Monday, January 13, 2014

ሕገ- መንግስት ወይስ ዶክመንተሪ ፊልም? (ተመስገን ደሳለኝ)

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ
አምስተኛው ዙር አገር አቀፍ ‹‹ምርጫ›› እንደወትሮው ሁሉ በቀጣዩ ዓመት ሊደረግ በዕቅድ ተይዟል፤
ወሬውም ከወዲሁ ለፖለቲካ ፍጆታነት እየዋለ ነው፤ ኢህአዴግም በበኩሉ ‹አውራ ፓርቲ›ነቱን ከቀደመው
በበለጠ አጠናክሮ የሚቀጥልበትን ሴራ ፈትሎ በመግመድ ውሎ ማደሩን ገና በማለዳ እያቀላጠፈው መሆኑን
እየታዘብን ነው፡፡ አቶ መለስ ዜናዊ (ከልቡ ባይሆንም) በ1996 ዓ.ም ወርሃ ሐምሌ ላይ በተደረገ የግንባሩ ጉባኤ
‹‹የሚቀጥለው ምርጫ እንከን-አልባ ይሆናል›› ሲል ‹ቃል› ገብቶ የነበር ቢሆንም፣ ከስድስት ዓመት በኋላ
በተካሄደው አራተኛው ዙር ‹‹ምርጫ›› በግላጭ ‹እንከን-አልባ ድል› በሚል ሲቀይረው ቅንጣት ታህል ሀፍረት
አልተሰማውም ነበር፡፡ ግና! ‹አንድ ለእናቱ› እንዲል አቤ ጎበኛ፣ የተቃውሞውን ስብስብ የምትወክል አንዲት
ወንበር ሾልካ ወደ ምክር ቤቱ በመግባቷ፣ ፓርቲው ዛሬም ድረስ እንደ እግር እሳት እያንገበገበችው መሆኑን
በተለያየ መንገድ እያሳየን ነው፡፡

 የሆነው ሆኖ ኢህአዴግ ከዚህ ትምህርት በመውሰድ በሚቀጥለው ዓመት በሚደረግው ‹‹ምርጫ›› እንዲህ አይነት ‹እንዝህላልነትን›
ለማረም በከፍተኛ ዝግጅት መጠመዱን የሚጠቁሙ መረጃዎች እያፈተለኩ ነው፡፡ መቼም የጉዳዩ እውነትነት ከተረጋገጠ፣ ምናልባትም
በ2012 ዓ.ም ልክ እንደ ኤርትራ ወይም እንደ ቻይና ‹ልማታዊ መንግስት እንጂ ምርጫ የሚባል ነገር አያስፈልግም! የምርጫ ፖለቲካ
የኒዎ-ሊበራሊስቶች አጀንዳ ነውና!!› ከማለት የሚመለስ አይመስለኝም፡፡ ማን ያውቃል? …እንዲህ እንደዛሬው የሶስት ሺ ዓመት ታሪክ
ያላትን እና የዘጠና ሚሊዮን ሕዝብ አገርን ፍርሃት በመንዛት አሸንፎ ከቆየ የምናየው ይሆናል፡፡

 ከዚህ ባለፈ ቀጣዩን ‹‹ምርጫ›› በፍፁማዊ ጠቅላይነት ለመጨረስ እያደረገ ያለው መሰናዶ በሶስት የተከፈለ ነው፤ የመጀመሪያው
ለመላው የድርጅቱ አባላት (የመንግስታዊ ተቋማት ኃላፊዎችን ጨምሮ) የተዘጋጀው ፓኬጅ ነው (ሰሞኑን በተለያዩ ከተሞች ስለ ‹አውራ
ፓርቲ› አስፈላጊነት እና የ‹ልማታዊ መንግስት›ን ጠቀሜታ በተመለከተ እየተሰጠ ያለው ሥልጠናም የዚሁ አካል እንደሆነ ሰምቻለሁ)፤
ሁለተኛው መራጩ ሕዝብ ላይ በተናጥል አተኩሮ ለመተግበር እየተሞከረ ካለው ቀመር ጋር የሚያያዝ ሲሆን፤ ይህም እንደ ቀድሞው ሁሉ
ለአቅመ-ምርጫ የደረሰውን ህዝብ በኮንዶሚንየም፣ በመልካም አስተዳደር እና በማይጨበጡ የተስፋ ፕሮፓጋንዳዎች ማማለልን
የሚያካትት ነው፤ የመጨረሻው ደግሞ ተቃዋሚ ፓርቲዎችና የግሉ የህትመት ሚዲያ ላይ ያነጣጥራል፤ በዚህ ፅሁፍም አጀንዳ
የምናደርገው አገዛዙ በዚህኛው ግንባር ከሚያስወነጭፋቸው የ‹ጦር መሳሪያዎች› በዋነኛነት በዘጋቢ ወይም በዶክመንተሪ መልክ
የሚያዘጋጃቸው ፊልሞችን የተመለከተ ነው፡፡

 ስውሩ አጀንዳ…
 በርግጥ ይህ አይነቱ አሰራር ዛሬ የተጀመረ አይደለም፤ ባለፉት ሃያ ዓመታት በሙሉ ሲተገበር የነበረ ነው፡፡ በተለይ ሕዝባዊ ተቃውሞን
የመሰለ ለሥልጣን የሚያሰጋ ድንገቴ አጋጣሚ ሲከሰት የሚመረቱት ፊልሞች ቁጥርም እንዲሁ ይጨምራል፤ እንደ ምሳሌም የ1993ቱን
የህወሓት ክፍፍልን ተከትሎ በየአካባቢው የሕዝብ ማጉረምረም በበረታበት ወቅት፣ የሰሜን አፍሪካ አብዮት በጋመበት ማግስት እና
የእስልምና እምነት ተከታዮች ሕገ-መንግስታዊው የኃይማኖት ነፃነት እንዲከበርላቸው በአደባባይ በጠየቁባቸው ጊዜያት በ‹‹ዘጋቢ
ትዕይንት›› ስም የተሰራጩትን ብቻ መመልከቱ በቂ ነው ብዬ አስባለሁ (በነገራችን ላይ እንዲህ አይነት ጭብጥ ያላቸው ፊልሞች
ደራሲያን፣ የስርዓቱ ዋነኞች ‹ኤጲስ-ቆጶሳት› እንጂ ተቋሙ የሰበሰባቸው ብላቴና ልማታውያን ጋዜጠኞች አይደሉም)
 ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የመረጃ ምንጮቼ እንዳረጋገጥኩት ‹ዶክመንተሪ ፊልሞች› የሚዘጋጁት በሁለት መንገድ ነው፤ የመጀመሪያው
በኢቲቪ ባልደረቦች ሃሳብ አመንጪነት በፕሮፓጋንዳ ላይ የሚያተኩር ሲሆን፣ በሚመለከታቸው ባለሥልጣናት ይሁንታን ሲያገኝ
እንዲተላለፍ የሚደረግ ነው፡፡ ሌላኛው ደግሞ፣ በጉምቱ የፓርቲው መሪዎች የጭብጥ አሰናጅነት ሙሉ ድራማው አልቆለት በቀጥታ አየር
ላይ እንዲውል ወደ ጣቢያው የሚላከው ነው፡፡ በዚህ ዘውግ የሚመደቡት አብዛኛዎቹ ፊልሞች ተቃዋሚ ፓርቲዎችን፣ በግል ሚዲያ ላይ
የተሰማሩ ጋዜጠኞችን፣ የኃይማኖት መሪዎችን እና ዓለም-አቀፍ ተቋማትን በመወንጀልና በመዝለፍ ላይ የሚያውጠነጥኑ ናቸው (የቅርቦቹን
እንኳ ለማስታውስ ያህል ብንጠቅሳቸው ይህንኑ ያስረግጣሉ፡- ‹አዲስ አበባን እንደ ባግዳድ›፣ ‹አኬልዳማ›፣ ‹ጀሀዳዊ ሀረካት›፣
‹ሽብርተኝነት በኢትዮጵያ› እና የመሳሰሉት)

 በጥቅሉ እስከ 2004 ዓ.ም መገባደጃ ድረስ የእነዚህ ፊልሞች ደራሲ አቶ መለስ ዜናዊ የነበረ ሲሆን፤ ከእርሱ ህልፈት በኋላ የኮሚኒኬሽን
መ/ቤት (ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የጠቅላይ ሚንስትሩ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር አማካሪዎች) በደህንነት እና ፀረ-ሽብር ግብረ ኃይል ስም
እንደሚያዘጋጁት ውስጥ-አወቅ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ኢቲቪ በእንዲህ አይነት ጭብጥ ዙሪያ በሚያውጠነጥኑ ፊልሞች ላይ ምንም
አይነት ተሳትፎ አያደርግም፤ ሳይቀንስና ሳይጨምር ለሕዝብ ማስተላለፍ አማራጭ ያልተተወለት ብቸኛ ግዴታው ነው፤ የህወሓቱ ሰው
ገራገሩ የተቋሙ ስራ አስኪያጅ ዘርዓይ አስግዶምም ቢሆን ይህ ኃላፊነት ሲሰጠው ትጉህ አገልጋይነቱ ለማን እንደሆነ ጠንቅቆ ያውቀዋልና፣
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በፍፁም ፈቃደኝነት ሥራውን ከማሳለጥ በቀር የሚቃወምበት ወይም የኤዲቶሪያል ነፃነቴን አላስገፋም ብሎ የሚቀብጥበት አንዳች
ምክንያት የለውም፡፡ በግልባጩ ውዳሴ መለስ፣ ስደት፣ የአባይ ቁጭት፣ የኮንዶሚንየም ቤቶችንና መሰል ጉዳዮችን በተመለከተ ደግሞ ሩቅ
አላሚዎቹ ‹‹ልማታዊ ጋዜጠኞች››፣ እንቅልፍ አጥተው የሚጨነቁበትና እርስ በእርስ ለመቀዳደም የሚተጉበት አጀንዳ ስለመሆኑ ራሱ
በረከት ስምዖንም ገና ድሮ የገባው ይመስለኛል (በነገራችን ላይ በየጊዜው ጥቂት የጣቢያው የተለያዩ ፕሮግራም አዘጋጆች እና የዘጋቢ
ፊልም ባለሙያዎች የቻይናን የሚዲያ ተሞክሮ አጥንተው እንዲመጡ እንደሚደረግ ይታወቃል)

 ለዚህ ፅሁፍም እንደ ማሳያ የምጠቅሰው፣ ባለፈው ሳምንት ‹‹ሽብርተኝነት በኢትዮጵያ›› በሚል ርዕስ ለተመልካች የቀረበው ዘጋቢ
ፊልም፣ ሙሉ በሙሉ በብሔራዊ መረጃ መ/ቤት ስም የተዘጋጀ ሲሆን፣ በንባብ የተሳተፉት ሁለቱ ‹‹ጋዜጠኞች››ም የኢቲቪ መደበኛ
ባልደረቦች እንዳልሆኑ ከምንጮቼ አረጋግጫለሁ፡፡ ምንም እንኳ የፊልሙ ‹ባለቤት› የሆነው የደህንነት ቢሮ በሽብርተኝነት ዙሪያ
የሚያውጠነጥን ነው ቢለንም፣ እንዲተላለፍ የተፈለገው ዋነኛ መልዕክት በቀጥታ ከቀጣዩ ምርጫ ጋር የተያየዘ ነው ወደሚል ጠርዝ
የሚገፉንን ማሳያዎች መምዘዝ የሚቻል ይመስለኛል፡፡ እንዴት ሆኖ? የሚለውን ጥያቄ በአዲስ ርዕስ ሥር እናፍታታው፡፡

 ከፍርሃት ጋር ወደፊት!

