Friday, February 28, 2014

ከባዶ ጭንቅላት ባዶ እግር ይሻላል!!!

የባህርዳር እና አካባቢው ሕዝብ ከባዶ ጭንቅላት ባዶ እግር ሺህ ጊዜ እንደሚሻል አካሉን ብቻ ሳይሆን ህሊናውንም ለትግራዩ ነፃ አውጪ ህወሓት ባርነት ላስገዛው “የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን)” እያለ እራሱን ለሚጠራው ድርጅት መሪዎች ተናገረ።
ባርነት ክፉ ነው። በባርነት ላይ የጭንቅላት ባዶነት ሲታከልበት ደግሞ አለምነው መኮንንን የመሰሉ የብአዴን መሪዎችን ይፈጥራል። የብአዴን መሪዎች ለጌታቸው ህወሓት ያላቸውን ታማኝነት ለማሳየት ራሳቸውን ማዋረዳቸው ሳያንስ እንወክለዋለን የሚሉትን ሕዝብ በጅምላ መስደባቸው ብአዴን እንደ ድርጅት የሚገኝበት የተዋረደ ደረጃ ያሳያል።
ህሊና ያለው ባርያ ዛሬ ነፃ ባይሆንም ወደፊት ነፃ የመውጣት ህልም አለው። ዛሬ በጉልበተኛ የባርያ አሳዳሪ ነፃነቱን ቢያጣም የህሊና ነፃነቱን ያላስደፈረ ባርያ ለነፃነት መታገሉ የማይቀር ነው። እንደ ብአዴን መሪዎች በታማኝ ባርያነቱ እየፈነጠዘ ያለ ባርያ ግን ነፃ ሰው የመሆን ህልሙንም ጭምር አጥቷል። እንዲህ ዓይነቱ ባርያ በአካልም፤ በመንፈስም ባሪያ ነው። ነፃ ሰው የመሆን እድል የለውም።
የአማራ ሕዝብ ብአዴንን የመሰለ አሳፋሪ ድርጅት በታሪኩ ገጥሞት አያውቅም። በፋሽስት ጣልያን ወረራ ጊዜ ለጠላት ያደሩ ባንዶች እንኳን ከዛሬዎቹ ብአዴኖች የተሻለ ክብር ነበራቸው። እነሱም ከዛሬዎቹም በተሻለ በጌቶቻቸው ጣሊያኖች ይሰሙ ነበር። በገዢዎቹ ለመወደድ የራሱን ሕዝብ የሚዘልፍ፣ የሚሰድብና የሚያዋርድ እንደ ብአዴን ያለ አዋራጅ ድርጅት በአማራ ምድር አልታየም።
ለዚህም ነው የባህርዳር እና አካባቢው ሕዝብ የብአዴንና የወያኔን አፈናዎችን በጣጥሶ የካቲት 16 ቀን 2006 ዓ.ም. ቁጣውን በባዶ እግሩ አደባባይ በመውጣት የገለፀው። እግር ባዶ መሆኑ ጭንቅላት ባዶ የመሆኑ ያህል የሚያሳፍር አይደለም። ድህነት ወንጀል አይደለም። ነፃ አዕምሮና የሕዝብ ይሁንታ ያገኘ አስተዳደር ካለ ድህነትን ማሸነፍ ይቻላል።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ ፈታኝ ሁኔታዎችን ተቋቁመው የየካቲት 16 ቀን 2006 ዓ.