Tuesday, August 13, 2013

17-year-old Ethiopian housemaid attacked her employer after a phone call: Police


MAKKAH — A 17-year-old Ethiopian housemaid who stabbed her employer several times in Makkah called her home country just before the attack last week, a local police station told Okaz/Saudi Gazette. The victim was stabbed in the hands, neck, chest, and shoulders but survived, sources at Al-Aziziya police station revealed. According to police initial investigations, the maid had worked for a year with her employer, a 40-year-old widow, before she decided to try and kill her. The maid told police the widow treated her well and never did anything wrong to her. Toward the end of Ramadan, she went with her employers to buy Eid groceries. Her employer bought her a calling card to talk to her family in Ethiopia and wish them happy Eid.
A few hours following the phone call, just before Fajr prayer, the maid jumped on her victim as she was leaving the bathroom. The first thing the maid did was hit the widow on her head and then started stabbing her in her hands, chest, and face. Somehow, the victim got away and locked herself in her room before calling her brother, who contacted her neighbors. The maid kept trying to force her way into the room to get to the widow, who was screaming and shouting while blood gushed out from her wounds. The neighbors called Civil Defense officers, who broke the apartment door open and helped the widow. The widow is currently being treated at Al-Noor Specialist Hospital, where she received over 50 stitches.
http://www.saudigazette.com.sa

250 ሺህ ዜጎች በግጭት በኦሮሚያና አማራ ክልሎች ተፈናቀሉ

ነሃሴ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተባበሩት አለም አቀፍ የምግብ ድርጅት በኦሮሚያና አማራ ክልሎች በተለያዩ ግጭቶችና አደጋዎች ጉዳት ለደረሰባቸው 250 ሺህ ዜጎች አስቸኳይ እርዳታ መስጠት መጀመሩን ለኢሳት በላከው መግለጫ አስታወቀ፡፡
ድርጅቱ በኦሮሚያና አማራ ደርሶ ስለነበረው ግጭት ዝርዝር መረጃን ከመስጠት ቢቆጠብም 250ሺህ ለሆኑት ዜጎች ግን ጊዜያዊ የሆነ የምግብና የገንዘብ እርዳታ መስጠት ላይ እንደሆነ ገልጿል፡፡             ከአውሮፓ ህብረት ሰብዓዊ እና ሲቪል ዜጎችን መከላከል ተቋም በተገኘ እርዳታ ጊዜያዊው እርዳታ እየተሰጠ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል፡፡  የተባበሩት የአለም የምግብ ድርጅት (ፋኦ) የኢትዮጵያ ተወካይ የሆኑት አብዱ ዲያንግ ተጎጂ ዜጎቹ በአሁኑ ሰዓት እንደሚኖሩበት አካባቢ የገበያ ሁኔታ በነፍስ ወከፍ በወር 150 ብር ድጋፍ እየተደረገላቸው እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
የአውሮፓ ህብረት ሰብዓዊና ሲቪል ዜጎችን መከላከል ተቋም ዜጎቹን በጊዜያዊነት ለመርዳት ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉ ታውቋል፡፡ በኦሮሚያና አማራ ክልል በተለያዩ ጊዜያት ዜጎች መብታቸውን ለመጠየቅ ባደረጉት እንቅስቃሴ በደረሰባቸው የመንግስት እርምጃ በርካቶች መፈናቀላቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡
በተያያዘ ዜና የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን ባለፉት ሁለት ዓመታት ከኢትዮጵያ ወደ የመን የሚሰደዱ ዜጎች ቁጥር መንግስት አልባ ተደርጋ ከምትቆጠረው ሶማሊያ በመብለጥ አዲስ ሪከርድ ማስመዝገቡን ሰሞኑን ይፋ ባደረገው ሪፖርት አስታውቋል፡፡
ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ 38 ሺህ 824 ኢትዮጵያን (ማለት ከጠቅላላው 84 ፐርሰንት) የሆኑ ዜጎች መሰደዳቸውን ገልጿል፡፡ በተመሳሳይ ወቅት 7ሺህ 559 ሶማሌያን እና 17 ኤርትራውያን ብቻ ወደ የመን መግባታቸውን ባወጣው መረጃ አስታውቋል፡፡
በየመን ከደረሱት ኢትዮጵያውያን ውስጥ በጣም ጥቂት የሆኑት ብቻ ጥገኝነት መጠየቃቸውን ያስታወቀው ድርጅቱ የተቀሩት ግን በመረጃ እጦትና የተለያዩ ችግሮች ለችግር መጋለጣቸውን አስታውቋል፡፡ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ድርጅት ባለፉት ስድስት ወራት 46 ሺህ ስደተኞች ወደ የመን አስቸጋሪ ጉዞ አድርገው መግባታቸውን ገልጾ ከነዚህ ውስጥ 38ሺህ 824ቱ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን አስታውቋል፡፡
ከፈረንጆቹ 2006 ዓ.ም. ጀምሮ ወደ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጉ የተለያዩ ሀገራት ስደተኞች ወደ የመን መሰደዳቸውን የገለጸው ድርጅቱ አብዛኛዎቹ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ገልጿል፡፡ ቀይ ባህርን በአነስተኛ ጀልባዎች በመጠቀም ወደ የመን የሚሰደዱ ኢትዮጵያውያን ቁጥር በዓመት ወደ 80 ሺህ እንደሚጠጋ ሰሞኑን ቢቢሲ ለአለም ባሰራጨው ዶክመንተሪ ፊልም መታየቱ ይታወሳል፡፡
ከሚሰደዱት ሴቶች አብዛኛዎቹ የመደፈር አደጋ የሚደርስባቸው ሲሆን በርካታ ዜጎችም በቀይ ባህር ላይ በመስመጥ መሞታቸው በተደጋጋሚ ሲነገር ቆይቷል፡፡

