Thursday, July 31, 2014

ሦስት የኢቴቪ ከፍተኛ ኃላፊዎች ከሥራቸው ለቀቁ Thee ETV senior officials resigned

በ ፍሬው አበበ (ሰንደቅ ጋዜጣ)
በርካታ ጋዜጠኞች በለውጡ ደስተኞች ሆነዋል
የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን (የቀድሞው የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት) ሦስት ከፍተኛ ኃላፊዎች በቅርቡ ሥራቸውን በገዛ ፈቃዳቸው ለቀቁ።
የቀድሞ የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የወቅታዊ ጉዳዮች ዳይሬክተር የነበረው ጋዜጠኛ አሸብር ጌትነት፣ የትምህርታዊ ፕሮግራሞች ክፍል ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ የነበረው አቶ ተመስገን ገ/ህይወት፣ የመዝናኛ ምክትል ሥራ አስኪያጅ የነበረው አቶ ፍቅር ይልቃል በወራት ልዩነት ድርጅቱን መልቀቃቸው ታውቋል።
የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ብርሃነ ኪዳነማርያም ከጥር ወር 2006 ዓ.ም ጀምሮ ከዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ከኃላፊነታቸው ተነስተው በኢቴቪ ከተሾሙ በኋላ የድርጅቱን የአሠራር ሥርዓት ለማስተካከል የወሰዱት ጠንካራ እርምጃዎች በኃላፊዎቹ እንዳልተወደደ ምንጮች ተናግረዋል።
በኢቴቪ ከከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር የሚደረጉ የውጪ አገር ጉዞዎች በጥቂት ግለሰቦች ሞኖፖሊ ብቻ ተይዞ የቆየ ሲሆን፤ አዲሱ ዳይሬክተር ይህን አሰራር በመሰረዝ የሚመለከታቸው ሪፖርተሮች በየተራ ተመድበው እንዲሰሩበት ማድረጋቸው፣ አንዳንድ ኃላፊዎች የጥቅም ግጭት በሚያስከትል መልኩ ኢቴቪ ውስጥ እየሰሩ በግል ድርጅታቸው አማካይነት ሥራዎችን ለመወዳደር ማመልከታቸውና ይህም ተቀባይነት ማጣቱ፣ እንዲሁም ለሙስናና ብልሹ አሰራር ክፍት የነበሩ አሰራሮች እየተዘጉ መምጣታቸው ኃላፊዎቹን ሳያበሳጭ እንዳልቀረ ምንጮቹ ጠቁመዋል።
አንድ የድርጅቱ ባልደረባ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደተናገረው፤ አዲሱ ማኔጅመንት ሥር ነቀል ለውጥ እያደረገ መምጣቱ በአብዛኛዎቹ ጋዜጠኞችና ሠራተኞች ዘንድ ድጋፍ ማግኘቱን ተናግረዋል። አንዳንድ ኃላፊዎች ያለ ችሎታቸው ጭምር ተመድበው የሚሰሩበት ሁኔታ እንደነበርና ይህም በሰራተኛው ዘንድ ቅሬታ ሲቀርብበት ነበር ያሉት እኚሁ አስተያየት ሰጪ፤ ይህ ሁኔታ አሁን እንዲስተካከል መደረጉ አስደስቶናል ብለዋል። በኢትዮጵያ ሬድዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ውስጥ የሚካሄደው ለውጥ በዚሁ ከቀጠለ በቀጣይ ሕዝባዊ ሚዲያ ለመፍጠር የሚያስችል ይሆናል ብለው እንደሚገምቱ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን የዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙላት ገዛኸኝን በስልክ አግኝተን ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።
    ባለፈው ሰኔ ወር አጋማሽ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀድሞ የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ወደ ኮርፖሬሽን ደረጃ እንዲያድግ የሚደነግገውን አዋጅ ተቀብሎ ማጽደቁ ይታወሳል።
source www.sodere.com

Tuesday, July 29, 2014

California Congressman demands the release of Andargachew Tsige

Rohrabacher
WASHINGTON – Rep. Dana Rohrabacher on Monday urged Ethiopia’s prime minister to release Andargachew Tsige, a native-born opposition leader with British citizenship who LAST month was extradited to the African nation from Yemen under questionable circumstances.
In a LETTER to Prime Minister Hailemarian Desalegn, the California Republican wrote: “Mr. Andargachew is a BRITISH citizen and a leader for political reform in Ethiopia. He should be released and allowed to return to his family immediately. Any maltreatment or harm to him, or other prodemocracy activists, in your country only serves to widen THE GAP between our two countries.”
Andargachew was traveling from DUBAI to Eritrea on June 23 when, stopping over in Yemen, he was forcibly flown back to Ethiopia, which he fled in 2005 following protests of the nation’s elections. He was granted asylum in Britain, where his wife currently lives. British officials have expressed concerns that his extradition was not properly handled.
The activist was charged with terrorism and sentenced to death in absentia. In his letter to the Ethiopian prime minister, Rohrabacher added concerns from the United States. His letter follows: >> http://rohrabacher.house.gov/media-cent … n-leader-0
Source Ze-Habesha

Thursday, July 24, 2014

Sudan death sentence woman in Italy

Meriam Ibrahim, from Sudan, disembarks with her family at Ciampino's military airport on the outskirts of Rome (AP)
Meriam Ibrahim, from Sudan, disembarks with her family at Ciampino’s military airport on the outskirts of Rome (AP)
ROME (AP) A Sudanese woman who was sentenced to death in Sudan for refusing to recant her Christian faith arrived Thursday in Italy en route to the United States along with her family, including an infant born in prison.
Italian Premier Matteo Renzi welcomed Meriam Ibrahim at Rome’s Ciampino airport, calling it “a day of celebration.”
Ibrahim and her family are expected to spend a few days in Rome before heading to the United States, where her Sudan-born husband has citizenship. The Vatican confirmed that Ibrahim will meet with the pope, but declined to offer further details.
Ibrahim, whose father was Muslim but whose mother was an Orthodox Christian from Ethiopia, was sentenced to death over charges of apostasy. She married her husband, a Christian, in a church ceremony in 2011. As in many Muslim nations, Muslim women in Sudan are prohibited from marrying non-Muslims, though Muslim men can marry outside their faith.
The sentence was condemned by the United States, the United Nations and Amnesty International, among others, and both the United States and Italy a strong death penalty opponent with long ties to the Horn of Africa region worked to win her release.
Sudan’s high court threw out her death sentence in June, but she was then blocked from leaving the country by authorities who questioned the validity of her travel documents.
Ibrahim arrived in Italy with her husband Daniel Wani, who is a citizen of both the United States and South Sudan, her 18-month-old son and an infant born May 27.
Lapo Pistelli, an Italian diplomat who accompanied the family from Sudan, said Italy was able to leverage its ties within the region, and “we had the patience to speak to everyone in a friendly way. This paid off in the end.”
Source www.Zehabesha.com

Wednesday, July 23, 2014

በሰሜን ሸዋ መርሃቤቴና አካባቢው የተነሳው ውጥረት ተባብሷል፤ ጫካ የገቡ መሪዎች የሕዝቡን አመጽ ተቀላቅለዋል


(በመርሃቤቴ አካባቢ በተነሳው ግጭት ተጎድተው ሆስፒታል ከገቡት መካከል)

