Monday, December 2, 2013

ኡ ኡ - የመግባባት ያለህ!! ግርማ ሠይፉ ማሩ


ግርማ ሠይፉ ማሩ 
girmaseifu32@yahoo.com
ኢትዮጵያዊያን በተለያየ ፓርቲ አባል ሆንን ማለት ላለመግባባት ቃልኪንዳን ያሰርን እስኪመስል ድረስ መላቅድሳችን
የጠፋብን ይመስለኛል፡፡ ለምሳሌ የመለስን ራዕይ እናሳካለን በሚለው ዙሪያ መስማማት ላይጠበቅብን ይችላል፡፡ እንጋባባ
ሲባል ደግሞ አንድ እንሁን ማለታችን አይደለም፡፡ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም እንደሚሉት ከፋብሪካ እንደወጣ
ሳሙና አንድ መሆን የህይወትን ቅመም ያሳጣል ብቻ ሳይሆን ለስው ልጅ ተፈጥሮውም አይደለም፡፡ በቤት ውስጥ እንኳን
አንድ ዓይነት መሆን ለጫወታም አይመችም፡፡ ከኢህአዴግ ጋር ለመግባባት ብሎ እናስቀጥላለን የሚሉትን የሟች ጠቅላይ
ሚኒስትር ራዕይ ማወቅ የሚፈልግ አንድ ቅን ሰው ቢገኝ ይህ የሚባለውን ራዕይ በግልፅ ከየትም አያገኝም፡፡
እርግጠኛ ሆኜ የምነግራችሁ የመጀመሪያ ደረጃ ተማሪዎች፣ የወጣትና የሴት ሊግ አባላት፣ የሀርብቶ አደርና
የሌሎችም መሰል ስብሰባዎች መሪ መፈክሮች ስለ መለስ ራዕይ የሚያወሩ ቢሆንም አንድም ተመሳሳይ የሆነ አጭር
ሀረፍተ ነገር “የመለስ ራዕይ ይህ ነው” ብሎ የሚያስረዳችሁ አታገኙም፡፡ አሁን ደግሞ የመለስ አሰተምሮ የሚል ፈሊጥ መጥቶዋል፡፡

ለእኔ ራዕይ የሚባለው በረጅም ጊዜ ለመድረስ ያሰብንበት ግብ (የተለወጠ ደረጃ) ሲሆን እዚያ ግብ ለመድረስ ግን ብዙ የምናደርጋቸው
ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች መኖር ይኖርባቸዋል፡፡ የእነዚህ ተግባራት ድምር ነው በእርግጥ ካስብንበት የሚያደርሰን፡፡ ራዕይ ያለ ትክክለኛ
ተግባር የተሳሳተ ጅምር ከመሆን አያልፍም (Vision without proper action is a false start)፡፡ ስለዚህ ዛሬ “ራዕይ”
እናሰቀጥላለን ከሚሉ የጅምላ መፈክሮች ወጥትን መቀጠል የሌለባቸውን የተሳሳቱ ተግባሮችን እያነሳን መወያየት ተገቢ መሰለኝ፡፡
መግባባት ያለብን ነው ብዬ ስለማምን፡፡

ከነዚህ የተሳሳቱ ተግባሮች አንዱ በተለያዩ ደረጃ ያሉ ሞዴል/አርሃያ ያላቸውን ሰዎች ያለማመስገን ሲሆን የሚከፋው ደግሞ እነዚህን ሰዎች
እየተከታተሉ አንገት የማስደፋት ተግባር ነው፡፡ ባለ ራዕይ መሪዎች ይህን አያደርጉም፤ ይልቁንም እነዚህ ሰዎች እንዲበራከቱ እና ለጋራ
ራዕይ ሌሎችን እንዲያስልፉ ያበረታታሉ፣ አርሃያም ይሆናሉ፡፡ ኢህአዴግ ከዚህ አንፃር ባህሪው እንዴት ነው የሚታየው የሚል ነገር በሃሳቤ
መጣና ብንወያይበት እና ለመግባባት መንገድ የሚከፍት ከሆነ ብዬ ኡ! ኡ! ማላት ፈለግሁ፡፡ መጮኽ፡፡ ለዚህ ጩኸት መነሻ የሆኑኝ
በአጭሩ የሚከተሉት ናቸው፡፡

በቅርቡ አሜሪካን ያለ አንድ ወዳጃችን (ግርማ ጌታቸው ካሣ የሚባል) በሳውዲ ጉዳት ስለደረሰባቸው ዜጎቻችን የተሰማውን መልዕክት
ሲያስተላልፍ የኢህአዴግ ባለስልጣናትን በጅምላ ክፉና ጭራቅ አድርጎ መሳል ተገቢ አለመሆኑን አበክሮ አንስቶ ከእነ ሽመልስ ከማል
ዓይነት አደገኞች ኢህአዴግንም ቢሆን መጠበቅ እንደሚያስፈልግ እና እንደ ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ዓይነቶችን ደግሞ ማወደስ
እንደሚያስፈልግ ጠቆም አድርጎ ነበር፡፡ የዚህ መልዕክት በጎ መሆን የሚያጠራጥር አይደለም፡፡ ይህ ፅሁፍ በደረሰኝ ዕለት ምሽት ደግሞ
እንዲሁ በኢህአዴግ ሰፈር በደግ ስለሚነሳ ታታሪ ታጋይ እና የኢህአዴግ ሹመኛ የሆነ አቶ ሀይለሥላሴ ቢሆን የሚባል በዓለማችን ከጦር
መሳሪያ ቀጥሎ አደገኛ ሙስና ውስጥ ለውስጥ የሚስራበትን የሕክምና መሳሪያዎችና መድሐኒት የሚቆጣጠር መስሪያ ቤት እየመራ በክፉ
ሰሙ የማይነሳ ሰው መሆኑን ሰዎች ነገሩኝ፣ በስራ አጋጣሚ ግለሰቡን ስለማውቀው የሚሉትን ለማመን ብዙ አልተቸገርኩም፡፡

በዚያው ሰሞን በእድሜ ልክ እስር ነገር ግን ከህሊና ዕዳ ነፃ የሆነው ወንድማችን አንዱዓለም አራጌ በጻፈው መፅሃፍ ደግሞ ወደ 1997
ምርጫ ወስዶ አቶ አርከበ ዕቁባይ በአዲስ አበባ ምርጫ ያለመመረጣቸው አንዳንዴ ፍርዳችን ፍርደ ገምድልና የጅምላ እንደሆነ ጠቅሶ
አስነበበን፡፡ የሚገርማችሁ ከ1997 ምርጫ ቀደም ብሎ ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን በሚመለከት ምንም ቃል
በማይሉበት ወቅት አቶ አርከብ ዕቁባይ እራሳቸው ኤች.አይ.ቪ ተመርምረው በአዲስ አበባ አስደናቂ የመሪነት ሚና ሲጫወቱ ይህን እንደ
ተምሳሌት ተደርጎ ቸርልችል ጎዳና ጫፍ ላይ ከአራዳ ሕንፃ ግርጌ ትልቅ ቢል ቦርድ እና በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ፖስተሮችን እንዲታተሙ
ተደርጎ ነበር፡፡ በማግስቱ ቢል ቦርዱ ወደቀ ተብሎ ተነሳና ምን ተፈጠረ ሲባል ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር “የምን እዩኝ እዩኝ ነው” ብለው
እንዲነሳ ትዕዛዝ እንደሰጡ ሰማን፡፡ በይፋ የተሰጠ ትዕዛዝ ስለአልነበረ በሚያስደንቅ ፍጥነት ፖስተሩን እንዳይሰበሰብ አድርገን በማስራጨት
አቶ አርከበን ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን አስመልክቶ የሚያደርጉትን የመሪነት ሚና በመላው ሀገሪቱ እንዲስራጭ ተደረገ፡፡ ሟቹ ቢወዱትም
ባይወዱትም ጥሩ ውጤት አመጣና ውሎ አድሮ እራሳቸው ተመርምረው “እዩልኝ ስሙልኝ” ለማለት አበቃቸው፡፡ አንዱን አንገት አስደፍቶ
እራሰን ቀና ቀና ማድግ ተገቢ ባለመሆኑ ላይ ሁላችንም መግባባት ያለብን ጉዳይ ይመስለኛል፡፡

ከላይ እንደመግቢያ ያነሳሁትን ሃሳብ ያነሳሁት በኢህአዴግ ፖለቲካ ውስጥ በጎ ምግባር ያላቸው እና የተግባቦት ችግር የሌለባቸው ሰዎች
እንዳሉ እሙን ነው፡፡ እነዚህን ሰዎች አንሰቶ በበጎ ምግባራቸው ተገቢውን ቦታ መስጠት አስፈላጊ እንደሆነ ከልቤ አምናለሁ፣ ለነዚህም
ሰዎች በበጎ ሰራቸው እንዲቀጥሉበት ስንቅ ሊሆናቸው እነደሚችል ምንም ጥርጥር የለኝም፡፡ አሰፈሪው ነገር ግን ኢህአዴግ በባሕሪው
እንደዚህ ዓይነት ሰዎችን እንዴት አድርጎ ነው የሚመዝናቸው የሚለው ነው፡፡ እነኚህ ሰዎች ከእኛ ከሚያገኙት ክብርና ሞገስ በተፃራሪ
በቁጥጥር ስር ያዋላቸው ፓርቲ እንዳይሞቱ እንዳይድኑ አድርጎ ማኮላሸት ይችልበታል፡፡ ለእነደዚህ ዓይነት ተግባር የሟቹ ጠቅላይ
ሚኒስትሩ ሚና ከፍተኛ እንደ ነበር በተግባር የተረጋገጠ ነው፡፡ እንግዲህ ይህ ተግባር መቀጠል አለበት የሚል እምነት የለኝም፡፡ ባለ ራዕዩ
መሪ ካስቀመጡልን መጥፎ ተግባራት አንዱ ነው እና ላለማስቀጠል መግባባት ይኖርብናል፡፡
ግርማ ሰይፉ ማሩ
ምክንያቱ በውል ባይታወቅም/የተለያዩ መላ ምቶች አሉ/ ከአቶ መለስ ዜናዊ ሞት በኋላ በኢህአዴግቾ መንደር መነቃቃት የታየባቸው
የኢህአዴግ ሰዎች እንዳሉ ሁላችንም የምንታዘበው መሬት የወረደ ሀቅ ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች አንገታቸውን ቀና እንዳያደርጉ ሟቹ ጥላቸውን
አጥልተው ነበር፡፡ አለበለዚያም የሆነ ፍላፃ ይዘው ከጀርባቸው ነበሩ ማለት ይቻላል፡፡ አሁንም ቢሆን እነዚህን ሰዎች በስም እያነሱ ማወደስ
በተግባራቸው እንዲገፉበት ማበረታት በተገባ ነበር፡፡ ከኛ በኩል ውዳሴ ካገኙ በዚያ በኩል መጥረቢያ የሚሳልላቸው ከሆነ ከጥቅሙ ጉዳቱ
ስለሚያመዝን ለጊዜው ስማቸውን አለማንሳት ተገቢ ይመስለኛል፡፡ እነሱም ይህን ይረዱታል፡፡ በእኔ እምነት አቶ ኃይለማሪያም ደሰለኝ
ማስቀጠል ከሌለባቸው ተግባሮች አንዱ በእንዲህ ዓይነት ሰዎች ላይ የሚመሩት ፓርቲ መጥረቢያ መሳሉን እንዲያቆም ማድረግ
ይመስለኛል፡፡ ለእርሳቸውም ለሌሎች ተተኪ መሪዎችም ከህዝብ በጅምላ ለፓርቲ ከሚሰጥ ድጋፍ በተጨማሪ ለግለሰቦች በአስተዋፅኦ
ደረጃቸው የሚመሰገኑበትና የሚጠየቁበት ስርዓት ፓርቲውንም ቢሆን ይጠቅመዋ እንጂ አይጎዳውም፡፡ ቀና የሚሉትን እየተከተሉ አንገት
ማስደፋት መቆም ይኖርበታል፡፡ ተግባባን!!