Sunday, August 11, 2013

Arabsat has stopped broadcasting ETV in a clear act of police hostility against Ethiopians

EMF – Arabsat took Ethiopian’s propaganda machine ETV off air on Friday next day after Ethiopian Federal Police brutal act against Ethiopian Muslims.
Ethiopian activists reached out to Arabsat and asked ETV to be removed fromplatform, alleging ETV broadcasting hatred and false accusation against oppositions and Ethiopian Muslims. Source told to EMF, Arabsat askedEthiopian government to give reasonable explanation why Police brutally attacked peaceful Ethiopians in Addis Ababa and other cities of the country.  According to EMF source, Arabsat will shut down Ethiopian TV signals until it gets reasonable explanation from Ethiopian Government.
TheCostofViolence
Ethiopia has been a land of absolute military dictatorship before and after the death of the late Meles Zenawi. It is believed that the current Ethiopian prime minister, Hailemariam Desalegn has no-say on actions taken by the military and security forces.
The move by Arabsat will give the opportunity to ESAT and other Ethiopian Media to gain control of covering events unfolding in Ethiopia. Ethiopian opposition Media accused the current Ethiopian regime for the killing of hundreds and violation of Human Rights in the country.
Following Thursday’s violation, Amnesty International released a statement calling on the Ethiopian government to end “repressive tactics against demonstrators”.
Recently, Arabsat stopped the broadcasting Syrian, Libya and other dictatorial regime, government Television channels including Press TV.
source (Ethiopian mrdia forum)

Saturday, August 10, 2013

መንግስት ህዝቡን ማስፈራራቱን ቀጥሎበታል!!

በዛሬው ጁምዓ በአንዋር መስጂድ ምንም አይነት ተቃውሞ እንደማይደረግ ይታወቃል፡፡ ነገር ግን ከጁምዓ ሰላት በፊት በርካታ የፖሊስ መኪኖች በአንዋር መስጂድ ዙሪያ ከነሙሉ ትጥቃቸው ሲዟዟሩ የነበረ ሲሆን፤ የተወሰኑት መኪኖች ደግሞ በርካታ አስለቃሽ ጭስ የያዙ አድማ በታኞችንና የፌደራል ፖሊሶችን በአካባቢው እንዳራገፉ የ”ፈስቢር” ሪፖርተር ዘግቧል፡፡
አንዋር መስጂድ የጁምዓን ሰላት ለመስገድ ይገቡ የነበሩ የተወሰኑ ሙስሊሞችም፤ ፖሊሶችን አስለቃሽ ጭስ ይዘው ሲያዩና፤ በብዛት በአካባቢው ሰፍረው ሲመለከቱ፤ መንግስት ህዝቡን ለመተንኮስ አስቦ እንደሆነ ስለገባቸው፤ እድሉን ለመንፈግ ብለው፤ ከአንዋር መስጂድ በመውጣት ወደ ሌሎች መስጂዶች ሄደው ጁምዓን መስገዳቸውንም ለማወቅ ችለናል፡፡
የዚህ ጽሁፍ አቅራቢ በዘገባቸው መጨሬሻ ላይ እንዳሉት ከሆነ፤ “እኛ ሙስሊሞች ተቃውሞ ማድረግ ካለብን ፖሊሶች በጭራሽ ሊገቱን አይችሉም፡፡ እኛ በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞ ማድረግ ባለብን ቀናት ሁሉ እናደርጋለን፡፡ ነገር ግን ሰላማዊ ህዝብን በመግድል፤ በመደብደብና በማሰር ጥያቄውን አስቀራለሁ ብሎ መንግስት ካሰበ ወላሂ ተሳስቷል፡፡ ሙስሊሙን ለማስፈራራት በየመስጂዱ የሚያደርገው የጦር መሳሪያና የፌደራል ፖሊሶች ሾው (show) እኛን በጭራሽ ወደ ኋላ እንድንል አያደርገንም! ድል ምንግዜም ለእውነተኞች ነው!” ብለዋል።
ምንጭ(የኢትዮጵያ ሜዲያ መድረክ)

Friday, August 9, 2013

ሙስሊም ወገኖቻችን፤ ቁስላችሁን አስራችሁ ከወያኔ ጋር በምናደርገው ፍልሚያ ተቀላቀሉን!!!!

ሙስሊም ወገኖቻችን፤ ቁስላችሁን አስራችሁ ከወያኔ ጋር በምናደርገው ፍልሚያ ተቀላቀሉን!!!!

ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ መግለጫ
ነሐሴ 3 2005 ዓ.ም.
በእስልምና እምነት እጅግ በደማቅ ሁኔታ ከሚከበሩት በዓላት አንዱ የሆነው ኢድ አልፈጥር ለ1434ኛ ጊዜ ነሐሴ 2 ቀን 2005 ዓ. ም. በመላው ዓለም በደስታ ሲከበር ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ግን ለዚህ አልታደሉም። በእለቱ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የኢድ ሰላታቸውን ሰግደው ወደ የመኖሪያ ቤቶቻቸው ሲመለሱ ለድብደባ በሠለጠኑ የወያኔ ወታደሮች አሰቃቂ ሰቆቃ ተፈጽሞባቸዋል። በዚህ እለት በአዲስ አበባና እና ሌሎች ትላልቅና ትናንሽ ከተሞች በርካታ ወገኖቻችን ሕይወታቸውን አጥተዋል፤ አሁን ሕፃናት የወያኔ የጥይት ሰለባ ሆነዋል፤ ከዚያ እጅግ አሰቃቂ ግድያና ወከባ ያመለጡት ደግሞ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል። በአስር ሺዎች የሚገመቱ ሙስሊሞች በዓሉን ያሳለፉት በወያኔ ማጎሪያዎች ውስጥ በሕመምና በረሀብ እየተሰቃዩ ነው።
ይህ ለምን ሆነ?
የኢትዮጵያ ሙስሊሞች በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት ጥንቃቄ የተሞላበት ተቃውሞ ሲያካሄዱ አንድ ዓመት አልፏቸዋል። እጅግ ጨዋ በሆነ መንገድ ላቀረቡት የመብት ጥያቄ በታላቁ በዓል ቀን ወያኔ የእንቢታ ምላሹን ወራዳ በሆነ መንገድ ሰጥቷል። ወያኔ ለሰላማዊ ተቃዉሞ ያለውን ንቀት እናቶችን፣ ሕፃናትንና አረጋዊያንን ጭምር በመደብደብ አሳይቶናል።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ሕይወታቸው ላለፈ ወገኖቻችን ቤተሰቦች መጽናናትን ይመኛል፤ የአካል ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖቻችን ሕመም ይጋራል። በባለጌ የወያኔ ወታደሮች የተገደለየ፣ የተረገጡ፣ በቆመጥ የተደበደቡ፣ የተሰደቡ፣ የተተፋባቸው ወገኖቻችን ሁሉ ሕመማቸውን ችለው፤ እልሃቸውን ውጠው ለመረረ ትግል እንዲዘጋጁ ግንቦት 7 ጥሪ ያደርጋል።
በሙስሊም ወገኖቻችን ላይ የደረሰው በደል በሁላችን ላይ የደረሰ ጥቃት፣ በደል ነው። የሙስሊም ወገኖቻችን የመብት ጥያቄ የኢትዮጵያዊያን ተበዳዮች ሁሉ ጥያቄ ነው። እነዚህ ጥያቄዎች በወያኔ አገዛዝ ሥር ምላሽ አያገኙም። ስለሆነም ተባብረን ኢትዮጵያችንን ከወያኔ ፋሽስታዊ አገዛዝ ነፃ አውጥተን ሁላችንም የነፃነት አየር የምንተነፍስባት አገር እናድርጋት ዘንድ ዛሬውኑ የጋራ የትግል ጉዞ እንጀምር።
“ሙስሊም ወገኖቻችን ሆይ! እልሃችሁን ውጣችሁ፤ ቁስላችሁን አስራችሁ ከወያኔ ጋር ለሚደረግ ፍልሚያ ተቀላቀሉን!!!” በማለት ግንቦት 7፣ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ጥሪ ያደርጋል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ
www.ginbot7.org                  pr@ginbot7.org      |      +44 208 133 5670

የእስክንድር ነጋ ባለቤት የሰርካለም ፋሲል የመጨረሻ ቃል – “የልጄ አዕምሮ እንዳይጎዳ ከሃገር መውጣትን መርጫለሁ”

