Monday, September 22, 2014

እሪ በይ ሃገሬ

ethiopian flag
Monday ,september 22nd,2014
ከአብርሃም ያየህ
ይህች  “እሪ በይ ኣገሬ” የተሰኘች ኣጭር ስንኝ፤ በኣሰብ ወደብ ያንድ የውጭ ባለሃብቶች የመርከብ ወኪልና የግምሩክ ኣስተላላፊ ትራንዚት ኩባንያ ቅርንጫፍ ስራ ኣስካያጅ በነበርኩበት ወቅት ታሪካቸውን በቅርበት ለማውቅላቸው፤
  • ለኣንጋፋው ኢትዮጵያዊ ስራ ፈጣሪና፥ ታላቅ ኣገር ኣልሚ ለሆኑት፤ 
  • ከትቢያ ኣፈር ተነስተው ዝነኛውን  የኢትዮጵያ ኣማልጋሜትድ ኩባንያ በመመስረት፥ ውድ ዋጋ በማስከፈል ህዝብ ሲበዘብዙ የነበሩትን የውጭ ኣገር ኩባንያዎችን በህጋዊ የዋጋ ውድድር ከገበያ ለማስወጣት ለቻሉት፤ 
  • በዚህ ኩባንያቸው ኣማካኝነትም በብዙ መከራ ያሳደጋቸውን የኢትዮጵያ ድሃ ገበሬን ህይወት ለመለወጥ ሲያኮበክቡ የ66ቱ “ኣብዮት” ደርሶ በሚያሳዝን ሆኔታ ላደናቀፋቸው፤ 
  • “ከኑግ ጋር የተገኘህ ሰሊጥ ኣብረህ ተወቀጥ” እንዲሉ፥ እኒህ ያንድ ድሃ ጭሰኛ ገበሬ ልጅ የሆኑትና፥ ምንም እንከን ሳይኖርባቸው በደርግ ማጎሪያ ቤት ለረጅም ዓመታት ለተሰቃዩት በኋላም ለስደት ለተዳረጉት፤ 
  • የማሌሊት/ወያነ ትውልደ ኤርትራዊያን መሪዎችና ግብረ-በላዎቻቸው ኣምርረው የሚጠሏትን ኢትዮጵያ እንደተቆጣጠሩ፥ የወራሪዎቹን ማንነት በውል ሳያወቁ በየዋህነት ወዳገራቸው ተመልሰው ባላቸው ከፍተኛ የስራ ልምድና እውቀት ኣማካኝነት ላገራችንና ለዝባችንን ከፍተኛ ጥቅም ለማበርከት ታጥቀው ቢነሱም፥ በደርግ እግር በተተኩት የህዝብ ጠላቶች፥ ኣገር ኣስገንጣዮችና ዳር-ድንበር ኣስደፋሪ ወያኔ/ማሌሊቶች እብሪት፥ የሚወዷትን ኣገራቸው ጥለው ለዳግም ስደት ለተዳረጉት፤ 
  • በቀ. ኃይለ-ሥላሴ ዘመነ መንግሥት በኢትዮጵያ ገበሬዎችና በቅርብ በሚያውቋቸው የወቅቱ ፖለቲካ እቀንቃኞች “ተራማጅ ነጋድራስ” የሚል እውቅና ለተሰጣቸው ለክቡር እምክቡራን ላቶ ገብረየስ ቤኛ የክብር ማስታወሻ ትሁንልኝ! 
እሪ በይ ኣገሬ
እሪ በይ ኢትዮጵያ ፥ ቅል ድንጋይ ሰበረ፤
ውሃ ሽቅብ ወጣ ፥ ዘመን ተቀየረ፤
ሌባ እየከበረ ፥ ነጋዴው ከሰረ፤
ኣገር ፈራረሰች ፥ ድንበር ተደፈረ፤
እንደ ቅርጫ ስጋ ፥ እየተመተረ፤
ላረብ ለድርቡሹ ፥ ይታደል ጀመረ፤
ጀግና ኣንገቱን ደፋ ፥ ባንዳ ተወጠረ።
(ግጥም፤ ከኢየሩሳሌም ጀማል Facebook የተወሰደ።)
ኣንጀት የሚያሳርረውና የሚያበግነው፥ ኣቶ ገብረየስ ቤኛ ከኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) ጋር ያደረጉት፥ በኣምስት ክፍል የቀረበ፥ ሰፊ የምስል (የቪዲዮ) ቃለ-መጠይቅ በትዕግስት በመመልከት፥ ኣሁን በኢትዮጵያ ቤተመንግስት የሰፈሩትና ፍፁም ፀረ-ኢትዮጵያ የሆኑት ኣደገኛ የዲያብሎስ ልጆች ምንነትና ኣጥፊ ዓላማ በትክክል ለመረዳት ያስችላል። በወያነ/ማሌሊት ኣመራር ምንነት ኣሁን ያለዎትን መረጃ በማዳበር ቢሆንም ተጨማሪ ኣቅም ይገነባል።  
  

No comments:

Post a Comment