የማንዴላ የጤና ሁኔታ እንደሰሞኑ ሁሉ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ነው የሚገኝ፤ ከአሳሳቢነቱም የተነሣ ፕሬዚደንት ጃኮብ ዙማ ሊያደርጉት የነበረውን የሀገር ውጪ ጉዞ እስከመሠረዝ ደርሰዋል፡፡ ዕንቁ ልጃችን – ብርቅዬ የአፍሪካ ብቻ ሣይሆን የዓለማችን ልጅ ማዲባ ሲያርፍ ደግሞ ነፍሱ በማኅተመ ጋንዲና በእማሆይ ተሬዛ፣ በአብርሃምና በያዕቆብ ነፍሳት አጠገብ እንድትቀመጥ የቸሩ እግዚአብሔር ፈቃድ ይሆን ዘንድ የሁላችንንም ጸሎት እኔም በበኩሌ እጸልያለሁ፡፡ ይቅርታችሁን – ቀደም ብዬ ማዲባን በአንቱታ የጠራሁት ብዙ ሰው ያለው እኔስ ለምን ይቅርብኝ ብዬ ከሰው ለመመሳሰል ነው፤ ስጨርስ በአንተ የጠራሁት የሕዝብ ሰው አንቱ እንደማይባል ስለምረዳ የአንጀቴን ነው – የሕዝብ ሰው ማለት ደግሞ የሚፈቀርና የሚወደድ ማለት ነው፡፡ አብንና ወልድን ማን አንቱ ይላል? ቅድስት ማርያምንስ? ኧረ መለስ ዜናዊንስ ማን በአንቱታ ጠርቶት ያውቃል? የሕዝብ ሰው ማለት እንዲህ ነው – ቺንዋ አቼቤ A man of the people የሚል ርዕስ ለአንድኛው መጽሐፉ የሰጠው እኮ ለነማንዴላ ዓይነቱ መላ ሕይወታቸውን ለራሳቸው ጥቅም መስዋዕት ላደረጉ ሣይሆን ለነመለስ ዜናዊ ዓይነቱ ለቤት ቀጋዎች ለውጭ አልጋዎች ነው፡፡ ዓለም ግን ምን ዓይነት የዕንቆቅልሽ ምድር ናት ጎበዝ?!
ውድ ማንዴላ ሆይ! ሁልጊዜ ከኅሊናችን አትጠፋም – በአካል ብትለየን በመንፈስ ምንጊዜም አብረኸን አለህ – ከአሁኑም ከወደፊቱም ትውልዶች ጋር፤ ፈጣሪ አንተን እንደወሰደ በምትክህ ለዓለም ሰላም የሚተጉ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ቅን አሳቢ ዜጎችን እንዲልክልን ስትሄድ አሳስብልን፡፡ አፈሩን ገለባ ያድርግልህ፡፡ የሁለት ወር ሀገርህን ኢትዮጵያንም በፈጣሪ ፊት አስባት፡፡ ስቃይና ጣር ሳይበዛብህ በቶሎ ሂድልን፡፡ በዚህች አንተን ሳይቀር ለ27 ዓመታት በእሥር ባንላታች የእርጉማን ምድር ከአሁን በኋላ ለሴከንድም መቆየቱ መከራና ስቃይ መጨመር እንጂ ጤናውም ጤና አይሆንህም፡፡ ሰዎች ስንባል ራስ ወዳዶች ነን፤ ‹ቆይልን› የምንልህ በአንተ ስቃይ የኛን ‹ኢጎ› ለማስደሰት እንጂ አንተ አልጋ ላይ ውለህ የመከራ ቀናትንና ሌሊቶችን በእዬዬ ማሳለፍህ፣ በድጋፍ ሰጪ የሕክምና ቴክኖሎጂ እየታገዝክ ካለ እንቅልፍ መቆየትህ አንዳችም ነገር አይፈይድልንም – ለአንተም ለእኛም፡፡ በሀገሬ ሰው ይሙት ተብሎ እንደማይጸለይ አውቃለሁ ማዲባየ – ግን ‹ይህን አለ› ተብዬ ኩነኔ መግባቱን እመርጣለሁ እንጂ ስትሰቃይ ለማየት ከእንግዲህ ቆይልን አልልህም፡፡ በቃ፡፡ በሰላም ሂድልን፡፡ ስትመጣ እንደምትሄድ ይታወቅ ነበር፡፡ እኛም በሕይወት አለን የምንል ወገኖችህም ወረፋችንን ጠብቀን እንከተልሃለን፡፡ ዱሮም መንገደኛ ፊትና ኋላ ነው መባሉም ለዚህ ነው፡፡ ይብላኝ ለኛ ግና፡፡ በጅቦችና በእሪያዎች መካከል እንደተጣልን ተለይተኸን ለምትሄደው ለኛ ይብላኝ እንጂ አንተማ ከፋም ለማም 95 የሚጠጉ ክረምቶችን ለሕዝብህ ስትል ከአፓርታይድና ከመጥፎ ግላዊ ገጠመኞችህ ጋር ስትፋለም ኖረህ አሁን በመጨረሻው ሥጋዊ ሽንፈትህ ደረጃ ላይ ደርሰሃል፡፡ በዚያች በደቡብ አፍሪካዊቷ አዜብ እንኳን ያየኸውን አበሳ ማን ይረሳዋል? ብቻ ሆድ ይፍጀው ማዲባየ፡፡ እዚያው እስክንገናኝ ደህና ሰንብትልኝ፡፡
ሰላም ለኢትዮጵያና ሕዝቧ፤ በዚህ ዓለም አቀፍ ሀዘን መጽናናት ለሚያስፈልገው ሁሉ ፈጣሪ እንዲያጽናናው እመኝለታለሁ፡፡
Short URL: http://www.zehabesha.com/amharic/?p=4791

