አዲስ አበባ፡- የሰማያዊ ፓርቲ ሉቀመንበር ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት በአሜሪካ መንግስት ስቴት ዲፓርትመንት የአፍሪካ
ስኬታማና በቀጣይነትም ሀገራቸውን መምራት የሚችለ ወጣት መሪ ተብለው ተመረጡ፡፡
ከፓርቲው የህዝብ ግንኙነት የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ኢንጅነር ይልቃል ለአሸናፊነት የበቁት ‹‹የአሁኑ
ወጣት የአፍሪካ መሪና ወደፊትም ለአገራቸው መሪ ሉሆኑ የሚችለ፣ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ጥሩ ስራ የሰሩ መሪዎች
መካከል በተደረገ ውድድር በአሜሪካ መንግስት ስቴት ዲፓርትመንት›› መስፈርቱን አሟልተው በመገኘታቸው ነው፡፡
ሉቀመንበሩ ለአሸናፊነት መብቃታቸው ይፋ ከመሆኑ በፊት የአሜሪካ መንግስት የኢንጅነር ይልቃልን መሰረታዊ
የሚባለትን የፖለቲካ ቆይታ፣ የትምህርት ዝግጅት፣ በፖለቲካው ውስጥ የነበራቸውን ተሳትፎ እና የመሳሰለትን
መረጃዎች ወስዶ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡
ኢንጅነር ይልቃል በዚህ ውድድር በመመዘኛዎች መሰረት በማሸነፋቸው በአሜሪካ መንግስት ስቴት ዲፓርትመንት
የጉብኝት ግብዣ ተደርጎሊቸዋል፡፡ በመሆኑም የአሜሪካ መንግስት ሙለውን ወጭ ሸፍኖ ለሶስት ሳምንት በአሜሪካ
የመንግስት አወቃቀርና ዴሞክራሲን ጨምሮ በተግባር የሚሰጡ ስልጠናዎችን የማግኘትና የአሜሪካ መንግስት
ባለስልጣናትም ባለበት ከተለያዩ ተቋማት ጋርም ለመገናኘት እድል እንደሚኖራቸው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
‹‹የሉቀመንበሩ ለዚህ ሽልማት መብቃት አዲሱን ትውልድ ወደ ፖለቲካው ለማምጣት በሚያደርገው ጥረት እንደ አንድ
ማበረታቻ ተደርጎ ሉወሰድ እንደሚችልና ሰማያዊ ፓርቲ እያደረገው ላለው ሰሊማዊ ትግል ትልቅ እውቅና እንደሆነ
ያሳያል›› በማለት የህዝብ ግንኙነቱ ያደረሰን መረጃ ይጠቅሳል፡፡ ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ዛሬ ወደ አሜሪካ
እንደሚያመሩም መረጃው ጨምሮ ገልጾዋል፡፡
source quatero.net.
No comments:
Post a Comment