Tuesday, October 29, 2013

ስለማህበረ ቅዱሳን ታሪክ ዝርዝር መረጃ የጠየቃችሁን የተዋህዶ ልጆች እንደሚከተለው እናቀርባለን:: የተዛባ አመለካከት የማይጋርደው ገሐድ እውነታ!!!!!

ስለማህበረ ቅዱሳን ታሪክ ዝርዝር መረጃ የጠየቃችሁን የተዋህዶ ልጆች እንደሚከተለው እናቀርባለን::
የተዛባ አመለካከት የማይጋርደው ገሐድ እውነታ
ማኅበረ ቅዱሳን ማን ነው? ምንስ እየሠራ ነው? ክፍል አንድ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሊቃውንት ብራና ዳምጠው፤ ቀለም በጥብጠው፣ ብዕር ቀርጸው በየአብያተ ክርስቲያናቱ የመቃብር ቤቶች ውስጥ በማስተማር ትውልዱ የሀገር መሪ፣ የቤተክርስቲያን አለኝታ፣ የእግዚአብሔር ቅን አገልጋይ እንዲሆን ያበረከቱት አገልግሎት ከዘመን ዘመን እየተሸጋገረ ለትውልድ ሲተላለፍ የኖረና የሚኖር ነው፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለሀገራችን ሥልጣኔ በር ከፋች ሆና የኖረች ከመሆኗም በላይ ዛሬ ላለው ዘመናዊ ሥልጣኔም መሠረት የጣለች ባለውለታ ናት፡፡ ቀደምት የቤተክርስቲያን አበው ደከመን፣ ሰለቸን ሳይሉ ዐረፍተ ዘመን እስከገታቸው ድረስ ሲያገለግሉ ኖረው ቤተክርስቲያኒቱ አሁን ከምትገኝበት የዕድገት ደረጃ አድርሰዋታል፡፡
በዚህ ዘመንም የሚገኙ የቤተክርስቲያኒቱ ልጆች ሁሉ ይህን ከአበው የተማሩትን ሃይማኖትና ሥርዓት ጠብቀውና አስጠብቀው ለሚመጣው ትውልድ የማቆየት ሓላፊነት ያለባቸው መሆኑ ግልጽ ነው፡፡

በመሆኑም ይሔንን አባቶች ወዛቸውን አንጠፍጥፈው፣ ዐይናቸውን አፍዘው፣ ደማቸውን አፍስሰውና አጥንታቸውን ከስክሰው በሰማዕትነትና በተጋድሎ ያቆዩትን ሃይማኖት ለማስጠበቅና ለቀጣዩም ትውልድ በተመቻቸ ሁኔታ ለማስተላለፍ በእግዚአብሔር ፈቃድ በቅዱስ ሲኖዶስ ሙሉ ድጋፍና ዕውቅና የተመሠረተው ማኅበረ ቅዱሳን በውጪ በአጽራረ ቤተክርስቲያንና በአሕዛብ፣ በውስጥ ዓላማውን ባልተረዱ፣ ዓላማውን ተረድተው የኑፋቄ ትምህርታቸውን እንደልብ በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ ለማስረግ ሌት ተቀን በሚተጉ አንዳንድ ግለሰቦችና ቡድኖች ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ እየተከሰሰ እየተወቀሰና ያለ ስሙ ስም እየተሰጠው ይገኛል፡፡

እነዚህ በውስጥና በውጭ የሚገኙት የቤተክርስቲያን ጠላቶች ቤተክርስቲያን ላይ በየዘመኑ በሚነሳው ፈተና እየተጠቀሙና በምክንያት እየተሳቡ ለቤተክርስቲያን ወዳጅ መስለው እየቀረቡና እያስቀረቡ ማኅበረ ቅዱሳንን ቢቻላቸው እንዲፈርስ፣ ባይቻላቸው ደግሞ የቤተክርስቲያኒቱን ሥርዓት ለማፍረስ በገንዘብ፣ በቁሳቁስ የሚያስታጥቋቸው መናፍቃን ሴራና ዓላማ እንዳይጋለጥ እና በቤተክርስቲያኒቱ ላይ እንደፈለጋቸው እንዲሆኑ ማኅበሩ አገልግሎቱ ተገድቦ እንዲዋቀር ለማስደረግና ለማድረግ የጥፋት ዘመቻዎችን በመክፈት ላይ ናቸው፡፡

እነዚህ የቤተክርስቲያን ጠላት ወዳጆች በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ጊዜ በሰጣቸው ጊዜ ሁሉ በመጠቀም ማኅበሩን ለማሳጣትና ለማጥላላት የሚጠቀሙባቸው ስልቶች በርካቶች ናቸው፡፡

ከብዙ በጥቂቱ ለመጥቀስ ያህል «ማኅበረ ቅዱሳን ሲኖዶስ ከሰጠው ደንብና መመሪያ ውጪ እየሠራ የሚገኝ፣ ፖለቲካዊ ዓላማ ያለውና ገቢና ወጪው የማይታወቅ ማኅብረ» እንደሆነ አድርገው» ሚያናፍሱት አሉባልታ ከብዙ በጥቂቱ የሚጠቀስ ነው፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን ግን ባለፉት 17 ዓመታት እነዚህ የውስጥና የውጪ የቤተክርስቲያን ጠላቶች በየጊዜው ማኅበሩ ላይ የሚያናፍሱትን ወሬ ችላ በማለት ከወሬ ሥራ ይቀድማል በማለት ከቅዱስ ሲኖዶስ የተቀበለውን ዓላማ በዓይን በሚታይ፣ በእጅ በሚዳሰስ መልኩ ሲሠራ ቆይቷል፡፡ ነገር ግን «ውሸት ሲደጋገም እውነት ይመስላል» እንዲሉ ማኅበረ ቅዱሳን ማን ነው? እንዴትስ ተመሠረተ? ዓላማውስ ምንድን ነው? ቅዱስ ሲኖዶስ የሰጠውን ሓላፊነት እንዴት እየተወጣ ነው? ለ17 ዓመታትስ ምን ሠራ? የሚሉትን ጥያቄዎት በስፋት ማቅረቡ አስፈላጊ መሆኑን ለምእመናን መግለጽ ግድ ብሎናል፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን ማን ነው? እንዴትስ ተመሠረተ?

ማኅበረ ቅዱሳን ማን ነው? እንዴትስ ተመሠረተ የሚለውን ጥያቄ ከመመለሳችን በፊት አጽራረ ቤተክርስቲያንና ዓላማቸውን ለማስፈጸም የሚንቀሳቀሱት ተላላኪዎቻቸው የውስጥ ዐርበኞች ማኅበረ ቅዱሳንን በሰው ውስጥ የጥላቻ መንፈስ እንዲያድር ከሚጣጣሩበት መንገድ አንዱ ማኅበሩ የሚጠራበትን ስያሜውን በማዛባት ነው የሚጀምሩት፡፡ ከዚህ አንጻር ማኅበረ ቅዱሳን ሲባል ምን ማለት ነው? የሚለውን ነገር ማብራራት ያስፈልጋል፡፡ ስለዚህ ስያሜው ላይ አጭር ትንታኔ በመስጠት ወደ ማንነቱና አመሠራረቱ እንለፍ፡፡

የማኅበሩ ስያሜ

አንዳንድ ሰዎች ስያሜውም ግራ ያጋባቸዋል፡፡ ከላይ እንደጠቀስነው አባላቱ ለራሳቸው ያወጡት አስመስለው የሚነግሯቸው ሰዎች አሉና የዋሀኑ ግራ ቢጋቡ አያስደንቅም፡፡ ነገር ግን የማኅበሩ ስያሜ እኩያኑ ማኅበሩን ለማጥላላት ከሚጠቀሙት ፕሮ­ጋንዳ በእጅጉ የተለየ ነው፡፡ ማኅበረ ሚካኤል «የሚካኤሎች ስብስብ»፣ ማኅበረ ማርያምም «የማርያሞች ስብስብ» ካልሆነ /እንዳልሆነ/ ማኅበረ ቅዱሳንም «የቅዱሳን ሰብስብ» አይደለም፣ ሊሆን አይችልም፤ ወይም ማኅበረ ጊዮርጊስን የመሠረቱ ሰዎች ራሳቸውን «ጊዮርጊሶች»ነን እንደማይሉት፤ እንዳልሆኑትም፣ ማኅበረ ቅዱሳንም ቅዱሳን ነን የሚሉ ሰዎች ስብስብ አይደለም፡፡ ይልቁንም ማኅበረ ማካኤል የሊቀ መላእክት የቅዱስ ሚካኤል አማላጅነት፣ ተራዳኢነት የሚታሰብበት ማኅበር እንደሆነው ሁሉ ማኅበረ ቅዱሳንም የቤተክርስቲያኒቱን ትምህርተ ሃይማኖትና ሥርዐት ከመጠበቅና ከማስተማር በተጨማሪ በቤተ ክርስቲያኒቱ ትምህርተ ሃይማኖት መሠረት የቅዱሳን ጻድቃንና ሰማዕታት እንዲሁም የቅዱሳን መላእክት ክብ ራቸው፤ ገድላቸውና ትሩፋታቸው፣ አማላጅነታቸውና በረከታቸው፤ በሰፊው እንዲታወቅና ትውልዱም የዚህ ተጠቃሚ እንዲሆን ትምህርት የሚሰጡበት ማኅበር ነው፡፡ ምእመናን በነዚህ ቅዱሳን አማላጅነትና ረድኤት እየታገዙ ለመንግሥተ ሰማያት እንዲበቁ ማድረግም ቀዳሚ ተግባሩ ነው፡፡

ከዚህ የተነሣ የእነዚያ ብዙ ማኅበራት ኅብረት የሆነው ማኅበር የነቢያት፣ የሐዋርያት፣ ጻድቃን ሰማዕታትና የቅዱሳን መላእከት ሁሉ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ ማኅበረ ቅዱሳን ተባለ፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን እንዴትስ ተመሠረተ?