ምን ሕዝባዊ ተቃውሞ ላደራጁና በተቃውሞውም ለተካፈሉ ሁሉ ያለውን አክብሮት ይገልፃል። ሕዝብ ብሶቱን የሚገልጽበት ሕዝባዊ ተቃውሞ ማደራጀትና መምራት መቻል ትልቅ ነገር ነው። ሕዝባዊ ተቃውሞዎች ወደ ሕዝባዊ እምቢተኝነት የማደግ እድል አላቸው። ስለሆነም ግንቦት 7 ለባህርዳሩ ሕዝባዊ ተቃውሞ አደራጆችና ተሳታፉዎች “እንኳን ደስ ያላችሁ” በማለት የትግል አጋርነቱን መግለጽ ይሻል።
ግንቦት 7፣ ብአዴንን ከአባላቱ ለይቶ ማየት ይሻል። ከዚህም በተጨማሪ የብአዴንን ከፍተኛ አመራር ከሌላው ለይቶ ይመለከታል። ብአዴን ነፍሳቸውን ሳይቀር ለወያኔ በሸጡ ሰዎች የሚመራ፤ ነፃ የመውጣት ተስፋ የሌለው ራሱ ባርያ የሆነ ድርጅት ነው። አባላቱ ግን ከዚህ የተለዩ ሊሆኑ እንደሚችሉ ግንቦት 7 ያውቃል።
ግንቦት 7፡ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ከዚህም በፊትም ደጋግሞ እንደገለጸው፤ በተለያዩ ጊዜያት ራሳቸውን ከወያኔ ባርነት ነፃ ለማውጣት በወሰዱት እርምጃ መስዋእትነት የከፈሉ የብአዴን አባላት መኖራቸውን ያውቃል። ግንቦት 7 ለእነዚህ ቆራጦች ትልቅ አክብሮት አለው። ዛሬም ህሊናቸውን ሙሉ በሙሉ ያልሸጡ የብአዴን አባላት አሉ ብሎ ያምናል። እነዚህ ወገኖቻችን ራሳቸውን ነፃ ለማውጣት የግል፣ የወገንና የአገር ግዴታ አለባቸው ብሎ ያምናል።
ስለሆነም ዛሬም ይህንን አጋጣሚ ተጠቅመን ጥሪዓችንን እናድሳለን።
የብአዴን አባላት ሆይ!!! የገዛ ራሳችሁን፣ የአማራን ሕዝብ እና ኢትዮጵያን እያዋረደ ካለው ብአዴን ተላቀቁ፤ አሊያም እውስጡ ሆናችሁ ድርጅቱን ግደሉት። የብአዴን መኖር ለወያኔ ካልሆነ በስተቀር ለማንም አይበጅም። ነፃነት ካለ ድህነትን በሥራ ማሸነፍ ይቻላል። ሰው ባርያ ሆኖ በሀብት ቢንበሸበሽ ምን ይፈይድለታል?
የብአዴን አባላት ሆይ!!! ወደ ህሊችሁ ተመለሱ። ራሳችሁንም የበደላችሁትን ሕዝብ የመካስ እድል አድል አላችሁ ተጠቀሙበት። ይህንን ባታደርጉ ግን ለገዛ ራሳችሁ ፀፀት፤ ለልጆቻችሁ ሀፍረትን የምታወርሱ መሆኑን አትዘንጉ። ወያኔ መሸነፉ በጭራሽ የማይቀር መሆኑን እያወቃቸው በድህረ ጣልያን ወረራ ባንዶች ያገኙትን ምህረት እናገኛለን ብላችሁ አታስቡ።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!
source www.ginbot7.org

