Monday, December 5, 2016

የ2016የወንዶች የእግር ኳስ ውድድር በስቮልቫር ቡድን አሽናፊነት በድል ተጠናቀቀ

በለፈው  ቅዳሜ ዕለት ማለትም 3/12/2016  በተደረገው  የመጨረሻው  የመዝጊያው  ውድድር  የስቮልቫር  ቡድን በዕለቱ ከተሳተፉት ቡድኖች ሁሉ የላቀ ቴክኔክ እና ዜዴ በመጠቀም ለተመልካቹና ለደጋፊው የተሻለ የኳስ ውበት የላቀ የጨዋታ የቡድን ስራውን በ አግባቡ በመጠቀም በማሳየት አስመስክሯል ይህም የሚያሳየው በቡድኑ ውስጥ የነበረውን የዲሲፒልን   የእርስበእርስ የመከባበር  የመመካከር  ውጤት ነው።

በ12/11/2016  በወቅቱ  የተሳተፉትን ቡድን  ለማስታወስ ያህል ስቮልቫር(Svolvær) ቬስትቮጋይ Vestvågøy ሎዲንገን Lødingen
በውድ ድሩ ወቅት ሶስቱ ሙታኮች Mottak ቡድኖቻቸውን በሁለት ግሩፕ በመክፈልGroup1 and Group2 በማለት ለውድድር እንዳቀረቡ የሚታወስ ነው በዛም ወቅት የስቮልቫር ሙታክ አብዛኛውን ጨዋታ እንዳሸነፈ የሚታውቅ ነው። 2016 SVOLVÆR TEAM PICTURE





 ወደ ትላንትናው ውድድር ስመለስ የተፎካካሪያችን ቡድኖች ቬስትቮጋይ VESTVÅGØY ባለፈው በ12/11/2016 እንዳሰለፈው ቡዱኑን በሁለት ግሩፕ በመክፈል ለውድድር አቅርቦል።

ውድ ድሩን በ አዲስ መልክ በመቀላቀል የተሳተፈው ዕድምያቸው ከ18ዓመት በታችየሆንቱን Under the age የቢሮ ሰራተኞች ቲም SVOLVÆR EM ANSATTE ከፍተኛ ግምት ከተሰጠው ቡድን አንዱ ነበር በተለይም በጠንካራ የኳስምትና የቦታ አሰላለፍ ጥሩ ተፎካካሪ ሆነው መልካም ጨዋታ አሳይተውን በሶስተኛ ደረጃነት በመውጣት ውድድሩን ፈፅመዋል።

ስቮልቫር በሶስት ግሩፕ በመከፈል ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ ነው የቀረበው።
 የመዝጊያው ጨዋታ የተካሄደው የሁለቱ የቡድን መሪዎች/አሰልጣኞች በስብሰባ በመሰማማት ከየግሩፑ ጥሩ የኳስ ብቃት 
አላቸው ብለው የመኑባቸውን ተጨዋቾችን በመምረጥ Beast player  በማቅረብ ከፍተኛ ወሳኝ እልህ የተቀላቀለበት ፉክክር በማድረግ እንደሚታወቀው በውድድር ሕግ የተሻልወና የበለጠው አሸናፊ ዋንጫውን ከፍ አድርጎ እንደሚስመው አይበገሪ አንበሳዎቹ The Lion Svolvær በአማረና የተመልካችን ቀልብ በመመሰጥ ያጠናቀቀው የኖርዌይ እግርኳስ ማሀበርNORGES FOTBALL FORBUND(THE FOOTBALL ASSOCITION OF NORWAY)(FAN) ያዘጋጀውን የወርቅ ሜዳልያ Mr Per Arne  በመሸለም አንገቱ ላይ አጥልቋል።3/12/2016 SVOLVÆR TEAM PICTURE




 በውድድሩ ወቅት ከተለያዩ ሀገሮች በስደት ኖርዌይ የሚኖሩ ተጨዋቾች በግልም ሆነ በቡድን ብቃታቸውን ያሳዩና ያስመሰከሩ
ወደፊትም ከፍተኛ ተስፋ የሚጣል ባቸው ታዳጊዎችም ጠንካራ ተጫዋቾችን አይተናል ይህ ደግሞ ትኩረት ተሰጥቶት
ደጋፊና በተለያየ አቅም የሚረዳቸው የሚንከባከባቸው ሰዎች ካገኙ ለሚረዳቸው አካልም ለግላቸውም በኳስ ጥበብ
ከፍተኛ ቦታ ይደርሳሉ።   Team VESTVÅGØY Picture 3-0 የተሸነፈው

በመጨረሻ ወደኔ ስመጣ ኳስ በመጫወት ቡድን በማሰባሰብና ፣በመስራት፣በመምራት ፣በመምረጥ አቅሜ የፈቀደውን
አስተዋፆኦ አበርክቻለው አድርጊያለው።

ከሁሉም በላይ ላመሰግን የምፈልገው ለዝግጅቱ መሳካት ሀላፊነቱን የወሰደውን አካል ወይም Sponsor የሆነን 
በዋንነት ለውጤቱ ማማርና መሳካት ከፍተኛ ጉልበታቸውን እና የኳስ ክህሎታቸውን ላሳዩን የተለያዩ ሀገሮች ዜግነት
ያላቸውን የ2016 የስቮልቫር ሙታክ ቡድን ወንድሞቼን የከበረ ልባዊ ምስጋናይኔ ከአንገቴ ጎንበስ በማለት አቀርባለው።
befiker09@gmail.com


