* ” እናንተስ በምርጫ ትወርዱ ይሆን? ” አልኩ የምርጫ ቦርድን ውሳኔ ቢያስገርመኝ
ምርጫ በቀረበ ቁጥር የእኛ ሀገር የውስጥና የውጭ ፖለ ቲካ ምህዳር ይደማምቃል፣ ይተረማመሳል ። በዘመኔ በሀ ገሬ እውነተኛ ሆኖ ብዙሃን የተሳተፉበት ምርጫ አላየሁም ። ” ያን የከፋ መስዋዕትነት የተከፈለበትን ትግል ጠረጴ ዛ ላይ ሆነህ ምርጫ በመቀስቀስ ልትወስደው ትፈልጋለህ? ” የሚል ጋን ጩር ፖለቲከኛ በሞላባት ሀገር ምርጫ ለይስሙላ እንጅ የህ ዝብን ፍላጎት ለማክበር ተደርጓል ማለት አልችልም። ምርጫ በእኛ ሀገር ጉልበተኞች ትላልቅ አሳዎች ፣ ትናንሾቹን አሳዎች እንደ ሚውጡት አይነት ነው ። አንዱ አውራ “ትልቅ ነኝ ” ባይ ፖርቲ ትንንሾቹን ተቃዋሚዎች ሲለው እየዳጠ ፣ እየሰለቅጠና በሌላ አምሳያ እየተካ መጓዙ በማን አለብኝነት ይጓዛል። ይህ እየሆነ ተቸግረናል። ገና ምርጫ ቅስቀሳ ሲባል ትንሹ ትልቁን የሚያንኳስስበት ፣ ፖለቲከኞች በሰላማዊ ፉክክር ሳይሆን በሰይጣናዊ ፉክክር የሚጠመዱበት ፣ የመጠላለፊያ ወቅት ሆኖ ችግር ላይ ነን ። ዛሬ ዛሬ ደግሞ ምርጫውን ነጻ ማድረ ግ ኋላፊነት የተሰጠው ምርጫ ቦርድ በዘባተሎው ፖለቲካ እጁን አስገብቶ ፖለቲካው የሚቦጫጨቅና የመዘራጠጥ የወ ረደ ምህዳር እያደረገው መሆኑን ዛሬ በሰጠው ውሳኔ እያሳየን ነው ! በዚህ ፉክቻ ከሚጎዳው ሰላማዊ የፖለቲካ ሂደት ብቻ አይደለም ፣ በንትርክ ግብግቡ ፣ በሚፈሰው የሰው ደም ሀገር ትጎዳለች !
የሃገሬው ብሶት ሲገለጥ ..
በምርጫ ማሸነፍ መሸናነፍ በወጉ በማይከወንባት ሃገር በኢትዮጵያ ድሮም ሆነ ዛሬ የሃገሬው እድገት በመንግስት ሲገ ለጽ ፣ የሃገሬው ድቀት ፣ ብሶትና ምሬት በሃገሬው በየጉራንጉ ሩ በጥብብ ተሸፋፍኖ ይገለጻል ። የሃገሬውን የውስጥ ነዲድ ወኔ ፣ ፍላጎትና ምኞት ገላጮች ደግሞ የስነ ጽሁፍ ባለሙያ ዎችና አርቲስቶች ናቸው ። ላለፉት ሃያ አመታት በሃገራቸው ፖለቲካዊና ማህበራዊ ኩነቶች ዙሪያ ድምጻቸውን ባንድ ጎራ ያሰሙ የነበሩና ያልነበሩት የእኛ የጥበብ ሰዎች መናገር መተን ፈስ ጀምረዋል ።