 በዚህ ፊልም ላይ ዋነኛ አጋፋሪ ሆነው የቀረቡት ሶስት ሰዎች ናቸው፤ የኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስቴር ሚንስትር ዲኤታ ሽመልስ ከማል
(ከጥቂት ዓመታት ወዲህ በእንዲህ አይነት ፊልሞች ላይ የመሪ-ተዋናይነትን ገፀ-ባህሪ ወክሎ መጫወቱን እየተካነው እንደሆነ እኔም ራሴ
እመሰክርለታለሁ¡)፣ የፌደራሉ ዋና ዓቃቢ-ሕግ ብርሃኑ ወንድማገኝ እና አቶ ዘሪሁን ተሾመ (ይህ ሰው ደግሞ አሉባልታና ጠቀሜታቸው
ረብ-የለሽ የሆነ ወሬዎችን በማቅረብ የሚታወቀው የ‹ዛሚ-90.7› ሬዲዮ ባለቤት ሚሚ ስብሃቱ የትዳር አጋር ነው) ከትዕይንቱ መካከል
የሚታወሱ ፊቶች ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች ድራማው ተጀምሮ እስኪያልቅ ድረስ ተሰፍሮ የተሰጣቸውንና በፈጠራ ታሪክ የተሞላውን
‹ስክሪፕት› ቃል-በቃል ሸምድደው መምጣታቸውን በግልፅ በሚያሳይ መልኩ ሲያነበንቡ ላስተዋላቸው ተመልካች ‹‹ብሔር፣ ብሔረሰቦች
እና ሕዝቦች›› የጣሉባቸውን ግዴታ በቁርጠኝነት ለማስፈፀም ‹ቀራኒዮ› ድረስ የሚጓዙ ሊመስለው ቢችል አይፈረድበትም¡ መቼም አገዛዙ
ዓለማዊ ፍላጎታቸውን እስካሟላላቸው ድረስ ሀገር፣ ሕገ-መንግስት፣ ሕሊና… ደንታ ሳይሰጧቸው ሕዝብን በማሸበር የስርዓቱ ዕድሜ
ይረዝም ዘንድ ‹ከፍርሃት ጋር ወደፊት!!› ለማለት የማያመነቱ ሰዎችን በዙሪያው የኮለኮለው ለእንዲህ አይነቱ ጊዜ ነው፡፡

 የሆነው ሆኖ ፊልሙ ከቀድሞዎቹ አንፃር እንኳ ሲመዘን የወረደና አሰልቺ ቢሆንም፣ ያን ያህል ከተደሰኮረለት የ‹‹ሽብርተኝነት ጉዳይ››
ባሻገር ሁለት ያደፈጡ ስውር ዓላማዎች ያሉት ይመስለኛልና፣ እነርሱን ነጣጥለን እንመልከት፡፡

 ፩
 የቀደሙ ልምዶችን ተንተርሰን ስናብሰለስለው፣ የዘጋቢ ትዕይንቱ ድብቅ ዓላማ ተደርጎ ሊጠቀስ የሚችለው የመጀመሪያው የቢሆን
ሃሳብ፣ ኢህአዴግ ከምርጫው መዳረሻ በፊት በተቃውሞ ፖለቲካው ውስጥ ንቁ ተሳትፎ እያደረጉ ያሉ የተወሰኑ የአመራር አባላትን እና
ጥቂት ጋዜጠኞችን እንደተለመደው ከግንቦት 7 ጋር አቆራኝቶ ለማሰር እየተዘጋጀ ነው የሚል ይሆናል፡፡ በርግጥም ይህንን መከራከሪያ
ከመቀበል ሌላ አማራጭ የሚያሳጡ ሁለት ገፊ ምክንያቶች አሉ፤ አንዱ ፓርቲው ቀጣዩን ምርጫ ከትግል ዘመኑ ጀምሮ ይመራው ከነበረው
ጉልበታሙ አቶ መለስ ውጪ የሚያደርገው መሆኑ ያሳደረበት ስጋት ወደ ጭፍን አምባገነንት እንዲቀየር ከማስገደድ አልፎ፣ ይህንኑ
የሰውየውን ህልፈት ተከትሎ የተከሰተው የኃይል መከፋፈል ያነበረው የመሳሳት ተፅእኖ ይመስለኛል፤ እነዚህ ኩነቶችም ስርዓቱ
ህልውናውን ካፀናበት አምባገነናዊ ባህሪው አኳያ ድንገቴ እርምጃ እንዲወስድ መግፋታቸው የሚጠበቅ ነው፡፡

 ሁለተኛው ደግሞ ካደረ ተሞክሮው የሚነሳ ነው፤ ይኸውም በ2002ቱ ምርጫ ዋዜማ በተልካሻ ምክንያት የአንድነት ለፍትሕና
ዴሞክራሲ ሊቀ-መንበር የነበረችውን ብርቱካን ሚደቅሳን እስር ቤት በመክተት ፓርቲውን እና የተቃውሞ ደጋፊ ኃይሉን እስረኛ
በማስፈታት አጀንዳ እንዲጠመድ ያደረገበት ስልት እና ሁነቱ የፈጠረው ማሕበረሰባዊ የፍርሃት ድባብ ያስገኘለት ጠቀሜታን ሊከልሰው
መሞከሩ አይቀሬ መሆኑ ነው፡፡ በአናቱም በወቅቱ ከፍተኛ ተነባቢነት የነበራትን የ‹‹አዲስ ነገር›› ጋዜጣ አዘጋጆች ምርጫው አራት ወር
ብቻ ሲቀረው በግልፅና ስውር ጫና ጋዜጣውን ዘግተው ከሀገር እንዲሰደዱ ያደረገበት መንገድም የዚሁ አፈና ጉትያ እንደነበረ
አለመዘንጋቱ፣ በቅርብ ከሚፈጠሩ ተመሳሳይ ክስተቶች ጋር ለማያያዝ ያስችላል፡፡

 ፪
 ሌላኛው የዘጋቢ ፊልሙ ዓላማ በቀጣዩ ምርጫ ለውጥ ፈላጊውን የህብረተሰብ ክፍል ወደ ተቃውሞ ጎራ ሊያሰባስብና መነቃቃት
ሊፈጥር ይችላል የሚል ብርቱ ጥርጣሬ ያሳደረበትን የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) ጣቢያን በመርገም (በሽመልስ ከማል
አነጋገር ‹‹ውጉዝ ከመአርዮስ›› በማለት) የተቀናቃኝ ድምፆች በተከበበላቸው ሞገድ ብቻ እንዲሰሙ ማስገደድ ነው፡፡ ይህ ሁናቴ አገር
ውስጥ ያሉ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች እና ጋዜጠኞች ለጣቢያው ቃለ-ምልልስ እንዳይሰጡ በፍርሃት ቆፈን መሸበብንም ያከተተ ነው፡፡
አስደንጋጩ ጉዳይ ደግሞ መከራከሪያ ሆኖ የቀረበው ሕገ-መንግስታዊው ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ሳይሆን፣ ለሚዲያ ተቋሙ
የብሶት መግለጫዎችን መስጠትም ሆነ ኢ-ፍትሀዊ አሰራርን ማጋለጥ በሽብርተኝነት እንደሚያስከስስ የሚተርክ ‹‹ዶክመንተሪ ፊልም›› መሆኑ ነው፡፡ በርግጥ ለዚህ ማስፈራሪያ እንደ መደገፊያ የተጠቀሙት ፀረ-ሽብር ሕጉ በግብረ-አበርነት ተጠያቂ የሚያደርግበትን
የተለጣጭነት ባህሪውን አፅንኦት በመስጠት እንደነበረ ታዝበናል፡፡

 በፊልሙ ላይ አቶ ዘሪሁን ምሬት በዋጠው ድምፅ ‹‹ኢሳት የግንቦት 7 ወፍጮ ነው!›› የሚል መፈክር ሲያሰማ፣ ሽመልስ ከማል ደግሞ
የአዋጁ ዋነኛ ዓላማ ከዚህ ቀደም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ‹አሸባሪ› ተብለው ከተፈረጁት ድርጅቶች ጋር ምንም አይነት ግንኙነት
እንዳይኖር ለማድረግ እንደሆነ ምሎ-እየተገዘተ ተመልካቹን በፍርሃት ለማንበድበድ ሲሞክር ተስተውሏል፡፡ ይሁንና የአቶ
ሽመልስን እርግጠኛነት ለማመን አመክንዮ መጠቀም የግድ ይሆናል፤ እናም ኢሳት የእነዚህ ድርጅቶች ዓላማ አራማጅ መሆኑን ለማሳየት
ምን ተጨባጭ ማስረጃ አቀረባችሁ? ለሚለው ጥያቄ እየነገሩን ካለው እንቶ-ፈንቶ ባለፈ በማስረጃ የተደገፈ መልስ መስጠት የሚኖርባቸው
ይመስለኛል፡፡ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ የኤርትራ መንግስት ከሰጠው አምስት መቶ ሺህ ዶላር ውስጥ ሁለት መቶ ሺውን ለኢሳት ሥራ ማኪያሄጃ
እንዲውል መወሰኑን በስልክ ሲናገር ከማሰማት በዘለለ ማለቴ ነው፡፡

 እግረ-መንገድ ለመጥቀስ ያህል የዚህ ፅሁፍ ዓላማ ኢሳትን መንግስት ለምን ወነጀለው በሚል ግብረ-መልስ መስጠት አለመሆኑን
ማስገንዘቡ አስፈላጊ ይመስለኛል፤ መነሻ ምክንያቴ እንደ ሚዲያ ተቋምነቱ ከእኔ ሞያ ጋር በቀጥታ መገናኘቱ ሲሆን፤ ለምን ይህ ሆነ?
ያልኩበት ተጠየቅም የሕግ የበላይነት ጉዳይ ብቻ በመሆኑ ነው፡፡ ምክንያቱም የተመለከትነው ፕሮግራም ኢሳት እስከ ዛሬ ባሰራጨው ዘገባ
ላይ ‹አሸባሪ› ሊያስብለው የሚያስችል ትዕዛዝ ያስተላለፈበትን ወይም ንፁሃን ኢትዮጵያውያንን በተጠመደ ፈንጂ ዶግ-አምድ እንዲሆኑ
መቀስቀሱን የሚያጋልጥ ሳይሆን፣ በሰላማዊም ሆነ በትጥቅ ትግል ከተደራጁ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር አባላት ጋር ያደረገውን ቃለ-
መጠይቅ ብቻ በመደጋገም ነው፡፡ ለዚህም ይመስለኛል የዘጋቢ ፊልሙ ድብቅ ዓላማ ስርዓቱ በሀገር ውስጥ ያሉትን ጥቂት የግል የሕትመት
ሚዲያዎች በፈርጣማ የፖለቲካና ቢሮክራሲ ክንዱ ደቁሶ ካኮሰመነ በኋላ፣ በተወሰነ መልኩም ቢሆን ድምፅ ላጡት ድምፅ መሆን እየቻለ
የመጣውን እና ለተፎካካሪ ፓርቲዎች አማራጭ የሚዲያ ምህዳር የፈጠረውን የቴሌቪዥን ጣቢያ ከተለመደው የአፈና መንገድ /ጃሚንግ/
በተለየ ስልት ከጨዋታ ውጪ ለማድረግና በቀጣዩ ምርጫ ‹አውራ ፓርቲ›ነቱን ለማስጠበቅ የሚያደርገው ዝግጅት ነው እንድንል
የተገደድነው፡፡

 ከዚህ ቀደም እነ እስክንድር ነጋ በግንቦታ 7 አባልነት ተወንጅለው በታሰሩበት ወቅት አቶ መለስ ዜናዊ ለፓርላማው ‹‹ክምር ማስረጃ
አለን›› ቢልም፣ ጉዳዩ ፍርድ ቤት ሲቀርብ ግን በጨበጣ እንደገባበት ማየታችን አደባባይ የወጣ ሀቅ ነበር፤ በርግጥም ማስረጃ ሆኖ
የተቆጠረው ራሱ ያዘጋጀው ‹‹አኬልዳማ›› የሚል ‹‹ዘገቢ ፊልም›› እንደነበረ ስንመለከት፣ ይህ ስርዓት አስቀድሞ የተናገረበት ጉዳይ
ስህተት መሆኑ እንዳይጋለጥ ምንም ነገር ከማድረግ እንደማይመለስ እንታዘባለን (በነገራችን ላይ በወቅቱ በፍትህ ጋዜጣ ‹‹አኬልዳማው!
የአይሁድ ወይስ የኢህአዴግ?›› በሚል ርዕስ የዘገባውን ፈጠራነት በተጠናከረ ማስረጃ ለማጋለጥ ከተሞከረ በኋላ እንዲህ የሚል ምክር
አዘል ቁም-ነገር ተላልፎ እንደ ነበር አይዘነጋም፡-