ዘመኑ የኮምዩኒዝም ርዕዮተ ዓለምና አስተሳሰብ የሰፈነበት፤ ስመ እግዚአብሔርን መጥራት አስቸጋሪ የሆነበትና ወደ ቤተ እግዚአብሔር መሔድ እንደ ኋላቀርነት የሚቆጠርበት ዘመን ነበር 1977 ዓ.ም፡፡

በተለይም በየከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ /ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች/ በሚገኙ ተማሪዎች ዘንድ ቃለ እግዚአብሔርን በግልጽ መነጋገርም ሆነ መሰማት የማይታሰብበት ወቅት ነው፡፡

ቀደም ባሉት ጊዜያት በተለይም በንጉሠ ነገሥት ዐፄ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት በዩኒቨርሲቲና ኮሌጆች እንዲያስተምሩ ከምዕራባውያኑ ሀገሮች መጥተው የነበሩ ሚሲዮናውያን የኑፋቄ ትምህርታቸውን ያሠራጩ የነበረውም በእነዚሁ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ነው፡፡

በዚህ ሁኔታ ትውልዱ በየአቅጣጫው በሚሲዮናውያኑ የኑፋቄ ትምህርት እንዲሁም በኮምዩኒዝም ርዕተ ዓለምና አስተሳሰብ እየተነጠቀ ከኦርቶዶከሳዊት ተዋሕዶ እምነት የኮበለለበት ከቤተክርስቲያን የራቀበት ዘመን ነበር፡፡

በዚህ ጊዜ ነው፤ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስድስት ኪሎ ዋናው ግቢ ከፍተኛ ትምህርታቸውን ይከታተሉ የነበሩ አምስ

ምንጭ ድምጻችን ይሰማ ዘኦርቶዶክስ

Monday, October 28, 2013

ሠላይና ተሠላይ፤ ወዳጅና ጠላት

አሜሪካዊ እንደራሴና የሥለላ ጉዳይ አዋቂ ፔተ ሆክስትራን የሚያስደንቀዉ ግን የአሜሪካ ሰላዮች የጀርመንዋ መራሒተ-መንግሥትን ስልክን መጥለፋቸዉ አይደለም።የነፍሬድሪሽ ቁጣና ብስጭት እንጂ።ሆክስትራ እንደሚሉት ካስደነቀ-የሚያስደንቀዉ የጀርመን መሪ ሥልክ መጠለፉን ፍሬድሪሽ የሚመሩት የጀርመን የስለላ ድርጅት አለማወቁ ነዉ።
ARCHIV - US-Präsident Barack Obama und Bundeskanzlerin Angela Merkel unterhalten sich am 18.06.2012 in Los Cabos, Mexiko, beim Familienfoto. Merkel setzt bei der Aufklärung der millionenfachen Datensammlung des Geheimdienstes NSA nun auf eine Reise von Vertretern der Bundesregierung und deutscher Geheimdienste in der nächsten Woche nach Washington. Foto: Peer Grimm dpa (zu dpa Merkel verspricht größtmögliche Offenheit bei US-Ausspähaffäre vom 05.07.2013) +++(c) dpa - Bildfunk+++
ወዳጁ ናቸዉ
ለካሳትሮ፥ ለብሬዥነቭ፥ ለማኦ፥ ለ ደጎል፥ ለንጎ በርግጥ አዲስ አልነበረም።አይደለምም።የኤንርኮ ፔና ኔቶ ኢሜል መጠለፍ- ጉድ አሰኝቶ ነበር።የዲልማ ሮሴፍ-ኢሜል መጠለፍ-አስደንቆ ነበር።የሜርክል ሥልክ መጠለፍስ? ጉዱን ጉድ ዘለቀዉ-እንበል ይሆን።የስላላዉ ቅሌት መነሻ፥ዳራዉ ማጣቃሻ፥ የፖለቲካዉ እድምታዉ መድረሻችን ነዉ-ላፍታ አብራችሁኝ ቆዩ።


ሚዚያ ሃያ-አንድ 1943 (ዘመኑ በሙሉ እንደ ጎርጎሮሳዉያኑ አቆጣጠር ነዉ።) ፈረንሳይን ከናዚ ጀርመኖች አገዛዝ ነፃ ለማዉጣት የሚዋጋዉ ጦር አዛዥ ጄኔራል ሻርል ደጎል የነፃዋ ፈረንሳይ ባሕር ሐይል ጦርን ለመጎብኘት ከተጠጉባት ብሪታንያ በብሪታንያ አዉሮፕላን ተሳፈሩ።ቆፍጣናዉ፥ ቁጡዉ፥ እልሐኛዉ ረጅሙ ጄኔራል ከትንሿ አዉሮፕላን እንደተሳፈሩ አብራሪዉ (ፓይለቱ) አዉሮፕላንኗን እንደማስነሳት ትንሽ አንገጫገጨና ወዲዚያዉ አቆማት።ጉዞዉ ተዘረዘ።

አዉሮፕላንኗ ስትፈተሽ የሞተሯ አካል በአሲድ መበላሸቱ ታወቀ።አሲዱን አዉሮፕላንዋ አካል ላይ የረጨዉ ወገን ማንነት-እስካሁን ሚስጥር ነዉ።ጄኔራሉ ግን ያኔዉኑ «የብሪታንያ ሰላዮች ሻጥር» ለማለት አላመነቱም።የአዉሮጳ እብሪተኞች የለኮሱት ጦርነት ዓለምን በሚያነድበት በዚያ ዘመን ወዳጅን ከጠላት መለየቱ-ከባድ ነበር።በዚሕም ሰበብ ደ ጎል እንደጠረጠሩት ብሪታንያዎች አድርገዉት ከነበር-ብዙዎችን ብዙም አላስደነቀም ነበር።
ARCHIV - US-Präsident Barack Obama (r) wischt sich am 19.06.2013 den Schweiß von der Stirn neben Kanzlerin Angela Merkel auf einem Podium vor dem Brandenburger Tor am Pariser Platz in Berlin. Foto: Marcus Brandt/dpa (zu dpa Obama war angeblich in NSA-Abhörattacken gegen Merkel eingeweiht vom 27.10.2013) +++(c) dpa - Bildfunk+++ተሠላይና አሰላይ


ከብዙ አመታት በሕዋላ የደጎልን ቤተ-መንግሥት የተረኩቡት ፕሬዝዳት ኒኮላ ሳርኮዚ ከጀርመንዋ መራሒተ-መንግሥት ከወይዘሮ አንጌላ ሜርክል ጋር የነበራቸዉ ግንኙነት ከመሪዎች-ወዳጅነትም ጠንከር፥ ጠለቅ ያለ-ነበር ይባላል።ሳርኮዚ ከሜርክል ጋር ሥላላቸዉ ግንኙነት ሥለሚያደርጉት ዉይይት ሲጠየቁ፥«ሁሌ እንገናኛለን፥ በስልክ፥ እንነጋገር፥ ኤስ ኤም ኤስ እንለዋወጣለንም» እያሉ የግንኙነት ዉይይታቸዉ ደረጃ ዘርዝረዉ ነበር።

የሜርክል መልዕክት ከሳርኮዚ አይን-ጆሮ በሚደርስበት ፍጥነት ከአሜሪካ ሰላዮች ኮምፒዉተር ላይ ይዘረገፍ ነበር።ይሕን በርግጥ ሳርኮዚም፥ ሜርክልም ከኛ እኩል ያወቁት ሰሞኑን ነዉ።NSA በሚል ምሕፃረ-ቃል የሚጠራዉ የአሜሪካ ብሔራዊ የሥለላ ድርጅት ባልደረባ የነበሩት ቶማስ ድራክ እንደሚሉት ሜርክልን መሠለል ዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲን መጣስ ነዉ።

«ይሕ ዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲን ክፉኛ መጣስ ነዉ።ይሕ ለመራሒተ-መንግሥት ሜርክል የግል ጉዳይ ነዉ።የግላቸዉ ተንቀሳቃሽ ሥልክ ነዉ።(ያን መጥለፍ) ለምን አስፈለገ።ከእዉነኛ ጠላትሕ ጋር በምታደርገዉ ዉጊያ የቅርብ ተባባሪሕን?»
ILLUSTRATION - Ein iPhone, auf dem der fiktive Name Angela Merkel zu sehen ist, liegt am 25.10.2013 in München (Bayern) auf einem Logo der NSA (National Security Agency). Nach Hinweisen auf eine Überwachung des Handys von Bundeskanzlerin Merkel (CDU) durch US-Geheimdienste haben Politiker aller Parteien umgehende Aufklärung gefordert. Foto: Sven Hoppe/dpa
ዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ፥ ዓለም አቀፍ ሕግ በቀዝቃዛዉ ጦርነት ወቅት ነበር።ዛሬም አለ።አንዴም ግን ተከብሮ አያዉቅም።ሕግ፥ ደንብ፥ ሥምምነቱን የሚጥሰዉ ደግሞ ሕግ-ደንቡን ካወጣዉ፥ አስከብረዋለሁ ከሚለዉ ሐያል ዓለም ሌላ ማንም አይደለም።

በቀዝቃዉ ጦርነት ወቅት ልክ እንደ ዓለም አቀፉ ሕግ ደንብ ሁሉ የሞስኮ፥ ቤጂንግ ተባባሪዎች፥ የለንደን-ዋሽግተን፥የቦን ፓሪስ ተሻራኪዎች ጎራ ለይተዉ አንዱ የሌላዉን ሚስጥር ማጭለጉ የፖለቲካዉ ፈሊጥ፥ የስለላዉ ወግ ነበር።

የሐገር መሪዎችን እንቅስቃሴ መከታተል አይደለም መግደል ማስገደልም የፖለቲካ መርሕን የማጠናከር፥ ርዕዮተ-ዓለምን የማዳን-ማስፋፋት ሥልት አካል ነበር።የአሜሪካዉ ማዕከላዊ የሥለላ ድርጅት CIA ሹም ኮሎኔል ጄ ሲ ኪንግ የኩባዉን ኮሚንስታዊ መሪ ፊደል ካስትሮ-ከማስገደል ሌላ ሌላ አመራጭ እንደለሌ የጠቆሙት በ1959 ነበር።

ያኔ ዓለም አቀፍ ማሕበር ዲፕሎማሲ፥ ሕግም ነበር።ዲፕሎማሲ ሕግ፥ ደንቡ የሚረቀቅ፥ የሚወሰን የሚበየነዉ ደግሞ ከኒዮርክ ነበር፥ ከዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ።የአሜሪካዊ ማዕከላዊ የሥለላ ድርጅት CIA ካስትሮን ለማስገደል ስድስት መቶ ሰላሳ-ስምንት ጊዜ ያደረገዉ ወይም አድርጓል የተባለዉ ሙከራ የብዙ መፅሐፍት፥ የዝነኛ ፊልም ርዕሥም ሆኗል።

አያቱላሆች የቴሕራንን ቤተ-መንግሥት ከተቆጣጠሩበት ከ1979 ጀምሮ ኢራን የእስራኤልም፥ የአሜሪካኖችም አሜሪካኖችን የሚመሩት የምዕራቡ ዓለምም ቀንደኛ ጠላት ናት።በሕዝብ የተመረጡት የኢራን ጠቅላይ ሚንስትር መሐመድ ሞስዳቅሕን በ1953 ከስልጣን ያስወገደዉ ማን ነበር? ፓትሪስ ሉምባ እንዴት-እና ማን ገደላቸዉ።ራፋኤል ሊኒዳስ ትሩሔሎስ፥ ንጎ ዲንሕ ዲየምንስ?
US-Bürger demonstrieren am 24.10.2013 nahe dem Kapitol in Washington DC gegen die Überwachung durch Geheimdienste wie die NSA. (Foto: Monika Griebeler / DW) - eingestellt von Andreas Grigoተቃዉሞ


ጥያቄዉ-ጥያቄ ይወልዳል እንጂ ማብቂያ የለዉም።ዓለምን የሚመራዉ ግን ዓለም አቀፉ ሕግ ዲፕሎማሲ ሳይሆን የሐያላን ፍላጎትና ፍቃድ መሆኑ ሐቅ ነዉ።የሐያላኑን ፍላጎት ለማስከበር ደግሞ በግልፅ የሚታወቀዉ ሐያላኑ ወዳጅ ከሚሉት ጋር መተባበር መሻረክ መወዳጀታቸዉ ነበር።እስከ 2007 ድረስ በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት የስለላ ጉዳይ ኮሚቴ ሊቀመንበር የነበሩት ፔተ ሆክስትራ እንደሚሉት ግን በስለላዉ ዓለም ከወዳጅም-መሐል ተጠርጣሪ ወዳጅ አለ።

«ይሕ ሊሆን የሚችል ይመስለኛል።በስለላዉ ዓለም ፈረንሳዮች፥ ጀርመኖች፥ እስራኤሎች አሜሪካኖች ሁላችንም ጥሩ ወዳጆች ነን።ግን አንዳችን ሌላችንን የምንሠልልበት ጊዜ ሊኖርም ይችላል-የሚል መግባባት ያለ ይመስለኛል።ይሕ (በሰላዮች ዘንድ) በጣም በጣም የታወቀ ነዉ።»