Monday, September 19, 2016

ከቀድሞው የኢትዮጵያ የሀገር የመከላከያና የፖሊስ ሠራዊት አርበኞች ማህበር የተላለፈ ወቅታዊ ጥሪ


እኛ የቀድሞው የኢትዮጵያ የሀገር የመከላከያና የፖሊስ ሠራዊት ዓባላት ለአለፉት 25 ዓመታት በውድ የሃገራችን ሕዝብ ላይ በወያኔ ህውሃት መራሹ ቡድን እየተፈፀመ ያለውን ሰቆቃ ከሕዝባችን ጋር እየተመለከትን እስካሁን ዘልቀናል። ይሁን እንጅ የሕዝባችንን ሰቆቃና መከራ፣ ስደትና ዕልቂት ከምንም ባለመቁጠር ይባስ ብለው የሃገሪቷን ልዑላዊነት ለታሪካዊ ጠላቶቻችን አሳልፈው ለመስጠት ሽር ጉድ በማለት ላይ ይገኛሉ።
በኢትዮጵያ የረጅም ታሪክ ውስጥ የሃገሪቷን ዳር ድንበር ለባዕድ አሳልፎ ለመስጠት የተደራደረ መንግስት ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅም ፣ ሃገሩንና ድንበሩን እንዲጠብቅ አደራ የተሰጠውም ወታደርና የፖሊስ ሠራዊት የዚህ እኩይ ተግባር ተባባሪ የሆነበት ዘመን አልታየም።
ከሁሉም በላይ የህውሃት አቀንቃኝ ካድሪዎች በየጊዜው ከሚጎነጉኑት የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ የሃገሪቷን ታላላቅ ብሄረሰቦች እርስ በርስ በማናቆር የጥላቻ ዘር በማህከላቸው በመበተን ስልጣኑን ለማራዘም ሁነኛ መሳሪያ አድርጎት ይገኛል።
ምንጭ ዘ-ሐበሻ 

Wednesday, July 20, 2016

የሰሜን ጎንደሩ ታጋይ አንጋው ተገኝ መልዕክት ከቂሊንጦ እስር ቤት – “ካሁን በኋላ ሽንታም አማራ አንባልም”

ቀጣዩ መልዕክት የመጣው በ እስር ላይ ከሚገኘው ታጋይ አንጋው ተገኝ ነው:: ታጋይ አንጋው በአሁኑ ወቅት በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ይገኛል:: የጎንደሩን ሕዝባዊ አመጽ ተከትሎ የሚከተለውን መል ዕክት አስተላልፏል:: እንደወረደ ያንብቡት::
ጀግናው የሰሜን ጎንደር የወልቃይት አማራ ሕዝብ ዘመዶቼ የአባቶችህ ታሪክ መድገምህ ካለሁበት ጠባቡ ክፍል ብንሰማ ቁጭ ብዬ ከጓደኞቼ ጋር አለቀስኩ ጀግናው የሰሜን ጎንደር ሰው ድሮም እናቀዋለን! ወገኔ ባንተ ትግል አሁን ለሀጫም ኣንባል! አሁን ሽንታም አማራ አንባልም! የድሮ ስርዓት ናፋቂ ሲሉን በማዕከላዊ አዋርዶ የሚገርፈን በፍርድ ቤት የምናለቅሰው ኣማራነት ማን እንደሆነ ዛሬ ጎንደር ሄዶ ማየት ይችላል፡፡ የጎንደር ሕዝብ የጀመረው ትግል ድንገት አይደለም ለዘመናት በኣማራ ላይ የታወጀበት የወያኔ እልቂት በሶት ያማጣው ቁጭት ነው፡፡
ቀድሞስ ትግላችን የነበረው ከዚህ ተነስተን አይደለምን? አዎ..ዛሬ ለመራር ትግል የተሰለፈነው እኛ ብቻ አይደለንም፡፡ ሁሉም ወገን ለነጻነት ለክብሩ የአባቶቹን ታሪክ ለመድግም ኣርበኛ ታጋይ ሆኗል፡፡ መላው ኣማራ የነጻነት አሸባሪ ተብሏል፡፡ በዚህ ግቢ ውስጥ ከሰሜን ጎንደር የመጣ ከ300 በላይ የኣካባቢው ተወላጅ ልቡ እናተው ዘንድ ይገኛል፡፡ በአማራ ስም እየነገደ የትግሬን የበላይነት የሚያስጠብቅ (ብአዴን) እደተጠበቀው ለህውሃት ያለው ሎሌነቱንና ታማኝነት ለአማራ ሕዝብ ያለውን ጠላትነትና ደም መጣጭነቱን በኣደባባይ በመግለጫው አረጋግጧል። የአማራ ሕዝብ ዛሬ በአንድነት ቆሞ ይህንን አስቸጋሪ ወቅት በብቃት መመከት ካልቻለ እንደትላንቱ የትውልዱን ጀግኖች በወራሪ አስበልቶ መቀመጥ ቀጣዩ ትውልድ ሀገር አለን ማለት አይታሰብም፡፡
ወገኔ ልብ በል በገዛ ሀገራችን እየተፈናቀልን ስንሰደድ ቆይተናል፡፡ ተፈጥሮ የለገሰን ርስታችን ተነጥቆ የጥቂት ቡድን የበዬ ተመልካች አድርገውናል፡፡ ተወልደን ባደግንበት ምድር ከፊት በህወሓት ሰራዊት ከጀርባች በሱዳን ድርቡሽ እያስገደሉን ሲጨፍሩ ብዙ ታዝበናል፡፡ አሁን ግን ነገሩ ተለውጧል እየገደሉ ማንቧረቅ እንግዲህ አበቃ… መሞትም እንዳለ ጀግናው ጎንደሬ ገድሎና ሞቶ አሳይቷል፡፡ ይሄን ሕዝብ አትነካኩት ብለን መክረን ነበር ሆኖም ግን የሚሰማን ጠፍቷል፡፡ እንግዲህ መንገዱን ለነሱም ጨርቅ ያድርግላቸው፡፡ አሁን የጎበዝ አለቃ ሁሉም አለው..ወገን አንድ ነገር መናገር እፈልጋለሁ፡፡
በተለይ የብአዴን አባላትና ደጋፊዎች የአማራን ሕዝብን በሥሙ እያስተዳደሩ በጥቂት ወረበላ ሲገደል ቆሞ ማየት ነገ የልጅ ልጆቻችሁ በኣማራ ምድር የታሪክ ውዳቂ ሆኖ እንደሚቀሩ መገንዘብ ያለባቸው ወሳኝ ጊዜ አሁን ነው፡፡ ይሄን ታላቅነት የሚመጥን የእዉቀትና የስነልቦና ልዕልና የተላበሰ የብአዴን አባል ስለመኖሩ በእርግጥ እጠራጠራለዉ፡፡ ግን ነገ ታፍሩበታላችሁ ይልቅ ከተበደለው በየጊዜው ከሚሞተው ምስኪኑ ወገናችሁ ጎን በመሰለፍ ታሪክ ስሩ መላው የአማራ ተወላጅ በውጪም በውስጥም በኣንድነት መቆም ጊዜው ያስገድዳል፡፡ ጎንደር ሲነሳ ጎጃም ወሎ የሸዋ ሰው መነሳት አለበት፡፡ ለሌውም ወገን በጋራ መሰለፍ ያስፈልጋል፡፡ ይሄ የነጻነት ትግል በሁሉም ስፍራ መቀጣጠል ይኖርበታል፡፡ የአማራ ሕዝብ የመኖር ያለመኖር የህልውና ጉዳይ መሆኑ መዘንጋት የለበትም፡፡