‹‹ሆሊውድ የሚሰሩ አስፈሪ (ሆረር) ፊልሞች እንኳ ቢያንስ ከ16 ዓመት በታች ያሉ ልጆች እንዳያዩአቸው የሚከለክል ሕግ አለ፣ ኢቲቪ
ግን የተበጠሰ አንገት፣ የተገነጠለ ክንድ፣ የተቆረጠ እጅ፣ የተፈረከሰ ጭንቅላት… እያሳየ፣ ‹13 ዓመት የሞላው ሕፃን በሙሉ ሊያየው
ይችላል› ማለቱ ኃላፊነት የጎደለው አሰራር ነው››

 ባለፈው ሳምንት በቀረበው ፊልም ላይ ቢያንስ ይህ ሁኔታ ታርሞ ከ16 ዓመት በታች ያሉ ልጆች ሊያዩት እንደማይገባ ከሚያስጠነቅቅ
መልዕክት ጋር መተላለፉ ስርዓቱ ምክር መስማት ጀመረ እንዴ? እንድንል የሚያጭር ነው፡፡ በርግጥም በሌሎች ጉዳዮችም እንዲህ
ቢያዳምጡን ኖሮ፣ እየዋጣቸው ካለው ጥልቅ ጨለማ ራሳቸውን መታደግ የሚችሉበት በርካታ ዕድል ነበር፡፡)

 የሆነው ሆኖ በዚህና መሰል ፊልሞች ላይ የሚነሳው ሌላው ለትዝብት የሚያጋልጠው ጉዳይ የደህንነት ተቋሙ ሁሉንም ዜጋ
አብጠርጥሬ አውቃለሁ የሚለው ማንአህሎኝነቱ ነው፡፡ አስቂኙ ጉዳይ ግን በአዋጅ የተቋቋሙት የመረጃው መስሪያ ቤት እና የፀረ-ሽብር
ግብረ-ኃይል፣ ያሻቸውን ዜጋ ቤት (በስውርም በግልፅም) መበርበር፣ ስልክ መጥለፍ፣ የኢ-ሜል እና የማሕበራዊ ሚዲያዎችን አካውንት
‹የሚስጥር ቁልፍ ቃላት› ሰብሮ መፈተሽ… ከሚያስችል ያልተገደበ ሥልጣን ጋር የሚንቀሳቀሱ ቢሆንም፣ ሽብርተኝነትን ለመከላከል እንደ
አዋጭ መፍትሄ የወሰዱት ‹ዶክመንተሪ ፊልም›ን እስኪመስል ድረስ በሳምንት አንዴ መመልከቱ የተለመደ መሆኑ ነው፡፡ ርግጥ እንዲህ
አይነት ትዕይንቶች ተጨማሪ ስርዓታዊ ጠቀሜታቸው ማህበራዊ ተቀባይነታቸው የጎላ ዜጎችን በስቅየት (ቶርቸር) እያንበረከኩ በቴሌቭዥን
መስኮት አንገት አስደፍተው በማቅረብ ትውልዱ ተጠራጣሪና ድንጉጥ እንዲሆን ያላቸው አስተዋፆኦ አንዱ ነው፡፡ ሌላው ደግሞ ይህው
ቃል በሚከሰሱት ንፁሀን ላይ ተመልሶ እንደ ማስረጃ ተቆጥሮ፣ ከአስር ዓመት እስከ ዕድሜ ልክ የሚደርስ ቅጣት በ‹ካንጋሮው› ፍርድ ቤት
እንዲጣልባቸው የሚያደርገው ግፈኝነት ነው፡፡ ለዚህም ቅጥ ያጣ አምባገነንነት አይደፈሬ ሥልጣኑ የሰጠውና ገና ሲረቅቅ ጀምሮ ጠንካራ
ተቃውሞ ሲቀርብበት የነበረውን የፀረ-ሽብር አዋጅን የሕጋዊነት ከለላ አድርጎ እየተባባሰ በመጣ መልኩ መጠቀሙን መቀጠሉ ነው፡፡
ከጥቂት ሳምንታት በፊት የታተመው ‹‹ኒውስ ዊክ›› መፅሄት ‹‹Ethiopia declares war on gay men›› በሚል ርዕስ ባስነበበው
አደገኛ መጣጥፍ አዋጁን ያብጠለጠለበት ሀረግ የትችቶቹን ሙሉ መንፈስ የሚጠቀልል ይመስለኛልና እዚህ ጋር ልጥቀሰው፡-
 ‹‹የፀረ-ሽብር ሕጉ መንግስት ሽብርተኝነት ብሎ የሚያስበውን ጉዳይ በ‹መፃፍ፣ ማቀናበር፣ ማተም ወይም ማሰራጨት› የሚከሰውን ዜጋ
በሃያ ዓመታት እስር እንዲቀጣ ፈቅዶለታል፡፡››

 እነዚህን ነገሮች ጠቅልለን ስንመለከት ገዥው ፓርቲ ለሀገሪቱ ስጋት እንደሆነ የሚነግረንን ሽብርተኝነት ራሱ ባዘጋጀው ሕገ-መንግስት
ሳይሆን፣ በዶክመንተሪ ፊልም ጎርፍ ለመግታት ነው የተዘጋጀው ወደሚል ጠርዝ ይገፋናል፡፡ በርግጥ የፓርቲው አላማ ሥልጣኑን መጠበቅ
ነውና ሕገ-መንግስቱን ወዲያ ጥሎ ዘጋቢ ፊልሞች ላይ ቢንጠለጠል እንዴት ልንገረም እንችላለን?!

 ወደ የፍርሃት ‹ሪፐብሊክ›

ይህች መከረኛ ሀገር በደርግና በኢህአዴግ ከተሠጣት ቅጥያዎች አንዱ ‹‹ሪፐብሊክ›› የሚል እንደሆነ ይታወቃል (የደርጉ የኢትዮጵያ
ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሲል፤ ይህኛው ደግሞ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ነች ይለናል)፡፡ ዝርዝር ሃተታውን
ትተን ከዚህ ፅሁፍ አውድ አንፃር የሪፐብሊክን ብያኔ ሕዝባዊ መንግስትነት የሚል ትርጓሜ ሰጥተን ማለፍ ይበቃል፡፡ ይሁንና
የተሻገርናቸው ሁለት አስርታት የሚያስረግጡት ብቸኛ እውነት ቢኖር ሀገሪቱ ከዚህ የተጠያቂ መንግስት ምስረታ ተፃራሪ የሆነውን መንገድ
መምረጧን ነው፡፡ ከላይ ለማሳያነት የጠቀስኩት ዶክመንተሪ ፊልምም ሆነ ተያያዥ አፋኝ ሕጎቹ እና ፖለቲካዊ አተገባበራቸው በፍርሃት
የሚርድ ማሕበረሰብ በመፍጠር፣ ቀጣይ አስርታቱን ካለአንዳች መደነቃቀፍ ረግጦ መግዛትን ዋነኛ ግብ ያደረጉ ናቸው፡፡ ይህን
ተቋማዊነትን ተደግፎ የሚካሄደው መንግስታዊ ሽብር፣ በአንዳች ክስተት ብርክ በሚያናውጣቸው ዜጎች ማሕበረሰቡ እየተሞላ እንደሚሄድ
ግልፅ ነው፤ ከፌደራላዊ ወደ ፍርሃት ሪፐብሊክ እየተደረገ ባለው በዚህ ጉዞ፣ ሀገሪቱን ከዝግመታዊ ሞት ለመታደግ የበረቱ መዳረሻቸውን
ስርዓቱ አዘጋጅቷል፡፡ እናም ዋጋው ምንም ቢሆንም በአደባባዩ ላይ የሚደረግ የተቃውሞን እንቅስቃሴ፣ ኢህአዴግን ከሥልጣን የማውረድ
ብቻ ከመሆን መታለፉን በሚገባ ልናስብበት እንደምንገደድ ይሰማኛል፡፡ እነርሱ ከሚቀጥለው ምርጫ በፊትም ሆነ በኋላ ሕዝባዊ
ምህዳሩን ምንም አይነት የተቃውሞ ድምፅ የማይሰማበት ምድረ-በዳ ለማድረግ ይህን ያህል ርቀት መጓዛቸውን ስንመለከት ምርጫችን
ሁለት ብቻ ይሆናል፡፡ ቀጣዩን ትውልድ በፍርሃት ሪፐብሊክ ውስጥ ትቶ ማለፍ፣ አሊያም አደባባዩን በጨኸት መሙላት፡፡






