Sunday, July 7, 2013
Saturday, July 6, 2013
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ በመንግስት ጥያቄ መሰረት የጎንደርን ሰላማዊ ሰልፍ ለሐምሌ ሰባት አዘዋውረናል አለ
ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ(አንድነት) የተሰጠ መግለጫ
አንድነት ፓርቲ የሶስት ወራት ህዝባዊ ንቅናቄ የትግል ስልት በመንደፍ የመጀመሪያውን የአደባባይ ላይ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ሰኔ 30/10/2005 በጎንደር ከተማ እንደሚያደርግ ማሳወቁ የሚታወስ ነው፡፡ ሁልጊዜም የሀገሪቱን ህግ ጠብቆ በሰላማዊ መንገድ የሚንቀሳቀሰው ፓርቲያችን የአገሪቱ ህገ መንግስት አንቀፅ 30ና የሰላማዊ ሰልፍ አዋጅ 50ኛ ዓመት ቁጥር 4 በሚደነግገው መሰረትም ከህዝቡ ጋር የሚያደርገውን ሰላማዊ ሰልፍ በጎንደር ከተማ ማወቅ ለሚገባው አካልና ለዞኑ አስተዳደር አሳውቆ ወደ ቅስቀሳ በመግባት ከ80 ሺ በላይ በራሪ ወረቀቶችን በማሳተም ከ20 ሺ በላይ በራሪ ወረቀቶችን በጎንደር ከተማ አሰራጭቷል፡፡ በመዋቅራችን አማካኝነትም የቤት ለቤት ቅስቀሳ በማድረግ ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ ድምፁን እንዲያሰማ እያደረግን ባለንበት ወቅት በክልሉ መንግስት የማደናቀፍና የማሰር ርምጃ እየተወሰደ ነው፡፡
በክልሉ መንግስት አባሎቻችን ላይና አመራሮቻችን ላይ በሕገ ወጥ መንገድ ህገ መንግስታዊ መብታቸው እየተገፈፈ፤ ሰብዓዊ ክብራቸውን በመጣስ ላይ ነው፡፡ በሰሜን ጎንደር ዞን በምዕራብ አርማጭሆ አብርሃ ጅራ ከተማ የፓርቲያችን አባላት የሆኑት አቶ አለልኝ አባይ፣ አቶ እንግዳው ዋኘው፣ አቶ አብርሃም ልጃለምና አቶ አንጋው ተገኝ የፓርቲውን የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ለምን በተናችሁ ተብለው ከሰኔ 22 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡ እንዲሁም በጎንደር ከተማ አቶ ማሩ አሻገረ ከሰኔ 26 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ፣ አቶ አምደማሪያም እዝራ እና አቶ ስማቸው ዝምቤ ከሰኔ 25 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ በእስር ላይ ናቸው፡፡ እንዲሁም በወገራ አቶ ጀጃው ቡላዴ ሰኔ 25 ቀን 2005 ዓ.ም ታስሮ ተለቋል፡፡ አቶ ጋሻው ዘውዱ ላይ ጥይት በመተኮስ የመግደል ሙከራ የተደረገ ሲሆን ሮጦ ለማምለጥ ችሏል፡፡ በአልፋ ጣቁሳ ወረዳ መምህር አዋጁ ስዩም ከሰኔ 26 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ በእስር ላይ ሲሆን ሁሉም የታሰሩት ለምን ቀሰቀሳችሁና ወረቀት አሰራጫችሁ በሚል ነው፡፡ ፓርቲያችንም የዞኑን መስተዳድር አፋኝነትና ህገወጥነትን እያወገዘ የታሰሩ አባሎቻችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ በፅኑ እንጠይቃለን፡፡ የታሰሩ አባሎቻችንም ህገወጥ እስሩን በመቃወም ከትናንት ጀምሮ የርሀብ አድማ ላይ ናቸው፡፡
የዞኑ አስተዳደርና የከተማው ም/ከንቲባ በአንድ በኩል ሰላማዊ ሰልፋችንን ለማፈን ርምጃ እየወሰዱ በሌላ በኩል የህዝቡ ሰላማዊ ትግል ወዳድነት ስላስደነገጣቸው የእንነጋገር ጥሪ በ25/10/2005 ዓ.ም አቀረቡ፡፡ በተለይም የከተማው ም/ከንቲባ የሆኑት አቶ ጌትነት አማረ ከሰላማዊ ሰልፉ አስተባባሪዎች ጋር በ27/10/2005 ዓ.ም 2 ሰዓት የፈጀ ድርድር ካደረጉ በኋላ ሰላማዊ ሰልፉ በሚደረግበት ዕለት በጎንደር የተማሪዎች ምረቃ ስላለና የመንገድ ምረቃ ስላለ እንዲሁም ፖሊስ ግምገማና ስልጠና ላይ በመሆኑ በቂ የጥበቃ ኃይል አይኖረንም በሚል ቀኑን አዘዋውሩልን የሚል ጥያቄ በማቅረባቸውና ይህም ጥያቄ ተገቢ ሆኖ ስላገኘነው በጎንደር የሚደረገውን ታላቅ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ከሰኔ 30 ቀን 2005 ዓ.ም ወደ እሁድ ሐምሌ 7 ቀን 2005 ዓ.ም ተዘዋውሮ እንዲደረግ ፓርቲያችን ወስኗል፡፡
በዚህም መሰረት ህዝባዊ ንቅናቄያችን የቆመለትን ዓላማ በምንም ህገ-ወጥነት የማይቀለበስ መሆኑን እየገለፅን ሰላማዊ ትግላችንን አጠናክረን እንደምንቀጥል እናረጋግጣለን፡፡ ሰላማዊ ትግል የሚያስከፍለውን ዋጋ ሁሉ ለመክፈል የቆምንለት ክቡር አላማ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብም ይህንን በመረዳት አሁንም እንደበፊቱ ሁሉ በቁርጠኝነት ከጎናችን እንዲቆም ጥሪያችንን በድጋሚ እናቀርባለን፡፡ የጎንደርና አካባቢው ሕዝብም ይህንን አፋኝ ስርዓት በማውገዝ ከጎናችን በመቆም ትግሉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ሀገራዊ ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡
የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት!!!
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
ሰኔ 28 ቀን 2005 ዓ.ም
አዲስ አበባ
Short URL: http://www.zehabesha.com/amharic/?p=4995
Friday, July 5, 2013
በኢትዮዽያ ‹‹ግብረ ሰዶማዊነት›› ስር ሰዷል – (ከዳንኤል ክብረት)
ወዳጆቻችሁ እንዲያነቡት ተጋሩት!?
አሁን ያለንበት ወቅት አብዛኞቹ ትምህርት ቤቶች ተዘግተው ልጆቻችን ቤት ውስጥ መዋል የጀመሩበት፣ ወይም የክረምት መክረሚያ ነገሮችን ማከናወን የጀመሩበት ጊዜ ነው፡፡ በበጋ ከነበረው የወላጆች ወከባ ዐረፍ ብለናል፡፡ ልጆችን ትምህርት ቤት ማድረስ፣ የቤት ሥራ ማሠራት፣ ግዙ፣ አምጡ፣ ኑ፣ ሂዱ ከሚሉ የትምህርት ቤቶች ትእዛዞች ዐረፍ ያልንበት ሰሞን ነው፡፡ አሁን ልጆቻችንን ስለሚመለከቱ ሌሎች ጉዳዮች ለመነጋገር ምቹ ጊዜ ነው፡፡ እኔ ሁለት ጉዳዮችን መርጫለሁ፤ ዛሬ አንደኛውን እናንሣው፡፡
ጉዳይ አንድ
ባለፈው ሰሞን አንዲት እናት ወደ ቢሮዬ መጥተው እንዲህ አወጉኝ፡፡ ‹‹ልጄ የአሥራ ሁለት ዓመት ልጅና የ 5ኛ ክፍል ተማሪ ነው፡፡ አልፎ አልፎ የማይበት ጠባይ ግራ የሚያጋባኝ እየሆነ ተቸግሬ ነበር፡፡ ወደ ትምህርት ቤት ሲሄድ የእኔን ሽቱ ይቀባል፡፡ እኔም ይህን ሳይ የልጅ ነገር አድርጌ ትቼው ነበር፡፡ በኋላ ግን ከሌላው ነገር ጋር ሲደረብብኝ ነው ግራ የተጋባሁት፡፡ ፀጉሩን እንደ ሴቶች ማስተኛት ይፈልጋል፡፡ ጥብቅ ያለ ሱሪ ካልገዛሽልኝ ይለኛል፡፡ አንድ ቀን ትምህርት ቤት አድርሼው መኪናዬን አዙሬ ልመለስ ስል ከኋላ ያለውን መኪና እንዳልነካው ዞር አልኩ፡፡ ያን ጊዜ ያየሁትን ነገር ዓይኔ ሊያምን አልቻለም ነበር፡፡ ከአንድ ሌላ ወንድ ልጅ ጋር ከንፈር ለከንፈር ሲሳሳሙ አየኋቸው፡፡ ከኋላዬ የነበረው መኪና በጡሩንባ እየጮኸብኝ እንኳን የማየውን ተጠራጥሬ ለረዥም ሰዓት ፈዝዤ ነበር፡፡
