Friday, December 27, 2013

ትግሉ የሁሉንም ተሳትፎ የሚጠይቅበት ወሳኝ ምእራፍ ላይ ደርሷል

ራሱን የብሄረ አማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) ብሎ የሚጠራው ድርጅት በከፍተኛ የፖለቲካ ኪሳራ ውስጥ ገብቷል። የህወሃትን ዙፋን ከመጠበቅ ባለፈ ምንም ሚና የሌላቸው የብአዴን አመራሮች ያለፉትን ሶስት ወራት በተለያዩ መንገዶች የድርጅቱን አባሎች ሲገመግም ከርመዋል። በግምገማዎች ላይ እንደተረጋገጠው ብአዴን የህወሀትን ዙፋን ሊሸከሙ የሚችሉ ወጣቶችን ኮትኩቶ ለማሳደግ አለመቻሉ ነው። በብአዴን ውስጥ ለሚታየው የውስጥ ትርምስ በድርጅቱ ውስጥ የሚገኙ የግንቦት7 አባላትና ደጋፊዎች እየተጫወቱት ያለው ሚና በሌሎች ድርጅቶች ውስጥ ላሉ የንቅናቄው አባላት ጥሩ ትምህርት የሚሰጥ ነው። የንቅናቄው አባሎችና ደጋፊዎች በድርጅቱ ውስጥ የታቀፉ ወጣቶችን የፖለቲካ ግንዛቤ ከማሳደግ ጀምሮ ፣ የንቅናቄውን መረብ እስከ ወረዳዎች በመዘርጋት ከፍተኛ ሚና በመጫወት ላይ ናቸው። ሰሞኑን በገሀድ በየግምገማዎች ላይ ሲነገር እንደነበረው ብአዴን እወክለዋለሁ ከሚለው የአማራ ህዝብ ሙሉ በሙሉ ተነጥሎ በአየር ላይ የተነሳፈፈ ድርጅት ሆኗል።
ይህን እውነታ ዘግይተው የተረዱት የብአዴን ዙፋን ጠባቂ አመራሮች የሚይዙትን የሚጨብጡትን በማጣት የተለያዩ ውሳኔዎችን እያሳለፉ ነው። ታማኝ የሚሉዋቸውን ካድሬዎች በየወረዳዎች በመላክ በግንቦት7 የሚጠረጠሩትን ወይም የግንቦት7 አባሎች ናቸው ተብለው ከሚገመቱ ሰዎች ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ግንኙነት አላቸው ተብሎ የሚታሰቡትን ሰዎች በመያዝና በማሰቃየት ሌላው ወጣት ንቅናቄውን እንዳይቀላቀል ለማድረግ እቅድ ነድፈው ለመንቀሳቀስ አስበዋል። እንዲሁም አንድ ለአምስት የተባለውን አደረጃጀት በመስሪያ ቤቶች፣ በቤተሰብ፣ በትምህርት ቤቶችና በተለያዩ ተቋማት ላይ በስፋት በማውረድ፣ የሰውን የእለት ተእለት እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር አልመዋል። ወጣቱ አካባቢውን እየለቀቀ ግንቦት7ን ለመቀላቀል የሚያደርገውን እንቅስቃሴ የአካባቢ ፖሊሶችንና የድንበር ጠባቂዎችን በማጠናከር ለመቆጣጠር ውሳኔ አሳልፈዋል።
በድርጅቱ ውስጥ የግንቦት7 ደጋፊዎች ናቸው ተብለው የሚጠረጠሩትን ወይም ዝንባሌ አላቸው የሚባሉትን ሁሉ ነቅሶ በማውጣት ለብአዴን ነፍስ ለመዝራት ሙከራ እየተደረገ ነው። እነዚህን ውሳኔዎች ያስፈጽማሉ የተባሉ በጭካኔያቸው ፣ በጎጠኝነታቸውና በንቅዘታቸው የሚታወቁትን የእነሱ ታማኝ ካድሬዎችን ወደ ፊት ለማምጣት በማሰብ ሰሞኑን ሹም ሽር አድርገዋል። ጉልቻ ቢቀያየር ወጥ አያጣፍጥም እንደሚባለው የሰዎች መለዋወጥ የብአዴንን ህልውና ከክስመት የሚታደገው አይሆንም።
ለመሆኑ ብአዴን የህወሀትን ዙፋን ከመጠበቅ በስተቀር ባለፉት 22 አመታት እወክለዋለሁ ለሚለው ህዝብ ምን ሰራ? ብአዴን ባለፉት 22 ዓመታት ከሰራቸው አሳፋሪ ስራዎች መካከል ሰፊው የአገራችን መሬት ለሱዳን ተላልፎ ሲሰጥ የስምምነት ፊርማውን ማስቀመጡ ነው። ከዚህ በተጨማሪ እወክለዋለሁ የሚለው የአማራ ህዝብ ከቦታ ቦታ ሲፈናቀል፣ ለአመታት ህዝቡ በኤድስና በወባ እንደቅጠል ሲረግፍ ፣ ወጣቱ ስራ አጥቶ በአደገኛ እጾች ደንዝዞና ተስፋ ቆርጦ የወጣትነት እድሜውን በከንቱ ሲያሳልፍ ብአዴን ዞር ብሎ ለማየት ፈቃደኛ አልሆነም።
የብአዴን ዙፋን ጠባቂነት የሰለቻቸው የድርጅቱ አባላት በተለያዩ ጊዜያት የውስጥ ትግል ሲያደርጉ ቆይተዋል። ብዙዎች በህወሀትና በተላለኪው ብአዴን የጸጥታ ሀይሎች ተገድለዋል፣ አንዳንዶች ድርጀቱን ለቀው ወጥተዋል፣ አንዳንዶች አሁንም በእስር ላይ ይገኛሉ።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በብአዴን ውስጥ ብቻ ሳይሆን በመላ አገራችን ስር ነቀል ለውጥ ለማምጣት ፈቃደኝነታቸውን አሳይተው በግንቦት7 ስር ታቅፈው በመንቀሳቀስ ላይ ያሉት ወጣት አባላት የቀድሞ አባሎች የጀመሩትን ትግል በተደራጀና ስርአት ባለው መልኩ ለማስኬድ የጀመሩት ትግል ንቅናቄው በትኩረት የሚከታተለው ነው። ይህ ትግል ተጠናክሮ በሌሎች ድርጅቶችም ተግባራዊ እንዲሆን ግንቦት7 በተለያዩ የኢህአዴግ ድርጅቶች ውስጥ ላሉ አባሎቹ ጥሪውን ያስተላልፋል።
ግንቦት7 መላውን የኢትዮጵያ ህዝብ ከዘረኛው፣ ዘራፊውና ራዕይ አልባው የህወሀት ጎጠኛ አገዛዝ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመገላገል እና በምትኩ የሁሉም የምትሆን ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመገንባት የጀመረውን ትግል ከመቼውም ጊዜ በላይ አጠናክሮ ቀጥሏል። በዚህ ወሳኝ የትግል ምእራፍ ወቅት የሁሉም ኢትዮጵያዊ ተሳትፎ አስፈላጊ ነው ብሎ ንቅናቄው እንደሚያምን በተደጋጋሚ ሲገልጽ ቆይቷል። በተለይም በኢህአዴግ ድርጅቶች ውስጥ ታቅፈው በመንቀሳቀስ ላይ ያሉ እውነተኛ የስርአት ለውጥ እንዲመጣ የሚፈልጉ ሀይሎች የብአዴን ወጣት የግንቦት7 አባላት እያሳዩት ካሉት እንቅስቃሴ ልምድ በመውሰድ በውስጥ የሚያደርጉትን ትግል አጠንክረው እንዲገፉበት ንቅናቄያችን ጥሪውን ያቀርባል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