ኢትዮሚድያ - Ethiomedia.com
January 12, 2014

Saturday, January 11, 2014

ለቴዲ አፍሮ 4.5ሚ. ብር ይከፈለዋል

በደሌ ለኮንሰርቶቹ 25 ሚ.ብር መድቦ ነበር ኮንሰርቶቹ ቢሰረዙም ውዝግቡ አልተቋጨም የቴዲ ደጋፊዎች የአፀፋ ዘመቻ ጀምረዋል
አለማቀፉ የኔዘርላንድ ኩባንያ ሄኒከን ከሚያስተዳድረው በደሌ ቢራ ጋር በመሆን በበርካታ ከተሞች ሊካሄዱ የነበሩ የቴዲ አፍሮ ኮንሰርቶች ቢሰረዙም፣ ቴዲ አፍሮ በውላቸው መሰረት 4.5 ሚ. ብር እንደሚከፈለው ምንጮች ገለፁ፡፡ እስካሁን በአገር ውስጥ ከተካሄዱ ኮንሰርቶች በላቀና ደረጃውን በጠበቀ መንገድ በድሬዳዋ ተጀምሮ በርካታ ከተሞችን እንዲያዳርስ ታስቦ የተፈረመው የቴዲ አፍሮና የበደሌ ቢራ ስምምነት፤ በኢንተርኔት በተካሄደ የተቃውሞ ዘመቻ ታውኮ ነው ሳምንት ሳይሞላው የፈረሰው፡፡ ከ20ሺ በላይ ሰዎች በኢንተርኔት በተሰባሰበ ድምጽ ለተካሄደው የተቃውሞ ዘመቻና ውዝግብ እንደመነሻ ሆኖ የሚጠቀሰው ዐረፍተ ነገር “የአፄ ምኒልክ ጦርነቶች ቅዱስ ናቸው” የሚል አባባል ሲሆን፤ ቴዲ አፍሮ የኔ አባባል አይደለም በማለት ማስተባበሉ ይታወሳል፡፡ በምኒልክ ጦርነት ብዙ ሰው አልቋል በሚል የገፋው ተቃውሞ፤ በደሌ ከቴዲ አፍሮ ኮንሰርት ጋር እንዳይተባበር ለሄኒከን ኩባንያ ጥያቄውን በማቅረብ እንዲሰረዝ አድርጓል፡፡
የቀድሞ የአገሪቱ ነገሥታትን በተመለከተ፣ በተለይም በአፄ ምኒልክ ዙሪያ ከየአቅጣጫው “መልካም ወይም መጥፎ ናቸው” የሚባሉ የንጉሱ ድርጊቶች እየተጠቀሱ በተደጋጋሚ የፖለቲካ ጭቅጭቆች፤ መነሳታቸው አዲስ አይደለም፤ በአንድ በኩል ምኒልክ ለአገሪቱ ነፃነት፣ አንድነትና ሥልጣኔ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል የሚሉ እንዳሉ ሁሉ፤ ስልጣናቸውን ለማስፋፋት ባካሄዱት ጦርነት ግፍ ተፈጽሟል፤ ብዙ ህዝብ አልቋል ብለው የሚያወግዙም ጥቂት አይደሉም፡፡ በመሃል ደግሞ፣ በታሪክ የተከሰቱ ነገሮችን ወደኋላ ተመልሶ መለወጥ እንደማይቻል የሚገልፁ ወገኖች፤ መጥፎ ነገሮችን እያስተካከልን መልካም ነገሮች ላይ አተኩረን እየወረስን ማሳደግ አለብን በማለት ለማስታረቅ የሚሞክሩ አሉ፡፡ ከተለያዩ አካባቢዎችና ብሔረሰቦች የፈለቁ ጀግኖች ከአፄ ምኒልክ ጋር ለአገራቸው ነፃነትና ስልጣኔ ተጣጥረዋል በማለት ከአስታራቂዎቹ ወገን የተሰለፈው ቴዲ አፍሮ፤ የምኒልክን መቶኛ ሙት ዓመት በማስመልከት ለ“እንቁ” መጽሔት በሰጠው ቃለ ምልልስ፣ ካለፈው ዘመን የሚወረሱ መልካም ታሪኮችን ጠቅሶ፣ የስህተቶችና የጥፋቶች መድሃኒት ፍቅር ነው በማለት የዘረዘራቸው ሃሳቦች ታትመው ወጥተዋል፡፡
“የአፄ ምኒልክ ጦርነቶች ቅዱስ ናቸው” የሚል ሃሳብ ግን እንዳልተናገረና በመጽሔቱ እንዳልታተመ በመጥቀስ ያስተባበለው ቴዲ አፍሮ፤ በኢንተርኔት የተሰራጨው አባባል እኔን አይወክልም ማለቱ ይታወሳል፡፡ የበደሌ ቢራ ባለቤት የሆነው የአለማችን ታዋቂ ቢራ አምራች ኩባንያ ሄኒከን፤ የበደሌ ቢራ ፋብሪካ እና የቴዲ አፍሮ ስምምነት እንዲሰረዝ የወሰነው፤ እንደብዙዎች ኩባንያዎች ሁሉ አደባባይ በወጣ ውስብስብ የፖለቲካ ውዝግብ ውስጥ መዘፈቅ ባለመፈለጉ እንደሆነ ምንጮቹ ተናግረዋል፡፡ እነዚሁ ቅርበት ያላቸው ምንጮች እንደገለፁት፤ በደሌ ቢራ “የፍቅር ጉዞ” በሚል ስያሜ ከዚህ ሳምንት ጀምሮ በበርካታ ከተሞች በተከታታይ ለሚካሄዱ ኮንሰርቶች 25ሚ. ብር ገደማ መድቦ ነበር፡፡ በደሌ 4.5 ሚ. ብር ለቴዲ አፍሮ ለመክፈል ተስማምቶ ውል ሲፈራረም 1.5 ሚ ብር የመጀመሪያ ክፍያ እንደፈፀመ የገለፁት እነዚሁ ምንጮች፤ በተለያዩ ከተሞች የሚቀርቡት ኮንሰርቶች ደረጃቸውን የጠበቁና ድምቀትን የተላበሱ ለማድረግ ከ20 ሚ. ብር በላይ ወጪ ለማድረግ ተዘጋጅቶ ነበር ብለዋል፡፡ በደሌ ቢራ በራሱ መሪነት በሚያዘጋጃቸው ኮንሰርቶች ላይ፣ ከትኬት ሽያጭ የሚሰበሰበውን ገቢ ለበጐ አድራጐት ድርጅቶች ለመለገስ ሃሳብ እንደነበረውም ምንጮቹ ጠቅሰዋል፡፡
በደሌ ከኮንሰርቶቹ ዝግጅት ራሱን ለማግለል ሲወስን፣ ቀደም ሲል የተፈራረመውን ውል በሚመለከት ከቴዲ አፍሮ ጋር ተደራድሮ የውል ማፍረሻ ስምምነት መፈራረሙንም ምንጮቹ ገልፀዋል፡፡ የስምምነት ማፍረሻ ስምምነቱንና የክፍያውን መጠን በተመለከተ በደሌ እና ቴዲ አፍሮ ዝርዝር መግለጫ ካለመስጠታቸውም ባሻገር፣ ከሁሉም ወገኖች መረጃ ለማግኘት የተደረጉ ሙከራዎች አልተሳኩም። በድርድር የተቋጩ ጉዳዮች ላይ ተዋዋይ ወገኖች ጉዳዩን በተናጠል በይፋ ላለመግለጽ መስማማታቸው የተለመደ እንደሆነ ምንጮቹ ጠቅሰው፤ በደሌ የመጀመሪያ ክፍያውን ጨምሮ ለቴዲ አፍሮ 4.5 ሚ. ብር የሚከፍል መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ ብለዋል፡፡ በኢንተርኔት ሲካሄድ የነበረው ዘመቻ፣ የበደሌ እና የቴዲ አፍሮ የስምምነት ውል ከፈረሰ በኋላ ቢረግብም፤ ያንን ተከትለው የመጡ ሌሎች ዘመቻዎች መፈጠራቸው አልቀረም፡፡ የቴዲ አፍሮን ኮንሰርት ለመቃወም የተጀመረው ዘመቻ፣ በተቃራኒ ኮንሰርቱን በመደገፍ ከተፈጠረው ሌላ ዘመቻ ጋር እንካ ሰላንቲያው ቀጥሏል፡፡ በቅርብ ጊዜ የሚካሄድ ኮንሰርት ባለመኖሩ ጭቅጭቁና ዘመቻው ምን ያህል የፌስቡክ ዕድምተኞችን ሳያሰለች ሊቀጥል እንደሚችል ገና አልታወቀም፡፡
ምንጭ አዲስ አድማስ

ሻምበል ጉታ ዲንቃ፤ ጊዜውን ጠብቆ ይነጋል – ከፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም

በአሁኑ ጊዜ ወያኔ ሰውን እያፈረሰ፣ ማህበረሰብን እያፈረሰ ሰማይ-ጠቀስ ሕንጻዎችን በሚሠራበት ጊዜ፣ ከትናንት ወዲያ የሰዎችን ቤቶች አፍርሶ ትናንት የመኪና መንገድ ከሠራ በኋላ ዛሬ መንገዱን አፍርሶ የባቡር መንገድ እየተሠራ አዲስ አበባ በትራፊክ መጨናነቅ መኪና መንዳት አደገኛ በሆነበት ጊዜ፣ ዛሬ ባለሥልጣኖች የሚሠሩት ጠፍቶአቸው የጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ የሚባለውን በአማካሪዎች ከሞሉት በኋላ ለሚኒስትሮችም አማካሪ መሾም በተጀመረበት ጊዜ፣ ዛሬ በሳኡዲ አረብያ ኢትዮጵያውያን እንደአደገኛ አውሬ እየታደኑ በሚደበደቡበት፣ በሚታሰሩበት፣ በሚደፈሩበትና በሚገደሉበት ጊዜ፣ ዛሬ በኬንያና በዩጋንዳ እንዲሁም በእሥራኤል ኢትዮጵያውያንን የማንገላታት ዝንባሌዎች በሚታዩበት ጊዜ፣ ዛሬ ኢትዮጵያውያን ከስዊድን እስከአውስትራልያ እየተሰበሰቡ በመጮህ ለማይሰሟቸው ሁሉ አቤቱታቸውን በሚያቀርቡበት ጊዜ፣ ዛሬ በተለያዩ አገሮች በኢትዮጵያውያን ላይ በሚፈጸመው ጥቃትና በደል፣ አለሁላችሁ የሚል መንግሥት በሌለበት ጊዜ —- ዛሬ ታሪካዊትዋ ኢትዮጵያ፣ ራሳቸውን የሚያከብሩና ኩራት ራታችን የሚሉት ኢትዮጵያውያን አልቀው ለሆድ በየሰው አገር መሰደድ ባህል በሆነበት ጊዜ፣ ዛሬ ዶር. በድሉ ዋቅጅራ ስለኢትዮጵያና ስለኢትዮጵያውያን ውርደት ደጋግሞ የነፍሱን ኡኡታ ባሰማበት ጊዜ በድንገት አንገታችንን ቀና አድርጎ ኩራታችንን ሊያስጎነጨን የሞከረ ሰው ተገኘ! ኢትዮጵያ ሁሌም የተአምር አገር ነች።

በታላቁ ሰው በኔልሰን ማንዴላ እረፍት ምክንያት አንድ ተደብቆ የኖረ ክቡር ኢትዮጵያዊ ብቅ አለ፤ ማንዴላ ለሥልጠና በኢትዮጵያ በነበረበት ጊዜ ምናልባትም እንግሊዞች ማንዴላን ሊያስገድሉ ከጠባቂዎቹ አንዱ የነበረውን ወታደር በገንዘብ ገዝተው ዓላማቸውን ለመፈጸም አቅደው ነበር፤ ወታደሩ ገንዘቡን ከተቀበለ በኋላ ሀሳቡን ለውጦ ገንዘቡን ለአለቃው ሰጠ፤ ማንዴላ ከሞት ተረፈ፤ አንድ ተራ ኢትዮጵያዊ ራሱንና አገሩን የሚያስከብር ሥራ ሲሠራ የሚኮሰኩሳቸው ባለሥልጣኖች ለእነሱ የማይተላለፍ ክብር በመሆኑ ተዳፍኖ እንዲኖር አደረጉት፤ እነሱ ሞተው ወይም ተሰድደው ሲያልቁ የተዳፈነው ምሥጢር ብቅ አለ፤ ባለሥልጣኖቹ ሸልመውት ይሆናል፤ ግን አላከበሩትም፤ ሻምበል ጉታን ያከበረው የማንዴላ ሞት ነው፤ የሚያሳዝነው ማንዴላ ይህንን የሱን ሕይወት ለማትረፍ ሁለት ሺህ ፓውንድ ያጣውን ኢትዮጵያዊ ወታደር ሳያውቀው መሞቱ ነው።
የኢትዮጵያ አርበኞች ታሪካቸው ተቀብሮ የቀረው እንዲህ እየሆነ ነው፤ ታዴዎስ ታንቱ ሥራዬ ብሎ የተረሱ አርበኞችን ከመቃብር እያወጣ ያስተዋውቀናል፤ በሌሎች አገሮች እንደዚህ ለአገር ትልቅ ፋይዳ ያለው ሥራ በአንድ ሰው በበጎ ፈቃድ የሚሠራ ሳይሆን ዋና የመንግሥት ተግባር ነው።
ሻምበል ጉታ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ባይሆንም ራሱን ችሎ ለኔልሰን ማንዴላ መቃብር ደርሶአል፤ በአገር ደረጃ በሥልጣን ወንበሮቹ ላይ ለአገር የሚያስቡ ሰዎች አለመኖራቸውን ለማወቅ ግሩም ማስረጃ ነው፤ ለቀብር የሄደው ባለሥልጣን ሻምበል ጉታን ይዞ ቢሄድ ኖሮ ለራሱም ሆነ ለአገሩ ክብርና ጌጥ ይሆንለት ነበር፤ ለደቡብ አፍሪካ ሕዝብም ሆነ ለዓለም በመላ አንድ ኢትዮጵያዊ ወታደር አልሸጥም-አልለወጥም ብሎ የኔልሰን ማንዴላን ሕይወት ማትረፉን በማስታወቅ አገሪቱን ያስከብር ነበር፤ የታፈነው ታሪክ አፈትልኮ ሲወጣ ከስደተኞች ጋር ተያይዞ መሆኑ ኢትዮጵያ የደረሰችበትን የአደባባይ መክሸፍ የሚያሳይ ነው፤ ባለቤት ያቀለለውን አሞሌ ባለዕዳ ተቀበለው፤ መንግሥት ያፈነውን ክብር ስደተኞች አጌጡበት!
ለእኔ አሁን አንድ ጥያቄ ይቀራል፤ ሻምበል ጉታ የአገሩን ክብር ከራሱ ጥቅም በላይ በማድረጉ፣ የተቀበለውን አደራ በመጠበቁ ቢያንስ ሁለት ሺህ ፓውንድ አጥቷል፤ እንዳጣ ሊቀር ነው? ቢያንስ የከፈለውን ሁለት ሺህ ፓውንድ ወይስ ያንን አሥር እጥፍ አድርገን እንከፍለዋለን? ሻምበል ጉታን የምናመሰግነው በርጥቡ ነው በደረቁ? እኛ ያለጥርጥር ኮርተንበታል፤ ሁላችንም በኢትዮጵያዊነታችን የሱን ክብር በመጋራት ራሳችንን አክብረናል፤ ሻምበል ጉታም በእኛ እንዲኮራና በእኛ እንዲከበር ማድረግ ያለብን ይመስለኛል፤ ስለዚህ ምን እናድርግ? ለራሱ ክብር፣ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን ክብር ሲል የከፈለውን እስቲ ከወሬ ያለፈ ነገር እናስብና ለዚህ ጀግና የምንችለውን አድርገንለት እግዚአብሔር ዕድሜ ይስጥህ እንበለው።
ምንጭ ዘ-ሐበሻ

Thursday, January 9, 2014

የቀደምቶቹን ወንጀል ለማጋለጥ መቃብር ሲምስ የኖረው ወያኔ በራሱ ጦር ካምፕ ውስጥ የተገኘውን አስከሬን መደበቅ ለምን አሰፈለገው?

አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ፈረንሳይ ለጋሲዮን በሚገኘው የክብርዘበኛ ጦር ካምፕ ውስጥ ማንነታቸው ያልታወቁ የ6 ዜጎች አስከሬን ለመንገድ ሥራ በተሠማሩ ቆፋሪዎች አማካኝነት መገኘቱ የሰሞኑ አሳዛኝ ዜና ነው።
አንድ አይነት ቀለም ባላቸው ብርድ ልብሶች ተጠቅልለው ከተገኙ 6 አስከሬኖች የመጀመሪያዎቹ ሁለት ሰለባዎች ታስረውበት የነበረው የእጅ ሰንሰለታቸው እንኳ እንዳልወለቀና ከተቀሩት የአንዱ እጆች ደግሞ የፍጥኝ ወደ ኋላ እንደታሰሩ መገኘታችው ግድያው በቅርብ እንደተፈፀም አንዱ አስረጂ ነው።
በእንዲህ አይነት ጭካኔ የተገደሉ ዜጎች አስከሬን መገኘት በመንግሥት ተብየው አካል ካለመገለጹም በላይ ግቢውን በማስተዳደር ላይ የሚገኘው 3ኛ ክፈለ ጦርም ሆነ በግብር ከፋይ ገንዘብ የሚተዳደሩ መገናኛ ብዙሃን እስከዛሬ አንድም ቃል መተንፈስ አለመፈለጋቸው ጉዳዩን እጅግ የሚያሳዝን ብቻ ሳይሆን የሚያስገርምም አድርጎታል። ይባስ ተብሎም በመንገድ ሥራ ቁፋሮው የበለጠ አስከሬን ሊወጣ ይችላል በሚል ስጋት አካባቢው በፖሊስ እንዲታጠር ከተደረገ በኋላ ሥራውም እንዲቋረጥ ተደርጓል።
በፓለቲካ መስመር ልዩነት ምክንያት ደርግ ያለ ርህራሄ የጨፈጨፋቸውን ከመቃብር እያወጣ ዘመድ አዝማድ በማላቀስ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ሲዳክር የኖረ አገዛዝ በእንዲህ አይነት አሳዛኝ ሁኔታና አጋጣሚ የተገኘውን የጅምላ አስከሬን አይቶ አንዳላየ ለማለፍ መሞከሩ ለምን ይሆን?
አብዛኛው የአዲስ አበባ ነዋሪ እንደሚያስታውሰው የክብር ዘበኛ ጦር ካምፕ በመባል የሚታወቀው የጃን ሜዳ 3ኛ ክፍለ ጦር ግቢ ድህረ ምርጫ 97 ወያኔ ለጅምላ እስር ቤትነት ከተጠቀመባቸው የማጎሪያ ቦታዎች አንዱ ነበር። ከዚያን ጊዜ በፊትና በኋላም ቢሆን ካምፑ በወያኔ ጠላትነት ተፈረጀ በጸጥታ ሠራተኞች ከታገቱ በኋላ አድራሻቸው እስከዛሬ ተሰውሮ ላሉ በርካቶች በምስጢር እስርቤትነት በማገልገል ላይ ከሚገኙ ወታደራዊ ካምፖች አንዱ እንደሆ ይታወቃል።
ዘመድ አዝማዶቻቸው ይመለሳሉ ብለው ሲጠብቋቸው ሳይመለሱ እንደወጡ የሚቀሩ በርካታ ዜጎች አሉ። በእንዲህ ሁኔታ ወጥተው ከቀሩ መካከል ከሰሞኑ የስድስቱ መቃብር በአጋጣሚ ተገኝቷል። የተገነዙበት ብርድ ልብስ ይነትብና ምንም ዓይነት ብልሽት ሳይደርስበት መገኝቱ ግዲያው በህወሃት ዘመነ መንግስት ስለመፈፀሙ ጥሩ ማስረጃ ነው። ለህወሃት ሰው መግደል ሥራ እንጂ ወንጀል አይደለም። በህወሃት ነፍሰ ገዳይ ይሞገሳል ይሾማል እንጂ አይወቀሰም አይጠየቅም። የስድስቱ ስዎች አስከሬን ሲገኝ መንግስትነኝ የሚለው ህወሃት አይቶ እንዳላየ መሆን ብቻ ሳይሆን ሌሎች አካላትም የሥፍራውን ሚስጢር እንዳያዩ ከልክሏል።በቁጥጥሩ ሥር ያሉ መገናኛ ብዙሃንም ዜናውን እንዳይናገሩ ታግደዋል። ህወሃት ከሚሰራቸው አስገራሚ ወንጀሎች መካከል አንዱይሄው ነው። ይሄ ግድያ በሌላ አካል ተፈፅሞ ቢሆን ኑሮ በረከት ስምዖንና እና ሺመልስ ከማል እየተፈራረቁ ያደነቁሩን ነበር።ይሄ የራሳቸው የእጅ ሥራነውና አይነገርም። የሄንንም የሚናገር እንደ ኢሳት ያለ ነፃ ሚዲያ ካለም ይታፈናል። አሸባሪም እየተባለ ይፈረጃል።
ግንቦት ሰባት የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ እነዚህ ዜጎች በህወሃት ተግድለው እንደተጣሉ ያምናል። ውሎ አድሮ እውነቱ እስከሚወጣ ድረስ ግን ዜጎች በሙሉ ይሄን ግድ በተመለከተ መረጃ የመሰብሰብና የማሰረጫት ሥራችውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ እናሳስባለን። ይሄን ወንጀል የፈፀሙ አካላት መጠየቅ አለባቸው። የዜጎች ደም እንዲሁ በከንቱ ፈሶ መቅረት የለበትም።
ለኢትዮጵያ ህዝብ መብትና ጥቅም እንታገላለን የሚሉ የፖለቲካና የስቪክ ድርጅቶች እንዲሁም ለሰው ልጆች የሰብአዊ መብት የሚሟገቱ ሁሉ የተገኘው አስከሬን በአስቸኳይ ተመርምሮ ማንነታቸው ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲገለጽ፤ ተጨማሪ አስከሬን ሊገኝ ይችላል በሚልስጋት የመንገድ ቁፋሮውን ከሰዎች እይታውጪ ለማካሄድ እንዲቋረጥ የተደረገው ሥራ ለህዝብ እይታ ግልጽ በሆነመንገድ በአስቸኳይ እንዲጀመር የመጠየቅ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ግንቦት 7 ያሳስባል::
በዚህአጋጣሚ ወያኔ ሥልጣን ከተቆጣጠረበት ጊዜጀምሮ በሱማሌ፣ በጋምቤላ፣ በአዋሳ፣ በጎንደር፣ በአዲስ አበባና ሌሎች የአገራችን ክፍሎች በጠራራ ጸሃይ ካስጨፈጨፋቸው በተጨማሪ በፖለቲካ እምነታቸው ምክንያት ታግተው በየእሥርቤቱ የተወረወሩትንና ከታገቱበት ዕለት ጀምሮ እስከ ዛሬ የደረሱበት ያልታወቁ ወገኖቻችንን ዝርዝር በአስቸኳይ ያሳውቅ ብለን አንመክረውም።እኛ ግን ህወሃት የደበቀውን ወንጀል ሁሉ ህዝብ እንዲያውቀው ለማድረግ ያለምንም ማቅማማት ጠንክረን እየሰራን ነው። መንግስት ነኝ ብሎ በሥልጣን ላይ የሚወጣ ማንኛውም አካል የህዝብ አገልጋይ እንጂ ነፍሰገዳይ እንዳይሆን የጀመርነው ትግል ተጠናክሮ ይቀጥላል።
እንግዲህ ህወሃት በህዝባችንና በአገራችን ላይ የሚፈጽመውን ሰቆቃ ለማስቆም ግንቦት 7 የጀመረውን የነጻነት ትግል አጠናክሮ እንደሚቀጥል እያስታወቅን እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ እንዲህ በየቦታው ተገድሎ ከመጣል ራሱን ለመታደግ ሲል የነፃነቱ ትግል አካል እንዲሆን ጥሪያችንን አሁንም ደግመን እናቀርባለን::
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!

Wednesday, January 8, 2014

The Silent Genocide on the Amhara Documentary.


Government carries out secret mass sterilization among Amhara women.