ኢሕአዴግ ማሸማቀቅ የሚፈልገው ግለሰቦችን ብቻ ሳይሆን የፈለገ ቀን የተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍል ብሎ በጅምላ ህዝቡን ሊሆን ይችላል፡፡
እንደምታስታውሱት በቅርቡ በተደረገው የፕሬዝደንት ለውጥ ኢህአዴግ የህዝብን አስተያየት ለመስማት ደንታ አልነበረውም፡፡ ይልቁንም
ለማሳሳት ተግቶ የሰራ ይመስለኛል፡፡ ፓርቲው ለዕጩነት ያሰባቸውን ጥቂት ሰዎች መደበኛ ባልሆነ መልኩ ይፋ አድርጎ የህዝብን ይሁንታ
ቢያዳምጥ ምንም አይጎዳውም ነበር፡፡ መግባባትን ከመፍጠር ውጭ፡፡ ህዝቡን አይደለም ለጥቅምም ይሁን ለመስዋዕትነት የተሰለፉ
አባላቶቹን ባይተዋር አድርጎ ስራውን አጠናቀቀ፡፡ ይህ ብቻ አይደለም ኢህአዴግ ሲፈልግ ቡና ነጋዴዎችን፣ ከፈለገ የፋይናንስ ሴክተሩን፣
ባሻው ቀን የሪል እስቴት ሴክተር፣ ከፈለገ በአከራይ ተከራይ፣ ወዘተ ነጥሎ ይመታል፡፡ ዓላማውም አንገት ማስደፋት ነው፡፡

በዚህ በኩል በተቃዋሚ ጎራም ቢሆን የጠራ አቋም አለ ብዬ አላምንም፡፡ ምስጋና ለሚገባው ምስጋና ከመስጠት ይልቅ እየገፉ ከክፋተኞቹ
ጎራ ለመቀላቀል ጥረት የሚደረግ ይመስለኛል፡፡ ለዚህ የሚቀርበው አመክንዬም ኢህአዴግን እንደ ስርዓት ነው መቃወም የሚል ነው፡፡
ይህን ስናደርግ ደግሞ ሁሉንም የፓርቲ አባላት በተለይም ከፍተኛ ሹሞች የሚያደርጉትን መቃወም ነው ብሎ የሚያምነው ቁጥር ቀላል
አይደለም፡፡ ይህ አስተሳሰብ ከመቀራረብ ይልቅ መራራቅን፣ ከመተማመን ይልቅ ጥርጣሬን፣ በማስፋት ሀገራችን ለምንላት ኢትዮጵያ እና
ለህዝቡ አለን የምንለውን ራዕይ ማሳካት እንዳንችል እርስ በእርስ ተጠላልፈን እንድንቀር እያደረገ ነው፡፡ በእኔ እምነት ለብዙ የኢህአዴግ
አባላት በሚፈፅሙት በጎ ምግባር የሚገባቸውን በቸርነት ለማድረግ ዝግጁ መሆን ይጠበቅብናል ከታቀፉበት ፓርቲ ሊወርድባቸው
የሚችለውን ፍላፃ ከግምት ውስጥ በማስገባት ጭምር፡፡ የእኛን ሰፈር ፍላፃ ለመቋቋምም ቢሆን ጥንካሬ ይጠይቃል፡፡ እባካችሁ በፓርቲ
ደረጃ ያሉን ልዩነቶች እንደተጠበቁ ሆነው ግለሰቦች በተናጥል ለሚያደርጉት በጎነት እውቅና ለመስጠት ብንግባባ አንዱን የልዩነት ግንብ
አፈረስን ማለት ነው፡፡ ከዚያም ለመቀራረብ መንገድ እንጀምራለን፡፡ የዛሬ ሁሁታዬ ይህው ነው፡፡

ቸር እንሰንብት!!



ኢትዮሚድያ - Ethiomedia.com
December 1, 2013

Sunday, December 1, 2013

የማለዳ ወግ ...የጅዳ ሸረፍያ እስከ ሽሜሲ የተሰማው የወገን ዋይታና እዚህ ያደረሰን መንገድ ! (ነቢዩ ሲራክ)

ፈታኙን ወቅት ለማለፍ ...
 የሳውዲ የምህረት Aዋጅ Aልቆ በሪያድ መንፉሃ ላይ Aለምን ያሳዘነ ሰቆቃ ተፈጸመ
...ስጋት ነግሶ ፣ ኑሮ ከብዶን ጨንቆን ጠቦን ከርመናል ! በዚህ ክፉ ቀን ወገን ወገኑን
ለመርዳት ደፋ ቀና በማለቱ ረገድ የሃገሬ ልጅ ከጫፍ Eስከ ጫፍ በቁጭት ስሜት
ሲንቀሳቀስ የፖለቲካው ትኩሳት ወላፈን Eያጓተተን Aልሰነበትንም Aይባልም። ግልጥልጥ
Aድርግን Eናውራ ካልን የኑሮ ውድነት Eና ድህነቱ Eየደቆሰን ቢያስቸግረን ከወገን
ቤተሰቦቻችን ተለይተን ፣ የEማማ Iትዮጵያውያን ምድር ለቀን በስደት ስንባዝን
በደረሰብን የከፋ Aደጋ ለመቋቋም ከምናደርገው ትግል ባልተናነሰ ልዩነትን የሚያገዝፉ
መሰናክሎችን ማለፉ የከበደ Aበሳ ሆኖብን ሰነባብቷል!
 በዚህ ፈታኝ ወቅት መፈተን ግድ ሆነና የዜጎች Eንግልት ከሪያድ Aልፎ ወደ ጅዳና
Aካባቢው ሲሸጋገር በርካታ ወገኖች በግልና በቡድን በመሰባሰብ በጎ Eርዳታ ለማድረግ
መንቀሳቀስ ጀመሩ። ቀጠሉና ወገኖችን ለመርዳት ብቸኛው Aደራጅ ለሆኑ የIትዮጵያ
መንግስት Iንባሲና ቆንስ ነመ/ቤቶች " ለወገኖቻችን Eንድረስ !" በሚል ያቀረቡት ጥያቄ
ምላሽ Aገኘ። የጅዳ ቆንስል በማህበራትና በIህAዴግ ድርጅቶችን "በነጻ የበጎ Eርዳታ
ድጋፍ Eናቅርብ " ባይ ዜጎች ጋር ጥምር Aስቸኳይ ስብሰባ በመጥራት በAይነቱ ነጻ
የተባለውን "ወገን ለወገን ደራሽ " የተባለውን ኮሚቴ Aቋቋመ። ኮሚቴው የEርዳታ Eና
ድጋፍ ሰጭ፣ የመረጋጋትና የህዝብ ግንኙነት ንUስ ኮሚቴን Aቋቋመ።