Thursday, December 26, 2013

ለኢትዮጵያ ሰማያዊ ፓርቲ ምስክርነት

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
ሰማያዊ ፓርቲን እንደፖለቲካ ድርጅት/ፓርቲ ለምን እንደምደግፈው፣
እ.ኤ.አ ዴሴምበር 15/2013 ከዋሽንግተን ዲሲ ወጣ ብላ በምትገኘው አርሊንግተን ከተማ የስብሰባ አዳራሽ በተዘጋጀው የሰማያዊ ፓርቲ የመጀመሪያ ስብሰባ ላይ ተገኝቼ  ንግግር እስካደረግሁባት ዕለት ድረስ በበርካታ ጥያቄዎች እወጠር ነበር፡፡ አንደኛው ተደጋግሞ የሚጠየቀው ጥያቄ ለበርካታ ዓመታት ገለልተኛ ሆኘ እና ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ወይም ቡድን ጋር ሳልወግን ከቆየሁ በኋላ በአሁኑ ጊዜ ለሰማያዊ ፓርቲ ለምን ያልተቋረጠ ድጋፍ በመስጠት ላይ እንደምገኝ በሚቀርብ ጥያቄ ላይ የሚያጠነጥን ነው፡፡
በኢትዮቱብ ድረገጽ/ethiotube.com በሰጠሁት ቃለ ምልልስ በግልጽ እንዳስቀመጥኩት ለሰማያዊ ፓርቲ ቀጣይነት ያለው ድጋፍ የምሰጥበት ዋና ምክንያት የኢትዮጵያ ትኩስ ወጣት ኃይል የሀገሩን መጻኢ ዕድል የመወሰን እና በሰላማዊ የትግል ሂደት በመሳተፍ ለውጥ ለማምጣት ዝግጁ ነው የሚል ሙሉ እምነት ያለኝ በመሆኑ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ከኢትዮጵያ ህዝብ ውስጥ ከ35 ዓመት የዕድሜ ክልል በታች የሚገኘው የህብረተሰብ ክፍል 70 በመቶ ይሸፍናል፡፡ እንዲሁም በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ በአብዛኛው የሰብአዊ መብት ድፍጠጣ ሰለባ ሆኖ የሚገኘው ወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል ነው፡፡ አብዛኛው የወጣት ህብረተሰብ ክፍል የኢትዮጵያ የማጎሪያ እስር ቤቶች የፖለቲካ ጭቆና እና ማስፈራራት፣ ከህግ አግባብ ውጭ በዘፈቀደ በቁጥጥር ስር የመዋል እና እስራት፣ የስቃይ፣ የመብት እረገጣ እና ከህግ አግባብ ውጭ የእስር ቤት አያያዝ ሰለባ ዒላማ ሆኖ ይገኛል፡፡ አብዛኞቹ የኢትዮጵያ ወጣቶች ስር በሰደደ የስራ አጥነት ወጥመድ ተጠፍረው እና ጥራት ያለው የትምህርት ዕድል እና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት መብታቸውን ተነፍገው በሀገራቸው ላይ የበይ ተመልካች ሆነው ይገኛሉ፡፡ እዚህ ላይ የእኔን “አስረጅ” ምሰክርነት ለማስመዝገብ እንዲሁም ለሰማያዊ ፓርቲ ‘ምስክርነት’ ለመስጠት ያህል  በማያወላውል መልኩ የኢትዮጵያ ወጣቶች የቆሸሸውን የጎሳ ፖለቲካ፣ አስፈሪውን የኃይማኖት ጥላቻ  እና በውሸት ድር እና ማግ የተደወረውን የቅጥፈት ተምኔታዊ ፖለቲካ በጣጥሰው በመጣል “ፍቅር የነገሰበት የኢትዮጵያ ማህበረሰብ” የሚባል አንጸባራቂ ከተማ ከተራራው አናት ላይ እንደሚገነቡ ያለኝን የማይታጠፍ እምነት ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡ ይህ የተቀደሰ ተግባር የዛሬው ወጣት ትውልድ ቋሚ ታሪካዊ ዕጣ ፈንታ ነው የሚል ጽኑ እምነት አለኝ፡፡
የእኔ “አስረጅ” ሆኖ መቅረብ የእራሴን ሀሳብ እና አስተያየት ከመግለጽ ባለፈ በምንም ዓይነት መልኩ የሰማያዊ ፓርቲን፣ የአመራሩን ወይም የአባላቱን ያለፈውን፣ የአሁኑን እና የወደፊቱን ድርጅታዊ እና ድርጅታዊ ያልሆነ አቋም አይወክልም፡፡ በሰማያዊ ፓርቲ ላይ ምንም ዓይነት ሚና የለኝም፡፡ ያለኝ ብቸኛ ሚና ቢኖር “የሰማያዊ ፓርቲ ቁጥር 1 አድናቂ” መሆኔን በኩራት መግለጼ ብቻ ነው፡፡ እዚህ ላይ የእኔ ለሰማያዊ ፓርቲ ‘በአስረጅነት’ በጽናት መቆም ቅንድቦችን ከፍ ሊያደርግ ይችላል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ጠንካራ ደጋፊ በመሆኔ ከአንዳንድ ወገኖች ህብረተሰቡን በእድሜ እየለያየ የሚል ትችት ሲሰነዘር ሰምቻለሁ፡፡ እኔ በእድሜ በመከፋፈል መረጃ የመስጠት ጨዋታ ተጫወትኩ እንጅ በስልጣን ላይ ያለው ገዥው አካል እንደሚያደርገው ሁሉ በዘር ወገኔን በመከፋፈል የቁማር ጨዋታ አልተጫወትኩም፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ወጣቱ ኃይል ብይን እንዲሰጥበት በአክብሮት እጠይቃለሁ፡፡ ጆርጅ ኦርዌል እንዳሉት ‘ዓለም አቀፋዊ ማጭበርበር ተንሰራፍቶ በሚገኝበት በዚህ ዘመን ስለእውነት መናገር አብዮታዊ ድርጊት ነው‘፡፡ በአሁኑ ጊዜ የፖለቲካ አጭበርባሪነት፣ የሞራል ዝቅጠት እና አታላይነት ተንሰራፍቶ በሚገኝበት ሁኔታ እኔ ስለሰማያዊ ፓርቲ እየሰጠሁት ያለው ‘አስረጅነት’ እንደ ‘አብዮታዊ ድርጊት’ ይቆጠራል የሚል ዘርፈ ብዙ አመለካከት አለኝ፡፡
የሰማያዊ ፓርቲ ቁጥር: 1  አድናቂ ለምን ሆንኩ?
በመጀመሪያ ደረጃ ሰማያዊ ፓርቲን የምደግፍበት ምክንያት ከወጣቶች፣ በወጣቶች፣ ለወጣቶች፣ የተቋቋመ የፖለቲካ ፓርቲ ስለሆነ ነው፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ የአብዛኛውን የኢትዮጵያን ህብረተሰብ ፍላጎት እና ጥቅም ሊወክል የሚችል ፓርቲ ስለሆነ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ከኢትዮጵያ ህዝብ ከ35 ዓመት የዕድሜ ክልል በታች ያለው የህብረተሰብ ክፍል 70 በመቶውን ይሸፍናል የሚለውን ሀቅ ላሰምርበት እፈልጋለሁ፡፡ (የሚቀርበውን መረጃ ታሳቢ በማድረግ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ አማካይ የህይወት እድሜ ከ49 – 59 ዓመት ነው፡፡)
የኢትዮጵያ የአቦሸማኔው ትውልድ (ወጣቱ ትውልድ) ብዙሀኑን የኢትዮጵያ ህዝብ ለመወከል የሚያስችል የራሱን የፖለቲካ ፓርቲ ማቋቋም ይፈልጋል፡፡ የአቦሸማኔው ትውልድ ለራሱ/ሷ መናገር፣ ለራሱ/ሷ መቆም፣ ለሴቶች፣ ለወንዶች መቆምን ይፈልጋሉ፡፡ የእራሳቸውን እና የአገራቸውን ዕጣ ፈንታ ሊወስኑ የሚችሉት እራሳቸው ወጣቶቹ ብቻ ናቸው፡፡
የጉማሬዎቹ ትውልድ (የእኔ ትውልድ) የፖለቲካ ፓርቲዎች በጉማሬዎቹ፣ ለጉማሬዎቹ የተቀመሩ እና በእነርሱ የአስተሳሰብ ንፍቀ ክበብ ውስጥ የታጠሩ ፍልስፍናዎች ስለሆኑ ከእረፍትየለሾቹ የኢትዮጵያ አቦሸማኔዎች (የወጣቱ ትውልድ) ህልሞች፣ ውስጣዊ ፍላጎቶች፣ ዓላማዎች እና የጋሉ ስሜቶች የስምምነት እምነቶች ንፍቀ ክበብ ውጭ ናቸው፡፡ እኛ የኢትዮጵያ የጉማሬዎች ትውልድ (የእኔ ትውልድ) የአቦሸማኔዎችን ትውልድ (የወጣቱን ትውልድ) ፍልስፍናአና አስተያየት አንረዳውም፡፡ ይህም በመሆኑ ብዙዎቻችን በጎሳ እና በክልል (“ባንቱስታን” ወይም “ክልላዊ”) የፖለቲካ ጭቃ፣ በሚያጣብቅ የጎሰኝነት ዝቃጭ ቆሻሻ፣ እና በታሪካዊ ምክንያተቢስ ጥላቻ  ውስጥ ለበርካታ ዓመታት ተዘፍቀን ስንዋኝ የቆዬን ስለሆነ ለስኬታማነት የማንበቃ የተሽመደመድን የህበረተሰብ ክፍል ነን፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የኢትዮጵያ የአቦሸማኔ ትውልዶች (የወጣቶች ትውልድ) የጥንቱ ወይም የኋላቀር ፋሽን የጎሳ ማንነት ፖለቲካ እስረኛ መሆን አይፈልጉም፣ እንዲሁም ከጥንት ጊዜ ጀምሮ ከእራሳቸው ጋር በጥብቅ ተቆራኝቶ በታሰረ የታሪክ ክስተት መንገድ ላይ ለመራመድ አይፈልጉም፡፡ እንዲሁም ነጻነታቸውን በማወጅ እና የእራሳቸውን ዕጣ ፈንታ ለመምረጥ በመወሰን የእራሳቸው የሆነቸውን ኢትዮጵያ መፍጠር ይፈልጋሉ፡፡
“የኢትዮጵያ የጉማሬ ቡድን” ታማኝ አባል እንዳለመሆኔ መጠን የኢትዮጵያ የአቦሸማኔ ትውልድ ከኢትዮጵያ የጉማሬ ትውልድ በጣም ልዩነት አለው የሚለውን እውነታ ለመቀበል እቸገራለሁ፡፡ ለእኔ እና ለእኔው የጉማሬ ትውልድ የዱላ ቅብብሎሹን ለአቦሸማኔው ትውልድ በማቀበል ከጎን ሆነን የአቦሸማኔውን ትውልድ በትህትና የምናግዝበት የመጨረሻው ጊዜ እየደረሰ መሆኑን ለመቀበል እቸገራለሁ፡፡ ለዚህም ነው እራሴን ከጉማሬ ትውልድ ወደ “አቦ -ጉማሬ” ትውልድ ያሸጋገርኩት፡፡ ይህንን ሽግግር “የአቦ – ጉማሬ ትውልድ መነሳሳት” በሚለው ትችቴ ላይ መዝግቤ ማስቀመጤ የሚታወስ ነው፡፡
በሁለተኛ ደረጃ የወደፊቱ የኢትዮጵያ ወጣት ዕጣ ፈንታ በጥልቅ ያሳስበኛል፡፡ ከጥቂት ዓመታት በፊት ለማስታወስ እንደሞከርኩት ሁሉ “ደስታ የራቀው እና በመጥፎ ሁኔታ ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ወጣት በጊዜ ቀመር ተሞልቶ ለመፈንዳት በመጠባበቅ ላይ የሚገኝ የሰው ቦምብ የመሁኑን ሀቅ ያመለክታል፡፡ የወጣቱ ተስፋ መቁረጥ፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ ደስታ እየራቀው መሄድ፣ በቅዠት ህይወት ውስጥ መኖር እና ለብዙ ጊዜ በሚቆይ የኢኮኖሚ ቀውስ በመደቆስ ጥንካሬን ማጣት፣ የኢኮኖሚ ዕድሎችን እና ተጠቃሚነትን ያለማግኘት እና የፖለቲካ ጭቆና በገፍ ተንሰራፍቶ መገኘት ሊፋቅ የማይችል አስተማማኝ መረጃ ነው፡፡ ወጣቱ ለነጻነት ያለው ጥልቅ ፍላጎት እና የለውጥ ፈላጊነት ስሜት በእራሱ ማረጋገጫ ነው፡፡ እዚህ ላይ ሊነሳ የሚችለው ብቸኛ ጥያቄ የሀገሪቱ ወጣቶች ለውጥን ሊያመጡ የሚችሉት እየጨመረ በመጣው ወይም በሌላ በሰላማዊ የለውጥ አማራጮች…የሚለው ነው፡፡” ሰማያዊ ፓርቲ ተስፋ ያጣውን የወጣት ኃይል ወደ ሰላማዊ ሽግግር በማምጣት በኢትዮጵያ ውስጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታል የሚል እምነት አለኝ፡፡
ሦስተኛ በወጣት ኃይል አድራጊ እና ፈጣሪነት ላይ በሙሉ ልቤ እተማመናለሁ፡፡ የወጣት ሀሳብ እና ጥልቅ የለውጥ ፈላጊነት ስሜት ልብን፣ አዕምሮን እና ሀገርን የመለወጥ ኃይል አለው፡፡ የወጣት ኃይል በዓለም ላይ ከሚገኙ ጠብመንጃዎች፣ ታንኮች እና የጦር አውሮፕላኖች በላይ የበለጠ ኃይል አለው፡፡ የአሜሪካ የሲቪል መብቶች እንቅስቃሴ የተካሄደው በወጣቶች ኃይል በተከፈለ የጉልበት መስዕዋትነት አማካይነት ነው፡፡ አብዛኞቹ በአመራር ቦታ ላይ የነበሩት እና የመብት ተሟጋቾች ወጣቶቹ የህብረተሰብ ክፍሎች ነበሩ፡፡ ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ በቢርሚንግሀም አላባማ የተካሄደውን የሲቪል መብቶች ሰላማዊ እንቅስቃሴ ሲመሩ የ26 ዓመት ወጣት ነበሩ፡፡ በዚያን ጊዜ ጆን ሌዊስ የ23 ዓመት ወጣት የነበሩ ሲሆን 24 ጊዚያት ታስረዋል፣ እንዲሁም ድርጊቱን ሊያስታውሱት በማይችሉት መልኩ በብዙ አጋጣሚዎች ሰውነታቸው ድቅቅ እስከሚል ድረስ ተደብድበዋል፡፡ እ.ኤ.አ በሜይ 6/1963 በበርሚንግሃም ከ2000 በላይ የሚሆኑ አፍሪካ አሜሪካውያን የሁለተኛ፣ የመለስተኛ ሁለተኛ እና የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ተማሪዎች የዘር መድልኦን በመቃወም ሰልፍ በመውጣታቸው ብቻ ለአሰቃቂው እስር ተዳርገዋል፡፡
ወጣት አሜሪካውያን በቬትናም ላይ በእብሪት በመነሳሳት የተካሄደውን ጦርነት እንዲቆም አድርገዋል፡፡ በካሊፎርኒያ የዩኒቨርስቲ የተጀመረው የመናገር ነጻነት እንቅስቃሴ በአሜሪካ የመናገር ነጻነትን እና የዩኒቨርስቲ አካዳሚ ነጻነትን አጎናጽፏል፡፡ ያለወጣቱ ድምጽ መስጠት ባራክ አቦማ ለፕሬዚዳንትነት መመረጥ አይችሉም ነበር፡፡ ኮሚኒስታዊ ገዥዎችን እና በቅርቡም በሰሜን አፍሪካ እና በመካከለኛው ምስራቅ አገሮች ለመለወጥ አስቸጋሪ ናቸው ተብለው ይታሰቡ የነበሩትን ርህራሄየለሽ አምባገነኖች በሰላማዊ ትግል አንኮታኩቶ በመጣሉ እረገድ ወጣቱ ኃይል ወሳኝ የሆነ ሚና ተጫውቷል፡፡
በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ በስልጣን ወንበር ላይ ተፈናጥጠው የሚገኙት ገዥዎች የንጉሳዊውን አገዛዝ እና አምባገነናዊውን የወታደራዊ መንግስት በትጥቅ ትግል ለማንበርከክ ሲፋለሙ የነበሩ ወጣት “አብዮተኞች” ነበሩ፡፡ በእርጅና የእድሜ ጊዚያቸው ግን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ከኢትዮጵያ ምድር ለማስወገድ ሲፋለሙት የነበረውን ጭራቅ ሆነው ተቀምጠዋል፡፡ ከዚህ አንጻር በኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ህብረተሰብ ለመመስረት ለበርካታ ዘመናት መስዕዋትነትን በመክፈል የእራሳቸውን ድርሻ በመወጣት ላይ ባሉት የኢትዮጵያ ወጣቶች ኃይል ላይ ሙሉ እምነት አለኝ፡፡ እ.ኤ.አ በ2005 አሁን በስልጣን ላይ ያለው የኢትዮጵያ ገዥ አካል ታጣቂዎች እንደ አበደ ውሻ በአዲስ አበባ መንገዶች ላይ በመክለፍለፍ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶችን በጥይት ጨፍጭፈዋል ገድለዋል፣ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩትን ደግሞ ለእስራት ዳርገዋል፡፡ (በዚያን ጊዜ በሰው ልጅ ህይወት ላይ በጣም አስደንጋጭ እና አስፈሪ የሰብአዊ መብት ድፍጠጣ ወንጀል በማየቴ በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ተሟጋችነት አንደቀላቀል ተገድጃለሁ፡፡) በአሁኑ ጊዜም እንኳ የኢትዮጵያ ወጣቶች ለዴሞክራሲ፣ ለህግ ልዕልና፣ ለነጻነት እና ለሰብአዊ መብት ጥበቃ ሲባል የደም፣ የላብ እና የእንባ መስዕዋትነት በመክፈል ላይ ይገኛሉ፡፡ የኢትዮጵያ ምርጡ እና ብሩህ አዕምሮ ያለው ወጣት እየተቀጣ፣ ፍርደገምድል ፍርድ እየተበየነበት፣ እየታሰረ፣ እና ጸጥ እረጭ ብሎ እንዲገዛ እየተደረገ ነው፡፡ ከእነዚህ የወጣት ዝርዝር የመጀመሪያው እረድፍ ላይ የሚገኙት ብርቱካን ሚደቅሳ፣ እስክንድር ነጋ፣ አንዷለም አራጌ፣ ርዕዮት ዓለሙ፣ በቀለ ገርባ፣ አቡበካር አህመድ፣ ውብሸት ታዬ፣ ኦልባና ሌሊሳ፣ አህመዲን ጀቤል፣ አህመድ ሙስጣፋ፣ ተመስገን ደሳለኝ፣ በቅርቡ ከህይወት የተለየው የኔሰው ገብሬ እና ሌሎች ለቁጥር የሚያታክቱ ትንታግ የኢትዮጵያ ወጣቶች ናቸው፡፡
በመጨረሻ ሆኖም ግን አስተዋጽኦው ቀላል ካልሆነው ከሰማያዊ ፓርቲ ፕሮግራም ጋር ሙሉ በሙሉ እስማማለሁ፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ በደንብ አስቦበት እና የሀገሪቱን ዘርፈ ብዙ ችግሮች ለመቅረፍ የሚያስችል ተግባራዊ ፕሮግራም ነድፎ የሚንቀሳቀስ ፓርቲ ነው፡፡ ከእኔ ልዩ አተያይ እና ስጋት አንጻር በፍትሀዊ አስተዳደር፣ በሰብአዊ መብቶች እና በህግ የበላይነት አተገባበር ላይ ትኩረት በማድረግ የፓርቲውን ፕሮግራም ስገመግመው በጠንካራ መሰረት ላይ የተዋቀረ ልዩ ፓርቲ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡ ፓርቲው ሙሉ በሙሉ ነጻ የሆነ እንዲሁም ከፖለቲካ ተጽዕኖ እና ጣልቃገብነት ፍጹም ነጻ የሆነ እና ብቃት ያለው የፍትህ ስርዓት በሀገሪቱ እንዲመሰረት ድጋፍ ያደርጋል፡፡ ዳኞች ሲያጠፉ መከሰስ ያለባቸው መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በሙያቸው በቋሚነት ጡረታ እስከሚወጡበት ጊዜ ድረስ ተቀጥረው እንዲሰሩ ያደርጋል፡፡ ፓርቲው ህገመንግስታዊ ፍርድ ቤት ከነሙሉ ስልጣኑ ጋር እንዲቋቋም ድጋፍ ያደርጋል፡፡ ኢትዮጵያ ፈርማ ባጸደቀቻቸው ዓለም አቀፍ ውሎች እና ስምምነቶች ለመገዛት እና ለተግባራዊነታቸውም ዕውን መሆን ፓርቲው ጠንክሮ እንደሚሰራ ቃል ገብቷል፡፡ የግለሰብ መብቶችን ጥበቃ የመናገር እና የእምነት ነጻነቶችን ጨምሮ ተግባራዊ እንደሚያደርግ ፓርቲው ቃል ገብቷል፡፡ መንግስት እና ኃይማኖት በግልጽ መለያየት እንዳለባቸው ፓርቲው በጽኑ ያምናል፡፡ ፓርቲው ማንኛውንም በብዙሀን መገናኛ ዘዴዎች ላይ የሚደረግን ቅድመ ምርመራ አጥብቆ ይቃወማል፣ እንዲሁም ከህግ አግባብ ውጭ የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች እና ማህበራት እንዳይዘጉ ያደርጋል፡፡ የሀገሪቱ የጦር እና የደህንነት ኃይል ታማኝነቱ ለሀገሪቱ ህገመንግስት መሆን እንዳለበት እና በምንም ዓይነት መልኩ ለፖለቲካ ፓርቲ፣ ለጎሳ ቡድን፣ ለክልል ወይም ለሌላ አካል ታማኝ መሆን እንደሌለበት ፓርቲው በፕሮግራሙ ላይ አጽንኦ በመስጠት አስፍሮታል፡፡ የፓርቲው የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ፣ የማህበራዊ እና የባህል ጉዳዮችም እንደዚሁ በተመሳሳይ መልኩ ትኩረትን በጣም የሚስቡ ናቸው፡፡
ሰማያዊ ፓርቲን  እንደ  ንቅናቄ እና የኢትዮጵያ የአቦሸማኔዎች (ወጣቶች) ትውልድን እውነተኛ ድምጽ ለምን እንደምደግፍ፣
እንደ እራሴ ሀሳብ ሰማያዊ ፓርቲ እንደማንኛውም ተወዳድሮ ስልጣን በመያዝ ወደ ስልጣን ቢሮ ከሚገባ  የፖለቲካ ድርጅት የበለጠ ነው፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ እንደፖለቲካ ድርጅት እራሱን ቢያዘጋጅ እና በተለመደው መልክ ምርጫ ቢያሸንፍ እና የፓርላማ ወንበር ቢይዝ ምንም አዲስ የማገኘው ነገር የለም፡፡ ከ80 በላይ “የተመዘገቡ ፓርቲዎች” ባሉባት ሀገር (በጣም አብዛኞቹ ለይስሙላ የተቋቋሙ የጎሳ የፖለቲካ ፓርቲዎች) እና ገዥው “ፓርቲ” በ99.6 በመቶ በሚያሸንፍበት ሁኔታ ከግማሽ ነጥብ በመቶ ያነሰ ድምጽ ለማግኘት እንደሰማያዊ ፓርቲ ሁሉ ሌላ ፓርቲ ተመዝግቦ ለዚህች በጣም በጣም ትንሽ ለሆነችው ድምጽ ለመወዳደር የመሞከሩን አስፈላጊነት ትርጉምየለሽ ያደርገዋል፡፡ ለዚህም ነው ሰማያዊ ፓርቲን በኢትዮጵያ ከወጣቶች፣ ለወጣቶች፣ በወጣቶች የተቋቋመ የወጣቶች ንቅናቄ ነው የሚል እምነት ያለኝ፡፡
“የሰማያዊ ፓርቲ ንቅናቄን” የኢትዮጵያ ወጣቶች ለእራሳቸው እና ለወደፊቱ ትውልድ የሚተላለፍ ህልማቸውን እና ሀሳቦቻቸውን የሚተገብር ድርጅታዊ ተቋም አድርጌ እወስወደዋለሁ፡፡ እንደ ንቅናቄ ሰማያዊ ፓርቲ በብዙ የአቅም ደረጃዎች ላይ በማገልገል ላይ ይገኛል፡፡ የኢትዮጵያን ወጣቶች ስለብዙው የሀገራቸው ታሪክ፣ ልማዶች እና ባህሎች እንዲያውቁ የሚያደርግ “የትምህርት” ተቋም ነው፡፡ የኢትዮጵያ ወጣቶች የማትከፋፈል የአንዲት ኢትዮጵያ፣ ኃያል ወራሪውን የአውሮፓ ኃይል አሸንፋ እና አሳፍራ የመለሰች የኩሩ አርበኞች ዘር የትውልድ ሀረግ መሆናቸውን ያስተምራል፡፡ እንደ አሁኑ ሳይሆን በአንድ ወቅት ኢትዮጵያ በዓለም እና በአፍሪካ ለሚኖሩ ጥቁር ህዝቦች የኩራት ፈርጥ ነበረች፡፡ የአሁኑ የሰማያዊ ፓርቲ ንቅናቄ የቀደመውን ኩራታችንን እንደገና መልሶ ለኢትዮጵያውያን ህዝቦች የማጎናጸፍ ዓላማን ሰንቆ ተነስቷል፡፡
“የሰማያዊ ፓርቲ ንቅናቄን” ዋና ዋና ዕሴቶች እጋራለሁ፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ገዥዎችን እና ኢፍትሀዊነትን በሰላማዊ የትግል ስልት መንገዶች የማስወገድ እምነት አለው፡፡ በዓለም ላይ በየትኛውም ቦታ ገዥዎችን እና ኢፍትሀዊነትን በሰላማዊ የትግል ስልቶች በመጠቀም ለማስወገድ እሰብካለሁ፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ በኢትዮጵያ ወጣቶች የሽግግር ኃይል ላይ እምነት አለው፡፡ ባለፉት ሰባት ዓመታት በኢትዮጵያ “እና በአፍሪካ” ላይ ወጣቶች የጻፍኳቸውን የሰኞ ዕለታዊ ትችቶች በሙሉ መልክ በማስያዝ በጥራዝ ቢዘጋጁ የኢትዮጵያ ወጣቶችን የሽግግር ኃይል በተጨባጭ የሚያመላክት ማስረጃ ይሆናልሉ፡፡ የእኔ መፈክርአሁንም በፊትም ወደፊትም ፣ “የኢትዮጵያ ወጣቶች ተባበሩ፣ በፍጹም እጅ እንዳትሰጡ፣ ኃይል ለኢትዮጵያ ወጣቶች!” ነው፡፡
የሰማያዊ ፓርቲ ንቅናቄ አንድ ግብ ብቻ አለው፣ “ፍቅር የነገሰበትን የኢትዮጵያ ማህበረሰብ” መፍጠር፣ ልክ ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ በረዥሙ የትግል ጉዟቸው በአሜሪካ የሰብአዊ እና የሲቪል መብቶችን በማለም “ፍቅር የነገሰበት ማህበረሰብን” ለመመስረት እንዳደረጉት ተጋድሎ ሁሉ፡፡ ዶ/ር ኪንግ እንዲህ ብለው አስተማሩ፣ “የሰላማዊ ትግል ማህበራዊ ለውጥ መጨረሻው ዕርቅ ነው፣ መጨረሻው ኃጢያትን ተናዝዞ ንስሀ መግባት ነው፣ መጨረሻው ፍቅር የነገሰበትን ማህበረሰብ መመስረት ነው፣ እንግዲህ ይህ ዓይነቱ አስተሳሰብ እና ፍቅር ነው በባላንጣነት የሚተያዩትን ወገኖች ወደ ጓደኝነት የሚያመጣው፡፡” “ፍቅር የነገሰበት የኢትዮጵያ ማህበረሰብ“ ከክልላዊነት (ባንቱስታን) አመድነት በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚወጣ እምነቴ የጸና ነው፡፡
“ፍቅር የነገሰበት የኢትዮጵያ ማህበረሰብ” የሰማያዊ ፓርቲ ንቅናቄ መሰረቱ አንድነት፣ ሰላም እና ተስፋ ነው፡፡ “ፍቅር የነገሰበት የኢትዮጵያ ማህበረሰብ” ሰው በመሆኑ ብቻ አንድ ይሆናል፣ በሌላ በኩል ደግሞ ከከፋፋይ የጎሰኝነት እና ከአፍቅሮ የጎሰኝነት ስሜት ነጻ ይሆናል፡፡ ይህ ዓይነቱ ማህበረሰብ እኩልነት፣ ፍትሀዊነት እና ተጠያቂነት ያለው ህብረተሰብ ለመመስረት ጥረት ያደርጋል፡፡ “ፍቅር የነገሰበት የኢትዮጵያ ማህበረሰብ“ ከእራሱ እና ከጎረቤቱ ጋር ሰላም ፈጥሮ የሚኖር ህብረተሰብ ነው፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ከጎሳ አለመቻቻል እና ጥላቻ ነጻ የሆነ እንዲሁም ከፍርሃት፣ ጥልቅ ጥላቻ እና ከገዥዎች እና ከጨቋኞች ነጻ የሆነ ማህበረሰብ ይፈጥራል የሚል እምነት አለኝ፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ደኃ እና ሀብታም፣ ወጣት እና ሽማግሌ፣ ወንድ እና ሴት፣ ክርስቲያን እና ሙስሊም… ለማለም ነጻ፣ ለማሰብ ነጻ፣ ለመናገር፣ ለመስማት እና ለመጻፍ ነጻ፣ ከጣልቃገብነት ነጻ ሆኖ ለማምለክ፣ ለመፍጠር ነጻ፣ ለመስራት ነጻ እና ነጻ ለመሆን ነጻ የሆነ ዓላማ ይዞ ነው የተነሳው፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ንቅናቄ ሰላምን በአግባቡ በመጠቀም ጥላቻን፣ የጥላቻ መንፈስን፣ ለመጣላት መቸኮልን፣ ወደ ጓደኝነት፣ መተሳሰብ እና መከባበር በማሻጋገር ለኢትዮጵያ ህዝብ ሰላምን ያመጣል የሚል እምነት አለኝ፡፡ ንቅናቄው ከመራራ ትችት በውይይት፣ ከመቃረን በስምምነት፣ ከጥላቻ በፍቅር፣ እና ጭካኔን፣ ወንጀለኝነትን እና ታጋሽየለሽነትን ለማሸነፍ የሰው ልጅን ክብር ከፍ የሚያደርጉትን መርሆዎች እንደሚከተል እምነቴ የጸና ነው፡፡ “ፍቅር የነገሰበት የኢትዮጵያ ማህበረሰብ“ “የተስፋ እና የህልሞች መሬት” ነው፡፡ ይህ ማህበረሰብ ወጣቶች ለእኩል ዕድሎች፣ ለእኩል መብት እና ፍትህ እንዲያስቡ የሚያደርግ ነው፡፡ ይህ ማህበረሰብ የኢትዮጵያ ወጣቶች ነጻ ሆነው ተስፋዎቻቸውን እና ህልሞቻቸውን በጋራ መካፈል እንዲችሉ የሚያበቃ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ወጣቶች የማይገታ ተስፋ አንዳላቸው ጽኑ እምነት አለኝ፡፡
