* ኢህአዴግ አሸነፈ፤ ፋና መሰከረ!
ምርጫ ያለ ነጻ ሚዲያ ተግባራዊ ሊሆን እንደማይችል ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ተመልካች (Human Rights Watch) በያዝነው ሳምንት ማገባደጃ አካባቢ በኢትዮጵያ የሚዲያ ነጻነትን አስመልክቶ አጠቃላይ ዘገባ እንደሚያወጣ ተሰማ፡፡
ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ መረጃውን ያቀረቡና ከዘገባው ጋር ተዛማጅነት ክፍሎች እንደተናገሩት የሰብዓዊ መብት ድርጅቱ ይህንን ዘገባ ያጠናቀረው በተጨባጭ ከሚዲያ ጋር በተያያዘ ሰለባ የሆኑትን በሚዲያው መስክ የተሰማሩትን በማነጋገርና የመጀመሪያ ደረጃ መረጃ በመሰብሰብ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ዘገባው ከዚህ በፊት ከወጡት ዘገባዎች ለየት ባለ መልኩ በፕሬስ ሚዲያው ላይ የተሰማሩትን ክፍሎች በስፋት የዳሰሰ ነው፡፡ በተለምዶው በጋዜጠኞች ላይ የሚደረገው አፈና በብዙ መልኩ የሚነገር ሲሆን በዚህ ዘገባ ግን ኢህአዴግ በአሳታሚነት፣ በአከፋፋይነት፣ በአታሚነት፣ በሻጭነት (አዟሪነት)፣ ወዘተ የተሰማሩትን እንዴት ስልታዊ በሆነ መልኩ እንደሚያዳክም፣ እንደሚያፍን፣ እንደሚያሰቃይና ባጠቃላይ ከሜዳው እንደሚያስወግድ የሚያስረዳ እንደሚሆን ጎልጉል ካገኘው መረጃ ለመገመት ተችሏል፡፡
በመጪው ግንቦት ከሚካሄደው ምርጫ ጋር በማያያዝ ይወጣል ተብሎ የሚጠበቀው ይህ ዘገባ በተለይ የኢህአዴግን ቋት የሚሞሉ ለጋሽ አገራት፣ ዓለምአቀፍ የፍትሕ አካላት፣ የሲቪክ ማኅበረሰቦች፣ ወዘተ ከወዲሁ ግንዛቤ ይዘው ኢህአዴግ አደርገዋለሁ ለሚለው “ዴሞክራሲያዊና ፍትሃዊ” ምርጫ ያለ ነጻ ሚዲያ ተሳትፎ እንዴት ውጤት አልባ እንደሆነ የሚያስረዳና ጠለቅ ያለ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡
በዘንድሮው ምርጫ ባልተጠበቀና ለመቀበል በሚያስቸግር መልኩ የአውሮጳ ኅብረት “በጀት የለም” በሚል ምርጫውን አልታዘብምምብሏል፡፡ በይፋ የተሰጠው ምክንያት ይህ ቢሆንም ጉዳዩ የበጀት ሳይሆን “ኢህአዴግ ከኢህአዴግ ጋር የሚያደርገውን የ99.6 በመቶ የምርጫ ውጤት መታዘብ በራሱ ያስታዝባል” በሚል ነው ኅብረቱ ምርጫ መታዘቡን በቅድሚያ ትዝብት የተወው በማለት የተሳለቁ መኖራቸው ተሰምቷል፡፡ ሆኖም ግን ኢህአዴግ በበኩሉ “ባትታዘቡ ምን ገደደኝ” በማለት ኅብረቱ ምርጫውን ለመታዘብ አለመፈለጉን በአብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ትዝብት አልፎታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በዚህ ስለ ሚዲያ ነጻነት በሚያትተው አዲስ ዘገባና በኅብረቱ ውሳኔ ዙሪያ ኢህአዴግ “ዓለምአቀፋዊ ሽልማት ባገኙ የዘርፉ ባለሙያዎቹ” ተጠቅሞ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዴት ባለ “ነጻነት” የሚዲያ ሥራ እንደሚሠሩ በነዚሁ “ሚዲያዎች” ምላሽ እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡
የአውሮጳ ኅብረትን “ምርጫ አልታዘብም” የማለት ውሳኔን በተመለከተ ከጉዳዩ ጋር ቅርበት ያላቸው ለጎልጉል እንደተናገሩት ኅብረቱ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ከበጀት እጥረት ሳይሆን እየከረረና እየመረረ የመጣውን የኢህአዴግን አምባገነንነት፣ በቀደሙት “ምርጫዎች” የተከሰተውን ዓይንአውጣ ቅጥፈት እንዲሁም የኢህአዴግን የሞራል ዝቅጠት በማገናዘብና ከተሞክሮ በመነሳት የግንቦቱን ምርጫ አስቀድሞ በማጣጣል ዋጋ እንደማይሰጠው ከመናገር አኳያ ነው በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
ይህንን አስደንጋጭ የአውሮጳ ኅብረት ማዕቀብ ተከትሎ የሰብዓዊ መብት ተመልካቹ ድርጅት በማስረጃ የተደገፈ ዘገባ ከምርጫው በፊት አስቀድሞ ማውጣቱ ታስቦና ታቅዶ የተደረገ ብቻ ሳይሆን የአውሮጳ ኅብረትን እነማን ይከተሉታል የሚል ጥያቄ አስነስቷል፡፡
በግንቦት 2007 አካሂደዋለሁ ለሚለው ምርጫ ኢህአዴግ አጋጣሚውን ተጠቅሞ የውጭ ምንዛሬ ኮሮጆውን እንዲሞሉለት ከአውሮጳ ኅብረት በተጨማሪ ሌሎች አገራትን በተናጠል መለመኑ ይታወቃል፡፡
source (http://www.goolgule.com
No comments:
Post a Comment