ሥራ ከገባሁ በኋላ እጅግ ፈዝዤ ነበር፡፡ የቢሮ ሰዎች ሁሉ እየደጋገሙ ምን እንደሆንኩ ይጠይቁኝ ነበር፡፡ ግን ለማን ምን ብዬ ልንገረው? ነገሩ እጅግ አሳፋሪ ነው የሆነብኝ፡፡ ቢቸግረኝ ወደ አንዲት ጓደኛዬ ባለቤት ጋር ደወልኩ፡፡ እርሱ ሐኪም ነበርና ምናልባት ከረዳኝ ብዬ አሰብኩ፡፡ በስልክ አነጋገሬ አደጋ የደረሰብኝ ይመስል ስለነበር እየከነፈ ቢሮዬ መጣ፡፡ ከእርሱ ጋር ተያይዘን ወጣንና አንድ ቦታ ቁጭ አልን፡፡ በልጄ ላይ ያየሁትን ነገር ሁሉ ነገርኩት፡፡ እርሱም ከሌሎች የሰማቸውን የባሱ ነገሮች እየነገረ አጽናናኝ፡፡ ከዚያም የበለጠ ርግጠኛ ለመሆንና ችግሩንም በሚገባ ለመረዳት ልጄ በማይኖርበት ሰዓት የልጄን ዕቃዎች እንድፈትሻቸው ነገረኝ፡፡ አንድ ቀን አባቱ ወደ መዝናኛ ቦታ እንዲወስደው ነገርኩትና እኔ ዕቃዎቹን መፈተሽ ጀመርኩ፡፡ ያኔ ነው የልጄን ጉዳይ በጥልቀት የተረዳሁት፡፡ እኔ ያልገዛሁለት አንድ ቀይ ቲሸርት አገኘሁ፡፡ ቲሸርቱ ላይ በእንግሊዝኛ ‹I am a gay› የሚልተጽፎበታል፡፡ ዕንባዬን መቆጣጠር አልቻልኩም፡፡ አልጋው ላይ ተቀምጬ ለረዥም ጊዜ አለቀስኩ፡፡ ከዚያ በኋላ መቀጠል አልቻልኩም፡፡ ልጄን እንዳጣሁት ገባኝ፤ ልጄን እንደማላውቀው ገባኝ፤ ልጄና እኔ በተለያዩ መንገዶች እየተጓዝን መሆኑ ገባኝ፡፡
የጓደኛዬ ባለቤት በጉዳዩ ላይ እንዴት ከልጄ ጋር ልወያይ እንደምችል መንገዶችን አመላከተኝ፡፡ አንድ ቀን ከልጄ ጋር ከአዲስ አበባ ወጣ አልን፡፡ አብሬው ስጫወት ዋልኩና ለሻሂ ዐረፍ ስንል አንድ ስልክ አነሣሁ፡፡
አሁን ያለንበት ወቅት አብዛኞቹ ትምህርት ቤቶች ተዘግተው ልጆቻችን ቤት ውስጥ መዋል የጀመሩበት፣ ወይም የክረምት መክረሚያ ነገሮችን ማከናወን የጀመሩበት ጊዜ ነው፡፡ በበጋ ከነበረው የወላጆች ወከባ ዐረፍ ብለናል፡፡ ልጆችን ትምህርት ቤት ማድረስ፣ የቤት ሥራ ማሠራት፣ ግዙ፣ አምጡ፣ ኑ፣ ሂዱ ከሚሉ የትምህርት ቤቶች ትእዛዞች ዐረፍ ያልንበት ሰሞን ነው፡፡ አሁን ልጆቻችንን ስለሚመለከቱ ሌሎች ጉዳዮች ለመነጋገር ምቹ ጊዜ ነው፡፡ እኔ ሁለት ጉዳዮችን መርጫለሁ፤ ዛሬ አንደኛውን እናንሣው፡፡
ጉዳይ አንድ
ባለፈው ሰሞን አንዲት እናት ወደ ቢሮዬ መጥተው እንዲህ አወጉኝ፡፡ ‹‹ልጄ የአሥራ ሁለት ዓመት ልጅና የ 5ኛ ክፍል ተማሪ ነው፡፡ አልፎ አልፎ የማይበት ጠባይ ግራ የሚያጋባኝ እየሆነ ተቸግሬ ነበር፡፡ ወደ ትምህርት ቤት ሲሄድ የእኔን ሽቱ ይቀባል፡፡ እኔም ይህን ሳይ የልጅ ነገር አድርጌ ትቼው ነበር፡፡ በኋላ ግን ከሌላው ነገር ጋር ሲደረብብኝ ነው ግራ የተጋባሁት፡፡ ፀጉሩን እንደ ሴቶች ማስተኛት ይፈልጋል፡፡ ጥብቅ ያለ ሱሪ ካልገዛሽልኝ ይለኛል፡፡ አንድ ቀን ትምህርት ቤት አድርሼው መኪናዬን አዙሬ ልመለስ ስል ከኋላ ያለውን መኪና እንዳልነካው ዞር አልኩ፡፡ ያን ጊዜ ያየሁትን ነገር ዓይኔ ሊያምን አልቻለም ነበር፡፡ ከአንድ ሌላ ወንድ ልጅ ጋር ከንፈር ለከንፈር ሲሳሳሙ አየኋቸው፡፡ ከኋላዬ የነበረው መኪና በጡሩንባ እየጮኸብኝ እንኳን የማየውን ተጠራጥሬ ለረዥም ሰዓት ፈዝዤ ነበር፡፡
ሥራ ከገባሁ በኋላ እጅግ ፈዝዤ ነበር፡፡ የቢሮ ሰዎች ሁሉ እየደጋገሙ ምን እንደሆንኩ ይጠይቁኝ ነበር፡፡ ግን ለማን ምን ብዬ ልንገረው? ነገሩ እጅግ አሳፋሪ ነው የሆነብኝ፡፡ ቢቸግረኝ ወደ አንዲት ጓደኛዬ ባለቤት ጋር ደወልኩ፡፡ እርሱ ሐኪም ነበርና ምናልባት ከረዳኝ ብዬ አሰብኩ፡፡ በስልክ አነጋገሬ አደጋ የደረሰብኝ ይመስል ስለነበር እየከነፈ ቢሮዬ መጣ፡፡ ከእርሱ ጋር ተያይዘን ወጣንና አንድ ቦታ ቁጭ አልን፡፡ በልጄ ላይ ያየሁትን ነገር ሁሉ ነገርኩት፡፡ እርሱም ከሌሎች የሰማቸውን የባሱ ነገሮች እየነገረ አጽናናኝ፡፡ ከዚያም የበለጠ ርግጠኛ ለመሆንና ችግሩንም በሚገባ ለመረዳት ልጄ በማይኖርበት ሰዓት የልጄን ዕቃዎች እንድፈትሻቸው ነገረኝ፡፡ አንድ ቀን አባቱ ወደ መዝናኛ ቦታ እንዲወስደው ነገርኩትና እኔ ዕቃዎቹን መፈተሽ ጀመርኩ፡፡ ያኔ ነው የልጄን ጉዳይ በጥልቀት የተረዳሁት፡፡ እኔ ያልገዛሁለት አንድ ቀይ ቲሸርት አገኘሁ፡፡ ቲሸርቱ ላይ በእንግሊዝኛ ‹I am a gay› የሚልተጽፎበታል፡፡ ዕንባዬን መቆጣጠር አልቻልኩም፡፡ አልጋው ላይ ተቀምጬ ለረዥም ጊዜ አለቀስኩ፡፡ ከዚያ በኋላ መቀጠል አልቻልኩም፡፡ ልጄን እንዳጣሁት ገባኝ፤ ልጄን እንደማላውቀው ገባኝ፤ ልጄና እኔ በተለያዩ መንገዶች እየተጓዝን መሆኑ ገባኝ፡፡
የጓደኛዬ ባለቤት በጉዳዩ ላይ እንዴት ከልጄ ጋር ልወያይ እንደምችል መንገዶችን አመላከተኝ፡፡ አንድ ቀን ከልጄ ጋር ከአዲስ አበባ ወጣ አልን፡፡ አብሬው ስጫወት ዋልኩና ለሻሂ ዐረፍ ስንል አንድ ስልክ አነሣሁ፡፡
እንደ ደነገጠ ሰው ሆኜ ነበር የማወራው፡፡ ልጄም ድምፄን እየሰማና ሁኔታዬን እያየ ተደናገጠ፡፡ ስጨርስ ምን እንደሆንኩ ጠየቀኝ፡፡ ‹‹አንዲት ጓደኛዬ ከባድ ነገር እንደ ደረሰባት፡፡ ልጇ ግብረ ሰዶማዊ እንደሆነባት፡፡ በዚህም ምክንያት በሕግ ሊጠየቅ መሆኑን›› ነገርኩት፡፡ እጅግ ደነገጠ፡፡ ‹‹የእኔ ልጅ መቼም እንዲህ ያለ ነገር አያደርግም›› ብዬ ተውኩት፡፡ አፍጥጦ ዓይን ዓይኔን ያየኝ ነበር፡፡ ‹‹በጣም ከባድ ነገር ነው የገጠማት፤ ግብረ ሰዶማዊ ማለትኮ በሃይማኖታችንም ትክክል አይደለም፤ እግዚአብሔር ግብረ ሰዶማውያንን አጥፍቷቸዋል፡፡ ከዚያም በላይ ግብረ ሰዶማውያን በኅሊናቸውም ሆነ በማኅበራዊ ኑሮአቸው ላይ ችግር እንደሚገጥማቸው፤ ከሕዝቡም እንደሚገለሉ፤ አኗኗራቸውም ከተፈጥሮ ሕግ ውጭ እንደሆነ፤ ወንድ ከሴት ጋር ሴትም ከወንድ ጋር እንጂ ወንድ ከወንድ፣ ሴትም ከሴትጋር የሚደረገው ግንኙነት እንስሳት እንኳን የማይፈጽሙት መሆኑን፡፡ የወሲብ ግንኙነት ማንኛውም ወንድ ከ ተፈቀደለት ሴት ጋር ብቻ፣ ባህሉና እምነቱ፣ ሕጉም በሚፈቅደው እድሜና ሁኔታ የሚፈጸም መሆኑን›› እየዘረዘርኩ መግለጥ ጀመርኩ፡፡ ዝም ብሎ ነበር የሚያዳምጠኝ፡፡ አንዳንድ ሰዎች ልጆቻቸውን ግብረ ሰዶማውያን እንደሚያደርጓቸው፤ እነዚህ ልጆችም ሌሎችን ልጆች አባብለው ወደዚህ እንደሚያስገቧቸው፤ እንዲያውም ‹I am a gay› የሚል ልብስ የሚለብሱ እንዳሉ ነገርኩት፡፡
ግራ ሳይገባው አልቀረም፡፡ ስለ እርሱ እንደምናገር ገምቷል፡፡ ስጨርስ ‹‹የኔ ልጅ አንተ ግን እንደዚህ አታደርግም አይደል?›› አልኩት፡፡ ምንም አላለኝም፡፡ ዝም አለኝ፡፡ መሬት መሬት ያይ ጀመር፡፡ ‹‹ምነው የኔ ልጅ ችግር አለ እንዴ›› አልኩት፡፡ ዝም አለ፡፡ ‹‹አደራህን አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ያሉ ልጆች ሌሎች ልጆችን ሳያውቁት ወደዚህ ነገር እያስገቧቸው ነውና ተጠንቀቅ›› አልኩት፡፡ እሺምእምቢም አላለኝም፡፡ ‹‹አንተ ይህንን ስታደርግ ካየሁ፤ እኔ ወዲያው ነው የምሞተው›› ስለው ተስፈንጥሮ መጥቶ ጭኔ ላይ ተደፋ፡፡ ሲያለቅስ ይሰማኛል፡፡ ዕንባውም እግሬን ሲያሞቀው ይታወቀኛል፡፡ እኔም እያለቀስኩ ነበር፡፡ ከብዙ የዝምታ ልቅሶ በኋላ ‹‹እማዬ እኔኮ ጌይ ሆኛለሁ›› አለኝ፡፡ ቀድሜ ባውቅም ያ ሰዓት ግን መብረቅ የመታኝ ነበር የመሰለኝ፡፡ ከልጄ አንደበት ይህንን ስሰማ ኩምሽሽ ብዬ ትንሽ የሆንኩ መሰለኝ፡፡ የማደርገው ጨነቀኝ፤ ምን ልመልስለት? ምንልበለው? ግራ ተጋባሁ፡፡ ‹‹ለምን ልጄ? ለምን?›› አልኩት፡፡ ከእኛ ራቅ ብለው የሚያዩን ሰዎች ሁኔታዬ ግራ አጋብቷቸው ሁሉም እኔን ያያሉ፡፡
‹‹እኛ ትምህርት ቤትኮ ብዙ ልጆች አሉ›› አለኝ፡፡
‹‹ምን ምን ታደርጋላችሁ?›› አልኩት
‹‹ሽቱ ተቀብተው ይመጣሉ፤ ደግሞ አንድ ዓይነት ማስቲካ ነው የምንበላው፤ ‹I ama gay› የሚል ቲሸርት እንለብሳለን›› አለኝ፡፡
‹‹ቲሸርቱን ማን ነው የሰጣችሁ?›› አልኩት
‹‹አንድ ልጅ ነው ያመጣልን፤ ለሁላችን ሰጠን፡፡ ግን ከዩኒፎርማችን ሥር እንድንለብሰው ነግሮናል››
‹‹ሌላስ?››
‹‹ደግሞ አንድ ልጅ የጌይ ፊልም በዕረፍት ጊዜ ያሳየናል››
‹‹የት ነው የሚያሳያችሁ?›› ‹‹በኪሱ የሚያመጣው ሞባይል አለ፡፡ እናቴ ናት የምትጭንልኝ ብሏል››
የምሰማውን እንዴት ልመነው?