የጅዳ ሸረፍያው ሁከት...
 በኮሚቴው መዋቀር መባቻ በጅዳ ሸረፍያ በተባለው Aንድ ሰፈር "ወደ ሃገር Eንግባ !"
ብለው ድልድይ ስር ከተቀመጡ Iትዮጵያውያን መካከል Aንዲት Aራስ Eህት "ልጇን
ሜዳ ላይ ጥላ ሔደች !" ተባለና ህጻን ወድቆ ተገኘች፣ ያንኑ ቀን ከቀትር በኋላ ሌላ Aሳዛኝ
ክስተት በድልድይ ተከሰተ። ከድልድዩ የቅርብ ርቀት Aንድ ወንድም በድንገት በመኪና
Aደጋ ሞተ! የቀን ጸሃይ ፣ የማታው ወበቅ ያደከመውን ወገን Aስቆጣው። ሸረፍያ
ታመሰች! ጸጥታ Aስከባሪዎች ጸጥታ ለማስከበር Aካባቢውን ከበቡት ፣ ፍጥጫ ነገሰ!
በሁኔታውን ግራ የተጋቡት ፖሊሶች ጥይት ወደ ሰማይ በመተኮስ ሁከቱን ለማረጋጋት
ሞክረው ባይሳካላቸውም ከጅዳ ቆንስል የተላኩ የድርጅት Aባላት ሁከቱን ለማረጋጋት
ቻሉ!
 በተፈጠረው ግርግር የተደናገጡት በድልድዩ ሁለት ሳምንታትን በመከራ የገፉ ወገኖች
"ለደህንነታችን ሰጋን! " ሲሉ በዚያው ምሽት ወደ ጅዳ ቆንስል ተመው በመምጣት
በቆንስሉ Aካባቢ ባለው ሜዳ በAሳዛኝ ሁኔታ ከተሙ። የወዳደቀ Eንጨት ፣ፕላስቲክና
Eንጨት Eየለቃቀሙ ጎጆ ሰሩ ! በከፋ ቀን ያልታሰበው ያልተገመተው ሁሉ ይሆናልና ፣
ያላሰብነው ሆነ ! ውሎ ሲያድር የሰው ቁጥር Eየበዛ የጅዳ ቆንስል በከፋቸው ዜጎች
ተጥለቀለቀ ... Aስደሳቹ የወገን ርብርብ ...
 ይህን ጊዜ ነበር ሰው ለሰው ልብሱ መሆኑን የታዘብኩት ። የከፋቸውን ለማጽናናት ፣
የጠማ የደረቀውን ጉሮሮ ለማርጠብ፣ በርሃብ የታጠፈውን Aንጀት ምግብ በማቅረብ
በመታደግ ፣ በተለይም ህጻናትን ለመደገፍ የተደረገው ርብርብ ፍጹም ልዩነታችን ያስረሳ
ልዩ የታሪክ Aጋጣሚ ነበር ። ... ፍጹም ከህሊናየ የማይጠፋ ህብረት !
 የወገኖች የሜዳ ቆይታ ከሳምንት Eንዳያልፍ የተደረገው ጥረት የሚያስደስት ሲሆን
ይህንን ለማደረግ "የዜጎቸ ስቃይ Aኔንም ያገባኛል! " በሚል ቀድሞ Eስከ Aስር ሽህ
የሳውዲ ሪያል በማዋጣት ከመጀመሪያው ቀን Aንስቶ Eስከ መጨረሻዎቹ ቀናት የሰሜንና
ደቡብ " ዋይት " ማህበር Aባላት ምግብ Eና ውሃ በማቅረብ ያሳዩት ትጋት ከEድሜ ጠገብ
ወንድሞች ያልጠበቅኩት ነበር ። ይህ ማህበር በተቋቋመው ኮሚቴ ውስጥ በEርዳታ Aልፎ
በማረጋጋቱ ኮሚቴ በመታቀፍ ያሳየው ፋና ወጊ Eንቅስቃሴ ወደር Aልነበረውም! የጅዳ
ኮሚኒቲ ፣ የIህAዴግ የድርጅት ፣ ለAደጋው የተቋቋመው ኮሚኒቴ ፣ የOሮሞ ልማት ፣
የጂዳ ቆንስል ሰራተኞች ፣የሳውዲው ትውልድ Iትዮጵያዊው የመርባይ ቤተሰቦች ፣
ስማቸው Eንዳይጠቀስ የፈለጉ ግለሰቦች Eና በግል ከጎናችን የተሰለፉ ነዋሪዎች ውሃ ምግብ
በተወሰነ ደረጃ ከማቅረብ ጀምሮ ሻንጣ በማጓጓዝ Eና ዜጎችን በማመላለስ ማስተናገዱ
ረገድ በህብረት የሰሩትን በጎ ምግባር ሳስበው ኩራት ይሰማኝል! ይህ ለበጎ ምግባር
የተደረገ ትብብር የባጀንበትን የከረረ ልዩነት ከAEምሯችን ሲያጠፋው በህብረት ለAንድ
Aፍታም ቢሆን የከፋውን ህይዎት ጠግኖት ማየት መቻል ስለ Eውነት ያኮራል !
የሽሜሲው መጠለያ ቆይታና የግፉAኑ ምሬት ...
 በዚህ መንገድ በቆንስላው ለቀናት የቆዩት ወገኖች መካ መግቢያ የቅርብ ርቀት ወደ
ሚገኘው የሽሜሲ መጠለያ Eስር ቤት ተላኩ ። "ወገኖቻችን ወደ ማጠለያ ገብተው ወደ
ሃገራቸው በሰላም ሊመለሱ ነው !" ብለን ደስታችን ወሰን ባጣበት Aጋጣሚ ግን ወደ
መጠለያው የተወሰዱ ወገኖች ከመጠለያው ሳይገቡ ከግቢው ውጭ ፈሰው ለሶስትና Aራት
ቀናት Eንግልት Eንደ ደረሰባቸው ተሰማ ! ተከፋን ! Eኔም Eንደለመድኩት በሰላም
የሸኘናቸውን ወገኖች ሮሮ መስማት ጀመርኩ ! በቀጣይ ቀናት በግልና ከኮሚቴው ጋር
በመቀናጀት የውሃ ፣ የምግብና የመጸዳጃ ጥያቄውን ለሚመለከታቸው ለማቅረብ ያደረግነው
ሙከራ ሳይሳካ ቀረ። በEርዳታና ድጋፍ ሰጭው ኮሚቴ በኩል የውሃ Aቅርቦቱን ለማድረግ
በተደረገው ሙከራ በAርባ Aውቶቡስ የሞላውን ወደ ሶስት ሽህ የሚሆነውን ሁሉንም
ማስተናገድ Aቅም Aጣን ! የሚቻለውን ግነወ Aደረፍን። Eለተ ሃሙስ ከሽሜሲ መጠለያ
በር ሜዳ ይ የተጣሉት ወገኖች ሮሮ በማየሉ ማታውኑ የEርዳታ Aስተባባሪዎች ባደረጉት
ጥረት የሰሜንና ደቡብ "ዋይት" ማህበር Aባላት ለAርብ ጠዋት የምግብ Eና ውሃ Eንዲ
ያቀርቡ ተጠይቆ በማህበሩ ይሁንታን Aግኝቶ Aርብ ጠዋት Aቅርቦቱን ለመከወን ቀጠሮ
ተያዘ !
የሽሜሲው ሁከት ...
 Eንዲህ Eንደሆነ ሃሙስ በAርብ ተተካ ! Aርብ ጎህ Eንደ ቀደደ በተንቀሳቃሽ ስልኬ
በውሃ ጥማት Eና በርሃብ የታመሱት ወገኖች በተለይም ህጻናትን የያዙ Eናቶች Eንባ
የተቀላቀለበትን የምሬት ጩኸት Eያመመኝ መስማት ጀመርኩ ... በደረሰባቸው ሰቃይ Aምርረው "ወደ ጅዳ Eንመለስ ፣ ሱቅ Eንኳ ከሌለበት ቦታ ከምንሰቃይ ሰው ሊያየን
ወደሚችል ቦታ Eንሄዳለን! " ያሉኝን መልEክት ለማሰማትና መፍትሔ ለማፈላለግ
ብሞክርም ሙከራየ የተሳካ Aልነበረም ። Eናም Eኩለ ቀን ላይ ምሬት ፈንቅሏቸው ወደ
መካና ጅዳ Aውራ ጎዳና መውጣት ሲሞክሩ ከጸጥታ Aስከባሪዎች ጋር መጋጨታቸውን
ተረዳሁ! የሁከት ብጥብጡን ጅማሬ ሂደት በቀጥታ በስልክ መረጃውን ከሚያቀብሉን
ግፉAን ወገኖች ድመጽ Aልፎ የሚሰማው የተኩስና የሁከት ጫጫታ ድምጽ Eየሆነ ያለውን
ያሳይ ነበር ... ይህ በEንዲህ Eንዳለ የሰሜንና ደቡብ "ዋይት" ማህበር Aባላት ለAርብ
ጠዋት የምግብ Eና ውሃ Aዘጋጅተው ወደ ሽሜሲ ሊንቀሳቀሱ ሲሉ የሁከቱን መረጃ
ደረሳቸው! የተዘጋጀው ምግብ ማቅረብ ሳይቻል ቀረ!
 ከሰAታት በኋላ የጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች Eና የሳውዲ መንግስት ከፍተኛ ሃላፊዎች
ችግሩ Eስኪከሰት ዘግይተውም ቢሆን ባደረጉት ድርድር ሁከቱ በርዶ ለሶስት ሰAታት
ተዘግቶ የነበረው የጅዳ መካ Aውራ መንገድ ተከፈተ ... የተዘጋጀው ምግብ ማቅረብ
ያልቻሉት ወንድሞች ምግብ ውሃውን በሽሜሲ ላሉት ወገኖች መድረስ ባይችሉም በመካ
ኩደይ በተባለ Aካባቢ በተመሳሳይ መንገድ "ወደ ሃገር Eንግባ! " በሚል Aደባባይ ለወጡት
ወገኖች ምግብና ውሃውን በAፋጣኝ መንገድ Aቀረቡ ፣ Aሁንም ካለው የህዝብ ብዛት
Aንጻር ምግቡና ውሃው ለሁሉም ባይዳረስ Eንደሚሆን Eንደሚሆን Aድረገው Eርዳታውን
Aከፋፈሉ ! ወገን ለወገን ደራሽ መሆኑን ለማየት ፣ ለመስማት ብሎም የመከራው ቀን በጎ
ስራ Eማኞች ለመሆንን ታደልን !
ይቅርታው ...
 Aርብ ምሽት - የወገን ለወገን ደራሽ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ Aድርገን Aንዱን
Aንስተን Aንዱን ስንጥል Aመሸን ። Eኩለ ሌሊት ስብሰባው ሲከወን የኮሚቴውን Aካሔድ
ለማስተካከል የተወሰደው ውሳኔ ተላለፈ፣ ከጎናችን ሆነው ደፋ ቀና የሚሉትን ወገኖች
Aስከፋ : ( ውሳኔው መተግበር ቢኖርበትም ከውሳኔው በፊት መስራት ያለብንን ስራ
ባለመስራታችን ወንደሞቻችን Aስቀይመናል! የሚሰራ ይሳሳታል ፣ ስንሰራ ተሳስተናል!
ይቅርታችን የከበደ ነው ! የAካሔድ ጠፋቱ Aካል ነበርኩና ያች ምሽት ለEኔ ከባድ ነበረች
... የከበደኝ መሆን ያለበት ወገንን ለመታደግ የሚደረገውን ሂደት ለማስተካከል
የተደረሰበት ውሳኔው ሳይሆን ቡና Eየጨለጡ የሚፈላሰፉ በበዙበት ከባቢ ደጋግ በጎ
Aድራጊ ወንድሞቻችን በማስከፋታችን ነበር! በዚሁ ስብሰባ "ገጽታችን Eንገንባ! "
የምትለው የAንዳንድ ወገኖች Aካሔድ Aንድምታ ግራ ሲያጋባኝ Aለም Aቀፉን ህብረት