ኮሚንስቶች የሐቫና፥ የሳንዲያጎ፥ የማናጉዋ የሌሎችንም የደቡብ አሜሪካ ሐገራት አብያተ-መንግሥታትን ሲቆጣጠሩ ወይም ለመቆጣጠር ሲያሰጉ የዩናይትድ ስቴትስዋ የቅርብ ጎረቤት፥ ታማኝ፥ ታዛዥነቷን አጓድላ አታዉቅም።ሜክሲኮ።

ከቀዝቃዛዉ ጦርነት በሕዋላ እነ-ሑጎ ሻቬዝ አሜሪካኖችን የሚቃወም ግንባር ለመፍጠር ሲፍጨረጨሩም ያቺ-የአሜሪካ የቅርብ ጎረቤት በታማኝ ታዛዥነቷ እንደፀናች ነበር።ነዉም።ኤንሪክ ፔና ኒቶ ለፕሬዝዳትነት ሲወዳደሩ-ሲመረጡም እንደ ብዙ ቀዳሚዎቻቸዉ ሁሉ ለሐያል፥ ሐብታም፥ ታላቅ ጎረቤታቸዉ ታማኝ ታዥነታቸዉን እንደጠበቁ ነዉ።

በእጩነት ከተመዘገቡ ጀምሮ በምርጫዉ ካሸነፉ-ለሚንስትርነት የሚሾሙ የሚሽሩትን ፖለቲከኛ ስብዕና ማንነት፥ የሚዘረዝር፥ የምርጫ ዘመቻቸዉን ሥልት የሚያትት መልዕክት ለወዳጅ ተከታዮቻቸዉ ኢሜይል ይፅፋሉ። የNSA ሰላዮች ዋሽግተን ቁጭ ብለዉ የሜክሲኮዉን ፕሬዝዳት ኢሜይል ከፕሬዝዳንቱ ደጋፊ፥ተከታዮች እኩል ያነቡ ነበር።የብራዚሏ ፕሬዝዳት የወይዘሮ ዲልማ ሮሴፍ ኢሜዬልም-እንደዚያዉ ነዉ።

አሜሪካዊዉ ሠላይ ኤድዋርድ ስኖደን ሐገር መስሪያ ቤቱን ክዶ ከኮበለለ ወዲሕ የማይሰማ ጉድ የለም።አንዳድ ዘገቦች እንደሚጠቁሙት የሶቬት ሕብረት ኮሚንስቶች በስታሊን ዘመን የሶቬት ሕብረት ሕዝብ ከሚሠልሉት በላይ የአሜሪካ መንግሥት አሜሪካዉያንን ይሰልላል።ለአሜሪካ ሕዝብ ያልራራ ሥርዓት የፈረንሳይ ኩባንያዮችን፥ የስጳኝ ፖለቲከኞችን፥ የዓለምን ሕዝብ የሜክሲኮ፥ የብራዚል፥ የሌሎች ከሰላሳ በላይ መሪዎችን ቢሰልል-በርግጥ ሊያስደንቅ አይገባም።

ያምሆኖ የጀርመንዋ መራሒተ-መንግሥት የሥልክ መልዕክት መጠለፉን ከአዉሮጳ ሕብረት አባል ሐገራት እስከ ሩሲያ መሪዎች ተቃዉመዋል።የጀርመን ፖለቲከኞች የሜርክል ደጋፊም ሆኑ ተቃዋሚዎችም እኩል አዉግዘዉታል።

«እንደሚመስለኝ ይሕ በጀርመን-አሜሪካኖችን ግንኙነት ያለዉን መተማመን ክፉኛ የሚጎዳ ነዉ።መተማመኑ ዳግም ሊገነባ የሚችለዉ እዉነታዉ በግልፅ ወጥቶ ማየን ከቻልን በኋላ ነዉ።

ይላሉ፥-የዋነኛዉ ተቃዋሚ ፓርቲ የSPD የምክር ቤት እንደራሴዎች አስተባባሪ ቶማስ ኦፐርማን ።ሥለ ጀርመን እና ጀርመንን የሚመለከቱ መረጃዎችን የመሰብሰብ መከታተሉ ሐላፊነት የጀርመን የሥለላ ድርጅት ነዉ።ቡንደስ ናሕሪሽተን ዲንስት።BND በጀርመንኛ ምሕፃሩ። የስለላዉን ድርጅት በበላይነት የሚያስተዳድርና የሚመራዉ ደግሞ የጀርመን ፌደራዊ የሐገር ዉስጥ ጉዳይ ሚንስቴር ነዉ።

የሐገር ዉስጥ ጉዳይ ሚንስትር ሐንስ ፔተር ፍሬድሪሽ ግን የመሪያቸዉን መሰለል እንደማንኛዉም ሰዉ ከመገናኛ ዘዴዎች የሰሙ ያክል ነዉ-የተቆጡት።

«ከአሜሪካኖች ጋር በዚሕ ሁኔታ አንሰራም።መተማመኑ ተበላሽቷል።እና እንደሚመስለኝ የተበላሸዉን መተማመን ለመጠገን ሁነኛ እርምጃ መወሰድ አለበት።»

አሜሪካዊ እንደራሴና የሥለላ ጉዳይ አዋቂ ፔተ ሆክስትራን የሚያስደንቀዉ ግን የአሜሪካ ሰላዮች የጀርመንዋ መራሒተ-መንግሥትን ስልክን መጥለፋቸዉ አይደለም።የነፍሬድሪሽ ቁጣና ብስጭት እንጂ።ሆክስትራ እንደሚሉት ካስደነቀ-የሚያስደንቀዉ የጀርመን መሪ ሥልክ መጠለፉን ፍሬድሪሽ የሚመሩት የጀርመን የስለላ ድርጅት አለማወቁ ነዉ።

«የዋሕነት ይመስለኛል።የጀርመን መንግሥት (ባለሥልጣናት) በወዳጆቻቸዉ ሊሰለሉ እንደሚችሉ ማወቅ ነበረባቸዉ።ነገሩ ከተፈፀመ አስደናቂዉ ነገር የሚመስለኝ፥ (ሥለላዉን) ለማስቆም የጀርመን የስለላ ማሕበረሰብ አስፈላጊዉ አፀፋ-እርምጃ አለመዉሰዱ ነዉ።»
Titel: Demonstration #stopwatchingus gegen NSA und Überwachung in Washington, DC, USA
Schlagworte: NSA, Überwachung, Demonstration, stopwatchingus
Wer hat das Bild gemacht?: Monika Griebeler
Wann wurde das Bild gemacht?: 26.10.2013
Wo wurde das Bild aufgenommen?: Washington, DC, USA
ተቃዉሞ
የጀርመንዋ መራሒተ-መንግሥት ስልክ መጠለፉ-መሰላላቸዉም እርግጥ ነዉ።ሜርክል መሰለላቸዉን ፕሬዝዳት ባራክ ኦቦማ ያዉቃሉ-አያዉቁም እያነጋገረ ነዉ።ካወቁ ከመቼ ጀምሮ የሚለዉም ያጠያይቃል። እራሳቸዉ ሜርክል እና የፈረንሳዩ ፕሬዝዳት ፍራንሷ ኦሎንድ የአዉሮጳ ሕብረት ወክለዉ ለኦባማ አቤቱታ ያቀርባሉ። ወደ አንድ ሺሕ የተገመቱ አሜሪካኖች በመንግሥታቸዉ መሠለላቸዉን በአደባባይ ሠልፍ አዉግዘዋል።አቤቱታ፥ ተቃዉሞ፥ ዉግዘት፥ ሰልፉ ምናልባት ይቀጥል ይሆናል፥ መሳለል-መጠላለፉ ያስቆመዋል ባይ ግን የለም።ምክንያት፥-ድሮ እንዲያ ነበር፥ ዛሬ እንዲያ ነዉ።ነገም።በዚሕ ዝግጅት ላይ ያላችሁን አስተያየት ላኩል። ማሕደረ ዜና ቢቃኘዉ ጥሩ ነዉ ብላችሁ የምትገምቱትን ወቅታዊ፥ ብሔራዊ፥ዓለም አቀፋዊ ጉዳይ በተለመደዉ አድራሻችን ጠቁሙን።ለዛሬዉ ነጋሽ መሐመድ ነኝ ቸር ያሰመን።
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ

AUDIOS AND VIDEOS ON THE TOPIC

  • ቀን 28.10.2013  www.dw.de

አደባባዩ ምን ያህል ይርቃል?