‹‹እርሱኮ [የልጁን ስም እየነገረኝ] አባቱ ትምህርት ቤት ሲሸኘው ሁልጊዜ ከንፈሩን ይስመዋል›› አለኝ፡፡ ይኼኔ ነቃሁ፡፡ አስታወስኩ፡፡ ሰውዬውንም ዐወቅኩት፡፡ እኔም ደስ አይለኝም ነበር፡፡ አባት ወንድ ልጁን፣ እናትም ሴት ልጇን ከንፈራቸውን መሳም እዚህ ትምህርት ቤት የማየው ነገር ነው፡፡ ይህ ነገር ልጆቻችን ይህንን መሰሉን ተግባር ከዕድሜ ቀድመው እንዲለምዱት ያደርጋል፡፡ ከዚያም አልፎ ነገ ሌሎች ግብረ ሰዶማውያን በልጆቹ ላይ ይህንን መሰል ተግባር ሲፈጽሙባቸው ምንም እንዳይመስላቸውና የፍቅር መግለጫ አድርገው እንዲወስዱት ያደርጋቸዋል፡፡ ከባህላችን ያፈነገጡ ነገሮችን በልጆቻችን ላይ ማድረግ እነዚህ ነገሮች በልጆቻችን ላይ በሌሎች አካላት ሲደረጉባቸው እንዳያስተውሉት እንዳይጸየፉትም ያደርጋቸዋል፡፡
‹‹ለመሆኑ አብራችሁ ስትሆኑ ምን ታደርጋላችሁ?›› አልኩት፡፡
‹‹አንዳንድ ወንዶች ልጆች ይሳሳማሉ፤ እኔ ግን ይደብረኛል፤ ደግሞ ይተሻሻሉ›› አለኝ፡፡ ከገጽታው የመቅፈፍ ስሜት አየሁበት፡፡ ይህንን ስሜት ስመለከት ወደ ችግሩ ውስጥ ዘልቆ እንዳልገባበት ተረዳሁ፡፡ እኔ የማዝነው በባህላችን ተከብሮ የኖረውን የወንድም ለወንድም፣ የእኅት ለእኅት ግንኙነት ግብረ ሰዶማዊነት እያጠፋብን በመሆኑ ነው፡፡ እኔ ከአክስቶቼ ልጆች ጋር አብሬ እየተጫወትኩ፣ አብሬእየተኛሁ ነው ያደግኩት፡፡ ልጆቻችን ግን እንዲህ ማድረግ ላይችሉ ነው፡፡ ከአጎታችን፣ ከአክስታችን ጋር መተኛት ለኛ ደስታችን ነበር፡፡ ዛሬ ግን ዘመዶች በዘመዶች ላይ እንዲህ የሚፈጽሙ ከሆነ ዝምድናችን ሊጠፋብን ነው፡፡ መምህሮቻችንን፣ የሃይማኖት አባቶችን፣ የቤት ሠራተኞችን፣ የጥበቃ ሠራተኞችን እየተጠራጠርን ልንኖር ነው፡፡ ግብረ ሰዶምነት ባህላችንን እጅግ አድርጎ ነው የሚያበላሸው፤ ማኅበራዊ ግንኙነቶቻችንን ነው የሚበጣጥሰው፤ እንዴት ያለ ችግር ውስጥ ነው የገባነው በእግዚአብሔር? በኋላ ከአንዳንድ የሕክምና ባለሞያዎች ጋር ስንነጋገር ብዙ ነገር ሰማሁ፡፡ በከተማችን ውስጥ የግብረ ሰዶማውያን ማዘውተሪያዎች የታወቁ ናቸው፡፡ የራሳቸው የመግባቢያ ‹ቋንቋም› አላቸው፡፡ ትልልቆቹ ግብረ ሰዶማውያን ድራግ በመውሰድ ቀዳሚዎች ናቸው፡፡ እጅግ የሚያሳዝነው ደግሞ ለሕፃናቱ ድራጉን በከረሚላ መልክ ይሰጧቸዋል፡፡ ከወላጆቻቸው ለመደበቅ ሲሉ ልጆቹ ግለኛነትን ይመርጣሉ፡፡ ከሌሎች ልጆች ወይም ከዘመዶቻቸው ጋር ከመጨዋት ይልቅ ከጌምና ከቴሌቭዥን ጋር ብቻ መሆንን ይፈልጋሉ፡፡ በተለይም ፌስ ቡክን በሚገባ ለዚህ አስተሳሰብ ማራመጃ ይጠቀሙበታል፡፡ ወላጆች ኢንተርኔትን ልጆቻችን ያለእድሜያቸው እንዳይጠቀሙበት ማድረግ አለብን፡፡ ስለ ኢንተርኔት አጠቃቀም፣ ስለ ጥቅምና ጉዳቱ ሳንነግራቸው ነው የምንፈቅድላቸው፡፡ ይኼኔ ከበጎው ይልቅ ክፉውን የመያዝ ዕድላቸው ይሰፋል፡፡ በቤታችን ውስጥ ያስገባናቸውን የቴሌቭዥን ቻነሎችንም መቆጣጠር አለብን፡፡ ልጆቻችን ክፉውንም ደጉንም ዝም ብለው እንዲያዩ ማድረግ የለብንም፡፡ ግብረ ሰዶምን የሚያበረታቱ ቻነሎች አሉ፡፡
‹አሁን ልጅዎ ከችግሩ በሚገባ ወጥቶልዎታል?›› አልኳቸው፡፡
‹‹ሙሉ በሙሉ ከችግሩ ወጥቷል ማለት አልችልም፤ አሁንም እጠራጠራለሁ፡፡ ፍርሃቱ ገና አልለቀቀኝም፡፡ ነገር ግን ክትትሌን አላቆምኩም፤ ከልጄ ጋር ያለኝን ቀረቤታም ጨምሬያለሁ፤ ስለ ብዙ ነገሮችም እንነጋገራለን፤ የሃይማኖት ትምህርት እንዲማርም እያደረግኩ ነው፡፡ አንድ የማውቀው የሥነ ልቡና ባለሞያ ስለ ግረ ሰዶም ጉዳት በሚገባ ነግሮታል፡፡ በተለይ በዚህ ክረምት የተለየ ነገር ለማድረግ እየሞከርኩ ነው፡፡ ትምህርት ቤቶቻችንን ግን ከትምህርት ጥራትና ከክፍያቸው ባለፈ ወላጆች መከታተል አለብን፤ ልጆቻችንም የተለየ ነገር ሲያዩ እንዲነግሩን ማሳሰብ ይገባል፡፡ ዘመኑ ወላጅነት ከባድ የሆነበት ጊዜ ነው፡፡ ›› አሉኝ፡፡
ወላጆች ሆይ
እስኪ በጉዳዩ ላይ እንምከርበት፡፡ ከልጆቻችንም ጋር እንነጋገር፤ መምህራን በተማሪዎች ላይ ይህንን ነገር ፈጽመዋል ተብለው የሚከሰሱበት ጊዜ ላይ ነንና ልጆቻችን እንዳይታለሉ እንንገራቸው፤ ከሃይማኖት፣ ከሥነ ምግባር፣ ከባህል፣ ከጤናና ከማኅበራዊ ኑሮ አንጻር የሚያስከትለውን ችግር እንንገራቸው፡፡ እኛም ስለዚህ ጉዳይ መረጃ እንዲኖረን እንጠይቅ፣ እናንብብ፣ እንመካከር፤ ከተለያዩ አካባቢዎች ከምሰማው አንጻር በተለይ በከተሞች ውስጥ ችግሩ ሳይታሰብ ሥር እየሰደደ ነው፡፡ ሰሞኑን የቀረበ አንድ ይፋ ያልሆነ ጥናት በአዲስ አበባ ከተማ መሰናዶ ትምህርት ቤቶች በሚማሩ 2000 ተማዎች ላይ በተደረገ ጥናት 48% ተማሪዎች የጌይና ሌዝቢያን ደጋፊ መሆናቸው ታውቋል፡፡ እኒህ እናት እንዳሉት በዚህ ዘመን ወላጅነት ፈተና ውስጥ ገብቷል፡፡ ኃላፊነቱ ሰፍቷል፡፡ መሰናክሉ በዝቷል፡፡ እስኪ የፈጣሪን ርዳታ እየጠየቅን ይህንን ነገር የሰሞኑ የቤተሰብ አጀንዳ እናድርገው፡፡
ግራ ሳይገባው አልቀረም፡፡ ስለ እርሱ እንደምናገር ገምቷል፡፡ ስጨርስ ‹‹የኔ ልጅ አንተ ግን እንደዚህ አታደርግም አይደል?›› አልኩት፡፡ ምንም አላለኝም፡፡ ዝም አለኝ፡፡ መሬት መሬት ያይ ጀመር፡፡ ‹‹ምነው የኔ ልጅ ችግር አለ እንዴ›› አልኩት፡፡ ዝም አለ፡፡ ‹‹አደራህን አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ያሉ ልጆች ሌሎች ልጆችን ሳያውቁት ወደዚህ ነገር እያስገቧቸው ነውና ተጠንቀቅ›› አልኩት፡፡ እሺምእምቢም አላለኝም፡፡ ‹‹አንተ ይህንን ስታደርግ ካየሁ፤ እኔ ወዲያው ነው የምሞተው›› ስለው ተስፈንጥሮ መጥቶ ጭኔ ላይ ተደፋ፡፡ ሲያለቅስ ይሰማኛል፡፡ ዕንባውም እግሬን ሲያሞቀው ይታወቀኛል፡፡ እኔም እያለቀስኩ ነበር፡፡ ከብዙ የዝምታ ልቅሶ በኋላ ‹‹እማዬ እኔኮ ጌይ ሆኛለሁ›› አለኝ፡፡ ቀድሜ ባውቅም ያ ሰዓት ግን መብረቅ የመታኝ ነበር የመሰለኝ፡፡ ከልጄ አንደበት ይህንን ስሰማ ኩምሽሽ ብዬ ትንሽ የሆንኩ መሰለኝ፡፡ የማደርገው ጨነቀኝ፤ ምን ልመልስለት? ምንልበለው? ግራ ተጋባሁ፡፡ ‹‹ለምን ልጄ? ለምን?›› አልኩት፡፡ ከእኛ ራቅ ብለው የሚያዩን ሰዎች ሁኔታዬ ግራ አጋብቷቸው ሁሉም እኔን ያያሉ፡፡
‹‹እኛ ትምህርት ቤትኮ ብዙ ልጆች አሉ›› አለኝ፡፡
‹‹ምን ምን ታደርጋላችሁ?›› አልኩት
‹‹ሽቱ ተቀብተው ይመጣሉ፤ ደግሞ አንድ ዓይነት ማስቲካ ነው የምንበላው፤ ‹I ama gay› የሚል ቲሸርት እንለብሳለን›› አለኝ፡፡
‹‹ቲሸርቱን ማን ነው የሰጣችሁ?›› አልኩት
‹‹አንድ ልጅ ነው ያመጣልን፤ ለሁላችን ሰጠን፡፡ ግን ከዩኒፎርማችን ሥር እንድንለብሰው ነግሮናል››
‹‹ሌላስ?››
‹‹ደግሞ አንድ ልጅ የጌይ ፊልም በዕረፍት ጊዜ ያሳየናል››
‹‹የት ነው የሚያሳያችሁ?›› ‹‹በኪሱ የሚያመጣው ሞባይል አለ፡፡ እናቴ ናት የምትጭንልኝ ብሏል››
የምሰማውን እንዴት ልመነው?
‹‹እርሱኮ [የልጁን ስም እየነገረኝ] አባቱ ትምህርት ቤት ሲሸኘው ሁልጊዜ ከንፈሩን ይስመዋል›› አለኝ፡፡ ይኼኔ ነቃሁ፡፡ አስታወስኩ፡፡ ሰውዬውንም ዐወቅኩት፡፡ እኔም ደስ አይለኝም ነበር፡፡ አባት ወንድ ልጁን፣ እናትም ሴት ልጇን ከንፈራቸውን መሳም እዚህ ትምህርት ቤት የማየው ነገር ነው፡፡ ይህ ነገር ልጆቻችን ይህንን መሰሉን ተግባር ከዕድሜ ቀድመው እንዲለምዱት ያደርጋል፡፡ ከዚያም አልፎ ነገ ሌሎች ግብረ ሰዶማውያን በልጆቹ ላይ ይህንን መሰል ተግባር ሲፈጽሙባቸው ምንም እንዳይመስላቸውና የፍቅር መግለጫ አድርገው እንዲወስዱት ያደርጋቸዋል፡፡ ከባህላችን ያፈነገጡ ነገሮችን በልጆቻችን ላይ ማድረግ እነዚህ ነገሮች በልጆቻችን ላይ በሌሎች አካላት ሲደረጉባቸው እንዳያስተውሉት እንዳይጸየፉትም ያደርጋቸዋል፡፡
‹‹ለመሆኑ አብራችሁ ስትሆኑ ምን ታደርጋላችሁ?›› አልኩት፡፡
‹‹አንዳንድ ወንዶች ልጆች ይሳሳማሉ፤ እኔ ግን ይደብረኛል፤ ደግሞ ይተሻሻሉ›› አለኝ፡፡ ከገጽታው የመቅፈፍ ስሜት አየሁበት፡፡ ይህንን ስሜት ስመለከት ወደ ችግሩ ውስጥ ዘልቆ እንዳልገባበት ተረዳሁ፡፡ እኔ የማዝነው በባህላችን ተከብሮ የኖረውን የወንድም ለወንድም፣ የእኅት ለእኅት ግንኙነት ግብረ ሰዶማዊነት እያጠፋብን በመሆኑ ነው፡፡ እኔ ከአክስቶቼ ልጆች ጋር አብሬ እየተጫወትኩ፣ አብሬእየተኛሁ ነው ያደግኩት፡፡ ልጆቻችን ግን እንዲህ ማድረግ ላይችሉ ነው፡፡ ከአጎታችን፣ ከአክስታችን ጋር መተኛት ለኛ ደስታችን ነበር፡፡ ዛሬ ግን ዘመዶች በዘመዶች ላይ እንዲህ የሚፈጽሙ ከሆነ ዝምድናችን ሊጠፋብን ነው፡፡ መምህሮቻችንን፣ የሃይማኖት አባቶችን፣ የቤት ሠራተኞችን፣ የጥበቃ ሠራተኞችን እየተጠራጠርን ልንኖር ነው፡፡ ግብረ ሰዶምነት ባህላችንን እጅግ አድርጎ ነው የሚያበላሸው፤ ማኅበራዊ ግንኙነቶቻችንን ነው የሚበጣጥሰው፤ እንዴት ያለ ችግር ውስጥ ነው የገባነው በእግዚአብሔር? በኋላ ከአንዳንድ የሕክምና ባለሞያዎች ጋር ስንነጋገር ብዙ ነገር ሰማሁ፡፡ በከተማችን ውስጥ የግብረ ሰዶማውያን ማዘውተሪያዎች የታወቁ ናቸው፡፡ የራሳቸው የመግባቢያ ‹ቋንቋም› አላቸው፡፡ ትልልቆቹ ግብረ ሰዶማውያን ድራግ በመውሰድ ቀዳሚዎች ናቸው፡፡ እጅግ የሚያሳዝነው ደግሞ ለሕፃናቱ ድራጉን በከረሚላ መልክ ይሰጧቸዋል፡፡ ከወላጆቻቸው ለመደበቅ ሲሉ ልጆቹ ግለኛነትን ይመርጣሉ፡፡ ከሌሎች ልጆች ወይም ከዘመዶቻቸው ጋር ከመጨዋት ይልቅ ከጌምና ከቴሌቭዥን ጋር ብቻ መሆንን ይፈልጋሉ፡፡ በተለይም ፌስ ቡክን በሚገባ ለዚህ አስተሳሰብ ማራመጃ ይጠቀሙበታል፡፡ ወላጆች ኢንተርኔትን ልጆቻችን ያለእድሜያቸው እንዳይጠቀሙበት ማድረግ አለብን፡፡ ስለ ኢንተርኔት አጠቃቀም፣ ስለ ጥቅምና ጉዳቱ ሳንነግራቸው ነው የምንፈቅድላቸው፡፡ ይኼኔ ከበጎው ይልቅ ክፉውን የመያዝ ዕድላቸው ይሰፋል፡፡ በቤታችን ውስጥ ያስገባናቸውን የቴሌቭዥን ቻነሎችንም መቆጣጠር አለብን፡፡ ልጆቻችን ክፉውንም ደጉንም ዝም ብለው እንዲያዩ ማድረግ የለብንም፡፡ ግብረ ሰዶምን የሚያበረታቱ ቻነሎች አሉ፡፡
‹አሁን ልጅዎ ከችግሩ በሚገባ ወጥቶልዎታል?›› አልኳቸው፡፡
‹‹ሙሉ በሙሉ ከችግሩ ወጥቷል ማለት አልችልም፤ አሁንም እጠራጠራለሁ፡፡ ፍርሃቱ ገና አልለቀቀኝም፡፡ ነገር ግን ክትትሌን አላቆምኩም፤ ከልጄ ጋር ያለኝን ቀረቤታም ጨምሬያለሁ፤ ስለ ብዙ ነገሮችም እንነጋገራለን፤ የሃይማኖት ትምህርት እንዲማርም እያደረግኩ ነው፡፡ አንድ የማውቀው የሥነ ልቡና ባለሞያ ስለ ግረ ሰዶም ጉዳት በሚገባ ነግሮታል፡፡ በተለይ በዚህ ክረምት የተለየ ነገር ለማድረግ እየሞከርኩ ነው፡፡ ትምህርት ቤቶቻችንን ግን ከትምህርት ጥራትና ከክፍያቸው ባለፈ ወላጆች መከታተል አለብን፤ ልጆቻችንም የተለየ ነገር ሲያዩ እንዲነግሩን ማሳሰብ ይገባል፡፡ ዘመኑ ወላጅነት ከባድ የሆነበት ጊዜ ነው፡፡ ›› አሉኝ፡፡
ወላጆች ሆይ
እስኪ በጉዳዩ ላይ እንምከርበት፡፡ ከልጆቻችንም ጋር እንነጋገር፤ መምህራን በተማሪዎች ላይ ይህንን ነገር ፈጽመዋል ተብለው የሚከሰሱበት ጊዜ ላይ ነንና ልጆቻችን እንዳይታለሉ እንንገራቸው፤ ከሃይማኖት፣ ከሥነ ምግባር፣ ከባህል፣ ከጤናና ከማኅበራዊ ኑሮ አንጻር የሚያስከትለውን ችግር እንንገራቸው፡፡ እኛም ስለዚህ ጉዳይ መረጃ እንዲኖረን እንጠይቅ፣ እናንብብ፣ እንመካከር፤ ከተለያዩ አካባቢዎች ከምሰማው አንጻር በተለይ በከተሞች ውስጥ ችግሩ ሳይታሰብ ሥር እየሰደደ ነው፡፡ ሰሞኑን የቀረበ አንድ ይፋ ያልሆነ ጥናት በአዲስ አበባ ከተማ መሰናዶ ትምህርት ቤቶች በሚማሩ 2000 ተማዎች ላይ በተደረገ ጥናት 48% ተማሪዎች የጌይና ሌዝቢያን ደጋፊ መሆናቸው ታውቋል፡፡ እኒህ እናት እንዳሉት በዚህ ዘመን ወላጅነት ፈተና ውስጥ ገብቷል፡፡ ኃላፊነቱ ሰፍቷል፡፡ መሰናክሉ በዝቷል፡፡ እስኪ የፈጣሪን ርዳታ እየጠየቅን ይህንን ነገር የሰሞኑ የቤተሰብ አጀንዳ እናድርገው፡፡
Short URL: http://www.zehabesha.com/amharic/?p=4975
መቼ ይሆን የኢትዮጵያ የጦር ሀይል ይህዝብ አጋር የሚሆነው?