Thursday, February 27, 2014

Open letter to the President of Switzerland [Abebe Gelaw]

The Swiss Confederation
C/O Embassy of Switzerland
2900 Cathedral Ave. NW
Washington, DC 20008 
February 24, 2014
Dear President Didier Burkhalter,
Re: Ethiopian Co-Pilot Hailemedhin Aberra Tegegn
It is to be recalled that on Monday, February 17th 2014, a Boeing 767 Ethiopian Airlines commercial airliner, Flight ET702, which was en route to Rome, was diverted to Geneva, where it safely landed at 6:02 am (0502 GMT). As it has been widely reported, the airliner was diverted from its official route by the Ethiopian co-pilot, Hailemedhin Abera Tegegn, who made a request for political asylum in Switzerland while hovering over Geneva.  
Those of us who have gathered here today at the Swiss Embassy in Washington D.C. as well us so many others who have been unable to come due to work and other commitments, are eager to humbly appeal on behalf of our compatriot Hailemedhin Aberra Tegegn, who appears to have great faith in the fairness, judiciousness and hospitality of the people and government of Switzerland. Having first-hand experience of facing persecution in Ethiopia, we have little doubt that Mr. Tegegn was desperate not only to seek political asylum but also feel that he was evidently eager to attract global attention to the predicament and suffering of his fellow citizens in Ethiopia who are routinely being killed, jailed and tortured by the TPLF-led regime.
We would, therefore, like the government of Switzerland to consider the following facts, inter alia, in dealing with Mr. Tegegn’s case, as he clearly wanted to attract global attention to the plight and suffering of Ethiopians under the tyrannical minority regime in Ethiopia, the Tigray People’s Liberation Front (TPLF/EPRDF).  
1.      Ethiopia under the TPLF is one of the most repressive states in the world. Human Rights Watch, Amnesty International, Genocide Watch, UN Committee against Torture, the Committee to Protect Journalists, the U.S. State Department, the European Parliament, the United Nations Human Rights Council, among others, have repeatedly and consistently, though in vain, demanded the Ethiopian government to desist from committing crimes against humanity, gross human rights violations, extra judicial killings, mass displacement, torture and other forms of degrading mistreatment against innocent citizens.
2.      The government of Ethiopia abuses its own anti-terrorism proclamation to harshly and vengefully punish dissidents, journalists, religious leaders and activists. Hundreds of dissidents, Muslim rights defenders, civil rights leaders, activists and journalists have been charged with or convicted of terrorism offences in a bid to completely suppress dissident voices. So many of our compatriots are languishing in jails just for demanding freedom and respect for their basic rights.  
3.      Among those convicted of terrorism offences under the Draconian law, are three internationally acclaimed award-winning journalists who are languishing in hellish jails. Eskinder Nega, Woubishet Taye and Reeyot Alemu, who is gravely ill but denied medical assistance, were convicted of trumped-up terrorism charges and are currently serving lengthy sentences. In Ethiopia, there is no freedom of expression, freedom of peaceful assembly, freedom of religion or freedom of movement under the current regime despite the fact that they were proclaimed in the ostensible Ethiopian constitution, which is violated willfully by its own authors.
4.      The Ethiopian Airlines, where Mr. Tegegn was in employment, is widely known to have been undermined and crippled by unbridled corruption, nepotism and ethnic discrimination. There are reports that indicate that Mr. Tegegn was a victim of discrimination due to his unwillingness to join the ruling party and ethnic background, a requirement that has been pervasively and forcefully implemented in the public sector.
5.      We are confident that the Swiss government has extensive information on the widespread human rights violations in Ethiopia, a reality which has forced so many Ethiopians to take extreme measures to leave the country including crossing perilous terrains, deserts and treacherous waters to in search of safe heavens. It should be remembered that so many of our compatriots have lost their lives in deserts, seas and oceans. This is the Ethiopia that Mr. Tegegn wanted to flee with a sense of urgency and desperation. By doing so, he has made a huge political statement and a call for attention to our suffering at a global scale.   
While we acknowledge the unusual nature of Mr. Tegegn’s action and the inconvenience it created to the passengers, the airport as well as the country, it was clear that Mr. Tegegn had no intention of harming anyone. We are very grateful that he took utmost care so that nobody would be in harm’s way.  
We appeal to the government of Switzerland to treat his asylum application expeditiously and the legal matters with sympathy, compassion, leniency and humanity because his fear of persecution is clear and present like so many Ethiopians face on a daily basis. We also call upon the government of Switzerland to reject any extradition bid on the part of the criminal TPLF government that tortures, kills and treats Ethiopian citizens in degrading and inhuman manners.
We call upon the people and government of Switzerland to grant political asylum and afford him a safe haven that he so desperately pleaded in your country, which is respected and known not only for its principle of neutrality but also for being an important seat for so many international organizations and UN agencies. 
We look forward to a hearing positive outcome in Mr. Tegegn’s asylum case and legal matters.
With utmost regards,

Washington DC Ethiopian Joint Task Force.
Contact Person: Abebe Gellaw, Tel: +1 (650) 924-2540+1 (650) 924-2540, Email: dcjointtaskforce@gmail.com  


