በታሪኩ ደሳለኝ
(ኢ.ኤም.ኤፍ) እውቁ ጋዘጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በጻፋቸው ጽሁፎች ምክንያት በፍርድ ቤት 3 አመት ተፈርዶበት በቅሊንጦ እስር ቤት እንዲቆይ ተደርጎ ነበር። ዛሬ የደረሰን ዘገባ እንደሚያመለክተው ደግሞ፤ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከቅሊንጦ ወደ ዝዋይ መወሰዱን ለማወቅ ተችሏል። ይህም በህገ መንግስቱ ላይ “አንድ እስረኛ ለቤተሰቡ ጥየቃ አመቺ እንዲሆን፤ የቅርብ ቤተሰብ ባለበት ስፍራ መታሰር አለበት” የሚለውን የእስረኛ ሰብአዊ መብት አያያዝ የጣሰ ነው። ለማንኛውን ዛሬ ከተመስገን ወንድም የደረሰውን ዘገባ ከዚህ በታች አቀናብረን አቅርበነዋል።
እንደለመድነው ዛሬም እኔና ሰውዓለም ታዬ የተመስገንን ስንቅ ይዘን በጠዋት ነው ቂሊንጦ እስር ቤት የደረስነው። በመታበይ ሰማይ የደረሱት የእስር ቤቱ አስተዳደሮች በንቀት “ማን ጋር ናቹህ?” አሉን።
“ተመሰገን ደሳለኝ ጋር”
“ማን ትባላለቹም?” ነገርናቸው።
“ዞኑ ስንት ነው?”
“ዞን አንድ” አልናቸው። መታወቂያ ጠይቁንና፤ መታወቂያ ሰጠናቸው። አገለብጠው መዘገብ ላይ ከፃፉ በኋላ ወረወሩል። መታወቂያችንን አንስተን እነሱን አልፈን ገባን፡፡
ብዙዎቹ ወፌ ላላ የሚሏት ግርፋት በዚህ መንግስት መገረፋቸውን ሲነግሩንና ሲፅፉልን አንብበናል። ቂሊንጦ ደግሞ የታሰሪ ቤተሰብን በሚሸማቀቅ ሁኔታ ወፌ ላላ እሚባል ፍተሸ አላቸው። ወፌ ላላን ተፈትሽን አለፍን። ተመሰገንን ልናስጠራ ስንል እስረኝ አንደሚጠራልን ተነገረን። ስንዞር የሙስሊም መፍትሄ አፈላለጊ ኮሜቴዎች አንዱ የሆነው አቡበከር ነው። ሲያየን በፊቱ ላይ ሃዘን አየንበት። ሌላ ግዜ በፈገግታ ስላምታ የሚያስቀድመው አቡበከር በመከፋት “ተሜን ዛሬ ለሌት ዝዋይ ወሰዱት።” አለን። ትላንት ተመስገን ስንጠይቀው ስለዚህ ጉዳይ ምንም እሚያውቀው ነገር የለም፤ አልነገሩትም። ለሱ እንኳን ባይነግሩት እኛ ቤተሰብ አንደሆን እያወቁ ሊነግሩን አልፈለጉም። የያዝኩትን ስንቅ ሳየው የእናቴ ንግግር ትዝ አለኝ። “በሉ ቶሎ ሂዱ ምግቡ ሳይቀዘቅዝ አድርሱለት” ነበር ያለችው። …. እናቴ ምግቡም ይቀዘቅዛል፤ ልጅሽም የለም …. አቡበከርን አመስግነን ወጣን፡፡
አሳሬዎቹ ተሜን በተለያየ ጊዜ ሀገሩን ለቆ እንዲሰደድ ያላደረጉት ነገር የለም ከሀገር ሀገር ማዘዋወሩ ቢያቅጣቸው ካንደኛው የግዞት እስር ቤታቸው ወደሌላኛው የግዞት እስር ቤታቸው ማዘዋወሩ ላይ ግን ታስክቶላቸዋል!! ተሜን ሲወሰዱት አላየሁም፤ ግን ተሜን አውቀዋለሁ ለሀገሩ ሲል ጉዞው ቀራኒዬ ድረስ አንደሆነ፡፡ ወደ መኪናው ሲወሰዱት እስረኞቹን እያበረታታ ሲሰናበታቸው ….ፖሊሶቹን አንድ ቀን ከህዝብ ጎን እንደሚሆኑ እያሰበ… ሊነጋ ሲል እምትወጣውን ፀሐይ በተስፋ እያየ በፈገግታ ወደ ዝዋይ እንደሄደ ሳሰበው ደሰ አለኝ፡፡ በአይምሯዬ ወደ ዝዋይ አቅጣጫ እየተመለከትኩ እንዲህ አልኩ።
ተመሰገን ደሳለኝ….
ከሀገር ወጣ ቢሉት፣ አልወጣም እዳለ
ከኛ ጎንን ሁን ሲሉት፣ ከህዝቡ እንደሆነ
ባላማው እንደፀና
እነደኮራ ሄደ፣ አንደተጀነነ!
ምንጭ የኢትዮጵያ ሜዲያ መድረክ
No comments:
Post a Comment