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ
እነሆ ይቺ ሀገር ኢትዮጵያ ናትና የመብት (የለውጥ) ጥያቄዎች፣ እንደ አህጉር ተጋሪዎቿ ሁሉ መልስ
የሚያገኙት ከአደባባይ ጩኸት ብቻ ይሆን ዘንድ ባህል ሆኖአል፡፡ ትውልድ ተሻጋሪ ታሪኳም የሚነግርህ
በየወቅቱ ከተፈራረቁ ገዥዎቿ አንዳቸውም እንኳ ለህዝብ ፍላጎትና ውሳኔ ተገዝተው አለማወቃቸውን ነው፤
ጠመንጃ አሊያም ተፈጥሮ ወደ ግብአተ መሬት ካልሸኛቸው በቀር፡፡ የሩቁን (የጨለማውን ዘመን) ትተን፣
የቅርቡን እንኳን ብንመለከት በወጡበት መንገድ፣ ቁልቁል ተምዘግዝገው መውደቃቸውን መረዳቱ
አይቸግርም፡፡ አዛውንቱ አፄ ኃይለስላሴ፣ ‹‹ቆራጡ›› ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማሪያም እና ‹‹ታጋዩ›› አቶ መለስ
ዜናዊ እጅ የሰጡት ለህዝብ ፍላጎት ሳይሆን ለጠመንጃና ለተፈጥሮአዊ ኃይል ነው፡፡ የሶስቱም የአመፃ ‹‹የዳቦ
ስም›› ደግሞ ተመሳሳይ ነበር፡- ‹‹ለሀገርና ህዝብ ጥቅም››፡፡
ንጉሰ ነገስቱ ልጅ እያሱን ያስወገዱበት ምክንያት ‹‹ሀገርን ከሚያጠፉ ጋር በማበሩና ህዝብን ከማስተዳደር ይልቅ፣ ለግላዊ ምቾት ጊዜውን
በዋል ፈሰስ በማዋሉ ነው›› የሚል ሰበብ እንደነበረ ይታወሳል፡፡ በግልባጩ እርሳቸውም ከግማሽ ክፍለ ዘመን በኋላ አደባባይ ባናወጠ
ንቅናቄ ተገፍተው፣ ገደል አፋፍ በቆሙባት በዛች ዕለት፣ የሠራዊቱን መለዮ ባጠለቀ አንጋች የተነበበላቸው የክስ ደብዳቤ፡- ‹‹ሀገርን
ለቆሞ-ቀር፣ ሀብትን ለቤተሰብና ለግለሰቦች ጥቅም መመዝበር፣ ህዝብን ለከፋ ጭቆናና ሰቆቃን ላዘነበ ረሀብ መዳረግ…›› የሚል እንደነበረ
ስናስታውስ ‹ታሪክ ራሱን ደገመ› ያሰኛል፡፡ በዚህ መልኩ ‹‹በደልና ግፍ ከምሽግ አስወጣን›› ባሉ ወታደራዊ መኮንኖች የተመሰረተው
የደርግ መንግስትም አስራ ሰባት ዓመት ሙሉ እንዳሻው ሲገድል፣ ሲፈልጥ፣ ሲሸልል… ቆይቶ ‹‹ብሶት ከትምህርት ገበታ አፈናቀልን›› ባሉ
በረኸኞች ፍፃሜው ይሆን ዘንድ ግድ ሆነበት፡፡ ታሪክም የሚነግረህ ይህንኑ ነው፤ ሌላ የለም፡፡ ያገዛዝ ጭቆናና መከራ ያስመረረው
አደባባዩን በኃይል ሲነጥቅ-ሲነጥቅ ዛሬ ላይ መድረሱን፡፡ በርግጥ ይህ እርግማን አይደለም፤ ለጨቋኞች በልክ የተሰፋ ፍትሀዊ ፍርድ
የሚተላለፍበት አማራጭ መንገድ እንጂ፡፡
የሆነው ሆኖ ዛሬም ቢሆን ትውልድ እንጂ ታሪክ አልተቀየረምና፣ የለውጥ መንገዶች በሙሉ ሄደው ሄደው ወደ አደባባይ የሚገፉ
ሆነዋል፡፡ በኢትዮጵያ ምድር ‹የነፃነት በር በብላሽ አይከፈትም› ያለው ማን ነበር? ...ርግጥ ነው መለስ ዜናዊም በርሃ ሳለ ‹‹ምኹሕዃሕ
ዘይፍለዮ ማዕፆ›› (ማንኳኳት ያልተለየው በር) በተሰኘ ታንክ ተደግፎ በፃፈው መፅሀፉ ላይ የደርጉን ፋሺስትነት ከመተንተኑ
በተጨማሪም ከጓደኞቹ ጋር ተስፋ ሳይቆርጥ ባደረገው ትግል ነፃነቱን ተቀዳጅቷል፡፡ ይሁንና በለስ ቀንቶት በትረ-ስልጣን ከጨበጠ
በኋላ ግን፣ የአስተዳደር ዘይቤውን የወረሰው ታግሎ ከጣለው ስርዓት ዶሴ እንደነበር ለመረዳት ብዙ አላስጠበቀም፤ ቀድሞ
የተተገበረውን አሻሽሎ፣ በከፋ መልኩ ደጋግሞ ተግብሮታል፡፡ የመፅሀፉ ዋና ገፅ-ባህሪ ‹‹እነይ ስላስ›› በእንባ እንደታጠቡት፣ በድህነት
እንደጎበጡት ሁሉ ዛሬም የኢትዮጵያ እናቶች በደህነት አጥንታቸው ገጥጧል፤ ለእስርና ለስደት በተዳረጉት ልጆቻቸው ጉልበታቸውን
ታቅፈው በሀዘን እንዲወዛወዙ ተፈርዶባቸዋል፤ ሥራ-አጥ ጎረምሳ ልጆቻቸውን ለመቀለብ ላይ-ታች ከመማሰን አልተገላገሉም፤
‹‹ለግርድና›› ወደ አረብ ሀገር የተሰደዱትን ሴት ልጆቻቸውን እያሰቡ በስጋት እየተናጡ ነው… እናም በኢህአዴግና እነርሱ ‹‹ፋሺስት››
በሚሉት በደርጉ ስርዓት መካከል የታየው የአስተዳደር አይነት የጊዜና የሰዎች ልዩነት ብቻ እስኪመስል ድረስ የአንድ ሳንቲም ግልባጭ
መምሰሉ ‹‹ነፃ አውጪ››ነቱን ምፀት አድርጎታል፡፡ በበረሃ የተደረሰው መዝገበ ቃላትም ‹‹ህዝብ በሁለት ይከፈላል›› ይላል-በ‹‹ደጋፊ›› እና
‹‹ተቃዋሚ›› ጎራ፡፡ ተቃዋሚ የተባለውንም የምድር እርግማን ሁሉ ይፈፀምበት ዘንድ ያዝዛል፤ ጭቆና፣ ግፍ፣ ጭካኔን… በህዝብ
ደህንነትና ሰላም ስም ማንበር፤ በህገ-መንግስት ትከሻ ማንጠልጠል፤ ህልምን፣ ምርጫን፣ ህዝበ-ውሳኔን… በክንደ-መሳሪያ መተርጎም…
በዚህ የተነሳ የለውጥ ሃዋርያት ወደ አደባባዩ ይጎርፉ ዘንድ ወቅቱ ግድ ብሏል፤ በርግጥም ስርዓቱ በደልን ዘርተው፣ በደልን በሚያፀድቁ፤
ጭቆናን ከዳር ዳር በሚያዳርሱ፤ በፍትሕ በሚዘባበቱ፤ ከመልካም አስተዳደር በእጅጉ በራቁ፤ በሀገር ሀብት ራሳቸውንና ዘመዶቻቸውን
ባበለፀጉ፤ ስቃይንና መከራን የአገዛዝ ስልት ባደረጉ፤ በአማላይ ዕቅድና ፖሊሲ በሚሸነግሉ፤ የምርጫን ውጤት እንደፍቃዳቸው
ማገለባበጥ በተካኑ… የተዋቀረ በመሆኑ እነሆ ሕዝቡ ለድፍን ሃያ ሁለት ዓመታት አሳር መከራውን እንዲቆጥር ተፈርዶበታል፡፡
መቼስ ከሁለት አስርተ ዓመታት በላይ በሥልጣን ስለቆየው የኢህአዴግ አስተዳደር ክስረትና ሽንፈት በእንዲህ አይነቱ የመፅሄት ፅሁፍ
ተንትኖ ለመጨረስ ቀርቶ፣ ጠቅሶ እንኳን ማለፍ የሚቻል አይመስለኝም፡፡ ምክንያቱም የድርጅቱ ገመና በዜጎች መሀል አለመተማመን
ከመፍጠር አንስቶ በሀገር ጥቅም መደራደር፣ ህግን የፖለቲካ መጠቀሚያ ማድረግ፣ ሰላዮችን አለቅጥ በሕዝብ መሀል መሰግሰግ፣
የሠብዓዊም ሆነ የፖለቲካ መብቶችን መጨፍለቅ፣ የሀገር ሀብትን መዝረፍና ማዘረፍ፣ በሥልጣን መባለግ፣ የልማት አጀንዳን
ለፕሮፓጋንዳ መሳሪያነት ብቻ መጠቀም፣ በዚህም የሥራ-እጥ ቁጥርን ማናር፣ የኑሮ ውድነትን ማሻቀብ፣ ዜጎችን ማፈናቀል፣ በሠላማዊ
ህዝብ ላይ የታጠቀ ኃይል ማዝመት፣ ፍርሃትን ማንገስ… እያለ ይቀጥላልና ስንቱን ዘርዝሮ መጨረስ ይቻላል? ይህ ተቆጥሮ የማያልቅ ሃያ
ሁለት ዓመታትን ያስቆጠረ አሳረ-መከራም ነው ብዙሃኑን ‹አደባባዩ ምን ያህል ይርቃል?› የሚል ጥያቄ እንዲያንሰላሰል ገፊ ምክንያት
የሆነው፡፡ ተቀራራቢው መልስም ከሚከተሉት አንዱ ሊሆን ይችላል፡- የሞትን ያህል፣ በእስር ቤት የመበስበስን ያህል፣ በስደት
የመንከራተትን ያህል ወይም ለተጨማሪ ሃያ፣ ሰላሳ፣ አርባ… የጭቆናን ዓመታት ያህል?
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ካገዛዙ ባህሪይ አንፃር ከላይ የተዘረዘሩት በሙሉ ለጥያቄው መልስ ሊሆኑ እንደሚችሉ አንድ እንኳ የሚጠራጠር ያለ አይመስለኝም፡፡
ምክንያቱም የስርዓቱ ስር የሰደደ ሴራ ‹ግደል› ሲባል የሚገድል፣ ‹ተኩስ› ሲባል የሚተኩስ፣ ‹አፍን› ሲባል ‹ለምን?› ብሎ የማይጠይቅ
የታጠቀ ኃይልን ማሰልጠኑ እና በሀሰት ለመክሰስ የማያመነታ ህሊና ቢስ ዓቃቢ ህግን፣ በሀሰት ለመፍረድ የማያቅማማ ዳኛን፣
በአጠቃላይ ሰጥ-ለጥ ብሎ የሚገዛ ሎሌ ትውልድ… ለመፍጠር አቅዶ መስራቱ ነውና፡፡
በአናቱም የምሁራኖቻችን አድርባይነትም ሆነ ዝምታ ለከፋፋይ አገዛዙ ጉልበት ሆኖታል፡፡ አብዛኛዎቹም ነገን አጥብቀው የሚፈሩ፣
ከሀገርና ህዝብ ጥቅም በላይ የግል ምቾታቸው የሚያስጨንቃቸው መሆንን መርጠዋል፡፡ የተቀሩት (ገቱ ያላቸው) ጥቂት ታላላቆችም
ቢሆኑ ኃላፊነታቸውን አልተወጡም፤ ወይም ሞክረው አልተሳካላቸውምና ለዛሬቷ ኢትዮጵያ ‹‹የቁልቁለት መንገድ›› የድርሻቸውን
ማንሳታቸው አከራካሪ አይሆንም፡፡
ሌላው ትልቁ እንቅፋት ደግሞ የአገዛዙ ቂመኝነት ከዕለት ዕለት፣ ከዓመት ዓመት እየከፋ መምጣቱ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ በአስከፊዎቹ
የሀገሬ እስር ቤቶች የከረቸመባቸውን እነዛን (ራሳቸውን መከላከል የማይችሉትን) የህሊና እስረኞች ‹ማኪያቬላዊ በቀል› በተሰኘው
መፅሀፉ ምሪት ፍዳቸውን ከማስቆጠር አልተመለሰም፡፡ እስክንድር ነጋ፣ አንዱአለም አራጌ፣ በቀለ ገርባ፣ ርዕዮት አለሙ፣ ውብሸት ታዬ…
የድርጊቱ ጥሩ ማሳያ ናቸው፡፡ ርግጥ ነው መንግስት ሰዎቹን ያሰረው ለሕዝብ ጥቅም ሲል እንደሆነ ዛሬም ድረስ ለማሳመን እየለፈለፈ
ነው፤ ይሁንና እስካሁን ያልነገረን ማሰቃየቱ፣ ፍትህ መንፈጉና ጠያቂ መከልከሉ… ለማን ጥቅም ሲባል እንደሆነ ነው፤ ለሕዝብ ይሆን?
ከሁሉም በላይ ግራ የሚያጋባው ነገር ደግሞ የእስረኞቹ ጠባቂዎች ልበ-ደንዳናነት ነው፤ የእነርሱን ያህል የተጎሳቆሉ፣ የእነርሱን ያህል