ድል ለሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ! (ኣንጋው ተገኝ)
ምንጭ (ዘ-ሐበሻ)

Tuesday, April 19, 2016

ህወሃት በኦሮሚያ ላፈሰሰው ደም 2.4 ቢሊዮን ብር ጉቦ ሰጠ


ከጉቦው ጎን ለጎን አጋዚ “አርሶ አደር” ኢንጂነር በዳዳን ገደለ
የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር (ህወሃት) በኦሮሚያ ክልል የተነሳውን ሰላማዊ ተቃውሞ ተከትሎ ላፈሰሰው ደም 2.4 ቢሊዮን ብር ጉቦ በኦህዴድ አማካይነት መስጠቱ ይፋ ሆነ። ገንዘቡ የኦሮሚያ ሥራ አጥ ወጣቶችን ባለሃብት እንደሚያደርግ ሲገለጽ፣ ስራ አጥቶ ግብርና የተመለሰው ኢንጂነር በዳዳ ጋልቻ በህወሃት አንጋቾች የእርሻ ስራውን ጨርሶ ሲመለስ በጥይት ተደብድቦ ተገድሏል።
በዳዳ ገልቻ ማን ነው? ምን ደረሰበት?
በዳዳ እስከ አለፈው ማክሰኞ ድረስ ጉጂ ዞን፣ አዶ ሻኪሶ ወረዳ፣ መጋደር መንደር ነዋሪ ነበር። በምህንድስና ትምህርት ከዩኒቨርስቲ ተመርቆ ስራ ማግኘት ተሳነው። ስራ ፈለጋ ሲታከተው ትውልድ መንደሩ ተመለሶ በራሱ ስራ ፈጥሮ ለመስራት ጥያቄ አቀረበ። ያካባቢው አስተዳደር ጥያቄውን በውል ባልተገለጸ ምክንያት ውድቅ አደረገበት። ዲግሪውንና የስራ እቀዱን ወደ ጎን ትቶ ሙሉ በሙሉ ግብርና ላይ ተሰማራ።
ባለፈው ማክሰኞ ማሳው ላይ ደቦ ነበረው። ለደቦ ከጠራቸው ጋር ሆኖ ሲሰራ ዋለ። ደቦው ተጠናቆ ከማሳው ሲወጡ አወል የተባለ ሰው ወዴት እንደሚሄድ ጠየቀው። እሱም ወደቤት እንደሚሄድ ነገረው። ከዚያም ይህ ሰው ብርሃኑ ከሚባል ደህንነት ጋር ሆኖ መንገድ ላይ ጠበቁት። አጋዚዎችም አብረው ነበሩ። ከበዳዳ ጋር የነበሩት ሰዎች ሲደናገጡ “እናንተን አንነካም። የምንፈልገው ሰው አለ” በማለት በዳዳን “ቁም” አሉትና በጥይት ደበደቡት። ያካባቢው ህብረተሰብ ተኩስ ስምቶ ተሰበሰበ። ደጋገመው በመተኮስ የተሰበሰበውን ህዝብ አጋዚዎች በተኑት። ከዚያም ታርጋ በሌለው መኪና ጭነው አዶላ ሆዬ ሆስፒታል ወሰዱት።
ሆሰፒታል ከደረሰ በኋላ በዚያው ቀን ከምሽቱ 2፡30 አካባቢ ህይወቱ አለፈ። በዳዳ ኢህአዴግ 100 እጅ አሸነፍኩ ባለበት ምርጫ ኦፌኮን የወከለ እጩ ተወዳዳሪ ነበር። እሱ በተገደለበት ቀን ተቃውሞ አልነበረም። ከወር በፊት የሼኽ መሐመድ ሁሴን አልሙዲ የአኮቴ የወርቅ ፕሮጀክትንና የማስተር ፕላኑን በመቃወም ተካሂዶ የነበረውን ሰልፍ አስተባብሯል በሚል ግን ይጠረጠር ነበር። ቪኦኤ ዳንኤል ቦሩ እና ጋሪ ሱኔ የተባሉ የአይን ምስክሮችን ጠቀሶ አርብ ምሽት ካቀረበው የተወሰደ።
“የተቃውሞው ዋና መንስኤ ስራ አጥነት ነው” ኦህዴድ
የበዳዳን መገደል በጉያው አድርጎ የኦሮሚያን ሥራአጥ ወጣቶች ባለሃብት የሚያደርግ አስቸኳይ ፕሮጀክት መነደፉን ይፋ ያደረገው ኦህዴድ ፕሮጀከቱ በሁለት ሳምንት ውስጥ ተግባራዊ መሆን ይጀምራል ብሏል። ሪፖርተር የጠቀሳቸው የክልሉ የኮሙኒኬሽን ጉዳይ ጽህፈት ቤት ሃላፊ 832 ሺህ ስራ አጦች “የዕድሉ ተጠቃሚ” ይሆናሉ ብለዋል።