ለሰማያዊ ፓርቲ ምን ማድረግ እንዳለብን እንጠይቅ፣
ሁሉም ኢትዮጵዊ በተለይም የእኔ የጉማሬው ትውልድ ከሰማያዊ ፓርቲ ንቅናቄ ጎን እንድንቆም  አበረታታለሁ፣ እማጸናለሁም፡፡ አውቃለሁ፣ ብዙዎቻችሁ ቀደም ሲል ድጋፋችሁን ለመስጠት በሞከራችሁበት ጊዜ በተፈጠረው ያልተሳካ የትግል ውጤት ምክንያት ተገቢነት ያላቸው ጥያቄዎች፣ ብዥታዎች፣ እና ጥርጣሬዎች ሊኖሯቹህ እንደሚችሉ እገነዘባለሁ፡፡ “እነዚህ ወጣት እና የአመራር ልምድ የሌላቸው ሰዎች ትክክለኛውን ነገር የሚሰሩ ለመሆናቸው ምን ማስተማመኛ አለን?“ በማለት ተጠይቂያሁ፡፡ እኔም እንዲህ የሚል መልስ ሰጠሁ፣ “ልምድ ያለን እና እምነት የሚጣልብን የጉማሬው ትውልድ አመራሮች የሆንነው ከዚህ ቀደም እንዴት ሰራን?“ አፍሪካ በማያቋርጥ አምባገነናዊ የአገዛዝ መዳፍ ስር ወድቃ ስለምትገኝ የወጣቱን የህብረተሰብ ትኩረት የሚስቡ በርካታ ነገሮች እየተፈጠሩ ነው፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ንቅናቄ አመራሮች፣ አባላት እና ደጋፊዎች ስብዕናዎቻቸው ከምን ከምን ነገሮች እንደተዋቀሩ አሳይተውናል፡፡ የተዋቀሩባቸው የመሰረት ድንጋዮች በዝርዝር ሲታዩ የሚከተሉትን ያካትታል፡ ድፍረት፣ የሞራል ጽናት፣ ስነስርዓት፣ ብስለት፣ ጀግንነት፣ ክብር፣ የመንፈስ ጽናት፣ ፈጣሪነት፣ ትህትና፣ ሀሳብ አፍላቂነት እና እራስን ለመስዋዕትነት ማዘጋጀት ናቸው፡፡ ስብዕናዎቻቸውን በማክበር ላለመንበርከክ ሲሉ በቁጥጥር ስር ውለዋል፣ ታስረዋል፣ እንዲሁም ተደብድበዋል፡፡ ሰላማዊ ትግሎቻቸውን አላቋረጡም፡፡ እኛን በማሳመን ሙሉ ድጋፋችንን ከማግኘታቸው በፊት ሌላ ምን ተጨማሪ መስዕዋትነት መክፈል ይኖርባቸዋል? ወጣቶች እና አዲስ ነገር ለማምጣት ጥልቅ ፍላጎት ያላቸው ናቸው፣ በሰላማዊ ትግል ለውጥ ለማምጣት ተገቢው ልምድ ያላቸው ሲሆን ይህንኑ ልምዳቸውን እስከመጨረሻው ይቀጥሉበታል፡፡
አንዳንድ ሰዎች ሰማያዊ ፓርቲ ለገዥው አካል ወይም ለሌላ ድብቅ ዓላማ ላላቸው ኃይሎች ተቀጣሪዎች ላለመሆናቸው ምን ማረጋገጫ አለ በማለት ይጠይቃሉ፡፡ ይህንን ጉዳይ አስመልክቶ የምለው ነገር ቢኖር የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች፣ አባላት እና ደጋፊዎች የገዥው አካል ታማኝ ሎሌዎች ናቸው ብለን የምናስብ ከሆነ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም፣ ፕሮፌሰር ያዕቆብ ኃይለማርያም እና ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያምም ሊጠቀሱ የሚችሉ ታማኝ ሎሌዎች ናቸው ማለት ነው፡፡ ገዥው አካል ብልህ ከሆነ ሰማያዊ ፓርቲ ስለየህግ የበላይነት እና ስለዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ያሉትን ፕሮግራሞች በመገናኛ ብዙሀን ለማስተላለፍ እንዲችል መፍቀድ ይኖርበታል፣ ይህን ካደረገ እኔ ለዚህ ደጋፊ ነኝ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ገዥው አካል ሁሉንም የፖለቲካ እስረኞች (በሚስጥር እስር ቤቶች የሚገኙትን ጨምሮ) የሚለቅ ከሆነ፣ ጨቋኝ ህጎችን የሚሰርዝ ከሆነ፣ የሰብአዊ መብት ድፍጠጣዎችን እና ምርጫ ማጭበርበርን የሚያቋም ከሆነ ከመንገድ በመውጣት የመጀመሪያ በመሆን እነሱን በማሞገስ የምዘምር እሆናለሁ፡፡ ጉዳዩ በስልጣን ላይ ስላሉት ሰዎች አይደለም፣ ሆኖም ግን ጉዳዩ በስልጣን ላይ ስላሉት ጭራቃዊ ድርጊት ስለሚፈጽሙት ሰዎች እንጅ፡፡
ባለፉት አስርት ወይም ከዚያ በላይ ዓመታት ተመስርተው በመንቀሳቀስ ላይ የነበሩት እና በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙት የፖለቲካ ድርጅቶች ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ስኬታማ ሳይሆኑ እንደቀሩ አንዳንድ ሰዎች ይነግሩኛል፡፡ እንዲህ በማለትም ይጠይቁኛል፣ “ሰማያዊ ፓርቲም ስኬታማ ሳይሆን የሚወድቅ ላለመሆኑ ምን ዋስትና አለህ?“ ሰማያዊ ፓርቲ ላለመውደቁ ምንም ዓይነት ዋስትናዎች የሉም፡፡ ስኬታማ ሳይሆን የሚወድቅ ከሆነ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች እና አባላት ጽናት እና እራስን ለስነስርዓት ያለማስገዛት፣ የዓላማ ጽናት እና እራስን መስዕዋት ለማድረግ ያለመቻል ጉድለት ሊሆን አይችልም፡፡ በዋናነት ለውድቀቱ ምክንያት ሊሆን የሚችለው ድጋፍ ያለማግኘት፣ ቅን መንፈስ ያለመኖር፣ በእራስ የመተማመን ጉድለት፣ የለጋሽነት እጥረት እና በአገር ውስጥ ካለው ኢትዮጵያውያን/ት ወገኖች እና ከዲያስፖራው ማህበረሰብ የማቴሪያል እና የሞራል ድጋፍ ለማግኘት ያለመቻል ነው፡፡ ፓርቲው ስኬታማ ባይሆን እና ለውድቀት ቢዳረግ በእብሪትነት ተነሳስተን፣ የሌባ ጣታችንን ወደ ፓርቲው በመቀሰር፣ “ተናግሬ አልነበረም!“ ስንል ሦስቱ ጣቶቻችን ደግሞ ቀስ ብለው ወደ እኛ እያመለከቱ መሆናቸውን መዘንጋት የለብንም፡፡ ኔልሰን ማንዴላ እንዲህ ሲሉ ተማጽነዋል፣ “እኔን በማስመዘግባቸው ስኬቶች አትገምግሙኝ፣ይልቁንም ምን ያህል ጊዜ እንደወደቅሁ እና ከውድቀቶች ተመልሸ እንደተነሳሁ እንጅ” ብለዋል፡፡ ከዚህ አንጻር ሰማያዊ ፓርቲ ወደፊት ምን ያህል ጊዜ አዳልጦት ይወድቃል ብለን ከመገምገም ይልቅ ፓርቲው በእኛ እገዛ እና ድጋፍ ከውድቀቱ እንደገና ለመነሳት ምን ያህል ጊዜ ጥረት ያደርጋል የሚለውን ነው መገምገም የሚኖርብን፡፡
ባለፉት በርካታ ጊዚያት እንደታየው የሚያዋጡት የገንዘብ ድጋፍ አላግባብ ሊባክን ይችላል የሚል ስጋታቸውን አንዳንድ ሰዎች ገልጸውልኛል፡፡ ጠንካራ የሆኑ የተጠያቂነት እና ግልጸኝነት ዋስትናዎችን ማግኘት ይፈልጋሉ፡፡ እንዲህ ብለውም ይጠይቁኛል፣ “ባለፉት ጊዚያት ሌሎች እንዳደረጉት ሁሉ ሰማያዊ ፓርቲም በእርሱ ላይ ያለንን እምነት ላለመሸርሸሩ በምን ሁኔታ ማረጋገጥ እንችላለን?”
በሰሜን አሜሪካ ያለው የሰማያዊ ፓርቲ የድጋፍ ስብስብ በጣም ጠንካራ እና በስነስርዓት የታነጸ የኢትዮጵያ ወጣት ኃይል ስለሆነ ከዚህ ስብስብ ጋር መተዋወቄ እና አብሬም መስራቴ ታላቅ ክብር እና ደስታ ይሰጠኛል፡፡ እነዚህ ወጣት ኢትዮጵያውያን/ት የኢትዮጵያን ወጣቶች ትግል ለመደገፍ ከኪሳቸው በርካታ ገንዘብ በማውጣት በስራ ላይ እንዲውል በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ የሙያ ስብጥራቸውን ስንመለከት ወጣት ፕሮፌሽናሎች፣ በንግድ የሙያ ዘርፍ የተሰማሩ ወንዶች እና ሴቶች እንዲሁም የኢትዮጵያን የጎሳ፣ የጾታ እና የባህል ህብረ ብሄር የሚወክሉ ናቸው፡፡ የተያቂነትን እና ግልጸኝነትን ዋጋ በሚገባ የተገነዘቡ ናቸው፡፡ እርስ በእርሳቸው በመተማመን እና ለእሴቶቻቸው ተገዥ በመሆን ድጋፋቸውን የሚሰጡ ናቸው፡፡ ለወጣቶቹ ዕድሎችን በመስጠት መሞከር እና ለምሰጠው የድጋፍ ገንዘብ ችግር የለብኝም፣ ምክንያቱም ወጣቶቹ የዚህ አይነት ዉርደት ላይ መውደቅ አንደማይሹ ተገንዝበአለሁ፡፡ መርህን በሚያከብሩት የኢትዮጵያ ወጣቶች እና ህዝቦች ታላቅ እምነት አለኝ፣ የኢትዮጵያ ወጣቶች ትክክለኛውን ነገር ይሰራሉ የሚል እምነት የእኔ ዋስትና ነው፡፡
እ.ኤ.አ ዴሴምበር 15/2013  በኣርሊንግቶን ከተማ አዳራሽ ለመጀመሪያ ጊዜ በተጠራው የሰማያዊ ፓርቲ ስብሰባ ላይ በመገኘት ባደረግሁት ንግግር የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ይልቃል ጌትነት እርዳታ ለመሰብሰብ እና ለኑስ አምስት ሳንቲም ልመና ወደ አሜሪካ አልመጣም በማለት ለተሰበሰበው ታዳሚ ተናግሬ ነበር፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ከእኛ በሰሜን አሜሪካ ከምንኖር ኢትዮጵያውያን/ት እርዳታ ወይም የገንዘብ ልገሳ አይፈልግም፡፡ ይልቁንም ይልቃል ወደ አሜሪካ የመጣው ገዥው አካል በሰማያዊ ፓርቲ ላይ እያደረሰ ያለውን አስቸጋሪ ሁኔታ፣ የህግ ስርዓት ሂደቱን፣ በአባላቱ ላይ የሚደርሱባቸውን ችግሮች፣ ጨካኝ አምባገነናዊ ስርዓት ባለበት ሁኔታ ፓርቲው ዓላማዎቹን ለማሳካት እንዴት እየሰራ እንዳለ እና የኢትዮጵያ ወጣቶች ነጻ እና ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመገንባት በሚደረገው ትግል ላይ ያሏቸውን ህልሞች እና ተስፋዎች ለእኛ ለወገኖቹ ለማካፈል ነው፡፡
በአሜሪካ ከተሞች ለሰማያዊ ፓርቲ ስብሰባዎች በተያዙ ፕሮግራሞች ሁሉ በመገኘት በኢትዮጵያ በሰላማዊ መንገድ ለውጥ እንዲመጣ ለሚታገሉት ባለራዕይ ወጣቶች ለይልቃል፣ ለሰማያዊ ፓርቲ አባላት እና ለንቅናቄው ድጋፍ ሰጭ ጀግኖች ወጣቶች አቀባበል ማድረግ እንዳለብን ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡ በከተማው የስብሰባ አዳራሽ የሚካሄዱትን ስብሰባዎች ወጣት መሪዎች እንደእነ ይልቃል፣ እስክንድር፣ አንዷለም፣ ርዕዮት እና ሌሎች ብዙዎቹ በግል ያደረጓቸውን የጀግንነት ስራዎች በማወደስ ብቻ የምናልፈው ሳይሆን በአዳራሹ ማክበር ያለብን ሌሎችም ወጣት ጀግኖች በአደባባይ በመንገዶች በመውጣት ተቃውሟቸውን እንዲህ እያሉ ላሰሙት ጭምር ነው፣ “አንለያይም! አንለያይም!“ (እንደተባበርን እንኖራለን!) ወይም ኢትዮጵያ፣ አገራችን! ኢትዮጵያ፣ አገራችን! (ኢትዮጵያ፣ የእኛ አገር!)፡፡ (አንለያይም! አገራችን፣ ኢትዮጵያ! በማለት ወጣቶቹ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ሲጮኹ ስሰማ ሁልጊዜ ይነሽጠኛል፡፡)
የሰማያዊ ፓርቲ መሪ ይልቃል እዚህ በመካከላችን መገኘቱ ለእኔ እ.ኤ.አ በ2005 በተደረገው ምርጫ የተጭበረበረውን ድምጽ በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተው በአምባገነኑ መሪ ትዕዛዝ በታጣቂዎች በግፍ ያለቁት ወጣቶች እንዳልሞቱ የሚያደርግ ኩራትን በመፍጠር እለቱን እንድናስታውሰው ያደርገናል፡፡ ይህ ዕለት የህግ የበላይነት ምንም ይሁን ምን መቀጠል እንዳለበት እና ለነጻ እና ለፍትሀዊ ምርጫ ዕውን መሆን በሰላማዊ ትግል ሲፋለሙ ለነበሩት እና በግፍ ለተገደሉት ወጣቶች መታሰቢያ ይሆን ዘንድ የይልቃል በመካከላችን መገኘት ሕያው ምስክር ነው፡፡
ለሰማያዊ ፓርቲ ንቅናቄ ምን ማድረግ እንችላለን? የተሸለ ጥያቄ ሊሆን የሚችለው ለወጣት ጀግኖቻችን፣ ሲፋለሙ ህይወታቸውን ላጡት፣ በእስር ቤት በመማቀቅ ላይ ለሚገኙት፣ የግርፋት ስቃይ እየተፈጸመባቸው ላሉት፣ በየዕለቱ ማስፈራራት ለሚፈጸምባቸው፣ ስቃይ እና ውርደት ለሚፈጸምባቸው  ምስጋናችንን፣ ክብር መስጠታችንን እና አድናቆታችንን እንዴት ነው መግለጽ የምንችለው? የሚል ይሆናል፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ ማግኘት የሚችለውን ማንኛውንም ድጋፍ ማግኘት ይፈልጋል፡፡ የሞራል ድጋፋችንን ይፈልጋሉ፡፡ የእኛን ማበረታታት ይፈልጋሉ፣ እኛ በእነርሱ ላይ እምነት ያለን መሆኑን ማወቅ ይፈልጋሉ፡፡ ከሁሉም በላይ ወጣቶችን በሙሉ ለመድረስ እንዲችሉ፣ ለትምህርት እና ለግንዛቤ መፍጠሪያ ፕሮግራሞች ማስፈጸሚያ ሊውሉ የሚችሉ ከእኛ የማቴሪያል ድጋፍ ይፈልጋሉ፡፡ ድርጅታዊ ህልውናቸውን ለማጠናከር እና በመላ አገሪቱ ቀጣይነት ባለው መልኩ መንቀሳቀስ እንዲችሉ የእኛን የማቴሪያል ድጋፍ ይፈልጋሉ፡፡ ጠንካራ የህግ መከላከያ ገንዘብ ለማግኘት የእኛን ድጋፍ ይፈልጋሉ፡፡ በአፍሪካ አህጉር አላግባብ በበለጸጉ፣ ሙስናን በሚያራምዱ እና ምህረትየለሽ አምባገነኖች ላይ ትግል ለማድረግ የማቴሪያል ድጋፍ ይፈልጋሉ፡፡
ለሰማያዊ ፓርቲ ንቅናቄ የምናደርገው የገንዘብ ድጋፍ በሰላማዊ ትግል ለፍትህ፣ ለእኩልነት፣ ለዴሞክራሲ እና ለሰብአዊ መብቶች መጠበቅ የሚያደርጉትን በቅርብ በመደገፍ ምስጋናቸንን በማቅረብ ከጎናቸው መሆናችንን ለመግለጽ ነው፡፡ ለሰማያዊ ፓርቲ ንቅናቄ ያለን ስጦታ ሰላሟ በእራሷ የተጠበቀ ኢትዮጵያን ለማየት ሀብትን ማፍሰስ ነው፡፡ እንሰጣለን፣ እንለግሳለን፣ በዚህም መሰረት ቀጣዩ የኢትዮጵያ ትውልድ በእኛ ስህተት እና ድንቁርና በተፈጠረው ሁኔታ ሳይቸገር በአዲሲቱ ኢትዮጵያ በሰላም ይኖራል፡፡ የእኛን ወጣት ትውልድ መደገፍ የእያንዳንዳችን እና እንደሀገርም የማህበረሰባችን ኃላፊነት ነው፡፡ እኛ ልጆቻችንን፣ ሁሉንም በኢትዮጵያ ያሉ ወጣቶችን ካልረዳን… ማን እንዲረዳ ይፈለጋል?
ሰማያዊ ፓርቲ ለእኛ ምን እንደሚያደርግልን እንጠይቅ፣
እ.ኤ.አ በኦገስት 2012 በአንድ ትችቴ ላይ “የአቦሸማኔው ትውልድ፣ የጉማሬው ትውልድ” በሚል ርዕስ እንዲህ ስል ጠየቅሁ፣ “ኢትዮጵያን ሊጠብቅ ሊያድን የሚችል ማን ነው?“ በሰላማዊ መንገድ በኢትዮጵያ ለውጥ ለማምጣት መከተል ያለብን መንገድ አገራዊ ውይይት ማድረግ እንደሆነ የኢትዮጵን ወጣቶች ተማጽኛለሁ፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ አቤቱታዬን ለበርካታ ጊዚያት በተደጋጋሚ ሳቀርብ ቆይቻለሁ፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ንቅናቄን በመጀመሪያ በተጠናከረ መልኩ በእራሳቸው በፓርቲው አባላት ላይ በቀጣይም በመላው የኢትዮጵያ ወጣት ማህበረሰብ ላይ የዕርቅ ውይይት ማድረግ እንደሚያስፈልግ ጥሪ አቅርቤ ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የዕርቅ ውይይት በኢትዮጵያ የወጣቱ ህብረተሰብ ውይይት መጀመር ቀጥሎ የሚፈጸም ይሆናል የሚል እምነት አለኝ፡፡
የኢትዮጵያ የአቦሸማኔ ትውልድ እራሳቸውን ማጠናከር አለባቸው፣ የእራሳቸውን የፖለቲካ እና የማህበራዊ ቦታ መፍጠር አለባቸው፡፡ አገራቸው ከአምባገነንነት ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት በሰላማዊ መንገድ ሽግግር ማድረግ እንድትችል የእራሳቸውን አጀንዳ በመቅረጽ ወጣቶቹ ዘርፈ ብዙ ውይይቶችን መጀመር አለባቸው፡፡ የቋንቋ፣ የኃይማኖት፣ የጎሳ፣ የጾታ፣ የክልል እና ወዘተ ገደብ ሳይኖር ወጣቶች የእራሳቸውን ግንዛቤ ለማሳደግ የዘመቻ እቅድ ማዘጋጀት እና በወጣቱ ማህበረሰብ ዘንድ ንግግሮችን ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ ውይይቶቻቸው ግልጽ በሆኑ መርሆዎች፣ በእውነት፣ በዴሞክራሲያዊ ተግባሮች እና በነጻነት እና በሰብአዊ መብቶች መከበር ላይ የተመሰረቱ መሆን አለባቸው፡፡ ከፍርሃት እና ከጭፍን ጥላቻ ነጻ ሆነው መወያየት አለባቸው፡፡ ሆኖም ግን በመከባበር እና በሰለጠነ መንገድ መከናወን ይኖርበታል፡፡ ከሁሉም በላይ የአቦሸማኔው ትውልድ የውይይት ሂደቱን “የእራሱ” ማድረግ አለበት፡፡ የአቦሸማኔው ትውልድ በሚሰበሰብበት ጊዜ የጉማሬው ትውልድም ይገኛል፣ ነገር ግን በዝምታ  ማዳመጥ ነው ያለባቸው:: ወጣቱን የህብረተሰብ ክፍል በቀላሉ ለማታለል የሚችሉ መሰሪ የጉማሬው ትውልድ አበጋዞች ስለሚኖሩ ምንጊዜም ቢሆን የአቦሸማኔው ትውልድ ነቅቶ ባይነ ቁራኛ ሊጠብቃቸው ይገባል፡፡ በአረብ የለውጥ አመጾች/Arab Spring እንደታየው ሁሉ ወጣቶች በወጥመድ ተይዘው የታዩባቸው ሁኔታዎች ስለነበሩ የኢትዮጵያ ወጣቶችም በወጥመዶች እንዳይጠለፉ ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው፡፡ በመጨረሻም በማታለል የተካኑት የጉማሬው ትውልድ አባላት ወጣቶችን ከጨዋታ ውጭ እንዲሆኑ፣ እንዲጭበረበሩ፣ እንዲደለሉ ያደርጓቸዋል፡፡ መጠንቀቅ ተገቢ ነው::
የዕርቅ ወይይቶች በድንገት እና ተራ በሆነ መልኩ በወጣት የመብት ተሟጋቾች መካከል መጀመር እንዳለባቸው አምናለሁ፡፡ ለምሳሌ እንደዚህ ያሉ ውይይቶች በሚግባቡ እና ተመሳሳይነት አስተሳሰብ ባላቸው የሰብአዊ መብት ተሟጋች ወጣቶች መካከል በመንደር ወይም በጎረቤት ደረጃ መካሄድ ይችላሉ፡፡ ወጣት የሰብአዊ መብት ተሟጋች ወጣቶች አቅማቸውን፣ ያላቸውን እምቅ ኃይል፣ ዕድሎችን እና ችግሮችን ለይተው በማውጣት ዕቅድ ነድፈው ትናንሽ ህብረተሰብ አቀፍ የዕርቅ ውይይቶችን ማካሄድ ይችላሉ፡፡ በአሁኑ ወቅት ያሉትን ድርጅቶች፣ ተቋሞች፣ ማህበራትን እና መድረኮችን በመጠቀም ወጣት የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች የዕርቅ ውይይቶችን በማካሄድ የወጣቶችን ግንዛቤ ማሳደግ  ይችላሉ፡፡
የዕርቅ ወይይት መነጋገርን ብቻ አይደለም የሚያካትተው ነገር ግን እርስ በእርስ በንቃት መደማመጥን ጭምር እንጅ፡፡ ወጣቶች ከኢትዮጵያ ብሄረሰቦች እርስ በእርስ በመማማር የእራሳቸውን ብዙሀንነት ማጠናከር ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም የኢትዮጵያ የአቦሸማኔ ትውልድ ከጉማሬው ትውልድ ስህተቶች እና ከሌሎች አገሮች ወጣቶች ልምዶችም ለመማር ይችላሉ፡፡ የኢትዮጵያ አቦሸመኔ ትውልድ የሚያደርጓቸው የዕርቅ ውይይቶች በመርህ ላይ የተመሰረቱ እንዲሆኑ አጥብቄ እማጸናለሁ፡፡ ወጣቶች ደስተኛ ባልሆኑባቸው ነገሮች ላይ መቃወም መቻል አለባቸው፡፡ በነገሮች ላይ አለመስማማት ማለት የዕድሜ ልክ ጠላት መሆን ማለት አይደለም፡፡ የሰለጠነ ውይይት ማድረግ ለጉማሬው ትውልድ ከባድ ቢሆንም ለአቦሸማኔው ትውልድ ግን በጣም አስፈላጊ ነገር ነው፡፡
ምነው ዝምታ?
“ዓለም አቀፍ ማጭበርበር በተንሰራፋባት ምድር ላይ“ ዝምታ ከቃላት እና ከስዕል የበለጠ ይናገራል፡፡ ማርቲን ሉተር ኪንግ እንዲህ አሉ፣ “በመጨረሻ የምናስታውሰው የጠላቶቻችንን ቃላት አይደለም፣ ነገር ግን የጓደኞቻችንን ዝምታ እንጅ“፡፡ ይህንን ትችት ካጠናቀቅሁ በኋላ “ስለጓደኞቻችን” “ዝምታ” መናገር አለብኝ፣ ምክንያቱም አንዳንድ ጊዜ ዝምታ ከመናገር የበለጠ የመግለጽ ችሎታ አለው፡፡ የኢትዮጵያ ወጣቶች ፓርቲ መሪ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ በመጡበት ጊዜ እና እስከ አሁን ድረስ ለበርካታ ዓመታት ታይቶ በማይታወቅ መልኩ እጅግ ብዙ ኢትዮጵያውያን ታዳሚዎች በተገኙበት ስብሰባ ላይ የወጣቶቹ መሪ ንግግር በሚያሰሙበት ጊዜ ትኩረትን በሚስብ መልኩ የአሜሪካ ድምጽ ወኪል ጋዜጠኛ ሳይገኝ ቀርቷል፡፡ የአሜሪካ ድምጽ ድርጊቱን ለመዘገብ አንድም ጋዜጠኛ ሳይልክ ቀርቷል፡፡ የአሜሪካ ድምጽ ዜናውን ለመዘገብ ለምን እንዳልተገኘ የማውቀው ነገር የለም፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ስብሰባ ግን ከተለያዩ የኢትዮጵያ ስፖርቶች፣ ባህላዊ፣ አካዳሚያዊ እና የማህበረሰብ ስብሰባዎች እንዲሁም የመጽሀፍት ርክክብ ፊርማ ስነስርዓት ሲኖር የአሜሪካ ድምጽ በሳምንቱ መጀመራያ እና በሳምንቱ ማጠቃለያ በዋሽንግተን ዙሪያ አካባቢ ሰፊ ሽፋን ሰጥቶ ከሚዘግበው የሚያንስ አለመሆኑን በእርግጠኝነት መናገር እችላለሁ፡፡ ምናልባትም ሰማያዊ ፓርቲ እና የኢትዮጵያ ወጣቶች ለአሜሪካ ድምጽ ምንም ያልሆኑ ቀላል ነገሮች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ የአሜሪካ ድምጽ ለወጣቶቹ ግድ ላይኖረው ይችላል፣ የኢትዮጵያ ወጣቶችም ለአሜሪካ ድምጽ ጉዳያቸው አይደለም፡፡
የአሜሪካ ድምጽ እንዲገነዘበው የምፈልገው ነገር ግን በሟቹ በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዝናዊ “ኢትዮጵያ  ላይ ዘር ማጥፋት” ፕሮፓጋንዳ አካሂደዋል የሚል ክስ በይፋ ባስታወቀበት ጊዜና ሌላም ጊዜ ወንጭፋቸውን ሲያነጣጥሩባቸው እና ቀስቶቻቸውን ሲቀስሩባቸው በነበረበት ወቅት ከእነርሱ ጎን ቆሜ ነበር፡፡ በዚያ ውንጀላ ጊዜ የአሜሪካ ድምጽ በጽናት ለመርህ የቆሙ መሆናቸውን፣ ለሙያው ክብር ሰጥተው ይዘግቡ እንደነበር፣ ያለአድልኦ እንደሚሰሩ ጊዜን አክብረው ደግመው እና ደጋግመው እንደሚዘግቡ ሽንጤን ገትሬ ተከራክሪያለሁ፡፡ የአሜሪካ ድምጽ በሰማያዊ ፓርቲ ጉባኤ ላይ በመገኘት እንደ ድሮው ሁሉ በጽናት ለመርህ ቆመው፣ ለሙያው ክብር ሰጥተው እና ያለአድልኦ የጉባኤውን ሂደት እንደሚዘግቡ እጠብቅ ነበር፡፡ ምናልባትም ኢትዮጵያውያን በአሁኑ ጊዜ የአሜሪካ ድምጽ የሚለውን ስያሜ የዝምታ ድምጽ ተብሎ መጠራት ጀመረ ወይ ብለው እየጠየቁ ይሆናል፡፡ የዝምታ ድምጹን ለመስማት እንቀጥላለን፣ ሆኖም ግን በዝምታ አይደለም የምንሰማው፡፡
ከዚህ በኋላ ዝምታ መኖር የለበትም፣ ድምጻችንን ከፍ አድርገን እንጩህ እና ለሰማያዊ ፓርቲ ንቅናቄ ድጋፋችንን እናሳይ፣ ዝምታን ከዚህ በኋላ እናቁም፡፡ ለሰማያዊ ፓርቲ ንቅናቄ ድጋፋችንን በይፋ እናውጅ፡፡ ቀጥ ብለን እንቁም እና በእነርሱ እንኩራ፡፡ ለሚያካሂዱት ሰላማዊ እና ግጭት አልባ የስርዓት ለውጥ ትግል አድናቆታችንን በመግለጽ ድጋፋችንን እንስጥ፡፡ ወደ ነጻነት የሚወስደው መንገድ የቱንም ያህል ረዥም ጉዞ ቢፈጅ ከእነርሱ ጋር መሆናችንን እናረጋግጥላቸው፡፡ ወጣቶቹ በመጨረሻም ድልአድራጊዎች ይሆናሉ፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ንቅናቄ አባላትን እንደምንወዳቸው በተግባር እናረጋግጥላቸው!
የኢትዮጵያ ወጣቶች ተባበሩ፣ በፍጹም እጅ እንዳትሰጡ፡፡ ኃይል ለኢትዮጵያውያን/ት ወጣቶች!
ታህሳስ 15 ቀን 2006 ዓ.ም
ምንጭ የኢትዮጵያ ሜዲያ መድረክ