የተገፉ፣ የእነርሱን ያህል የተበደሉ ታሳሪዎችን ለማንገላታትና ለማሰቃየት ያላቸው ሞራል የበዛ ነውና፡፡
መቼም በዚህ ዘመን የእኛዎቹን እስር ቤቶች ያህል አስከፊ የሰቆቃ ቦታዎች በየትኛውም የዓለም ክፍል ያሉ አይመስለኝም (ለካስ! እንዲህ
ዘመን የተጣላት፣ ታሪክ የተቃረናት ሀገር ዜጋ መሆን የከፋ ስቃይ ኖሯል!!) …ይህ ሁኔታም ይመስለኛል ከስርዓቱ አጋፋሪና አጫፋሪዎች
ይልቅ ጨካኙን በሽር አልአሳድን በሶሪያ ጎዳናዎች የሚፋለሙት ነፃነት ናፋቂዎች በሥጋ የተዛመዱህ ያህል እንድትቆረቆርላቸው
ያደረገው፤ ከጨቋኝ የሀገርህ ገዥዎችም ይልቅ፣ በየትኛውም ክፍለ ዓለም ያሉ ጭቁን ህዝቦችን ‹ወገኔ› እንድትል ያደረገው፤ ከእነርሱ
የመንፈስ አንድነትን፣ የነፍስ ትስስርን በፅኑ ስለምትጋራ ነው፡፡ አንተም ጭቁን ነህና የተጨቋኞች አበሳ ይቆጠቁጥሀል፤ አንተም
መብትህና ክብርህ ተገፏልና፣ ተመሳሳዩ ከተፈፀመባቸው ሕዝቦች ጎን መቆምህ ግድ ነው፡፡ …ከዚህ በተረፈ ‹እንመራሀለን› የሚሉህ
ወንድሞችህ፣ ልብህን በጩኸት ከማሸበር፣ ዘመንህን ካለፉትም በላይ የከፋ ከማድረግ፣ ለዓመታት ቀጥቀጠው ከመግዛት ያለፈ የፈየዱት
ቁም-ነገር የለምና ለእነርሱ ቀረቤታና ሀዘኔታ ከቶም ሊሰማህ አይችልም (በነገራችን ላይ አንዳንድ ለውጥ ናፋቂዎች ስርዓቱን ከመላው
የትግራይ ተወላጆች ጋር ደርበው መውቀሳቸውና መክሰሳቸው ስህተትና ለሀገር አንድነት ጠንቅ መሆኑን አምነው ካልተቀበሉ የትግሉን
ዕድሜ ከማራዘሙም በላይ ለከፋ ችግር መዳረጉ አይቀሬ ነው፡፡ በዚህ መልኩም ተሰልቶ የሚመጣ ውጤትም የኢህአዴግን ስህተት
በእጥፍ መመንዘር ነው የሚሆነው፡፡ እናም ምርጫው ሁለት ይመስለኛል፤ ይህ አይነቱን ሸውራራ /ጨለምተኛ/ አተያይ አስተካክሎ
ታላቂቷን ኢትዮጵያ በጋራ መገንባት፣ አሊያም የህወሓትን መንገድ በመከተል ለውጡን በዜሮ አባዝቶ ሀገርን እንደአንባሻ ዘጠኝ ቦታ
ለሚከፋፍል አደጋ ማጋለጥ)
የመነቃቃት መንፈስ…
ጥያቄው ይህ ነው፡- ህማማቱ ስንት ቀን ይፈጃል? የማራኪና ተማራኪ አስተዳደር ዕድሜው ምን ያህል ይረዝማል? ስለምንድር ነው
ባለስልጣናት አስፈራሪ፣ ቀለብ ሰፋሪ ህዝብ ደግሞ ተስፈራሪ የሆኑት? ማን ነውስ መብታቸውን የሚጠይቁ የሃይማኖት መሪዎችን-
አክራሪና አሸባሪ፣ ተቃዋሚዎችን-በሀገር ላይ የሚያሴሩ፣ ጋዜጠኞችን-የጠላት ሀገር ተላላኪ ያደረገው? በየትኛው ህግስ ነው ስርዓትን
መደገፍ-ሀገር ወዳድ፣ መቃወም-ይሁዲነት የሆነው? …ግና እመነኝ ውንጀላው በጉልበታም ገዥዎች ዘንድ የተለመደ የፖለቲካ ጨዋታ
ነው፡፡ በተቀረ ነፃነትን ያጣጣሙ ነባር ሀገራትን ትተህ፣ የቅርቦቹን እነቱኒዚያን ብትወስድ እንኳ፣ አደባባዩ ሽንፈት ያወጀባቸው
ገዥዎቻቸው ተመሳሳዩን ይፈፅሙ እንደነበር ድርሳናቶቻቸው ይነግሩሀል፡፡ ምንም እንኳ ዛሬ ታሪክ ቢሆኑም፡፡
ያንተም ጨቋኝ ገዥዎች ታሪክ የሚሆኑት፣ ይህ ሁሉ አሳረ-ፍዳ ከእነጦስ ጥንቡሳሱ ሊወገድ የሚችለው ዋጋን በሰማይ በሚከፍለው
‹‹ንሰሃ›› አይደለም፣ ጎዳናዎችን በሚያጥለቀልቅ ህዝባዊ ቁጣ እንጂ፡፡ እናም የአደባባዩን ርቀት ከጭቆናው ጋር እያለካኩ፣ የፍርሃት
ሰንሰለትን አየበጠሱ፣ በሁከተኛው ስርዓት ላይ የሚጮኹ የነፃነት ድምፆችን ማስነሳቱ አማራጭ አልባ መፍትሄ ነው፤ እነዛ ጎበዛዝቶች፣
በሚከፍሉት ዋጋ ታጋይ እንጂ ትግል እንደማይሞት እያስመሰከሩ፣ መንገዶቹን የሚያንቀጠቅጡ ፋኖዎች ከቁም እንቅልፍ የሚባንኑበትን
ዕለት ማሳጠር የግድ ይላል፡፡
በዚህም አለ በዚያ ይህ ኩነት ይለወጥ ዘንድ ስደት መፍትሄ አይሆንም፤ ማሳደዱን፣ ማስፈራራቱን፣ ማደህየቱን፣ ማሰር፣ መግደሉን…
ከቶም ቢሆን ሀገር ጥሎ በመሄድ ማሸነፍ አይቻልም፤ ምክንያቱም የስርዓቱም ፍላጎት ይኸው ነውና፤ የተቃወመውን፣ በስልጣን
አደገኛነት የጠረጠረውን ከሀገር በማባረር፣ ከአደባባዩ ይበልጥ ማራቅ፣ ከአይን መሰወር፣ በዚህም ለውጥ ያረገዘውን የቁጣ ቀን ማዘግየት፡፡ ለዚህም ነው ‹እኔ ምን አገባኝ›ም ሆነ ስደት መፍትሄ አይሆንም የምለው፡፡ አዎን! ሀገሪቱን የጥቂቶች ብቻ ለማድረግ
የተያዘውን ግብግብ ማጨናገፍ የምትችለው መሬት በሚያርድ ሠላማዊ ቁጣ ብቻ ነው፤ የሰብዓዊ መብት አፈናም ሆነ ሥራ እጥነትና
ድህነት የሚያሰድዳቸው ወንድም እህቶቻችን የባሕር ሲሳይ የሚሆኑበትን አሳዛኝ ዕጣ መለወጥ የምትችለው በአደባባይ ቁጣ ነው፤
የህሊና እስረኞችን ነፃነት ማወጅ የምትችለው እጅ ለእጅ ተያይዘህ የጎዳና ቁጣን በማሰማት ነው፤ ረሀብና ድህነትንም ማጥፋት
የምትችለው በቅድሚያ በሰንካላ ፖሊሲና ደካማ አስተዳደር በሚመራው ስርዓት ላይ መቆጣትና ማምረር ስትችል ነው፡፡ ይህ ሲሆን
ብቻ ነው ኢትዮጵያ የአንተም ሀገር የምትሆነው፡፡
 የጥሪው ድምፅ
‹‹ሰላም ይሉናል፣
ጥርሳቸውን እያፋጩ በጥል
ቤት እያፈረሱ በበቀል
ኑሮን እያደረጉ ገደል
ሰላም ይሉናል፣
እኛ እንግዛ፣ እናንተ ተገዙ
እኛ እንዘዝ፣ እናንተ ታዘዙ
እኛ እናስብ፣ እናንተ ደንዝዙ
ንገሯቸው እባካችሁ
ሰላም ነፃነት ነው ብላችሁ
ዝም አትበሉ
እሪ በሉ
ጠመንጃቸውን እስቲጥሉ፡፡›› (ፕ/ር መስፍን ወ/ማሪያም ‹‹ዛሬም እንጉርጉሮ›› የግጥም መድብል)
እነሆም የሀገሬ ጀግኖች ከአንቀላፉበት አዚም ይነቁ ዘንድ ጩኸቱ በርክቷል፤ የደውል ድምፁም አስተጋብቷል፤ አምነት የሚጣልበት
የአርነቱን ‹ሙሴ›ም፡-
‹‹ጥሩት አያ’ገሌን ያሳየን መንገዱን
መሪ ነው ያጣነው፣ ስናቋርጥ ዱሩን›› (አንዱአለም አባተ ‹‹የረዘመ ትንፋሽ›› የግጥም መድብል) የሚሉ ድምፆች እያፈላለጉት ነው፡፡
እውነት እውነት እልሀለሁም፡- ይህ ሲሆን ነው በነብያቶች አንደበት የተነገረው በኢትዮጵያ ‹‹ታህሪር›› ታሪክ የሚሰራበት፣ ጭቆና-ድባቅ
የሚመታበት፣ ያጎነበሰ አንገት-የሚቃናበት፣ የተሰበረ ልብ-የሚጠገንበት፣ የደከመ መንፈስ-የሚበረታበት፣ ነፃነት የሚዋጅበት፣
በምኩራቦቹ ፍትህ-የሚሰበክበት፣ ህግ-የሚከበርበት፣ አድሎአዊነት-የሚወገዝበት… ይሆናል፤ ደጀ ሰላሞቹም የሰብዓዊ መብት
የሚከበርባቸው፣ የመኖር ዋስትና የሚረጋገጥባቸው…፤ አውደ ምህረቶቹም ያለቀሱ የሚስቁበት፣ የአዘኑ የሚፅናኑበት… ይሆናል፡፡ ይህ
ነው ነብያቶቹ የተናገሩት የተስፋው ቀን፤ የተስፋው ምድር፡፡ … እነሆም በገዥዎች ላይ ሰቆቃንና ዋይታን ከሚያዘንበው የመጨረሻዎቹ
ቀናት በፊት እንዲህ ማለትን ወደድኩ…
 አንድ ምክር-ለጓዶች
ደጋግማችሁ የአደባባይ ተቃውሞን፣ ሕዝባዊ ንቅናቄን ለማውገዝ እንደ ምክንያት የምትጠቀሙበት ‹‹ሀገሪቱን በልማት ጎዳና አከነፍናት፣
እድገታችን ለተከታታይ ዓመታት ከሁለት ዲጂት በላይ ከሆነ ሰነበተ›› የሚለው ሀቲት፣ተራ ፕሮፓጋንዳ እንደሆነ የታወቀ ቢሆንም እስቲ
‹‹ይሁን›› ብለን ብንቀበለው እንኳ እንደምኞታችሁ የተቃውሞው ድምፆች ይዘጉ ዘንድ የግድ እንዲህ የሚሉትን ወሳኝ ጥያቄዎች መመለስ
ይኖርባችኋል፡- የፖለቲካ ነፃነት አለመኖሩስ? በስርዓቱና በአምሳሉ የተቀረፁ ተቋማት ተአማኒነት ማጣታቸውስ? ጎሳን እየነጠሉ ለፖለቲካ
ጥቅም ማዋሉስ? አዋጅና ፖሊሲ ከመፅደቃቸው በፊት ሀቀኛ ተቀናቃኞች፣ ገለልተኛ ምሁራን እና የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ በድፍረት
እንዲተቹበት አለመደረጉስ? (‹ሰው በእንጀራ ብቻ ይኖራል!› የሚል እምነት አራማጅ የሆኑትን የኢቲቪ ሸንጋይ ‹‹ምሁራኖች››ን
እርሷቸውና ማለቴ ነው)፣ ሃሳብን በነፃነት ለመግለፅ የሚያበረታ መደላድል አለመኖሩስ? ማንም ሰው ባመነበት ሃሳብ መደራጀት
አለመቻሉስ? የህግ የበላይነት ከወረቀት አለመዝለሉስ? መከላከያ ሠራዊት፣ ፌዴራል ፖሊስና የደህንነት ተቋሙ ተጠሪነታቸው ከህገ-
መንግስቱ ይልቅ ለፓርቲ መሆኑስ? …እናም ‹ህዝብን ከፍ ከፍ አድርጎ ያከበረ መንግስት መንበሩ የፀና ይሆናል!›› እንዲል ጠቢቡ፣
የረዣዥም ተራሮቻችንን አናት ሳይቀር ለማንቀጥቀጥ በማስገምገም ላይ ያለው ይህ ብርቱ የቁጣ ድምፅ የሚረግበው፤ የፈረሱ ቅፅሮችን
በጋራ ለማነፅ በመሀከላችን መተማመን የሚሰፍነው፤ ‹ባቢሎናውያን›ነት ሰክኖ፣ እርስ በእርስ መደማመጥ የሚቻለው እነዚህ ከላይ
የተጠቀሱት የለውጥ ፈላጊው ወሳኝ ጥያቄዎች በአስቸኳይ ሁሉንም ወገን በሚያሳምን መልኩ መፍትሄ የተሰጣቸው እንደሆነ ብቻ ነው፡፡
ከዚህ ሌላ መፍትሄ የለም -ታሪክን በከፋ መልኩ ከመድገም በስተቀር፡፡
መልካም ዕድል!
ኢትዮሚድያ - Ethiomedia.com – October 27