CC:
Office of the Attorney General of Switzerland
Amnesty International
Human Rights Watch
UN Committee against Torture
United Nations Human Rights Council
Genocide Watch
Refugees International
UNHCR
European Parliament
Various human rights and media organizations
Source www.quatero.net

Wednesday, February 26, 2014

የኢትዮጵያ ሴቶች ጉዳይ ሚ/ር ዘነቡ ታደሰ ዩጋንዳ የጸረ ጌይ ሕግ ማውጣቷን ተቹ

(ዘ-ሐበሻ) ኢትዮጵያ የሴቶች ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት ዘነቡ ታደሰ ኡጋንዳ የጸረ ጌይ አዋጅ ማውጣቷን መተቸታቸውን ሃፊንግተን ፖስት የተባለው ጋዜጣ ሚኒስትሯ በትዉተር ገጻቸው የጻፉትን አስተያየት አያይዞ ባቀረበው ዘገባው አስታወቀ። እናት ድርጅታቸው ኢሕአዴግ ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ የአፍሪካ ጊዮች ስብስባ እንዲደረግ መፍቀዱና በጁፒተር ሆቴል ይደረጋል በተባለው በዚህ ስብሰባ ከፍተኛ ተቃውሞ መነሳቱ ይታወሳል።
በትዊተር ገጻቸው ዘነቡ ታደሰ ኡጋንዳ የጸረ ጌይ (ጸረ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን) አዋጅን ካጽደገቀች በኋላ በእንግሊዘኛው There is no place for hate, discrimination in my beloved Africa. It’s not Governments’ business to make dress code or anti-gay laws #Uganda.” ብለው ጽፈዋል ያለው ሃፊንግተን ፖስት የኡጋንዳን መንግስት ሕጉን በማጽደቁ ተችተዋል ብሏል።
“ስለአለባበስም ሆነ የጸረ ጌይ ሕግ ማውጣት የመንግስት ጉዳይ መሆን የለበትም” በሚል የተናገሩት የኢትዮጵያ የሴቶች ጉዳይ ሚኒስተር ዘነቡ ታደሰ የጌይን ሕግ መጽደቅ ይደግፋሉ በሚል መነጋጋሪያ ሆነዋል።
ዘነቡ ታደሰ በትዊተር ገጻቸው የጻፉት የሚከተለው ነው፦
source Ze -Habesha

Monday, February 24, 2014

የኢትዮጵያን ገጽታ አደባባይ ያወጣው አውሮፕላን አብራሪ ሃይለመድህን አበራ (ዳኛቸው ቢያድግልኝ)