Wednesday, June 26, 2013

ማነዉ ፈሪዉ ተቀዋሚ ወይስ ህወሃት/ ኢህአደግ?

ሰላም ፍቅሬ / ከጀርመን
ሰሞኑን በ20/06/2013 በአሜሪካ ኮንግረስ በኮንግረስ ማን የተከበሩ ሚስተር ስሚዝ ኢትዮጵያ ከመለሰ በኋላ ፦የወደፊት ዲሞ ክራሲና የሰበአዊ መ ብት በሚ ል ርዕስ በተደረገዉ  የም ስክርነት ቃል ላይ የተከበሩ አም ባሳደር ያማ ማ ቶ በተቃዋሚ ዎች ዙሪያ ሲናገሩ በራሳቸዉ  ስለማይተማ መኑና ስለሚፈሩ ነዉ ብለዉ መናገራቸዉን አድምጠናል።
በዚህ ጉዳይ ብዙ ማለት ይቻላል ፤ ይሁንና ለዛሬ በቅርብ የሆኑትንና በተወሰኑ ጉዳዮች ላይ ብቻ ላተኩር።
እዉነት አምባሳደር ያማማቶ እንዳሉት ፍርሃት ያለዉ በተቀዋሚ ጎራ ነዉ ፤ በህወሃት አካባቢ ነዉ ፤ ወይስ አሜሪካ የኢትዮጵያ ጉዳይ እያስፈራት መጣጉዳዩን ለፖለቲካ ጠበብቶች እተወዋለሁ ።
እድሜ ለሰማያዊ ፓርቲ አምባሳደር ያማማቶ ከመናገራቸዉ በፊት ቀደማቸዉ እንጂ ሁሉንም ፈርታችሁ ነዉ ይሉ ነበር። አንድ ነገር አምባሳደር ያማማቶን ልጠይቃቸዉ ለመሆኑ ፍርሃት ዝም ብሎ ይመጣል? ከ1997 ዓ.ም ምርጫ በኋላ ኢትዮጵያ ውስጥ  ህዝቡ ግንባር ግንባሩን እየተባለ ሲገደል ባያዩ እንኳን አልሰሙም ታዲያ አሁንስ ህወሃት ጥቅሞቹ እንዳይነኩበት ለ39 ዓመታት ያከማቸዉን የጭካኔ ልምድ የሰማና ያየ ለምን አይፈራ 
ግን እኮ አምባሳደር ያማማቶ እዉነታቸዉን ነዉ፤ ከፍርሃት ዉጡና ታገሉ ማለታቸዉ እንደሆነስ? ካለ ትግል ድል የለምና ከፍርሃት ወጥቶ መ ታገል የድል መሰረት በመሆኑ ጥቆማቸዉ ዋናና ጠቃሚ ጉዳይ ነዉና በጥሩ ጎኑ ብናየዉስ
የኢትዮጵያ መንግስት ለ8ዓመታት በግዳጅና በማስፈራራት ይዞት የቆየዉን የሰላማዊ ሠልፍ ፍቃድ ክልከላ ሳይወድ በግድ መፍቀዱን መንግስትና ሰማያዊ ፓርቲ ባሳዩት እንቅስቃሴ ለማወቅ ችያለሁ።
ሠማያዊ ፓርቲ የተከበሩ አምባሳደር ያማማቶ በዚሁ የምስክርነት ቃል ላይ የተናገሩትን አስቀድሞ ያወቀ ይመስላል። ምክንያቱም  ፓርቲዉ ምንም ፍርሃት ሳይገባዉ ህወሃት/ ኢህአደግን ብቻ እያስፈራራ ሰላማዊ ሰልፉን አድርጓል። ከሰልፉም ፍርሃቱ የቱጋ እንዳለ አሳይቷል።
ህወሃት/ ኢህአደግ ግን ይፈራል?።አዎ ይፈራል። ህወሃት ለምን ይፈራል? የስንቶች የንጹሃን ደም በእጁ አለ፣ሰንቶችን አስለቅሷል፣ ስንቶችን አሳብዷል፣ ስንቶችን የአልጋ ቁራኛ አድርጓል፣ ስንቶችን ንጹሃን ከመቃብር በታች አድርጓል። ስንቶችን በዘር መሰረታቸዉ አሳድዷል ፣ ከቦታቸዉ አፈናቅሏል፣ንብረታቸዉን ነጥቋል፣አለጥፋታቸዉ አስሯል። ስንት በኢትዮያውያን ህዝብ ስም የመጣ ሃብትና ንብረት ተበዝብዟል፤በዚህም ሰንቶች ህወሃቶች ሃብት አጋብሰዋል።እነዚህ ብቻ አይደሉም  ህወሃት የሰራቸዉ ሃጥያቶችና ወንጀሎች ብዙ ናቸዉ ።