Eየነቀነቀ ያለውን የወገን ለወገን የመድረስ Aላማ ወደ ሌላ Aቅጣጫ የሚጎትት ምሽት ላይ
በስልክ ካደረግኩት የራዲዮ ውይይት ጋር በAንድና በሌላ Aቅጣጫ ሲሳሳብ ከፊቴ ተደቀነ!
ስብሰባው Eኩለ ሌሊት ተጠናቀቀ! ... ወደ ቤት ገብቸ Eንዲህ ስል የተጎዳ ስሜቴን
Eንዳሻኝ ስሜት ህመም ፣ ተስፋ ህልም ስጋቴነወ Eንዳሻኝ በምገልጽባት የፊስ ቡክ ገጼ
ተነፈስኩት ...ተቃዋሚው ባንድ ወገን መንግስትና ደጋፊው በሌላ ወገን ይሳሳባሉ ፣ ሁለት
ዝሆኖች ይታገላሉ ፣ ድሃ መውጫው ቀዳዳ ጠቦታል ፣ ወገኔ ከዝሆኖች ጥል ስር የበቀለ
ያልታደለ ሳር ሆኖ ይደቆሳል ፣ የባሰውኑ ታምሜ Aመሸሁ ! Aይመሽ የለም መሽቶ
ከተማሩ ከተመራመሩ ፣ ከወለዱ ከከበዱት ወንድሞቸ ጋር ወገኔን መረጃ ከማቀበል
በተግባር ወደ መርዳት ልሸጋገር ስብሰባ ተቀመጥኩ ! ትልልቆቹ Aንሰን ቢታየኝ ህምም
ታምሜ Eኩለ ሌሊት ወደ ቤት ገባሁ ! ያየሁ የሰማሁ የሆነውን ለመርሳት Eየሞከርኩ
Aይተኛ የለም ተመስገን ብየ ተኛሁ ! ዛሬ Eንጃ ! የማውቀው የትናንቱን ክፉ ቀን ነው ! በተስፋ የተጀመረው ቀንና የምስራቹ ...
 Eለተ ሰንበት ቅዳሜ - በልጀ የማለዳ ሳቅ ታጅቤ በተስፋ ተነሳሁ ... Eንዲህም Aልኩ
...ዛሬ Eንጃ ! የማውቀው የትናንቱን ክፉ ቀን ነው ! ልጀ ሆይ! መውለድ ደጉ ዛሬን ባንች
ፈገግታ በተስፋ ሊጀመር ነው ! ተመስገን ! ተመስገን ! ተመስገን ! መልካም ቀን
ለሁላችሁ!
 የEኔን የሃጥUን ጸሎት ሳይሆን ልጆቻቸውን ታቅፈው ጨንቋቸው ፣ ጮኸው ሰሚ
ያጡትን ወገኖች ሃያሉ Aምላክ Aልተዋቸውም! EግዚAብሔር Aምላክ በስደት የተሰበረውን
የወገኖቻችን ጉዳት ሰማ ! የጨነቃቸው የጠበባቸው በደስታ ፊስታ ተናኙ ! በጭንቀት
ሁከት የሰነበቱት ወገኖች ወደ ሃገር ቤት ለመሄድ ዝግጅት መጠናቀቅ መረጃ የደረሰኝ
በተስፋ የጀመርኩትን ቀን የሚያበላሽ ቧልት ሰምሁና Aዘንኩ ። ሞራል ያጡ ፣ በወገን
ችግር ጀርባ በቪዛ ሽያጭ ፣ በድለላ Eና በመሳሰሉት ጥቅምን በማጋበስ የለመዱ ክፉዎች
በዚህ ክፉ ቀን Eንኳ ስለሚንገላታው ወገን Aይጨነቁም! ለጆቻቸውን ስለሚያስተምሩበት
ትምህርት ቤት Eያደር መበለሻሸት ግዳቸው Aይደለም! Eናም ተበሳጭቸ ከጅዳ ኮሚኒቲ
ካፍቴርያ Eንደወጣሁ ስልክ ተደውሎ የምስራች መልEክት ደረሰኝ!
" ነቢዩ ደስ ብሎናል ! Eንኳን ደስ ያለህ ! ትናንት Eየደወልን ስጨናንቅህ የነበርነው
ሁላችንም ወረቀታችን Aልቆልን ወደ ጅዳ Aየር መንገድ Eየተጓዝን ነው! " ተመሳሳይ
የስልክ ጥሪ ደረሶኝ ተመሳሳይ የምስራች ሰማሁ! ዛሬ ለቅሶ የለም! Eኒያ ሲንገላቱ የሰነበቱ
ወገኖች ሳቅ በሳቅ ሆነው ፣ በደስታ ተውጠው የምስራቹን ሲያበስሩኝ የተሰማኝ ደስታ ወሰን
የለውም ! Aዎ ወደ Aራት ሽህ የሚገመቱት ወገኖች የሃገራቸውን መሬት ለመርገጥ
መታደላቸው በEርግጥም ታላቅ የምስራች ነው ! ተመስገን !
ከሽሜሲው ግጭት የምንማረው ...
 ከሽሜሲው ግጭት ብዙ ልንማር ይገባል ። በጅዳ ቆንስል የቅርብ ርቀት ከትመው
ለሳምንት ከቆዩ በኋላ ወደ ሺሜሲ መጠለያ በወገን ትብብር የተወሰዱት ወገኖች
በመጠለያው ግቢ Eንዳይገቡ ተደርገው ነበር። በጠራራው ጸሃይ በAውቶቡስ Eና በሜዳ
ላይ ያለ ምግብና ወሃ መሰንበታቸውን የጅዳ ቆንስል ሰራተኞችና ሃላፊዎች ወደ መጠለያው
ሲገቡና ሲዎጡ ይመለከቷቸው ነበር ። ያም ሆኖ ከሶስትና ከAራት ቀናት በላይ ህጻናትን
የያዙተን ጨምሮ Aቅመ ደካማ Eህቶች በወሃ ጥማት ሲጠበሱና በርሃብ Aንጀታቸው
ሲታጠፍ ከቅርብ ርቀት ያሉት የቆንስል መስሪያ ቤቱ ሰራተኞችና ሃላፊዎች መፍትሄ
Aላፈላለጉላቸውም። በዚህ መሰል Aስከፊ ሁኔታ ህጻናት ደክመው ፣ ነፍሰ ጡር Eህቶች
ደክመው ፣ የተወሰኑት AEምሯቸው ተነክቶ ታዝበናል። የሁከቱ መንስኤ ለቀናት በርሃብና
በውሃ ጥማት የተቸገሩት ግፉAኑ ወገኖች ትEግስት ማጣት Eንጀ ሁከትን ለማስነሳት ታቅዶ
የተፈጸመ Eንዳለሆነ ግልጽ መሆን Aለበት!
 " ወደ መጠለያ Aስገባሁ !" ብሎ በመጠለያው በር ሜዳ ላይ ያፈሰሳቸውን የሳውዲ
መንግስት Aካል ከመሞገት ባለፈ ይህን መሰል Aስነዋሪ ስራ Eንዳይሰራ የጅዳ ቆንስል
ሃላፊዎች መስራት የነበረባቸውን ስራ በበቂ ሁኔታ ሰርተዋል Aልልም። የጅዳ ቆንሰል
ሃላፊዎች ወደ መጠለያው የተላኩ ዜጎቹን ጉዳይ በEግር በEግር ተከታትለው ማስፈጸም
ነበረባቸው። ይህ Aልተደረገም ወይም ተደርጎ Aልተሳካም ይሆናል። በAንድ Aቅጣጫ
ያልተሳካውን በሌላ Aቅጣጫ ለማስፈጸም የቆንስሉ ሃላፊዎች ያደረጉት ሙከራ Aንድ ሁለት ቀን ቢከሽፍ ከAራት ቀን በላይ መጓተቱ ዲፕሎማቶቻችን ከፍተኛ ጫናን ፈጥረው
ጉዳዩን በማስፈጸሙ ረገድ Eንዳልተሳካላቸው በግልጽ ያሳያል። የሳውዲ መንግስት Eና
የጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች በፈጻሚና Aስፈጻሚ Aለካት መካከል መግባባት ቢኖር ኖሮ ዜጎችን
ወደ መጠለያው Eንኳ ማስገባት ቢገድ ካሉበት ቦታ ምግብና ውሃ በማቀበል Aጠቃላይ
ሂደቱን መቆጣጠር ይቻል ነበር። በሂደቱን የጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች በቅርብ ተከታትለውት
ቢሆን ኖሮ Aነወዱ Aንኳ ቢያስቸግር የጉዳዩን Aሳሳቢነት ለማስረዳት ከከፍተኛ የሳውዲ
መንግስት ሃላፊዎች መድረስ ይችሉ ነበር። ከዚህ በተጓዳኝ ለመገናኛ ብዙሃን በAሰራር
የሚገጥማቸውን መሰናክል በማቅረብ ድምጻቸውን ሊያሰሙ ይገባ ነበር ። ይህ Aልሆነምና
ትኩረት ባለመሰጠቱ ሰው ተራበ ተጠማ ሁኔታዎች ከቁጥጥር ውጭ ሆኑ ! ወደ ዝርዝር
ሳንገባ ካለፈው ጥፋት ልንማር ግድ ይለናል! ካለፈው ስህተት ከተማርን ከተመሳሳይ ሁከት
ልንድን Eንችላለን !
የማይበጀን ሁከት ፣ የማይፈይድልን መረጃ ....
 ይህን መሰል ችግር መቅረፍ የሚቻለው ሁላችንም ያገባናል ብለን በህብረት ስንደጋገፍ
ብቻ ነው! ሰላማዊ ሰልፍ Aና የAደባባይ ላይ ተቃውሞ በማይፈቀድ በማይታሰብባት
ሳውዲ Aረቢያ ችግር Eንኳ ቢሆር የሚፈታባቸውን መንገዶች ከማፈላለግ ባለፈ ሁከት
Aመጽን መከተል Aይጠቅመንም። ወደ ሁከት የሚወስደውን ሁሉ Eንቅስቃሴ በማስዎገድ
Eና መረጃን በመለዋወጥ ችግሮች Eንዲሰሙ ማድረግና ማስተካከል ይቻል ይመስለኛል!
በነጻነት መረጃን ከተለዋወጥን የማይቻል የለም ይቻላል! ነዋሪውን ለማረጋጋረት ብሎ
ያልሆነውን ሆነ ብለን "የዋሽቶ ማስታረቅ! " ዘይቤ ፍጹም Aይበጀንም! ገጽታን Eናሳምር
ምናምን ብለን "ቅባቱን " ተጠቅመን መረጃውን Eና Eውነቱን ካዛባነው መረጃው ዘባተሎ
ይሆናል ፣ ከዚሁ ጋር ችግሩን ለመታደግ የምንወጣ የምንወርደው ሁሉ የተዛባው ባለቅባት
መረጃ ተAማኒነትን ያሳጣናልና ድካሙን ሁሉ የEንቧይ ካብ ያደርገዋልና ጥንቃቄ
ማድረግ ይገባል : )
የስኬቱ ባለድርሻዎች ...
 በመላ ሳውዲ ችግሩ በEኛ ላይ ከጠና ወዲህ ወገኖቻችን ወደ ሃገራቸው Eንዲገቡ
የሚደረገው ስኬት በተወሰኑ ግለሰቦች ወይም ቡድኖች የተከወነ Aይደለም ። በሃገር ቤት
በውጭ ሃገር ያሉ ወገኖች በሳውዲ መንግስት ላይ ያሳደሩት ተጽEኖ ፣ በሳውዲ Aረቢያ
የተለያዩ ከተሞች የምንገኝ ሁላችንም በህብረት የሰራነው ስራ ውጤት ነውና ደስ ሊለን
ይገባል! ምስጋናውም ለሁሉም ነው ! ወገንን መደገፍ ምስጋና ካስፈለገው ማለቴ ነው ...
ደስ ሲል ...!
ለወገን ደራሹ ወገን ነው ፣ በህብረቱ ፣ Eንበርታ !
ነቢዩ ሲራክ
ምንጭ የኢትዮጵያ ሜዲያ መድረክ

Saturday, November 30, 2013

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀ-መንበር ኢ/ር ይልቃል በጀርመን- በስዊዘርላንድ – በሆላንድ – በዋሽንግተን ዲሲ ውይይት ያደርጋሉ

(ኢ.ኤም.ኤፍ) የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀ-መንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት የአውሮፓና የሰሜን አሜሪካ ጉብኝታቸውን ጀምረዋል። ትላንት ኖቨምበር 29 ጀርመን ፍራንክፈርት የገቡት ኢ/ር ይልቃል በመጪዎቹ ቀናት በአውሮፓ ከተሞች ተከታታይ የስራ ጉብኝት እንደሚያደርጉ አስተባባሪ ኮሚቴው በተለይ ለኢ.ኤም.ኤፍ አስታውቋል።
ለጊዜው በደረሰን የስራ ሰሌዳ መሰረት :-
- ቅዳሜ ኖቬምበር 30 በጀርመን ኑረንበርግ ከኢትዮጵያኖች ጋር ውይይት ያደርጋሉ።
- ሰኞ ዲሴምበር 2 በፍራንክፈርት የሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ይገኛሉ።
- ዲሴምበር 5 ጄኔቭ ስዊዘርላንድ የሚደረገው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ይሳተፋሉ።
- ቅዳሜ ዲሴምበር 7 በሆላንድ ህዝባዊ ውይይት ያደርጋሉ።
ከአውሮፓ ቆይታቸው በኋላ ወደ ዋሺንግተን ዲሲ በመጓዝ በዲሴምበር 30 አርሊንግተን በተዘጋጀው ስብሰባ ከፕ/ር አል ማርያም ጋር ንግግር ያደርጋሉ።
Nov 30: Nuremberg : Public meeting and fundraising
Dec 02: Frankfurt: Appearance at a rally; Meet with invited guests for dinner
Dec 05: Geneva: appearance at a rally
Dec 07: Amsterdam: Public meeting
Washington DC Public Meeting with Semayawi Party Chairman Eng. Yilkal Getnet – Sunday Dec 15, 2013 – Sheraton Arlington Hotel.     Source Ethiopian media forum 
Blue-Party-at-USA1

Thursday, November 28, 2013

“ሁከት ፈጠሩ” የተባሉት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ጉዳይ ፍ/ቤት ቀረበ

(አራያ ጌታቸው) ዛሬ ህዳር 18 ቀን 2006 ዓ.ም ከላይ ባለው የክስ መጥሪያ የሰማያዊ ፓርቲ የምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ የሽዋስ አሰፋ እና የሰማያዊ ፓርቲ የምክር ቤት አባል አቶ ስሜነህ ጸሀይ አዲስ አበባ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ወንጀል ችሎት ቀርበው፤ አቃቤ ህግ ወንጀሉን ከዘረዘሩ በኋላ ፍርድ ቤቱም ጥፋተኝነታቸውን ያምኑ ወይም ይቃወሙ እንደሆነ ጠይቆ ተከሳሾቹም ምንም አይነት ጥፋት እንዳለጠፉ ገልጸዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ የምስክሮችን ቃል ለመስማት ለህዳር 26 ቀን 2006 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቶ አሰናብቷቸዋል፡፡
የክሱን ዝርዝር እንዲያነቡት ከዚህ ዜና ጋር አቅርበነዋል።                                                 ምንጭ የኢትዮጵያ ሜዲያ መድረክ

Sunday, November 24, 2013

“እኔ ራሴ ስድስት ያበዱ ሴቶችን ይዤ መጥቻለሁ..” ራውዳ ጀማል – ከሳዑዲ ተመላሽ ኢትዮጵያዊት (ቃለ ምልልስ)

በሃገር ቤት እየታተመ የሚወጣው አዲስ አድማስ ጋዜጣ ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሃገራቸው ከተመለሱ ኢትዮጵያውያን ጋር ቃለ ምልልስ አድርጓል። ቃለ ምልልሱ ዘ-ሐበሻ ከዚህ ቀደም ትዘግባቸው የነበሩ የሳዑዲ ሕይወቶችን የሚያጠናክሩ በመሆናቸው ጋዜጠኛ አበባየሁ ገበያው ያደረገችውን ቃለምልልስ ለአንባቢዎቻችን እንደወረደ ይኸው፦
ራውዳ ጀማል ትባላለች፡፡ የሃያ ዓመት ወጣት ናት፡፡ ስለራስዋም ሆነ በሳኡዲ ስላሉ ኢትዮጵያውያን ወቅታዊ ሁኔታ ስታወራ እያለቀሰችና እየተወራጨች ነው፡፡ ለማነጋገር ስቀርባት “ወንድ ከሆናችሁ ጋዜጠኞች ነን፣ የህዝብ አፍ ነን ካላችሁ፤ እዚህ ተቀምጣችሁ፣ “ሁለት ሰው ሞተ” እያላችሁ ከምታቅራሩ ሳኡዲ ሂዱና በየቀኑ ሁለት ሶስት ሰው የሚሞትበትን እልቂት ተመልከቱ፣ “ሰዎቹን ምን እየሰራችሁ ነው?” ብላችሁም ጠይቁልን” አለችኝ። መቅረፀ ድምፄን ሶስት አራት ጊዜ ያስጠፋችኝ ቢሆንም በመጨረሻ ግን ለቃለ ምልልስ ፈቃደኛ ሆነችልኝ፡፡

ስንት ዓመት ቆይተሽ መምጣትሽ ነው?
ከሁለት ዓመት በኋላ ነው የመጣሁት፡፡ እስከ አስረኛ ክፍል የተማርኩት አዲስ አበባ ቢሆንም፤ የኮምቦልቻ ልጅ ነኝ፡፡
እንዴት ነበር የሄድሽው?
በፓስፖርት… በኮንትራት ነበር የሄድኩት … ካላስ! የሰውየው ልጆች ግን “የማይሆን” ፊልም ተመልከቺ እያሉ ያስቸግሩኝ ነበር፡፡ ሲመረኝ ጠፍቼ ወጣሁ፡፡ ከዚያም ከጓደኞቼ ጋር በነፃነት ቤት ተከራይተን እየኖርን፣ በ1800 ሪያል ተቀጥሬ መስራት ጀመርኩኝ፡፡ ቤተሰቤንም ገንዘብ እየላኩ እረዳ ነበር፡፡
ወደ አገርሽ እንዴት ተመለስሽ?
ውጡ ሲባል… ረብሻ ሲነሳ.. ጓደኞቻችን ሲሞቱ.. ሲደፈሩብን.. ‘ድሮም ስደተኛ ክብር የለውም’ ብዬ ተመልሼ መጣሁ..ከሚገሉኝ ከሚያበለሻሹኝ ብዬ እጄን ሰጠሁ፡፡ ብዙ ኢትዮጵውያኖች ችግር ላይ ናቸው.. እባካችሁ ድረሱላቸው፡፡ ብርዱም ፀሃዩም ሲፈራረቅባቸው.. ያሳዝናሉ፡፡ ብዙ ያልመጡ አሉ፤ መምጣት እየፈለጉ፡፡ ስቃይ ላይ ናቸው፡፡ እኔ አሁን አስራ ሶስት ቀን ታስሬ ነው የመጣሁት፡፡ እስቲ ስለ እስሩ ንገሪኝ … ሁለት ቀን ያለ ምግብ ያለ ውሃ ነው የታሰርነው። ከዛ በኋላ ግን ጥሩ ምግብ ሰጥተውናል፣ ጥሩ መኝታም አግኝተናል፡፡ ብዙዎቹ ግን ከእኛ የባሰ ችግር ላይ ናቸው፡፡ መጠለያ ያላገኙ አሉ… ኤምባሲያችንም አይሰማም እንጂ ስንት ጊዜ ደውለን ተናግረናል መሰለሽ፡፡ ግን የሚሰማ የለም፡፡ ከአገራችን ውጡ ካሉ በኋላ ትዕግስት ያጡና መልሰው ይዩዙናል፡፡ በዛን ጊዜ አበሻው፣ ሻንዛ/ጩቤ ይመዛል፡፡ ፖሊስ ራሱን ለማዳን ይተኩሳል። እኔ እንደውም ደህና ነኝ፤ እዛ ላሉት ድረሱላቸው። በምድረ ዱርዬ እየተደፈሩ ነው ያሉት /ለቅሶ/ ስንት ህፃናት አሉ የሚሞቱ፣ የሚታመሙ፡፡ ስንመጣ ደሞ፤ ሻንጣ አትያዙ ተብለን ተመናጭቀን…በጥፊ ተመትተን..መከራችንን በልተናል፡፡
ወንዶችና ሴቶች ለብቻ ነበር የተቀመጣችሁት?
የተቀመጣችሁት አትበይ! የታሰራችሁት በይ፡፡ … የሴት እስር ቤት ለብቻው ነው በሴቶችና በህፃናት ለቅሶ የተሞላ ነው፡፡ እኔ ራሴ ስድስት ያበዱ ሴቶችን ይዤ መጥቻለሁ…/ለቅሶ/
አሁን ቤተሰብ እየጠበቅሽ ነው?
ነበረ ግን ሻንጣዬ ጠፋብኝ፡፡ በርግጥ ጤነኛ ሆኖ መምጣትም ቀላል አይደለም፡፡ እዛ ያሉትን ጥለናቸው ስንመጣ እያለቀስን ነው፡፡ እስር ቤቱ ውስጥ አንድ እርጉዝ ሞታብናለች፡፡ እዛው እስር ቤት እያለን ምጥዋ መጣ፤ ግን የህክምና እርዳታ ባለማግኘትዋ ሞተች፡፡
እስር ቤት ያሉት ምን ያህል ይሆናሉ?
ሰማኒያ ክፍል አለ..በየክፍሉ ስልሳ አምስት ስልሳ አምስት ሰው ነው ያለው፡፡ መካሲመሺ እስር ቤት ይባላል፡፡ የወንድና የሴት እስር ቤት የተራራቀ ነው፡፡ በጣም ረጅም ከመሆኑ የተነሳ በመኪና እንጂ በእግር አይሞከርም፡፡ በአሁኑ ሰዓት በከተማው ያለው እስር ቤት ሞልቶ የመዝናኛና የስብሰባ አዳራሹን ሁሉ እስር
ቤት አድርገውታል፡፡ የተደፈሩት የሞቱት..ሴቶች ብዙ ናቸው፡፡ አንዷን እርጉዝ ለሶስት ሲደፍሯት ሞታለች፡፡
የሌሎች አገር ስደተኞችም እየወጡ ነው ተብሏል…
አዎ፡፡ ኢትዮጵያዊው ከበደሉ ብዛት የተነሳ እየተናነቀው እኮ ነው ግጭቱ የሚከረው፡፡
ሚስቱን እህቱን ከእጁ መንትፈው ሊወስዱበት ሲሉ ነው ጦርነት የሚነሳው፡፡ አበሻ ወንድ እየሞተ ያለው ‹‹ሴቶቻችንን አትንኩብን..›› ስለሚል እኮ ነው፡፡ ኤምባሲው ሊደርስላቸው ይገባል፡፡
ምንጭ ዘ-ሐበሻ