የግብፅ ህዝብ መብቱን እና ነፃነቱን ለማስጠበቅ በአንድነት በመቆም በሁለት አመት ውስጥ ሁለት መንግስት ለመግልበጥ
ቆራጥነቱን በማሳየት በአደባባይ በህብረት እየገለፀ ይታያል በተለይም በታህሪር አደባባይ ቀደመው አምባገነኑን ሁሴን ሙባረክ
የውረድልን በማለት ለረጅም ወራት እየዋሉ እዛውእያደሩ ህዝባዊ አመፃቸው ለድል አብቅቷቸዋል ይሁሉ ሲሆን ያለመሳዋትነት
ደል የለምና ህያው ህይወታቸውን የከፈሉ በርካታ ግብፃዊያን ናቸው አሁን ደግሞ በእስላማዊ ብራዘርሁድ ደጋፊ የሚመራአው
የሙርሲ መንግስት ለህዝቡ ቃል የገባውን በአግባቡ ባለመፈፀሙ ለህዝብ ተቃውሞ ተዳርጓል በዚህም የተነሳ ኩሁሉም በላይ
የሚያስደስተው የግብፅ ህዝብን ሊያኮሯው ይችለው አብይ ጉዳይ ከህዝብ አብራክ የተገኘው የጦር ሀይሉ ህዝባዊ ወገናዊነቱን
በማሳየቱነው።
ምናልባትም ወንድሙ ወይም እህቱ በአደባባይ ወጥተው ሲቃወሙ ወታደሩ እንዴት ከቤተስቡ አካል ላይ ቃታ ይስባል፣
ይህን ለማለት ያስቻለኝ ከአገራችን ወቅታዊ ሁኔታ ጋራ ለማገናኘት ፈልጌ ነው ይህዉም በሁላችንም አምሮውስጥ ትልቅ ጠባሳ
ጥሎ ያለፈውን የምርጫ 97 ትውስታ በአካለም ተግኝቼ ሁኔታውን ስላይው ነው ትዝታዬን ቀስቅሶት ነው የትጨበረበረውን
የተሰረቀውን ድምጻችንን ይመለስልን ብለን በአደባባይ ለተቃውሞ የወጣነውን ስላማዊ ህዝብ በወርሃ ጥቅምት 22,1989
ከአንድ ጎጥና ብሔር የተወጣጣው በፋሽስቱ መለስ የሚመራው የአጋዚን ልዩ ጦር በንፁሀን ኢትዮጵያኖች ላይ የፈፀመው
ኢሰባዊ ግድያ ከሁላችንም ህሊና መቼም ቢሆን አይረሳነም። ከአንድ ብሄር የወጣው የአጋዚን ወታደር የኢትዮጵያ ደም
ሰለሌው ነው እንደግብፅ ወታደር ለህዝብ የቆም ስላልሆነ ንው ለአንባገነኖቻ።
እኛ ኢትዮጵያኖች ከግብፅ ህዝብ ልንማር የምንችለው ቁምነገሮች አሉ ለውጥ ሊመጣ የሚቺለው በትግል መሆኑን ሁላችንም
ጠንቅቀን እናውቃለን ከቀደምት አባቶቻችን እና እናቶቻችን ታሪክ የሚያስተምሩን አንዳንድ ጥቃቅን ችግሮች እንኳን
ቢኖራቸው በአገርህልውናላይ በአንድነት ነው የሚቆሙት ከኢትዮጵያ አልፈው ለጥቁር ህዝቦች ሁሉ ደማቅ ታሪክ ስርተው
ያለፉት የህም ትውልድ የአባቶቹን እና የ እናቶቹን አደራ በጎሳወይም በብሄር ሳይከፋፈል በመከባበርና እና በመቻቻል
ልዩነታችንን ወደ ጎን ትተን ለአንዲት ከማነም አገር በፊት ቀደምት ታሪክ ላላት ወድ ሀገራችን ለኢትዮጵያችን በጋራና በህብረት
እንደ ግብፅ ህዝቦች መቆም አለብን።
የመከላከያም ተቋምም ይሁን የፖሊስ ሰራዊት እንዲሁም የህዝብ ደንነት ከህዝብ አካል ስለተገኛ ህዝባዊ አጋርነቱን
ማሳየት አለበት እድሜልኩን ለአባገነኖች ለዘረኞች ማገልገል የለበትም ከግብፅ ወታደር ብዙ ቁም ነገርቹን መማር አለብት
በቃ በሎ ከህዝብ ጎን መቆም ይኖርበታል።
ኢትዮጵያ በቆራጥ ልጆቿ ለዘላለም ትኑር!!!!!!
ዳዊት ወንድሙ!!!!!
አስቸኳይ የንስሃ ጥሪ ለሁሉም!!! (ከዲያቆን አሸናፊ መኮንን)
ከዛሬ ሠላሣ ሁለት ዓመት በፊት በአንድ ገዳም ውስጥ ይኖሩ የነበሩና ለ40 ዓመት የዘጉ አንድ ባሕታዊ ከዘጉበት ቤተ ጸሎት ወጥተው ለሕዝቡ ታዩ፡፡ ታይተው የማያውቁ እኚህ አባት ዛሬ መውጣታቸው ሕዝቡን አስደንግጦታል፡፡ ለሰንበት ቅዳሴ ለተሰበሰበው ሕዝብ እንዲህ በማለት ተናገሩ፡- “በሕልሜ ቤበ- መኩ- እፍ- ጸጉ የሚሉ ቃላትን ያሳየኛል፡፡ ተጨንቄአለሁና እባካችሁ ፍቱልኝ” አሉ፡፡ ሕዝቡም፡- “አባታችን እኛ ምኑን እናውቀዋለን? ለእርስዎ እንዳሳየ ይፍታልዎ እንጂ” አሏቸው፡፡ እርሳቸውም ሕልሙን ሲተረጕሙ፡-
ቤበ – ማለት ቤተ ክርስቲያን በረት ሆነች ማለት ነው፡፡
መኩ – መሥዋዕት ኩበት ሆነ ማለት ነው
እፍ - ዕጣን ፍግ ሆነ ማለት ነው፡፡
ጸጉ – ጸሎት ጉባዔ/ ታይታ/ ሆነ ማለት ነው በማለት ተረጎሙ፡፡
ሕልምም ሆነ ትንቢት በፍጻሜው ይታወቃል፡፡ እኝህ አባት ያሳያቸው እውነት እንደሆነ ዛሬ እያየነው ነው፡፡ በረት ቆሻሻ የበዛበት፣ ንጽሕና የጎደለው፣ ሥነ ሥርዓት የሌለበት፣ የሕያው ነፍስ ሳይሆን የደመ ነፍስ /የእንስሳት/ መከማቻ፣ ነጻነት የማይሰጥ፣ በውስጡ የሚኖሩት የሕሊና፣ የሰብአዊና የመንፈሳዊ ሕግ የማያዛቸው፣ ዙሪያው የሚበርድ ክፍት የሆነ ስፍራ ነው፡፡ እኝህ አባት ቤተ ክርስቲያን በረት ሆነች ይለኛል አሉ፡፡ ንስሐን የመሰለ የሕይወት ውኃ የሚነገርባት ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮቿ ያልታጠቡባት፣ ንስሐን ተሸክመው ንስሐ የሚቀበሉባት፣ በዓለም የሌለ ነውር በእርስዋ የሚሰማባት፣ ቅድስና የራቃት፣ ሁሉም በፊቱ ደስ ያለውን የሚያደርግባት፣ የደፈረ የሚኖርባት፣ እንኳን መንፈሳዊነት ሰብአዊነት የማይሰማቸው አገልጋዮች የተሰበሰቡባት፣ ትሩፋት የሚሠራ አይደለም የታዘዘውን የሚፈጽም የታጣባት፣ ለሚያያቸው ዕረፍት የማይሰጡ ያልተገሩ ሠራተኞች የሞሉባት፣ ለእግዚአብሔርና ለአገር ሕግ የማይገዙ የተከማቹባት፣ ሲያስቧቸው ብርድ ብርድ የሚሉ ሥርዓት አልበኞች የነገሡባት ስፍራ ሆናለች፡፡
መንፈሳዊት ተቋም የሆነችው ቤተ ክርስቲያን ከመንፈሳዊነት አቋም ወጥታ ድርጅታዊ ሥርዓትን እንኳ አለማግኘቷ ያሳዝናል፡፡ የሥርዓት መገኛ ሥርዓት ስታጣ፣ የፍርድ ሰባኪ ፍርድ የለሽ ስትሆን፣ የነፍሶች ሰብሳቢ በታኝ ስትሆን፣ የራእይ መውጫ ራእይ ሲጨልምባት፣ የነገሥታት መካሪ በነገሥታት ስትመከር፣ ለገዛ ሕገ መንግሥቷ ለመጽሐፍ ቅዱስ አልገዛ ስትል፣ የኃጥአን መጠጊያ ሳትሆን የኃጢአት መለማመጃ ስትሆን፣ መሪዋን ክርስቶስን ለመስማት እምቢ ስትል እያየን ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን በረት ሆነች ያሉት እኒያ አባት የታያቸው እውነት መሆኑን እያየን ነው፡፡
በጸጋ የተመሠረተች ቤተ ክርስቲያን በሕግ የምትከራከርና የምትካሰስ ስትሆን፣ ሁሉን ትተናል መስቀል ተሸክመናል የሚሉት አገልጋዮችዋ ሁሉን ይዘናል፣ መስቀል ጥለናል የሚሉ ቅምጥሎች ሲሆኑባት እያየን ነው፡፡ ዓለምን ሰልችተው የሚመጡ ምእመናን ዓለምን በቤተ ክርስቲያን ሲያገኙ፣ ቤተ ክርስቲያንም የዓለምን መመሪያ የምትፈልግ ስትሆን፣ እንደ ቃሉ ሳይሆን እንደ ዘመኑ ለመኖር ስታቅድ ማየት፣ የተጣሉትን የምታስታርቀው በገላጋይ ስትኖር፣ ዓለምን በቅድስና ውበቷ የምትማርከው በዓለም ስትማረክ ማየት ያሳዝናል፡፡ የትዕግሥት አምላክ በትዕግሥቱ ቤተ ክርስቲያንን እየጠበቃት ነው፡፡ ትዕግሥቱ ካልገባት በዓለም ፊት የምትቀጣበትና የውስጥ ልብስዋ ተገልጦ የምትገረፍበት ዘመን ቅርብ ነው፡፡ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በታላቅ ትዕግሥቱ እያያት ነው፡፡ እርሱ በፍርድ የተነሣ ቀን ግን በትሩ እስኪያልቅ ይቀጣታል፡፡
“የወፍ ዘፈን አውራጁ አይታወቅም” እንደሚባለው መደማመጥ የሌለባት፣ ሁሉም በየአቅጣጫው የሚዘፍንባት፣ ሕዝቡን እንደ ቅርጫ ከፋፍሎ የሚበላባት የጠላት ቤት ሆናለች፡፡ እኒያ ጭምት ልጆችዋ ከአደባባይዋ ርቀው፣ አመንዝሮችና ቀማኞች አለሁ አለሁ የሚሉባት፣ አንድ ሐሰተኛ ሲነቀል ሁለት የሚበቅልባት፣ በእውነት ቃል ሳይሆን በአፈ ጮሌነት የሚኖርባት … የእውነትን ሚዛን የጣለች ቤት ሆናለች፡፡ ለዚህ ሁሉ የሚቆጭ የለም፡፡ በክፋት ከመወዳደር በቀር የእግዚአብሔር ቤት ንጹሕ ይሁን ብሎ የሚቆረቆር ቢጠፋም ቤቱን የማይተው ጌታ ግን ይነሣል፡፡ ያልገመትነውንና ጆሮአችን ያልጠበቀውን ቍጣ እናያለን፣ እንሰማለን፡፡ ይህ ጊዜ የእግዚአብሔር የትዕግሥቱ ጥላ የተዘረጋበት ነው፡፡ የታጠፈ ቀን ግን የመዓቱን እሳት፣ የቍጣውን በረዶ አንችለውም፡፡ እግዚአብሔር መቀጣጫ እንድንሆን አድርጎ ይቀጣናል፡፡ እርሱ ከታሪካችን ርዝመት ጋር ጉዳይ የለውም፡፡ የዛሬን መታዘዛችንን ያያል፡፡ የማያምኑትን ከቀጣ አውቀው የሚያጠፉትንማ በደንብ ይቀጣል፡፡ ዛሬ የኮራንበት ካባ አልሠራንበትም ነገ እናፍርበታለን፡፡ እግዚአብሔር ከጣለን የሚያነሣን የለምና ዛሬ የምናከማቸው ሀብት አይረባንም፡፡ እግዚአብሔር ምንም ቢሆን ጥሎ አይጥለንም ብለን በባዶ የኮራንበት ቃልም አይጠልለንም፡፡ እርሱ እግዚአብሔር የሚያከብሩትን የሚያከብር፣ የናቁትን የሚንቅ ነው /1ሳሙ. 2፡30/፡፡ እንኳን እኛን እስራኤልን የጣላቸው ባለመታዘዝ ነው፡፡ ኃጢአት ትንቢት የተነገረለትን፣ ሱባዔ የተቆጠረለትን የሰሎሞንን መቅደስ አፍርሷል፡፡