ሌላ ህወሃት የሚፈራበት ነገር አለ ወይ? አዎ። ምን?ይህ ዘመን አምባገነኖችን ያንቀተቀጠ ዘመ ን መሆኑና አምባገነኖችን እረፍት መንሳቱ አንድ ቀን ለእነሱም እንደማይቀር ስለገባቸዉ ፤ በአረቡ አለም የወደቁት አምባገነኖች የነበራቸዉ ትጥቅ ከህወሃት ትጥቅ በላይ መሆኑና ያላዳናቸዉ መሁኑን ህወሃት ጠንቅቆ ስለተረዳ፤ በሌሎችም አገሮች ለምሳሌ በአሁኑ ወቅት በብራዚል እና በቱርክ ህዝብ ምን ሊያመጣ እንደሚችል ስለሚያስረዳቸዉና የህዝብን ብሶት መሳሪያ እንደማይገድበዉ ህወሃት ስለተማረ።
ታዲያ ምን ያስፈረዋል? ለምን አያስፈራ? ህዝቡ ትግሉን ወደ ከፍተኛ ደረጃ ካደረሰዉ ለህወሃት ትልቅ አደጋ ስለሆነ ነዉ ።
ህወሃትን አሁን የሚያስፈራዉ የኢትዮጵያ መኖር አለ መኖር ሳይሆን ፤ የዘረፉት ንብረት ፣ በፓርቲያቸዉ ስር ያለዉ  ግዙፍ የንግድ እንቅስቃሴና ሌሎች ሊያስጠብቋቸዉ የፈለጋቸዉን ፤ስዉር ዓላማዎቻቸዉን ሁሉ የሚጠራርግ ማዕበል እየመጣ መሆኑ ስለገባቸዉ ለምን አይፈሩም
አንዳንድ ተቀዋሚ ፓርቲዎች ሰማያዊ ፓርቲ አብረን ሰላማዊ ሰልፍ እንውጣ ባለ ጊዜ ምክንያት እየደረደሩ አስቸግረዉ ነበር ይባላል።ይሁንና አሁን ከሰልፉ በኋላ ፦ይህም አለ እንዴ ? ያሉ ይመስላል።አሁንም ትግሉን መደገፋቸዉና መጀመራቸዉ ይበል የሚያሰኝ ጅምር በመሆኑሊበረታታ ይገባል።መነሻዉ የትም ይሁን የት መጀመሩ በራሱ አበረታች ነዉ ።ከፍርሃት ወጥተዋል ማለት ነዉ።
አንድነት ፓርቲ የሚሊዬኖችን ድምጽ ለማስጠበቅ በሚል መነሳታቸዉን እየሰማን ሲሆን ይህም ማነዉ ፈሪዉ የሚለዉን ለማወቅ ጊዜዉ እየደረሰ መ ሆኑንና ሰላማዊ ትግሉ ሊቀጥል እንደሆነ ይታያል። እንግዲህ ህዝቡ ወደ ጨዋታዉ ሜዳ በመጠጋት ድጋፉን እንደሚሰጥ የሚጠበቅ ሲሆን፤መሪ አጣን ለሚሉም ቀጥተኛ መልስ መገኘቱ ታዉቋል።
ትግሉን ከግብ ለማድረስ ከፍርሃት ዉጭ  ሆኖ ስራን መፈጸም ይጠይቃልና ከሰማያዊ ፓርቲ ትምህርት መዉሰድ የበታችነት ሳይሆን ብልህነት ነዉ።ትምህርት ትልቅ ጉልበት ይፈጥራል፤ተጨማሪም የሞራል ዝግጅት ማድረግ ያስችላልና፤በዚህ ዙሪያ ቆራጥነትንና ሌሎች የልምድ ግብአቶችን መጋራት ጠቃሚ ነዉ እላለሁ።
ለራሳችን መ ፍትሔ የምናመጣዉ  በእርግጥ እራሳችን ነን፤ አንድ ትልቅ ነገር ለተቀዋሚ ዎች እመክራለሁ ። እርሱም  ከየዋህነት እንድንወጣ ። በየዋህነት ህወሃትን ማሸነፍ አይቻልም ። የህወሃትን የክፋት መጠን የሚመጥን እና የሚቋቋም የትግል ስልትና አቋም ይዞ መነሳት ህወሃትንም ላይቀርለት ወደ ፍጻሜ ያቀርበዋል።
የኢትዮጵያ ህዝብም  ፤ በአገር ዉስጥም  ሆነ ከሃገር ዉጭ  ያሉ ሁሉ ተገቢዉን ድጋፍ  ለትክክለኛና ለእዉነተኛ ተቃዋሚዎች በመ ስጠት ህወሃትን ከጫንቃችን ላይ እናዉርድ ፤በዚህም የእፎይታ ዘመናችንን እናፋጥን ። ካልሆነ ግን መንግስትም የራሱን ጥላ  ባየ ቁጥር ሰዉ ከሚገልና ቃሊቲ ከሚወረዉር፤ተቃዋሚም ፈርቶ በመንግስት ከሚያላክክ ፤ ህዝብም ፈርቶ የሚመራን አጣን እያለ ከሚያዝን፤ ትግሉ ይጀምር፣ይቀጥል፥ ለጥያቄዉ መ ልስ ይገኝ። ሁሉም  ከፍርሃት ይዉጣ ።
ኢትዮጵያ የነጻነት ፣የዲሞክራሲና የብልጽግና አገር ትሁን።ለራሳችንና ለትዉልዳችን ጥቅም ሲባል ቢያንስ ተቃዋሚዉ ከፍርሃት ይውጣ ። በመጨረሻም ፈሪዉ ማን እንደሆነ ይታወቅ።
አም ላክ ኢትዮጵያን ይባርክ 