(በመርሃቤቴ አካባቢ በተነሳው ግጭት ተጎድተው ሆስፒታል ከገቡት መካከል)
ምኒልክ ሳልሳዊዝ እንደዘገበው፦

በሰሜን ሸዋ መርሃቢቴ እና አካባቢው ላይ የተነሳው የህዝብ እምቢተኝነት ከቀድሞው የበለጠ ተባብሶ ያለበት ሁኔታ መኖሩን ከአካባቢው የሚወጡ ዘገባዎች ጠቁመዋል። ሕዝቡ የመብራት ትራንስፎርመር መወሰዱን መሰረዙ ቢነገረውም ልታዘናጉን ነው። የከተሞቻችንን ንብረት የመጠበቅ ሃላፊነት አለብን የፌዴራል ፖሊሶች ከአካባቢያችን ይውጡልን የሚሉ ጥያቄዎችን በማንገብ መሳሪያውን ይዞ ወደ ከተማው በመውጣት አካባቢውን በውጥረት እንደሞላው ታውቋል።
የመርሃቢቴ ህዝብ አሁንም በያለበት እየተጠራራ የተደበቀውን የጦር መሳሪያ በማውጣትበመሰባሰብ መንገዶችን ተራሮችን ሸጦችን ተቆጣጥሮ ለውጊያ እየተዘጋጀ ነው። ጎረቤት ወረዳዎችም ይህንን የመሬን ህዝብ አመፅ በመደገፍ ወገናዊ ድጋፍና ትብብር ለማድረግ እየተዘጋጁና ግንኙነት እያደረጉ መሆኑን ከሚደርሱን መረጃዎች አረጋግጠናል። የየአካባቢው የወያኔ ታጣቂ ሚሊሻዎች፣ አስተዳደሮች፣ ካድሬዎች በሚያስደስት ሁኔታ ከህዝቡ ጎን ተሰልፈዋል።
እንደምኒልክ ዘገባ ከሆነ ወያኔ በከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ወድቋል ወደ ማይችለው አዘቅትም ገብቷል። ህወኃትን ከነ ግሳንግስ አገዛዙ ለማስወገድ ጊዜው አሁን ነው፣ በተለያየ መንገድ ሸፍተው በጫካ የነበሩ መሬዎች ሁሉ የህዝቡን አመፅ ተቀላቅለዋል ሲል ዘገባውን ቁጭቷል።
ምንጭ ዘ-ሐበሻ

Monday, July 21, 2014

ከድምፃችን ይሰማ የተላለፈ ጥሪ፦ “መንግስታዊው ‘ጥቁር ሽብር’ የህዝብን የድል ችቦ አያጠፋውም!”

ሰኞ ሐምሌ 14/2006
demtschin yesema 2
ከቀናት በፊት በእለተ ጁምአ በታላቁ አንዋር መስጂድ በመንግስት ታጣቂዎች የተወሰደው ድንበር የለሽ ጭፍጨፋ የሙስሊሙ ህብረሰተብ ሰላማዊ ትግል በታሪኩ ሌላ መጠምዘዣ ውስጥ እንዲገባ ምክንያት እንዲሆን የሚያስገድድ ነው፡፡ በዚህ በመንግስት የደህንነት ኃይሎችና በፖሊስ ሀላፊዎች ከቀናት በፊት ታቅዶ በተወሰደ እርምጃ ከ6 ሺ በላይ የመንግስት ቅጥረኛ ሲቪል ለባሾች እንደተሳተፉበት መገለጹ ይታወሳል፡፡ ቅጥረኞቹ የተከበረው የረመዳን ወር የጁምአ ሰላት ከመሰገዱ በፊት በመስጊዱ ውጫዊ ሰሜናዊ አቅጣጫ ግርግር በማስነሳትና ከፖሊሶች ጋር ከሁለቱም አቅጣጫ ድንጋይ በመወራወር የታለመውን ውጤት ለማምጣት ሞክረዋል፡፡ በዚህም በአካባቢው የነበሩትን ጨምሮ በሁሉም አቅጣጫ የነበሩና በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች የጁምአ ሰላታቸውን እንዳይፈጽሙ እክል ከመሆናቸውም በላይ እጅግ በርካታ ጾመኛ ሙስሊሞች ላይ እጅግ አሰቃቂ ጭፍጨፋ ፈጽመዋል፡፡
በእለቱ በተካሄደው ጭፍጨፋ እንደተለመደው የመንግስት የጦር ሜዳ ስልት ሙስሊሙን ከሁሉም አቅጣጫ በቆረጣ ስልት ለሰላት በተቀመጠበት በመቁረጥ በነፍስ ወከፍ በያዙዋቸው ዱላዎችና የመሣሪያ ሰደፎች ርህራሄ አልባ በሆነ ሁኔታ ደብድበውታል፤ ጭፍጨፋ አድርሰውበታል፡፡ ጭፍጨፋው እድሜ፣ ጾታ፣ አስተሳሰብና፣ የአካል ሁኔታን ሳያገናዝብ ነበር የተወሰደው፡፡
ይህን ጭፍጨፋና ክስተቱ የደረሰበትን እለት ማሰብና በሌላ የታሪክ የቀን መቁጠሪያ ውስጥ መክተቱ አስፈላጊ ከመሆኑ አንጻር ለእለቱ ልዩ ስያሜ እንዲሰጠው ታምኖበታል፡፡ በዚህም መሰረት በእለቱ የተወሰደው መንግስታዊ ሽብር ‹‹ጥቁር ሽብር›› የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ ‹‹ጥቁር ሽብር›› በሰለጠነ ውይይት ከማያምን፣ ሰላማዊነትና ዲሲፒሊን ከማይገባው መንግስት የሚፈልቅ፣ ሰዎች ሳይሆኑ ዱላ ብቻ የሚናገርበት፣ ሐሳብ የሚንሸራሸርበት ሳይሆን ነውጥና ግፍ የሚሰፍንበት ሂደት ነው፡፡ ‹‹ጥቁር ሽብር›› አይናቸውን የጋረደው ጥቁር ግርዶሽ የህዝብን እውነታ እንዳይረዱ ያደረጋቸውና ብቃት የሌላቸው ኃላፊዎች የሚወስኑት፣ ሰብዓዊነት በጭካኔ ጭለማ ውስጥ የሚሰጥምበት አስከፊ ክስተት ነው፡፡ አዎን! ለሰላማዊ ሕዝብና ጥያቄ ምላሹን ዱላ ያደረገ ኃይል፣ ባልታጠቀና በእጁ ድንጋይ ባልጨበጠ ጾመኛ ሕዝብ ላይ የጥይት ቃታ የሚስብ መንግስት ከርሞም የሚነዳው በ‹‹ጥቁር ሽብር›› ብቻ ነው፡፡ ሰላማዊ ትግላችንም ከዚህ በኋላ በሚኖረው ሂደት የሐምሌ 11/2006ን አሰቃቂ የመንግስት ጭፍጨፋ የታሪክ ካስማ በማድረግ እለቱ ‹‹ጥቁር ሽብር›› ሲባል ከዚህ በኋላ ያሉ ክስተቶችም ‹‹ከጥቁር ሽብር በኋላ›› ወይም ‹‹ከጥቁር ሽብር በፊት›› እየተባሉ የሚዘገቡ ይሆናል፡፡
‹‹ጥቁር ሽብር›› ከአወሊያ መስጂድ የውድቅት ሰዓት ቀድሞም በአሳሳ በጁሙአ ሰላት ወቅት የተፈጸመ ነው፡፡ ‹‹ጥቁር ሽብር›› ጨለማ ተገን ተደርጎ በአወሊያ መስጂድ ከሁለት አመታት በፊት እንደተወሰደው፣ በጠራራ ጸሐይም በሲቪል ለባሽ ካድሬዎች አሻጥር ተከልሎ ልባቸው በተንኮል በጠቆረ ኃላፊዎች ትእዛዝ፣ በታወረ ህሊና እና አይን የሚወሰድ የአላዋቂነት ድርጊት ነው፡፡ ‹‹ጥቁር ሽብር›› እውቀት አይጠይቅም፤ ዱላና እርግጫ ብቻ ነው የሚጠይቀው፡፡ ‹‹ጥቁር ሽብር›› ህገ መንግስቱን በድቅድቅ ጨለማም ሆነ በቀትር ጸሐይ ንዶ ያሻውን የሚገድል፣ የተቀረውንም የሚያቆስል ጸያፍ ድርጊት ነው፡፡ የእለቱ ስያሜ እስከመቼውም የሚዘልቅ ሲሆን ለወደፊቱም በዚህ የ‹‹ጥቁር ሽብር›› አሻጥር ውስጥ የተሳተፉ ወንጀለኞች ለፍርድ የሚቀርቡበት ጊዜ ሩቅ እንደማይሆን እናምናለን፡፡
ይህ በእውር ድንበር የተወሰደና ማንንም ሳይለይ ድንገት እንደደራሽ ጎርፍ የደረሰ ‹‹ጥቁር ሽብር›› ብዙዎችን በአካል ያቆስል ይሆናል፤ በተቃራኒው ግን ዱላውና ግድያው የሰዎችን ሞራል ከፍ ያደርጋል፡፡ በመብት ነጠቃ የ‹‹ጥቁር ሽብር›› ሰለባነት ማግስት የሞራል ከፍታና የአላማ ጽናት ጎልቶ ይታያል፡፡ ባለፉት ሶስት በሚጠጉ አመታት መሰል በርካታ የ‹‹ጥቁር ሽብር›› ዘመቻዎች ተፈጽውብናል፡፡ በማግስቱ ግን ሁሌም ጎልተን እንታያለን፡፡ በተደበደብን ቁጥር፣ በደሉ ባረፈብን ቁጥር ቁስላችን ከመመርቀዝ ይልቅ እየጠገገ ጥንካሬያችንን ሲያጎላው አይተናል፡፡ ሁላችንም እንደምንረዳው ኃይል የተስፋ መሟጠጥ፣ የሐሳብና ዴሞክራሲያዊነት መራቆት አይነተኛ ምክንያት ነው፡፡ ተስፋ መቁረጥ ሲናኝ ኃይል ባህሪ ይሆናል፡፡ የእኛ ትግል ግን በሰላምና ዲሲፕሊን ውስጥ እያለፈ ድልን ይቀዳጃል!
መንግሥታዊው ‹‹ጥቁር ሽብር›› የህዝብን የድል ችቦ አያጠፋውም!
ትግላችን በአላህ ፈቃድ እስከ ድል ደጃፎች ድረስ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!
ምንጭ ዘ-ሐበሻ