ልማታዊ ግስጋሴ እስከ ግድበ ህዳሴ በደረሰበት ታሪካዊ ወቅት፣ ኢትዮጵያ በፈጣን የእድገት መስፈርት ውስጥ ከአፍሪካ አንደኛ ከአለም
ከቻይና ቀጥሎ ሁለተኛ ነች እየተባለ በመሪዎቿ በሚነገርላት ጊዜ። አሸባሪዎችን ከመነሻቸው ለማምከን በአይነቱ ልዩ የሆነ የአንድ
ለአምስት አደረጃጀት የሰዎችን ድርጊት ብቻ ሳይሆን አስተሳሰብን ጭምር የሚመረምር ምትሃታዊ ሃይል ተደራጅቶ ባለበት ሁኔታ
የዴርቶጋዳን ልብወለድ መሰል ነገር መታየቱ ብዙዎችን አስደምሟል። ለመሆኑ የዛሬ ልጆች ጀግና አይደሉም የሚል ማን ነው?
በውጭ ሃገር የዜና ማሰራጫዎች ወሬው እንደተሰማ አስተያየት ለመክተብ ጣታቸው እንደ ክላሺኒኮቭ ፊደል የሚያንጣጣ ሁሉ ፓይለቱ
ጥገኝነት ለማግኘት ብሎ እንዲህ ማድረጉ አሳፋሪ ነው፣ አላዋቂ አፍሪካዊ መሆን አለበት፣ ይቀጣ! ይቀጣ! የሚሉ ሃረጎች በርክተው
ነበር። እነዚህ በአብዛኛው አፍሪካ ማለት አንድ ሃገር የሚመስላቸው የእውቀት ብርሃን የጨለመባቸው ናቸውና ምንም ማድረግ
አይቻልም።
ሁለተኛው ሰሞኑን ነገረ ስራው አያምርም ነበር የሚልና አእምሮው ለየት ያለ ነገር የሚያሳየው ‘ሺዞፍሬንያ’ እሚሉት ነገር
እየጀማመረው ነበር የሚለው ነው። እህት ሁሉም ይስማልኝ በማለት በመረጃ መረቦች በተነች የሚባለውን ያነበበ ሰው ለበረራ ብቁ
ነው የሚለውን ፈቃድ ሰጪም ወፈፍ ያደረገው መሆን አለበት ቢል አላጋነነም። ይሄ እብድ እየመሰለ ሲሰልል የኖረ ወያኔ ወፈፌነትን
በጣም ስለተለማመደው አማኑኤል ሆስፒታልን የደህንነት ማሰልጠኛ ኮሌጅ አድርጎ ቢመለከት አይፈረድበትም ብለን መሳቅም
መብታችን ነው። ቁም ነገሩ ግን የበረራውን ደህንነት ለማስጠበቅ የአብራሪዎችንምጤናና ደህንነት መከታተል ስለሚገባው ያንንም
ማድረግ ባለመቻሉ ወደ ትልቅ ስህተት ራሱን እየጨመረ ነው። በዚህ ሁኔታ ምን ያህል ወፈፌ ፓይለቶች ይኖሩ ይሆን ብሎ
መጠየቅም ያስፈልጋል። ከሆነም ምን አይነት አስተዳደር ቢኖር ነው ጨርቅ ጥሎ የሚያሳብደው፣ ሃገር ጥሎ የሚያስኮበልለው ብሎ
መጠየቅም ተገቢ ነው። የአይጥ ምስክሯ ድንቢጥ እንደሚባለው በአንድ-ለአምስት ተጋግዞ መዋሸት ይቻል ይሆናል ከዚያ መረብ ውጪ
ላለነው ግን አስቂኝ ትዕይንት ነው።
እኔ አውሮፕላኑን ጠለፈ የሚለው አገላለጽ እጅግም አልተመቸኝም። ረዳት አብራሪው ድምጼ ይሰማልኝ በማለት ማቆም የማይገባው
ስፍራ ላይ አውሮፕላኑን አቆመ ለዚያውም ያለ ፍርሃትና ሽብር መደናገጥና መርበትበት ተሳፋሪውም ኮሽታ ሳይሰማ። አቅጣጫ
በቀየረው አውሮፕላን ውስጥ የነበሩ ሰራተኞች ለተሳፋሪዎቻቸው ቡና ሻይ እያቀረቡ ምቾታቸውን እየጠበቁ ዋናው አብራሪ
ጋዜጣቸውን እያነበቡ ምቾታቸው ሳይጓደል አረፉ። ተሳፋሪዎች የሆነውን ሁሉ ሳያዩ ረዳቱ አብራሪ በገመድ ወርደው ለፖሊሶች