ሀምሌ16/2005 ዓ.ም. በጣም መጥፎና ጥሩ ስሜት የማይፈጥር ቀን ነበር፡፡ ቤተሰብን፣ ወዳጅ ዘመድን በተለይ የሚወዷትን ሃገር ጥሎ መውጣት ምንኛ ይከብዳል? ከሀገርስ በላይ ምን አለ? አፈር ፈጭቼ ካቦካሁባት፣ ተወልጄ ካደግኩባት፣ ክፉ ደጉን ካየሁባት አገሬ የመውጣቴ የመጨረሻ ቀን መቃረቡን ሳስብ በሕይወቴ አጋጥሞኝ የማያውቅ የመደበት ስሜት ውስጥ ነው የተዘፈቅኩት፡፡ ከቤተሰብ፣ ከጐረቤት፣ ከወዳጅ ዘመድ የመለያየት መቃረቢያው ክፉኛ ያሳምማል፡፡ ከምንም በላይ በሀገር መኖር ክብር መሆኑን እረዳለሁ፡፡ ከሚወዷት ሃገር ተገፍቶ እና ተገፍትሮ መውጣት ከመርግ የከበደ መሆኑን አሁን መጨረሻው ላይ የግዴን አወቅኩት፡፡ በቅርብ የሚያውቁኝ “ሰርካለም ከምትንሰፈሰፍላት ውድ ሀገሯ ወጥታ ለመኖር እንዴት ጨከነች?” እንደሚሉ እገምታለሁ፡፡ ሀገሬን እጅግ እወዳታለሁና “እንደወጣሁ እቀራለሁ” የሚል ድምዳሜ ላይ አልደረስኩም፡፡ ደሕንነቴ አደጋ ውስጥ ሲወድቅ፣ ውክቢያና እንግልቱ ሲከፋብኝ ግን ለራሴ ብቻ ሳይሆን በአባቱ እስራት ለሚንገላታው ልጄ ስል ይሕን መወሰኔ ግድ ሆነብኝ፡፡ ቤተሰብ ያለው ሰው የሚሰማው የተለየ ስሜት ይኖራል፡፡ ለኔ ሕይወት የራሷ የሆነች ስም ካላወጣችለት በቀር ከመደበኛው የተለየች ሆናብኛለች ማለት እደፍራለሁ፡፡ ሁሌም በውክቢያና እስር፣ በማጠስጠንቀቂያና ማስፈራሪያ ሥር ሆኖ መኖር በእጅጉ ያስመርራል፡፡ የኔ ሕይወት ይሄ ነው፡፡ ባለቤቴ እስክንድር ነጋ ለእስር ከተዳረገ ዓመቱን ሊደፍን ከአንድ ወር ያልበለጠ ጊዜ ነው የቀረው፡፡ በእስር ቤት የተወለደው ልጃችን ናፍቆት እስክንድር ነጋ የአባቱ ናፍቆት እያሰቃየው፣ እንደ እኩዮቹ ከመፈንጠዝና ከመቦረቅ ርቆ በትካዜ ውስጥ መኖሩ በእጅጉ ሲያሰቃየኝ ቆየ፡፡ ከዚህ በኋላ በዚህ እየተሰቃየና እየተጎዳ መኖር አይኖርበትም፡፡ በእስር ያጣው ውድ አባቱን በየሳምንቱ እያየው ከሚሰቃይ ከሃገር ርቆ “አንድ ቀን እንገናኛለን” የሚል ተስፋ ውስጥ ቢገባ የተሻለ ሊሆንለት እንደሚችልም አምኛለሁ፡፡ ማንም ወላጅ ይሕን ስሜቴን ይረዳኛል ብዬ እገምታለሁ፡፡ ልጃችን ናፍቆት ዕድሜው ከሚችለው በላይ መከራ በመቀበል ከማናችንም በላይ ተጐድቷል፡፡ በትምሕርት ቤት ከአቻ ጓደኞቹ ጋር መጫወት ትቶ ብቻውን አቀርቅሮ መሬት ሲጭር ይውላል፡፡ “አባቴ መቼ ነው የሚመጣው?” ከሚለው የመናፈቅ ጥያቄው ጋር እየታገለ ትምሕርቱን መከታተል የማይችልበት ደረጃ ላይ ደረሰ፡፡ ሞራሉ እየወደቀ ሲሄድ ያየሁ መሰለኝ፡፡ የወለድኩት ቃሊቲ ወሕኒ ቤት ስለሆነ እንደ እናት ተገቢውን እንክብካቤ እንኳን አላደረግኩለትም፡፡ ከሰው ተነጥዬ የምችለውን ላደርግለት የሞከርኩ ቢሆንም አንድ ሕፃን ሊደረግለት ከሚገባው በትንሹ እንኳን ሊያገኝ አልቻለም፡፡ ልጄ ባህሪው በእጅጉ ተለወጠ፤ ከሰው ጋር መግባባት ተቸገረ፤ ዝምታንና ለብቻው መገለልን ምርጫው አደረገ፡፡ ሰው ይፈራል፤ ከእኔ ከእናቱና ከወንድሜ ጋር ብቻ የሚግባባው ናፍቆት ከሌላ ሰው ጋር መግባባት አልሆንለት አለ፡፡ እኛ ተጐድተን… በስነ ልቦና የተጐዳ ልጅ መፍጠር አይኖርብንም፡፡ እኔና ልጄ ከእስር ስንፈታ፣ አባቱ ተመልሶ ወሕኒ ከወረደ በኋላ ደግሞ የልጃችን የባህሪ ለውጥ እየከፋ ሄደ፡፡ እስቲ ለሰከንዶች ብቻ እንደ አንዲት እናት ሆናችሁ አስቡት፡፡ ማንም የወለደው ልጅ ሲጐዳበት ማየት አይፈልግም፡፡ ዘጠኝ ወር አርግዤው በ1998 ዓ.ም. በእስር ቤት የወለድኩት ናፍቆት እስክንድር ነጋ ላለፉት ሠባት ዓመታት የገፋው የሰቆቃ ኑሮ እንዲበቃው መፈለጌ ነው ወደማልፈልገው ስደት እንዳመራ ያስገደደኝ፡፡ የውክቢያ ዘመኑ ያኔም ዛሬም ፈፅሞ አልተቀየረም፡፡ ባለቤቴ እስክንድር ያለ ፍትሕ መታሰሩ፣ እኔና ናፍቆት የምንመራው የሰቆቃ ሕይወት የብዙሃን ግፉአን ኢትዮጵያውያን ሕይወት ግልባጭ ነው፡፡ በጠመንጃ ታጅቤ ፖሊስ ሆስፒታል የወለድኩት፣ የሕፃንነት ጊዜው የቃሊቲ እስር ቤት በር ተዘግቶበት ያሳለፈው የምወደው ልጄ አዕምሮው እንዳይጎዳ ለጊዜው ከስደት የተሻለ አማራጭ አላገኘሁም፡፡