ሰላማዊ ጥያቄ በማንሳታቸው በህወሃት ታጣቂዎች ወንድምና እህቶቻቸው የተሰዉባቸው ሥራአጥ የኦሮሚያ ወጣቶች ንጹህ ውሃ ማምረት ይጀምራሉ። የምግብ ማዘጋጃ ፋብሪካ ባለቤት ይሆናሉ። ማዕድን ማምረት ይጀምራሉ። ሪፖርተር እንዳለው ሥራአጥ የነበሩት የኦሮሚያ ወጣቶች “ባለሃብቶች” ይሆናሉ። ይህ ሁሉ የሚሆነው ከህዝብ ጋር በተደረገ ውይይት ዋና ቁልፍ ችግር ሥራአጥነት መሆኑ በመታወቁ ነው።
ህወሃት ለኦህዴድ ጉቦ?
የኦሮሚያን ሥራአጥ ወጣቶች ባለሃብት የማድረግ ፕሮጀክት ይፋ መደረጉን አስመልክቶ የጎልጉል የአዲስ አበባ መረጃ አቀባይ ወሊሶ፣ ነቀምት፣ አዳማ፣ አለለቱና አርሲ ኮፈሌ የሚገኙ ነዋሪዎችን ትዝብት የማግኘት እድሉ አጋጥሞት እንደነበር ያወሳል። ከ800 በላይ የተለያዩ አመራሮችን ከሃላፊነት ዝቅ ያደረገውና ያሰናበተው ኦህዴድ አሁን ያስቀራቸው ሃይሎች ለህወሃት ታማኝ የሆኑት ብቻ መሆናቸው በስፋት እንደሚነገር ይገልጻል።
አሁን ከህወሃት ጋር የሚቀጥለው የኦህዴድ ታማኝ ክፍል የህዝብ፣ በተለይም የወጣቱን ታማኝነት ለማግኘት ይችል ዘንድ ትግራይ ውስጥ በከፊል ተግባራዊ ተደርጎ የኖረውን አሠራር ተግባራዊ እንዲያደርግ ተፈቅዶለታል። ህወሃት በክልሉ ሃብታም ያደረጋቸው ታማኝ ወዳጆቹ እንደሚንከባከቡት ሁሉ ኦህዴድም እንደአቅሚቲ ባለሃብት ወጣቶችን እንዲያፈራ ተመከሯል። 2.4 ቢሊዮን ብርም ተመድቦለታል። ፕሮጀከቱ ለቀጣዩ ምርጫ ሩጫም ጭምር እንደሆነም ይተቻል።
የ2.4 ቢሊዮን ፕሮጀክት ይፋ መሆኑን ተከትሎ “ህወሃት ለኦህዴድ የሰጠው ጉቦ ነው። የህወሃት ታጣቂዎች ላፈሰሱት ደም የተሰጠ ጉቦ ነው። በቀጣይ በወገኖቻቸው ደምና አጥንት ላይ ቆመው ብር የሚቆጥሩ ዜጎችን እናይ ይሆን?…” የሚሉ የመረሩ ተቃውሞዎች ይሰማሉ።
“ከሃጂዎችና ሆዳሞች፣ ከሃጂና ሆዳም ትውልድን ነው የሚፈጠሩት። ህወሃትን ክህደት እንደወለደው ሁሉ ከሃጂዎችን ስብስቦ እዚህ ደረሰ። አሁን ያለው ትውልድ ግንዛቤው በማደጉ ከበላው ማካፈል ግድ ሆነበት። 2.4 ቢሊዮን ብር ፈቅዶ የማካፈል ፖለቲካን ሊጀምር ወሰነ። ይህ ኢምንት ገንዘብ በኦሮሚያ ከፈሰሰው ደምና ከተፈጸመው ግፍ በላይ ገዝፎ የዜና ሚዛን ማግኘቱ ያሳዝናል። አንድ አገር የምትቆመውና ሰላሟ የሚጠበቀው ፍትህ ሲሰፍንባት ብቻ ነው። የሰው ልጆች የማይደበቁት ህሊና አላቸው” ሲሉ ከኦህዴድ አስቀድመው የተሰናበቱ አስተያየት ሰጠተዋል። ኦህዴድ የክህደት መንገዱን እስካላቆመና ኦሮሚያን አስቀድሞ እስካልሰራ ድረስ ችግሩ ሁሌም አለ። አቶ ሃይለማርያም ህዝብ ነቀቷል፤ ካሁን በኋላ በዚህ ህዝብ ጫንቃ ላይ ሆኖ እንዳሻው መጋለብ አይቻልም ሲሉ የተናገሩት ጉዳዩ በውል ገብቷቸው ከሆነ ትክክል የሚሆኑት ራሳቸውንና ሌሎችን ነጻ ባለስልጣን ሲያደርጉ ብቻ ነው – እንደ ኦህዴዱ ሰው!!
source (http:www.goolgule.com)