Friday, October 25, 2013

የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ ተሰደዱ

ሲኖዶሱ ያሳለፈውን ውሳኔ ፓትርያርኩ ቀለበሱት 
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አመታዊ ስብሰባውን እያከናወነ በሚገኝበት ሰዓት በተለያዩ አነጋጋሪ ክስተቶች መታጀቡን የፍኖተ ነጻነት ምንጮች ገልጸዋል፡፡
የሲኖዶሱ ስብሰባ ከመጀመሩ አስቀድሞ የፌደራል መንግስት ጉዳዩች ሚኒስትር ተወካዩች በተገኙበት የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሰዎች፣የገዳማትና የአድባራት አስተዳዳሪዎችና ጳጳሳት በተገኙበት በተካሄደ ውይይት ጳጳሳቱ የመንግስት ተወካዩች ላቀረቡት ሐሳብ ያላቸውን ልዩነት በመግለጽ መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ እጁን እንዲሰበስብና ለህገ መንግስቱ ተገዢ እንዲሆን መጠየቃቸው ይታወሳል፡፡በዚህ ስብሰባ ወቅት የሚመሩትን የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት በመወከል ተሳታፊ የነበሩት ሃላፊው ያለ ቤተ ክህነቱና ሃገረ ስብከቱ እውቅና ውጪ ወደ አሜሪካ ማቅናታቸው ተረጋግጧል፡፡
የአዲስ አበባው ሃገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ መጋቤ አዲስ ይልማ ቸርነት ለስደት ሲዳረጉ ምክትላቸው የነበሩት አቶ ዩናስ ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ ተደርገዋል፡፡መጋቤ አዲስ አገራቸውን በመልቀቅ ለስደት የተዳረጉበትን ምክንያት ከወቅቱ ፓትርያርክና አመራራቸው ጋር ስምምነት በማጣታቸው የተነሳ መሆኑን ምንጮቻችን ግምታቸውን አኑረዋል፡፡
ቅዱስ ሲኖዶሱ በትናንትናው የስብሰባ ውሎው ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ በአብላጫ ድምጽ ወስኖባቸው የነበሩት የአዲስ አበባው ሊቀ ጳጳስ አቡነ እስጢፋኖስ በዛሬው ዕለት ፓትርያርኩ አቡነ ማቲያስ ‹‹አዲስ አበባ የእኔ ልዩ ሐገረ ስብከት በመሆኑና ማንም ሊያዝበት ስለማይችል ሊቀ ጳጳሱ በቦታቸው እንዲቀጥሉ በመወሰን የትናንቱን ውሳኔ ሽሪያለሁ››ማለታቸውን ምንጮቻችን ተናግረዋል፡፡
ሲኖዶሱ በማድረግ ላይ የሚገኘውን አመታዊ ስብሰባ ነገ የሚያጠናቅቅ ቢሆንም ሂደቱን በመከታተል ጋዜጠኞች እንዳይዘግቡ ሲኖዶሱ ለጋዜጠኞች ወደ ስብሰባው የመግቢያ ፈቃድ ከልክሏል፡፡

ምንጭ UDJ

Thursday, October 24, 2013

ሕዝባዊ እምቢተኝነት በውጭ አገር፤ እንዴት?

ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በሁለገብ ትግል ወያኔ ማስወገድ ይገባል ብሎ የሚያምና ለዚህም የሚታገል ድርጅት ነው። “ሁለገብ ትግል” ሲባል ሰላማዊም ሰላማዊ ያልሆኑም የትግል ስልቶችን መጠቀም ማለት ነው። “ሁለገብ ትግል” ሲባል በአገር ውስጥም ከአገር ውጭም የሚደረጉ ትግሎች ማለት ነው።
ከዚህ አንፃር በውጭ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ሚና ምን ሊሆን ይገባል?
በግንቦት 7 እምነት በውጭ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በድጋፍ ሰጭነት ሳይወሰኑ የትግሉ ቀጥተኛ ተሳታፊዎች መሆን ይኖርባቸዋል። በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በወያኔ ጥቅሞችና ተቋማት ላይ በማመጽ ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን አርዓያ መሆን ይኖርባቸዋል።
በዚህ ረገድ የተጀመሩ አበረታች ጥረቶች አሉ፤ ለምሳሌ:
  1. ወያኔ ሙስሊሞችን ከክርስቲያኖች ለማጣላት ያልፈነቀለው ድንጋይ የለም። በውጭ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን “እንቢ አንጣላልህም” ያሉት መሆኑ የሚያኮራ ነው። ወያኔ ከጠበቀው በተቃራኒ የሁለቱም ሃይማኖቶች መሪዎች በጋራ ጉዳዮች ላይ ሲመክሩ መታየቱ ተስፋ ሰጪ ጅማሮ ነው። አብሮነታችንን ማጎልበትና ይህንን በአደባባይ፣ በአዳራሾች፣ በቴሌቪዥን መስኮቶች ለኢትዮጵያ ሕዝብ ማሳየት እጅግ አስፈላጊ ነገር ነው። ውጭ የተጀመረው አገር ቤት መዳረሱ የማይቀር ነው። ይህ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርብናል።
  2. ወያኔ በአባይ ግድብ ስም በውጭ አገራት ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በርከት ያለ ገንዘብ እንደሚያገኝ ተስፋ አድርጎ የነበረ ቢሆንም ኢትዮጵያዊያን “ከአባይ በፊት የሰብዓዊ መብት ጥሰት ይገደብ” “ከአባይ በፊት ሙስና ይገደብ” እያሉ ወዋጮዎቹን እንቢ ብለዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ እስካሁን የታየው ጽናት በጣም አበረታች ነው። የወያኔ ሹማምንት በአባይ ጉዳይ እንኳንስ ገንዘብ ስብሰባም ሊሰበሰቡ አልቻሉም። ይህም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል።
  3. ኢትዮጵያዊያን በስፖርትና በኪነጥበባት መስኮች የሚያደርጓቸው መሰባሰቦች ለትግሉ ትልቅ እገዛ ይሰጣሉ። የኢትዮጵያ ስፓርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ (ESFNA) ከወያኔና ከወያኔ ሸሪክ ቱጃር ጋር ያደረገው ትንንቅ የሚያኮራ ነው። በርካታ ኢትዮጵያዊያን አገር፣ ነፃነት፣ ክብር ይበልጥብኛል ብለው የቀረቡላቸውን አጓጊ ማባበያዎችን “እንቢ” ብለዋል። ይህ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል።
  4. ባለፈው ዓመት ጋዜጠኛ አበበ ገላው በመለስ ዜናዊ ላይ፤ ዘንድሮ ደግሞ ጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድና አቶ መስፍን የዘረኛው ወያኔ ግንባር ቀደም አስተባባሪ በሆነው ስብሀት ነጋ ላይ ያሰሙት ተቃውሞ በጣም የሚደገፍና በውጭ አገራት የምንገኝ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ባህል ሊሆን ይገባዋል።
  5. በስዊድን የሚገኙ የሕግ ባለሙያዎች የጀመሩት እና በኢትዮጵያዊያን ከፍተኛ ተሳትፎ እየተካሄደ ያለው የወያኔ ወንጀለኞችን ወደ ፍርድ የማቅረብ ሂደት ተጠናክሮ መቀጠል አለበት።
እነዚህ መልካም ሥራዎች ምሳሌቶች ሲሆኑ በውጭ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ከዚህ በላይ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። አንዳንዱን ለአብነት ያህል ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል።
  1. በአገራችን ውስጥ መሠረታዊ የሆነ ለውጥ እንዲመጣ ከፈለግን ወያኔን ማስደንገጥ፣ ማሸበር፣ ካስፈለገም ማስወገድ የሚችል የአመጽ ኃይል መኖሩ ወሳኝ ነው። እንዲህ ዓይነት የወገን ኃይል ከጀርባው መኖሩ ሲሰማው ነው ሕዝብ ለእንቢተኝነት የሚነሳሳው። በውጭ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ይህንን ኃይል ቢቻል መቀላቀል፤ ካልተቻለም በአባላት ምልመላ፣ በፋይናንስ፣ በሎጂስቲክስና ዲፕሎማሲ መደገፍ ይጠበቅባቸዋል። ይህ ከሁሉ የላቀ የእምቢተኝነት መገለጫ ነው።
  2. ትግሉ እየመረረ መሆኑ በመረዳት በርቀት ሆነን ከመብሰክሰክ በትግል ላይ ያሉትን ድርጅቶች መቀላቀል ሌላው አሁኑኑ ልናደርገው የሚገባ ነገር ነው። ድርጅቶች “አይረቡም” ብለን ስላጣጣልናቸው አይጠናከሩም። ድርጅቶችን ማጠናከርና ማዘመን ያለብን እኛው ነው። መሪዎችን ማውጣት ያለብን እኛው ነው። እስካሁን ድርጅቶችን ያልተቀላቀልን ካለን መቀላቀልና ትግሉን ማጧጧፍ ይኖርብናል።
  3. በየተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ወያኔን “እንቢ” እንበል። “እንቢ” የማለትን አጋጣሚ ማሳለፍ የለብን። “እንቢ” ማለት የምንችልባቸው አጋጣሚዎች ብዙዎች ናቸው። ለምሳሌ: -
ሀ) ወያኔ የመኖሪያ ቤቶች ግንባታን አዲስ የገንዘብ ማለቢያ ለማድረግ አቅዶ ተነስቷል። ወደ ሚሊዮን የሚጠጉ ቤቶችን በ2 ዓመት ጨርሼ አስረክባለሁ በሚል ማባበያ በውጭ አገራት ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ገንዘብ ለመሰብሰብ ዝግጅቱን አጠናቋል። ይኸንን ነገር አጠንክረን “እንቢ” ማለት ይኖርብናል። “ለኛ ቤት ከመሰጠቱ በፊት፤ የተፈናቀሉ ወገኖቻችን መወደቂያ ያግኙ” ማለት ካልቻልን በራሳችን ማፈር አለብን። የአውሮፓና የአሜሪካ መንግሥታትን አምባገነኖችን በገንዘብ አትደግፉ እያልን እኛ ራሳችን ወያኔን በገንዘብ የምንደግፈው ከሆነማ ከነሱ ብሰን መገኘታችንን እንወቀው።
ለ) ወያኔ በስደተኛ ስም በመካከላችን የሰገሰጋቸውን ካድሬዎችን የማጋለጥ ዘመቻ ማፋፋም አለብን። የወያኔ ደጋፊዎችን በኤርትራ ስደተኞች ስም እንደሚገቡ መረጃዎች አሉ። በደል ደርሶብናል ብለው መንግሥታትን አሳምነው የመኖሪያ ፈቃድ ካገኙ በኋላ አጠቃን ካሉት አገዛዝ ጋር የሚሠሩ መሆናቸው የሚያረጋግጡ ማስረጃዎችን አጠናቅረን ለየሀገሩ መንግሥታ ማቅረብ እንደ አቢይ ሥራ መያዝ ይኖርብናል።
ሐ) የወያኔ ባለሥልጣናት የሚገዟቸውን ቤቶች፤ የሚያስተዷድሯቸውን ቢዝነሶች እያደንን ማጋለጥ ይኖርብናል።
መ) የወያኔዎች ሹማምንት በአሜሪካና አውሮፓ በነፃነት ሊዘዋወሩ አይገባም። በሄዱት ሁሉ ተቃውሞና ውርደት ሊከተላቸው ይገባል።
ሠ) የወያኔ ቢዝነሶች ላይ ማዕቀብ ማድረግን (ቦይ ኮት) መልመድ አለብን። ጥረቶቻችንን በፈጠራ ከደገፍን ወደ አገር ቤት የምንልከው ገንዘብ የወያኔ የውጭ ምንዛሬ ረሀብ ማስታገሻ የማይሆንበት መንገድ መሻት አለብን።
ረ) ለወያኔ ባለሥልጣኖች ዲግሪ የሚያድሉ ዩኒቨርስቲዎችና ኮሌጆችን ማዋረድ መጀመር አለብን። ስምንተኛ ክፍል እንኳን በወጉ ላልጨረሱ ሰዎች የማስትሬት ዲግሪ እንደሰጡ ማሳወቅ የኛ ኃላፊነት መሆን አለበት።
በግንቦት 7 እምነት ትግሉ በሁሉም ሥፍራ ነው። ኢትዮጵያዊያን በያለሉበት ቦታ በተደራጀና በተቀናጀ መልክ ወያኔን ፊት ለፊት ከተጋፈጥን የድላችን ቀን እናቀርባለን።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!