2014፡ የኢትዮጵያ የአቦ-ጉማሬው ትውልድ ዓመት – ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
(ክፍል አንድ) 2014 የኢትዮጵያ የአቦ -ጉማሬው ትውልድ የሚነሳሳበት ዓመት፣
እ.ኤ.አ በ2013 በመጀመሪያው ሳምንት ባቀረብኩት ሳምንታዊው ትችቴ ዓመቱ “የኢትዮጵያ የአቦሸማኔው (የወጣቱ ትውልድ) ዓመት ይሆናል “የሚል ትንበያ ሰጥቼ ነበር፡፡ እንደትንበያውም ዓመቱ የኢትዮጵያ የአቦሸማኔው (ወጣቱ) ትውልድ ታላቅ የስኬት ዓመት ሆኖ ተጠናቅቋል፡፡
2014 ደግሞ “የኢትዮጵያ የአቦ-ጉማሬው ትውልድ ዓመት ይሆናል” የሚል ትንበያ እሰጣለሁ፡፡  የአቦ-ጉማሬው ትውልድ በአፈጣጠሩ የጉማሬው (የቀድሞው ትውልድ) አባል ሲሆን በተግባራዊ እንቅስቃሴው ግን እንደ አቦሸማኔው (ወጣቱ ትውልድ) የሚያስብ፣ አቦሸማኔውን የሚመስል እና እንደ አቦሸማኔው ሁሉ የክንውን ድርጊቶችን የሚፈጽም የማህበረሰብ ክፍል ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የአቦ-ጉማሬው ትውልድ ለፍትህ እና ለነጻነት በሚደረገው የትግል ሂደት ላይ የጉማሬው (የቀድሞው ትውልድ) የሚያንጸባርቃቸውን ድክመቶች በሚገባ የተገነዘበ እና እነዚህን ግድፈቶች በማስወገድ የወጣቱን የትግል መንፈስ እና ወኔ ወደ ላቀ የእድገት ምዕራፍ ለማሸጋገር በአንድ ዓላማ ለአንድ ዓላማ ከአቦሸማኔው (የወጣቱ) ትውልድ ጎን በመሰለፍ የሚሰራ የህብረተሰብ ክፍል ነው፡፡
የኢትዮጵያ የአቦ-ጉማሬው ትውልድ በአፈጣጠሩ ልዩ የሆነ የትውልድ ዝርያ ነው፡፡ ይህ ትውልድ በተፈጥሮው ድልድይ ቀያሽ እና በኃይል አሰላለፍ ላይ ያለውን ወቅታዊ እና ነባራዊ ሁኔታ በተገቢው መንገድ እያጠና ወጣቱን ትውልድ ለድል የሚያበቁ የኃይል ምንጮችን ቀጣይነት ባለው መልክ የሚፈበርክ የህብረተሰብ አካል ነው፡፡ የአቦ-ጉማሬው ትውልድ ወጣቱን ከቀዳሚው ትውልድ የሚያገናኙ ጠንካራ ትውልድ አገናኝ የትውልድ ድልድዮችን የሚገነቡ ናቸው፡፡ ደኃውን ከሀብታም የሚያገናኙ ድልድዮችን የሚገነቡ ናቸው፡፡ ህዝቦችን ከአምባገነናዊ ስርዓት ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት የሚያሸጋግሩ ድልድዮችን የሚገነቡ ናቸው፡፡ በጎሳ የተለያዩ ህዝቦችን የሚያገናኙ ድልድዮችን የሚገነቡ ናቸው፡፡ “ክልላዊ ደሴቶች (የጎሳ መንደሮች ወይም ባንቱስታንስ)” ተብለው ተነጣጥለው የሚኖሩ ህዝቦችን የሚያገናኙ ድልድዮችን የሚገነቡ ናቸው፡፡ በቋንቋ፣ በኃይማኖት እና በክልል ተነጣጥለው የተቀመጡ ህዝቦችን የሚያገናኙ ድልድዮችን የሚገነቡ ናቸው:: ባለመተማመን ሸለቆዎች፣ በእምነት ማጣት ጥልቅ  ገደሎችና   እና  በጥርጣሬ ጎርፍ ወንዞች ላይ ድልድዮችን የሚገነቡ ናቸው፡፡ ብሄራዊ ዕርቅ ለማውረድ እና የብሄራዊ አንድነትን ለማምጣት ህዝቦችን የሚያገናኙ ድልድዮችን የሚነገነቡ ናቸው፡፡ በአገር ቤት ውስጥ ያሉትን ወጣቶች በውጭ አገር ከሚኖሩት የዲያስፖራ ወጣቶች ጋር የሚያገናኙ ድልድዮችን የሚገነቡ ናቸው፡፡ የአቦ-ጉማሬው ትውልድ ለመሻገር አስቸጋሪ በሆኑ የውኃ አካላት ላይ ድልድዮችን የሚገነቡ ናቸው፡፡
የኢትዮጵያ የአቦ-ሸማኔው ትውልድ አባላት ኃይል አባዥዎችም ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ ዘለቄታ ያለው መዋቅራዊ ለውጥ ለማምጣት እንዲቻል የአቦሸማኔው ትውልድ አባላት ከእራሳቸው እውቀት፣ ዘዴ እና ልምድ አኳያ በመቀመር የወጣቱን ኃይል፣ ፍቅር እና ጽኑ ዓላማ በአግባቡ ያለምንም ብክነት በስራ ላይ እንዲውል ያደርጋሉ፡፡ በግትር የአምባገነኖች ተለዋዋጭ ባህሪያት ላይ የእራሳቸውን ፈጠራ በመጠቀም በወሳኝ ጉዳዮች ላይ የወጣቶች የለውጥ አራማጅነት የትግል መንፈስ ውጤታማ እና ስኬታማ እንዲሆን ያደርጋሉ፡፡
የአቦ -ጉማሬው ትውልድ አባል በመሆኔ ኩራት ይሰማኛል!
የኢትዮጵያ የአቦሸማኔ ትውልድ በአስፈሪ ዕጣ ፈንታ ውስጥ፣
በእኔ አስተያየት የኢትዮጵያ 21ኛው ክፍለ ዘመን ግንባርቀደም ችግር ሆኖ የሚቀርበው የኢትዮጵያ ወጣቶች ችግር ነው፡፡ በአሜሪካ የህዝብ ቆጠራ ቢሮ ትንበያ መሰረት ከ37 ዓመታት ባነሰ ጊዜ ውስጥ የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር አሁን ካለበት ደረጃ በሶስት እጥፍ በማደግ 278 ሚሊዮን በመሆን ኢትዮጵያን ከዓለም በህዝብ ብዛት ከአንድ እስከ አስር ደረጃ ከሚይዙ አገሮች ተርታ ውስጥ ምድብተኛ ያደርጋታል፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ዕድገት ላለፉት አስርት ዓመታት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ነው የመጣው፡፡ እ.ኤ.አ በ1967 የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር 23.5 ሚሊዮን ነበር፡፡ በ1990 ወደ 51 ሚሊዮን ያደገ ሲሆን በ2003 ደግሞ ቁጥሩ እየጨመረ በመምጣት 68 ሚሊዮን ደረሰ፡፡ በ2008 ይህ ቁጥር እየጨመረ በመምጣት ወደ 80 ሚሊዮን ከፍ አለ፡፡ በ2013 የኢትዮጵያ ህዝብ ብዛት ከ94 ሚሊዮን በላይ እንደሚደርስ ተገምቷል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ወደ 70 በመቶ (66 ሚሊዮን) የሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ከ35 ዓመት በታች እንደሆነ ይገመታል፡፡ እ.ኤ.አ ከ1995 ጀምሮ የኢትዮጵያ ህዝብ ዓመታዊ አማካይ የዕድገት መጣኔ ከ3 በመቶ በላይ እንደሆነ ቀጥሏል፡፡
ኔልሰን ማንዴላ እንዲህ በማለት አመላክተዋል፣ “ልጆቻችን ታላቅ ኃብቶቻችን ናቸው፡፡ ልጆቻችን የወደፊት ተስፋዎቻችን ናቸው፡፡ የልጆቻችንን መብት የሚጥስ ማንም ቢሆን የህዝባችንን የትስስር ክር የሚበጥስ እና አገራችንን የሚያዳክም ነው፡፡“ ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ወጣቶች የአገሪቱ ታላቅ ኃብቶች ናቸው ብለን ካሰብን እና በአሁኑ ጊዜ በታላቅ አደጋ ውስጥ ይገኛሉ ከተባለ የሀገሪቱ የወደፊት ዕጣ ፈንታም በአደጋ ላይ መሆኑን በግልጽ ያመላክታል፡፡ የኢትዮጵያ ታላቅ ኃብቶች ተረስተዋል፣ መብቶቻቸው ተደፍጥጠዋል፣ ወርቃማው ጊዚያቸው፣ ዕውቀታቸው፣ ጉልበታቸው እና ብሩህ አዕምሯቸው ለሀገር ጥቅም ሳይውል ቀርቷል፣ እንዲሁም ባክኗል፡፡ “ኢትዮጵያ ዝቅተኛ የሆነ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት የቅበላ መጣኔ (Enrollment Rate) ከሚያስመዘግቡ በዓለም ላይ ከሚገኙ አገሮች አንዷ ናት፡፡…የአፍሪካ የህዝብ እና የጤና ምርምር ማዕከል ባቀረበው ዘገባ መሰረት በኢትዮጵያ የትምህርት ጥራት እያሽቆለቆለ እና የክፍል ደጋሚ ተማሪዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣት፣ እንዲሁም በጾታ፣ በገጠር እና በከተማ መካከል የሚታየው ሰፊ ልዩነት የአገሪቱ ከባድ ፈተናዎች ሆነው ቀጥለዋል፡፡“ የከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎች ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመግባት፣ ወይም ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ስራ የማግኘት ዕድላቸው የመነመነ ሆኗል፡፡
እ.ኤ.አ በ2012 ዩኤስኤይድ/USAID በኢትዮጵያ ላይ ባደረገው ጥናት መሰረት “ኢትዮጵያ 50 በመቶ የከተማ ወጣቶች ስራ አጥ መጣኔ/Unemployment Rate በማስመዝገብ ከፍተኛ ደረጃ የያዘች መሆኗን እና 85 በመቶ ገደማ የሚሆነው ህዝብ በሚኖርበት የገጠር አካባቢ ያለው ወጣት ከፍተኛ በሆነ ስውር ስራ አጥነት/underemployment/disguised unemployment ውስጥ ተተብትቦ ይገኛል፡፡“ በማለት የጥናት ውጤቱን ይፋ አድርጓል፡፡ በ2012 በዓለም አቀፍ የዕድገት ማዕከል/International Growth Center በተባለ ድርጅት በተደረገ የወጣት ስራ አጥነት ሌላ የጥናት ዘገባ መሰረት “የአሁኑ የኢትዮጵያ የ5 ዓመት የልማት ዕቅድ ማለትም እ.ኤ.አ ከ2010/11–2014/15 ድረስ በሚዘልቀው ገዥው አካል የዕድገት እና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ/Growth and Transformation Plan እያለ በሚጠራው ዕቅድ ውስጥ የወጣቶች የስራአጥነት ጉዳይ አልተካተተም…“ ያ ጥናት “እ.ኤ.አ በ2011 38 በመቶ የሚሆነው ወጣት መደበኛ ባልሆነው የስራ ዘርፍ ተቀጥሮ የሚገኝ“ ሲሆን “ዝቅተኛ ተከፋይነት ያላቸው እና የምርት ጥራታቸውም ዝቅተኛ የሆኑ“ እንደነበሩ የጥናቱ ግኝት አመላክቷል፡፡ በርካታ ቁጥር ያላቸው ወጣቶች ስራ አጥ ሆነው ይገኛሉ፡፡ ሆኖም ግን ስራአጥ መሆናቸው ብቻ ሳይሆን   ወደፊትም ተቀጣሪ የመሆን ዕድል የላቸውም፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ወጣቶች ከትምህርት አደረጃጀቱ እና አሰጣጡ አንጻር የጥራት ጉድለት የሚንጸባረቅበት በመሆኑ መሰረታዊ የሙያ ክህሎት ያልጨበጡ በመሆናቸው ነው፡፡ ወጣቶቹ በስራ ላይ ለመቀጠር የሚችሉት በሰለጠኑባቸው እና ክህሎት በጨበጡባቸው የሙያ ዘርፎች በመንግስት ስር ያሉ ቀጣሪ መስሪያ ቤቶች ተቀጣሪዎችን በብቃታቸው እና በተወዳዳሪነታቸው መዝነው ሳይሆን አብዛኛውን ጊዜ ከገዥው አካል ጋር ካላቸው የፖለቲካ እና የማህበራዊ ግንኙነት ቅርርብ አንጻር የፓርቲ አባል በመሆን ብቻ ነው፡፡ ማንኛውም ወጣት ኢትዮጵያዊ በትክክል የእራሱን ጥረት አድርጎ የዩኒቨርስቲ ዲግሪ ከመያዝ ይልቅ የገዥውን ፓርቲ የአባልነት ካርድ መያዝ የበለጠ ዋጋ እንዳለው ይገነዘባል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ መሬት የሌላቸው የገጠር ወጣቶች ወደ ከተማ ስራ ፍለጋ በገፍ በሚመጡበት ወቅት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ የመጣውን ከገጠር ወደ ከተማ ፍልሰት፣ ስራ አጥነት እና ተስፋ የማጣት ቀውስ የበለጠ እያወሳሰበው ይገኛል፡፡