Tuesday, June 25, 2013

በቤተመንግስት ግቢ ዙሪያ አንድ ሰው ተገድሎ ተገኘ



ሰኔ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና :-ባለፈው ሀሙስ ከጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ጽህፈት ቤት ጀርባ  ሁለተኛው በር ከ150 እስከ 200 ሜትር  ባለ ርቀት ላይ አንድ ጎልማሳ አንገቱ ተቆርጦ  መገኘቱን የአይን እማኞች ለኢሳት ገልጸዋል።  -
እማኞች እንደሚሉት  ሟቹ እድሜው ከ45 እስከ 53 የሚጠጋ ጸጉር አልባ ጎልማሳ ነው። የሟቹ የራስ ቅል  ባእታ ክሊኒክ አቅራቢያ ባለ አንድ ቦታ ላይ ተጥሎ መገኘቱን የጠቆሙት ነዋሪዎች፣ ፖሊስ በአካባቢው ተገኝቶ አስከሬኑ እንዲነሳ ከአደረገ በሁዋላ ለአስከሬን ምርመራ ወደ ሚኒሊክ ሆስፒታል እንዲወሰድ አድርጓል።
የአይን እማኞች ” አካባቢው 24 ሰአት ሙሉ በስለላ ካሜራዎች የሚጠበቅ በመሆኑ ድርጊቱ በቤተመንግስት ጠባቂዎች ካልተፈጸመ በስተቀር በሌሎች ዜጎች ተፈጽሟል ብሎ  ለማመን አስቸጋሪ ነው” ይላሉ።
በጉዳዩ ዙሪያ የሚኒሊክ ሆስፒታልንና አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንን ለማነጋገር ላለፉት 5 ቀናት በተደጋጋሚ ሙከራ ብናደርግም የሚኒሊክ ሆስፒታል ዛሬ መልስ ለመስጠት ፈቃደኛ ሲሆን፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር፣ የህዝብ ግንኙነት እና የወንጀል ምርመራ ክፍሎች ስልኮች አይነሱም። ሚኒሊክ ሆስፒታል የአስከሬን ምርመራ ውጤቱን በተመለከተ መውሰድ የሚችለው ፖሊስ በመሆኑ ፖሊስን መጠየቅ አለባችሁ የሚል መልስ ሰጥተዋል።
የአካባቢውን ሁኔታ በደንብ የሚያውቁ አንድ ሰው እንደገለጹት አስከሬኑ በተገኘበት አካባቢ፣  በምሽት  ሰዎች እንደሚይዘዋወሩ ገልጸው ግድያው የተፈጸመው ምናልባትም በጠባቂዎች ሊሆን ይችላል ብለዋል። ያም ካልሆነ ግን መንግስት በመገናኛ ብዙሀን መረጃውን ይፋ ማድረግ ይጠበቅበታል ብለዋል ግለሰቡ ።