ጉዞ ወደ አሜሪካ የጉዞዬ ዓላማ ኑሮን በአሜሪካ ማድረግ አይደለም፡፡ የአሜሪካን የተንደላቀቀ ኑሮ ብንፈልግ ኖሮ እኔም ሆንኩ ዛሬ እስር ላይ የሚገኘው ባለቤቴ እስክንድር ነጋ ልጃችንን ይዘን ቀድመን ከሀገር በወጣን ነበር፡፡ እስክንድር ለዓመታት አሜሪካ ኖሮ በሃገሩ ሃሳብን የመግለጽ መብት “ኤክሰርሳይስ” ለማድረግ ነው የመጣው፤ እኔም ብሆን አሜሪካ ደርሼ የተመለስኩት ሃገሬን ስለምወድ እንጂ ሌላ ጥቅም ስላለ ነው፡፡ ሁለታችንም ከሃገር የመውጣት ሃሳቡ አልነበረንም፤ ዛሬ የእኔው ግድ ሆነ፡፡ የልጃችን የአእምሮና ስነ ልቦና ጉዳይ በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደረሰ፡፡ ናፍቆት እስክንድር ነጋ ከሰኞ እስከ አርብ በትምሕርት ቤት ሲናውዝ ቆይቶ፣ የቅዳሜና እሁድ የዕረፍት ቀኑን እንደ እኩዮቹ መዝናኛ ቦታ ሣይሆን ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ነው የሚያሣልፈው፡፡ ናፍቆት ለአባቱ ያለው ፍቅር የተለየ ነው፡፡ እስክንድር ዳግም ሲታሰር ልጃችን ናፍቆትን ከትምህርት ቤት እያመጣ እንደነበር ይታወሳል፡፡ መሣሪያ የታጠቁ ፖሊሶች እስክንድርን ሲይዙት፣ ልጃችን ናፍቆት “አባቴን ልቀቁት” እያለ ያለቅስ ነበር፡፡ ይህንን ክስተት እስኪ ለአፍታ መለስ ብላችሁ አስቡት፡፡ እስክንድር ነጋ በሃገሩ የሚኖር ሕጋዊ ሰው፣ ቋሚ አድራሻ ያለውና ፖሊስም ሆነ የደሕንነት ባልደረቦች በፈለጉበት ጊዜ ጠርተው ሊያስሩት እንደሚችሉ ግልጽ ነው፡፡ ልጁን ከትምህርት ቤት ሲያወጣ ጠብቀው በጠመንጃ ከበው፣ እየደነፉ የያዙት እሱንም ሆነ ልጃችንን ለማሳቀቅ እንደሆነ ማንም ሰው ይረዳዋል ብዬ አምናለሁ፡፡ በወቅቱ እስክንድርን የያዙት ሰዎች የልጅ አባት ይሆኑ ይሆናል፡፡ እነርሱ በእስክንድርና በናፍቆት ላይ ያደረሱት ሽብርና ማሸማቀቅ በራሳቸውና በልጆቻቸው ቢፈፀም ምን ሊሰማቸው እንደሚችል ለመገመት ለምን እንደተቸገሩ አይገባኝም፡፡ እናም “ምነዋ! ሰርካለም ከሀገር ወጣች” ብላችሁ ለጠየቃችሁ ምላሼ ይድረሳችሁ፡፡ ወደአሜሪካ የጉብኝት እድሉን ከቅርብ ወዳጃችን ነው ያገኘነው፡፡ ልጄ የተወሰነ ቢሆን ቦታ መቀየር የራሱ የሆነ እገዛ ይኖረዋል ድምዳሜ ላይ በመድረሴ ግብዣውን ተቀበልኩት፡፡ የስማችን መጠሪያ፣ ሃገር ተረካቢው ልጃችን በኛ ዳፋ ሞራሉ ደቆ ሲጐዳ ከማየት እንዲያገግም ስል ይኸው ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ተጉዣለሁ፡፡ (ዘ-ሐበሻ ድረገጽን ሁሌም ያንብቡ)
እስክንድርን ጥሎ መሄድ ባለቤቴ እስክንድር ነጋ እስር ላይ ነው፡፡ የቃሊቲን አታካችና አሰልቺ ጉዞ ተቋቁሞ “ማን ስንቅ ያቀብለዋል?” የሚለው ጥያቄ ውሳኔዬን እንድቀለብስ ሞግቶኝ ነበር፡፡ እሱን ጥሎ መሄድ እጅግ ከባድ ነው፡፡ ለእኔ፣ ላንተ፣ ላንቺ መብት አይደል የታሰረው? እና ለእኔ ሲል ታስሮ እሱን ጥሎ መሄድ እንዴት እደፍራለሁ፡፡ እስክንድር የልጃችንን ጉዳት በመረዳቱ ከሃገር ርቀ ቢቆይ የተሻለ ነገር እንደሚየገኝ ሲያግባባኝ ዓመት አልፎታል፡፡ እስካሁን ሳልቀበለው ቆይቻለሁ፡፡ አሁን ግን እስክንድርም አመረረ፡፡ “ልጃችን ሲጎዳ እምቢኝ ከሃገር አልወጣም ያልሽኝ አንቺ ከእኔ የተሻለ አንፃራዊ ነፃነት ስላለሽ (ስላልታሰርሽ)፣ ነው” የሚለውን ግፊት አጠነከረው፡፡ ቀደም ባሉት ጊዜየት በተደጋጋሚ ወዳጆቻችን የእረፍት ቪዛ ሲልኩልን አሻፈረኝ ብዬ ሳቃጥለው የነበረውን ዕድል ማክተሙን ተረዳሁት፡፡ እስክንድር “እኔ የታሰርኩበት አላማ አለኝ፤ በዚህች ሀገር ፍትህና ዴሞክራሲ እንዲሰፍን አሁንም ትግሌ ይቀጥላል፤ በእስር ቤት የተወለደው ልጄ ግን አዕምሮው ከዚህ በላይ መጐዳት አይኖርበትም፡፡ እና በአፋጣኝ እረፍት እንዲያደርግ ብለሽ ውጡ” ነው ያለኝ፡፡ በሣምንት አራት ቀን የምጠይቀው ባለቤቴን መራቅ ቢከብደኝም በአንድ ነገር ግን ገዘተኝ፡፡ “እስክንድር ቢታሰርም አይሟሟም፤ እኔ ስለፍትህ፣ ነፃነትና ዴሞክራሲ የምናገር እንጂ አሸባሪ አይደለሁም፤ ልጄ ደግሞ በኔ እስር የአባቱን ፍቅር አጥቶ መጨነቅና አእምሮው መጐዳት የለበትም፤ ሲያድግ ጥሩ አእምሮ ኖሮት ሀገሩን እንዲያገለግል ውሳኔዬ ነው” የሚል ድምዳሜ ላይ መድረሱ የጉዞ ውሳኔ ላይ አድርሶኛል፡፡ እናም የእሱን ቃል ማክበር ስላለብኝ ይህን አደረኩ፡፡ ውድ ኢትዮጵያዊያን ወንድሞቼና እህቶቼ እኛ ማለትም ባለቤቴና እኔ ወደ አሜሪካ የምንሄድበት እድል ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ተፈጥሮልን ነበር፡፡ ግን ለምን ሀገራችንን ለቀን አንሄዳለን ብለን ነው የወሰን ነው፡፡ የኔም ሆነ ባለቤቴ አቋም ተመሳሳይ ነው፡፡ በተለይ ባለቤቴ እስክንድር ነጋ ስለዴሞክራሲ ከሀገር ወጥቶ መታገል በሚለው ነገር ላይ ፈፅሞ እምነት የለውም፡፡ ሰላማዊ ትግል በሀገር ውስጥ ማድረግ ነው የሚል እምነት አለው፡፡ ከዛ በመነሣት ነው ብዙ የቆየ ነው፡፡ አሁን ግን የልጃችን አእምሮ እየተጐዳ በመምጣቱ መቼም ወላድ ….ኢትዮጵያዊ ይመስክር የልጅን ነገር የወለደ ያውቀዋልና ለዛም ስንል የተወሰነ እረፍት ቢያገኝ ብለን ወደ አሜሪካ ይዤው ለመሄድ ተገደድኩ፡፡ ይህ ህፃን በእስር ላይ ተወልዶ የቤተሰብ ፍቅር ያልጠገበ ባይተዋር ልጅ ሆነብን፡፡ በሁሉም መጐዳት የለብንም ልጃችን በእኛ ስህተት ሣይሆን እኛ በምናደርገው ትግል ሁሌም መታሰራችን የፈጠረበት የቤተሰብ እንክብካቤ ማነስ ተጐዳ፡፡ አያት ወይም አጐት እንደ ወላጅ ሆኖ ለማሣደግ ይቸገራል፡፡ ለሀገራችን ስንታገል የልጃችን ጭንቅላት ጐዳት እስክንድርንም እኔንም ለውሣኔ አበቃን፡፡ እስክንድር ብቻውን አይደለም መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በቃሊቲ “ዞን 2″ እየሄድ ይጠይቀዋል፡፡
ያለፉት ስድስት አመታት በ1998 ዓ.ም. ታስረን ከእስር ከተፈታን በኋላ ምናልባትም የስድስት አመታት ጊዜያት ተቆጥረዋል፡፡ ለእስክንድር የከበደ ጊዜ ነበር፡፡ የጋዜጣ ፈቃድ አውጥቶ በሞያው ለመንቀሣቀስ ቢፈልግም ፈቃድ የማግኘት እድል ግን ፈፅሞ ማግኘት አልቻለም፡፡ ከዛ በኋላ በፖለቲካዊ ትንታኔዎች ዙሪያ መንቀሣቀስ ጀመረ፡፡ እስክንድር እንደሌሎች ከሀገር እንደወጡ ፖለቲከኞች ውጭ ሆኖ ድምፁን ማሰማት ይችላል፡፡ ግን የእሱ አላማ ህጋዊና ዴሞክራሲያዊ በመሆኑ በሀገር ውስጥ መንቀሣቀስ ጀመረ፡፡ ያ ነገር ግን በጠላትነት አስፈርጆት ሁሌም በክትትል ሕይወት ውስጥ እንዲኖር አደረገው፡፡ እስክንድር ሁሌም “በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ክትትል ስር የወደቀ ነበር” ቤታችን ይጠበቃል፣ እሱም ነፃ ሆኖ መንቀሣቀስ አልቻለም፡፡ እሱን ለመጠየቅ የመጣ፣ ከእሱ ጋር የቆመና የተነጋገር ችግር ይገጥመዋል፡፡ የሰቆቃ ዘመን ነበር ያሣለፈው፡፡ በመጨረሻም ታሰረ፡፡ ዳግም መታሰር ይከብዳል፡፡ እስክንድር ባለፉት 20 አመታት ወይም በኢትዮጵያ ነፃ ፕሬስ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ” የፕሬሱ ፋና ወጊ ነው” ግን በእስር እጁን እስከመሰበር ደርሷል፡፡ ከአሜሪካ ሀገር ድረስ መጥቶ በዚህች ሀገር ላይ ስለዴሞክራሲ ፣ ነፃነትና መብት የሚናገር ማነው እናም እነዚህ ያለፉት ስድስት አመታት እጅግ ውስብስብና አስቸጋሪ የሆኑ ጊዜያት ነበሩ፡፡