በምርጫ ማሸነፍ መሸናነፍ በወጉ በማይከወንባት ሃገር በኢትዮጵያ ድሮም ሆነ ዛሬ የሃገሬው እድገት በመንግስት ሲገ ለጽ ፣ የሃገሬው ድቀት ፣ ብሶትና ምሬት በሃገሬው በየጉራንጉ ሩ በጥብብ ተሸፋፍኖ ይገለጻል ። የሃገሬውን የውስጥ ነዲድ ወኔ ፣ ፍላጎትና ምኞት ገላጮች ደግሞ የስነ ጽሁፍ ባለሙያ ዎችና አርቲስቶች ናቸው ። ላለፉት ሃያ አመታት በሃገራቸው ፖለቲካዊና ማህበራዊ ኩነቶች ዙሪያ ድምጻቸውን ባንድ ጎራ ያሰሙ የነበሩና ያልነበሩት የእኛ የጥበብ ሰዎች መናገር መተን ፈስ ጀምረዋል ።
የአርቲስት ሜሮን ጌትነት የተዋጣ የተጨበጨበለት “የአት ሂድ” መልስ “ሂድ ” ግጥም ጥልቅ ለመሆኑ ከእውነት ጋር ያለ ው ተዛማጅነት ብቻ ነውና በጥበብ እስትንፋሷ የህዝብ ብሶት ተገልጧል ባይ ነኝ ። ግጥሙ አሁን ድረስ ከጓዳ እሰከ አደባባ ይ የተለያዩ መድረኮችን ጠረጴዛ በመነጋገሪያነት የማድመቁ ሚስጥር በግጥም የተገለጸው እውነት በመሆኑ ብቻ እንጂ ደልዳላዋ ቆንጆ ባማረ ቅላጼ ስላቀረበችው አይደለም። እውነቱን ዘርግፋ በመናገሯ እንጅ !
ሌላዋ ተጠቃሸ የአርቲ ስት አስቴር በዳኔ በጥበብ የደመቀ ታላቅ መጽሃፍ እንደጻፈች ስሟ ከዳር አስከ ዳር የመግነኑ ሚስ ጥር በዳበረው ክህሎቷ ፖለቲካ ቀመስ ጥበብ ተቀኝታ ፣ አለያ ም ደርሳ አሳይታን አይደለም። ጋዜጠኞች ሀሞት አጥተን መ ጠየቅ ያልቻለነውን አስተያየትና ጥያቄ አርቲስት አስቴር በዳኔ በመጠየቋ እንጅ ! …ቦታው ህወሃት የተመሰረተበትን 40ኛ ዓመት የተከበረበት ደደቢት ነው ። አስቴር በዚያ ቦታ በአብዛኛ ው ነዋሪ አዕምሮ የሚላወስ ጥያቄ ” …አዲስ ታሪክ አዲስ አስተሳሰብ በዲሞክራሲያዊ ምርጫ ተለውጦ እናያለን? እናን ተስ በምርጫ ትወርዱ ይሆን? ” አለቻቸው የአባይ በዳኔ ልጅ በድፍረት ፊቷን ክችም አድርጋ … አብረዋት የተጓዙት ጓደኞቿ በአብዛኛው ህወሃትን ሲያወድሱና ሲያሞካሹት አስቴ ር በታላላቅ የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣናት መካከል በተደረ ገ ውይይት ፈርጠም ብላ ለጀኔራል ሳሞራ ያቀረበችው ያልተ ጠበቀ ጥያቄ የተወደደ ፣ የተወደሰበት ሚስጥሩ አርቲስት አስቴር በዳኔ ስለተናገረችው ሳይሆን ጥያቄው የህዝብ በመሆኑ ነው !