እጃቸውን ሰጡ። እንግዲህ የአእምሮ በሽተኛ እንደዚህ ከሆነ ተጋግዘን ብንታመምስ ምን ነበረበት?
ረዳት አብራሪው ሃይለመድህን አበራ ማስተላለፍ የፈለገው መልዕክት ስለመኖሩ መጠራጠር አውቆ መጨፈን ይሆናል። በአንድም
ይሁን በሌላ መልኩ የሀገሪቱ አስተዳደርን ገጽታ የሚያበላሽ ድርጊት ተከናውኗል። ስለምን የሃገሪቱን ገጽታ የሚያጎድፍ እንደሚባል
አይገባኝም። የሀገሪቱን ገጽታ የሚያጠለሹት ጎጠኞችና አምባገነኖች ናቸው። የነርሱ አስተዳደር መበስበሱን፣ ሁሉንም ዘርፍ ማለትም
ብዙሃኑን የሀገሪቱ ሕዝብ ማሳዘኑን በዚህም ምክንያት ምሬት መኖሩን ነው ይህ ወንድማችን አደባባይ ያወጣው። አዎ የአስተዳደሩን
ብልሹነትና እንዳይድን ሆኖ መታመም ነው አደባባይ ያወጣው። ስለዚህ የኢትዮጵያ ገጽታ ሳይሆን ዓለም የተመለከተው የአስተዳደሩን
መጥፎነት ነው።
ቤተሰቦቹ ተገድደው የሚያወጧቸው መግለጫዎች ይበልጥ የሚያጋልጡት ይህ ማፍያ ቡድን እስከምን ድረስ ሊሄድ እንደሚችልና
በቤተሰብ ችግርና ሃዘን ውስጥ እንኳን በመግባት ሊፈጽም የሚችለውን አረመኔያዊ ድርጊት ነው። ቤን የሚሉት ለማጅ ጋዜጠኛ ወሎ
ሄዶ ባላቸውን አለቆቹ ገድለው እርሱ ደግሞ በሙስሊም አክራሪዎች እንደተገደሉ ለማስመሰል ሃዘንተኛዋን ባለቤት ሌላ ፖለቲካ
ሲያሰራ እንደነበረው ያለ ዜናን ማስታወስ ተገቢ ነው። ያለንበት ዘመን የራሽያ አብዮት የፈነዳበት ጊዜ አይደለም በአይነቱ በተለይም
በመረጃ ቅብብሎሹ ረገድ እጅግ በጣም የተለየ ዘመን ነው። የዚያን ጊዜ ታክቲክ በመጠቀም አሁን የሚታየውን አመጽ ማፈን
አይቻልም። ይልቁኑ እብዶቹ መንግስት ነኝ ባዮችና ወፈፌዎቹ ጋዜጠኛና ካድሬዎች ከአሳፋሪ ተግባር ቢታቀቡ ነው የሚሻላቸው።
ረዳት አብራሪው ሃይለመድህን አበራ ቃል ሳይተነፍስ ማለት የሚፈልገውን የተናገረ ይመስለኛል። የምቾት ህይወትን ትቶ ሙያውን
ተሰናብቶ መሄዱ ጀግንነት ነው። የብዙዎችን ሰቆቃና ቁጣ ያለውን የአስተዳደር በደልና ዘረኛነት ማጋለጡ ጀግንነት ነው። ራሱን ከዚህ
ጨቋኝ ስርዓት ነጻ ማውጣት ለርሱ ቀላል እጅግ በጣም ቀላል ነገር ሆኖ ሳለ በሙያው በክህሎቱ የአለምን ትኩረት የሚስብን ነገር
የአንድ ሰው ሕይወት ሳያጠፋ ማስተላለፍ መቻሉ ጀግንነት ነው። ይልቁንም ደግሞ የታወከ አእምሮ ኖሮ(አዋኪውና አስቀዋሹ ምክንያት
ምን እንደሆነ ይታወቃልና) በዚህ አይነት የተረጋጋ መንፈስ እንዲህ ያለ መልዕክት ማስተላለፍ መቻሉ ይበልጥ አስደናቂ ያደርገዋል።
ምናልባትም በሽታ መሆኑ ቀርቶ ልዩ ስም የሚሰጠው የመንፈስ ጥንካሬ ተብሎ የሚታወስ ይሆናል። ለወንድማችን ሃይለመድህን አበራ
መልካም ጤንነትና ፍትህን እመኛለሁ። ቤተሰቡና ወዳጆቹ ተመሳሳይ የመንፈስ ጥንካሬ ያድርባቸው ዘንድም አሳስባለሁ።
biyadegelgne@hotmail.com
source www.ethiomedia.com