ታዲያ ጥሎ አይጥለንም እንዴት ማለት እንችላለን? የኮራንበት የጦር መሣሪያም አያድነንም፡፡ እንኳን የእኛ መሣሪያ ኒውክለር የታጠቁም ከቍጣ አያመልጡም፡፡ ታላቅ ሕዝብ ነህ እያልን አመንዝራውንና ነፍሰ ገዳዩን ተከታያችንን አድንቀናል፡፡ ያው ሕዝብ ግን ይበላናል፡፡ ያላስተማርነው ሕዝብ ጠላት መሆኑን የምናይበት ዘመን ቀርቦአል፡፡ የማይሞላው ከረጢታችን ዘላለማዊ እሳት ይበላዋል፡፡ የመበለቶችን ቤት የዘረፍንበት፣ ወጣቶችን ያስነወርንበት፣ የድሆች ልጆችን ጉሮሮ የዘጋንበት፣ በመማፀኛ ዘመን ወገናችንን አውጥተን የጣልንበት፣ በወገናችን ሞት የተሠረግንበት፣ በጭንቁ የሳቅንበት፣ ትዳርን ያፋታንበት፣ እስቲ ይህን ሕዝብ ልጩህበት ያልንበት፣ እንደ አማልክት ውዳሴና ስግደት የተቀበልንበት፣ እግዚአብሔር ካለ ይህን ያድርግ ያልንበት፣ ወገንና ወገን ሲተላለቅ እንደሌለ ሆነን የተቀመጥንበት፣ ንጹሐንን የገደልንበት፣ ወንጌልን የገፋንበት፣ እውነትን የቀበርንበት … ያ የእርም ጽዋችን ሞልቷልና እግዚአብሔር ይነቅለናል፡፡ ቍጥቋጦ ሳይቀረን ከሥራችን ይፈነቅለናል፡፡ ያን ቀን የቀድሞ ወዳጆቻችንን እንፈልጋለን፡፡ እነርሱ ግን ከጠላት ይልቅ ይከፉብናል፡፡ ያን ቀን ያጠራቀምነውን ገንዘብ እንፈልጋለን፡፡ ለአንድ ቀን መታከሚያም አይሆነንም፡፡ ያን ቀን ወንጌል የቱ ነው? አሁንም ሰብከን እንብላ እንላለን፣ ጆሮ ግን ይከዳናል፡፡ ያን ቀን መንግሥት እንኳ ጥግ ይሁነን እንላለን፣ እንደ አጸያፊ ቆሻሻም እንጣላለን፡፡ ያን ቀን ሠርጋችንን አጅቡት እንላለን፣ የልቅሶ ያህል አይደምቅም፡፡ ያን ቀን ማዘዝ እንፈልጋለን ቃላችን ግን ይቀላል፡፡ ዛሬ ያለነው የመጨረሻው መጀመሪያ ላይ ነን፡፡ አስማት ጥንቆላችን፣ ብዙዎችን ያሳበድንበት መተታችን ያለ ያዢ አብደን በአደባባይ ያሽከረክረናል፡፡ የሚያዝንልን አጥተን ያለ ታዛቢ እንቀራለን፡፡ ይህ አገልጋዮች ነን ለሚሉ ሁሉ የተደገሰ ድግስ ነው፡፡ ንስሐ በማይገቡት ላይ እግዚአብሔር ይህን መዓት ያፈስሳል፡፡ ትዕግሥቱ ይህ ሁሉ እንዳይመጣ ነበር፡፡ የትዕግሥቱ ምሥጢር ካልገባን የመዓቱን ሰይፍ እንጎርሳለን፡፡ እፈራለሁ ከቀድሞ ይልቅ ዛሬ እፈራለሁ፡፡ እግዚአብሔር ትዕግሥቱን ሲያሰፋ ይበልጥ እፈራለሁ፡፡ ካልተመለስን ጥበብ፣ ጉልበትና ሀብት የማያልፋት ብርቱ ቀን መጥታብናለች፡፡
የጠፋው እረኛ ብቻ አይደለም በግም ጠፍቷል፡፡ የምንመራው በአብዛኛው በግ መሳይ ነው፡፡ ሲሰክር አድሮ ጠዋት ጠበል የሚጠጣ፣ ሲያመነዝር አንግቶ ማለዳ ቅዳሴ የሚገኝ፣ ለሃይማኖቴ እገድላለሁ የሚል ለሃይማኖቱ ግን የማይሞት፣ ለእምነቱ የማይኖርላት ግን ሲሳደብላት የሚወል፣ ቅበላና ፋሲካን በኃጢአት የሚፈጽም ጾመኛ መሳይ፣ በመድረክ ሳይሆን በሕይወቱ ድራማ የሚሠራ፣ ከዘረፈው ላይ ዓሥራት የሚያወጣ፣ ቆርቦ የሚያብድ፣ አምኖ የማያምን፣ ሠራተኞቹን እያስጨነቀ ቀሳውስትን የሚቀልብ፣ ድንበር እየገፋ አቤት አቤት እያለ የሚጸልይ፣ ጋራ ጋራውን ጠንቋይ ፍለጋ ሲያስስ አድሮ ጠዋት ለኪዳን የሚደርስ፣ እጁ በደም ተጨማልቆ ቤተ ክርስቲያን የሚያንፅ፣ የንስሐ ስብከት የሚወድ ንስሐን ግን የማይወድ፣ ሰባኪ ቀላቢ ወንጌል ተቃዋሚ፣ ለስድብ አጨብጫቢ ለእውነት አጉረምራሚ፣ ሕይወት ሲነገር የሚያንቀላፋ የሰው ነውር ሲወራ የሚነቃ፣ በለው የሚል ድምፅ የሚፈልግ ጦረኛ፣ ማንበብ የማይወድ የነገሩትን ብቻ የሚሰማ፣ እስኪሞላለት የቤተ ክርስቲያን ወዳጅ ከሞላለት በኋላ ኵሩ፣ ዛሬን ለመርካት ስበኩኝ የሚል ዘላቂ ሕይወትን የማይሻ፣ ከእግዚአብሔር ርቆ አገልጋይ በመወዳጀት እድናለሁ የሚል፣ የመንገዱን ካርታ ጥሎ የሚንከራተት፣ ተረኛ ብልጥ እንደ ዘረፈው የሚኖር፣ ታላቅ ሕዝብ እያሉ የሚያሳንሱትን አወዳሾች የሚሸልም፣ ተመለስ ያለውን የሚወግር፣ እውነተኞችን ጥላሸት የሚቀባ፣ የአሉ ተከታይ የወሬ አንጋሽ፣ ከነሕመሙ ቤተ ክርስቲያን መጥቶ ከነሕመሙ የሚመለስ፣ የዋህ ሳይሆን ሞኝ የሆነ አማኒ ይዘናል፡፡ ይህ በአንድ ቤተ ክርስቲያን ብቻ ሳይሆን በየአብያተ ክርስቲያናቱ እየፈላ ያለ ሞገደኛ ወገን ነው፡፡ ንስሐ ካልገባ ይህ ወገን ብርቱ ቅጣት ይጠብቀዋል፡፡ መከራን እንደተለማመደ የሚኖር፣ አሁን ያለው መከራ ሳይደንቀው የሚመጣውን መከራ የሚናፍቅ ደንዳና ሕዝብ ይዘናል፡፡ የትዕግሥት አምላክ ዝም ያለን ሥራችን ተስማምቶት አይደለም፡፡ ለንስሐ ጊዜ እየሰጠን ነው፡፡ ራሳችንን የምናይበት ቍርጥ ጊዜ ቢኖር አሁን ነው፡፡ ስለዚህ ንስሐ እንግባ፡፡
በዓመት ውስጥ ባሉት ሦስት መቶ ስድሳ አምስት ቀናት ጸሎት፣ አገልግሎት እንፈጽማለን፡፡ ይህ በሌላው ዓለም የሌለ የታደልነው ሀብት ነው፡፡ ነገር ግን ፍቅር የሌለው ጸሎት፣ ቅድስና የሌለበት ቅዳሴ፣ መታዘዝ የሌለበት አገልግሎት ስለሆነ ይሄው አልተባረክንም፡፡ ተገልጋዩ ግዳጅን ለመፈጸም ያህል ወደ ቤተ ክርስቲያን ይመጣል፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር የናፍቆት ፍቅር የለውም፡፡ አገልጋዩ ለእንጀራ ይጮኻል፡፡ ከሚሰማው አምላክ ጋር አይነጋገርም፡፡ ልማድ እንዳይቀር ስለምናደርገው ጸልየን ለምን መልስ አጣን? ጾመን ለምን አልተባረክንም? ቀድሰን ለምን ጸጋ አልፈሰሰልንም? አገልግለን ለምን አላፈራንም? ብለን ራሳችንን ለመጠየቅ ጊዜ የለንም፡፡ ግን የተለመደው እንዳይቋረጥ ሕይወት የሌለውን ሥነ ሥርዓት፣ ቅዱስ ፍርሃት የሌለበትን ጸሎት፣ ተመስጦ የሌለበትን ዜማ፣ መገዛት የሌለበትን ቅኔ እናቀርባለን፡፡ ከሚሰማን አምላክ ጋር እየተነጋገርን መልስ አጥተን ዘመናት አልፈዋል፡፡
እግዚአብሔር ከመሥዋዕት በፊት መታዘዝን ይፈልጋል፡፡ የእኛ የሆነውን ከመስጠታችን በፊት ራሳችንን እንድንሰጠው፣ ከአገልግሎት በፊት እንድናውቀው ይሻል፡፡ እኛ ግን ኑሮአችን ይዞታ ማስከበር እንጂ የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ መናኘት አይደለም፡፡ ሕዝቡን ባለማወቅ መጋረጃ ጋርደን መፍረድ የምንፈልግ ቃልቻዎች እንጂ ሰብከን የምንለውጥ አገልጋዮች አልሆንም፡፡ ሕዝቡም ጧፍና ዕጣኑን አምጥቷል እርሱ ግን አልመጣም፡፡ የቤተ ክርስቲያን ደጃፍም ያዘነውንና የተከፋውን ለመቀበል ሳይሆን ብርና ወርቅ ለመቀበል ተከፍተዋል፡፡ ጴጥሮስ ብርና ወርቅ የለኝም ያለኝን ግን እሰጥሃለሁ ብሎ ሽባውን ፈወሰ /የሐዋ. 3፡6/፡፡ ዛሬ ግን ቤተ ክርስቲያን ብርና ወርቅ የለኝም አትልም፡፡ ግን የሥጋና የነፍስ በሽተኞች አይፈወሱም፡፡
እየዘመርን እንሰዳደባለን፣ ተጣልተን እንቆርባለን፣ ለወንድማችን ጉድጓድ እየቆፈርን አቤት አቤት እንላለን፡፡ እግዚአብሔር አዝኖብናል፡፡ እርሱን የሰው ያህል እንኳ ስላላከበርነው፣ ቤቱንም የቤታችንን ያህል እንኳ ስላላከበርን እግዚአብሔር ተቀይሞናል፡፡ ዛሬ የመዓቱን ሰይፍ በቁጣው ሰገባ ስለተያዘልን እንዝናናለን፡፡ ሰይፉ የተመዘዘ ቀን ግን የደሙ ምልክት እንጂ ገንዘባችን አያድነንም፡፡ እያደረግን ያለነው እግዚአብሔር ከቻለ ይፍረድብን የሚል ድፍረት ነው፡፡ ግን መከራውን ባንጎትተውም ሊወርድ ነው፡፡