Tuesday, December 24, 2013

‹‹በታማሚዎች መነገድ ስንት ያተርፋል?›› (ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ – ከቃሊቲ እስር ቤት)

በውብሸት ታዬ
“ፀሐይ በሞቀው…” የፍርድ ሂደት ራሴን ለመከላከል አቅርቤው ከነበረው የተከሳሽ የመከላከያ ቃል በኋላ ዳግም ድምጼን ለማሰማት የተመለስኩበት አጋጣሚ ለወራት ሲያሰቃየኝ ለቆየው የኩላሊት ሕመሜ የቃሊቲ ማ/ቤት “የጤና ባለሙያዎች” ምንም ሕክምና ሊሰጡኝ እንደማይችሉ መሆኑ ቅር ያሰኘኛል፡፡ ጥልቅ ፍቅር እና ክብር ላለኝ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ከመልካም ዜና ጋር ብመጣ እንዴት ደስ ባለኝ ነበር፡፡ አልሆነማ!
ጉዳዩን የበለጠ ግልፅ ለማድረግ በተደረገልኝ የኩላሊት የአልትራሳውንድ ምርመራ በተለይ በግራ ኩላሊቴ ላይ በአሳሳቢ ሁኔታ እጅግ የተከማቸ አሸዋ መኖሩ ተረጋግጧል፡፡ በግራም በቀኝም ያሉ ወገኖች ይህን በማንኛውም ጊዜ መመልከት ይችላሉ፡፡ (ለጠላትም ለወዳጅም አላልኩም፡፡ ምክንያቱም በግራና በቀኝ በተሰለፉት ውድ ኢትዮጵያውያን መካከል እየከረረ የመጣ የሀሳብና የመስመር ልዩነት እንጂ ጠብታ የጠላትነት መሰረት እንደሌለ ታሪክና እውነት ይመሰክሩልናል፡፡) ለማንኛውም የቃሊቲዎቹ ሐኪሞች ስቃዬ ሊሰማቸው አልቻለም፤ ወይም አልፈለጉም፡፡ ከቶ ለምን ይሆን?
Ethiopian Journalist arrested
Ethiopian Journalist arrested
ይህን አስደማሚ የሰቆቃ ድራማ ከጀርባ ሆኖ እየመራ ያለው ባለ እጀ ረጅሙ ማን ይሆን? ለመሆኑስ አማራጭ በሌላቸው ታማሚዎች ጤንነት መነገድ ስንት ያተርፋል? ምን ይሉት ርካታስ ያጐናፅፋል? ከእኛ ስር የበቀለው የነገይቱ ኢትዮጵያችን ተረካቢ ትውልድስ ይህን አስፀያፊ ድርጊት እንዴት ይመለከተዋል ትላላችሁ? ሁላችንንም ቸርና ፍፁም የሆነው እግዚአብሔር ይርዳን፡፡
በተለይ እኔ ባለሁበት የእስርና የጤንነት ሁኔታ ላይ የሚገለፅ ሀሳብ ስሜታዊነት ሊንፀባረቅበት ቢችል ትረዱኛላችሁ ብዬ አምናለሁ፡፡ ሌሎችን ለመውቀስም፣ የጥላቻ ስሜትንም ለመግለፅ ተደርጎ እንዳይወሰድብኝም በትህትና እጠይቃለሁ፡፡ ክብርና ፍቅር የሚገባችሁ ውድ ኢትዮጵያዊያን በግሌ የእስር ቆይታዬ በነፍሴ ውስጥ እንደ ውቅያኖስ የጠለቀ ፍቅርና የእናንተን አጋርነት በማይነጥፍ አሳቢነት አገኘሁበት እንጂ ጥላቻን አልተማርኩበትም፡፡
እኛ ኢትዮጵያዊያን ነን፡፡ የታሪክ፣ የእምነት፣ የወግና የባሕል በአጠቃላይም የማንነት ፅኑ መሰረት አለን፡፡ ትናንት የመጣን ነገ የምንሔድ አይደለንም፡፡ እንኖራለን፤ ቢያንስ ትውልድ ይኖራል፡፡ ታዲያ እንዴት ህክምና በመንፈግ፣ ከቤተሰብ አርቆ በማሰር (የሁለትዮሽ እንግልት ለመፍጠር በማሰብ) ይህን ማንነት እንጣው? አይሆንም!
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ፡፡
አክባሪ ወንድማችሁ ውብሸት ታዬ /ከቃሊቲ እስር ቤት/፤
ምንጭ የኢትዮጵያ ሜዲያ መድረክ

Saturday, December 21, 2013

የሸራተን ሰራተኞች “መብታችን ተጣሰ” በማለት ሰላማዊ ሰልፍ ሊወጡ ነው!!!!

የሸራተን አዲስ ሆቴል ሰራተኞች፤ የውጭ አገር ዜጋ በሆኑት የሆቴሉ ስራ አስኪያጅ የሚደርስብን ችግር ከአቅም በላይ በመሆኑ ሰላማዊ ሰልፍ ልንወጣ ነው አሉ፡፡ ከዚህ በፊት  የመብት ጥሰት እንደደረሰብን ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ለሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በደብዳቤ ብንገልፅም ምላሽ ባለማግኘታችን በድጋሚ ደብዳቤውን አስገብተናል ብለዋል - ሰራተኞቹ፡፡ 
በትምህርት ደረጃና በእውቀት ከሀበሾቹ የማይበልጡ የውጭ ዜጐች አሰሪዎቻችን ያንቋሽሹናል፤ ዛሬ ፆም ነው ይህን አንበላም ስንል “ድሮ ረሀብተኞች ስለነበራችሁ ረሀባችሁን ለማስታወስ የምታደርጉት ነው” ይሉናል፤ ጥቅማጥቅሞቻችን አይከበሩም፣ እድገት እንከላከላለን ያሉት ሠራተኞቹ፤ “ፈረንሳዊው ስራ አስኪያጅ ዲፓርትመንቶችን በመበታተን፣ ሰራተኞችን ወዳልፈለጉትና ወደማይመለከታቸው ቦታ ይመድባሉ፤ ይህን ስንቃወም እስከመደብደብ እንደርሳለን” ብለዋል፡፡ 
“የዜጐች ደህንነት ጥበቃ ከአገር ውስጥ ይጀምራል፤ በአገራችን ነጮች እያንቋሸሹን እና ሞራላችን እየተነካ ነው” የሚሉት ሰራተኞቹ፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ችግራችንን በዝምታ ማለፋቸው አሳዝኖናል ብለዋል፡፡ 
“ችግራችን ሲብስ ፒቲሽን ተፈራርመን ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያስገባነው ደብዳቤ፤ ለሆቴሉ ስራ አስኪያጅ ለሚስተር ዦን ፒይር ማኒንጐፍ ከደረሰ በኋላ፣ ስቃያችን በዝቷል ያሉት ሰራተኞቹ፤ አንድ ነገር ለማስፈቀድ፣ አቤቱታ ለማሰማትና ለእድገት ለመወዳደር ስንጠይቅ ስራ አስኪያጁ  ፒቲሽን የፈረሙትን ሰራተኞች ስም ያወጡና “በእኔ ላይ ፈርመሀል፤ እድሜ ልክህን እድገት አታገኝም፣ ይህ አይፈቀድም” እያሉ እንደሚያንገላቷቸው ተናግረዋል፡፡ ሸራተን አዲስ ሆቴል ከ800 በላይ ቋሚ ሰራተኞች እንዳሉት የገለፁት ሰራተኞቹ፤ ይህ ሁሉ ሰራተኛ ባለበት ስራ አስኪያጁን ጨምሮ አንዳንድ የውጭ አሰሪዎቻችን እያንጓጠጡንና ጫና እየፈጠሩብን ስለሆነና የሚመለከተው የመንግስት አካል ምላሽ ስላልሰጠን በቅርቡ ሰላማዊ ሰልፍ ለመውጣት አስበናል ብለዋል፡፡ 
የሆቴሉ ሰራተኞች ማህበር ሊቀመንበሩ አቶ ዳንኤል አለሙ ታሪኩ በበኩላቸው፤ “ሰራተኞቹ ከማህበሩ ወጥተው በራሳቸው ተደራጅተዋል፤ ነገር ግን ማኔጅመንቱና ሰራተኛው ተቀራርበው እንዲሰሩና በውይይት ችግራቸውን እንዲፈቱ ብዙ ርቀት ብንሄድም የሆቴሉ ስራ አስኪያጅ ሚስተር ዦን ፒይር ማኒንጐፍ ፈቃደኛ አልሆኑም” ብለዋል፡፡ 
የሆቴሉን ስራ አስኪያጅ  ሚስተር ዦን ፒይር ማኒንጐፍን ለማነጋገር ብንሞክርም እረፍት ላይ በመሆናቸው ሳይሳካልን ቀርቷል፡፡ ሌላ ሃላፊ ለማነጋገር ፀሃፊዋን ጠይቀን፤ በጉዳዩ ላይ ምላሽ የሚሰጡት ስራ አስኪያጁ ብቻ እንደሆኑ ገልፃልናለች፡፡ 
   ምንጭ
 አዲስ አድማስ

‘ነውጥ አልባ ትግል’ – ጋዜጠኛ ኤልያስ ወንድሙ ስለ አዲሱ ጥናታዊ ፊልም ይናገራል – ሁሉም ሊያዩት የሚገባው

በአለም ዙርያ ተበታትነው ያሉ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከነ ጋንዲ ምን ይማራሉ? የሳውዲ አረቢያ መንግስት በዜጎቻችን ላይ እያደረሱ ያሉት ግፍና መከራን እንዴት መቋቋም ይቻላል? ይህ በሌሎች ላይስ እንዳይደርስ እንዴት መከላከል ይቻላል? – ‘ነውጥ አልባ ትግል’ ለእነዚህና ሌሎች ተዛማች ጥያቄዎች ምላሽ አለው – ጋዜጠኛ ኤልያስ ወንድሙ ስለዚሁ አዲስ ጥናታዊ ፊልም ይናገራል። አስተናጋጁ ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ነው።
ምንጭ የኢትዮጵያ ሜዲያ መድረክ