Friday, July 18, 2014

አገራዊ ጥሪ ለመከላከያና የፓሊስ ሠራዊት አባላት

ግንቦት 7፡ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የኢትዮጵያ የመከላከያና የፓሊስ ሠራዊት አባላትን ከአለቆቻቸው ለይቶ ይመለከታል።
የመከላከያና የፓሊስ ሠራዊት ከፍተኛ ሹማምንት ከህወሓት የተቀዱ፣ ለህወሓት ሥልጣን የቆሙ፣ ዘረኞች፣ ፋሽስቶችና ሙሰኖች መሆናቸው በገሃድ የሚታወቅና በተደጋጋሚ ጥናቶችም የተረጋገጠ ጉዳይ ነው። በዘመነ ወያኔ የሠራዊት አዛዥነት ሹመት መሥፈርቶች ዘር፣ የፓለቲካ አመለካከትና ለህወሓት ያላቸው ታማኝነት ነው። በዚህም ምክንያት ሁሉም ቁልፍ የአዛዥነት ቦታዎች የተያዙት ሙሉ በሙሉ የህወሓት አባላት በሆኑ የትግራይ ተወላጆች ነው። እነዚህ የጦርና የፓሊስ ሹማምንት ኢትዮጵያን ወረው እንደያዙት አገር ሲዘርፉ፣ ሕዝቧንም ሲገሉና ሲገርፉ እንሆ 23 ዓመታት አልፈዋል። በእነዚህ 23 ዓመታት ትግራይን ጨምሮ በደል ያልደረሰበት የኢትዮጵያ ግዛት እና የኅብረተሰብ ክፍል የለም። ሁሉም ኢትዮጵያዊ በእነዚህ ፋሽስቶች ተረግጧል፣ ተዋርዷል፣ ተግዟል። የንቅናቄዓችን ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጨምሮ በርካታ ኢትዮጵያዊያን የነፃነት አርበኞች በእነዚህ እኩይ የሠራዊቱና የፓሊስ አዛዦች ሰቆቃ እየተፈፀመባቸው ነው። የወያኔ የጦርና የፓሊስ አዛዦች እና ሰላዮች አገራችን እያደሙ፤ ሕዝባችንን እያስለቀሱ ነው። በወያኔ ፋሽስት የጦርና የፓሊስ አዛዦች እና ሰላዮች ጥምረት ሰቆቃ የሚፈፀምበት የኅብረተሰብ ክፍል በየጊዜው እየጨመረ ይገኛል። የወያኔ ማሰቃያዎችን የሞሉት የፓለቲካና የሀይማኖት መሪዎች፣ ጋዜጠኞችና ብሎገሮች መሆናቸው ለዚህ አንድ ማሳያ ነው።
የሠራዊቱ የበታች ሹማምንትና ተራ አባላት ጥንቅር ግን ከአዛዦቹ ፈጽም የተለየ ነው። የመከላከያና የፓሊስ ሠራዊት አባላት ከመላው የኢትዮጵያ ግዛቶች የተውጣጡ፤ እንደሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉ በነፃነት እጦት፣ በመብቶች መገፈፍ እና በኑሮ ውድነት የሚሰቃዩ ዜጎች ናቸው። የኢትዮጵያ ወታደር በወያኔ አዛዦቹ እየታዘዘ ወገኑን የሚበድል ቢሆንም ራሱ ከመበደል ግን አይድንም። የኢትዮጵያ ወታደር በወያኔ አዛዡ ታዞ ሌላኛውን ወገኑን ቢያስርም ሹሙ ፊቱን ባዞረበት ጊዜ እራሱ ደግሞ ከመታሰር አይድንም። የኢትዮጵያ ወታደር ወያኔ አዞት ምስኪኖችን ይደበድባል፤ ራሱ ደግሞ በወያኔ ይደበደባል። የኢትዮጵያ ፓሊስ በወያኔ ትዕዛዝ ንጹሀን ዜጎችን ያስራል፣ ያሰቃያል፤ እራሱ ደግሞ በወያኔ ይታሰራል፣ ይሰቃያል። ይህ ምን የሚሉት ባርነት ነው? የወያኔ ሹማምንቶች በሚመሩት የመከላከያና የፓሊስ ሠራዊት ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን በህወሓት የሚደርስባቸው በደል ሌላው ኢትዮጵያዊ ከሚደርስበት ይብስ እንደሆን እንጂ የሚያንስ አይደለም።
ግፍ መብቃት አለበት። በጥቂት የህወሓት ሹመኖች ትዕዛዝ በኢትዮጵያዊው ወታደር ላይ የሚደርሰው ውርደት ማብቃት አለበት። ሠራዊቱ የኢትዮጵያ እንጂ የህወሓት ሠራዊት አይደለም፤ ሊሆንም አይገባውም። ሠራዊቱ ለራሱ ነፃነት ብቻ ሳይሆን ለአገርና ለሕዝብ ደህንነት ዘብ የመቆም ኃላፊነት አለበት። የኢትዮጵያ ሠራዊት የህወሓት የባንዳ ሠራዊት ሆኖ ሕዝብን በማሰቃየትና ሀገርን በመበደል ተግባር ላይ ተሠማርቶ ማየት አንሻም። ይህንን ለራሱ ክብር ያለው፤ አገሩንና ሕዝቡን የሚወድ የሠራዊቱ አባልም የሚፈቅደው ጉዳይ አይደለም።
ስለሆነም ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የሚከተለው ሀገራዊ ጥሪ ለመላው የመከላከያና የፓሊስ ሠራዊት አባላት ያቀርባል።
ውድ የኢትዮጵያ የመከላከያ ወይም የፓሊስ ሠራዊት አባል! በጥቂት የህወሓት ፋሽስቶች መዳፍ ውስጥ ሆነህ የገዛ ራስህን፣ የቤተሰቦችህን፣ የወገንህን እና የአገርህን ስቃይ ማራዘምህን አቁም። አንተ የኢትዮጵያ ሕዝብ አለኝታ እንጂ የጥቂት ጎጠኞች ሎሌ ልትሆን አይገባም። አንተ የኢትዮጵያ ሕዝብ መከታ እንጂ የእያንዳንዱ ቤተሰብ ስጋት መሆን የለብህም። አንተ የመጪው ትውልድ አርዐያ እንጂ ሕፃናትንና ወጣቶችን ማስፈራሪያ መሆን የለብህም።
የኢትዮጵያ ወታደር ሆይ! ራስህን ተመልከት! ራስህን ታዘብ! ዛሬ ያለህበት ሁኔታ አሳፋሪ ነው። አዛዦችህ አገርን፣ ትውልድንና ታሪክን ለማጥፋት የተነሱ ናቸው። አንተን ተጠቅመው ነው ይህንን ዓላማቸውን የሚያስፈጽሙት። ይህ ላንተ ብቻ ሳይሆን ለልጅ ልጆችህ ውርደት ነው። ከወያኔ ባርነት ራስህን ነፃ አውጣና የነፃነት ታጋዮችን ተቀላቀል። ወያኔ መጥፋቱ አይቀርም። ወያኔ የቀድሞውን ጦር እንደበተነው አንተን ለመበተን የሚሻ የለም። አንተ ዛሬ ከወገን ጋር ወገንተኛነትህን ካሳየህ ከአገዛዙ ጋር እጠፋለሁ ብለህ አትስጋ። ለዚህም ነው አንተ ዛሬ በግልም ሆነ በቡድን የምትወስደው እርምጃ የአገራችንን ብቻ ሳይሆን የሠራዊቱን እጣ ፈንታ ይወስናል ብለን ወገናዊ ጥሪ የምናቀርብልህ።
ውድ የኢትዮጵያ የመከላከያና የፓሊስ ሠራዊት አባላት ወገናችን!ከበዳዮች ጎን ሳይሆን ከተበዳዮች ጎን ቁም። ከገራፊዎችና ገዳዮች ጎን ሳይሆን ከነፃነት ታጋዮች ጎን ሁን። ዛሬውኑ ወስን። አሁን የነፃነት ታጋዮችን መቀላቀል ቀላል ሆኗል። ያሉበትን ታውቃለህ፤ ተቀላቀል። አልያም የጠመንጃህን አፈሙዝ በፋሽስት አለቆችህ ላይ አዙር። ይህንን እርምጃ በመውሰድ ከታሪክ ተወቃሽነት እራስህን በመታደግ ለአገርህና ለወገንህ አለኝታህን አረጋግጥ።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!
source www.ginbot7.org

