Wednesday, July 20, 2016

የሰሜን ጎንደሩ ታጋይ አንጋው ተገኝ መልዕክት ከቂሊንጦ እስር ቤት – “ካሁን በኋላ ሽንታም አማራ አንባልም”

ቀጣዩ መልዕክት የመጣው በ እስር ላይ ከሚገኘው ታጋይ አንጋው ተገኝ ነው:: ታጋይ አንጋው በአሁኑ ወቅት በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ይገኛል:: የጎንደሩን ሕዝባዊ አመጽ ተከትሎ የሚከተለውን መል ዕክት አስተላልፏል:: እንደወረደ ያንብቡት::
ጀግናው የሰሜን ጎንደር የወልቃይት አማራ ሕዝብ ዘመዶቼ የአባቶችህ ታሪክ መድገምህ ካለሁበት ጠባቡ ክፍል ብንሰማ ቁጭ ብዬ ከጓደኞቼ ጋር አለቀስኩ ጀግናው የሰሜን ጎንደር ሰው ድሮም እናቀዋለን! ወገኔ ባንተ ትግል አሁን ለሀጫም ኣንባል! አሁን ሽንታም አማራ አንባልም! የድሮ ስርዓት ናፋቂ ሲሉን በማዕከላዊ አዋርዶ የሚገርፈን በፍርድ ቤት የምናለቅሰው ኣማራነት ማን እንደሆነ ዛሬ ጎንደር ሄዶ ማየት ይችላል፡፡ የጎንደር ሕዝብ የጀመረው ትግል ድንገት አይደለም ለዘመናት በኣማራ ላይ የታወጀበት የወያኔ እልቂት በሶት ያማጣው ቁጭት ነው፡፡
ቀድሞስ ትግላችን የነበረው ከዚህ ተነስተን አይደለምን? አዎ..ዛሬ ለመራር ትግል የተሰለፈነው እኛ ብቻ አይደለንም፡፡ ሁሉም ወገን ለነጻነት ለክብሩ የአባቶቹን ታሪክ ለመድግም ኣርበኛ ታጋይ ሆኗል፡፡ መላው ኣማራ የነጻነት አሸባሪ ተብሏል፡፡ በዚህ ግቢ ውስጥ ከሰሜን ጎንደር የመጣ ከ300 በላይ የኣካባቢው ተወላጅ ልቡ እናተው ዘንድ ይገኛል፡፡ በአማራ ስም እየነገደ የትግሬን የበላይነት የሚያስጠብቅ (ብአዴን) እደተጠበቀው ለህውሃት ያለው ሎሌነቱንና ታማኝነት ለአማራ ሕዝብ ያለውን ጠላትነትና ደም መጣጭነቱን በኣደባባይ በመግለጫው አረጋግጧል። የአማራ ሕዝብ ዛሬ በአንድነት ቆሞ ይህንን አስቸጋሪ ወቅት በብቃት መመከት ካልቻለ እንደትላንቱ የትውልዱን ጀግኖች በወራሪ አስበልቶ መቀመጥ ቀጣዩ ትውልድ ሀገር አለን ማለት አይታሰብም፡፡
ወገኔ ልብ በል በገዛ ሀገራችን እየተፈናቀልን ስንሰደድ ቆይተናል፡፡ ተፈጥሮ የለገሰን ርስታችን ተነጥቆ የጥቂት ቡድን የበዬ ተመልካች አድርገውናል፡፡ ተወልደን ባደግንበት ምድር ከፊት በህወሓት ሰራዊት ከጀርባች በሱዳን ድርቡሽ እያስገደሉን ሲጨፍሩ ብዙ ታዝበናል፡፡ አሁን ግን ነገሩ ተለውጧል እየገደሉ ማንቧረቅ እንግዲህ አበቃ… መሞትም እንዳለ ጀግናው ጎንደሬ ገድሎና ሞቶ አሳይቷል፡፡ ይሄን ሕዝብ አትነካኩት ብለን መክረን ነበር ሆኖም ግን የሚሰማን ጠፍቷል፡፡ እንግዲህ መንገዱን ለነሱም ጨርቅ ያድርግላቸው፡፡ አሁን የጎበዝ አለቃ ሁሉም አለው..ወገን አንድ ነገር መናገር እፈልጋለሁ፡፡
በተለይ የብአዴን አባላትና ደጋፊዎች የአማራን ሕዝብን በሥሙ እያስተዳደሩ በጥቂት ወረበላ ሲገደል ቆሞ ማየት ነገ የልጅ ልጆቻችሁ በኣማራ ምድር የታሪክ ውዳቂ ሆኖ እንደሚቀሩ መገንዘብ ያለባቸው ወሳኝ ጊዜ አሁን ነው፡፡ ይሄን ታላቅነት የሚመጥን የእዉቀትና የስነልቦና ልዕልና የተላበሰ የብአዴን አባል ስለመኖሩ በእርግጥ እጠራጠራለዉ፡፡ ግን ነገ ታፍሩበታላችሁ ይልቅ ከተበደለው በየጊዜው ከሚሞተው ምስኪኑ ወገናችሁ ጎን በመሰለፍ ታሪክ ስሩ መላው የአማራ ተወላጅ በውጪም በውስጥም በኣንድነት መቆም ጊዜው ያስገድዳል፡፡ ጎንደር ሲነሳ ጎጃም ወሎ የሸዋ ሰው መነሳት አለበት፡፡ ለሌውም ወገን በጋራ መሰለፍ ያስፈልጋል፡፡ ይሄ የነጻነት ትግል በሁሉም ስፍራ መቀጣጠል ይኖርበታል፡፡ የአማራ ሕዝብ የመኖር ያለመኖር የህልውና ጉዳይ መሆኑ መዘንጋት የለበትም፡፡

ድል ለሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ! (ኣንጋው ተገኝ)
ምንጭ (ዘ-ሐበሻ)

No comments:

Post a Comment