የነዋሪውን ቀልብ የሳበው የአርቲስት አስቴር በዳኔ ጠንካራ፣ ሞጋች አስየያየትና ጥያቄ ትዝ አለኝ …እንዲህ ነበር ያለችው አስቴር ” ዛሬ ባልናገረው የሚቆጨኝ የተከፈለው መስዋዕትነት እጅግ በጣም ከባድ እንደ ነበር ግልጽ ነው፡፡ በጆሮ ስሰማው ደርግ ተደምስሶ ታጋይ እንዲህ ሆኖ ሲባል ከሁለቱም ወገን የተሰዉት በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ልጆች ናቸው፡፡ የሞቱት፣ እግራቸው የተቆረጠ፣ ዓይናቸው የጠፋ ስላሉ ለሁለቱም ‹ጠላት› የሚለው ቃል ተገቢ አይመስለኝም፡፡ የወንድማማቾች ደም በመፍሰሱ ቤተሰቦቻቸው ዘንድ ሄደን ስናይ ልብ የሚሰብር ነው፡፡ ነገር ግን ይህ የጦርነትና የትግል ታሪክ ዘመኑ የፈጠረው ነው፡፡ በወቅቱ መንግሥታዊ ለውጥ ለማምጣት የትጥቅ ትግሉ አማራጭ አልነበረውም፡፡ አሁንስ ? የትግሉ ዋና ሐሳብ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት በአገሪቱ ለማምጣት ነው፡፡ የመንግሥትም ሆነ የሥርዓት ለውጥ በጦርነት ሳይሆን በዲሞክራሲ እንዲሆን ነበር ያ ሁሉ ከባድ መስዋዕትነት የተከፈለው፡፡ አሁን ላይ ሲታሰብ የሚመጣው ግንቦት ላይ 24 ዓመት የሚሆነው ሥልጣን ላይ ያለው አንድ ፓርቲ ነው፡፡ ዲሞክራሲያዊ ለውጥ ላይ ልባችሁ ምን ይላል? ያኔ ለሥልጣን ሳይሆን ለሕዝብ ስትታገሉ በጦርነት ሳይሆን በዲሞክራሲ ለውጥ እንዲደረግ ነበር፡፡ አይለደም? በእርግጥ የድሮን አስተሳሰብ መናፈቅ አዲስ አስተሳሰብ ለመቀበል ይከብዳል፡፡ አሁን ዝም ብዬ ሳስበው ራሱ ተቃዋሚ የሚለው ቃል ራሱ ጥሩ አይደለም፡፡ ተፎካካሪ ቢባል፡፡ አዲስ አስተሳሰብና ፍልስፍና ያለው ተተኪ መሪ ሊፈጠር አይችልም የሚል አቋም ነው ያላችሁ? እውነት መናገር እውዳለሁ ምክንያቱም እግዚአብሔር ምስክሬ ነው፡፡ ‘So, next time’ ምን ያህል አዲስ ታሪክ አዲስ አስተሳሰብ በዲሞክራሲያዊ ምርጫ ተለውጦ እናያለን? እናንተስ በምርጫ ትወርዱ ይሆን? ” ብላ አጠየቀች አርቲስት አስቴር ፣ መልስ ተሰጥቷል ! የጀኔራል ሳሞራ መልስ ግን በአርቲስቷ ውስጥ ያለፈውን የብዙሃን ዜጎች ጥያቄ የመለሰ ነው ለማለት ይከብዳል ! ግራን ነፈሰ ቀኝ የሀገሬው ጥያቄ ግን በባለጥበቧ በኩል ተላልፏል !