Monday, July 7, 2014

Andargachew Tsige at risk of torture: Amnesty International

UA: 171/14 Index: AFR 25/003/2014 ETHIOPIA Date: 4 July 2014
URGENT ACTION ETHIOPIAN ACTIVIST AT RISK OF TORTURE Andargachew Tsige, an Ethiopian political activist in exile, appears to have BEEN ARRESTED in transit in Yemen on 24 June and forcibly returned to Ethiopia. He is at risk of torture and other ill-treatment. Andargachew Tsige is a British national of Ethiopian origin and Secretary-General of Ginbot 7, an outlawed Ethiopian opposition group. He disappeared on 24 June at Sana’a airport in Yemen, while in transit between the United Arab Emirates and Eritrea. Although no official statements have been released by the Yemeni or Ethiopian authorities about his current whereabouts, human rights activists in Yemen told Amnesty International that he was forcibly returned to Ethiopia the same day he landed after being detained at the Sana’a airport.
He is at high risk of torture and other ill-treatment in Ethiopia, where political detainees are frequently tortured in order to extract INFORMATION and confessions. His incommunicado detention in an unknown location increases this risk.
Ginbot 7 is one of five organisations proscribed as TERRORISTorganisations by the Ethiopian parliament in 2011. In 2012, Andargachew Tsige was prosecuted in absentia on terrorism charges (alongside journalist and prisoner of conscience Eskinder Nega, and others) and sentenced to life imprisonment. Previously, in 2009, he was convicted in absentia on charges related to an aborted coup attempt and was sentenced to death. He was also tried in absentia in the 2005-2007 trial of political opposition members, journalists, activists and others.
In recent years, many Ethiopians wanted by the authorities on the grounds of their political activities have been kidnapped in neighbouring countries and forcibly returned to Ethiopia. This has often involved the collaboration of security forces in those countries. Another of the defendants in the 2012 trial had been kidnapped and forcibly returned from Sudan. All those returned are at risk of arbitrary detention, torture and unfair trial.
Please write immediately in Amharic, English or your own language:  Calling on the authorities to guarantee Andargachew Tsige is not subjected to torture or other forms of ill- treatment;  Calling on the authorities to immediately provide information on the location where he is being held, and to ensure that he has full and immediate access to legal and consular representation and family members;  Calling on the authorities to ensure that Andargachew Tsige is not required to serve any sentence for a conviction in absentia and must be retried on any charges against him in a trial that meets international standards, before a new court and without the possibility OF THE DEATHpenalty.
PLEASE SEND APPEALS BEFORE 8 AUGUST 2014 TO: Minister of Justice Berhanu Hailu Ministry of Justice, PO BOX 1370, Addis Ababa, Ethiopia Fax: +251 11 5517755 Salutation: Dear Minister
Minister of Federal Affairs D. Shiferaw Teklemariam Ministry of Federal Affairs P.O.Box 5718 Addis Ababa, Ethiopia Email: shiferawtmm@yahoo.com Salutation: Dear Minister
And copies to: Prime Minister His Excellency Hailemariam Desalegn Office of the Prime Minister, PO BOX 1031, Addis Ababa, Ethiopia Fax: +251 11 552030 (keep trying)
Also send copies to diplomatic representatives accredited to your country. Please insert local diplomatic addresses below: Name Address 1 Address 2 Address 3 Fax FAX NUMBER Email Email address Salutation Salutation Please check with your section office if sending appeals after the above date.
URGENT ACTION ETHIOPIAN ACTIVIST AT RISK OF TORTURE
ADDITIONAL INFORMATION Andargachew Tsige is a former member of the ruling Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front (EPRDF) party and was Deputy Mayor of Addis Ababa from 1991 to 1994, when he resigned on ACCOUNT of differences with the government.
Based in the UK, he travelled to Ethiopia shortly BEFORE THE 2005 elections to support the opposition party Coalition for Unity and Democracy (CUD). On 8 June 2005, in the wake of the controversial election results, he was detained in Ethiopia and held at Ziway army camp. He was released on bail in July of that year. Like many detainees, Andargachew was accused of organizing the demonstrations, seeking to subvert the Constitution and other offences, which he denied, but he was not formally charged with any offence. After he was released he returned to the UK, but was subsequently named, tried and convicted in absentia in a major political trial of the leadership of the CUD, journalists, human rights activists and others, on charges including high treason, in 2005-2007. At the time he was the CUD representative in the UK.
After the CUD trial, fellow defendant Berhanu Nega founded the ‘Ginbot 7 Movement for Justice, Freedom and Democracy’ from exile in the US, of which Andargachew Tsige became SECRETARY General. Berhanu Nega was also tried in absentia in the 2009 and 2012 trials.
Name: Andargachew Tsige GENDER m/f: M
UA: 171/14 Index: AFR 25/003/2014 ISSUE Date: 4 July 2014
Source ethioforum.org.