Friday, February 26, 2016

ጭፍጨፋውን ለማስቆም ሆ ብሎ መነሳት ብቸኛው መፍትሄ ነው !

የዛሬ 79 አመት ባህር አቋርጦ ድንበር ተሻግሮ የመጣው የጣሊያን ፋሽስት ሠራዊት በአዲስ አበባ ነዋሪ ወገኖቻችን ላይ ከፈጸመው ዘግናኝ የጭፍጨፋ እርምጃ የማይተናነስ እልቂት፣ ዛሬም በኦሮሞ ወገናችን ላይ በአገር በቀል የህወሃት አልሞ ተኳሽ የአጋዚ ጦር ሠራዊት እየተፈጸመ ይገኛል።
የካቲት 12 ቀን 1929፣ በሮዶልፎ ግራዚያኒ ትዕዛዝ የአዲስ አበባን ነዋሪ ሕዝብ በደም ጎርፍ ባጥለቀለቀው ዘግናኝ ጭፍጨፋ ህጻናት፣ ጎልማሶች ፣ ሽማግሌዎች፣ አሮጊቶች፤ ነፍሰጡሮች፣ ለጋ ወጣቶች፣ በአጭሩ ኢትዮጵያዊ የሆኑ ሁሉ ዘራቸው ፣ ሃይማኖታቸውና ጾታቸው ሳይለይ በጅምላ በመታረዳቸው፣ ደማቸው በስድስት ኪሎ አደባባይ እንደ ወራጅ ወንዝ መፍሰሱን፣ ታሪክ ጊዜ በማያደበዝዘው ብዕሩ መዝግቦት ይገኛል። የግራዚያኒ ጦር በወገኖቻችን ላይ ያንን አሰቃቂ እልቂት የፈጸመው ለነጻነታቸው ቀናይ የሆኑት ሞገስ አስግዶምና አብረሃ ደቦጭን የመሳሰሉ ጀግኖች ኢትዮጵያኖች፣ የጣሊያንን ቅኝ አገዛዝ በመቃወም በጠላት ላይ የፈጸሙትን ጥቃት ለመበቀልና በጠመንጃ ሃይል የአገሪቱን ህዝቦች በባርነት ቀንበር ሥር አውሎ ሃብትና ንብረት ለመዝረፍ በማለም ነበር።
ከጊዜ ወደ ጊዜ ግልጽ እየሆነ የመጣው በፋሽስት ጣሊያንና ለጠባብ የቡድንና የግል ጥቅም የመንግሥትን ሥልጣን የሙጥኝ ባለው ህወሃት መካከል ያለው ልዩነት አንዱ ባዕድ ወራሪ ሌላኛው አገር በቀል ከመሆን ያለፈ አይደለም። ጣሊያን የኢትዮጵያን ማዕከላዊ ሥልጣን የፈለገው ለአገሩ ኢንዱስትሪ የሚሆን ጥሬ የተፈጥሮ ሃብት ፍለጋ ሲሆን፣ ህወሃት ደግሞ የአገሪቱን ለም መሬት በርካሽ ዋጋ ለባዕድ በመቸብቸብ ጭምር ባለሥልጣናቱና የጥቅም ተጋሪዎቹ ሃብት እንዲያካብቱ ከማድረግ የዘለለ ራዕይ ኖሮት እንዳልሆነ በበርካታ ተግባሮቹ አስመስክሯል።
ወያኔ አጋዚ የሚባል ልዩ ጦር አሰልጥኖና አስታጥቆ ከህዝብ የሚነሳን ተቃውሞና እሮሮ ለመጨፍለቅ የሚወሰደው ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ፣ መነሻው ለዘረፋ መሣሪያ አድርጎ የሚጠቀምበትን በትረ ስልጣን ለመከላከል እንደሆነ በተደጋጋሚ ገልጿል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኦሮሚያ አካባቢ የተጀመረውን ህዝባዊ ተቃውሞ በሃይል ለመጨፍለቅ የህወሃት ልዩ ቅልብ ጦር በህዝባችን ላይ እየወሰደ ያለው ጭፍጨፋ የፋሺስት ግራዚያን ጦር አዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ህዝብ ላይ የዛሬ 79 አመት ከፈጸመው የሚለየው በሟቹች ቁጥር እና በገዳዮቹ ማንነት ብቻ ነው። የአጋዚን ጦር አሰልጥኖና አስታጥቆ በገዛ ወገኑ ላይ ፣ እንደባዕድ ሠራዊት፣ ጭካኔ የተሞላበት ጭፍጨፋ እንዲፈጽም ያሰማራው ህወሃትም ሆነ ከአለቆቹ የተሰጠውን ትዕዛዝ በፍጹም ታማኝነት ተቀብሎ በገዛ ወገኖቹ ላይ ታሪክ ይቅር የማይል ወንጀል በመፈጸም ላይ የሚገኘው ይህ ሠራዊት፣ ላለፉት 25 አመታት ያልአግባብ ያፈሰሰው ደምና የቀጠፈው ወገኖቻችን ህይወት ቁጥር ለመቁጠር እያዳገተ መጥቷል።
በተለያዩ ጊዜዎች በኦጋዴን፤ በጋምቤላ፤ በቤኔሻንጉል፤ በአፋር፤ በአማራና ደቡብ አካባቢዎች ከደረሰው የግድያ ፍጅት በተጨማሪ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኦሮሚያ አካባቢ የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ ለመደፍጠጥ የአጋዚ ጦር ከአለቆቹ በተሰጠው ትዕዛዝ የጨፈጨፋቸው ዜጎች ቁጥር ከ300 በላይ ደርሷል:: ቁጥሩ ከዚህ በእጥፍ የሚበልጥ ቁስለኛና ከ8 ሺህ በላይ እስረኞችም እንዳሉ ገለልተኛ የሆኑ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እየተናገሩ ነው። በአልሞ ተኳሾች ህይወታቸው ከተቀጠፉት መሃል ዕድሜያቸው ገና 8ና 9 አመት የልበለጣቸው ታዳጊዎች፤ አሮጊቶችና እርጉዝ ሴቶች ይገኛሉ። ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በአምቦ ከተማ በደረሰው ጥቃት የ9 አመት ታዳጊ ህጻንን ግንባር አነጣጥሮ የመታው የአጋዚ ጦር፣ ወንድሟን ከወደቀበት ለማንሳት ጎንበስ ያለቺውን እህቱን በሌላ ጥይት በመምታት ቤተሰቦቿንና የከተማውን ህዝብ የመረረ ሃዘን ውስጥ ጥሏል፤ ተመሳሳይ ግድያ በአሰላ ከተማ ውስጥ በምትኖር የ8 ዓመት ታዳጊ ላይም ተደግሟል።