የኢትዮጵያ ወጣቶች አጠቃላይ የአገሪቱን የማህበራዊ ችግር ቀውሶች ቀንበር የመሸከም ኃላፊነት ወድቆባቸዋል፡፡ እንደሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ ጎል/GOAL ዘገባ ከሆነ በመንገዶች ላይ በመንከላወስ የሚኖሩ 150,000 ህጻናት ሲኖሩ ከእዚህ ውስጥ 60,000 የሚሆኑት የአገሪቱ ዋና ማዕከል በሆነችው በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ናቸው፡፡ ህጻናት ቤትአልባ የሚሆኑባቸው እና ወደ መንገድ የሚወጡባቸው የመጀመሪያዎቹ ዓመታት በአማካይ 10 እና 11 ዓመት ዕድሜ ሲያስቆጥሩ ነው፡፡ ወጣቶች በኤችአይቪ ኤድስ እና በሌሎች በግብረስጋ ግንኙነት በሚተላለፉ በሽታዎች የመጠቃት ዕድላቸው እየጨመረ በመምጣት ላይ ይገኛል፡፡ የተሻለ ዕድል ማግኘት ያልቻሉት በርካታዎቹ የኢትዮጵያ ወጣቶች በአደንዛዥ ዕጽ እና አልኮል እንዲሁም በዘሙት አዳሪነት እና በሌሎች የወንጀል ድርጊቶች ተዘፍቀው ይገኛሉ፡፡ ምንም ዓይነት የትምህርት ዕድል እና ስራ ያላገኙ የከተማ ወጣቶች ዕጣፈንታቸው ስራየለሽ፣ ቤትየለሽ፣ እረዳትየለሽ እና ተስፋየለሽ መሆን ብቻ ሆኗል፡፡
ከአስርት ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል “የብሄራዊ ወጣቶች ፖሊሲ” ሰነድ አዘጋጀ እና “44 በመቶ የሚሆነው ህዝብ ከፍጹም የድህነት ወለል በታች ነው“ በማለት መግለጫ ሰጠ፡፡ በዚህ ዓይነት የድህነት ሁኔታ ውስጥ ወጣቱ በከፍተኛ ሁኔታ ለጥቃቱ ተጋላጭ የሆነ የህብረተሰብ ክፍል ነው… ከስራ አጥ ወጣቱ አብዛኛውን የሚሸፍኑት ሴት ወጣቶች የመሆናቸው ሀቅ በአብዛኛው በሚባል መልኩ የችግሩ ሰለባ ወጣት ሴቶች መሆናቸውን ያመላክታል፡፡” በአጠቃላይ መልኩ ሲታይ “የብሄራዊ ወጣቶች ፖሊሲ” ተብሎ የሚጠራው የድርጊት መርሀግብር ለገዥው አካል እና ለፓርቲው ደጋፊነት መመልመያ ሰነድነት ከማገልገል በዘለለ የፈየደው ነገር የለም፡፡ የዚህን ፖሊሲ የማስፈጸም ብቃት ከፍ ወዳለ ደረጃ ለማድረስ “መንግስት የመምራት፣ የማስተባበር፣ የማዋሀድ እና የመገንባት ኃላፊነት ተጥሎበታል” በማለት በግልጽ አስቀምጦታል፡፡ ሆኖም ግን የዓለም አቀፉ የዕድገት ማዕከል የጥናት ውጤት በግልጽ እንደሚያመለክተው ከ2010/11-2014/15 ድረስ ለአምስት ዓመታት በሚዘልቀው የአሁኑ የኢትዮጵያ የዕድገት እና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ውስጥ ቀጥታ የወጣቱን የስራ አጥነት የሚመለከት ጉዳይ አልተካተተም፡፡ “ብሄራዊ የወጣቶች ፖሊሲ ሰነድ” በተግባር ላይ ያልዋሉ የብሄራዊ ወጣት ፖሊሲዎች ዓለም ዓቀፋዊ የመረጃ ቋት በመሆን ላለፉት አስርት ዓመታት በመደርደሪያ ላይ ተቀምጦ አቧራ በመጠጣት ላይ ይገኛል፡፡
የሁለት ትውልዶች ትረካ፣ በኢትዮጵያ የጉማሬው እና የአቦሸማኔው ትውልዶች ተቀራርቦ የመነጋገር አስፈላጊነት፣
አሁን በኢትዮጵያ የሰዓት አቆጣጠር መሰረት ስንት ሰዓት ነው? በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ የአቦ-ገማሬው ትውልድ ሰዓት ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ የአቦሸማኔው እና የጉማሬው ትውልዶች ተቀራርበው ለመነጋገር እና ብሄራዊ ዕርቅ ለማውረድ ጥረት የሚያደርጉበት የመጨረሻው ሰዓት ነው፡፡ ጊዜው የኢትዮጵያ እረፍትየለሾቹ የአቦሸማኔው ትውልዶች እና ተራማጁ፣ ብሩህ አዕምሮ ያላቸው እና አርቆ አሳቢነት የተላበሱት የጉማሬው ትውልዶች በአንድ መድረክ በአንድነት ተቀራርበው የሚያስቡበት እና በአንድነት ወሳኝ እርምጃ የሚወስዱበት ጊዜ ነው፡፡ አሁን ጊዜው 2014 ነው፡፡
ተቀራርቦ መነጋገር ስል በአቦሸማኔው እና በጉማሬው ትውልድ መካከል በግልጽ እና ግልጽ ባልሆኑ መድረኮች ሁሉ… ማለትም ከእራት ግብዣ አዳራሾች እስከ አካዳሚክ የጥናት ማዕከሎች፣ ከቤተክርስቲያኖች እና መስጊዶች እስከ ሲቪክ ድርጅቶች እና ማህበራት ድረስ የሚያካትት የንግግር እና የውይይት መድረኮችን ማለቴ ነው፡፡ የመነጋገሪያ አጀንዳዎቹ ያልተወሰኑ ሊሆኑ ይችላሉ፣ ነገር ግን ዓላማዎች አንድ ዓይነት ናቸው፡፡ በአሮጌዎቹ ሀሳቦች ላይ ጥያቄዎችን ለማንሳት እና ጥሩዎችን ለማካተት አስፈላጊ ያልሆኑትን ደግሞ ለማስወገድ የንግግር መድረኮች ሊኖሩን ይገባል፡፡ አሮጌዎችን፣ ጠባብ አስተሳሰቦችን እና ለሰላም እና እድገት እንቅፋት የሚሆኑ አሉታዊ እንቅስቃሴዎችን ለመለወጥ የንግግር መድረኮች አስፈላጊዎች ናቸው፡፡ ስለፖለቲካ፣ መንግስት እና ህዝብ አዳዲስ ሀሳቦችን ለማመንጨት የንግግር መድረኮች አስፈፈላጊዎቻችን ናቸው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ቀፍድደው ከያዙን የማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ችግሮች በድል አድራጊነት ለመውጣት የንግግር መድረኮችን በማመቻቸት ገንቢ እና አዳዲስ የመፍተሄ ሀሳቦችን በማመንጨት የውይይት መድረኮችን ማዘጋጀት ይኖርብናል፡፡ ላለመስማማትም ቢሆን በሰለጠነ እና በመከባበር ላይ በተመሰረተ አቀራረብ የንግግር መድረኮችን በማዘጋጀት ስምምነት ማድረግ ይቻላል፡፡ ስህተቶችን በማረም ወደ ትክክለኛው መንገድ ለመምጣት እንዲቻል ተቀራርቦ መወያየት አስፈላጊ እንደሆነ እርስ በእራሳችን መተማመን አለብን፡፡ ይህንን ከባድ ኃላፊነት ለመሸከም እና ለማስተባበር የሚችለው “አዲሱ ትውልድ” ያስፈልገናል፡፡ ሀሳበ ሰፊዎቹ የአቦሸማኔው እና ተራማጅ የጉማሬው ትውልዶች የውይይቱን ሂደት ሊያፍጥኑልን ይችላሉ፡፡
የውይይቱ ዓላማ ያልሆነው የቱ ነው? እንዲካሄድ የሚፈለገው ውይይት አንዱ ሌላውን ጥላሸት ለመቀባት፣ ለመካሰስ እና አንዱ በሌላው ላይ ጣቶቹን ለመቀሰር አይደለም፡፡ እንደዚሁም ደግሞ ቀደም ሲል በተከናወኑ እና ባልተከናወኑ ድርጊቶች ላይ የሆድ ቁርጠት፣ የልብ ስብራት፣ ወይም ጥርስ መንከስ ድርጊቶችን ለማበረታታት አይደለም፡፡ የአቦ-ጉማሬው ትውልድ ኃላፊነት የያዘባቸው የንግግር መድረኮች ሁለት ዓላማዎችን ያካተቱ ናቸው፡፡ እነሱም 1ኛ) ዓለም አቀፋዊ ዕርቅ በማውረድ የንግግር ስራውን መጀመር እና 2ኛ) በአቦሸማኔው እና በጉማሬው ትውልዶች መካከል ባለው የስራ ክፍፍል እና ሚና መግባባት ላይ መድረስ ናቸው፡፡
“የቋንቋ” መግባባት ችግር ባለበት ሁኔታ ዓለም አቀፋዊ መግባባት ሊኖር አይችልም፡፡ በጸጥታ በሚናገሩት የኢትዮጵያ የጉማሬው ትውልድ አባላት እና በዚያ በማይሰማው ንግግር ከኢትዮጵያ የአቦሸማኔው ትውልድ ጋር የመግባባት ችግር አለ የሚል ጽኑ እምነት አለኝ፡፡ ጥቂት ምሳሌዎችን እስቲ እንመልከት፡፡ ብዙዎቻችን የጉማሬው ትውልድ አባላት ስለለውጥ ስናነሳ የሚታየን ነገር በአሁኑ ወቅት በስልጣን ላይ የሚገኘውን ገዥ አካል ከስልጣን መንበር ላይ በማስወገድ እራሳችንን ከስልጣን ወንበር ላይ ፊጥ ማድረግ ነው፡፡ በስልጣን ላይ ያሉት ሰዎች መጥፎዎች ናቸው፣ እኛ ግን ጥሩዎች ነን፡፡ አይደለም እኛ የተሻልን ነን፣ በእርግጥም እኛ እጅግ የተሻልን ነን፡፡ በአሁኑ ጊዜ በስልጣን ላይ ያሉት የጉማሬው ትውልድ አባላት እራሳቸውን ብቸኛ የለውጥ ሀዋርያ አድርገው ያስባሉ፡፡ እኛ የጉማሬው (የቀድሞው) ትውልድ አባላት ስለአመራር ጉዳይ ስናነሳ የአዲሱ ትውልድ አባላት የእኛን ትዕዛዞች ብቻ እንዲከተሉ እንፈልጋለን፣ ምክንያቱም እኛ ኃይል፣ ልምድ፣ ዘዴዎች እና/ወይም እውቀት ያለን አድርገን እንቆጥራለን፡፡ የኢትዮጵያ የአቦሸማኔው ትውልድ የበግ መንጋ ሆነው እኛን የሚከተሉ ብቻ እንጅ እነርሱ መልካም ነገሮችን በውል የሚያጤኑ እና ወሳኝ ድርጊቶችን ሊፈጽሙ የሚችሉ ልዩ ችሎታ እና የአመራር ብቃት ያላቸው ወጣቾች እንዳሉ ለመቀበል በጣም እንቸገራለን፡፡ ወጣቶቹ ከእኛ በተለየ መልኩ የእራሳቸው ልዩ የሆነ እና የእራሳቸው ነጻነት እንዲኖራቸው እንፈልግም፡፡ በአጠቃላይ ወጣቱን አሳንሶ የማየት ባህል ተጠናውቶናል፡፡ ወጣቱ ኃይል ዝቅ ያለ ዳኝነት የመስጠት ወይም ነገሮችን በጥልቀት የመረዳት ችሎታ ስለሚያንሰው የእኛን የበግ ጠባቂነት ሚና ማግኘት እና እኛ የምንነግራቸውን ብቻ መከተል አለባቸው እያልን አስተያየት እንሰጣለን፡፡ “ልጆችመታየት አንጂ መደመጥ የለባቸውም”፣የሚሉ ጊዜ ባለፈባቸው የአረጁ እና የአፈጁ አባባሎች ወጣቶቹን ዝቅ አድርገን እንመለከታለን፣ እንዲህ እያልንም እንተርትባቸዋለን፣ “ልጅ ያቦካው ለእራት አይበቃም“፡፡ የወጣቶቹን ሀሳቦች አናከብርም፣ ወይም ደግሞ ለየት ያለ ነገር ሲያቀርቡ እና የተሻሉ ነገሮችን ሲሰሩ እየተመለከትን አድናቆት አንቸራቸውም፣ ነገር ግን እነሱን ለመተቸት እና ለማውገዝ የሚቀድመን የለም፡፡