Saturday, July 5, 2014

አዋጅ አዋጅ !!!………..ልብ ያለዉ ልብ ይበል ጆሮ ያለዉ ይስማ !! የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል

አዋጅ አዋጅ !!!
ልብ ያለህ ልብ በል ጆሮ ያለህ ስማ !!
የግንቦት7 ህዝባዊ ሃይል የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በየመን መታገት አስመልክቶ አጭር መግለጫ ማውጣቱ ይታወቃል::በመግለጫችን የመን ታጋዩን ልታግት የምትችልበት የጸጉር ስንጣቂ  የምታክል  ምክንያት እንደሌላት ሊኖራትም እንደማይችል ስለሆነም ታጋዩ  ባስቸኳይ  እንዲለቀቅ በተደጋጋሚ ጠይቀን፣ ይህ ሳይሆን ቀርቶ  የነጻነት ታጋዩ ለፋሽስቱ የወያኔ ቡድን ተላልፎ  ቢሰጥ የመን የማይሰረዝ ታሪካዊ ስህተት የምትሰራ  መሆኑን ህዝባዊ ሃይላችንም የበቀል እርምጃዎችን  እንደሚወስድ አሳውቀን ወያኔም ምናልባት ትግሉን አስቆማለሁ በሚል የሞኝ  ስሌት  ያደረገው ከሆነ  ድርጊቱ  ትግሉን በዕልህ  እና  በበቀል አጅቦ ከመውሰድ እና  ከማፋጠን የዘለለ ትልቁ የሃሳብ አባት አንዳርጋቸው በሃገሪቱ  ሰማይ ላይ  የለቀቀውን የኢትዮጵያዊነት ጸረ ወያኔ መንፈስ አስሮ አሰቃይቶ፣ገሎ ማስቆም እንደማይችል አሳስበን አስገንዝበን ነበር:: መግለጫችን የተጻፈበት ቀለም ሳይደርቅ ግን የየመን መንግስት  እንደሰጋነው ትልቁን የቁርጥ ቀን ልጅ ለወያኔ አሳልፎ መስጠቱን አውቀናል::
የተከበርከው የታላቅ ታሪክ ባለቤት የሆንከው የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ  አሁንስ  ምን ትጠብቃለህ?? ምንቀረህ ?? ያለህበትን ሁኔታ የሚገልጽ ከዚህ በላይ ገላጭ ነገር ከቶ ከወዴት ይመጣል??ወያኔ የአንዳርጋቸው በእጁ መግባት ለጊዜውም ቢሆን ከሚፈጥርለት ፌሽታ  ጎን ለጎን እገታው በይፋ  ከተገለጸበት ቅጽበት ጀምሮ ግን  የሚፈራው የሚጠላው ነገር ብቅ ብሏል፦የአንድነት መንፈስ!!  የጋራ ድምጽ!!እገታው ለኢትዮጵያ  ህዝብ  በይፋ  ከተነገረ በኋላ በሁሉም አቅጣጫ የሚኖር መላው ኢትዮጵያዊ የፖለቲካ  አመለካከት እና  ፍልስፍና  ሳያግደው ለአንዳርጋቸው ያለውን ድጋፍ እና  ያገባኛል ባይነቱን አሳይቷል፣እያሳየ ነው፤ገልጿል እየገለጸ ነው::
ይህ መጥፎ አጋጣሚ ለተቃውሞ  የፖለቲካ  ትግሉ ይዞት የመጣው መልካም ሁኔታ እና ክስተት ይኸው ነው:፤ተባብሮ መጮህ!! የተባበረ ነጎድጓዳዊ ቁጣ!!
በእውኑ ከዚህ በላይ ወያኔን የሚያሸብር ዙፋኑን የሚያርድ ጉዳይ ከወዴት ይገኛል?? የትም::
የተከበርከው የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ከቶ በምን አይነት አመክንዮ እና የታሪክ ምጸት ነው ወያኔን የመሰለ አንድ ተንቀሳቃሽ የሽፍታ ቡድን ተሰደን  እንኳን መተንፈስ እንዳንችል አድርጎ ለ 23 ዓመታት ቀጥቅጦ እና  አዋርዶ ሊገዛን የቻለው??
እራሳችን በዘር፣በሃይማኖት፣በፖለቲካ  አመለካከት ልዩነት ከፍለን የተባበረ ክንዳችን የጋራ ጠላታችን ላይ ማንሳት ባለመቻላችን አይደለምን?? ነው እንጅ!!!
የግንቦት 7 ህዝባዊ  ሃይል በዚህ  ታሪካዊ ወቅት የታሪክ ጠርዝ ላይ ቆሞ የሚያስተላልፈው መልዕክት አለው፦
እስከመቸ ነው ጥቁሩን በሬ ጅብ ሲበላው ነጩ በሬ  ሳይደንቀው፣ያጣማጁ ደም ሳይሸተው ፣ ነጩን በሬ  ጅብ ሲከበው ጥቁሩ  በሬ አደጋውን የነጩ ብቻ  አድርጎት ጉዳዩን ችላ  ሲለው በመጨረሻ  ግን ሁለቱም የጅብ መንጋ  ሲሳዮች ሲሆኑ ተረት እየተተረተብን የምንጓዘው???? ሃገራችን ጨርሳ እስክትጠፋ ማህበረሰባችን እስኪበተን ነውን?? ብዙዎቻችን የምናውቀውን አንድ ታሪክ እዚህ ላይ ብንጠቅስ ያለንበትን ሁኔታ  በተወሰነም ደረጃ  ቢሆን ለማሳየት  የሚረዳ ይመስለናል::ናዚ ወደ ስልጣን ሲመጣ እና  የስልጣን ማማ ላይ ቆሞ የሚሰራውን እየሰራ  በነበረበት ወቅት ላይ የወቅቱ የጀርመን ልሂቃን ዝምታ የገረመው አንድ አስተዋይ ታላቅ ሰው ይህን ታዝቦ ነበር፦
በቅድሚያ  ኮሚንስቶች ላይ አነጣጠሩ
የዚያን ጊዜ ኮሚንስት  ስላልነበርኩ ዝም አልኩ
ቀጥለው በሶሻሊስቶች ላይ አነጣጠሩ
የዚያን ጊዜ ሶሺያሊስት  ስላልነበርኩ ዝም አልኩ
ለጥቀው ወደ ሰራተኛው  ማህበር አነጣጠሩ
የዚያን ጊዜ  የሰራተኛው ማህበር አባል ስላልነበርኩ ዝም አልኩ
በመጨረሻ  ወደ  እኔ መጡ በዚያን ጊዜ ለኔ  የሚጮህልኝ አንድም ሰው አልተረፈም ነበር ::
እስከመቼ ነው አንዳንችን ለአንዳችን እና  ተባብረን እንዳንጮህ የዘር፣የእምነት እና  የፖለቲካ  አስተሳሰብ ልዩነት አሎሎ ትናጋችን ውስጥ ተቀርቅሮ በጩሀት እንኳን እንዳንደጋገፍ የሚያንቀን???? በ እውኑ ከላይ  የተቀመጠው ትዝብት በትክክል ወቅታችንን አያንጸባርቅምን??!
ስለዚህ የአንዳርጋቸው መታገት  እና  ለወያኔ  ተላልፎ መሰጠት የፈጠረው የአንድነት ስሜት በስርዓት ተኮትኩቶ  በፍጥነት ፋፍቶ ወያኔን ወደመጣል እና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት የመገንባት ዋና  ዓላማችን ድረስ ሊወስደን  ይገባል::ምንድን  ነው የምንጠብቀው? እንዴትስ ነው በዚህ ደረጃ  ያፍዝ ያደንግዝ የተደገመብን??ምን ዓይነት  የመንፈስ ክሽፈት ነው እግር ከዎርች ያሰረን??