በሴቶችና በህጻናት ላይ ጥይት የሚያስተኩስ የአውሬነት ባህሪ ከየትኛው ባህላችን የመጣ ነው? ይህንን አሰቃቂ ድርጊት የተመለከተ ወይም የሰማ ሰው እንዴት አድርጎ ነው ሠራዊቱንና አዛዦቹን ከአብራኩ የተገኘ የአገሩ ዜጋ አድርጎ ማሰብ የሚችለው? የዚህ አይነት አሰቃ ድርጊት ዛሬ የጀመረ ሳይሆን በድህረ ምርጫ 97 በአዲስ አበባና በሌሎችም የአገሪቱ ክፍሎች ውስጥም ተፈጽሟል። በመለስ ዜናዊ ትዕዛዝ በወቅቱ ከተማዋን ወሮ የነበረው የአጋዚ ጦር ያገኘውን ሁሉ በጥይትና በቆመጥ ሲያዋክብ፣ ሠይድ የተባለ የ10 አመት ልጅ የጨርቅ ኳሱን ከመሬት አንስቶ ለመሮጥ ሲንደረደር አናቱን በጥይት ተመቶ እስከወዲያኛው አሸልቦአል። በስተርጅናቸው ይጦሩኛል ብለው መርካቶ ውስጥ ሽንኩርት በመቸረቸር ሁለት ልጆቻቸውን ተቸግረው ያሳደጉ የእነ ፍቃዱ እናት በአጋዚ ጥይት ሁለቱንም በአንድ ጀንበር ተነጥቀዋል:: ምንም ጥፋት እንዳላጠፋ እየመሰከሩ ባላቸውን ከእስር ለመታደግ የሞከሩ የልጆች እናት ወ/ሮ እቴነሽ ሴት ልጆቻቸው ፊት በጥይት ተገድለው ቤተሰብ የተገደሉበትን ጥይት ዋጋ ከፍሎ አስከሬን አንዲወስድ ተደርጓል። የ14 አመቱ ነብዩ አለማየሁም ባንክ ልትዘርፍ ነበር ተብሎ በግፍ ተገድሏል። ያ እሮሮ ያ ጩኸት ወያኔ ሥልጣን ላይ እስካለ ብቻ ሳይሆን እስከ ወዲያኛውም ከህሊናችን አይጠፋም። ታሪክ ራሱን ይደግማል እንዲሉ የድህረ ምርጫ 97 አይነቱ ጭፍጨፋ አሁንም የኦሮሚያ ከተሞችንንና መንደሮችን እያዳረሰ ነው። “እናቴን ለምን ገደላችሁብኝ” ያለ ወጣት ደምቢዶሎ ውስጥ በጠራራ ጸሃይ ህዝብ ፊት ተረሽኗል፤ ምንም አይነት መሣሪያ ያልታጠቁ እናትና ልጅ በአንድ ቀን በአንድ ጀንበር በግፈኞች ጥይት ለህልፈት በቅተዋል፤ በደኖ ውስጥ ፍሮምሳ አብዲ የተባለ የ10 አመት ታዳጊና ወላጅ እናቱም እንዲሁ። ምስራቅ ሃራርጌ ውስጥ ደረታቸው ላይ በተተኮሰ ጥይት ህይወታቸውን ያጡት የ60 አመቷ አዛውንት አዴ ጁሃራ ሙሳንና የሌሎች ሰለባዎችን ፎቶግራፍ በማህበራዊ ድህረ ገጽ የተመለከትን ሁሉ ልባችን በሃዘን ተወግቶአል ፤ በቁጭትም በግኗል። በመቻራ፤ በነገሌ፤ በነቀምት፤ በኮፈሌ፤ በመንዲ፤ በሆሮ ጉዱሩ፡ በቦቆጂ፤ በአሰላ፤ በሮቤ፤ በጎባ፤ በመቱ ወዘተ በየቀኑ እየፈሰሰ ባለው ደም ምክንያት ተመሳሳይ ለቅሶ ተመሳሳይ ዋይታ የአገራችንን ምድር እያናወጠ ነው። ይህ አረሜኔያዊ ጭፍጨፋ የዕለት ተዕለት በሆነበት ሰሞን ባለፈው ሰኞ ለአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ የኦሮሚኛ ፕሮግራም ቃለመጠይቅ የሰጠው ጌታቸው ረዳ፡ በገዛ ወገኑ ላይ እንዲህ አይነት ዘግናኝ እርምጃ እየወሰደ ያለውን የአጋዚ ጦር “በመልካም ሥነምግባር የታነጸና ህዝባዊ ወገናዊነቱን ያረጋገጠ” በማለት ሲያሞካሸው ተሰምቷል። ከሶስት አራት ቀን ቆይታ ቦኋላ ደግሞ ሃይለማሪያም ደሳለኝ በኦሮሚያ ያለው እንቅስቃሴ “የመንግሥትን ሥልጣን በሃይል ለመንጠቅ የሚደረግ እንቅስቃሴ ስለሆነ የማያዳግም እርምጃ ይወሰዳል” ሲል በቴለቪዢን መስኮት ብቅ ብሎ ዝቷል። ታዳጊ ህጻናትንና እርጉዝ ሴቶችን ግንባር አልሞ የሚመታ ሃይል ከማሰማራትና ህዝብ ከማስጨፍጨፍ የበለጠ ምን አይነት የማይዳግም እርምጃ ለመውሰድ ህወሃት እንደተዘጋጀ ሃይለማሪያም ደሳለኝ እራሱ የሚያውቅ አይመስለንም። ህዝባዊ ተቃውሞ በሚካሄድባቸው ቦታዎች ታንክና መትሬየስ እየተተራመሰ እየተመለከትን የማያዳግም እርምጃ የሚሉን እንደ ባህሪ አባታቸው ፋሽስት ጣሊያን የመርዝ ጭስ ከአየር የሚለቅ አይሮፕላን ለማሰማራት ፈልገው ይሆን ? ወቅቱ ፈቀደም አልፈቀደ ወያኔ ሥልጣኑን ለመከላከል ይጠቅማል ብሎ እስካመነ ድረስ የማይወስደው የጭካኔ እርምጃ ይኖራል ብሎ ማሰብ ቢያዳግትም፣ እንደ ሁለተኛው የአለም ጦርነት የመርዝ ጭስ በመጠቀም ሥልጣን ላይ ተደላድሎ መቀመጥ እንደማይቻል የመረዳት አቅም ያለው ወያኔ ውስጥ አለ ብሎ መዘናጋት አያስፈልግም።