Wednesday, December 18, 2013

ኦባንግ ከደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ጋር ተነጋገሩ

“በራችሁን ዘግታችሁ እርቅ አውርዱ”
* “ባለውለታችሁ የኢትዮጵያ ህዝብ አዝኖባችኋል፣ አርቃችሁ እዩ”
“በትግሉ ወቅት ለነጻነት ስትዋደቁ ኢትዮጵያ በጋምቤላ አኙዋክ ምድር ላይ ሙሉ ከለላና ዋስትና በመስጠት ያበረከተችው አስተዋጽኦ የሚረሳ ነው? ከነጻነት ታጋዮችችሁ ጎን በመሰለፍ ብረት ያነሱ የአኙዋክ ኢትዮጵያውያን ልጆች መስዋዕትነት ይዘነጋችኋል? አሁን ድረስ የትግሉ የመስዋዕትነት ቁስላቸው ያልዳነ የአኙዋክ ልጆች እንዳሉ ትዘነጋላችሁ?” በማለት የተናገሩት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ /ጥቁሩ ሰው/ ናቸው።
በታላላቅ መድረኮችና በበርካታ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ተሰሚነታቸውና ስብዕናቸው እየጎላ የሄደው ጥቁሩ ሰው ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ እንደተናገሩት፣ ከላይ የተገለጸውን ህሊና የሚፈታተን ጥያቄ ያቀረቡት ለደቡብ ሱዳን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ባርናባ ማሪያል ቤንጃሚን ነው። ለረዥም ሰዓት ጊዜ ወስደው ውይይት ማድረጋቸውን ተከትሎ የጎልጉል የአሜሪካ ዘጋቢ እንደዘገበው አቶ ኦባንግ ዶ/ር ባርናባን ያገኟቸው አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ነበር።
በጁባ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ መደረጉ ይፋ ከተደረገበት አንድ ቀን በፊት አስቀድሞ በተያዘ የውይይት መርሃ ግብር የተገናኙት ዶ/ር ባርናባና አቶ ኦባንግ በርካታ ወቅታዊ ጉዳዮችን አንስተው መነጋገራቸው ታውቋል። አቶ ኦባንግ የደቡብ ሱዳን የነጻነት ትግል ወቅት ኢትዮጵያ በመንግስት ደረጃ የሰጠችውን ሙሉ ድጋፍና፣ ድንበር ሳይከልላቸው በሁለቱም አገራት የሚገኙት የአኙዋክ ልጆች ትግሉን የነፍስ ዋጋ በመክፈል መደገፋቸውን በማስታወስ በውይይቱ ወቅት ያነሱት ያለ ምክንያት አልነበረም።
“በጆን ጋራንግ ይመራ የነበረው ትግል ፍሬ አፍርቶ ደቡብ ሱዳን ነጻ ስትወጣ የማይረሳ ውለታ ለሰራቸው ኢትዮጵያና የአኙዋክ ልጆች የተከፈላቸው ብድር አሳዛኝና የወደፊቱን ጊዜ ያላገናዘበ ነው” በማለት በውይይቱ ስለተነሱ ነጥቦች ማብራሪያ የሰጡት አቶ ኦባንግ፣ “ለህዝቦች ነጻነትና ለሰብአዊ መብት መከበር የታገለ ድርጅትና አመራሮች ለነጻነታቸው የተከፈለላቸውን የደም ዕዳ ያወራረዱትና እያወራረዱ ያሉት ከወያኔ መሪዎች ጋር በማበር ከለላ የጠየቁ ህጋዊ ስደተኞችን እያፈኑ ለወያኔ አሳልፎ በመስጠት መሆኑ አሳዝኖኛል። ኢትዮጵያዊያን አዝነዋል” በማለት ነበር።
ህጋዊ ከለላ የጠየቁ ስደተኞች ቶርቸር እንዲደረጉ፣ እንዲገደሉ፣ እንዲታሰሩና ኢሰብአዊ ግፍ እንዲፈጸምባቸው ለአምባገነኖች አሳልፎ መስጠት ዘግይቶም ቢሆን ዋጋ እንደሚያስከፍል አቶ ኦባንግ አስረግጠው ተናግረዋል። በ1993 የአኙዋክ ጄኖሳይድ /የጅምላ ጭፍጨፋ/ ሸሽተው በስደት ደቡብ ሱዳን የገቡ የአኙዋክ ልጆችን ለገዳዩ የወያኔ አንጋች ሃይል ማስረከብ መቆም እንዳለበት ያሳሰቡት አቶ ኦባንግ “ይህንን ተግባር የፈጸሙትም ቢያንስ ዓለም አቀፋዊውን ህግ ተላልፈዋልና ሊጠየቁ ይገባል። እርስዎም ይህንኑ የማስፈጸም ሃላፊነት ይኖርብዎታል” በማለት ለውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ አሳስበዋል።
የአኙዋክና የበኩር ልጆችና የደቡብ ሱዳን ግንኙነት ከድንበር ያለፈ የደም ትስስርና ኢትዮጵያ የማይረሳ ውለታ በመክፈል ያከበረችው ውህደት በመሆኑ መንግስታቸው ቆም ብሎ ሊያስብ እንደሚገባው አቶ ኦባንግ ምክር አዘል መልዕክት ማስተላለፋቸውን አመልክተዋል። ኢትዮጵያ አስተማማኝ ከለላና ዋስትና በመስጠት የፈጸመችውን ሊዘነጋ የማይችል ተግባር አለማክበር ለወደፊቱ ወዳጅ የሚያሳጣ ብድር ለራስ የማስቀመጥ ያህል እንደሆነም በወጉ እንዲገነዘቡ ሚኒስትሩን ተማጽነዋል።
photoአምባገነኑና በህዝብ የሚጠላው የህወሃት አገዛዝ እድሜ አሁን ካለው ትውልድ እድሜ በላይ ዘሎ የሚሄድ ባለመሆኑ በኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ የፖለቲካ ድርጅቶችን ማቅረብ፣ መተዋወቅና መልካም ግንኙነት መመስረት ለወደፊቱ ጠቃሚ መሆኑንም አስረድተዋል። እርሳቸው በዋና ዳይሬክተርነት የሚመሩት ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄም /አኢጋን/ ከተመሰረተበት ዓላማ አንጻር የደቡብ ሱዳን መንግሥት ህወሃት/ኢህአዴግን ለማስደሰት ሲል ኢትዮጵያዊያን ላይ ፈጸመውና እየፈጸመ ባለው ተግባር ያዘኑ ወገኖች የቀድሞውን የፍቅር መንገድ እንዲከተሉ አበክሮ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።
ሕዝብ ያልወደደው መንግስትና ህዝብ ያልተቀበለው ኢንቨስትመንት መጨረሻው ኪሳራ በመሆኑ የደቡብ ሱዳን መንግስት ሊጠነቀቅ እንደሚገባው አቶ ኦባንግ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ነግረዋቸዋል። ከደቡብ ሱዳን ተነስቶ በጋምቤላ አድርጎ ወደ ኬኒያና ጅቡቲ ይዘረጋል የተባለው የነዳጅ ማስተላለፊያ ቱቦ ሕዝብን በመግፋትና በመበደል ከቶውንም ተግባራዊ ሊሆን እንደማይችል ያለማቅማማት ጠቁመዋል።
ህዋሀት በጋምቤላ ንጹሃንን ከቀያቸው በጠመንጃ ሃይል በማባረር፣ መሬታቸውን በሳንቲም ቸብችቦ፣ የህይወታቸው ዋስትና የሆነውን ደናቸውን አስጨፍጭፎ፣ ለምን በማለት የጠየቁትን አስሮና ገድሎ ያቋቋመው ኢንቨስትመንት በዜሮ መጣፋቱን ለአብነት ጠቅሰው ማስረዳታቸው የጠቆሙት ጥቁሩ ሰው “ኢንቨስትመንት መልካም ነው። ህዝብ ካልተቀበለው ተግባራዊ ሊሆን አይችልም። ህዝብ ይሁንታ የማይሰጠው ኢንቨስትመንት ፍሬ አያፈራም። ከውስጥም ከውጪም ያላችሁን ግንኙነት መርምሩ። ያዘኑባችሁ ተበራክተዋል” ሲሉ መክረዋል።
በአዲስ የምትቋቋመው “አዲሲቷ ኢትዮጵያ” ለደቡብ ሱዳን ወንድምና እህቶች ጭምር ቦታ በማዘጋጀት መሆኑንን አቶ ኦባንግ አረጋግጠው “በሌላ በኩል ደግሞ በአሁኑ ወቅት ስጋት ውስጥ መሆናቸውን ተናግረዋል። ለዲሞክራሲ መከበርና ለነጻነት በተከፈለው መስዋዕት የተገኘውን ድል የደቡብ ሱዳን መንግስት በአግባቡ እየተጠቀመበት አለመሆኑን አቶ ኦባንግ ለውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ገልጸውላቸዋል። አዲሲቷ ደቡብ ሱዳን ከድል በኋላ የትግሉን መሐላ ሙሉ በሙሉ ረግጣለች በማለት መሪዎቹን ወቅሰዋል።
ከድል በኋላ በደቡብ ሱዳን በርካታ ችግሮች መከሰታቸውን በመዘርዘር የማስጠንቀቂያ ምክር መሰንዘራቸውን ያመለከቱት አቶ ኦባንግ “አሁን ባለው ሁኔታ በደቡብ ሱዳን ባሉ ሃያ አንድ ጎሳዎች መካከል ቀውስ መፈጠሩ አይቀርም። ስለዚህ በራችሁን ዘግታችሁ እርቅ አውርዱ። በቀደሙት ሰማዐታቶች ደምና አጥንት ላይ ዴሞክራሲን መስርቱ። ይህንን ካላደረጋችሁና አሁን በያዛችሁት የአምባገነንነትና የአንድ ሰው ወይም ጎሣ የበላይነት መንገድ ከቀጠላችሁ ጣጣው ወደኛም ያመራል” ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን አስጠንቅቀዋቸዋል። አሁን ያለው የውስጥ ሽኩቻ መልኩን ሳይቀይር መፍጠን እንደሚገባቸውም አስገንዝበዋቸዋል። (አቶ ኦባንግ ይህንን ለውጭ ጉዳይ ሚ/ሩ የተናገሩት እሁድ መፈንቅለ መንግሥት ከመሞከሩና አሁን ደግሞ በዘር /ጎሣ/ መስመር ተከፋፍለው ደቡብ ሱዳናውያን መጫረስ ከመጀመራቸው አንድ ቀን በፊት ነበር)
ambassador 1
አቶ ኦባንግ በአሜሪካ የደቡብ ሱዳን አምባሳደር ጋር
በደቡብ ሱዳን እውነተኛ እርቅ ለማውረድ የአኙዋክ የፍትሕ ምክርቤት አንድ ግብረ ሃይል ወደ ጁባ እንደሚልክ መረጃ እንዳላቸው የጠቆሙት አቶ ኦባንግ በውይይቱ ወቅት ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቀና ምላሽ ማግኘታቸውን አመልክተዋል። በመጨረሻም አቶ ኦባንግ የሚመሩት ድርጅት ኢትዮጵያ ውስጥ የእርቅ ደጆች የሚከፈቱበት አግባብ ላይ ከሚመለከታቸው ተጽዕኖ አድጊራዎችና አቅሙ ካላቸው አካላት ጋር እየሰሩ መሆናቸውን ገልጸውላቸዋል። በማያያዝም “እኛ ሩቅ እያየን እየሰራን ነው። እኛ በስፋት እያሰብን በመራመድ ላይ ነን። በስፋት አስበን፣ ሩቅ እያየን ስንሰራ እናንተንም አንዘነጋም። በተቃራኒው እናንተ ለነጻነታችሁ የተዋደቁላችሁን የራሳችሁን ዜጎች እያነቃችሁ ለወያኔ አሳልፋችሁ ትሰጣላችሁ። ደም ያፈሰሱላችሁንና አጥንታቸውን የከሰከሱላችሁን ውድ ዜጎች ሳትታረቁ በምድራቸው ላይ ቱቦ ዘርግታችሁ ብር ልታመርቱ ታቅዳላችሁ። ይህ ከቶውንም ጤነኛ አካሄድ አይደለምና ህዝብን አስቀድሙ። አብረን እንስራ። ይህ መልካም ጅምር ነው” በማለት መሰናበታቸውን አቶ ኦባንግ ለጎልጉል ተናግረዋል።
የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክትር አቶ ኦባንግ ሜቶ ከደቡብ ሱዳን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ባርናባ ማሪያል ጋር ለመወያየት የቻሉት ሚኒስትሩ አሜሪካ ከመምጣታቸው በፊት በኤምባሲያቸው አማካይነት አስቀድሞ በተያዘ መርሃ ግብር መሰረት እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። በውይይቱ ወቅት ሚኒስትሩ ስለ ሰጡት አስተያየትና ምላሽ አቶ ኦባንግ በዝርዝር ለመናገር አልፈለጉም። አቶ ኦባንግ በትውልድ አኙዋክ ቢሆኑም እርሳቸው የሚመሩት ድርጅት /አኢጋን/ ኢትዮጵያውያን ከአገራቸው ውጭ በስደት በሚሰቃዩበት ቦታ ዘር፣ ቀለም፣ ጎሣ፣ ቋንቋ፣ ወዘተ ሳይለይ ፈጥኖ በመድረስ እርዳታ በማድረግ እርሳቸውም በተመሳሳይ ተግባር ተጠምደው በቅንነት በማገልገል እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ የእርቅ ደጆች እንዲከፈቱ አግባብ ካላቸውና አቅሙ ካላቸው ክፍሎች ጋር እየሰራን ነው በማለት አቶ ኦባንግ ለሚኒስትሩ የገለጹላቸውን ሃሳብ እንዲያብራሩ ከጎልጉል ተጠይቀው “ሁሌም የእርቅ ደጆች እንዲከፈቱ እንሰራለን። ይህ የጋራ ንቅናቄውና አርቀው የሚመለከቱ ዜጎች ሁሉ እምነት ነው። ብዙ ስራ እየሰራን ነው። ስንጨብጠውና ለህዝብ ሪፖርት የምናቀርብበት አሳማኝ ጊዜ ላይ ስንደርስ ብቻ ይፋ እናደርጋለን። ስራው በባህሪው ከንግግር በመቆጠብ ተግባር ላይ ማተኮርን ስለሚጠይቅ እኛም ባናወራው ጊዜው ሲደርስ ሁሉም በየፊናው የሚገልጸው ይሆናል። ስራው ሳይሰራ ፕሮፓጋንዳው ከቀደመ በሁሉም ወገን ተዓማኒነትን የማጣትና የመጣል አደጋ አለው። የኢትዮጵያ ህዝብ ተግባር የናፈቀው ይመስለኛል” የሚል ድፍን መልስ ሰጥተዋል።
source http://www.goolgule.com

Sunday, December 15, 2013

ነጋሪቱም ተጎስሟል፤ፋኖም ተሠማርቷል !!!