ምናልባት የምናሳድጋቸው ልጆች  ይኖሩናል::አንዳርጋቸውም እኮ  እንደሰው የወለዳቸው ህጻን ልጆች አሉት ::አንድም ቀን አብሯቸው ውሎ  አያቅም እንጅ::እዚህ በረሃ  ውሃ እና  ትርፍ ስዓት ሲገኝ የታጋዩን ልብስ የሚችለውን ያህል  ያጥብ ነበር፣የልጆቹን ልብስ  እንዳላጠበ  ግን እርግጠኝ ሆኖ መናገር ይቻላል:፡ከ ዓመት በላይ  በረሃ  ውስጥ ከረሃብ እና ጥም ጋር ሲታገል ልጆቼ የሚል ቃል  ካፉ ወጥቶ  አያቅም :: እንደሰው  ልጆቹን  ስለማይናፍቅ ግን አይደለም::ለዚች መከረኛ ሃገር ሙሉ ራሱን ስለሰጠ የልጅና  የቤተሰብ ናፍቆት የመሰሉ ሰዋዊ ፈተናዎችን ታላቅ ራዕይን በሰነቀች ልቡ ውስጥ አስቀምጦት እንጅ::እና አንዳርጋቸው  ልጆቹን ስለሚጠላ አይደለም የት እንደሚሄድ እንኳን ሳይነግራቸው ወደ በረሃ ሹልክ ያለው::ልጁን ማን  ይጠላል!!የአንዳርጋቸው ጭንቀት ልጆቻችን ያለ ሃገር ወልደናቸው ምን ሊሆኑ ነው የሚል ነበርና ሃገር ሰርቶ ፣ማህበረሰብ ገንብቶ የማስረከብ ስራውን  ቅድሚያ  ሰጠው::
ምናልባት ሃብት፣ትዳር ይኖረን ይሆናል::ግን ያለሃገር እና  ያለነጻነት ሃብትና  ትዳር ምንምን ይላል?? ይጣፍጣል?? አይመስለንም::በዘርህ  እና  በፖለቲካ  አስተሳሰብ ልዩነትህ  ምክንያት ከሞያሌ አሜሪካ ፣ከጎንደር አውስትራሊያ ፣ከጋምቤላ ካናዳ ድረስ በምትሳደድበት እና በምትታደንበት ሁኔታና ዘመን ውስጥ እስከ  አፍንጫ ተነክሮ ሃብትና  ትዳር ምንድን ናቸው??ምናልባት እንደቀንድ አውጣ ራሳችንን የምንቀብርባቸው ቅርፊቶች ካልሆኑ በስተቀር::አንዳርጋቸው ለዚች ጣጣዋ ያላላቀ ሃገር፣ለዚች የምትንገላታ ባንዴራ ኪሱ ውስጥ 5  የአሜሪካን ዶላር እስኪቀረውና አላላውስ እስኪለው ኢትዮጵያዊ እምነቱን ለመግለጽ፣ለማስተማር፣ለመቀስቀስ ዞሯል ወጥቶ ወርዷል::
ምናልባት_________እያልን ብዙ  እንደምክንያት የሚጠቀሱ ነገሮችን ስንደረድር  ልንውል  እንችላለን::አንድን ሃገር እና  ትውልድ ሙሉ በሙሉ ሊያጠፋ እየጣረ  ያለ  ስርዓትን በግልጽ  እስከ ህይወት መስዋዕትነት ላለመታገል ብዙ  ምክንያት  እያነሳን ራሳችን ልንሸነግል እንችላለን:: ከቁም ሞት  እያዳነን አይደለም እንጅ!!
ከቶ በምን ዓይነት ተፈጥሯዊ ወይ ሰው ሰራሽ ተጠየቅ ይሆን አንድ የሽፍታ ቡድን 97 ሚሊዮን  ህዝብ ለ 23 ዓመታት አምበርክኮ ለገዛ የሚሞክረው?? ለቆመ አይደለም ለሞተ የሚገርም ጉድ አይደለምን??ከዚህ በላይ አሳፋሪ ነገርስ በየትኛው የዓለም ጫፍ ቢታሰስ ይገኛል???ይህ አዋጅ ለተደራጁ  የፖለቲካ  ሃይሎች ብቻ አይደለም፣ለሲቪክ ተቋማት ብቻ  አይደለም፣ለወጣቱ ሃይል ብቻ አይደለም፣ለወንዶች  ብቻም  አይደለም::ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የታወጀ አዋጅነው:: ተነስ !!! መሳሪያ አንሳ !!! ወያኔን በጉልበትህ ከራስህ ላይ አውርድ!!!የመከራ እና  የውርደት ዘመን ይብቃ !!!ያለበለዚያ ሁለት ምርጫዎች እጃችን ላይ አሉ፦አንድ በጋራ ታግለን ነጻነታችን ማዎጅ ሁለት ባርነትን መርጦ ፣ባርነትን ተቀብሎ እንደባሪያ መገዛት!! በቃ !!
አንድ አለመሆናችንን የታዘቡ እናም የናቁን ፣በየስርቻው መወሸቃችንን የተገነዘቡ እናም የተጸየፉን የተጻፈ እና ያልተጻፈ  የረጅም ጊዜ ፖሊሲ ያላቸው የብሄራዊ ቤተሰብ ምስረታ  ሂደታችን  አደናቃፊ ብሄራዊ ጠላቶቻችን ነጻነታችንን  ስለማይፈልጉ ቅኝ ገዝዎቻችን ሌት ተቀን እየተባበሯቸው ነው::የሚፈልጉትን ሰው አንስተው እየሰጧቸው ነው::
እልፍ አዕላፍ ኢትዮዮጵያዊያን ከተጠጉበት እየታደኑ  ለእርድ ሲቀርቡ ይሀው ድፍን 23 ዓመት ሞላን::አንዱ ከሆነ ሃገር ሲያዝ  እና  ተላልፎ  ሲሰጥ እንደነጩ በሬ የጓዳ አጋራችን ደም አልከረፋ  ሲለን፣እኔ  ምን አገባኝን ስንቀኝ፣ይህ እኮ የኮሚኒስቶች ጉዳይነው፣የነከበደ ጣጣ ነው እዛው ይወጡት ስንል በየተራ  እየተለቀምን እያለቅን ነው::
አንዳርጋቸው ለዕርድ  ቀርቧል!!ምናልባት ታሪካዊ ጠላቶቻችን የእርድ ቢላዎቻቸውን ስለው ደም  በቋጠረ  የበቀል አይን ከበው እያዩት ይሆናል::ሊያርዱት!!እንደታሳሪ  ፈርቶ  ሳይሆን መልካም ስራ  ሰርቶ  ክርስቶስ/አላህ ዙፋን ፊት እንደቀረበ ጻድቅ በኩራት ቆሞ አንገቱን እንደሚሰጥ ግን ጥርጥር የለንም::ታዲያ  የኛ አዋጅ አንኳር መልዕክትም ያለው እዚህ ጋር ነው::አንዳርጋቸው በየሰርጡ እና  በየእርሻው እየዞረ  የዘራው የአንድነት፣የኢትዮጵያዊነት፣የነጻነት፣የፍትህ ፣የዴሞክራሲ ዘር የሱ በድን ላይ ይብቀል፣ደሙን ጠጥቶ  ይፋፋ ከሱ በኋላ ግን ይብቃ  የሚል ነው ::ኢትዮጵያዊዪ አንድ ሆኖ ተቆጥቶ  እንደ አንበሳ  ያገሳ ዕለት የሰሜን ነፋስ እንደነካው ጉም በነው  እንደሚጠፉ እናውቃለን::ያውቃሉ::ማድረግ ያቃተን ተደጋግፈን መቆም፣እጅለ እጅ መያያዝ፣አንድ ላይ መጮህ አንድ ላይ የቁጣ  ክንዳችን መሰንዘር ብቻ  ነው::ታዲያ  ካሁን በኋላ  የአንዳርጋቸውን አንገት የቆረጠ ካራ ለሌሎች ተረኞችም ተስሎ  እንዲቀመጥ እንፈልጋለን?? የማንፈልግ ከሆነ  እጆቻችንን እርስ በርስ አጣምረን መብረቅ  እናስተፋቸው፣ነጎድጓድ  እንሙላቸው::ከዚያ  ውጤቱን በታሪክ ገጽ ላይ ጎልቶ  ተጽፎ  እናየዋለን::ያለበለዚያ ኢትዮጵያዊያን የለንም ጨርሰን ጠፍተናል ማለትነው::ስለዚህ  ከዛሬ  ጀምሮ አዋጅ አዋጅ፣ ልብ ያለው ልብ ይበል ፣ጆሮ ያለው ይስማ !!!ምታ ነጋሪት ክተት ሰራዊት ሳትጠፋ ጠላቶችህን አጥፋ !!!!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!
ምንጭ የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል 