Saturday, November 23, 2013

ኦባንግ – ከዓለምአቀፍ ተቋማት ጋር እየሠራሁ ነው አሉ የሳዑዲ ልዑል አንጋቾቻቸውን አወደሱ

November 22, 2013 09:19 pm By 
በሳዑዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውንና እየደረሰ ያለውን ፈር የለቀቀ አስነዋሪ ግፍ ዓለምአቀፍ ይዘት እንዲኖረው ለማድረግ ከሰብዓዊ መብት ተሟጋች እና ሌሎች ዓለምአቀፋዊ ድርጅቶች ጋር እየሠሩ መሆናቸውን አቶ ኦባንግ ሜቶ በተለይ ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ተናገሩ፡፡ የሳዑዲ ልዑል ሰብዓዊነት የረገፈበትንና በግፍ የተሞላ የወሮበላ ተግባር የሚፈጸምበትን አሰቃቂ ተግባር የሚከናውኑትን አንጋቾች አሞካሹ፡፡
ያለ አንዳች ልዩነት ኢትዮጵያውያን በኅብረት ድምጻቸውን በማሰማት እየተቃወሙት ያለውን ኢሰብዓዊ ተግባር አስመልክቶ በተለያዩ መንገዶች ይፋ ከሆኑት በተጨማሪ ድብቅ መረጃዎች እየተሰበሰቡ መሆናቸውን ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር አስታውቀዋል፡፡ ዳይሬክተሩ አቶ ኦባንግ ሜቶ የጋራ ንቅናቄው ከዓለምአቀፍ የመብት ተቋማት ጋር በቅርበት እየተሰራ ስላለው ዝርዝር ጉዳይ ግን ከሁኔታው ምስጢራዊነት አኳያ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡
“አልዘገዩም” በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱም “አኢጋን ችግር በተከሰተ ቁጥር የሚቋቋምና የሚፈርስ የዕቁብ ይዘት ያለው ድርጅት አይደለም፡፡ ወይም እሣት ሲነሳ ድምጽ እያሰማ እንደሚከንፍ የእሣት አደጋ መኪና የሚመሰል ድርጅት አይደለም” በማለት የጋራ ንቅናቄውን የተጠና አካሄድ በመጠቆም የመለሱት አቶ ኦባንግ ይህ ችግር እንደሚከሰት አስቀድሞ ማስጠንቀቂያ መስጠታቸውን ተናግረዋል፡፡
ችግሩ አስቀድሞ እንደሚከሰት ቢታወቅም ምላሽ የሚሰጥ ብቃት ያለው አካል ባለመኖሩ አንገት የሚያስደፋና ኃፍረት የሚላብስ፤ “አገር አለኝ ወይ?” የሚል ጥያቄ የሚያስነሳ በኢትዮጵያ ታሪክ ተሰምቶና ታይቶ የማይታወቅ ኃፍረት ሊደርስብን ችሏል፡፡ “ይሁን እንጂ” አሉ ኦባንግ “ይህ መራር ዜና ከተሰማበት ሰዓት ጀምሮ የጋራ ንቅናቄው የበኩሉን” ሲያደርግ መቆየቱን አመልክተዋል፡፡
“ከተለያዩ ዓለምአቀፋዊ ተቋማት፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች፣ አግባብ ካላቸው መንግሥታዊ አካላትና በተለያየ ደረጃ ላይ ከሚገኙ የሳዑዲ ባለስልጣናት ጋር ተነጋግረናል” በማለት አቶ ኦባንግ ተናግረዋል፡፡ ለዓብነት ያህልም የሳዑዲ ም/ጠ/ሚ/ር እና የመከላከያ ሚ/ር፣ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር፣ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚ/ር፣ የፍትሕ ሚ/ር እና ሌሎች ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸውን የመንግሥት መ/ቤቶችን ጨምሮ በአውሮጳና በሰሜን አሜሪካ የሚገኙትን የሳዑዲ ኤምባሲዎችን እንዲሁም የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽነርን፣ የአፍሪካ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ACHPR)፣ ወዘተ ማነጋገራቸውንና በየደረጃውም ምላሽ ማግኘታቸውን አመልክተዋል፡፡
በመላው የመካከለኛው ምስራቅ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ ዕረፍት የሚሰጥ እንዳልሆነ የጠቆሙት “ጥቁሩ ሰው” ሳዑዲ ካላትና ከምትከተለው “የበርህን ዝጋ ፖሊሲ” አንጻር በአካል በቦታው ላይ ከመገኘት ይልቅ አቅም ካላቸው ዓለምአቀፋዊ አካላት ጋር በአፋጣኝና በቅርበት መሥራቱ ድርጅታቸው የወሰደው አማራጭ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ የሎጂስቲክሱ ጉዳይ መስመር ሲይዝም የጋራ ንቅናቄው ከዚህ በፊት በየአገራቱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ጉዳይ ሲያስፈጽምበት የነበረውንና በውጤታማነቱ የሚታወቀውን አማራጭ እንደሚተገብር ጨምረው ገልጸዋል፡፡
ኢህአዴግ አገርን እንደሚያስተዳድር ድርጅት በዜጎቹ ላይ እየደረሰ ያለውን አስነዋሪ ተግባር ትኩረት ሰጥቶ አለመመከቱ ተቃውሞ አስነስቷል፡፡ ይህንኑ አስመልክቶ አቶ ኦባንግ ሜቶ “ወገኖቻችንን ድንበር በማሻገርና ኤጀንሲ ከፍተው ወደ አረብ አገራት ሲልኩ የነበሩት ሁሉ ሕግ ፊት ቀርበው ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ የተለያዩ ተግባራት” እየተከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
alamudi-ሼክ መሐመድ አላሙዲ የሠራተኛ ኃይል ወደ ሳዑዲ እንዲላክ ከኢህአዴግ ጋር በይፋ ስምምነት ማድረጋቸው የሚታወስ ነው፡፡ ኢንቨስትመንትን በተመለከተ ከሚፈልጉበት ክልል መሬት ለመውሰድ፣ ከሚፈልጉበት ባንክ ኮሪደር ገንዘብ ለመበደር ገደብ የሌላቸውና በሞቀበት ሁሉ ባለመጥፋት በጀት መድበው በሚያስተዳድሯቸው ሚዲያዎች እንዲሁም አንደበታቸውን በሙስና ላሰሯቸው ባለሥልጣናት “ኢትዮጵያዊ ነኝ” እያሉ በተገኙበት ቦታ ሁሉ ለሚዲያ ፍጆታ የሚደሰኩሩትና ግጥም የሚያስደረድሩት ሼክ መሐመድ አላሙዲ፣ “ወገኔ” የሚሉት ሕዝብ በአባታቸው አገር ወሮበሎች ሲያልቅና ሲጨፈጨፍ ዝም ማለታቸው ኢንቨስትመንቶቻቸውን ጥያቄ ውስጥ ከትቷል፡፡
አንዳንዶች እንደሚሉት ይህ አሰቃቂ ድርጊት መስመር ለቅቆ ከመውጣቱ በፊት የሳዑዲ አረቢያ ዜጎችን ከርስ እንዲሞላ በኢትዮጵያ የተቋቋመው ሳዑዲ ስታር ኩባንያ በገንዘብ እጥረት ሊዘጋ እንደሚችል መዘገቡ የሚታወስ ነው፡፡ በወቅቱ ሪፖርተር ባወጣው ዘገባ ሳዑዲ ስታር በኪሣራ ወደ መዘጋት መድረሱ የኩባንያው “ባለቤት የሆኑትን ሼክ ሙሐመድ አል አሙዲንና የሳዑዲ ዓረቢያን ስም የሚያጎድፍ ከመሆኑም ባሻገር፣ ኢትዮጵያ ውስጥ እስኪታክት የተወራለት ይህ ፕሮጀክት መና መቅረቱ ሁለቱን አካላት በሕዝቡ ዘንድ ለከፍተኛ ትችትና ወቀሳ እንደሚያጋልጣቸውም” ጠቁሞ ነበር፡፡
mohammed bin nayef
ልዑል ሞሐመድ ቢን ናይፍ
በአሁኑ ጊዜ “ሕገወጥ ናችሁ” በሚል ሰብዓዊነት የጎደው እርምጃ እየተወሰደባቸው ያለው የበርካታ አገራት ዜጎች በተለይም ኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈጸመውን ሰቅጣጭ ተግባር ሕገወጦችን የማባረር “ዘመቻ” በማለት ያቃለሉት የሳዑዲው አገር ውስጥ ሚ/ር ልዑል ሞሐመድ ቢን ናይፍ ወንጀለኛ ሬንጀር ለባሾችን፣ ፖሊሶችንና ወሮበሎቹን ሸባቦች አደፋፍረዋል፡፡ “ዘመቻው ይቀጥላል … በተወሰነ ጊዜ የተገደበ አይደለም” በማለት “እስክንጨርስ እንጨርሳችኋለን” የሚመስል የማፊያ መሪ መሰል መልዕክት ለአንጋቾቻቸው አስተላልፈዋል፡፡
አብዛኛዎቹ ኢትዮጵያውያን በሕጋዊነት የሚኖሩትም ጭምር በሳዑዲ ያለው ሁኔታ አሳሳቢነት ወደፊት ችግር ውስጥ ሊከትታቸው እንደሚችል በመገመት ወደ አገራቸው መመለስ ይፈልጋሉ፡፡ በአሁኑ ወቅት ለከፍተኛ ሰቆቃ የተጋለጡት ኢትዮጵያውያን “ቤት አለን ቤታችን መልሱ” እያሉ የሰቆቃና የድረሱልን ጥሪ በሚያስተላልፉበት ወቅት ሰብዓዊነት የጎደላቸው የኢህአዴግ መሪዎች ይህ ነው የሚባል አፋጣኝ ምላሽ መስጠት አለመቻላቸው “በእርግጥ ኢትዮጵያውያን አገር አላቸው?” ብሎ የሚያስጠይቅ እንደሆነ በርካታዎች የሚጋሩት ነው፡፡
አቶ ኦባንግ በበኩላቸውም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለአንድ ሳምንት ሥራውን አቋርጦ እንኳን ቢሆን ስደተኞቹን ባፋጣኝ የማመላለስ ተግባር መፈጸም ይገባው ነበር በማለት ቁጭታቸውን ተናግረዋል፡፡ ዜጎች በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ህይወታቸው እየተቀጠፈ “3ሺህ ዛሬ ገቡ … ድምሩ 10ሺህ ሆኗል …” የሚል የሞላ ጎደለ ቁማር ዓይነት ጨዋታ በትዊተር መጫወት የቴድሮስ አድሃኖምን ዘመነኛነት ሳይሆን ለሰውልጅ ህይወት ያላቸውን ደንታቢስነት የሚያሳይ መሆኑን ሁኔታው ያስቆጣቸው አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ አቶ ኦባንግም “ቤቴ መልሱኝ” ብሎ ለሚለምን አንድ ዜጋ የተከፈለው ተከፍሎ ትራንፖርት በማቅረብ ክቡር ህይወትን በአስቸኳይ ለመታደግ አለመቻል ለትውልድ የሚተላለፍ የታሪክ ጠባሳ መሆኑን በአጽዕኖት ተናግረዋል፡፡
source http://www.goolgule.com