Monday, October 21, 2013

የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ

ዓለም ዓቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሚዋጋች ድርጅት ሂዩማን ራይትስ ዎች ባለፈው ዓርብ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ላይ ያተኮረ በተለይም አዲስ ኣበባ በሚገኘው እና ማዕከላዊ ተብሎ በሚታወቀው የፌደራሉ የምርመራ ማዕከል በእስረኞች ላይ ይፈጸማሉ ባላቸው ሰብዓዊ ሰቆቃዎች ላይ ያነጣጠረ አዲስ ሪፓርት ይፋ ኣድርገዋል።
Zu: Boss von mexikanischem Golf-Kartell festgenommen - Neuer Schlag gegen Drogenmafia
A relative of an inmate observes policemen behind the security fence after a riot inside Apodaca prison, on February 20, 2012, near Monterrey, state of Nuevo Leon, Mexico. At least 44 inmates have been killed during a riot Sunday and about 30 alleged members of the drug cartel Los Zetas were rushed out from the prison. AFP PHOTO/Julio Cesar Aguilar (Photo credit should read Julio Cesar Aguilar/AFP/Getty Images)
ሰብዓዊ መብት ሲባል በነገስታት መልካም ፈቃድ የሚቸሩ ወይንም መንግስታት ከሚመሩባቸው ህግጋተ መንግስታት የሚመነጩ ብቻ ሳይሆኑ በ ተ መ ድ የሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌዎች መሰረት ሰዎች ሰው በመሆናቸው ብቻ በተፈጥሮ የተቀዳጁኣቸው መሰረታዊ የሰው ልጅ መብቶች ናቸው። በእነዚህ ህጎች መሰረት ደግሞ እንደ መኖ ኣልባሳት እና መጠለያ የመሳሰሉ የሰው ልጅ መሰረታዊ ፍላጎቶችን ጨምሮ ዜጎች እንደ ህክምና እና ትምህርት የመሳሰሉ ማህበራዊ ፍላጎቶችን ሁሉ የማግኘት መብት ኣላቸው።
እናም ጥቂት ለማይባሉ ዓመታት እንዲያውም ዓስርተ ዓመታት ማለት ይቻላል በረኃብ አለንጋ ከሚገረፈው የኢትዮጵያ ህዝብ አንጻር ለምን የሚል ጥያቄ ቢቀርብላቸው እንደ ምክኒያት አዲሶቹ መንግስታት በቀድሞዎቹ ላይ እያላከኩም ቢሆን መልሳቸው ግን ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት ይቻላል። ድህነት። በእርግጥ የፖሊሲ ችግሮች ሳይዘነጉ ከድህነት ወለል በታች በምትገኘው ኢትዮጵያ ኣምኖ ለመቀበል ማስቸገሩ ባይቀርም ኣይደለም ብሎ ለመከራከር ግን ሊከብድ ይችላል።
ሌሎች በርካታ የግል እና የቡድን መብቶች በገኃድ ሲጨፈለቁ እና በዚሁ ምክኒያት ሰዎች ሲታሰሩ ሲሰቃዩ እና ሲገደሉ ግን የሂዩማን ራይትስ ዎች የበላይ ኃላፊዎች እንደሚሉት በየኣጋጣሚዊ ከየኣቅጣጫው በተለያየ መልኩ ተቃውሞ እና ውግዘት ተለይቶት ኣያውቅም። ለዚህ ግን ባለስልጣናቱ ኣንድም እንደተለመደው ከጥያቄ መራቅ እና ኣሊያም ከእውነት የራቀ የፈጠራ ወሬ እያሉ ከመካድ ያለፈ ምላሽ የላቸውም የሚለው ሂዩማን ራይትስ ዎች ባሳለፍነው ሳምንት ማገባደጃ ላይም የኢትዮጵያን የሰብዓዊ መብት ይዞታ የሚያብጠለጥል አዲስ ሪፖርት ኣውጥተዋል።
ARCHIV - Ein Häftling in Guantanamo in Fußschellen. (am 27.04.2010von der US-Armee herausgegebenes Archivfoto). Seit zehn Jahren halten die USA Terrorverdächtige auf ihrem Marinestützpunkt Guantánamo Bay in Kuba fest. Nach den Anschlägen vom 11. September 2001 hatte US-Präsident George W. Bush dort die Errichtung eines Internierungslagers angeordnet. Sein Nachfolger Barack Obama beschloss zwei Tage nach seinem Amtsantritt im Januar 2009, das Camp binnen Jahresfrist zu schließen. Es war zum Symbol für Folter und Willkür geworden. Aus Obamas Versprechen wurde nichts. EPA/Michelle Shephard / POOL POOL PHOTO. EDS: IMAGE REVIEWED BY U.S. DEPARTMENT OF DEFENSE OFFICIAL PRIOR TO TRANSMISSION. (zu dpa-Themenpaket Guantanamo) +++(c) dpa - Bildfunk+++
በዚሁ ባለፈው ዓርብ ይፋ በሆነው እና 70 ያህል ገጾች ባሉት የሂዩማን ራይትስ ዎች ዘገባ መሰረት በኢትዮጵያ እስር ቤቶች በተለይም አዲስ ኣበባ በሚገኘው እና ማዕከላዊ ተብሎ በሚታወቀው የፌደራሉ የምርመራ ማዕከል በሚገኙ እስረኞች ላይ ይፈጸማሉ የተባሉ ሰቆቃዎችን ለማጋለጥ ተሞክረዋል። ከሁሉም በላይ በሪፖርቱ መሰረት የፖለቲካ እስረኞች ግርፋት ወይንም ቶርችን ጨምሮ ፈታኝ በሆነ ኣያያዝ እየተሰቃዩ መረጃ እንዲአጡ ይደረጋሉ። የሐሰት ሰነድም እንዲፈርሙ ይገደዳሉ ተብለዋል። ይኸው መረጃ ኣንዳንዴ እስረኞቹ ተከሰው ችሎት በሚቀርቡበት ሳዓት እንደ ማስረጃ እንዲቀርብባቸው የሚደረግበት ኣጋጣሚም እንዳለ ተወስተዋል።
35 የቀድሞ እስረኞችን እና ቤተሰቦቻቸውን ዋቢ በማድረግ ሪፖርቱ እንደገለጸው በዚሁ በማዕከላዊ የምርመራ ማዕከል እስረኞች በጥፊ በእርግጫ በጠመንጃ ሰደፍ በዱላ እና በተለያዩ ነገሮች መደብደባቸውን ለሆዩማን ራይትስ ዎች ኣስረድተዋል። ኣንድ ከኦሮሚያ የተያዘ የኦሮሞ ተማሪም ለወራት እጆቹን በካቴና እና እግሮቹን በእግር ብረት ታስሮ ለምግብም ሆነ ለመጸዳዳት በእስረኞች እርዳታ ብቻ መክረሙን በምሬት ያስታውሳል ሲል ሂዩማን ራይትስ ዎች ዘግበዋል።
በሂዩማን ራይትስ ዎች የኣፍሪካ ጉዳዮች ም/ዳይሬክተር የሆኑት ሚ/ስ ሊስሌ ሌፍኮቭ እንደሚሉት ደግሞ የማዕከላዊው እስር ቤት በእሳቸው ኣባባል ማጎሪያ ቤት የተለመዱ ሶስት ክፍለ ማጎሪያዎች ኣሉት። ኣንደኛው ሰዎች ያለ መብራት ተነጥለው ለብቻ የሚታሰሩበት እና ጭለማ ቤት የሚባለው ነው። ሁለተኛው ለግርፋት የተመቻቸው እና በእስረኞቹ ኣጠራር ጣውላ ቤት የሚባለው ሲሆን ሶስተኛው ደግሞ በኣንጻራዊነትም ቢሆን የተሻለ እና እስረኞች እየተንቀሳቀሱ በጋራ የሚታሰሩበት እና ከዚሁ የተነሳ ሸራተን ተብሎ የሚታወቀው ነው።
ሌላው ኣስቸጋሪ ጉዳይ በሪፖርቱ እንደተጠቀሰው እስረኞች ከዘመዶቻቸውም ሆነ ከጠበቆቻቸው እንዳይገናኙ መደረጉ ነው። ምክኒያቶቹ ደግሞ ሚ/ስ ሌፍኮቭ እንደሚሉት እስረኞችን ኣስፈራርቶ ኣሰቃይቶ እና ኣደናግሮ መረጃ ለማወጣጣት እና ቢያንስ ጉልህ የሆኑ የግርፋት ኣሻራዎች እንዳይታዩ ለማድረግም ጭምር ነው።
በኢትዮጵያ ያለው የሰብዓዊ መብት ይዞታ ይበልጥ እየተበላሸ የመጣው የተጭበረበረውን የ2005ቱን ምርጫ ተከትሎ ሲሆን ከ2010 ዓ ም ወዲህ በተለይ ህወኃት መራሹ የኢትዮጵያ መንግስት የሚያካህደው የመብት ጥሰት ህገ ወጥ ብቻም ሳይሆን ሰብዓዊነትም የጎደለው መሆኑን የሂዩማን ራይትስ ዎች ዘገባ ኣመልክተዋል።
የጸረ ሽብር ህግ የተባለው የኢትዮጵያ ህግም ይላል ሪፖርቱ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ተቃዋሚዎችን ለማፈን ሰላማዊ እንቅስቃሴዎችን ለማሽመድመድ የኃይማኖትም ሆነ የብሔር ተቐማት ኃላፊዎችን ለማሰር እና በኣጠቃላይ ሰብዓዊ መብትን ለመጣስ የሚጠቀሙበት ተጨማሪ መሳሪያ ሆነዋል።
ከኢቲኂጵያ መንግስት በኩል የጠ/ሚ/ሩ ቃል ኣቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ ግን የተባለው ሁሉ ከዕውነት የራቀ እና የተለመደ የሂዩማን ራይትስ ዎች ተራ ድራማ ነው ሲሉ ኣጣጥለውታል።
መንግስታዊው የኢትዮጵያ ሰብኣዊ መብት ኮሚሺን ሊቀመንበር ኣንባሳደር ጥሩነህ ዜናም ከአቶ ጌታቸው ረዳ ጋር በተቀራረበ መልኩ የሂዩማን ራይትስ ዎች ዘገባን ደካማ ሪፖርት ብለውታል።
የቀድሞው የሰብዓዊ መብት ጉባዔ ሰመጉ ዳይሬክተር አቶ እንዳልካቸው ሞላ ግን በዚህ ኣይስማሙም። እንደ አቶ እንዳልካቸው እምነት የሂዩማን ራይትስ ዎች ዘገባ ትክክለኛ እና ተጨባጭ ሪፖርት ነው።
በኢትዮጵያ እስር ቤቶች የቶርች ሰለባ ከሆኑት መካከል ደግሞ አቶ ሁሴን ኣህመድ በኢትዮጵያ እስረኖች ላይ ቶርች ስለመካሄዱ ኣንድ እና ሁለት የለውም ይላሉ። በኣሁኑ ጊዜ በኖርዌይ ኣገር የሚኖሩት አቶ ሁሴን ከደረሰባቸው ድብደባ የተነሳ አካላዊ እና አእምሮኣዊ ጉዳት እንደ ደረሰባቸው ይናገራሉ። ከዚሁ የተነሳ ያለ ድጋፍ መንቀሳቀስ እንደማይችሉም ኣስረድተዋል። አቶ ሁሴን ኣህመድ ይህንኑ ለዓለም ህብረተሰብ ለማሳወቅ ከዓለም ዓቀፉ የጸረ ቶርች ኮሚቴ ጋርም እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ ይታወቃል።
ጃፈር ዓሊ
ሂሩት መለሰ
source DW.DE Amharic 