Friday, July 4, 2014

የመን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ለወያኔ ፋሽስቶች አሳልፋ መስጠቷን በማስመልከት የወጣ መግለጫ

የመን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ለወያኔ ፋሽስቶች አሳልፋ መስጠቷን በማስመልከት የወጣ መግለጫ -( Audio MP3)
ሰኔ 27 ቀን 2006 ዓ.ም
የግንቦት 7፣ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ሰኔ 16 ቀን 2006 ዓ.ም ለሥራ ጉዳይ በየመኒያ አየር መንገድ አይሮፕላን ተጉዞ በትራንዚት ሰንዓ ከተማ እያለ በየመን መንግሥት ፀጥታ ኃይሎች በሕገወጥ መንገድ ታግቶ መቆየቱ ማስታወቃችን ይታወሳል።
የየመን መንግሥት በህገወጥ መንገድ ያገተብንን የንቅናቄዓችንን አመራር በአስቸኳይ እንዲፈታ በተለያዩ መንገዶች ላለፈው አንድ ሣምንት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። የአገሩን የረዥም ጊዜ ጥቅም ማየት የተሳነው የየመን መንግሥት ከኢትዮጵያ ሕዝብ ይልቅ አምባገኑን ወያኔ መርጦ መሪያችንን ለእርድ አሳልፎ ሰጥቶብናል። በዚህም ሳቢያ የየመን መንግሥት ይቅርታ የማያሰጥ፤ ዘመን የማይሽረው ታሪካዊ ስህተት ፈጽሟል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ለወዳጅ ጎረቤት ትሁትና ቀና ቢሆንም ጥቃት በሚያደርስበት የቅርብም ሆነ የሩቅ ጎረቤት ላይ ግን ቁጣውን የሚመጥን የአፀፋ እርምጃ መውሰድ ያውቅበታል።
የወያኔ ፋሽስቶች አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በማሰቃየት ትግላችንን ማቀዝቀዝ እንደማይችሉ ልናረጋግጥላቸው እንወዳለን። እንዲያውም በግልባጩ ቁጣና እልሃችን በእጥፍ ድርብ በመጨመር ትግላችንን ያጦዘዋል። ወያኔ፣ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በውንብድና ጠልፎ መውሰዱ የትግሉን ሜዳ አስፍቶታል፤ የትግሉንም ዓይነት አብዝቶታል። ይህ ደግሞ የወያኔ ፋሽስቶችን ከፍ ያለ ዋጋ ያስከፍላቸዋል።
የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ህገ ወጥ እገታ ከተሰማ ዕለት ጀምሮ የፓለቲካ ልዩነት አጥር ሆኖ ሳይከልላችሁ ከጎናችን ለቆማችሁ የፓለቲካ ድርጅቶች፣ የሲቪክ ማኅበራትና ዜጎች ሁሉ ምሥጋናችንን እናቀርባለን። በወገናዊ ተግባራችሁ ልባችን ተነክቷል። ከዚህ በላይ ደግሞ ለቀጣዩ ወሳኝ ፍልሚያም እንደምንቆም እና የወያኔን እድሜ እንደምናሳጥር እምነታችን አጠንክሮልናል።
ከዛሬ ጀምሮ አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ አንዳርጋቸው ጽጌን ሆኗል። ዛሬ ዘጠና ሚሊዮን አንዳርጋቸው ጽጌዎች በአንድነት ተነስተዋል። በአንድ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ የደረሰው ጥቃት ሰበብ ሆኖ የተቀሰቀሰው የሕዝብ ቁጣ የወያኔ ፋሽስቶችን ይጠራርጋል። በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ ለደረሰውና ለሚደርሰው ጥቃት እያንዳንዱ የወያኔ ሹም በግል ዋጋ ይከፍላል። ከእንግዲህ በምሬት የተነሳሳው የኢትዮጵያ ሕዝብ ለሚወስደው እርምጃ ተጠያቂው ራሱ ወያኔ መሆኑን እውን ሆኗል። በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እስር የክተት አዋጅ ታውጇል። ለፍትህ፣ ለነፃነት፣ ለሀገር፣ ለእኩልነት ግድ ያለህ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ተነስ!!!
በመስዋዕትነት ድልን እንቀዳጃለን።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!
source www.ginbot7.org

Thursday, July 3, 2014

አንዳርጋቸው የማይጨበጥ ጽኑ መንፈስ እንጂ አንድ ግለሰብ አይደለም!!!