የወጣትነት ዘመን እኔ የወጣትነት ዘመን ምን እንደሆነ አላውቅም፡፡ እኔና እስክንድር ስንገናኝ የ21 አመት ወጣት ነበርኩ፡፡ ከዛ ጊዜ ጀምሮ የመዋከብና በዚህ ሕይወት ዙሪያ የመረጋጋት ሕይወት ሣይኖረን ቆይተናል፡፡ ወጣትነት ብዙ ነገር ማለት ነው፡፡ “ፈፅሞ አላውቀውም” ከእድሜ እኩዮቼ ጋር ሆኖ መዝናናት ፣ በእኔ እድሜ ላይ የምትገኝ ወጣት ልታደርግ የሚገባውን ነገር ፈፅሞ አድርጌ አላውቅም፡፡ በእኛ ስር ሦስት ጋዜጦች ነበሩ፡፡ ምኒልክ፣ አስኳልና ሳተናው፡፡ ሦስቱም በሣምንቱ ውስጥ ይወጣሉ፡፡ እነዚህን ማዘጋጀት መምራት ምን ጊዜ ይሰጣል፡፡ ለዛውም የፖለቲካ ጋዜጣ ማዘጋጀት ቀላል ነገር አይደለም፡፡ በዚህ በሦስት ጋዜጣ ስር ደግሞ ምን ያህል ሠራተኞች አሉ፡፡ እናም ወጣትነቴን አላውቀውም፡፡”ወጣትነት ምንም እንደሆነ ስለወጣትነት የተፃፈውን መፅሐፍ ከማንበብ ባለፈ ይህ ነው የሚባል የወጣትነት ትዝታ ፈፅሞ የለኝም፡፡” በበርካታ ውጣ ውረድ ውስጥ ነው ወጣትነቴን ያሣለፍኩት፡፡ ያ አልፏል ብዙም አልቆጭበትም፡፡ ከዚህ በኋላ ወጣት የሚባል ደረጃ ላይ አይደለሁም፡፡ ባለፉት ጊዜያትም የምቆጭ አይደለሁም፡፡ ስለዴሞክራሲ ስሰራ በመኖሬ ደግሞ እኮራለሁ፡፡
የእስክንድር ዳግም እስር ምን ፈጠረ; የእስክንድር ዳግም መታሰር ቤተሰባችን እንዲበተን አድርጓል፡፡ ማንም ኢትዮጵያዊ በሕይወቱ ሊያደርጋቸው ከሚገባቸው ነገሮች መካከል በትዳር ተጥምሮ ወልዶ መኖር ነው፡፡ ይህ ግን ለእኛ የተፈቀደ አይደለም፡፡ እስክንድር ከጥሩ ቤተሰብ የወጣ ጥሩ አቅም ያለው ነው፡፡ የእሱ ቤተሰብ ምንጭ ጥሩ ነጋዴ ሆነን ተንደላቀን እንድንኖር ያደርገናል፡፡ ግን አልሆነም፡፡ የእሱ ቤተሰብ ንብረት ፈፅሞ በሚገርም መልኩ ሽብርተኛ በሚል ተወረሰ፡፡ በመጨረሻም ይኸው ዳኛ ቤተሰብ በተነ፡፡ እስክንድር 18 አመት ተፈረደበት፡፡እኔም ለልጄ ጭንቅላት ስል ለተወሰነ ጊዜም ቢሆን ወዳጅ ዘመድ በፈጠረው እድል ተጠቅሜ ወደ አሜሪካ አመራሁ፡፡ ይገርማችኋል እኛ ሰላማዊ ነን ልጃችን አፍ ፈቶ መናገር ከቻል በኋላ አብረን ለመኖር መታገዳችን ምን ያህል ያስቆጫል፡፡ እስክንድር በኢትዮጵያ ዴሞክራሲና ፍትህ የእውነት ካልሰፈነ በቀር በአደባባይ ቢሰቀልና ቢሰቃይ ቦታ የለውም፡፡ ግን ልጃችን ለምን ይሰቃይ የሚል እምነት አለው፡፡ ማንም ቢሆነ የልጁን ስቃይ ማየት አይወድምና፡፡
የሀገር ነገር ይህንን ስል እንባዬ ምን ያህል በአይኔ ላይ እየወረደ እንደጠረኩት አውቃለሁ፡፡ ያለቀስኩበት ዘመን አልፏል፡፡ …. ሀገሬን እወዳለሁ፡፡ ግን መልካም አስተዳደርን እመኛለሁ፡፡ ከሀገሬ አልርቅም ፣ ወደ ሀገሬም እመለሣለሁ፡፡ እኔና ባለቤቴ ለልጃችን ስንል እንጂ የደረሰብን በርካታ ስቃዮች የጐዳን አይደለም፡፡ እናም ሁሌም ቢሆን ኢትዮጵያን እወዳለሁ፡፡ ከሀገሬ መራቅ የምፈልግ አይደለሁም፡፡ ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር፡፡ እስክንድር ነጋ ሀገሩን የሚወድ አሜሪካ መኖር እየቻለ ስለሀገሩ ሲል ቃሊቲ /ማረሚያ ቤት/ መኖሪያው የሆነ ሰው ነው፡፡
Short URL: http://www.zehabesha.com/amharic/?p=6151