Tuesday, November 19, 2013

የሳዑዲ ጉዳይ፡ ካስጨነቀ፣ ካስጠበበን የመንፉሃ ሁከት መልስ! – ነብዩ ሲራክ ከሳዑዲ (ጋዜጠኛ)

    ትናንት እንደ ቀልድ  …      የማለዳ ወግ
        በያዝነው የፈረንጆች 2013 ዓም በወርሃ መጋቢት አጋማሽ የሳውዲ አረቢያ መንግስት ” ህጋዊ ሰነድ ያልያዙትን አስወጣለሁ !” ብላ አወጀች ። ቀጠለና አፈሳ አሰሳው ተከተለ! አስፈሪው ያ ክፉ የጭንቅ ቀን በሳውዲው ንጉስ ሌላ የምህረት አዋጅ ተተክቶ ህገ ወጥ  የተባሉትን ህጋዊ በሚያደርግ ህግ ተተካና የምህረቱ አዋጅ በያዝነው ህዳር መባቻ እንደሚያልቅ በተጠቆመው አዲስ የምህረት አዋጅ ተተካ ! በሂደቱ የታደሉት የተበላሸ መኖሪያ ፍቃድን ከማደስ ጀምሮ አዲስ ፈቃድን አገኙ ። ያላለላቸው ከፖስፖር እድሳት መዘግየት ጀምሮ አዲስ ለማውጣት ባለው ውስብስብ የኢንባሲና የቆንስል አሰራሮች ህልማቸው ሳይሰምር እዚህ ደረሱ …ወደ ሃገር ለመግባት ፈልገው ከሃገራቸው ተወካዮች ህጋዊ ሰነድ ለማግኘት ሳይችሉ ቀሩና ተሰነካክለው ቀሩ  !  በላይ በታች ብለው የመውጫ ሰነዱን ያገኙት ጥቂቶች በሰላም ወደ ሃገራቸው በሰላም ሲሸኙ የቀሩት ብዙዎች ደግሞ ሳውዲዎች እንደለመዱት ይለሳለሳሉ ብለው ከፉውን ጥቂት ቀን እቤታቸው መሽገው ሊያሳልፉ ተዘናጉ …
    አደጋውን በቅርብ የሚያዩት የመንግስታችን ተወካዮች ዜጎቻቸውን ሰብስበው መምከር ሳይችሉ ቀሩ! እንዲህ እያለ ቀን ቀንን ወልዶት የምህረቱ አዋጁ ህዳር ላይ ባባተ ማግስት ግን ዜጎች አደጋ ላይ ወደቁ … ይህ በሁሉም ሃገር ዜጎች የመጣ ነበርና በጸጋ መቀበል የግድ ነበር ። ፍተሻ አሰሳው በመላ ሳውዲ ተጠናክሮ ሲቀጥል ቤት ” ለበቤት ፍተሻ አይደረግም !” የሚል መመሪያ ወጣ ። ይህ መመሪያ ብዙዎችን አስደሰተ! ሪያድ መንፉሃ ላይ ግን መመሪያው በእኛ ዜጎች ላይ ብቻ ተጣሰ  … ህጋዊ የመንፉሃ ነዋሪዎች ሳይቀር የጥቃቱ ዳፋ ቀማሽ ሆኑ ። መንፉሃ ተሸበረች ! የሃበሻ ልጅ ቤቱ እየተሰበረ ያለ ገላጋይ በወሮበላ አረብ ወጣቶች ተቀጠቀጠ  ፣ ንብረቱ ተዘረፈ ፣ ተደፈረ ! የጸጥታ ሃይሎች ቤት እየሰበሩ በመፈተሽ ወንዶችን ወደ እስር ቤት እየተለዩ ሲልኩ “ጅብ በቀደደው ውሻ …!”  እንዲሉ በፈታሾች እግር”ሸባብ ” የሚባሉት ወጣት አረቦች ንብረት ከመዝረፍ ጀምሮ አቅመ ደካማ ሴት እህቶችን አጠቁ!  ቁጣ ተቀሰቀሰ!
       ይህን ግፍ  የተመለከቱ ደራሽ ገልጋይ አጥተው ተስፋ የቆረጡት ወጣት ኢትዮጵያውን ወንድሞች በአካባቢው ሳውዲዎች ዝር እንዳይሉ በማድረግ መኪናዎችን መሰባበር ያዙ! ሁከቱ ግሞ የበቀል እርምጃው በነጭ ላባሾች ተካሄደ! ጥቃቱን የአካባቢውን ነዋሪ እርምጃ ያስከፋው ነዋሪ ሻንጣውንና ቤተሰቦቹን ይዞ አደባበይ በመውጣት “ሴቶቻችን አይደፈሩ ፣ ከነቤተሰቦቻችን ወደ ሃገራችን መልሱን! ” የሚል ድምጹን በአደባባይ ሲያሰማ ከጸጥታ አስከባሪዎች ጋር ወደ አላስፈላጊ ግጭት አመሩ ! ተነግሯቸው መስማት ያልቻሉት የመንግስት ተወካዮች ጣልቃ ገብተው መብት ማስከበሩ ቢቀር  መሸምገል ሳይችሉ ቀረና የተፈራው ደረሰ  !
ዛሬ …በተስፋ 
ዛሬ ሌላ ቀን ነው! መንፉሃ ላይ ቁጥሩ በውል ያልታወቀ የወገን ደም ተገብሮ የሳውዲ መንግስት ህገ ወጥ ባላቸው ዜጎች ላይ የጣለው የመቶ ሽህ ብር ቅጣትና የሁለት አመት እስራት ተነሳ  ! እስካሁን ባለው መረጃ 50 ሺህ የሚገመት ወገን ወደ ሃገሩ ለመግባት በማቆያ እስር ቤት እና በመጠለያ ከትሟል! የእኛ ነገር “ሰርገኛ መጠሰ በርበሬ ቀንጥሱ !” ሆነና  የመንግስት ተወካዮች በስደተኛው መብት መከበር የማይተጉ ሃላፊዎችን በቅርብ መልምሎ እርምጃ በመውሰድ የስደተኛውን ህይወት ያልደገፈው መንግስታችን ዜጎች በከፋ ችግር ማጥ ስንወድቅ አለሁላችሁ እያለን ነው ። ” የምትኮሩበት ሃገር አላችሁ!  ኑ በእቅፍ እንቀበላችኋለን! ” ማለትም ጀምሯል!  አዎ!  ደስ ይላል!