Monday, June 24, 2013

አቶ ገብረመድህን አርአያ የዘማናችን አሉላ አባ ነጋ ተብለው በከፍተኛ ክብር ተሰየሙ

June 24, 2013
በምእራብ አውስትራሊያ በፐርዝ ከተማና አካባቢዋ ኗሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ጁን 23 ቀን 2013 ባደረጉት ልዩ ዝግጅት ታዋቂውን የነፃነት ተፋላሚና የቁርጥ ቀን የኢትዮጵያ ልጅ አቶ ገብረመድህን አርአያን የዘመናችን አሉላ አባ ነጋ በማለት በክብር ሰይመዋቸዋል። በዚህ ለእርሳቸው ታስቦ በተደረገው ልዩ የእራት ግብዣ ስነ ስርዓት ላይ በርካታ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያውያን የተገኙ ሲሆን፣ እንግዶቹ ለአቶ ገብረመድህን አርአያ ያላቸውን ልዩ ክብርና አድናቆት በየተራ እየተነሱ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል። በዚሁ መሰረትም አቶ ገብረመድህን ህወሓት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ይዞ የተነሳውን እኩይ አላማና ተግባር በማጋለጥ ያደረጉት ጉልህ አስተዋጽኦ፣ በተለያዩ የሚዲያ ዘርፎች በመረጃ የተደገፉ መግለጫዎችን እና ትምህርቶችን በመስጠት የከወኗቸው ሥራዎች፤ እንዲሁም ለእሩብ ምእተዓመታት ያህል በጽኑነት፤ በቆራጥነትና በሕዝብ ወገናዊነት መቆማቸው በምሳሌነት በጉልህ ተጠቅሰዋል።

