Monday, September 19, 2016

ከቀድሞው የኢትዮጵያ የሀገር የመከላከያና የፖሊስ ሠራዊት አርበኞች ማህበር የተላለፈ ወቅታዊ ጥሪ


እኛ የቀድሞው የኢትዮጵያ የሀገር የመከላከያና የፖሊስ ሠራዊት ዓባላት ለአለፉት 25 ዓመታት በውድ የሃገራችን ሕዝብ ላይ በወያኔ ህውሃት መራሹ ቡድን እየተፈፀመ ያለውን ሰቆቃ ከሕዝባችን ጋር እየተመለከትን እስካሁን ዘልቀናል። ይሁን እንጅ የሕዝባችንን ሰቆቃና መከራ፣ ስደትና ዕልቂት ከምንም ባለመቁጠር ይባስ ብለው የሃገሪቷን ልዑላዊነት ለታሪካዊ ጠላቶቻችን አሳልፈው ለመስጠት ሽር ጉድ በማለት ላይ ይገኛሉ።
በኢትዮጵያ የረጅም ታሪክ ውስጥ የሃገሪቷን ዳር ድንበር ለባዕድ አሳልፎ ለመስጠት የተደራደረ መንግስት ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅም ፣ ሃገሩንና ድንበሩን እንዲጠብቅ አደራ የተሰጠውም ወታደርና የፖሊስ ሠራዊት የዚህ እኩይ ተግባር ተባባሪ የሆነበት ዘመን አልታየም።
ከሁሉም በላይ የህውሃት አቀንቃኝ ካድሪዎች በየጊዜው ከሚጎነጉኑት የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ የሃገሪቷን ታላላቅ ብሄረሰቦች እርስ በርስ በማናቆር የጥላቻ ዘር በማህከላቸው በመበተን ስልጣኑን ለማራዘም ሁነኛ መሳሪያ አድርጎት ይገኛል።
ምንጭ ዘ-ሐበሻ