Monday, August 5, 2013

ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ወያኔን እናስወግድ!!

ሐምሌ 28 2005 ዓ.ም.
ወያኔ ወገኖቻችንን እየገደለ፤ አገራችንን እና ሕዝቧን በሽብር እያመሰ ነው። ከአርብ ሐምሌ 26 ቀን 2005 ዓም ጀምሮ በአገራችን የተለያዩ ክፍሎች የወያኔ ሠራዊት ባልታጠቁና ባልተዘጋጁ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ጥይት እያዘነበ ይገኛል። እስካሁን የሞቱና የቆሰሉ ሰዎች ቁጥር ማወቅ ቀርቶ መገመት እንኳን አዳጋች ነው። ሞስሊም ወገኖቻችን፣ በሕጋዊ መንገድ ለውጥ እናመጣለን ብለው የሚያምኑ ሰላማዊ ታጋዮች፣ ሕፃናትና አዛውንት የጥቃቱ ሰለባ ናቸው።
የወያኔ ግንባር ቀደም የጥቃት ሰለባዎች ሰላማዊነታቸው ለማሳየት እጆቻቸውን አስረው ፍትህ ሲማፀኑ የነበሩ ዜጎች ናቸው። ሕግ የማያውቀው ወያኔን በሕጋዊ መንገድ ታግለን መሠረታዊ መብቶቻችንን እናስከብራለን ያሉ ወገኖቻችን በግፍ ተግደዋል፤ ተደብድበዋል፤ ተግዘዋል። የምዕራብ አርሲ ከተሞችና መንደሮች በአጋዚ ጦር ተወረዋል። አዲስ አበባም ውስጥ ዋይታ በርክቷል።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በወያኔ ፋሽስታዊ እርምጃ ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን ቤተሰቦች ሁሉ የተሰማው መሪር ሀዘን ይገልፃል። እንደዚሁም ለአካል ጉዳት ለተዳረጉ፣ ለተዋከቡ፣ ለተረገጡ፣ ለጅምላ እስር ለተዳረጉ ወገኖቻችን ሁሉ በደረሰባቸው በደል መቆጨቱን ይገልፃል።
ወያኔ በሥልጣን ላይ እስካለ ድረስ የእምነትም ሆነ ሌላ ማናቸውን ነፃነት ሊኖር እንደማይችል የትናትናና የዛሬው ድርጊት አንድ ተጨማሪ ማስረጃ ነው። ወያኔ በሥልጣን መንበር ላይ ውሎ ባደረ መጠን እንዲህ ዓይነቱ መርዶ መስማታችን የማይቀር ነው ብሎ ግንቦት 7 ያምናል። የኢትዮጵያ ሕዝብ መከራ እንዲያበቃ ወያኔ ከሥልጣን መወደግ አለበት፤ ገዳዮች ለፍርድ መቅረብ አለባቸው።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የሰላማችን ዋስትና የወያኔ መወገድና በምትኩ የሕዝብ ይሁንታ ያገኘ መንግሥት መተካት ነው ብሎ ያምናል። ስለሆነም በአገራችን ሰላም እንዲሰፍን እና መሠረታዊ መብቶቻችን ተከብረውልን መኖር እንድንችል ወያኔን ለማስወገድ ቆርጠን እንነሳ።
መጽናናት ለተገዱ ወገኖቻችን ቤተሰቦች!!!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!