Saturday, February 22, 2014

የመከላከያ ተቋም ተግባር አገርን መጠበቅ ነዉ ወይስ አገርን መዝረፍ?

የአዉሮፓ ቅኝ ገዢዎች አፍሪካን ሲቀራመቱ ባህር ተሻግረዉ በመጡ የነጭ ባዕዳን ኃይሎች መገዛትን መርጦ የአዉሮፓን ወራሪዎች በሰላም በሩን ከፍቶ ወደ አገሩ ያስገባ እንድም የአፍሪካ አገር አልነበረም፤ የኋላ ኋላ ተሸንፈዉ በቅኝ አገዛዝ ቀንበር ስር ቢወድቁም ሁሉም የአፍሪካ አገሮች እንደ አቅማቸዉ ከወራሪ ኃይሎች ጋር ተፋልመዋል። በአንድ ወቅት የቅርብ ጎረቤቶቻችንን ጨምሮ ብዙዎቹ የአፍሪካ አገሮች በወራሪ ኃይሎች ተሸንፈዉ የቅኝ ገዢዎች ቀንበር ጀርባቸዉ ላይ ሲጫን አገራችን ኢትዮጵያ ብቻዋን የአለም ጥቁር ህዝቦች የነፃነት ተምሳሌት ሆና የኖረችዉ ጣሊያኖች፤ እንንግሊዞችና ፈረንሳዮች ከሌሎች የአፍሪካ አገሮች ለይተዉ ስለወደዷት ወይም ስላከበሯት አይደለም። ይልቁንም ነፃነታችንና የግዛት አንድነታችን ተከብሮ የኖረዉ ኢትዮጵያ እናት አገሩ በጠላት ስትደፈር ከሚያይ ምትክ የሌላት ህይወቱ ብታልፍ ደስ የሚለዉ የኩሩና የጀግና ህዝብ አገር በመሆኗ ነዉ። የሚገርመዉ ይህ ኩሩና ጀግና ህዝብ ጣሊያንን የመሰለ በዘመናዊ መሳሪያ የታጀበ ኃይል ዉርደቱን ተከናንቦ ወደመጣበት እንዲመለስ ሲያስገድድ እንደ ዛሬዉ የተደራጀ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት አልነበረዉም። ዛሬ አራት ኪሎና ስድስት ኪሎ ላይ የተተከሉት ሁለቱ ታሪካዊ ሀዉልቶቻችን የሚነግሩንም ይሀንኑ የኢትዮጵያ ህዝብ በዘመናዊ መልክ የተደራጀ ሠራዊት ሳይኖረዉ የጎበዝ አለቃ እየመረጠ በጣሊያን ፋሺስቶች ላይ የተጎናጸፈዉን አኩሪ ድል ነዉ።
ኢትዮጵያ ዉስጥ ዘመናዊና የተደራጀ መከላከያ ሠራዊት ጥንስስ የተጣለዉ በዳግማዊ ሚኒልክ ዘመነ መንግስት ሲሆን እሱም ቢሆን ከአድዋ ድል በኋላ ቆይቶ የመጣ ክስተት ነዉ። በአፄ ኃ/ሥላሤና በደርግ ዘመነ መንግስት ኢትዮጵያ ለአንድ ፓርቲና ይህ ፓርቲ እወክለዋለሁ ለሚለዉ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ሙያዊ ብቃት የነበረዉ፤ሙያዉን የሚያከብርና ለአገሩና ለወገኑ ታማኝ የሆነ የመከላከያ ሠራዊት ነበራት። የወያኔ ዘረኞች አዲስ አበባን ሲቆጣጠሩ የመጀመሪያ ኢላማቸዉ አድርገዉ ካወደሟቸዉ ዋና ዋና የአገራቸን ተቋሞች ዉስጥ የመጀመሪያዉ ይሄዉ የአገርና የህዝብ ደጀን የነበረዉ ተቋም ነበር። ዛሬ ኢትዮጵያ ዉስጥ የአገር መከላከያ ሠራዊት እየተባለ የሚጠራዉ ተቋም ለጎጠኞች ጥቅምና የስልጣን መራዘም የቆመ፤ በዘረኝነት የተካፋፈለ፤ ይህ ነዉ ተብሎ የሚጠቀስ ሙያዊ ብቃት የሌለዉና የወገንና የአገር ፍቅር እንዳይኖረዉ ተደርጎ የተደራጀ ሰራዊት ነዉ። ይህንን ሠራዊት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ሳይሆን የወያኔ ሠራዊት እያልን የምንጠራዉም በዚሁ ምክንያት ነዉ።