ዛሬ ኢትዮጵያዊያን እያዩ ያሉት ውርደት ቃል የሚገልፀው አልሆነም። ኢትዮጵያ በታሪኳ ዛሬ እየደረሰ ያለ ዓይነት ውርደት ደርሶባት እንደሆነ በታሪክ የተመዘገበ ነገርም ተፈልጎ አልተገኘም። ይሄ ለኢትዮጵያዊያን የጨለማ ዘመን ነው። በኢትዮጵያ እንዲህ ስደትና እንግልት፤ ሃዘንና ዋይታ የበዛበት ዘመን ታይቶ አይታወቅም።
በዚህ ግዜ በኢትዮጵያችን መንግስት ነኝ እያለ ራሱን የሚጠራ ቡድን አለ።ይሄ ቡድን አገሪቷን ከተቆጣጠረ ዘመን ጀምሮ ኢትዮጵያ የገባችበት የውርደት አዘቅት ከባድ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ በህወሃቶች አዝማችነት ተስምቶ የማይታወቅ ጆሮን ጭው የሚያደርግ ግፍ በዜጎች ላይ ይፈፀማል። የተለየ የፖለቲካ አመለካከት ያላቸውን ሰዎች ይዘው ግብረ ሶዶም እንዲፈፀምባቸው ያደርጋሉ፤ ሴቶች ልጆችን በጋራ ሁነው ይደፍራሉ፤ በተቀደሱ ስፍራዎች ገብተው ቅዱሱን ስፍራ ያረክሳሉ፤ ዜጎችን ከእርሻ ማሳቸው አፈናቅለው በገዛ አገራቸው መፃተኛ ያደርጓቸዋል። በአጠቃላይ ዜጎች በአገራቸው ተስፋ አጥተው ሃዘንተኛ እንዲሆኑ ያደርጋሉ። ተስፋ የቆረጡ ዜጎች ኢትዮጵያ ውስጥ ከምኖር ሂጄ ብሞት ይሻለኛል ብለው እግራቸው በመራቸው መንገድ ይሰደዳሉ። በእንዲህ ሁኔታ ከኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ250ሺህ በላይ ወጣቶች ይሰደዳሉ።ገሚሱ በየበርሃው በውሃ ጥማት ወድቆ ይቀራል፤ ገሚሱም የባህር አዞ ቀለብ ሁኖ ዱካው ይጠፋል። ከሞት ተርፈው በየአርብ አገራቱ የደረሱ ዜጎች በሰው ልጆች ላይ ሊደርስ የማይገባ ወንጀል ይፈፀምባቸዋል።ባንዲራቸውን በአንገታቸው እንደጠመጠሙ ሬሳቸው ሜዳ ላይ ተጥሎ የአርብ መሳቂያ መሳለቂያ ይሆናሉ። በዚህ ሰሞን በሳውዲ ዓረቢያ እየተፈፀመ ያለው ግፍ ለኢትዮጵያዊያን ትልቅ ብሄራዊ ውርደት ሁኗል።
ይሄ በእንዲህ እንዳለ “መንግስት ነኝ “ እያለ ራሱን የሚጠራው ህወሃት በዜጎቹ ሲቃና መከራ እየቀለደ ይገኛል።አንድ ግዜ ዜጎቼን እያወጣሁ ነው ይላል፤ ሌላ ግዜ ደግሞ የሥራ ፈቃድ የሌላቸው ስለሆኑ አላውቃቸውም ይላል። ህወሃቶች በዚህ ብቻ አላበቁም በኢትዮጵያዊያኑ ላይ እየተፈፀመ ያለውን ግፍ ለማስቆም አዲስ አበባ በሚገኘው በሳውዲ እምባሲ ፊት ለፊት ሠላማዊ ሠልፍ እንዳይደረግ መከልከል ብቻ ሳይሆን ለሠላማዊ ሰልፍ የወጡ ዜጎችን የቻሉትን ያክል ወደ እስር ቤት አግዘዋል፤ ያገኙትን ሁሉ በቆመጥ እንዲደበደቡ አድርገዋል። የአካል ጉዳትም አድርሰዋል። ይሄን ሁሉ ግፍ የሚታደግ፤የህዝቡንም ሮሮ የሚሳማ መንግስታዊ አካል አልተገኘም። ዓለምም ፊቷን ያዞረችብን የሚመስል ሁኔታ ታይቷል።
ኢትዮጵያዊያን ቀና ብለን በኩራት በአርብ አገራት ጎዳናዎች ላይ የምንመላለስ ዜግች ነበርን። ስማችን ያማረ፤ ማንነታችን የተከበርን ዜጎች ነበርን። አረብ የሚያከብረን እንጂ እንዲህ የሚንቀንና የሚያዋርደን ዜጎች አልነበርንም። በዘመነ ህወሃት ግን ያ ሁሉ ክብራችን ተዋርዶ ዜጎቻችን እንደ ሌጦና ቆዳ በገንዘብ የሚሸጡ ሆኑ። በኢትዮጵያችን ላይ የነበሩ የቀድሞው ገዥዎች ምንም እንኳ ጨቋኞች ቢሆኑም ዜጎቻቸው በሌላ በማንም እጅ እንዲገላቱና እንዲዋረዱ የሚፈቅዱ አልነበሩም።በአንድ ወቅት አፄ ኃ/ስላሴን” ሠራተኛ ይላኩልኝ” ብለው የሳውዲው ንጉስ ሲጠይቋቸው “ለመሆኑ ምንድ ነው የምትፈልጉት መሃንዲስ ነው ወይስ ሃኪም “ብለው ይጠይቋቸዋል። አይ “እኛ የምንፈልገው በቤት ሠራተኛነት የሚያገለግሉንን ነው” ይላሉ አረቦቹ።አይ “እኛ ለቤት ሠራተኛ የሚሆን ዜጋ የለንም” ብለው መለስውላቸዋል።ለራሱም ሆነ ለወገኑ ክብር ያለው መሪ መልሱ እንዲህ እንጂ ሳውዲ ድረስ ሂዶ ዜጎቹን ለባርነት ለመሸጥ ሲዋዋል አይገኝም።
ደሳለኝ ኃ/ማሪያም ከስድስት ወር በፊት ሳውዲ ድረስ ገስግሶ ሂዶ የቤት ሠራተኞችን ለአረቦቹ ለመላክ ተዋውሎ መመለሱ የሚታወስ ነው። ይሄን ውል ሲዋዋል ግን ስለ ክፍያ፤ ስለ ዕረፍት ግዜ፤ በህመም ግዜ ምን ይሆናል የሚሉ መሠረታዊ ቁም ነገሮች በውሉ ውስጥ አልተካተቱም። በእነዚህ ነገሮች ምክንያት የኢንዶኔዥያ እና የፊሊፕልንስ መንግስታት ግን ምንም እንኳ ድሃ ብንሆንም ዜጎቻችንን የምንሰደው የታወቀ የክፍያ መጠን፤ የእረፍት ግዜ፤ የህመም ፈቃድ እነዚህንና ሌሎችን መሠረዊ ሁኔታዎችን በተመለከተ የተሟላ የህግ ድንጋጌ ሲኖራችሁ ነው። ይህን ህግ እስከምታበጁ ዜጎቻችን የእናንተ መጫወቻ እንዲሆኑ አንልክም ብለው እምቢ ማለታቸው ይታወቃል። ህወሃት መራሹ መንግስት ግን ስለውጪ አገር አኗኗር ምንም ዓይነት ግንዛቤ የሌላቸውን ወጣት ልጆችን ያለ ምንም ህግ ከለላ አሳልፎ ለባእዳን ይሰጣል። ወጣት ሴቶችንና ወንዶችን ለግርድናና ለአሸከርነት የመላኩ የድለላ ሥራም ህወሃቶች ባቋቋማቸው ድርጅቶች ተካሂዶ ከዚህ ንግድ በተገኘው ገንዘብ ህውሃቶች ብዙ ገንዘብ አፈሱ። ወገኖቻችን ግን በአረቦች እጅ እንባቸውን በመዳፋቸው የሚሰፍሩ ሆነው ቀሩ።
ለዚህ ሁሉ መከራ እና ውርደት ያበቃን ምንድ ነው የሚል ርዕስም የሰሞኑ የመወያያ ርዕስ ሆኗል። የመከራውና የውርደቱ ምንጭ ፈርጀ ብዙ ቢሆንም ህወሃት ዋነኛው የችግሩ ምንጭ ስለመሆኑ ብዙ ማስረጃዎችን ማቅረብ ይቻላል። በአጠቃላይ ግን ህወሃት መንግስት ነኝ ብሎ ሲያበቃ ዜጎችን ለመታደግ ምንም ዓይነት ተግባራዊ እንቅስቃሴ አለማድረጉ ብቻ ሳይሆን ዜጎች በሰላማዊ ሰልፍ እንኳ ቁጣቸውን እንዳይገልጹ መከልከሉ ማንነቱን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው።ለዚህ ብሄራዊ ውርደትና መከራ በመጀመሪያ ደረጃ ሊጠየቅ የሚገባው ህወሃት እንጂ ሌላ ማንም አይደለም። ህወሃት የኢትዮጵያዊያን ጠላት መሆንን የመረጠ የጠባብ ዘረኞች ቡድን ነው። ዜጎቻቸን እንዲህ ላለው ጉስቁልናና ውርደት እንዲጋለጡ ያደረጋቸው ህወሃት መሆኑን መያዝ ለነፃነት ለሚደረገው ትግል አንዱ አካል ነው።
የተከበራችሁ ወገኖቻችን፤
በሳውዲ አረቢያ የሚሰቃዩ ዜጎችን በተመለከተ ህወሃቶች ምንም ተቆርቋሪነት ያሳዩበት ሁኔታ እንዳልታየ ታውቃላችሁ።ለወገን ተቆርቋሪነት ከህወሃቶች የሚጠበቅ ስላልሆነ እኛ አንደነቅም። አስቀድመው በገንዘብ አሳልፈው ለሸጧቸው ዜጎች ይቆረቆራሉ ብሎ መጠበቅ የህወሃቶችን ባህሪይ ካለመረዳት የሚመነጭ ብቻ ሳይሆን ህወሃቶች ዜጎች ማኩረፊያ አገር እንኳን እንዳይኖሯቸው የሚያሴሩትን ሴራ ለመረዳት ካለመፈለግ የሚመነጭም ጭምር ነው። ወደ አረብ አገር የተሰደዱም ሆኑ በሌሎች አገር በስደት ላይ ያሉ ዜጎች በከፋቸው ግዜ ተመልሰው የሚገቡበት ሥፍራ አላቸው ለማለት የሚያስደፍር ሁኔታ በኢትዮጵያ የለም። ጉራፈርዳ እና ቤንሻንጉል አገርህ አይደለም ተብሎ የተባረረ ወጣት መግቢያው የት ነው ? ከዚህ ሥፍራ ወደ ሳውዲ የተሰደደ ወጣት መመለሻው ወደየት ነው ? በዚያች አገር ድንጋይ ለመፍለጥ እንኳ የኢሕአዴግ አባል እንዲሆን በሚገደድበት አገር ምን አገር አለኝ ብሎ ነው የከፋው ወደ ኢትዮጵያ የሚመለሰው? አዎን ኢትዮጵያዊያን ማኩረፊያ አገር የሌለን ከርታታ ዜጎች እንድንሆን ተደርገናል።አገር ያሳጡንም ህወሃቶች ናቸው እንጂ ሌላ ማንም አይደለም።
እንግዲህ ምን ይደረግ?
ይሄ ጥያቄ ግልጽና ቀላል መልስ አለው።አምርሮ መነሳት። ህወሃቶች በአዲስ አበባ ላይ ወንድ ልጅን አስገድደው ግብረ ሶዶም እንዲፈፀምበት ሲያደርጉ ሰምቶ “እነዚህ ምን ዓይነት አረመኔዎች ናቸው” ማለት ብቻ በቂ አይደለም።ለአረመኔ የሚገባውን ቅጣት ለመስጠት የአያቶቻችንን ጋሻና ጦር ማንሳት ግዜው የሚጠይቀው ታሪካዊ ግዴታ ነው። በሳውዲ አረቢያ በወገኖቻችን ላይ እየተፈፀመ የቆየውን ውርደት እንምባ ብቻ የሚያስቆመው አይሆንም። እንዲህ የአረብ መቀለጃ የሆነውን ማንነታችንና ክብራችንን አስመልሰን አንገታችንን ቀና አድርገን በአርብ ጎዳናዎች ላይ እንደቀድሞው ዘመን በኩራት እንድንመላለስ የአያቶቻችንን ትጥቅ ከተሰቀለበት አውርደን መታጠቅ ግዴታችን ሁኗል።
ግንቦት ሰባት ንቅናቄ ውስጥ ያለን ኢትዮጵያዊያን በወገኖቻችን ላይ እየተፈፀመ ያለው ውርደት ብሄራዊ ውርደት ነው እንላለን። ከዚህ በላይ ሌላ ብሄራዊ ውርደት የለም። ለዚህ ውርደት ያደረሰንም ህውሃት ነው። ህወሃት እስካለ ድረስ ብሄራዊ ውርደታችን ይቀጥላል እንጂ አይሻሻልም። እኛ የሚደርስብንን ውርደት ለማስቆም አምርረን ተነስተናል። እኛ እንዲህ ተዋርደን መኖርን ከቅድሞዎቹ ኩሩዎች አያቶቻችን አልተማርንም።እኛን ባንዳዎችና የባንዳ ልጆች ህወሃቶች አንገታችንን አስደፍተው አዋርደው አይገዙንም። አያቶቻችን ለነፃነታቸው እና ለአገራቸው ክብር ሲሉ በቆሙበት በጀግኖች ሥፍራ ለመቆም መንገዱን ጀምረናል። ከእንግዲህ ወዲያ ከዚህ ጉዞ የሚያቆመን ምንም ዓይነት ምድራዊ ኃይል የለም። ለእኛ ነጋሪት ከተጎሰመ ቆይቷል እኛ የነጋሪቱን ድምፅ በሰማን ግዜ ሳናቅማማ ተነስተናል።
እናንተስ ሳትቅማሙ ለመነሳት የነጋሪቱን ድምፅ ሰምታችኋል ? ከወደ ሳውዲ የተሰማው ያ የሲቃ ጩኸት፤ ያ ሮሮ፤ ያ እንምባ አስደንጋጩ የነጋሪት ድምፅ ነው። ከዚህ ድምፅ በኋላ ፋኖ ይሠማራል እንጂ አያለቅስም።ማልቀስ የናቁንና ያዋረዱን እንዲያከብሩን አያደርግም። ነጋሪቱ ከተጎሰመ በኋላ አገሬን፤ ክብሬን የሚል ተነስቶ ያያቶቹን ጋሻና ጦር ያነሳል እንጂ እንዲያው ዝም ብሎ አያጉረመርምም።አገር ተዋርዳ፤ ህዝብ ተበደሎ ዝም ብሎ ተንጋሎ የሚተኛ ካለ ይህን ብሄራዊ ውርደት ካመጡ ቡድኖች በምን እንደሚለይ ራሱን ይጠይቅ። አበቃን።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!!!
 source www.ginbot7.org

Friday, December 13, 2013

አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ስለምኒሊክና ስለኢትዮጵያ

የአጼ ምኒሊክን መቶኛ የሙት አመት መከበር ምክንያት በማድረግ በ DW ሬድዮ በተደረገው ጥያቄና መልስ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ፣ ዶ/ር ሓይሌ ላሬቦና ዶ/ር ሹመት ሲሳይ (የታሪክ ተመራማሪዎች) ቃለ መጠይቅ ተደርጎ በሚሰጠው መልስ ላይ ስለ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በተናገሩት ላይ አስተያየቴን አቀርባለሁ።
አንባቢያንን ቃለመጠይቁን ቢያዳምጡ ጥሩ ነው ባይ ነኝ፤ ሁለቱ የታሪክ ምሁራን ትምህርታዊ ትንተና ይሰጣሉና፡፡
ውሸት ሲደጋገም እውነት ሊመስል ይችላል፤ በተለይም የአገራችንን የኢትዮጵያን ታሪክ ለማያውቁ እውነታው ምን እንደሚመስል መረጃ ለማቅረብ እሞክራለሁ።
አቶ ቡልቻ ኦሮሞ ከባሌ እየተስፋፋ ሲመጣ ልብነ ድንግል እንዳይስፋፋ አቆሙት ይላሉ፡፡ ለምን ይህን ምሳሌ እንዳቀረቡም ግልጽ አይደለም ለሳቸው ትንታኔ የማይመች በመሆኑ፤ ለዛውም በአጼ ልብነ ድንግልና በኦሮሞች መሀከል ስለነበረው ግኑኝነት በከፊል ዶ/ር ሃይሌ ላሬቦ ሊያስረድዋቸው ሞክረዋል፤ ስለመስፋፋቱና እንዲያውም አማራውን እንደገፋው ለአቶ ቡልቻ መረጃ ላቅርብ፡፡
ጥንት ሌላ ስም የነበራቸው በኦሮሞ ከተያዙ ማግስት ስማቸው የተቀየረ፤ ደዋሮ-ጨርጨር፣ ጋፋት-ሆሮ፣ ገራሪያ-ሰላሌ፣ ዳሞት-ወለጋ፣ አበቤ-በቾ፣ ሽምብራ ኩሬ-ሞጆ … (የሃያኛው ክፍለዘመን ኢትዮጵያ ገጽ 50 በጥላሁን ገ/ስላሴ) በቅኝ ተገዛ የሚሉት ኦሮሞ ተጨማሪ ቦታ እንደያዘ እንጂ እንደተወሰደበት አይደለም ታሪኩ የሚመሰክረው፡፡
BULCHADEMEKSAአቶ ባልቻ የኦሮሞን ታሪክ ከደቡብ አፍሪካ ጋር ሊያዛምዱት ይሞክራሉ፤ ኦሮሞም እንደ ደቡብ አፍሪካ ጥቁሮች ኢትዮጵያ ውስጥ ሲረገጥ የኖረ ሕዝብ አድርገው ያቀርቡታል። መፍትሄውንም ሲጠይቁ reconciliation እርቅ ኦሮሞ ይቅርታ ተጠያቂ የተቀረው ይቅርታ ጠያቂ በተለይም የፈረደበት አማራ ለዚህ ወንጀል ትልቁን ድርሻ ይወስዳል፡፡ ባለፉት አስተዳደሮች ስህተቶች አልተሰሩም ብሎ የሚከራከር የለም፤ ጥያቄው እንዴት አብረን ወደፊት መሄድ እንችላለን ነው?
እንደቅኝ ተገዛን የሚሉት ቡልቻ ደመቅሳ አገሪቱን በእርሻ ሚኒስቴርነትና በምክትል ገንዘብ ሚኒስቴርነት አስተዳድረዋል – ቸር ቅኝ ገዢ ነበር የነበራቸው፤ እኛ ቅኝ እየተገዛን ስለሆንን በሚኒስቴርነት ቅኝ ገዢዬን አላገለግልም ብለው አላንገራገሩም፡፡
ኦሮሞ በሲቪሉም ሆነ በወታደራዊው ክንፉ ታላቅ የሚባሉትን ስልጣኖች ይዞ የኖረና ያለ የህብረተሰብ ክፍል ነው፡፡ አገሪቱ ውስጥ ለነበሩትና ላሉትም ደግ ነገሮችም ሆነ ክፉ ነገሮች ተጠያቂነቱ እኩል ነው፡፡ አቶ ቡልቻ ቅኝ ገዢ የሚሉትን የአማራውን ክፍለሀገር ደጃዝማች ክፍሌ ዳዲ ያስተዳድሩት ነበር፡፡ (ምሳሌ የሚያቀርቡበት ደቡብ አፍሪካ የማስተዳደር ቅንጦት ይቅርና ነጭ በሚዝናናበት ቦታ ጥቁር መግባት አይፈቀድለትም ነበር)፡፡
ስለኦሮሞ ባለስልጣናት እስቲ እንመልከት
ምኒሊክ በሸዋ ሲነግሱ የረዷቸው አብሮ አደግ ባልንጀራቸው ጎበና ዳጬ ናቸው፡፡ የወለጋውም አስተዳዳሪ ኩምሳ ምኒሊክን በደጃዝማችነት አግልግለዋል፤ እነ ባልቻ አባ ነፍሶም የማይረሱ ታላቅ ኢትዮጵያውያን ናቸው፡፡
የአጼ ሃይለስላሴ አባት ራስ መኮንን ወልደሚካኤል (ጉዲሳ) አባታቸው ኦሮሞ ነበሩ፤ እናታቸውም ወ/ሮ እመቤት እናታቸው ኦሮሞ ነበሩ፡፡
ራስ ዳርጌ የሸዋው ንጉስ ሳህለስላሴ ከወለዷቸው አራት ወንዶች መሃከል አንዱ ሲሆኑ ጥናታቸው አርሲ ውስጥ የአንድ አካባቢ ኦሮሞ ባላባት ልጅ ነበሩ (አባ ቦራ በታቦር ዋሚ፤ ገጽ 9)
ራስ አበበ አረጋይ  መከላከያ ሚኒስትር
አቶ ይልማ ዴሬሳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፤ የገንዘብ ሚኒስትር
ደጃዝማች ክፍሌ ዳዲ የጎንደር አስተዳደር
አቶ ቡልቻ ደመቅሳ የእርሻ ሚኒስትርን ምክትል የገንዘብ ሚኒስትር
ሜጀር ጀኔራል ሙሉጌታ ቡሊ የክብር ዘበኛ አዛዥና የባህል ሚኒስትር
ደጀዝማች ገረሱ ዱኪ የኢሊባቡርና የጎሙገፋ አስተዳዳሪ
ሜጀር ጀኔራል ደምሴ ቡልቲ የሁለተኛው ክፍለ ጦር አዛዥ
ሌተና ጀኔራል ጃጌማ ኬሎ የአራተኛው ክፍለጦር አዛዥና የባሌ አስተዳደር
ፊታውራሪ ለማ ወልደጻድቅ የሲዳሞ ምክትል አስተዳደር
ሜ/ጀኔራል አበራ ወልደማርያም የአየር ኃይል ምክትል አዛዥ
ደጃዝማች በቀለ ወያ የጨቦና ጉራጌ አስተዳደር ከዚያም የጨርጨር አስተዳደር
ደጃዝማች ካሳ ወልደማርያም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንትና የእርሻ ሚኒስትር
አንባቢያን መረዳት ያለብን ሁላችንም በመጀመሪያ ደረጃ ኢትዮጵያውያን መሆናችን ነው፡፡ ሕዝባችን በጋብቻ፣ በእምነት፣ በባሕል፣… የተሳሰረ በመሆኑ መሰረት የሌለው ታሪክ እያነበነቡ ሊበታትኑን የሚያስቡትን ታሪካዊ መረጃ እያቀረብን ወግዱ ልንላቸው ይገባል፡፡ ድር ቢያብር አንበሳ ያስር ነው፤ ምኒሊክም ያስተማሩን መቻቻልን አንድነትንና ፍቅርን ነው፡፡
ዶ/ር ካሳሁን በጋሻው
source www.goolgule.com.

Thursday, December 12, 2013

«ድምጽ አልባው አሳዛኝ የወገኖቻችን ለቅሶ በሳዑዲ አረቢያ ሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ግቢ!»

በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ መዝናኛ ክበብ ሰራተኞች ሰንደቃላማችን በተሰቀለበት ግቢ ግፍ እና በደል እየተፈጸመባቸው መሆኑን ገለጹ
በኢትዮጵያን ሃገሬ ከጅዳ ዋዲ
በሳውዲ አረቢያ ሪያድ ከተማ ሁለት የጸጥታ ጥበቃዎችን ጨምሮ ከ13 በላይ ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች በስሩ እንደሚገኙ የሚነገርለት ይህ የመዝናኛ ማዕከል ከተቆርቆረ ሁለት አስርተ አመታትን ቢያስቆጥርም ከቅርብ ግዜ ወዲህ በተለያዩ ሰንካላ ምክንያቶች ከትርፋማነት ይልቅ ኪሳራ፤ ከእድገት ይልቅ ውደቀትን እያቀነቀነ አሁን ላለበት ደረጃ መድረሱን የሚናገሩ እማኞች በሰራተኞቹ ላይ እየተፈጸመ ያለው በደል ከመቸውም ግዜ በላይ እየከፋ መምጣቱን ገልጸዋል።
ይህ የኮሚኒቲ ማህበር ካፍቴሪያ ማዕከል ዛሬ ላለበት አሳፋሪ ደረጃ ምክንያት መሆኑ የሚነገረው በተለያዩ ወቅቶች በሪያድ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች ጀርባ ታዝለው ያለችሎታቸው አመራር የሚሆኑ ግለሰቦች ከኮሚኒቲው ካፍቴሪያ ሰራተኞች ጋር በቅርበት ተነጋግረው የካፍቴሪያውን መሰረታዊ ችግር ለመቅረፍ የሚጠበቅባቸውን ሃላፊነት ከመወጣት ይልቅ ከማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ እና ስርአት ውጭ በብሄር ተከፋፍለው እርስ በእርስ በመጋጨት በሪያድ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች ተላላኪ እና አፋሽ አጎንባሽ በመሆናቸው መሆኑንን ይጠቅሳሉ። የኮሚቲው አመራር አባላቶች ዲፕሎማቱ በሚሰጧቸው ትዕዛዝ እንደሚንቀሳቀሱ የሚናገሩ ምንጮች ከ10 አመት በላይ ያለ ደሞዝ ጭማሪ ደፋ ቀና የሚሉ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን መብት በመደፍጠጥ ፍሬ ፈርስኪ በሆኑ ጉዳዩች ተጠምደው «ሲሻም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል እንዲሉ» በተለያየ አቅጣጫ የወጪ ቀዳዳዎችን በማበጀት ወደ ማህበሩ ካዝና ዲፕሎማቱ እጃቸውን እንዲሰነዝሩ በመጋበዝ በሚፈጸም አስነዋሪ ተግባር ለኮሚኒቲው ውድቀት ግንባር ቀደም ምክንያት መሆናቸውን አክለው ይገልጻሉ። በዚህም ምክንያት የኮሚኒቲው ካፍቴሪያ በየአመቱ ኪሳራ አሳይቷል እየተባሉ አንገታቸውን እስከዛሬ አንገታቸውን ለመድፋት የተገደደዱት የኮምኒቲው ካፍቴሪያ ሰራተኞች በሳውዲ አረቢያ ውስጥ እየጨመረ የመጣውን የኑሮ ውድነት ተከትሎ ከዛሬ 10 አመት በፊት በተቀጠሩበት ደሞዝ የስደት አለሙን ህይወት መግፋት ተስኗቸው ለከፍተኛ ችግር በመዳረግ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።


በሳውዲ አረቢያ ምድር በባዕዳን የሚፈጸምብን ግፍ እና ስቃይ ሳያንሰን ባዲራችን ከፍ ብሎ በሚውለብለበት የኢትዮጵያ ኮሚኒት ግቢ በገዛ ወገኖቻችን መገፋታችን ያሳዝናል ያሉ አንድ የካፍቴሪያው ሰራተኛ ባለተዳር እና የሶስት ልጆች አባት መሆናቸውን ገልጸው ዛሬ በየአመቱ የመኖሪያ ፈቃዳቸውን ለማሳደስ እስከ 10 ሺህ ሪያል ለማውጣት እንደሚገደዱ አውስተው ለምኖርበት መኖሪያ ቤቴ በየስድስት ወሩ ከምከፍለው የቤት ኪራይ ጋር ተዳምሮ በ 2 ሺህ ሪያል ደሞዝ አይን ካልገለጹ ልጆቼ ጋር ኑሮን ማሸነፍ ተስኖኝ አቤት ለምለው አጥቼ በነዚህ ጨካኞች የሚፈጸምብኝን በደል ሳልወድ በግድ ለመቀበል ተገድጃለሁ ብለዋል። በተጠቅሰው ካፍቴሪያ ከ 8 ሰአት በላይ ያለ ተጨማሪ ክፍያ « ኦቨር ታይም» ሃይማኖታዊ በአላትን ጨምሮ ደስታ ምን እንደሆነ ሳያውቁ ከእጅ ወደ አፍ የሆነውን ኑሮቸውን ለማሸነፍ ደፋቀና እያሉ መሆናቸውን የሚናገሩ እነዚህ ወገኖች ተጨማሪ ስራ ሰርተው እራሳቸውን መደጎም የሚችሉበት ግዜ እንደሌላቸው እና አቅማቸው እንደማይችል ጠቁመው ጉዳዩ ያችን እልባት እስኪያገኝ ለወግን ተቆርቋሪ የሆኑ ኢትዮጵያዊ ሁሉ በጸሎት ከጎናቸው ይቆም ዘንድ ተማጽነዋል።
ይህ የኮሚኒቲ ማህበር እንደ ማህበር ህጋዊ ህልውና አጊቶ ስራ ከጀመረ ሁለት አስርት አመታትን ማስቋጠሩን የሚያወጉ አንዳንድ እድሜ ጠገብ አባላቱ በተጠቀሱት አመታት የአንባሳደሩን መኖሪያ ቤት ጨምሮ በሪያድ የኢትዮጵያን ኤንባሲን በ20 ሚልዮን ሪያል ወጪ አስገንብቶ ለኢትዮጵያ ህዝብ ያስረከበ ታላቅ እና ስመጥር ማዕከል እንደ ነበር በማስታወስ ዛሬ ይህ የኮሚኒቲ ማህበር ግቢ ጥቂቶች እንዳሻቸው የሚያዙበት የአይንህ ቀለም አላማረኝም እያሉ የገዛ ወግናቸውን በቡጢ እይነረቱ ከግቢ የሚያባርሩበት ከሰሪዎቻቸው አምልጠው ህይወታቸውን ለማትረፍ ወደ ቅጥር ግቢው በሚመጡ እህቶቻችን ላይ ጾታዊ ጥቃት የሚፈጸምበት እና የወገኖቻችን ሬሳ የሚቆጠርበት የጥቂት ወሮበሎች መሸሸጊያ መሆኑ አሳዛኝ እና ሳፋሪ ነው ብለዋል። በአጠቃላይ ከቅርብ ግዜ ውዲህ ይህ በሪያድ የኢትዮጵያ የኮሚኒት መዝናኛ ማዕከል በወገኖቻችን ላይ ኢሰባአዊ ድርጊት የሚፈጸምበት መዕከል ለመሆኑ ምስክርነታቸውን የሚሰጡ ምንጮች የመዝናኛው መዕከል ሰራተኞች አብዛኛዎቹ የወጣትነት እድሜያቸውን እዛው የኮሚቲ ማእከል ውስጥ የጨረሱ እና በብስጨት ለስኳር በሽታ ለድም ግፊት እና መስል ተዛማጅ በሽታዎች ተዳርገው የተጎሳቆሉ በመሆናቸው ሌላ ስራ ፈልገው የማግኘት እድል እንደሌላቸው በማውሳት የሚመከተው አካል አሁን የሳውዲ አረቢያ ሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት ያወጣውን ህግ መስረት በማድረግ የደሞዝ ጭማሪ ሊደረግላቸው እንደሚገባ እና የሳውዲ አረቢያ መንግስት አሁን ባወጣው ህግ መስረት የተጠቀሱትን ወገኖቻችንን ከህገወጥነት ለመታደግ የመኖሪያ ፈቃዶቻቸው በኤንባሲው ስር ሊሆን የሚቻልበትን መፍትሄ ማፈላለግ በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ሃላፊነት መሆኑንን ይገልጻሉ።

ይህን ተከትሎ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አክሳሪ ነው በሚል ለአያሌ አመታት ሲመዘበር መቆየቱን የሚናገሩ የሪያድ ነዋሪዎች በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያ አንባሳደር መሃመድ ሃሰን የቅርብ ዘምድ እንደሆኑ የሚነገርላቸው የኮሚኒትው ሊቀመንበር ሼክ ሙስጠፋ ሁሴን አሊዬ ምንጩ የማይታወቅ 2 ሚልዮን ሪያል «25 ሚልዮን ብር » ከሳውዲ አረቢያ ወደ ሶስተኛ ሃገር ሊያሻግሩ ሲሞክሩ በሳውዲ አረቢያ መንግስት ደህነት ሃይሎች ቁጥጥር ስር ውለው እስካሁንም እስር ቤት እንደሚገኙ ይገልጻሉ።
ምንጭ ዘ-ሐበሻ

Tuesday, December 10, 2013

ማንዴላ፣ ኦባማና የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ጉዳይ – ከሳዲቅ አህመድ (ያድምጡ) Zehabesh Amharic


አንዱዓለም አራጌ ከእስር ቤት “እኔ እስሩ አልከበደኝም፤ በጣም ያሳዘነኝ ግን በኔ መታሰር ልትጠቀሙበት አልቻላችሁም” አለ

(ዘ-ሐበሻ) የ2005 ዓ.ም የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች ምርጥ ተብሎ የተሰየመውና በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበት የሚገኘው ወጣቱ ታጋይ አንዱዓለም አራጌ እስር ቤት ሊጠይቁት ለሄዱት የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች መልዕክት አስተላለፈ። በጣም ማዘኑንም ገለጸ።

ዕድሜ ልክ እስራቱን ተቀብሎ እስር ቤት የሚገኘው አንዷለም አራጌ “ይቅርታ አልጠይቅም” በሚል እስካሁን በእስር ቤት እየማቀቀ ሲሆን “በእኔ መታሰር ብዙ ልትጠቀሙበት ስትችሉ አለመጠቀማችሁ ያሳዝነኛል:: እኔ አሁን በእስር ባለሁበት ሰዓት የኢትዮጵያን ሕዝብ የነፃነት ትግሉን ወደ ፊት ለመግፋት አጋጣሚ ሊሆንላችሁ ቢችልም አልተጠቀማችሁበትም ” ሲል የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችን መውቀሱን የዘ-ሐበሻ ታማኝ ምንጮች ገልጸዋል።
“እኔ መታሰሩና፤ በእስር ቤት እየደረሰብኝ ያለው ስቃይ አልከበደኝም። የከበደኝ ግን በኔ መታሰር ልትጠቀሙበት አለመቻላችሁ ነው። በኔ መታሰር መንግስት ብዙ ጫና ውስጥ እንዳለ ይታወቃል። በኔ መታሰር ብዙ ሥራ ልትሰሩበት፤ ትግሉን ወደፊት ልታስኬዱበት ስትሉ ይህን አላደረጋችሁም” ያለው አንዷለም አራጌ አሁንም የመንፈስ ጥንካሬው አብሮት እንዳለ በ እስር ቤት ካነጋገሩት ወገኖች መካከል ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል።
አንዷለም አራጌ የፌደራሉ ማረሚያ ቤት የሚጠይቁህን ሰዎች ስም ዝርዝር አስመዝግብ ተብሎ ተጠይቆ የነበረ ሲሆን እርሱ ግን ማንም ሰው መጥቶ ሊጠይቀኝ መብቱ ነውና ስም ዝርዝር አውጥቼ አልሰጥም ሲል ፈቃደኛ አለመሆኑን ዘ-ሐበሻ ከዚህ ቀደም መዘገቧ አይዘነጋም።

Sunday, December 8, 2013

African Leaders Must Follow in Mandela’s Footsteps – Activists

BY TESFA-ALEM TEKLE, 6 DECEMBER 2013 (ST)
Addis Ababa — As the world mourns the passing of former South African president, Nelson Mandela, political activists in Ethiopia have stressed the need for African politicians to emulate the anti-Apartheid hero.
Reacting to reports of Mandela’s death, activists and ordinary Ethiopians in several interviews with Sudan Tribune said the former South Africa president’s passing should serve as a wakeup call for African leaders to “begin implementing best political practices.”
“African leaders must learn from Mandela on how to leave a better place to the continent and to the world at large” Solomon Negassi, an Ethiopian politician told Sudan Tribune.
Negassi said African leaders are failing in working towards building unity, national reconciliation, Justice and human rights in their respective countries.
Separately, Genet Yohannes, an economist, says unless African leaders follow a positive political path like Mandela achieving African unity will be difficult.
Mandela, who died on Thursday at the age of 95, became the first South African Black president in 1994 after he spent 27 years in prison under the then Apartheid regime.
After serving one term as a president, Mandela handed over power to Thabo Mbeki in 1999, something uncommon among African leaders.
An Ethiopian opposition official who sought anonymity told Sudan Tribune that African leaders particularly the despotic must learn from Mandela and limit their stay in office.
“African leaders must learn to limit their grip on power” the opposition official said adding “I don’t think African leaders are yet ready to make such a decision”
Once he gained power, Nelson Mandela, winner of the 1993 Nobel Peace Prize didn’t seek reprisal against those – under the white minority rule – that threw him in prison to serve a long jail term.
A memorial service will be held in Johannesburg on December 10 and his funeral will take place on 15 December.
ETHIOPIA PAYS TRIBUTE
In a statement released on Friday, Hailemariam Dessalegn, the Ethiopian prime minister and African Union (AU) chairperson expressed sympathy with the family of Mandela and the South African people.
“President Mandela did not only lead his country’s struggle against Apartheid but has also been the torch bearer in the quest for Africa’s freedom” said a statement by the ministry of foreign Affairs.
Mandela inspired generations of world leaders to stand for justice, human dignity and freedom.
The Anti-Apartheid icon was in Ethiopia during his exile in the 1960s while he was leading the struggle for freedom.
“Indeed, President Mandela leaves behind a great vision from which all of us Africans should draw inspiration” said the Ethiopian premier.
The statement added the Ethiopia government will continue to value the principles of democracy, freedom, justice, tolerance and reconciliation for which President Mandela dedicated his life.
source Ethiopian media forum.

Friday, December 6, 2013

በወያኔ ስርዓት ውስጥ በሙስና ያልተጨማለቀ ሰው ቢኖር እኔ ነኝ ዓሉ ወ/ሮ አዜብ

የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ሰራተኛ የነበሩት አቶ ወልደስላሴ ወልደሚካኤል ከሁለት ቤተሰቦቻቸው ጋር በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል ተጨማሪ ክስ ተመሰረተባቸው። “የአቶ ወልደስላሴ እህት የ8ኛ ክፍል ተማሪ ስትሆን ፥ ምንም አይነት የገቢ ምንጭ የሌላት እንደሆነች ነው በክስ መዝገቡ የተገለጸው…ግለሰቧ በ 81 ሺ ዩሮ የተገዛ አንድ ስካቫተር ፣ አውቶሞቢል መኪና፣ በአዲስ አበባ ቦሌና የካ ክፍለ ከተሞች እንዲሁም በለገጣፎ ፣ በመቀሌና አክሱም ከተሞች 3 ሺህ 266 ካሬ ሜትር ቦታዎች በስሟ ተመዝግቧል ፤ በተለያዩ ባንኮችም ከ 8 ሚሊየን ብር በላይ ተቀማጭ ገንዘብም እንዲሁ ተመዝግቧል።…….” ተከሳሾቹ አቶ ወልደስላሴ ወልደሚካኤል፣ የመከላከያ ሚኒስቴር ባልደረባ የነበሩት ወንድማቸው ዘርአይ ወልደሚካኤል፣ እህታቸው ወይዘሪት ትርሃስ ወልደሚካኤልና የቅርብ ጓደኛቸው ዶሪ ከበደ ናቸው ።ተከሳሹ በ 2002 ዓ.ም ቱሪዝም ኢን ኢትዮዽያ ኤንድ ዘ ሆርን ኦፍ አፍሪካ የተሰኘ መጽሃፍ ያሳተሙ ሲሆን ፥ ይህንን መጽሃፋቸውን በስፖንሰር ለማሳተም ባደረጉት እንቅስቃሴም የመንግስት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር የሆኑትን አቶ በየነ ገብረስላሴ የነበራቸውን ቀና አስተሳሰብ ተጠቅመው ያለአግባብ በልጽገዋል ነው የሚለው የክስ መዝገቡ። መጽሃፉ በመስሪያቤታቸው ስም እንደተዘጋጀ በሚያስመስል ሁኔታ አቶ በየነ የሚመሯቸው የቦሌ፣ የብርሃንና ሰላምና የአርቲስቲክ ማተሚያ ቤት ሃላፊዎች በጋራ የአቶ ወልደስላሴን 3 ሺህ መጻህፍት በ124 ሺህ ብር እንዲያሳትሙ ተደርጓል ነው የሚለው ክሱ።
ማተሚያ ቤቶቹ በርካሽ ያሳተሙት አቶ ወልደስላሴ ከነበራቸው ተሰሚነትና ስልጣን መነሻነት መሆኑንና ይህንን መጽሃፍ ኢትዮ ቴሌኮም ምንም በማይመለከተው 10 ሺህ መጻህፍት የሚታተሙበትን የ385 ሺህ ብር ክፍያ ለአቶ ወልደስላሴ እንዲከፍልም መደረጉንም ነው የክስ መዝገቡ የሚያስረዳው። አቶ ወልደስላሴ የሙገር ሲሚንቶ ኢንተርፕራይዝና የአትክልትና ፍራፍሬ ገበያ ማህበር የቦርድ ሰብሳቢ በነበሩበት ጊዜ ሃላፊነታቸውነ ተጠቅመው ፥ ሁለቱ ድርጅቶች 310 ኮፒዎችን በግድ እንዲገዙ መደረጉም ተመልክቷል። 26 የሚሆኑ ግለሰቦችና ድርጅቶችም እያንዳንዳቸው ከ 25 እስከ 1ሺህ 500 ፥ በጥቅሉ ከ73 ሺህ የሚልቁ ኪፒዎችን ሳይወዱ በግድ እንዲገዙ መደረጉ ፣ ይሄ ሁሉ ሲደረግ ተቋማቱ ለመጻህፍቱ ገንዘብ ከፍለው መጻህፍቱን አለመረከባቸውም ጭምር ነው በክስ መዝገቡ የተዘረዘረው። ተከሳሹ አቶ ወልደስላሴ ባልደረባቸወ የሆኑ አንዲት ሴት ጋር በነበራቸው መቀራረብ የመስሪያቤቱን መኪና በህገ ወጥ መንገድ ነዳጅ እያስሞሉ ግለሰቧ እንደልባቸው በአዲስ አበበባና ከከተማ ውጪ እንዲጠቀሙበት አስደርገዋል የሚለውም ተጠቅሶባቸዋል።
ተከሳሹ ከ2003 እስከ 2004 ዓ.ም አቶ ሳቢር አርጋው የተሰኙ ነጋዴን ለምሰራው ቤት ሴራሚክ ስለጎደለኝ የጣሊያን ስሪት ገዝተህ ስጠኝ በማለት ፥ በስልጣናቸው አስፈራርተዋቸው የ65 ሺህ ብር ሴራሚክ ተቀብለዋል ፣ ከ 2001 እስከ 2005 ባሉት የግብር አመታት አሳትሞ ከሸጣቸው መጻህፍት ካገኘው ገቢ ላይ መክፈል የነበረበትን ከ496 ሺህ ብር በላይ ለመንግስት አስታውቆ አለመክፈሉም ተጠቅሷል። ተከሳሹ ባለ4 ፎቅ የግል ቤቱን ወንድሙ ለሆነው ሁለተኛ ተከሳሽ ዘርአይ ወልደስላሴ ውክልና ሰጥቶና ከመኖሪያ ቤት ውጭ ለሆነ አገልግሎት እንዲውል አድርጎ በ14 ወራት ውስጥ 790 ሺህ ብር ገቢ አግኝቷል ፤ ከገቢው 126 ሺህ ብር የሚሆነው የመንግስት ግብርን ለግብር አስገቢው መስሪያቤት ሃሰተኛ መግለጫ በማቅረብ ሳይከፍል መቅረቱም በክሱ ተመልክቷል። ከዚሁ ቤት ኪራይ መንግስት ከተርን ኦቨር ታክስ ማግኘት የነበረበትን ከ119 ሺህ ብር በላይ ገቢ ሳያገኝ መቅረቱና ተከሳሹ በህገ ወጥ መነገድ ያገኘውን ገንዘብ ማንም እንዳያውቅበት ለማድረግ በሰኔ 28 1998 ዓ.ም ለሁለተኛው ተከሳሽ (ወንድም) ዘርአይ ወልደሚካኤል ሙሉ ውክልና መስጠቱ ተዘርዝሯል።
እንዲሁም ምንም አይነት የገንዘብ ልውውጥ ሳያደርጉ ከ3ኛዋ ተከሳሽ እህቱ ትርሃስ ጋር መጋቢት 24፣ 2005 ዓ.ም የብድር ውል ማድረጋቸውም ተጠቅሷል።በተጨማሪም ተከሳሹ ከእህቱና ወንድሙ ጋር ያለአግባብ አፈሯቸው የተባሉ የገንዘብና የአይነት ሃብቶች በክስ መዝገቡ ተጠቅሰዋል። 1ኛው ተከሳሽ ወልደስላሴ ወደሚካአል ከ1983 እስከ የካቲት 2005 ዓ.ም የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የውስጥ ሰራተኛ ሆኖ ሲሰራ ፥ ወርሀዊ ደመወዙ ከ 1,600 እስከ 6,000 ብር የነበር ሲሆን ፥ ነገር ግን ስልጣኑን እና የነበረውን ተሰሚነት በመጠቀም በፈጸመው የሙስና ወንጀል ከባለ4 ደረጃ ህንጻ ውጪ ፣ ከ3 ሚሊየን ብር በላይ በተለያዩ የግልና የመንግስት ባንኮች ተቀማጭ ማድረጉም ተመልክቷል። 2ኛ ተከሳሽ አቶ ዘርአይ ወልደስላሴ ከመከላከያ ሚኒስቴር በጡረታ እስከሚገለል ድረስ ወርሀዊ ደመወዙ 532 ብር የነበር ሲሆን ፥ በክስ መዝገቡ ተከሳሹ በተለያዩ ባንኮች 5 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ማስቀመጡ ፣ በአዲስ አበባ ቤቴል ቁጥር 3 በተባለ አካባቢ በ74 ካሬ ሜትር ይዞታ ላይ መሰረት የተጀመረበት ቦታ ፣ በአፋር ክልል ከ 1 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው ሁለት የእርሻ ኢንቨስትመንቶችና 2 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር ግምት ያላቸው ሁለት ሎደር ማሽነሪዎችም በስሙ መኖራቸው ተመዝግቧል ።
3ኛዋ ተከሳሽ የአቶ ወልደስላሴ እህት የ8ኛ ክፍል ተማሪ ስትሆን ፥ ምንም አይነት የገቢ ምንጭ የሌላት እንደሆነች ነው በክስ መዝገቡ የተገለጸው።ግለሰቧ በ 81 ሺ ዩሮ የተገዛ አንድ ስካቫተር ፣ አውቶሞቢል መኪና፣ በአዲስ አበባ ቦሌና የካ ክፍለ ከተሞች እንዲሁም በለገጣፎ ፣ በመቀሌና አክሱም ከተሞች 3 ሺህ 266 ካሬ ሜትር ቦታዎች በስሟ ተመዝግቧል ፤ በተለያዩ ባንኮችም ከ 8 ሚሊየን ብር በላይ ተቀማጭ ገንዘብም እንዲሁ ተመዝግቧል።
http://www.zehabesha.com/amharic/archives/10554