እምነታችንን የያዝነው ለፉክክር እንጂ ለሕይወት አይደለም፡፡ ሌሎች ሲሰብኩ እንሰብካለን፣ ካልነኩን በእንቅልፋችን ራሳችን እንሞታለን፡፡ ሲነኩን በወንድነት ሃይማኖትን ለማስከበር እንነሣለን፡፡ “የእንጦጦ መምህር ቢናገር ባመት፣ ያውም እሬት” እንዲሉ፡፡ በንጹሕ ልብ መጸለይ አልሆነልንም፡፡ አገር ለአገር በመዞር እግዚአብሔርን የምናገኘው ይመስለናል፡፡ እርሱ ግን በንጹሕ ልብ እንጂ በፈጣን እግሮች የሚገኝ አይደለም፡፡ ጸሎታችንም ጉባዔ ወይም ለታይታ እንጂ ከእግዚአብሔር ጋር ለመገናኘት አይደለም፡፡ ድንጋይ ውርወራ ስንጀምር፡- “ኃይል የእግዚአብሔር ነው” በሚል ዝማሬ በመሆኑ ምን ያህል እንደማናስተውል ይታያል፡፡ በእውነት የምናምነው ኃይል የእግዚአብሔር ነው ብለን ነው? ታዲያ ዓመፁ ከየት መጣ? “የአምልኮት መልክ አላቸው ኃይሉን ግን ክደዋል” /2ጢሞ. 3፡5/ የሚለው ቃል ደርሶብናል፡፡ ስብከቱ፣ ዝማሬው ቢበዛም የእኛ ደንዳናነት ግን አልተፈረካከሰም፡፡ እዩኝ እዩኝ የሚል ክርስትና እንጂ የሚታይ ክርስትና የለንም፡፡ በሕይወታችን ነውር የሸሹንን በስብከታችን ለመመለስ የምንጥር ሞኞች ነን፡፡ ስብከት ሲጠፋን እንሳደባለን፡፡ የተጨነቀውን ሕዝብ በማስፈራራት እንዘርፋለን፡፡ የጠላነውን ሰው ታርጋ ሰጥተን ቅንዓታችንን የሃይማኖት ካባ እናለብሰዋለን፡፡ ቁመናችንን እንጂ የክርስቶስን መልክ ልናሳይ አልቻልንም፡፡ የልብሳችን ሽቱ እንጂ የሕይወታችን መዓዛ ሊያውድ አልቻለም፡፡ አጥንተን እንጂ ኖረን መናገር አልሆነልንም፡፡ ለምንዝርናችን ድንበር ብናሳጣውም የእግዚአብሔር ቁጣ ግን ሊገድበው ነውና ፈጥነን ንስሐ እንግባ፡፡ በዘርፋፋው ቀሚሳችን ሳይሆን በተትረፈረፈው ክርስትናችን፣ በነጭ ነጠላችን ሳይሆን በነጭ ልባችን የትዕግሥትን አምላክ ደስ እናሰኘው፡፡ ቃሉ፡- “እግዚአብሔር የእውነት ዳኛ ነው ኃይለኛም ታጋሽም ነው፤ ሁልጊዜም አይቆጣም፡፡ ባትመለሱ ግንሰይፉን ይስላል” /መዝ. 7፡11-12/ ይለናል፡፡ ትዕግሥቱ ለንስሐ ነው፡፡ ንስሐ መግባት እስከ ዛሬ ለታገሠው ትዕግሥቱ ክብር መስጠት ነው፡፡
እግዚአብሔር የንስሐና የፍቅርን መንፈስ ያድለን!
Tuesday, July 2, 2013
የአደባባይ የብልግና ቧልት በሕጉ እንዴት ይታያል? የ"Big Brother" ተዋናያን ከሕግ ዕይታ
የዛሬው ጽሑፍ የሚያጠነጥነው በወንጀል ሕግ ዙሪያ ነው፡፡ የወንጀል ሕግና የኅብረተሰቡ የሞራል አስተሳሰብ የጠበቀ ቁርኝት አላቸው፡፡
በአብዛኛው በኅብረተሰቡ እንደ ኃጢአት ወይም ነውር የሚቆጠሩ ድርጊቶች በወንጀል ሕግም የሚያስጠይቁ ናቸው፡፡ አመንዝራነት፣ ስርቆት፣ ስድብ፣ ግብረ ሰዶም ወዘተ. ኃጢአት ወይም ነውር ብቻ ሳይሆኑ ወንጀልም ተደርገው በወንጀል ሕጉ እንደሚያስቀጡ ተመልክቶ እናገኛለን፡፡ ይሁን እንጂ ኃጢአት ወይም ነውር የሆነ ድርጊት ሁሉ ግን ወንጀል ላይሆን ይችላል፡፡ ዝሙት አዳሪነትን ለዓብነት ብንመለከት ድርጊቱ ኃጢአት ወይም ነውር መሆኑ ባያጠያይቅም፣ በወንጀል ሕጋችን በመርህ ደረጃ የወንጀል ኃላፊነት የማያስከትል ድርጊት ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ የወንጀልና የኃጢአት ግንኙነት ስፋት እንደ ኅብረተሰቡ የሞራል አስተሳሰብ የሚለያይ ስለሚሆን በሁሉም ዘንድ ተመሳሳይ መግባባት ላይኖር ይችላል፡፡
እ.ኤ.አ. በ1957 በእንግሊዝ ሕግ ግብረ ሰዶም ሊኖረው የሚገባውን ቦታ በተመለከተ በጊዜው የቀረበው ሪፖርት (The Wolfeden Report) ሕግ የኅብረተሰቡን የሞራል አስተሳሰብ የማስከበር ወሰኑን በተመለከተ አከራካሪ ጽንሰ ሐሳቦችን አንስቷል፡፡ በዘመናት የሕግና የሞራል ግንኙነት የሚታዩበት ሁኔታ እየሰፋ ቢመጣም፣ በጊዜው በሪፖርቱ ተነስተው ሙግት የተደረገባቸው ግራና ቀኝ አስተሳሰቦች አሁንም አከራካሪነታቸውን አልለቀቁም፡፡ በሪፖርቱ እንደተገለጸው የሕግ ዓላማ የሕዝብን ሥርዓትና መልካም ሥነ ምግባር በማስጠበቅ ዜጎቹን ከሚጎዳ ነገር፣ ከብልግና እንዲሁም ከጥቃት መከላከል መሆኑ ተሰምሮበታል፡፡ ሆኖም ‹‹ሕጉ ይህንን ዓላማውን በማስፈጸም ሰበብ በግለሰቦች ግላዊ ሕይወት ጣልቃ በመግባት ወንጀልና ኃጢአት አንድ እስኪሆኑ ድረስ በሞራል አስተሳሰብ ላይ አቋም መውሰድ የለበትም፤›› ይላል ሪፖርቱ፡፡ ይህን መሠረት በማድረግ ሪፖርት አቅራቢው በእንግሊዝ ሕግ ግብረ ሰዶም በአደባባይ ሲፈጸም እንጂ በፈቃድ በግል ሕይወት (In private) ሲፈጸም እንደዝሙት አዳሪነት ሁሉ ወንጀል ሊሆን አይገባም የሚል ሐሳብ አቅርበዋል፡፡
ሪፖርቱን በመቃወም ሕግ የኅብረተሰብን ሞራል ሊያስከብር የሚገባበትን ሁኔታ ሰር ፓትሪክ ዴቭሊን በዝርዝር አቅርበዋል፡፡ እንደእርሳቸው አመለካከት፣ ኅብረተሰብ ሕግን እንደ መሣሪያ በመጠቀም የዜጎቹን ድርጊት መልካም ወይም ጎጂ በማለት የመፈረጅ ሥልጣን አለው፡፡ መንገደኛ ሰው (Reasonable man) ሥነ ምግባርን በተመለከተ የሚሰጠው አስተያየት ኅብረተሰቡን የሚወክልና ሕጉ ጥበቃ ሊሰጠው የሚገባ ስለመሆኑ ምሁሩ ይገልጻሉ፡፡ በዴቭሊን አስተሳሰብ ‹‹What makes a society of any sort is community of ideas, not only political ideas but also ideas about the way its members should behave and govern their lives, these latter ideas are its morals.››
ስለዚህ ሕግ የግለሰብን ነፃነት የመጨረሻው ጥግ ድረስ ሲጠብቅ የኅብረተሰቡንም ህልውና ለቅፅበት ሳይዘነጋ መሆኑን ምሁሩ ይገልጻሉ፡፡ ይህንን መሠረት በማድረግም አገርን መድፈር ወንጀል ሆኖ የሚያስጠይቀውን ያህል በግልም ሆነ በአደባባይ የሚፈጸም ግብረ ሰዶም በወንጀል ሊያስጠይቅ ይገባል፡፡ የሁለቱም ዓላማ የኅብረተሰብን ህልውናና ቀጣይነት ማረጋገጥ በመሆኑ፡፡
ጸሐፊው ይህን ክርክር በመግቢያነት የተጠቀመው ያለ ያለምክንያት አይደለም፡፡ አገራችን ሁለተኛውን ዘመናዊና የተደራጀ የወንጀል ሕግ እ.ኤ.አ. በ1957 ዓ.ም. (ከ1930 በኋላ ማለት ነው) ስታወጣ፣ እነዚህ አስተሳሰቦች በወቅቱ ተፅዕኖ ስለማድረጋቸው ስቴቨን ሎዌንስቲን ስለ ኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ ጥናት እንዲረዱ ባዘጋጁት መጽሐፍ ላይ ገልጸውታል፡፡ በ1997 ዓ.ም. የወጣው አዲሱ የወንጀል ሕግ እ.ኤ.አ. በ1957 ዓ.ም. የወጣውን የወንጀል ሕግ የተካ ሲሆን፣ ወንጀልና የሞራል እሳቤዎችን ግንኙነት በማስቀመጥ ረገድ ከሞላ ጎደል ተመሳሳይ ይዘት አላቸው፡፡ በወንጀል ሕጋችን የኅብረተሰቡን የሞራል አስተሳሰብ የሚያስጠብቁ የተለያዩ ድንጋጌዎች ተቀምጠዋል፡፡ ግብረ ሰዶም በአደባባይም ይፈጸም በግል፤ በሴትም ይፈጸም በወንድ በወንጀልነት ተፈርጆ በጽኑ እስራት የማስቀጣቱ ነገር አንዱ ማሳያ ነው፡፡ አመንዝራነት፣ አስገድዶ መድፈር (አንቀጽ 620) በእንስሳት ላይ የግብረ ሥጋ ግንኙነት መፈጸም (አንቀጽ 633)፣ በዘመዳሞች መካከል የሚፈጸም ግብረ ሥጋ (654) በሕጋችን ከሞራል አመክንዮ አንፃር በወንጀልነት መፈረጃቸውን ልብ ይሏል፡፡ ያም ሆኖ በ1997 ዓ.ም. የወጣው አዲሱ የወንጀል ሕግ ሞራላዊ እሴቶችን በመጠበቅ ረገድ የተወሰኑ ክፍተቶች አሉበት፡፡ በዚህ ጽሑፍ ከእነዚህ ወንጀሎች ክፍል የሚመደበውን በመልካም ጠባይ ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን በሰሞኑ ከሚነሱ ነጥቦች አንፃር በመቃኘት የሕጎቻችንን አቋም ለመፈተሽ እንሞክራለን፡፡
በአደባባይ የሚፈጸም ብልግና
በወንጀል ሕጉ በአደባባይ የሚፈጸም ብልግና በግልጽ ተደንግጓል፡፡ ግለሰቦች በአደባባይ ብልግና ለመፈጸም ቢፈልጉ እንኳን ሕጉ አይፈቅድላቸውም፡፡ ሕጉ ከግለሰቦች ነፃነት ይልቅ የኅብረተሰብን ሞራል የመጠበቅ ዓላማ አለው፡፡ ይህን መሠረት አድርጎ የወንጀል ሕጉ አንቀጽ 639 ‹‹ማንም ሰው አስቦ ሕዝብ በሚያዘወትርበት ቦታ ወይም በሕዝብ ፊት የግብረ ሥጋ ድርጊትን ወይም ለመልካም ጠባይ ወይም ለመልካም ሥነ ምግባር በብርቱ ተቃራኒ የሆነውን ማናቸውንም ሌላ ጸያፍ ድርጊት የፈጸመ ወይም በአኳኋን ያሳየ እንደሆነ ከሦስት ወር እስከ አንድ ዓመት በሚደርስ ቀላል እስራት ወይም ከአንድ ሺሕ ብር በማይበልጥ መቀጮ ይቀጣል፤›› ሲል ይደነግጋል፡፡ በዚህ ድንጋጌ መሠረት የተወሰኑ ነጥቦችን መመልከት እንችላለን፡፡