በኢትዮጵያ ዘመናዊ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ከታዩ አርቆ አሳቢ፣ አስተዋይና ብልህ ፖለቲከኞች አንዱ የሆነው ታላቁ የነፃነት ታጋይ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ለሥራ ጉዳይ ሲንቀሳቀስ የመንን እንደመሸጋገሪያ በሚጠቀምበት ወቅት በሰኔ 16 ቀን 2006 ዓ.ም. በየመን ሰንዓ ከተማ በሚገኘው አውሮፕላን ማረፊያ ላይ በሀገሪቱ መንግሥት ትዕዛዝ በፀጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር መሆኑን ለማወቅ ተችሏል:: ምንም አይነት ምድራዊም ይሁን ሰማያዊ መነሻ ምክንያት ለአቶ አንዳርጋቸው በየመን መንግሥት መታገት እና መታሰር ምክንያት ሊሆን እንደማይችል እንደማይገባም በመግለጽ የየመን መንግሥት የነፃነት ታጋያችንን ባስቸኳይ እንዲለቅ ላለፉት ተከታታይ ቀናት የተደረገው ሁሉን አቀፍ ጥረት ውጤት አላስገኘም:: ከዚህም በመነሳት አቶ አንዳርጋቸው ለዘረኛው እና ከፋፋዩ የወያኔ ቡድን ሊሰጥ ይችላል የሚለው ስጋታችን ቀን በገፋ እና ምላሽ በራቀ  ቁጥር እየጨመረ መጥቷል::
በግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል በኩል የነፃነት ታጋዩ ለወያኔ ተላልፎ መሰጠቱን መቶ በመቶ እስከምናረጋግጥበት ቅጽበት ታጋዩን የማስለቀቅ ጥረቱ መቀጠል እንዳለበት በጽኑ እናምናለን:: አንዳርጋቸውን ማሰር ይቻላል፤ ምናልባትም በዚህ ቅጽበት ተችሏል፤አንዳርጋቸውን ማሰቃየት ይቻላል፤ ምናልባትም በዚህ ቅጽበት ተችሏል፤ አንዳርጋቸውን መግደል ይቻላል። ሞትን ፈርቶ ወደ ትግል አልገባምና አንዳርጋቸውን በማሰር የአንዳርጋቸውን እንደ እቶን የሚያቃጥል የፍትህ፣ የነፃነት፣ የዴሞክራሲና የእኩልነት መንፈስ ግን ለሴኮንዶች እንኳን ማሰር አይቻልም። አንዳርጋቸውን በማሰቃየት ያን ዘመን ተሻጋሪ የሆነ የትውልዱን መንፈስ የሚገዛ የሁላችንም የምትሆን የጋራ ኢትዮጵያን የመፍጠር ንጹህ ራዕዩን ግን ፈጽሞ ማቁሰል አይቻልም!!! አንዳርጋቸውን በመግደል ዕንቁ ዓላማውን መግደል ከቶ አይቻልም፤ የታሪክ መዛግብት ገጾች ለዚህ ሃቅ በሚመሰክሩ እውነታዎች የተሞላ ነውና። አንዳርጋቸውን በመግደል “ከአባቶቹ የማይበልጥ ትውልድ እንዳልተፈጠረ  ይቆጠራል፣ ልጅ አባቱን ሩጦ መቅደም አለበት፣ ስለዚህ እናንተ ወጣቶች እኛን ሩጡ እና ብለጡ ቅደሙን፣ ቀናዎች ሁኑ፣ ርስ በርስ ተዋደዱ፣ ያለፉት ትውልዶች የሰሩትን ስህተት ላለመድገም ታሪክን ከስሩ ተረዱ፣ ያለማወቅ ጠንቅ ከሚያመጣው ጥፋት ለመዳን ሁሌም ለእውቀት ጉጉዎች ሁኑ። ለማወቅ ጣሩ፣ የማይቀረው ሞታችሁ ለፍትህ፣ ለዴሞክራሲ እና  ለነፃ ኢትዮጵያ ይሁን” እያለ ላለፉት በርካታ አመታት ያስተማራቸው እና የኮተኮታቸው የነፃነት ታጋይ አርበኛ  ወጣቶችን እና እሳት መንፈሳቸውን መግደል አይቻልም::
ታሪካዊ ስህተት በመሥራት በአዲሱ ትውልድ ልብ ውስጥ የበቀል እና የቂም ጓዝ ለማስቀመጥ እየተንደረደረ ያለው የየመን መንግሥትም ሆነ ወያኔ ሊያውቁት የሚገባው ተፈጥሯዊ ሃቅ ይህ ነው:: አንዳርጋቸውን በአንድ ካቴና በማሰር፤ በአንድ ክፍል ውስጥ በመዝጋት ወይም በአንድ ጥይት በመግደል “መገላገል” የሚቻል አንድ ግለሰብ አይደለም:: አንዳርጋቸው ለሽህ ካቴናዎች የማይታጠፉ እጆች፤ ለሽህ ማጎሪያዎች የገዘፈ ገላ፤ ለሽህ ጥይቶች የሰፋ እና ሽህ ጥይቶችን የሚተፋ ግንባር እና ደረት ያለው ብርቱ ታጋይ ነው። አንዳርጋቸው አንድ ግለሰብ አይደለም፤ የማይጨበጥ ጽኑ መንፈስ እንጅ!!!
አንዳርጋቸው ለአርባ አመታት በሚጠጋ የፖለቲካ ሕይወቱ ሁሉ በረሃ የሚወረወረው አፈር ላይ የሚንከባለለው፤ በእሱ እድሜ  በማይታሰብ ሁኔታ እንኳን የበረሃ ሃሩር፣ ጥም እና ረሃብ የሚያንገላታው ነገ ኢትዮጵያን በፕሬዝዳንትነት ወይ ደግሞ በጠቅላይ ሚኒስቴርነት ለመምራት ካለው ሰዋዊ ፍላጎት አይደለም:: የሱ ምኞት የሁላችንም የሆነች ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ማየት ነው!!! ይህን በተለይ የግንቦት ሕዝባዊ ኃይል አመራሮች እና መላው አባላት ጠንቅቀን እናውቃለን:: አንዳርጋቸው ሁሌ ለሚያልማት ንጽህት ኢትዮጵያ መሥራት የነበረበትን ፈታኝ እና ታሪካዊ ሥራዎች  ቀድሞ አከናውኗቸዋል:: ላለፉት 6 እና 7 ዓመታት ከጥልቅ የፖለቲካ  ተሞክሮው እየቀዳ ለወጣት ኢትዮጵያውያን በየበረሃው እየዞረ አስተምሯል:: እያማጠ አደራ ብሏል:: እያለቀሰ ምኞቱን፣ ፍላጎቱን እና ራዕዩን ከውስጡ አውጥቶ መዳፉ ላይ በማስቀመጥ ልቡን ለታዳጊዎች አሳይቷል:: ንጹህ ዓላማው ሽህ ባለ ራዕዮችን  ፈጥሯል የተግባር ሰዎችን አምርቷል:: የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል አንዳርጋቸው እንደመጥምቁ ዮሃነስ በበረሃ  እየዞረ ሲያስተምር እና  ሲሰብክ ከፈጠረው ንጹህ የኢትዮጵያዊነት መንፈስ ላይ የበቀለ ኃይል ነው::
ትናንት አብሮ ውሎ ዛሬ በድንገት መተጣጣት የትግል አንዱ ባህሪው ነውና ዛሬ አንዳርጋቸው በአካል አብሮን ላይኖር ይችላል:: ነፍሳችን ውስጥ ያሰረፀው ዘላለማዊ መንፈስ ግን እስከመጨረሻ ህቅታችን ድረስ አብሮን ይዘልቃል:: አንዳርጋቸውን በማስቆም ትግሉን አቆማለሁ ብሎ የሚያስብ ካለ ዓለምን እና ሁኔታዎችን መገንዘብ የማይችል ከራሱ የተጣላ የወያኔ አይነት ቂል ብቻ ነው:: አንዳርጋቸውን በማስቆም ትግሉን ማስቆም አይቻልም:: መንፈስን ማስቆም ከቶ ማን ይቻለዋል?? አንዳርጋቸው እኮ መንፈስ ነው:: ሁሉም ቦታ፣ ሁሉም ጫፍ ፣ሁሉም ልብ ውስጥ የሚገኝ እና የሚንሳፈፍ መንፈስ::
የየመን መንግሥት የፈጸመው ድርጊት እጅግ  ስህተት  መሆኑን  ዘግይቶም ቢሆን  ተረድቶ የነፃነት ታጋያችንን ባስቸኳይ ይለቀው ዘንድ አሁንም ደጋግመን እንጠይቃለን:: ይህ ሳይሆ ን ቀርቶ  ታጋያችን ወያኔ  እጅ ውስጥ ከገባ ግን የትውልዱ  የበቀል ሰይፍ ከዛሬ ጀምሮ ከሰገባው መውጣቱን እንዲያውቁት እንፈልጋለን:: ወያኔም ይህ የቂል ድርጊት የነፃነት ታጋዮችን የበለጠ ቁጭት እና የበቀል እርምጃዎች ውስጥ የሚከት መሆኑን አብሮ ሊገነዘበው ይገባል:: ለዚህ ቃላችን ታሪክ ምስክር  ይሁንብን::
ድል ለ ኢትዮጵያ  ሕዝብ!!!
source www.ginbot7Pf.org