Tuesday, December 3, 2013

የወያኔ አገዛዝ በመልዕክተኞቹ በኩል ላቀረበው የ“እንደራደር” ጥያቄ ከግንቦት 7 የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የተሰጠ ምላሽ

December 2, 2013 posted by admin
ወያኔ ኢትዮጵያ ዉስጥ የገነባዉ ሥርዓት በከፍተኛ ችግሮች የተወጠረ ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የመሪው ሞት በወያኔ መሀል ያስከተለው ቀውስ፤ የሕዝብ ሁለገብ ትግል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎለበት መሄድ የፈጠረበት ስጋት እና ምርጫ በደረሰ ቁጥር የሚደርስበት ጭንቀት መጨመር ተደማምረው ውጥረቱን ወደ ከፍተኛ ደረጃ እያደረሱት መሆኑን የሚያሳዩ በቂ ምልክቶች አሉ። የእስካሁኑ ተሞክሮዓችን እንደሚያሳየው ወያኔ ውጥረት ሲበዛበትና መዉጪያና መግቢያዉ ሲጠፋዉ ፣ ተቃዋሚ ድርጅቶችን “እንወያይ፣ እንደራደር” በማለት ለውጥረት ማስተንፈሻ ጊዜ የሚገዛ መሆኑን ነው። ሰሞኑን በወያኔ አገዛዝ መልዕክተኞች በኩል የደረሰንን “የእንደራደር” ጥያቄ ንቅናቄያችን በዋናነት ያየው ወያኔ እንደለመደው ድርድርን ለውጥረት ማስተንፈሻነት ለመጠቀም እየሞከረ መሆኑን ነው።
የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚመኘው ዲሞክራሲያዊ ለውጥ በሰላማዊ መንገድ በሚደረግ ትግልና በጠረጴዛ ዙሪያ በሚደረጉ ዉይይቶች ቢመጣ የግንቦት 7 ምርጫ መሆኑን ንቅናቄያችን በተደጋጋሚ ግልጽ አድርጓል። ግንቦት 7ን ሁለገብ ትግል ውስጥ እንዲገባ ያስገደደው የወያኔ እምቢተኝነትና እብሪት ብቻ ነው።
የግንቦት 7 ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የሰሞኑ የወያኔ የእንደራደር መልዕክት እንደደረሰው በጉዳዩ ዙሪያ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ይህ ጉዳይ የኢትዮጵያን ሕዝብ ባጠቃላይ እንጂ ግንቦት 7ን ብቻ የሚመለከት ጉዳይ እንዳልሆነ ከድምዳሜ ላይ ደርሷል። ይህ ጉዳይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ከሚያደርገው ትግልና እየከፈለ ካለው መስዕዋትነት ጋር በቀጥታ ግንኙነት አለው። በመሆኑም፤ ለቀረበልን ጥያቄ ግልጽ መልስና፤ ድርድር ስለሚባለው ጉዳይም ያለንን አቋም ጉዳዩ በቀጥታ ለሚመለከተው የኢትዮጵያ ሕዝብና የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ሁሉ ለማቅረብ የሚያስችል ተጨማሪ አጋጣሚ አድርገን ወስደነዋል። በዚህም መሠረት ለቀረበልን ጥያቄ የሰጠነዉን መልስና አቋማችንን በድርጅታችን ድረ ገጽ ላይና በሌሎች መገናኛ ብዙሀን በኩል በይፋ ለመግለጽ ወስነናል።
በድርድር ስለሚመጣ ለውጥ ያለን የመርህ አመለካከት:
ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ግልጽ እንዳደረግነው ድርጅታችን ከምሥረታው ጀምሮ የትግል ስልቱን ሲወስን እምነቱ አድርጎ የተነሳው ዴሞክራሲያዊ ለውጥ በሀገራችን በሰላማዊ መንገድና በድርድር ቢመጣ በእጅጉ የሚፈልገውና የሚመኘው መሆኑን ነው:: ድርጅታችንን ወደ ሁለንተናዊ ትግል የገፋው በመግቢያው ላይ እንደገለጽነው የወያኔ እብሪት ብቻ ነው:: የቀረበልን ምርጫ በባርነትና በውርደት መኖር ወይም ለነፃነት እየታገልን መሞት ቢሆን ኖሮ ንቅናቄያችን የሚመረጠው ምን ግዜም ለነፃነትና ለአገር አንድነት ታግሎ በክብር መሞት መሆኑን በተደጋጋሚ ለሕዝብ ግልጽ አድርገናል። ይህ የማይናወጥ አቋማችን ደግሞ ለይምሰል የተቀመጠ አቋም ሳይሆን ከልባችን የምናምንበትና ኢትዮጵያን ጨምሮ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ አባላቶቻችንን ያሰባሰብንበት አቋም ነው። ዛሬ በትግሉ ግንባር የምንንቀሳቀሰውና ወደ ግባችን የሚወስደንን ተጨባጭ እርምጃዎች እየወሰድን ያለነውም በዚሁ አቋማችን ዙሪያ ነዉ።
ይህ አቋማችንና እምነታችን በአንድ ላይ ጎን ለጎን የሚሄዱ ሁለት መርሆችን አጣምሮ የያዘ ነዉ። አንደኛው፣ ሂደትን በሚመለከት ሁሌም ለድርድር ክፍት መሆኑን የሚያመለክት ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ፣ ይህ የድርድር ሂደት እንዲያው ለለበጣ የሚደረግ ሳይሆን ወደሚፈለገው ነጻነት በአነስተኛ መስዕዋትነት ሊያደርስ ይችል ከሆነ በሩን ላለመዝጋት እንጂ፣ በምንም አይነት ዋና ውጤቱን፤ ማለትም ኢትዮጵያን እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሀገር ማድረግን፤ የሚቀይር ወይንም ከዚያ ያነሰ ውጤትን ለመቀበል መፍቀድን ፈጽሞ የማያመለክት መሆኑን ነው::
በእኛ በኩል ድርድሩን አስፈላጊና ጠቃሚ የሚያደርጉት መነሻ የፖለቲካ እሳቤዎችም ከእነኝሁ ሁለት መንታ ገጽታዎች የሚመነጩ ናቸው:: በድርድር ለሚገኝ ፍትሀዊና እውነተኛ ውጤት ክፍት መሆናችንን ሁሌም እናሳያለን፤ ነገር ግን ይህን የምናደርገው የሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነት የተረጋገጠባትን ኢትዮጵያን እውን ማድረግ የሚጠይቀውን ማንኛውንም መስዋዕትነት መከፈል አለበት የሚለውን መሠረታዊ የአካሄድ መርህ በመመርኮዝ እንጂ መርሀችንን ለድርድር ለማቅረብ እንዳልሆነ በግልጽ መታወቅ ይኖርበታል::
ስለዚህም:
ሀ)    የድርድሩ ውጤት የኢትዮጵያን ሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነት ያረጋገጠ የዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን በአስቸኳይ እውን ማድረግ መሆን ይኖርበታል:: ይህ ዋናው ግብ ሆኖ ከዚህ በመለስ የሚኖሩ በሂደት የሚገኙ አነስተኛ ግቦች ሊኖሩ ይችላሉ (ለምሳሌ የፖለቲካ እስረኞች ማስፈታት…ወዘተ):: ሆኖም በምንም አይነት ለእነኝህ መለስተኛ ግቦች ተብሎ ዋናውን ግብ የሚያሳጣ ወይንም ጊዜውን ያላግባብ የሚያስረዝም ድርድር፣ ድርድር ነው ብሎ ድርጅታችን አይቀበልም። ስለዚህም ዋናው የድርጅታችን ዓላማና ግብ የሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነት ፣ በፍጹም ለድርድር የሚቀርብ ጉዳይ አይደለም:: በሥልጣን ላይ ባለው ኃይል በኩል ወደዚህ ግብ ለመድረስ ቁርጠኝነቱ በሌለበት ሁኔታ በሚደረግ ማንኛውም አይነት ድርድር ውስጥ ግንቦት 7 አይሳተፍም::
ለ)  በግንቦት 7 እምነት ማንኛውም ድርድር ወያኔ ከግንቦት 7 ጋር በተናጠል የሚያደረገው ሳይሆን ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ሁሉንም የፖለቲካ ኃይሎች ያካተተ መሆን ይኖርበታል:: ድርጅቶችን በተናጠል እየለያዩ “እንደራደር” ማለት በራሱ ጊዜያዊ የፖለቲካ ጥቅም ስሌትን የያዘ እሳቤ እንጂ፣ በዘላቂነት አገሪቱን እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ አገር ለማድረግ መፈለግን አያመለክትም:: ለአንድ ድርጅት ለብቻው የሚመጣ ወይም የሚጠቅም ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የለም:: ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የመፍጠር ፍላጎት ያለው ድርድር በአገሪቱ ያሉትን የተለያዩ የፖለቲካም ሆነ የሲቪክ ኃይሎችን ያካተተና ያመኑበት መሆን ይኖርበታል:: የሚደረገው ድርድርም ማን በስልጣን ላይ ይውጣ ወይንም የፖለቲካ ስልጣንን ባሉት ኃይሎች መሀከል እንዴት እናከፋፍለው የሚል የስልጣን ቅርምት ድርድር ሳይሆን፤ ሕጋዊና የሕዝቡን የሥልጣን ሉዓላዊነት ባረጋገጠ ሁኔታ የፖለቲካ ስልጣን እንዴት እንደሚያዝ ፍትሀዊ የሆነ ሂደትን ለማስጀመር የሚደረግ ድርድር መሆን አለበት::
ሐ) ቀደም ብለን እንደጠቀስነው ይህ ጉዳይ የሚመለከተው አንድን ድርጅት ወይንም የፖለቲካ ድርጅቶችን ብቻ ሳይሆን መላውን የኢትዮጵያን ሕዝብ ነው:: ይህ እስከሆነ ድረስ እንዲህ አይነት ድርድር ከሕዝቡ በተደበቀ ሁኔታ በሚስጥር የሚካሄድበት ምንም ምክንያት የለም::
2)   ከዚህ በፊት ከወያኔ ጋር ከተደረጉ ድርድሮች ያገኘናቸው ተመክሮዎችና ከዚህ በመነሳት ወደፊት በሚደረጉ ምንም አይነት ድርድሮች እንዳይደገሙ ለመጠበቂያ የሚሆኑ ከአሁኑ መወሰድ ያለባቸው እርምጃዎች
ከማንኛውም ወገን ጋር የሚደረግ ድርድር የተደራዳሪዎቹ ምንነት፤ ውስጣዊ ባህርያቸውን፤ ከተለምዶ ተግባራቸው ያላቸውን ተአማኒነትና ወደዚህኛው ድርድር ያመጣቸውን ምክንያቶች በበቂ ከመገንዘብ ጋር ተያይዞ የሚታይ ጉዳይ ነው:: ቃሉን አክባሪና ተዓማኒ ከሆነ ሰው ጋር የሚደረግ ድርድርና ያለፈው ታሪኩ ምንም አይነት የተዓማኒነት ባህርይ ከማያሳይ ቡድን ጋር የሚደረግ ድርድርም ሆነ ለድርድሩ የሚደረግ ዝግጅት ለየቅል ናቸው:: ይህ ማለት ግን ተዓማኒነት ካለው ኃይል ጋር ብቻ ነው ድርድር የሚካሄደው ማለት አይደለም:: በፍጹም ተዓማኒ ካልሆነ ኃይል ጋር የሚደረግ ማንኛውም ድርድር ግን ድርድሩ በእርግጥም ተግባራዊ ሊሆን የሚችል መሆኑን የሚያሳዩ ጠንካራ መጠበቂያዎች (System of Verification) እንዲሁም ግልጽ የመተግበሪያ ሥርዓቶች (Implementation Mechanism) ሲደረጉለት ብቻ ነው ከምር ሊወሰድ የሚችለው:: ከዚህም ባሻገር ግን መጀመሪያውኑ ወደ ድርድር የሚመጣው ለጊዜያዊ የፖለቲካ ጥቅም ሳይሆን በእዉነተኛ መንፈስ ከድርድር የሚመጣውን ውጤት በመፈለግ መሆኑን የሚያሳዩ “የመተማመኛ” ምልክቶች ሲያሳይ ነው በእርግጥም ወደ ድርድር የመጣው ከልቡ ድርድሩንና ከድርድሩ የሚመጣዉን ዉጤት ፈልጎ መሆኑን ለማመን የሚያስችለው::
ወያኔ ከተቀናቃኝ ወገኖች ጋር “ድርድር” ሲያደርግ የመጀመሪያ ጊዜዉ አይደለም:: እኛ እስከምናውቀው ድረስ ምናልባት በኃይል ይበልጡኛል ብሎ ከሚያምናቸው ወገኖች ጋር ካልሆነ በስተቀር፣ በረሃ ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ በማንኛውም ጊዜ ለቃሉ ታማኝ፤ ለመርሁ እውነተኛ፤ ለደረሰበት ስምምነት ተገዢ ሆኖ አያውቅም:: ይልቁንም ሶስተኛ አደራዳሪ ወገኖችን በሚያሸማቅቅና በሚያሳፍር መልኩ ውሸትን እንደ አዋቂነት፤ ማጭበርበርን እንደ ብልጠት፤ የተስማማበትን በገሀድ ማፍረስን እንደ የአመራር ብልሀት አድርጎ የሚያይ፤ ምንም እፍረትና ጨዋነት የሚባል ነገር ያልፈጠረበት እኩይ ኃይል ነው:: ከራሱ የድርጅት ጥቅምና በስልጣን ከሚገኝ የዝርፊያ ሀብት ማካበት ባሻገር፤ ለአገር ዘላቂ ጥቅም ብሎ የራሱን ጥቅም አሳልፎ የሚወስደው ምንም እርምጃ እንደሌለ በተግባር በተደጋጋሚ ያረጋገጠልን ኃይል ነው:: በግንቦት 7 ውስጥ ያለን ወገኖች ይህንን የወያኔ ባህርይ በንድፈ ሀሳብ ደረጃ ሌሎች ጽፈውት ያነበብነው ሳይሆን፣ እራሳችን በተግባር በተሳትፈንበት ሂደት ያገኘነው ጥልቅ ግንዛቤ ነው:: ይህንን ደግሞ በአንድ አጋጣሚ ብቻ ሳይሆን ከድርጅቱ ታሪክ ጋር የተጣበቀ፤ በአመራር አባላቱ ላይ እንደ ግል ባህርይ የሰረጸ መሆኑን እስክንገነዘብ ድረስ በተደጋጋሚ የተመለከትነው ነው:: ስለዚህም ከዚህ ኃይል በኩል የሚመጣን የ “እንደራደር” ጥያቄ ከዚህ በፊት እንዳደረገው ለገባበት የፖለቲካ ውጥረት ማስተንፈሻ፣ ለውሸት ፕሮፓጋንዳው መጠቀሚያ፤ ለጊዜያዊ የፖለቲካ ትርፍ መሰብሰቢያ፤ የዴሞክራሲ ታጋዮችን ትጥቅ ማስፈቺያና ወኔ መስለቢያ አድርጎ እንዲጠቀምበት በፍጹም አንፈቅድለትም:: ስለዚህም ከላይ በመርህ ደረጃ ከጠቀስናቸው ሶስት ጉዳዮች በተጨማሪ ምንም ዓይነት ድርድር ከመደረጉ በፊት ወያኔ ጉዳዩን ከምር የወሰደው መሆኑን የሚያሳዩ “የመተማመኛ” እርምጃዎች መውሰድ አለበት ብለን እናምናለን::
እነኝህም፣
ሀ)  ሁሉንም የፖለቲካ እስረኞች፤ ጋዜጠኞች፤ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መፍታት:: ይህ ደግሞ በግልጽ     የሚታወቁ እስረኞችን ብቻ ሳይሆን በድብቅ የተቋቋሙ ማጎሪያና ማሰቃያ ቤቶች ያሉትን ሁሉ ማጠቃለል አለበት።
ለ)  በሕዝብ በተለይ በተቃዎሚ ኃይሎች ላይ ወያኔ በየቀኑ እያካሄደ ያለውን ወከባና እንግልት ባስቸኳይ ማቆም፣ ሰብዓዊና የዜግነት መብታቸውን ማክበር አለበት።
ሐ)   በፖለቲካ ምክንያት ከዚህ በፊት የተወሰዱ ሁሉም ዓይነት ፍርድ ተብዮ ውሳኔዎች እንዲሻሩ ማድረግ፤ በሂደት ላይ ያሉ ከፖለቲካ ጋር የተያያዙ ምንም አይነት ክሶችን ማቋረጥ አለበት።
መ)   ሕዝብን በፍርሃትና በስጋት ለማቆየት ሆነ ተብለው የወጡ አፋኝ ህጎችን በአስቸኳይ ማንሳት አለበት።
ሠ)   ማንኛውም ድርድር ገለልተኛ የሆኑ ሶስተኛ ወገኖች ባሉበት፤ የድርድሩ ሂደት በምስልና በድምጽ ተቀርጾ በገለልተኛ ወገኖች እጅ ብቻ የሚቀመጥ፣ የድርድሩ ቦታም የተደራዳሪ ወገኖች በጋራ በሚስማሙበት ቦታ መሆኑን መቀበልና ይህንንም በግልጽ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ማሳወቅ አለበት።
እነኝህ ከላይ ያስቀመጥናቸው በወያኔ በኩል የሚወሰዱ “የመተማመኛ” እርምጃዎች ለተቃዋሚዎች ተብሎ የሚወሰዱ እርምጃዎች አይደሉም:: ወያኔ እነዚህን እርምጃዎች ለመውሰድ ቁርጠኝነት ሳይኖረው ለእውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መመስረት የሚደረግ ድርድር ላይ ከምር ይሳተፋል ብለን ማመን በፍጹም ስለማንችል ነው ::
እስከዚያው ድረስ ግን ግንቦት 7ም ሆነ ሌሎች ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መመስረት በቁርጠኝነት የምንታገል ኃይሎች፣ ወያኔ እነኝህን የመተማመኛ እርምጃዎች እስኪወስድና ቀደም ብለው በተቀመጡት መርሆች መሠረት በሚደረግ ድርድር በተግባር ሊመነዘር የሚችል ስምምነት፣ አልፎም ለምንም አይነት ማጭበርበርና መንሸራተት እድል የማይሰጥ ጠንካራ መጠበቂያዎች መኖራቸው እስኪረጋገጥ ድረስ፣ የጀመርነውን ትግል ይበልጥ አጠናክረን የምንገፋበት እንጂ በምንም አይነት ለአንድ አፍታም ቢሆን በድርድር ስም የማንዘናጋ መሆኑን አበክረን እናስታውቃለን::
የግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ፣
ኅዳር 23፣ 2006 ዓ:ም