ድርጊቱ ብልግና መሆን አለበት
ብልግና የሚባለውን ሕጉ በግልጽ ለማመልከት ሞክሯል፡፡ በዋናነት የተጠቀሰው በሕዝብ ፊት የግብረ ሥጋ ግንኙነት መፈጸም ነው፡፡ ይህ የብልግናው ጥግ ሲሆን ከዚያ መለስ ለመልካም ጠባይ ወይም ሥነ ምግባር በብርቱ ተቃራኒ የሆኑ ድርጊቶችም ሊካተቱ ይችላሉ፡፡ የሕጉ የእንግሊዝኛው ቃል ‹‹Public indecency›› ‹‹Obscene act›› የሚሉ ቃላትን ስለሚጠቀም ማንኛውም ኅብረተሰቡ ከተቀበለው የሞራል አስተሳሰብ ጋር የማይሄድ ድርጊት (አካልን ማጋለጥ፣ ብልግናን በምልክት መግለጽ) ወዘተ. በወንጀሉ ሥር የሚወድቅ ይሆናል፡፡ በእንግሊዝኛው ትርጉም ‹‹Obscene›› የሚለው ‹‹Indecent›› ከሚለው ቃል የከበደ ከሥነ ምግባር ጋር የሚፃረር ጸያፍ ድርጊትን ይገልጻል፡፡ ቶም ሉዊስ የተባለ የእንግሊዝ የሕግ ምሁር የሁለቱን ድርጊቶች ልዩነት የፍርድ ቤት ጉዳይን በመጥቀስ በምሳሌ እንደሚከተለው ይገልጸዋል፡፡
‹‹It is easier to illustrate than define and illustrate it thus. For a male bather to enter the water nude in the presence of ladies would be indecent, but it would not necessary be obscene. But if he directed the attention of a lady to a certain member of his body his conduct would certainly be obscene››
በዚህ ገለጻ መሠረት ብልግናው የተለያየ ደረጃ ሊኖረው እንደሚችል ማሰብ ይቻላል፡፡ የብልግና ድርጊቱ ወንጀል እንዲሆን ፈጻሚው አስቦ ሊያደርገው የሚገባ ሲሆን፣ አፈጻጸሙም በድርጊት ወይም በአኳኋን በማሳየት ሊሆን ይችላል፡፡ በዚህ ረገድ በአገራችን አንዳንድ ባህሎች እርቃን መሄድ፣ በአደባባይ ግንኙነት መፈጸም፣ እንደ ባዕድ አገር መሳሳም ወዘተ. ለመባለግ ስለማይፈጸሙ በወንጀል እንደማያስጠይቅ መገንዘብ ይቻላል፡፡
የወንጀል ሕጉ አንቀጽ 640 እና 641 ተጨማሪ የብልግና ድርጊቶችን ይዘረዝራሉ፡፡ ብልግናው በጽሑፍ፣ በፊልም፣ በምሥል፣ በሥዕል፣ በቴአትር፣ በሲኒማ፣ በሬዲዮ፣ በቪዲዮ፣ በቴሌቪዥን ወዘተ. ጭምር ሊካተቱ ይችላሉ፡፡ እነዚህን ድርጊቶች የያዙ ነገሮችን ያዘጋጀ፣ ያስገባ፣ የሸጠ፣ ለሕዝብ ያሳየ፣ ያከራየ ወዘተ. ሁሉ በወንጀሉ ተጠያቂ ይሆናል፡፡ ያም ሆኖ ወሲብን ወይም ፍትወት ሥጋን ለመቀስቀስ ያልታሰቡ በባህሪያቸው በሞላ ሥነ ጥበባዊ፣ ሥነ ጽሑፋዊ፣ ወይም ሣይንሳዊ የሆኑ ሥራዎች እንደጸያፍ ወይም ለመልካም ጠባይ ተቃራኒ የሆኑ ድርጊቶች እንዲሆኑ ሊቆጠሩ አይችልም፡፡ (642) በወንጀሉና በተፈቀዱ ሥራዎች መካከል ያለውን መስመር የመለየት ኃላፊነት የዳኞች ይሆናል፡፡ በሌሎች አገሮች የዳበሩ አስተምህሮዎችና ትርጉሞች በመኖራቸው መለየቱ አስቸጋሪ ላይሆን ይችላል፡፡ በእኛ አገር ግን መስመሩን ማስመር ፈታኝና በዳኞች ግላዊ አተያይ ላይ መውደቁ አይቀርም፡፡ ወግ አጥባቂ የሆነ ሰው ጉዳዩን ከተመለከተው ልዩ ሁኔታው መጥበብ ካለበትም የበለጠ ሊቀጭጭ ይችላል፡፡
በሕዝብ ፊት ወይም ሕዝብ በሚያዘወትርበት ቦታ
የወንጀል ሕጉ አንቀጽ 639 ተፈጻሚ የሚሆነው የብልግና ድርጊቱ በአደባባይ ተፈጽሞ ሲገኝ ነው፡፡ ከሕዝብ ተሰውሮ፣ በግል ሕይወት የሚፈጸመውን ጸያፍ ድርጊት ሁሉ የመግዛት ሐሳብ ሕጉ የለውም፡፡ በዚህ ሰሞን በቢግ ብራዘር አፍሪካ የተነሳው የእውነታ ማሳያ (Reality show) ጉዳይ አከራካሪነቱ ከዚሁ የሚመነጭ ነው፡፡ በአንድ በኩል ጉዳዩ የተፈጸመው በግል ሕይወት (In private life) በመሆኑ በአደባባይ አልፈተጸመም የሚል ሙግት አለ፡፡ የዝግጅቱ ተሳታፊዎች በግል የሚኖሩትን እውነተኛ ሕይወት በአንድ የተገደበ ቦታ እንዲኖሩት ሁኔታዎችን ያመቻቸ በመሆኑ ብልግናው በሕዝብ ፊት የተደረገ አለመሆኑን በማንሳት ይከራከራሉ፡፡ ይህን የሚያራምዱ ወገኖች ተጠያቂነቱን ከፈጻሚዎቹ ወደ ነጋሪዎቹ (አሳይዎቹ) ያሸጋግሩታል፡፡ መጠየቅ ካለበት ለሕዝብ እንዲደርስ ያደረገው የመገናኛ ብዙኀን እንጂ ተሳታፊዎቹ አይደሉም ይላሉ፡፡ በሌላ በኩል ግን ተሳታፊዎች ላይ ማዕከል ያደረጉ ትችቶች በማቅረብ ለሕዝብ በቀጥታ እንደሚተላለፍ በታወቀ መርሐ ግብር የብልግናን ድርጊት መፈጸም ወንጀሉን በሕዝብ ፊት መፈጸም ነው ይላሉ፡፡ የቀጥታ ሥርጭቱ እያንዳንዱ ቤት በቴሌቪዥን፣ በኢንተርኔትና በሌላ መንገድ እንደሚደርስ አውቆ የሚፈጸመው በሕዝብ ፊት መፈጸሙን አውቆ ውጤቱን የተቀበለ ነው የሚል ሙግት አለ፡፡ እነዚህ ወገኖች ፈጻሚዎቹ ከመገናኛ ብዙኅኑ ጋር በጣምራ በኃላፊነት ሊያስጠይቅ ቢችል እንጂ አንዱን ወንጀለኛ ሌላው ነፃ አያደርገውም የሚል ሐሳብ ያቀርባሉ፡፡ ጉዳዩ በብሮድካስት አገልግሎት አዋጅ መሠረትም የሚታይበት ሁኔታ አለ፡፡ አዋጁ ከሞራል ጋር የሚቃረን መርሐ ግብር እንዳይተላለፍ የሚከለክል ድንጋጌ አለው፡፡ የአዋጁን አንቀጽ 30-31 ይመለከቷል፡፡
ብልግናው በሕዝብ በፊት ተፈጽሟል የሚል መደምደሚያ ላይ ቢደረስ እንኳን የወንጀል ኃላፊነቱ ከፍርድ ቤት ሥልጣን (Jurisdiction) ጋር የሚያያዝ በመሆኑ ተጨማሪ ሙግት ማስከተሉ አይቀርም፡፡ የወንጀል ሕጉ አንቀጽ 11 የወንጀል ሕጉን ጂኦግራፊያዊ አፈጻጸም ሲደነግግ ሕጉ ተፈጻሚ የሚሆነው ወንጀሉ በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ (በየብሱ፣ በአየሩና በውኃ አካላቱ) የተፈጸመ ሲሆን ነው፡፡ በዚህ መነሻነት የሰሞኑን ጉዳይ ከተመለከትነው በባዕድ አገር የተፈጸመ የብልግና ተግባር በኢትዮጵያ ስለሚዳኝበት አሳማኝ ነጥብ ማግኘት አስቸጋሪ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ሕጉ በልዩ ሁኔታ በኢትዮጵያ ላይ ከግዛቷ ውጭ የሚደረግ ወንጀል በኢትዮጵያ ሊታይ የሚችልበትን ሁኔታ በአንቀጽ 13 ቢደነግግም፣ ወንጀሎቹ በመንግሥት ደኅንነት፣ አንድነት፣ ተቋማት፣ ጥቅምና በገንዘቡ ላይ ለሚፈጸሙት በመሆኑ ለዚህ ጉዳይ አግባብነት አይኖረውም፡፡
የሆኖ ሆኖ ብልግናው ወይም ጸያፍ ተግባሩ በወንጀል እንዲያስጠይቅ በሕዝብ ፊት መፈጸሙ በአሳማኝ ሁኔታ ሊረጋገጥ የሚገባው ሲሆን፣ የተፈጸመውም በኢትዮጵያ ግዛት ሊሆን ይገባል፡፡ ይህ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ግን ውግዘት ካለ የሕግ ሳይሆን የባህልና የሞራል መሆኑ አይቀርም፡፡
የቅጣቱ ነገር
በአደባባይ የሚፈጸም ብልግና በቀላል እስራት ወይም በገንዘብ መቀጮ ሊያስቀጣ ይችላል፡፡ ቀላል እስራቱ ከሦስት ወር እስከ አንድ ዓመት የሚያስቀጣ ሲሆን፣ መቀጮው ከ1000 ብር አይበልጥም፡፡ ድርጊቱ የተፈጸመው አካለ መጠን ባልደረስ ልጅ ፊት ከሆነ ቅጣቱ ከስድስት ወር እስከ አምስት ዓመት የሚደርስ ቀላል እስራት ይሆናል፡፡ ሕጉ ያስቀመጠው ቅጣት በቀላል እስራት ወይም በመቀጮ በአማራጭነት መሆኑ ወንጀሉን ቀላል ያደርገዋል፡፡ በኅብረተሰብ ሞራል ላይ የተፈጸመ ጸያፍ የብልግና ወንጀል በ1000 ብር ብቻ እንዲቀጣ ማድረግ የሞራሉን ዋጋ ማሳነስ ነው፡፡ የፍትሐ ብሔር የሞራል ካሳ በ1952 የፍትሐ ብሔር ሕግ አንቀጽ 2116(3) መሠረት አንድ ሺሕ ብር ብቻ መሆኑ ሊደንቀን አይገባም፡፡ ከ50 ዓመት በፊትም አሁንም የሞራል ዋጋው አንድ ሺሕ ብር ብቻ መሆኑ ሕጉ ለሞራል ጥበቃ የሰጠውን አነስተኛ ቦታ አመላካች ነው፡፡
ወንጀል፣ ኃጢአት፣ ነውር