በህዝብና በአገር ሃብት ጠንካራ ሠራዊት ገንብቶ ህዝብ እየገደለ፤ እያፈናቀለና እያሰደደ እስከወዲያኛው ሥልጣን መቆጣጠር የቻለ መንግሥት በታሪክ አይታወቅም። የወያኔም መንግስት የመጀመሪያው ሊሆን አይችልም:: የግራዚያኒ ቁራጭ የዛሬው ጥቁር ፋሽስት ወያኔ እራሱን የተለየ ጠንካራ አድርጎ የሚቆጥረው የአለም አምባገነኖችን ታሪክ ብቻ ሳይሆን የአገራችንን የቀደምቶቹን አወዳደቅ ታሪክ እንኳ መለስ ብሎ ለመመልከት ባለመቻሉ ነው። በጠመንጃ ሃይል በአንድ ወቅት በአንድ ቦታ የሚነሳውን ወይም የተነሳውን ተቃውሞ ማዳከም ወይም መቆጣጠር ይቻል ይሆናል። አፍኖና ነጻነት ገፎ ሥልጣን ላይ ተደላድሎ ለረጅም ጊዜ መኖር ግን በፍጹም እንደማይቻል ወያኔ እራሱ ካካሄደው የጸረ ደርግ ትግል መማር ነበረበት:: ባለመማሩም የራሱን የወደፊት ዕጣ ከቀድሞው የዩጎዝላቪያ ፕሬዝደንት ስሎባዳን ሚሎሶቪችና የአይቬርኮስቱ ሎሬንት ባግቦ ተርታ እያሰለፈ ነው:: ሁለቱም በየአገራቸው ባደራጁትና በሚመሩት ሠራዊት ተማምነው በአገርና በህዝብ ላይ ለፈጸሙት ወንጀል በመጨረሻቸው አፍንጫቸውን ተሰንገው አለም አቀፍ ፍርድ ቤት ተወረውረዋል:: የአገር መከላኪያ ጦር ዋና አላማና ተግባር የአገርን አንድነትና ሉአላዊነት ከባዕድ ወረራ መከላከል ነው። ወያኔ እየገዛት ባለችው አገራችን ግን እየሆነ ያለው በሠላም አስከባሪነት ሥም ለወያኔ መሪዎችና የጦር ጀነራሎች በውጪ ምንዛሪ ገቢ የሚያስገኝ ድንበር ዘለል ግዳጅ ተግባር ላይ መሠማራት ወይም የገዛ ወገንን መግደልና ማሠር ሆኗል:: ይህ አካሄድ በአስቸኳይ መቆም አለበት:: የወያኔን የሥልጣን ዕድሜ ለማራዘም ሲባል የሚሰጠውን ትዕዛዝ ተቀብሎ ህዝብ መጨፍጨፍ፤ ማቁሰልና ማሰር የፍርድ ቀን ሲመጣ “ታዝዤ ነው” በሚል ከተጠያቂነት ነጻ የማያደርግ ወንጀል መሆኑን ሁሉም ሊያውቅ ይገባል:: አሁን በኦሮሚያ ውስጥ እየተካሄደ ባለው ተቃውሞ ህዝብ በመፍጀት ለወያኔ ግዳይ ጥሎ የመሸለም አባዜ የተጠናወታቸው አዛዦች ካሉ ቆም ብለው
ማሰብና ከድርጊታቸው መታቀብ ያለባቸውም ከታሪክና ከህግ ፍርድ እራሳቸውን ለማዳን ነው።
አርበኞች ግንቦት 7 በኦሮሚያ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለውን ጭፍጨፋ ለማስቆም ሁላችንም ሆ ብለን መነሳት፤ አምርረን በመታገል ይህን እጅግ ጨካኝ ዘረኛ ስርአት በማስወገድ ወንጀለኞቹን ለህግ ማቅረብ መቻል ይኖርብናል ብሎ ያምናል:: አባቶቻችን በፋሽስት ጣሊያን ጦር የተሰነዘረብንን ወረራና ጥቃት ለማክሸፍ ሆ ብለው በህብረት እንደዘመቱት ሁሉ፣ ይህ የኛ ትውልድም አገራችንንና ህዝባችንን ለከፋ መከራ የዳረገውን የወያኔ አገዛዝ ከላያችን አሽቀንጥሮ ለመጣል በህብረት መነሳትና መዝመት ያለብን ግዜው አሁን ነው።
በወያኔ ከፋፍለህ ግዛው ፖሊሲ ምክንያት በፍርሃትና በጥርጣሬ መተያየታችን የአገዛዙን ጡንቻ አፈርጥሞታል። አንዱ ሲጠቃ ሌላው ዝም ማለቱን ከቀጠለ ሁላችንም በየተራ ተደቁሰን በባርነት ቀንበር ሥር ስንማቅቅ እንኖራለን። ይህ እንዳይሆን የፈለገ ሁሉ ዛሬውኑ በኦሮሚያ እየተቀጣጠለ ያለውን የነጻነት ትግል ይቀላቀል። ከአሁን ጀምሮ አንዱ ሲደማ የሌላው ከዳር ሆኖ ተመልካችነት ማብቃት ይኖርበታል። አርበኞች ግንቦት 7 የወያኔን ጭፍጨፋ ለማስቆምና አገራችን ውስጥ ሠላም ፍትህና እኩልነት እንዲሰፍን የሚያካሂደውን ትግል ከጫፍ እስከ ጫፍ ያለው ኢትዮጵያውያን ሁሉ እንዲቀላቀሉት የትግል ጥሪውን በድጋሚ አጠናክሮ ያቀርባል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!
Source www.patriotg7.org