እኛ የጉማሬው ትውልድ አባላት ስለስልጣን ስንነጋገር ምንም ዓይነት ተጠያቂነት እና  ግልጽነት በሌለው መልኩ ስልጣንን እንድንይዝ እንገልጋለን፡፡ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ያለው የጉማሬ ትውልድ ስልጣኑን የሚጠቀምበት ለመከፋፈል እና ለመግዛት ነው፣ ስልጣናቸውን በስልጣን ላይ ለመቆየት ከህግ አግባብ ውጭ ይጠቀሙበታል፣ ስልጣናቸውን ከህግ አግባብ ውጭ በመጠቀም ላይ ይገኛሉ ምክንያቱም ማድረግ ይችላሉና፡፡ ከስልጣን ውጭ ያሉ የጉማሬው ትውልድ አባላት ስልጣን ማግኘትን ይፈልጋሉ ምክንያቱም የላቸውምና፣ ምክንያቱም ስልጣን በእራሱ ሁሉንም ነገር ነውና፡፡ የጉማሬው ትውልድ አባላት ስልጣን ያጡትን ወይም ስልጣን የሌላቸውን  ስልጣን እንዲያገኙ አያደርጉም፡፡ በኢትዮጵያ ያሉት ወጣቶች ምንም ዓይነት ስልጣን የሌላቸው እና ስልጣን አልባ የህብረተሰብ ክፍሎች ናቸው፡፡ ይህም ማለት 70 በመቶ (66 ሚሊዮን) ያህሉን የኢትዮጵያ ህዝብ የሚይዘው የህብረተሰብ ክፍል ስልጣን የለውም፡፡
የኢትዮጵያ የአቦሸማሜው ትውልድ በአቦ-ጉማሬው ትውልድ ላይ እምነት አጥቷል የሚል ጽኑ እምነት አለኝ፡፡ ያ እምነት ወደ መተማመን ሊመለስ የሚችለው በጋራ በመከባበር እና በመግባባት እንዲሁም በመተማመን እና በመቀራረብ ብቻ ነው፡፡ ወጣቶቹ ከእኛ ጋር እኩል እንደሆኑ እና እነሱን በአግባቡ በማስተናገድ መተማመን እና እርቀሰላምን ማውረድ ይቻላል፡፡ የኢትዮጵያ ወጣቶች ለሀገራቸው ያሏቸው ሀሳቦች እና  ራዕዮች ጠቀሜታቸው ከእኛ ሀሳቦች እና ራዕዮች ያላነሱ መሆናቸውን ሙሉ በሙሉ መቀበል አለብን፡፡ ከወጣቶቹ ጋር በእኩልነት በመከባበር እና ተቀራርቦ በመወያየት የጋራ ችግሮቻችንን መፍታት አለብን፡፡
የጉማሬዎቹ አስተምህሮ ለአቦሸማኔው ትውልድ፣
የአቦሸማኔው ትውልድ አባላት ከእኛ ከጉማሬው ትውልድ አባላት ጋር ተቀራርበው መነጋገር ለእነሱ በጣም አስፈላጊና ጠቃሚ ነው ፡፡ ምሳሌ በማቅረብ የጉማሬው ትውልድ ትምህርት ማስተማር ይችላሉ፡፡ ከታላላቆቻቸው ስህተቶች ሊማሩ የማይችሉ ወጣቶች ተመሳሳዮቹን ስህተቶች ይደግማሉ፡፡ እኛ የጉማሬው ትውልድ አባላት ብዙ ስህተቶችን ሰርተናል፡፡ ሁለተኛው ትምህርት የአቦሸማኔው ትውልድ አባላት የጉማሬውን ትውልድ አባላት ድክመቶች ማሸነፍ እና የእራሳቸውን አዲስ ጅምሮች መተግበር ነው፡፡ የጉማሬው ትውልድ ለአቦሸማኔው ትውልድ ሊያስተምሯቸው የሚችሏቸው ነገሮች የድፍረት ወኔን፣ መተማመንን፣ ለበጎ ነገር መስዕዋትነት መክፈልን፣ ታማኝነትን፣ መንፈሰ ጠንካራነትን፣ ችግሮችን በጽናት የመቋቋም ችሎታ የማዳበርን፣ ለውሳኔ ተገዥነትን፣ እና ችግሮችን በድል አድራጊነት እንዴት መውጣት እንደሚቻል ማስተማር ከብዙዎች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ በአሁኑ ጊዜ “ክብር እና ሞገስ አጥተን” በታላቅ ችግር ላይ ነን፡፡ እነዚህን ክብር እና ሞገሶች ለመመለስ ግን በጋራ ሆነን መሞከር እና ለመተግበር መሞከር ነው፡፡ የአቦሸማኔ ትውልዶችን ከግትርነት፣ ከቁጣ፣ ከጥርጣሬ፣ ከታጋሽየለሽነት፣ ከሙስና፣ ካለመቻቻል፣ ስልጡን ያልሆነ አካሄድን ካለመከተል፣ ከፍርሀት፣ መጥፎ ነገር ከማድረግ፣ ከበቀልተኝነት እና እራስን ከማድነቅ በማለት በእርግጠኘነት የአቦሸማኔውን ትውልድ ለማስተማር ይቻላል፡፡ የአቦሸማኔውን ትውልድ ግልጽ የሆኑ ውይይቶችን በማድረግ በግል እና በህዝብ ህይወት ላይ የተጠያቂነት እና ግልጽኘነት የማስተማር ዘዴን በማሳየት የአቦሸማኔውን ትውልድ ማገዝ እንችላለን፡፡
የአቦሸማኔው አስተምህሮ ለጉማሬው ትውልድ፣
የአቦሸማኔው ትውልድ የፖለቲካ እና የማህበራዊ ችግሮችን በሰላማዊ እና ኃይልን ባልተጠቀመ መልኩ ሰላማዊ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ለጉማሬው ትውልድ ማስተማር ይችላሉ፡፡ ወጣቶቹ የሚማሩት እና የሚሰለጥኑት የጦር ተዋጊዎች እንዲሆኑ ብቻ ለማድረግ ብቻ አይደለም ነገር ግን የሰላም ጠበቃዎች እንዲሆኑ ጭምር እንጅ፡፡ ወጣቶቹ ጤናማ የህብረተሰብ ግንኙነቶችን የመፍጠር እና የጎሳ፣ የኃይማኖት ጽንፈኝነትን እና የዘር ጥላቻን የማስወገድ ችሎታ አላቸው፡፡ ወጣቶቹ የህብረተሰብ ትብብሮችን፣ ፍቅርን፣ መግባባትን፣ ሰላምን፣ አንድነትን እና ተስፋን የሚፈጥሩ አስፈላጊ ጉዳዮች ሁሉ ለጉማሬው ትውልድ ማስተማር ይችላሉ፡፡ ሁላችንም በሰላም፣ በእኩልነት እና ፍትህ በነገሰበት መልኩ የምንኖርባት “አዲሲቷን ኢትዮጵያ” ለመገንባት የሚያስችል ችሎታ እንዳላቸው ለጉማሬው ትውልድ ማስተማር ይችላሉ፡፡ የአቦሸማኔው ትውልድ አባላት ከተፈቀደላቸው እና በማህበራዊ እና በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ እውነተኛ ተባባሪ እና አጋር እንዲሆኑ ከተደረጉ ለውጥን የሚያመጡ የለውጥ ዘዋሪነት ሚና ሊጫወቱ የሚችሉ መሆናቸውን ለጉማሬው ትውልድ ማስተማር ይችላሉ፡፡ ወጣቶቹን በጥሞና የምናዳምጣቸው ከሆነ እራሳችንን ከእራሳችን እንድንጠብቅ ሊያደርጉን ይችላሉ፡፡ ይኸንን ጉዳይ እናስብ! ወጣቶቹ ከጎሳ እስር ቤቶች ግድግዳዎች ሰብረን እንድንወጣ፣ ከምናባዊ ፍርሀቶች እንድንላቀቅ እና የሌሎቸን ሀሳቦች ያለመቀበል እና መጥፎ ሀሳቦች ዓይናችንን እንዳያይ ሸፍነው “አዲሲቷን ኢትዮጵያ” ከአድማሱ ባሻገር እንዳናይ አድርገውን የነበሩትን እንድናስወግድ ሊረዱን ይችላሉ፡፡
ኢትዮጵያውያን እንደ አገር እና እንደ ህዝብ ህልውናቸው ተጠብቆ እንዲቆይ ከተፈለገ ያ ህልውና የሚወሰነው በፈጣሪነት፣ በአዕምሯዊ ሃይል እና ጥንካሬ፣ መንፈሰ ጽናት፣ መልካም አመለካከት እና  በወጣቶቹ መንፈሰ ጠንካራነት እና በሚከፍሉት መስዋዕትነት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ያ ሁኔታ በወጣቶች ላይ ከባድ ሸክምን ይጥላል፡፡ ወጣቶቹ ያንን ከባድ ሸክም፣ ከባድ ስራ እና ታላቅ መስዋዕትነት በመክፈል የአንበሳውን ድርሻ መያዝ አለባቸው፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ኢትዮጵያውያን እንደ ሀገር እና እንደ ህዝብ ህልውናቸው ተጠብቆ እንዲቆይ ከተፈለገ ያ የመቆየት ህልውና የሚወሰነው የቀድሞው ትውልድ አባላት ለአዲሱ ትውልድ አባላት ቀልጣፋ እና ቀጣይነት ያለው ድጋፍ ማድረግ ስንችል ነው፡፡ እኛ የጉማሬው ትውልድ አባላት የምንችለውን ነገር ሁሉ በማድረግ የአቦሸማኔዎቹ (ወጣት) ትውልድ እምነት እንዳያጡ እና ውድቀት እንዳይደርስባቸው ተጋድሎ ማደረግ ይጠበቅብናል፡፡ ወጣቶቹ ይህንን ሲያደርጉ ማበረታታት፣ ማገዝ እና ደጋግመው እንዲሰሩት ድጋፍ መስጠት ይኖርብናል፡፡ ትግሉ የፈለገውን ያህል ረዥም ጊዜ ቢወስድም ምንጊዜም ቢሆን ከወጣቶቹ ጎን መሰለፍ አለብን፡፡ ከወጣቶቹ ጋር መወያየት እና መነጋገር አለብን፡፡ ወጣቶቹን መደገፍ እና መውደድ ይኖርብናል፣ ወጣቶቹ በአዲሲቱ ኢትዮጵያ የፕሮጀክት የግንባታ መስክ ላይ ሆነው በጽናት እየሰሩ አስከቆዩ ድረስ ለእነሱ ውኃ ማቀበል እና ሌሎችንም ድጋፎች በደስታ በማድረግ መደገፍ ይኖርብናል፡፡
የኢትዮጵያ ወጣት ኃይል ምንም ማንም ሊያቆመው የማይችል ኃይል ነው፡፡ የኢትዮጵያን ተወርዋሪ የአቦሸማኔ ትውልድ ሊያቆመው የሚችል ምድራዊ ኃይል፣ እስካፍንጫው የታጠቀ አምባገነን ኃይል ሊያሸንፈው የሚችል ኃይል የለም፡፡ እኛ የቀድሞው ትውልድ አባላት ምንጊዜም ቢሆን የሚከተለውን የድሮ አባባል ልንከተል ይገባል፣ “ልታሸንፋቸው አለመቻልህን ካረጋገጥህ ተቀላቀላቸው፡፡“ የአቦሸማኔውን (የወጣቱን) ትውልድ በውይይት እንቀላቀል፡፡ ከእነርሱ ጋር ቀረብ በማለት እንወያይ፣ ምን ፍላጎት እንዳላቸውም እንጠይቃቸው፡፡ የእኛን ምክር የሚወዱ እና የሚፈልጉ ከሆነ ይህንን በለጋሽነት እና በነጸነት እንችራቸው፡፡ የእኛን ቴክኒካዊ እገዛ የሚፈልጉ ከሆነ ዕገዛውን እናድርግላቸው፡፡ የሞራል ድጋፋችንን የሚፈልጉ ከሆነ ለእነሱ እናደርግላቸው፡፡ የማቴሪያል ድጋፍ የሚፈልጉ ከሆነ ለእነርሱ የገንዘብ መዋጮ በማሰባሰብ ድጋፍ እናድርግ፡፡ ወጣቶቹ ታላቅ ሸክሞችን ከጫንቃቸው ላይ ለማውረድ፣ ድልድይ በሚገነቡበት ጊዜ፣ የመንገድ ጥገና በሚያካሄዱበት ጊዜ እና ተራሮችን በሚወጡበት ጊዜ በትህትና የተሞላን ውኃ አቀባያቸው ሆነን መቅረብ አለብን፡፡ ለወጣቶቻችን የኃይል ምንጮች መሆን አለብን!
(ክፍል ሁለት ይቀጥላል፡፡) 
ታህሳስ 29 ቀን 2006 .
ምንጭ የኢትዮጵያ ሜዲያ መድረክ