የሦስቱ ጽንሰ ሐሳቦች ግንኙነት በአገራችን ያለውን ትስስር በግርድፉ ለተመለከተ በጊዜ ሒደት ልዩነታቸው እየሰፋ መምጣቱን ያስተውላል፡፡ በድሮው ዘመን ሁሉም ኃጢአቶች ባይሆኑም አብዛኛዎቹ ነውሮች በወንጀልነት በሕግ የተፈረጁበት ሁኔታን እናስተውላለን፡፡ በአደባባይ የሚፈጸም የብልግና ወንጀል የሦስቱ ግንኙነት የሰመረበት መሆኑን መመስከር እንችላለን፡፡ ድርጊቱ ኃጢአትና ነውር ብቻ ሳይሆን ወንጀል ሆኖ ያስቀጣል፡፡ ሕግ የኅብረተሰቡን የሞራል ሁኔታ (Public morality) የሚያከብርና የሚያስከብር ሊሆን ይገባዋል፡፡ በመነሻችን እንደገለጽነው እንደ አንድ ማኅበረሰብ ያስተሳሰረን የፖለቲካ ውህደት ብቻ ሳይሆን የሞራል አስተሳሰብ ውህደት ነው፡፡ የሞራል መስፈርቶችን የሚሸረሽር ሕግ ከበዛ አብሮነታችንንም መሸርሸሩ አይቀርም፡፡ በዚህ ረገድ የወንጀል ሕጉ ግብረ ሰዶምን መከልከሉ፣ አመንዝራነትን ወንጀል ማድረጉ፣ ብልግናን መቅጣቱ ወዘተ. የሚያስመሰግነው ቢሆንም፣ በአሁኑ ወቅት የወጡ ሕጎች ሞራልን በመጠበቅ ረገድ ያላቸው ጥንካሬ የቀድሞውን ያህል መሆኑን መመስከር ዳገት መሆኑ አይቀርም፡፡ ጽንስ ማስወረድ መፈቀዱ (ወይም የመፈቀድ ያህል ላልቶ በሕጉ መካተቱ)፣ የአጎትና የአክስትን ልጅ ማግባት የሚፈቅድ የቤተሰብ ሕግ መፅደቁ፣ ማኅበራዊ ተቋም የሆነውን ጋብቻን በተራ ስምምነት ለማፍረስ የሚያስችል የሕግ መሠረት መጣሉ ወዘተ. የተወሰኑ ማሳያዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ጉዳዮች ከኅብረተሰቡ የሞራል አስተሳሰብ ጋር የተጣመሩ በመሆናቸው የሕጉ ዕውቅና ሲነፈጋቸው በኅብረተሰቡ ላይ የሚያመጣው አሉታዊ አስተዋጽኦ ነጋሪ አይፈልግም፡፡ አሁን አሁን የአገሮችን የሕግ ይዘት ታሪካቸው፣ ባህላቸውና የሞራል አስተሳሰባቸው ሳይሆን የሌሎች ተሞክሮ፣ በሰብዓዊ መብት ስም የሚገቡ ባዕድ ሐሳቦችና የገንዘብ ድጋፍ የሚወስናቸው መሆኑን በዕለት ተዕለት ኑሮአችን እናስተውላለን፡፡ የታወቀ የሞራል ኮድ የሌለው ሕዝብ ደግሞ የማይቀበለው ባዕድ ሐሳብ ስለማይኖር ጉዳቱ ሰፊ ነው፡፡
ስለዚህ ብልግናን የሚያወግዝ ሕግ መኖሩ የሕጉ ጥሩ ጐን ነው፡፡ ባህላቸውን ዘንግተው በአደባባይ ጸያፍ ድርጊትን ለሚፈጽሙ ተገቢ ዋጋ መዘጋጀቱን ሕጉ ያበስረናል፡፡ የቅጣቱ ማነስ አሳሳቢ ቢሆንም፣ የድንጋጌው መኖር ያጽናናል፡፡ የወንጀል ሕግ ተጠያቂነት ከኅብረተሰብ ውግዘት በላይ የሚታይ ተጨባጭ ውጤት አለው፡፡ ብልግናን ወንጀል ያደረገ ሕግ ግን ሌሎችንም ከኅብረተሰቡ ሞራል ጋር የሚቃረኑ ድርጊቶች ለመግዛት/ለማስተዳደር ጉልበት ሊያንሰው አይገባም፡፡ ለዝሙት አዳሪነት፣ ለጽንስ ማቋረጥ፣ በጋብቻ ላይ ጋብቻ ወዘተ. ትርጉም ያለው አቋም ቢያዝ ሕጉ ኅብረተሰባዊ መሠረት ይኖረዋል፡፡ አፈጻጸሙም በጥንቃቄ ሊጠናና ሊዳብር ይገበዋል፣ በየአደባባዩ አልፎ አልፎ የሚስተዋሉት ድርጊቶች ሃይ ባይ ይፈልጋሉ፡፡ (ምንጭ፤ ሪፖርተር)
ከአዘጋጁ፡- ጸሐፊው የሕግ ጠበቃና አማካሪ ሲሆኑ፣ በኢሜይል አድራሻቸው getukow@gmail.com ማግኘት ይቻላል፡፡
Monday, July 1, 2013
አልሸባብ በሶማሊያ ተሽመደመደ፤ ሼኽ ዳሒር ሃዌስ ተይዘዋል፤ አሸባሪነትን በመዋጋት ሲሞዳሞዱ የቆዩት ኢትዮጵያና አሜሪካ ወዴት ያመሩ ይሆን?
የአልሸባብ መሪዎች በራሳቸው ተዋጊዎች መገደላቸው ተሰማ። ከተገደሉት መካከል አንደኛው ያሉበትን ለጠቆመና ላጋለጠ አምስት ሚሊዮን ዶላር ጉርሻ እንደሚሰጥ የታወጀባቸው ነበር። የቪኦኤ የአማርኛው ክፍል በዘገበው ዜና መሰረት አልሸባብ በሶማሊያ እየተንኮታኮተ የመክሰም ደረጃ ላይ መድረሱን አመላካች ይመስላል።
አብዱልአዚዝ አቡ ሙስ አብ ባሠራጨው የድምፅ መልዕክት የሙጃሕዲኑ ታጣቂዎች በመካከላቸው መከፋፈልን ለመፍጠር ይጥሩ በነበሩ አባሎቻቸው ላይ ዘመቻ ካካሄዱ በኋላ የተወሰኑትን በቁጥጥር ሲያውል፣ እጅ ለመስጠት አሻፈረኝ ያሉ ነበሩ ብሏል። “ሁለቱ እጃቸውን እንዲሰጡ ሲጠየቁ አሻፈረን ብለው አንገራገሩ፣ በተኩስ መካከል ተገደሉ፤ አምላክ ነፍሳቸውን ይማርና በገነት ያስቀምጥ፡፡ ሃሣቡ እነርሱን ለመግደል አልነበረም፡፡ በቁጥጥር ሥር አውለን እሥልምና ችሎት ፊት ልናቀርባቸው ነበር” ሲል እስልምና ችሎት ፊት ሳይቀርቡ በተኩስ ልውውጡ ወቅት መገደላቸው እንዳሳዘነው መግለጹን የቪኦኤ ዜና ያስረዳል።
ሰዎቹ የተገደሉት ከሞቃዲሾ 350 ኪ.ሜ በስተደቡብ በምትገኝ ብራቫ የምትባል ከተማ ውስጥ እንደሆነ ታውቋል፡፡ የተገደሉት ሰዎች እነማን እንደሆኑ የአል-ሻባብ ቃል አቀባይ አልተናገረም፡፡ ይሁን እንጁ የቪኦኤ ሶማሊኛ አገልግሎት የተለያዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮችን አነጋግሮ በተለያዩ ስም የሚጠሩት የአልሸባብ አመራር መሞታቸውን አመልክቷል። በዚሁ መሰረት ኢብራሂም ሃጂ ጃማ ፣ ኢብራሂም አል-አፍጋን ፣ በተቀጥያ መጠሪያው አቡ ባካር አል-ዛይሊዪ እና ሼኽ አብዲሃሚድ ሃሺ ኦልሃዬ ወይም በቅፅል ስም ሞዐሊም ቡርሃን የተገደሉ መሆናቸውን አረጋግጧል፡፡
መሪዎቹ የተገደሉት የዛሬ አሥር ቀን ሰኔ 12 መሆኑንም የቪኦኤ ምንጮችን የጠቀሰው የሶማሊኛ አገልግሎት ዘገባ አመልክቷል፡፡የአል-ሻባብ ምንጮች እንደሚሉት አል-አፍጋን የተገደለው ከመስጂስ እየወጣ ሳለ በተተኮሰበት ተከታታይ ጥይት ሲሆን ሙዐሊም ቡርሃን የተገደለው ከቤቱ ተይዞ ከተወሰደ በኋላ ነው፡፡
ይህ አጋጣሚ ከተፈጠረ ከሁለት ቀናት በኋላ ለተገደሉት ሁለት ሰዎች የቅርብ ወዳጅ እንደነበረ የሚነገረው ዋነኛው የአል-ሻባብ መሪ ሼኽ ሐሰን ዳሂር አዌይስ ከአካባቢው በጀልባ በማምለጥ ማዕከላዊ ሶማሊያ ውስጥ ተይዞ እጁ ለመንግሥት አስረክቧል። ከተገደሉት አንዱ ኢብራሂም አል-አፍጋን በአል-ሻባብ ውስጥ በርካታ የሥልጣን ቦታዎች የነበሩት ሲሆን የቡድኑ ምክትል መሪ፣ የገንዘብ መምሪያው ኃላፊና የኪስማዮ ገዥ ሆኖ ሠርቷል፡፡ ተይዘው ለፍርድ እንዲቀርቡ ያሉበትን መረጃ ለሚሰጥ በእያንዳንዳቸው ራስ የአምስት ሚሊዮን ዶላር ጉርሻ እንደምትሰጥ ዩናይትድ ስቴትስ ማስታወቂያ ካወጣችባቸው ሰባት የአል-ሻባብ መሪዎች አል-አፍጋን አንዱ ነው፡፡
አል-አፍጋን ዩናይትድ ስቴትስ፣ ቨርጂንያ ውስጥ ይኖር የነበረ ሲሆን እአአ በ1980ዎቹ ውስጥ ከሙጃሕዲን ጎን ተሰልፎ ለመዋጋት ወደ አፍጋኒስታን መሄዱንና በ1991 ዓ.ም የሶማሊያ ማዕከላዊ መንግሥት ሲወድቅና ሥርዓተ-መንግሥቱ ሲፈራርስ እጅግ የከፋ ዓይነት ጂሃድ ወደ ሶማሊያ ማስገባቱና ሶማሊያ ውስጥ የመጀመሪያውን የጂሃድ ማሠልጠኛ ሠፈር ማቋቋሙን ዘገባዎች ይጠቁማሉ፡፡
አል-አፍጋን ከአል-ቃይዳው መሥራችና መሪ ኦሣማ ቢን ላደን ጋርም ብዙ ግንኙነቶች እና ንግግሮች እንደነበሩት ቢን ላደን በ2011 ዓ.ም ከተገደለ በኋላ ሲናገር ድምጹ ይሰማ እንደነበር ታውቋል፡፡ ሌላው ተገዳይ ሙአሊም ቡርሃን አል-ሻባብ ውስጥ ዋነኛ የሚባል የሃይማኖት ሊቅ እና የቡድኑ የመማክርት ምክር ቤት አባል እንደነበረ ተገልጿል፡፡
የአልሻባብ አመራር በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ ሲዳከም፤ ባለፉት በርካታ ዓመታት ኢህአዴግ የአሜሪካ ወዳጅ ነኝ በማለት እንዲሁም አሜሪካም “ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ ሸሪካችን ነች” በማለት ሲሞዳሞዱበት የነበረው አጀንዳ “በቀጣናው አሸባሪዎችን መዋጋት የሚል ነበር”፡፡ በተለይም እነ አቶ መለስ አልሻባብ የአልቃይዳ ስሪት ነው፤ አሸባሪነትን እንዋጋለን በማለት በአልሻባብ ስም የፈለጉትን የፖለቲካ ጥቅም ሲፈጽሙ ኖረዋል፡፡ ታዲያ ይህ የአልሻባብ መዳከም በዕቅድ የተከናወነ ይሆን? ወይስ የተበላበት ዕቁብ ስለሆነ ሌላ የታሰበ አዲስ ፕሮጄክት አለ? አልሻባብ ቁጥር 2 ወይም “ጸረ አሸባሪነትን መዋጋት ቁጥር 2”? ወይስ ፕሬዚዳንት ኦባማ በአፍሪካ ጉብኝታቸው ከምስራቅ አፍሪካ ኢትዮጵያን አለመምረጣቸው ጋር ተዳምሮ አሜሪካ ለምስራቅ አፍሪካ ድራማ አዲስ የፖለቲካ ጽፈ ተውኔት አዘጋጅታ ይሆን? መቆየት ደጉ ብዙ ያሳየናል!
Subscribe to:
Posts (Atom)