Tuesday, January 26, 2016

የሰላምን በር ጠርቅሞ የዘጋው ወያኔ ነው

የወያኔ አረመኔያዊ ያገዛዝ ስርዓት በህዝባችን ላይ የሚፈጽመው አፈና ግድያና ዝርፊያ በመጠኑም በዘግናኝነቱም ይበልጥ እያገጠጠ ስለመጣ ለወትሮው እንዳላዩ አይተው የሚያልፉትን ምዕራባውያን ለጋሾቹንና ወዳጆቹን ሳይቀር በእጅጉ ማሳስብ ጀምረዋል። ወያኔ ለምዕራባውያን ደህና ሎሌ በመሆን ወንጀሌን እንዳላዩ እንዲያዩልኝ ማድረግ እችላለሁ የሚለው አካሔዱ በውንብድና ተግባሩ ለከት የለሽነትና ዘግናኝነት ምክንያት ሙሉ ለሙሉ እየተሸረሸረበት ነው። ብዙዎቹ ምዕራባውያን ላለፉት ሁለት ወራት በተለይ በኦሮሚያ ውስጥ የሚካሄደውን ጭፍጨፋና አፈና ለማውገዝ የተገደዱበት ሁኔታ ተፈጥሯል።
አሜሪካንን ጨምሮ የወያኔ ለጋሽ ሀገራት የሆኑት ምዕራባውያን ሰሞኑን በኦሮሞ ወገኖቻችን ላይ ወያኔ የከፈተውን የዕብሪት ጭፍጨፋ፣ እስራትና አፈና አስመልክቶ ችግሩን በውይይትና በስልጡን መንገድ ይፈታ ዘንድ የሚያሳስቡ ግልጽና ባንጻራዊ ደረጃ ሲታዩ ጠንከር ያሉ መግለጫዎችን አውጥተዋል። የደረሰውም ጥፋት ተመርምሮ ጥፋተኛ ወገን እንዲጠየቅ የሚጠይቁና ችግሩም በሰላምና በውይይት እንዲፈታ እየጎተጎቱ ይገኛሉ። ባለፉት በርካታ ዐመታት ምዕብራባውያኑ የወያኔ ጉጅሌ ይህንን አቅጣጫ እንዲከተል ተጽዕኖ የመፍጠር አቅማቸውን ተጠቅመው ያደረጉት በቂ ግፊት እንደሌለ ይታወቃል። የአሜሪካ መንግስትና የአውሮፓ ሕብረት አባል ሀገሮች ዘግይተውም ቢሆን ሀገራችን ውስጥ የተካሄደውንና እየተካሔደ ያለውን ጭፍጨፋ ማውገዛቸውና ወደፊትም በዝርዝር ተመርምሮ ተጠያቂው እንዲታወቅ ያቀረቡትን ሀሳብ እንደ በጎ ጅምር እንመለከተዋለን።
ለሀገራችንና ለህዝባችን እጣ ፋንታ የምንጨነቅና የህዝቡ ጥቃት ያንገፈገፈን የሀገሪቱ ልጆች የችግሩ የመፍትሔ መጀመሪያ ይህ በጉልበቱ ህዝባችን ላይ የተጫነ መንግስት ነኝ ባይ የግፈኞች ጥርቅም በሃይል በሚደረግ ትግል ጭምር መወገድ አለበት ወደሚለው ውሳኔ የደረስነው የሰላም በርና ጭላንጭል ሁሉ በመዘጋቱ እንደሆነ ስንገልጽ ቆይተናል ። ላለፉት ሁለት ወራት በኦሮሞ ወገኖቻችን ላይ የተፈጸመውና ከመቶ ሀምሳ በላይ ወገኖቻችን ያለቁበት ጭፍጨፋ እንዲሁም በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች በሚኖሩ ዜጎቻችን ላይ እየተፈጸመ ያለው ተመሳሳይ ግድያ፣ እስራትና የተቀናቃኝን አድራሻ ደብዛ ማጥፋት እርምጃ የሚያሳየው ይህ ስርዓት የበለጠ ጥፋት ከማድረሱ በፊት በፍጥነት መወገድ ያለበት መሆኑ ላይ ያለን አቋም ለሁሉም ይበልጥ ግልጽ እየሆነ መምጣቱን ነው። እንደ ወያኔ ያለ ከህዝብ የተጣላ የፖለቲካ ሀይል የፖለቲካ ጥቅምን የሚያየው ከራሱ ህልውናና ደህንነት አንጻር እንጂ ከህዝቡ ሰላም ብልጽግናና ነጻነት ወይም ከሀገሪቱ የረጅም ጊዜ እጣ ፋንታ አንጻር አይደለም። የወያኔን ገዥዎች የሚያስጨንቃቸው የህዝቡ ኑሮ ሳይሆን የራሳቸው የዝርፊያ ስርዓት ባግባቡ መጠበቅ አለመጠበቁ ነው። ለዚህ ነው ስርዓታቸውን ለመጠበቅ የነጻነት ጥያቄ ኮሽታ በሰሙ ቁጥር የሚባንኑት። ለዚህ ነው በሰላም መብቱን የጠየቃቸውን ሁሉ መደዳውንና በጭካኔ በጥይት የሚረፈርፉትና የተረፋቸውን እንደ እንስሳ ወህኒ በረት ውስጥ የሚያጉሩት።
አርበኞች ግንቦት 7 የወያኔ ጸረ ህዛብና ጸረ አገር እርምጃ ሊቆም የሚችለው ላለፉት 25 አመታት ወያኔ በመካከላችን የገነባው የመከፋፈልና የልዩነት ግድግዳ ለመናድ ሁላችንም እጅ ለእጅ ተያይዘን በአንዳችን ላይ የሚፈጸመው ጥቃት በሁላችንም ላይ እንደ ተፈጸመ ቆጥረን በጋራ ስንንቀሳቀስ ብቻ ነው ብሎ ያምናል:: ዛሬ በኦሮሚያ ወገኖቻ ላይ እየተፈጸመ ያለው ሰቆቃና ግዲያ ትናንት በጋምቤላ ፤ በኦጋዴን ፤ በአፋር፤ በቤኔሻንጉል ፤ በደቡብና በአማራ ወገኖቻችን ላይ በፈረቃ ሲፈጸም የቆየና እየተፈጸመ ያለ መከራ መሆኑን የማይገነዘብ የለም:: በፈረቃ መገደል፤ በፈረቃ ወህኒ መወርወር ፤ በፈረቃ መፈናቀል፤ በፈረቃ ለስደት መዳረግ የሁላችንም ዕድል ፈንታ ሆኖአል:: ይህንን ስቃይና መከራ ማስቆም ለፍትህና ለነጻነት የቆመ ዜጋ ሁሉ ግዴታ ነው::
ወያኔ የሰላም በሮችን በሙሉ ጠርቅሞ ሲዘጋ ለአገራቸው ጥቅም ሲሉ ዝምታን የመረጡ ምዕራባዊያን የህዝብ ብሶት ገንፍሎ አደባባይ ከወጣና ብዙዎች በአጋዚ ጦር ጨካኝ ግዲያ ህይወታቸውን ከገበሩ ቦኋላ ዘግይተውም ቢሆን መናገር መጀመራቸው መልካም ጅምር ነው:: ነገር ግን በእብሪት የተወጠሩ የወያኔ መሪዎች በባዕዳን አለቆቻቸው ቁጣ ከአቋማቸው ፍንክች ይላሉ ብሎ መጠበቅ መዘናጋት እንዳያስከትል መጠንቀቅ ተገቢ ነው::  ችግሮችን ተነጋግሮ መፍታት ትልቅ አቅምና ችሎታን የሚጠይቅ የዘመናችን ሥልጣኔ ውጤት ነው:: በጠመንጃ ተጸንሶ በጠመንጃ የተወለደው ወያኔ ለእንዲህ አይነት ዕድገትና ሥልጣኔ አልታደለም::
አርበኞች ግንቦት 7 የወያኔ ስርዓት ሊወገድ እንጂ ሊጠገን የማይችል የተበላሸ ስርዐት መሆኑን ይገነዘባል:: በመሆኑም በህዝባችንና በአገራችን ላይ የሚፈጸመውን ወንጀል ለማስቆም የጀመረውን ሁለገብ ትግል የወያኔ አገዛዝ እስኪወገድና ሠላምና ዲሞክራሲ በአገራችን እስኪሰፍን ድረስ አጠናክሮ እንደሚቀጥልበት ለወዳጅም ለጠላትም ያረጋግጣል ::
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ
Source www.patriotg7.org