የአማራ ህዝብ ስቃይ እንዲያበቃ ወያኔን መቅበር ይኖርብናል

 ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ያፈናቀላቸው አማሮች የመጀመሪያዎቹ የወያኔዎች የጥቃት ሰለባዎች አይደሉም። የመጨረሻዎቹም አይሆኑም። ወያኔ ከነ ጸረ አማራ ፖሊሲው በስልጣን እስካለ ድረስና በአማራ ስም አማራውን እያፈኑ፣ እየሰለሉ ከወያኔ ፍርፋሪ እየለቀሙ ለመኖር የቆረጡ ከአማራው መሃል የወጡ ከሃዲዎች አማራውን መቆጠጠር እስከቻሉ ድረስ የአማራ ህዝብ መራቆት፣ ስደት፣ ውርደት፣ ሰቆቃና ሞት የማይለዩት ህዝብ እንደሆነ ይቀጥላል።
የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ሃይል ይህን በእብሪትና በጥላቻ የተሞላ በወያኔ የሚፈጸም በአማራ ህዝብ ላይ ያነጣጠረ የባላጌዎች ጥቃት ማስቆም የሚቻለው የወያኔን እብሪት በጠመንጃ እና በተባበረ የህዝብ አመጽ ማስተንፈስ እስከተቻለ ብቻ ነው ብሎ ያምናል። እስካሁን ወያኔ በከንቱ ያፈሰሰውን የንጹሃን አማሮች ደም መፋረድ የሚቻለው ከጠምንጃ አፈሙዝ በሚወጣ እሳት ብቻ ነው ብሎ በጽኑ ያምናል። ከንፈር መምጠጥ፣ ዋይታ፣ ኡኡታ፣ ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ሰላማዊ ሰልፍና በየፈረንጅ በር ደጅ መጽናት ወያኔ የአማራን ህዝብ ቅስም ለመስበር የወያኔ እንጨት ሰባሪና ውሃ ተሸካሚ አድርጎ፣ ነጻነቱንና ክብሩን ገፎ አዋርዶ ለመግዛት የዘረጋውን መርሃ ግብር እንዲያጥፍ አያደርገውም።
ወያኔ ይሉኝታ ያልዘራበት፣ ትእግስትን እንደፍራቻ፣ አርቆ ሳቢነትን እንደሞኝነት የሚቆጥር በአማራው ላይ ቂምና ጥላቻን ሰንቆ የተነሳ ጨካኝ ድርጅት ነው። ይህን ድርጅት ስለጀግንነቱና ስለወርቅ ዘርነቱ እጅግ የተሳሳተና የተጋነነ ግምት ያለው፣ ማንም ምንም አያደርገኝም በሚል ትምክህት ተወጥሮ የሚኖር ድርጅት ነው። ከእንዲህ አይነቱ በራሱ ፕሮፓጋንዳና ከንቱ ውዳሴ ከሰከረ ድርጅት ጋር የሚደረግ ትግል ያለምንም መወላወል በከፍተኛ እልህና ጭካኔ የሚካሄድ ብቻ ነው። የአማራውን ሰቆቃ ለማስቆም ወያኔ “እዩኝ እዩኝ” እንዳለለ “ደብቁኝ ደብቁኝ” እስከሚል የሚዘምቱበት እና ክንዳቸውን የሚያሳዩት ጀግኖችን ይሻል። ከወያኔ ጋር ፊት ለፊት ተጋፍጠው ገድለው ለመሞ ት የቆረጡ የወገን ደምመላሾችን ይጠይቃል። ቤታቸውን ዱርና ገደሉን አድርገው፣ “ወተት ይሸፍታል እንኳን ሰው ሲበደል” የሚሉ ቁጡዎችን ይፈልጋል። የአማራውን ህዝብ እልቂት ለማቆም፣ የወንድ ልጅ እናት በገመድ የምትታጠቅበት፣ ልጇን አሞራ እንጂ ሰው የማይቀብርበት ሌላ ታሪካዊ ዘመን መምጣቱን ሁላችንም መቀበል ይኖርብናል።
የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ሃይል አባላት ወያኔ በአማራ ህዝብ ላይ በሚያሳየው እብሪት ተቃጥለናል። በግነናል። የእዚህ እብሪት ማርከሻ ጠመንጃ ነው፡ እሳትና አርር ብቻ ነው ብለናል። ሌላው ሁሉ አማራጭ ተፈትሿል፣ተሞክሯል፣ታይቷል ሌላ አማራጭ የለም ብለናል። የቀረው አንድ ምርጫ ነው፦:መሞ ት ወይም መግደል ። እኛ ይህን አውቀን ከያለንበት ተጠራርተን የአማራን ህዝብ በቀላሉ ልንደርስበት በምንችልበት ምድር እየተሰባሰብን ነው። የከፋህ፣ የመረረህ፣የተበደልክ በቃኝ ያልክ ና ተቀላቀለን፣ የወገናችንን የአሳርና የመከራ ዘመን ማብቃት በወያኔ ቀብር ላይ እናረጋግጥ ።
ውድመት ለአማራ ህዝብ ጠላት ለዘረኛው ወያኔ!!!!!!!!!
ድል በወያኔ ለሚረገጡ ኢትዮጵያውያን በሙሉ!!!!!!!!!!!!!
የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል
 
 