ዛሬ የሰሞኑ ሮሮ በረድ ብሎ ብሏል! በውጭ ሃገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያንም የሳውዲ መንግስት በወገኖቻቸው የደረሰውን አሰቃቂ በደል ተመልክቷልና ሰብአዊ መብት ረገጣውን ከማውገዝ ባለፈ እርዳታ እያሰባሰቡ መሆኑን መስማት ያሰደስታል!  ለዚህ መሰሉ አለም አቀፍ እንቅስቃሴ  ታላቅ አክብሮት አለኝ !  በሳውዲ የከተምን ከአራት መቶ ሺህ በላይ የምንገመት የዚያች ሃገር ዜጎች አለንና ተቃውሞው በቀልን እንዳያጭር ያሳስበናል ።
ሳውዲና የእኛ ስደት   …
     ሰማችን ማንቴስ ብለንና እድሜያችን ቆልለን ከደላንና ከቀናን በጠያራ ፣ አልሆን አልመች ሲል የባህር የበርሃውን ሰቆቃ ተፋጥጠን እዚህ ለደረስነው ኢትዮጵያውያን ሳውዲ አረቢያ ባለውለታችን ናት !  በአብዛኛው በሳውዲ አሰሪዎችና በአንዳንድ የመንግስት ተቋማት ሰራተኞች የሚደርስብንን የመብት ጥሰት ችለን ላለፍን ሰላማዊ ነዋሪዎች “በሰብአዊ መብት ጥሰት የምትወነጀለው አረባዊቷ ሀገር ከሀገራችን የተሻለች ናት! ” እስከ ማለት መድረሳችን እውነት ነው ። ስለ እውነት እንነጋገር ከተባለና የሰብአዊ መብቱን ነገር ችላ ብለን ራስን መደገፉ ካመራን ሳውዲ አረቢያ  ራሳችን ጠቅመን ቤተሰቦቻችን መጥቀም የቻልንባት ሁለተኛ ሃገራችንናት ብል ማጋነን አይቦንም ። ይሁንና ይህች የምናመሰግናት ሃገር አልፎ አልፎ  ከምታወጣው ህግ ጋር በተገናኘ  የእኛን መብት የሚያስከብርልን ጠንካራ ተወካይ  አጥተን ህግ እየተጣሰ ተጎድተናል። ይህ ብቻ አይደለም በግርድፉ እናውራው ካልን ህግና ስርአትን ተከትለው የማይኖሩ ወገኖች በሚሰሩት ህገነወጥ ስራ በሚሰጠን ስም ገጽታችን ከመጉደፉ አልፎ ተርፎን “ለሃጥአን የመጣው ለጻድቃን !” እንደሚባለው  የሃጥአኑ ጥቃት ለቀረው ሰላማዊ ነዋሪ ሲተርፈው የመንግስት ተወካዮቻችን ዋቢ አልቆምልን እያሉ ኑሯችን ከፍቷል ። ካለን የገቢ ምንጭ አንጻር አኗኗራችን በህብረት መሆኑም ጎድቶናል። ይህ ከጥቂቱ ጉዳት መካካል ጥቂቱ ቢሆንም ኑሯችን ካከፋው ምክንያትነት ቀዳሚ ለመሆኑ ጥርጥር የለኝም!  ከዚህ አንጻር በሰሞኑ አሰሳና ፍተሻ በላቡ ከሚያድረው ጎልማሳ እና ጉብሏ ጀምሮ አባወራው ሆነ የቤት እመቤቷ ህገ ወጥ ተብለን እንደወጣን ልንቀር የምንችልበት አደጋ ተደቅኖብናል። ዜጎች በከባድ ውጣ ወረድ ለአመታት ያፈራነው  ሀብት ቀርቶ የአብራክ ከፋይ ልጆች ቤተሰቦቻቸውን ሳይሰናበቱ ከሀገር ለሚባረሩበት አካሄድ በምክክር መላ ካልተበጀለት  አሰፈሪና አስደንጋጭ ነው !
የወገን ቁጭትና ቁጣ እና ቁጣው የደረሰው የሳውዲ መንግስት …
    በመንፉሃን የተፈጸመብንን ቅጥ ያጣ ጥቃት ተከትሎ ግፍ በደል መከራውን በዘመንኛው የመረጃ መረብ ሲናኝ ሃዘናችን የተጋራው ከሃገር ቤት ጀምሮ በመላ አለም ከጫፍ እስከ ጫፍ በቁጣ የተነሳው የኢትዮጵያን ቁጣ መልዕክት ለሳውዲዎች ደርሷቸዋል። ወደ ቀጠለው አለም አቀፍ  ከጅምሩ ሳውዲን ከአልቃኢዳ ጋር በመወንጀል የተጀመረው አስፈሪ የነበረ ቢሆንም  በቀጣይ ሰልፎች ጥያቄው ሰብአዊ መብትን አክብሩ በሚል መሻሻሉ ለሳውዲ ንጉሳዊ ቤተሰቦች እያስተላለፈ ያለው መልዕክት ቀላል አይደለም ባይ ነኝ ።  በዋሽንግተኑ የመጀመሪያ ተቃውሞ የተሰማው ሳውዲን ከአልቃኢዳ ጋር አጎዳኝቶ የመወንጅል እና ከበቂ ማነስ የተነሳ የብዙሃን ሙስሊማንን መመሪያ የቁርአን መልዕክት በነጭ ቀለም የተጻፈበትን ደማቅ አረንጓው የሳውዲ አረቢያ ባንዴራን ወደ ማንቋሸሽ  እንዳያመረ የነበረን ስጋት መወገዱ ያስደስታል ። ይህም ብዙ የሳውዲ ነዋሪዎችን አስደስቶናል!
ለተፈጸመው ግፍ ማካካሻ ባይሆንም በመጠለያዎች የምንሰማው የሰቆቃ ጩኸት ረገብ ብሏል። የሳውዲ መንግስት በመጠለያ ያሉትን ዜጎች መጠለያ ሲታይ የሰነበተውን የምግብ ፣ የውሃ እና የህክምና አቅርቦት እያስተካከለው መገኘቱን ከመጠለያው ከሚገኙ ግፉአን ማረጋገጥ ችያለሁ ። በቀን አንድ ሚሊዮን ብር የሚደርስ ወጭን የሳውዲ መንግስት ፣ ከማውጣት ጀምሮ ወደ ሃገር ቤት መግባት የሚፈልጉ ኢትዮጵያውንን ለማሰባሰብ 300 ያህል አውቶቡሶች በሪያድ በመካ ተመድበው የማጓጓዙን ሂደት ከጀመሩ ቀናት ተቆጥረዋል።  ወጭውን ይሸፍነዋል ተብሎ ከተነገረኝ ከኢትዮጵያ አየር መንገዳችን ወደ ሃገር ቤት የማጓጓዙ ዘመቻ ጎን ለጎን የሳውዲ መንግስት በሳውዲ አየር መንገድ በኩል ነጻ የማጓጓዝ ስራ  በመካሄድ ላይ መሆኑን መረጃዎች ደርሰውኛል ።
መልካሙ ጅምር ፣ ሰው ሃይልና የመረጃው እጥረት…

       ከላይ ለመጠቆም እንደሞከርኩት በሪያድና በመካ ስደተኛን የመቀበሉ ስራ እየተሰራ ቢሆንም በማቆያው ባለው የስደተኛ ብዛት አንጻር በጅዳ ወደ ሃገር መግባት የሚፈልጉትን  ወደ ማረፊያ የማጓጓዙም ሆነ ባሉበት የመመዝገቡ እንቅቃሴ በጅዳ ገና አልተጀመረም ። በጅዳ የሽሜሲማረፊያ እስር ቤትና በሪያድ መጠለያ ያለውን ምዝገባ እና የመጓጓዣ ሰነድ አቅርቦት ለማሳለጥ የኢትዮጵያ መንግስት ልዑክ እና ድጋፍ የሚሰጡ ሃላፊዎችን አሰማርቶ ስራው እየተሰራ ቢሆንም ከፍተኛ ቁጥር ላለው ዜጋ ግልጋሎት ለመስጠት የሰው ሃይል እጥረት መስተዋሉ አልቀረም። ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነን በቅርቡ ለቀናት ዝግ የነበረውን የጅዳ ቆንስል አመዘጋት መጥቀስ ይቻላል። ምንም እንኳን ቆንስል መስሪያ ቤቱ ስራውን ለቀናት የዘጋበትን ምክንያት በግልጽ ባወጣው ማስታወቂያ አልተገለጸም ። ምክንያቱ ባልተገለጸው የጅዳ ቆንስል መዘጋት ብዙዎችን አስቆጥቷል ” የታመመ ቢሞት እንዴት እንቅበር? ፖስፖር ለማሳደስ ፣ የታደስ ለመቀበል ፣ ሰነድ ማስተካከል ቢያስፈልግ ፣ የጋብቻ ወረቀት ማረጋገጫና እና ተመሳሳይ ግልጋሎት ስንፈልግ የት እንሂድ? ” ሲሉ በማጠየቅ በአስቸኳይ ቆንስሉ እንዲከፈት ነዋሪዎች መንግስትን ተማጽነዋል። የቆንስሉን መዘጋት ምክንያት ሃላፊዎችን ጠይቀን መላሽ ብናጣም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩም ቴዎድሮስ አድሃኖም “የጅዳ ቆንስል አገልግሎት እንዳይሰጥ የተዘጋው የቆንስላው ሰራተኞች ስደተኞቹን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ እንዲያግዙ ስለተፈለገ ነው ” ብለው በትዊተር መረጃ አቀብለውናል። ይህ የሚያሳየው የሰው ሃይል እና የመረጃ ልውውጥ እጥረት መሆኑን ለመረዳት መማር መመራመርን አይጠይቅም። ይህ እውነታ ፈጦ እያለ የጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች ግልጋሎት ለመስጠት ፈቃደኛ የሆኑትን የኮሚኒቱ መስሪያ ቤትና ችግሩ ችግራችን ነው በሚል መክረውና ዘክረው አቤቱታ ያቀረቡ ወገኖችን ለመቀበል አልደፈሩም። ምክንያቱን የሚያውቁት ሃላፊው ቢሆኑም ሲሆን ነዋሪውን አስቸኳይ ሰብሰባ ጠርተው ፣ ያ ቢገድ የድጋፍ ጥያቄውን በበጎ ተመልክተው አፋጣኝ እርምጃ መውሰድ አለመቻላቸው ሂደቱን ከመሳለጥ እንዳይገታው ስጋት አለ። ሌላው በሪያድና በጅዳ ሃላፊዎች ዙሪያ የሚታየው የመረጃ ክፍተት የግልጋሎት አሰጣጡን አልፎ አልፎ የሚስተዋለውን የመብት ገሰሳ ከቁጥጥር ውጭ እንዳያወጣው ትኩረት ሊሰጠው ይገባል። ለዚህም በሪያድ መንፉሃና በተለያዩ አካባቢዎች ፣ በጅዳና በመካ “ወደ ሃገራችን ውሰዱን ?” በሚሉ ዜጎች እና በመንግስት ጸጥታ አስከባሪዎች መካከል የሚፈጠሩ  ፍጥጫና ግጭቶችን በመንፉሃ የታየውን አደጋ እንዳይደግመው ለመከላከል ይረዳል። በመንፉሃ ባየነው የተንቀሳቃሽ ምስል ባየነው ድብደባና ውክቢያ አድራሻቸው የጠፋ ወገኖች በፖሊስ ጣቢያዎች፣ በሆስፒታልና በመጠለያው ፈልገው ያጧቸውን ወገኖቻቸውን በሚመለከት መረጃ ለመስጠት ፈልገው ወደ መንግስት ሃላፊዎች ቢደውሉም ምላሽ  እንዳላገኙ በምሬት የገለጹልኝ በርካታ ናቸው ። በውክበቱ ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች የትየለሌ የመሆናቸውን ያህል የደረሱበት የማይታወቅ ዜጉች ጉዳይ ከሚሰራው የማጓጓዝ ስራ በተጓዳኝ በመረጃ ልውውጥ ተደግፎ መሰራት ያለበት ስራ ነው ። ይህንና ይህን መሰል ጉዳዮችን ስንመለከት በመንግስት ሃላፊዎች የመረጃ ተቀባይ አለመኖር ነገ  ቢያንስ ለህሊናችን ተወቃሽ እንዳያደርገን ዛሬ መሰራት ያለበት ስራ ነው ባይ ነኝ።  ከዚህ አንጻር መረጃ ትልቅ አስተዋጽጾ እንዳለው በቦታው የሚገኙ የመንግስት ተወካዮች ሊያጤኑት ይገባል። ይህን ክፍተት ለመዝጋትም  የአደጋ ጊዜ ተጠሪና መረጃ ተቀብሎ የሚያጣራ ኮሚቴ በአፋጣኝ ሊቋቋም ይገባል። የኮሚቴው አባላትም ነዋሪውን ሃያ አራት ሰአት ክፍት የሆነ ነዋሪውን የሚያስተናግዱበት ስልክ ሳይውል ሳያድር መሰራት ካለበት ስራ አንዱ መሆኑን ማጤን ብልህነት መሆኑን ጠቁሜ የማለዳ ወጌን ልቋጨው ወደድኩ ..
እስኪ ቸር ያሰማን!
ነቢዩ ሲራክ
source -ze-habesha