ሃሳቡን በሳልና በሰላ ቋንቋ ፣ ፍልስፍና ባልተለየው አቀራ ረብ ከምስልና ከማራኪ አቀራረብ ጋር እያዋሃደ የጥበብ በረከት ከሚቸረን የጥበብ ሰዎች መካከል አንዱ የሆነው ገጣሚ ታገል ሰይፉ ነው ። ገጣሚ ታገል ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ህልፈትን ተከትሎ ” ተከፍሎን አለቀስን ” በሚል ባቀረበው በምስል የተቀነባበረ መታሰቢያን ጨምሮ ለኢህአዴ ግን መንግስት በሚሰጠው ድጋፍ ይታወቃል። ታገል ለፖርቲ ውና ለግለሰቡ የሰጠው ድጋፍ የግል አቋሙና መብቱ በመሆ ኑ በግል ባከብርለትም በብዙሃን ዘንድ ግን የገጣሚውን ተወ ዳጅነቱን ሳይሸረሽርበት እንዳልቀረ መናገር ይቻላል ። ብዙ አድናቂዎቹ አኩርፈውታል ። እሱም ይህን ያጣው አይመስልም …
ገጣሚ ታገል ሰው በእሱ ላይ የሚሰነዝረው አሉታዊ አስተ ያየትን ግልጽ ለማድረግ ምላሽ ለመስጠትና ግልጽ ለማድረግ ይመስላል ፣ ያን ሰሞን በኤፍ ኤም 97 እድል አገኘ ። በዚሁ ፕሮግራም ተጋብዞ ” ሰው እንዲያውቅልኝ እንዲረዳኝ የምፈል ገው ” በሚል አንድምታ ከዚህ ቀደም ባልለመድነው መንገድ በሃገራችን ፖለቲላ ምህዳር ዙሪያ የሚሰማ የሚታየውን አዲ ስ ሃሳቡን ገልጦታል ። “ሰዎች የማይረዱት ነገር አለ። ” ሲል ደደቢት ተጋብዞ ስለመቅረቱ ፣ በዘመነ ኢህአዴግ ስለወረደው ስነ ጽሁፍና እየተሸረሸረ ስላለው የትውልድ ሞራል ዝቅጠት እንዲህ ሲል ተናገረ …”ሰዎች የማይረዱት ነገር አለ። ለምሳሌ ባለፈው የመቀሌ ጉዞ ላይ እኔ አልሄድኩም። አርቲስቶች ሲሄዱ ጥሪ ተደርጎልኛል። ነገር ግን የደደቢቱን ጉዞ ስላላመ ንኩበት ቀርቻለሁ። ስለማልፈልገው ማለት ነው። …ለነሱም የምለው ነው። በተለይ ባለፉት 15 አመታት ብዙ ነገር አልተሰ ራም። ለስነ ጽሁፍ የሚመች ግዜ አይደለም። ስነጽሁፍን ትኩረት አልሰጡትም። እያየን ነው። ግድቡ ሲገነባ ደስ ይላል። ቤት ሲሰራ ደስ ይላል። ነገር ግን የሞራል ሃብታችን እየወደቀ ነው። በደርግ ግዜ ለስነ ጽሁፍ ትኩረት ተሰጥቶት አድጓል። ብዙ ትላልቅ ደራሲዎቻችን በሳንሱር ዘመን ነው የወጡት። እንደ እነ ጸጋዬ ገብረመኅን፣ እነ በአሉ ግርማ… አሁን ግን እንደነዚያ አይነት ትላልቅ ሰዎች አልወጡም። ምክ ንያቱም ለስነ ጽሁፍ ትኩረት አልተሰጠም። ይህ መንግስ ትን ዋጋ ያስከፍለዋል። እንዲያውም ጠቅላይ ሚንስትሩ የሞቱ ግዜ ለሳቸው የተሰማኝን ሃዘን የሚገልጽ ግጥም አቅርቤ ነበር። እና ከዝግጅቴ በኋላ አንድ ጋዜጠኛ ‘ጠቅላይ ሚንስ ትሩ ለኪነ ጥበቡ ማደግ ምን አድርገዋል?’ ሲለኝ ‘ምን ም’ ነበ ር ያልኩት። እርግጥ ይህ ያልኩትን ቆርጠው አውጥተው ታል ።