Sunday, June 23, 2013

“Millions of Voices for Freedom”: Ethiopians Standing against the Brutal Regime


“Millions of Voices for Freedom”: Ethiopians Standing against the Brutal Regime





The Unity for Democracy and Justice (UDJ), the most important opposition political party working under the narrowest political landscape of Ethiopia, has launched a “peaceful struggle campaign” with a motto——“Millions of Voices for Freedom” against the brutal regime ruling the country since 1991. Many millions of Ethiopians suffering from racial discrimination, exploitation, injustice, abject poverty, rampant human rights violations are expected to actively participate in the struggle.
In a launching press conference held on 20 June 2013, Mr. Dawite Solomon, the spokesperson of the party, called upon the people, political parties, civic organizations, the mass media, the Ethiopian diaspora and concerned members of the ruling party who give priority to the interest of the nation to take an active part and participate in the campaign. He said that it is the time to get together and struggle for freedom.
The press release of the party issued on 20 June 2013 says that the “objective of the campaign is to oppose the ever growing system of dictatorship that deprives citizens of their human and democratic rights, forces them to live in a state of fear and to sell their dignity for petty favors and privileges.” The press release further says: “we shall struggle resolutely to create a society where our basic rights are respected, power belongs to the people, citizens are not imprisoned for expressing their views freely and where justice prevails.”
According to the party, the campaign includes several peaceful activities including public discussions, signature gathering, and frequent rallies. The struggle is planned to be done throughout the country including the capital Addis Ababa.
“We have made public a document on which people will put their signatures in opposition of the Anti-Terrorism Law”, the press release says. “Along with this, we shall demand that imprisoned politicians, journalists and those who demand religious freedom be released. To translate this demand into action, we shall organize meetings and public square rallies. We shall conduct six public meetings in Addis. In the regions, we shall organize ten public meetings initially. The peaceful public demonstrations that give expression to the millions of voices to ensure freedom will involve all Ethiopians”, the press release explains.
Answering questions raised by journalists in the press conference, the Chairperson of the UDJ’s National Council, Mr. Tigestu Awolu, said that the struggle is absolutely different from those in the past. He said that it’s not spontaneous and improvised but strategically well designed in such a way which can bring about the needed changes effectively and efficiently. In line with this, different political activities are suggesting that the campaign would be successful as far as it is well organized.
Ethiopia is one of the most repressive nations in Africa, and has very poor human right records. It is a place where there is no freedom of assembly and freedom of expression. It is a place where law abiding citizens are simply imprisoned, beaten or executed; where innocents are subjected to mass arrests and theatrical charges just because they demanded for their religious freedom; where journalists are considered as enemies and their rights are completely denied and thrown into prison because they expressed their ideas freely.
Different researches show that since recent years these human rights violations coupled with widespread discrimination, corruption, unemployment, and sky rocket price inflation have made the country an intolerable prison for the majority and lead many to the fact that drastic political change is badly needed to transform the country for the better.