ተገዥነታችን ለሕዝብና ለሕግ እንጅ ለአምባገነኖች ማስፈራሪያ አይደለም!!!

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ(አንድነት) የተሰጠ መግለጫ
        ፓርቲያችን አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በሰላማዊና ሕጋዊ መንገድ ተመዝግቦ በሀገራችን ላይ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲሰፍንና ፍትሃዊነት እንዲኖር በቁርጠኝነት እየታገለ ይገኛል፡፡ በትግሉ ውስጥም ፓርቲያችን የተጋረጡበትን ፈተናዎች እየተወጣና የሚከፈለውን ዋጋ እየከፈለ ሰላማዊ ትግሉን አጠናክሮ በመቀጠል ለህዝቡ ያለውን ታማኝነት እያረጋገጠም ነው፡፡
        ፓርቲያችን በመላ ኢትዮጵያ ያለውን አደረጃጀት በመጠቀምና ሕዝቡን በማሳተፍ ለሶስት ወራት የሚቆይ ህዝባዊ ንቅናቄ በማካሄድ የመጀመሪያ ዙር የሆነውን ሰላማዊ ትግል ለማጠናቀቅ ችሏል፡፡ የሚልዮኖች ድምጽ ለነፃነት በሚል መሪ ቃል የተጀመረው ይህ ህዝባዊ ንቅናቄ አራት መሰረታዊ ጥያቄዎችንና ወቅታዊ ጉዳዮችን ያነገበ ሲሆን እንደ ሁልጊዜውም ፓርቲው ሰላማዊነቱን በጠበቀ መልኩ በቁርጠኝነት ንቅናቄውን በታቀደለት መሰረት አካሂዷል፡፡ ወደፊትም ይህንን አጠናክረን የምንቀጥል መሆኑን ለማረጋገጥ እንወዳለን፡፡
      ኢህአዴግና መሪዎቹ መንግስት እንደመሆናቸው መጠን በሰላማዊ መንገድ ለምንንቀሳቀስ ፓርቲዎች ድጋፍና ትብብር ማድረግ ሃላፊነታቸው ቢሆንም ከዚህ በተቃራኒ በሰላማዊ መንገድ እየተንቀሳቀስን ያለን ፓርቲዎችን ለማጥፋት ቀን ከሌሊት እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ ልክ ከዚህ በፊት ሲያደርጉት እንደነበረው ባልዋልንበት ዋሉ፣ ባልተገኘንበት ተገኙ… በማለት ህዝባዊ መሰረታችን ጥርጣሬ ላይ እንዲወድቅ ለማድረግ ያገኙትን አጋጣሚ ሁሉ ይጠቀማሉ፡፡ ለዚህ አባባላችን ጥሩ ማስረጃ የሚሆነን ባለፈው ሳምንት ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በመሪ ደረጃ በማይጠበቅ መልኩ ህጋዊና ሰላማዊ እንቅስቃሴችንን እሳቸው ከፈለጉት አካል ጋር በማገናኘት ስም ለማጥፋት መሞከራቸው ነው፡፡
    አቶ ኃይለማርያምም ሆኑ መንግስት የሆነው ፓርቲያቸው ለሚነሱ ሀገራዊ ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ ከመስጠትና በተነሱ ጉዳዮች ዙሪያ ለመነጋገር በርን ከመክፈት ይልቅ ዙሪያ ጥምጥም በመሄድ ለጥያቄ አቅራቢዎች የተለየ መልክ ለመፍጠር የሚያደርጉት ጥረት የምናውቀውና የነበረ አሮጌ መንገድ ነው፡፡
     ፓርቲያችን ህዝባዊ ንቅናቄ ያደረገው ህጋዊ አግባቡን ጠብቆና የራሱን አጀንዳ ቀርፆ ነው፡፡ ጠ/ሚንስትሩ የራሳቸው አጀንዳ የላቸውም፤ የሻዕቢያ መልክት አድራሾች ናቸው ወዘተ ያሉበት ድፍረት የራሳችን አጀንዳ እንዳለን ጠፍቷቸው ሳይሆን ሆን ብለውና አቅደው ስም ለማጥፋት፣ ህዝቡ ውስጥ ጥርጣሬ ለመጫር በመፈለጋቸው ብቻ ነው፡፡ እኛ ተላላኪነታችን ለኢትዮጵያ ህዝብና ይጠቅማል ብለን ለቀረፅነው የፖለቲካ ፕሮግራም ብቻ ነው፡፡ እንደዚህ አይነቱን ስም ማጉደፍም ፓርቲያችን በቸልታ አይመለከተውም፡፡ ስለዚህ አቶ ኃይለማርያም ከባለፈው ስህተታቸው በመማር ከአጉልና ማስረጃ አልባ ፍረጃ እንዲላቀቁ አጥብቀን እንመክራለን፡፡
      የሙስሊም ወገኖችን ጥያቄ በተመለከተ ፓርቲችን ያለው አቋም ግልፅ ሲሆን አሁንም ጥያቄያችው በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ መመለስ፤ ዜጎች የመብት ጥያቄ ሲያነሱ መፈረጁ ይቁም፤ ካላግባብ የሃማኖት ነፃነት ጥያቄ ስላነሱ ወደ እስር ቤት የተወረወሩ ዜጎች ባስቸኳይ ይፈቱ የሚል ነው፡፡ በተጨማሪም ስርዓቱ ካላግባብ ያሰራቸው ጋዜጠኞችና የፖለቲካ እስረኞች ባስቸኳይ ይፈቱ ብለን እንጠይቃለን፡፡ ወደፊትም ይህንን ጥቄያችንን አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡ እኛ እያልን ያለነው ከኢ-ፍትሃዊነት ጋር አንደራደርም፤ አንቀበለውም ነው፡፡ ስለዚህ ፓቲያችንን ከሙስሊም ወገኖች ጥያቄ ጋር በማያያዝ ትርፍ ፍለጋ መሯሯጥ ስህተት ብቻ ሳይሆን ወንጀልም ነው፡፡
      አቶ ኃይለማርያም በህገ መንግስቱ በግልጽ የተቀመጡ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ፣ የመሰብሰብና አቤቱታ የማቅረብ መብትን በአደባባይ የጨፈለቀው ንግግራቸው ሰላማዊ ሰልፍን በተመለከተ ነው፡፡ በቂ ጥበቃ የለንም በሚል ተልካሻ ሰበብ የዜጎችን መብት መንጠቅ አይቻልም፡፡ በቂ ጥበቃ ማድረግ ያልቻለ መንግስት ስልጣኑን ለህዝብ በማስረከብ ይቅርታ ጠይቆ መሄድ እንጅ ከአሁን በኋላ መብታችሁን አታገኟትም በማለት መዛት ትዝብት ውስጥ የሚጥል ድርጊት ነው፡፡
        ስለዚህ ፓርቲያችን አንድነት አሁንም ተገዥነቱን ለህዝቡና ለህግ አድርጎ በአምባገነኖች ዛቻ ሳይበረግግ፤ ዘር፣ ፆታ፣ ሀይማኖት፣ ቀለም ሳይለይ ዜጎች የሚያነሱት ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎች እንዲመለሱ፤ የመንግስት በሐይማኖት ጣልቃ ገብነትም እንዲቆም ትግሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ያረጋግጣል፡፡
      ከዚህ በተጨማሪም ፓርቲያችን የአፍሪካ መሪዎች ብዙ መፍትሄ ፈላጊ ችግሮች ባሉባት አፍሪካ ተሰብስበው እንግደል፣ እንሰር፣ እንጨፍጭፍ፣ ዘር እናጥፋ፣ ዜጎቻችንን እናሰቃይ ግን መታሰርም መከሰስም የለብንም በሚል የያዙት አቋም አሳፋሪና ተቀባይነት የሌለው ነው፡፡ ሕግ እየጣሱ በህግ አለመጠየቅ አይቻልም፡፡ ዘር እያጠፉ ያለመታሰር መብት አይኖርም፡፡ ማንም ሰው ከህግ በላይ የመሆን መብት የለውም፡፡
    የአፍሪካ መሪዎች ተሰብስበው ማለት ያለባቸው አይሲሲ ሊከስሰን አይገባም ሳይሆን የዜጎቻቸውን እንባ ማበስ ነው፡፡ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች እንዲረጋገጡ መጣር ነው፡፡ መሳሪያና ጉልበት የችግሮች መፍቻ መሆናቸው እንዲያበቃ የሰለጠነ መንገድ መከተል ነው፡፡ የሚያስከስሳቸውና የሚያሳስራቸው ስራቸው እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ ስለዚህ ፓርቲያችን አሁንም ሆነ ወደፊት በዜጎቻቸው ላይ ግፍና ሰቆቃ የሚፈፅሙ ሁሉ ሳይውል ሳያድር ወደ ፍርድ መቅረብ አለባቸው ብሎ ያምናል፡፡ አንዳንድ የአፍሪካ መሪዎች አይሲሲን በተመለከተ የሚያራምዱት የአትክሰሱን አቋም ፓርቲያችን አይቀበለውም፡፡
ዘላለማዊ ክብር ለኢትዮጵያ!!!
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
                                              ነሐሴ 11 ቀን 2005 ዓ.ም
                                             አዲስ አበባ      
 ምንጭ ዘ-ሐበሻ