…እናም ወደ ትግራይ ለጉብኝት ሲሄዱ ስላላ መንኩበት እኔ አልሄኩም። በሁለተኛ ደረጃ የግል አቋም አለኝ። ለምሳሌ በደር ግ እና ኢህአዴግ’ መካከል የተካሄደው ጦርነት የሁለት ወንድ ማማቾች ጸብ ነው። እዛ ጸብ ውስጥ አንዱን በሌላው ላይ ጀግና ማለት እምነቴ አይደለም። ለኔ የመንግስት ጀግንነት የሚጀምረው ጦርነቱን ጨርሶ አዲስ አበባ ከገባ በኋላ ባሳያ ቸው ለውጦች ነው የምለካው። እንጂ እዛ ጋር ገዳይም ወንድሜ ነው፤ ሟችም ወንድሜ ነው። አንዱን በአንዱ ላይ ጀግና ለማለት እዚያ አልሄድም። አስፈላጊም አልነበረም። አሁን እኔ እንደዚህ አይነት አቋም አለኝ። ሆኖም አንዳንድ ድረ ገጾች ላይ ስታይ፤ (ለአባይ ግድብ ያቀረበውን ግጥም አይተ ው፤ ሰዎች ”ባንዳ ባንዳ’ ብለው የሰደቡትን በማስታወስ ይመስላል… የንዴት ትንፋሽ አስማ) የአባይ ጉዳይ ሲሆን በዚህ ሁሉ ልዩነት መሃል አገሪቱን ዲያብሎስም ቢመራት የአባይን መገደብ እደግፈዋለሁ። ብዙ ሰዎች ይህንን በደንብ አይረዱትም። ….ወደኋላ ሄደህ ብትመለከት ወንድሙን ገድሎ ስለመጣው ኢህአዴግ ጀግንነት ጽፌ አላውቅም ።…ከመንግ ስት ጋር ብዙ ደስ የማይሉኝ ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ።አባይ ሲባል ግን… ይህ የአገር ጉዳይ ነው። …ማንም የፈለገውን ትርጉም ቢሰጠው ይህ ለዘመናት አያት ቅድማያቶቻችን እንዲሆን ሲመኙት የነበረው ነገር ነው። ስለዚህ አባይን በተመለከተ ሰዎች በዚህ በኩል ቢረዱኝ ደስ ይለኛል፤ ለማለት ነው።” ሲል ደመደመ ! የገጣሚ ታገልም ድምጽ ለመጻኢዋ ክብርት ሀገር መልካምን የማሰብ የመቆርቆርና አዙራችሁ እዩነየሚል መልዕክት ያያዘ የህዝብ ድምጽ ነው !
ዛሬ ከቀትር በኋላ ተሰይሞ በአንድነት ፖርቲ የውስጥ ጉዳይ ፍርደ ገምድል የሰጠው የምርጫና የምርጫ ኮሚሽኑ ነገር አስገርሞኝ አመሸ። ከህዝብ ውስጥ የህዝብ ሆነው ስለህዝብ መብት ፣ ለሰላማዊ ውሎ አዳር ፣ ስለምንጓዝበት አደገኛ መንገድና ስለመጭው የእኛ ጉዞ አሳስቧቸው መንቀ ሳቀስ የጀመሩት ጥበበኞች ድምጽ የህዝቡን ድምጽ ነውና ሰሚ ያስፈልገዋል ። ጥበበኞች እንደ ቀድሞው ” ሊቀ መኳስ ” አዟዙረው ሳይሆን በቀጥታ የህዝቡን ሮሮ ማስተጋባት መጀ መራቸው የለውጥ ፈላጊውን ቁጥር መበራከት መግነን እኛ እንዳየነው ፖለቲከኛ ገዥዎቻችን ካሳያቸው መልካም ነው! ይህ ካልሆነ አደጋ አለው !
እየሆነ ያለው ቢያስደምመኝ ዝም አልኩና የአርቲስት አስቴርን ጥያቄ ደጋገኝኩና ጠየቅኩ ” ምን ያህል አዲስ ታሪክ አዲስ አስተሳሰብ በዲሞክራሲ ያዊ ምርጫ ተለውጦ እናያለን? እናንተስ በምርጫ ትወርዱ ይሆን? ” ብየ የአስቴርን ጥያቄ ላጠይቅ ግድ አለኝ ! አዎ እናንተስ በምርጫ ትወርዱ ይሆን? ” አልኩ የዛሬውን የምርጫ ቦርድን በአንድ ፖለቲካ ፖርቲ ላይ የወሰደውን ቅጥ ያጣ እርምጃ መግለጫ ቢያስደምመኝ … !
እስኪ ቸር ያሰማን !
ጥር 21 ቀን 2007 ዓም
ምንጭ የኢትዮጵያ ሜዲያ መድረክ
No comments:
Post a Comment