የዛሬውን የኢሳት ዜና






አንዳንድ የፓርላማ አባላት አዲሱን የአማራ ህዝብ ቁጥር እንደማይቀበሉት አስታወቁ

አንዳንድ የፓርላማ አባላት አዲሱን የአማራ ህዝብ ቁጥር እንደማይቀበሉት አስታወቁ

ሰኔ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና :- በማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ የሕዝብ ቆጠራ ኮምሽን በ1999/2000 ዓ.ም የሶስተኛው የሕዝብና ቤት ቆጠራ ውጤት ይፋ በተደረገበት ወቅት በተለይ የአማራ ክልል ሕዝብ ብዛት ከሌሎች ክልሎች በተለየ ሁኔታ ከትንበያው ዝቅ ብሎ ተገኝቷል በሚል በቀድሞ የፓርላማ አባላት በቀረበው ቅሬታ ላይ ኮምሽኑ ፍተሻዎችን ቢያደርግም፣ አዲስ የቀረበውንም ሪፖርት አንዳንድ የፓርላማ  አባላት ሳይቀበሉት ቀርተዋል።
የብአዴን ሊቀመንበር እና የትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን በአሁኑ ጊዜ የአማራ ህዝብ ቁጥር 19 ሚሊዮን መድረሱን፣ ከዚህ ቀደም የአማራ ህዝብ ቁጥር በ 1 ነጥብ 73 በመቶ ብቻ እያደገ መሆኑ የተገለጸው በስህተት መሆኑን እንዲሁም  ጥናቱ በጥንቃቄ ተካሂዶ በአዲሱ ጥናት መሰረት የአማራ ህዝብ ቁጥር 2 ነጥብ 4 በመቶ ማደጉን ለፓርላማ አባላቱ ተናግረዋል።
በክልሉ ውስጥ የሚታየው የህዝብ መፈናቀል ከዚህ ቀደም በጥናቱ ውስጥ አለመካተቱን የገለጡት አቶ ደመቀ፣ በአዲሱ ቆጠራ የተፈናቀሉ ሰዎች መካተታቸውን አስረድተዋል። ጥናቱን እንደገና ለማካሄድ ከመንግስት በተሰጠው ትእዛዝ መሰረት ተግባራዊ መደረጉን፣ አሁኑ ጥናት በጥንቃቄና ግልጽነት በተሞላበት መንገድ መሰራቱን አክለዋል።
የማዕከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ሳሚያ ዘካሪያ እና አቶ ደመቀ ቀድሞውንም ችግሩ የተፈጠረው ትንበያ ላይ እንደነበረ በሰፊው አስረድተዋል።
የአቅራቢዎችን ገልጻ ተከትሎ አቶ ሙጬ የተባሉ የፓርላማ አባላት የጥናቱን ውጤት እንደማይቀበሉት ገልጽ አደረጉ። ጥናቱ አሉ አቶ ሙጬ  ” የህዝብና ቤት ቆጠራ ኪሚሽን ከዚህ ቀደም የአማራ ህዝብ ቁጥር የቀነሰው ህዝቡ በበሽታ ስላለቀ ነው በማለት ለዚህ ፓርላማ ተናግሯል። ሰዎቹ በምን ሞቱ ስንላችሁ ደግሞ በኤድስ ብላችሁ መለሳችሁልን። ይህ ስህተት ነበር። የሞቱ ምክንያት ወረርሽኝ፣ ጦርነት ወይም ሌላ ሊሆን ይችላል፤ በዚህ ጊዜ ስለዚያ ጉዳይ አንስቶ መነጋገሩ ፋይዳ ለውም። የህዝቡ ቁጥር የቀነሰው በ ሞት ነው ብላችሁ በቀላሉ መደምደም ችላችሁዋል፣ እንዲህ በማለታችሁ  ስህተት ሰርታችሁዋል ህዝቡን ይቅርታ ልትጠይቁ ይገባል።” ብለዋል።
ተወካዩ አክለውም ” የአማራ ህዝብ ከሌላው ክልል ህዝብ ለብቻው ተነጥሎ የኤድስ ቫይረስ አልተወጋም። እንደዚህ ብላችሁ መናገር አልነበረባችሁም። የአማራ ህዝብ በ1 ነጥብ 7 በመቶ እያደገ ነው ብላችሁ ትናገራላችሁ፣ ይሄ የህዝብ ቁጥር እድገት ቀንሶባቸዋል በሚባሉት በስካንደቪኒያ አገራትም አልታየም። ” ካሉ በሁዋላ ” የአማራ ህዝብ ባለፈው ጊዜ በ1 ነጥብ 7 አደገ ማለታችን ስህተት ነበር ካላችሁና  ትክክለኛ እድገቱ  2 ነጥብ 4 ነው ካላችሁ እናንተው በሰጣችሁን መሰረት 969 ሺ የአማራ ህዝብ ላለፉት 6 አመታት ያለበጀት እንዲኖር ተፈርዶበት ነበር ማለት ነው። እነዚህ ሰዎች ላለፉት 6 አመታት ዳቦ አልበሉም ወይም ካገሪቱ ዳቦ እንዲበሉ አልተደረገም ነበር ማለት ነው። ይቅርታ ልትጠይቁ ይገባል ብለዋል።
ሌላው ተናጋሪ ደግሞ እናንተ በአቀረባችሁት አዲሱ የእድገት አሀዝ ቢሰላ የአማራ ህዝብ ቁጥር 22 ሚሊዮን ይሆናል እንጅ 19 ሚሊዮን ሊሆን አይችልም፣  ስለዚህ አሁንም ያቀረባችሁት ሪፖርት ትክክል አይደለም አልቀበለውም ብለዋል።
ብቸኛው የአንድነት ፓርቲ ተወካይ አቶ ግርማ ሰይፉ በአዲስ አበባ ህዝብ ቁጥር ላይ የቀረበውን አዲስ አሀዝም ሳይቀበሉት ቀርተዋል።
ማእከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ የኢንተር ሴንስዋል ሰርቬይ የስነሕዝብ ጥናት በአማራ ክልል በ4 ሺ 322፣በአዲስአበባ በ7 ሺ 576 ፣በሶማሌ ክልል በ7 ሺ 826 የቆጠራ ቦታዎች በሚገኙ ለናሙና በተመረጡ ቤተሰቦች ላይ አምና ጥናት አካሂዶ የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር  በ2004 ዓ.ም ወደ 82 ነጥብ 6 ከፍ ማለቱን፣ የአማራ ሕዝብ ቁጥር ከ17 ሚለዮን 100ሺ ወደ 19 ሚሊዮን 2 መቶ ሺ ማደጉን የአዲስአበባ ሕዝብ ከ2 ሚሊዮን 6 መቶ ሺ ወደ 2 ሚሊዮን 9 መቶ ሺ ማደጉን መግለጹ ይታወቃል።