ዛሬ ሙሉ በሙሉ በወያኔ ዘረኞች ቁጥጥር ስር የወደቀዉ የአገር መከላከያ ተቋም የሚታማዉ በዘረኝነት፤ በሙያ ብቃት ማነስና የአንድ ፓርቲ ጥቅም አስከባሪ በመሆኑ ብቻ አይደለም፤ ተቋሙ ከእነዚህ ዋና ዋና ጉድለቶቹ በተጨማሪ በቀድሞዉ የኢትዮጵያ መከላከያ ተቋም ላይ በፍጹም ያልታዩ ሌሎች ትላልቅ ጉድለቶች አሉበት። ከእነዚህ ጉድለቶች ዉስጥ አንዱ የወያኔ የመከላከያ ተቋም ህገ መንግስቱ ከሰጠዉ ኃላፊነት ዉጭ በንግድና በንብረት ይዞታ ላይ ላይ መሰማራቱ ሲሆን ሁለተኛዉ ደግሞ ከዚህ ፀባዩ ጋር ተያይዞ በመከላከያ ሠራዊት ተቋም ዉስጥ ከላይ እስከታች የሰፈነዉ ቅጥ ያጣ ሙሰኝነት ነዉ። ዛሬ የወያኔን የመከላከያ ተቋም፤ የህወሀትን ፓርቲና ኤፎርት በሚል ምህጻረቃል የሚታወቀዉን የወያኔን የገንዝብ ማምረቻ ድርጅት ነጣጥለን ወይም አንዱን ከሌላዉ ለይተን ማየት የማንችልበት ደረጃ ላይ ደርሰናል።
በላፈዉ አመት ወያኔ እራሱ ያቋቋመዉ ፀረ ሙስና ኮሚሺን የገንዘብ ዝርፊያን፤የንብረት መባከንንና መዝረክረክን አስመልክቶ ለፓርላማዉ ባቀረበዉ ሪፖርት ላይ ከጠቀሳቸዉ መንግስታዊ ተቋሞች ዉስጥ ቀዳሚዉን ደረጃ የያዘዉ የመከላከያ ተቋም ነዉ። ሆኖም ፓርላማዉም ሆነ የወያኔ አገዛዝ ለዚህ ሪፖርት የሰጡት ምላሽ የመከላከያና የደህንነት ተቋሞች ከአሁን በኋላ ያሻቸዉን ያክል ገንዝብ ቢዘርፉ የሂሳብ መዝገባቸዉ “ለአገር ደህንነት” ሲባል በኦዲት ኮሚሺን አይመረመርም የሚል ምላሽ ነበር። እንግዲህ ይህ በሙሰኝነት የተጨማለቀ፤ ለህግ የማይገዛና መጠበቅና መንከባከብ የሚገባዉን የአገር ኃብትና ንብረት የሚዘርፍ ተቋም ነዉ ባለፈዉ ሳምንት “የመከላከያ ቀን” ተብሎ አመታዊ በዐል የተከበረለት።
መናገሻ ከተማችን አዲስ አበባ ዉስጥ በየቦታዉ የሚታዩትን ሰማይ ጠቀስ ህንፃዎች ሰርተዉ የሚያከራዩት የወር ደሞዛቸዉ ከ2500 ብር የማይበልጥ መከላከያ ሠራዊት ዉስጥ የተሰገሰጉ የወያኔ ጄኔራሎች ናቸዉ፤ኢትዮጵያ ዉስጥ ትርፋማ በሆኑ ቦታዎች ሁሉ ትላልቅ ሆቴሎች፤ የአገልግሎት ተቋሞችና የንግድ ድርጅቶች ከፍተዉ ቁጥር ስፍር የሌለዉ ኃብት የሚያጋብሱት የወያኔ ጄኔራሎች ናቸዉ፤ ድሃዉና የወያኔ ዘረኝነት ሰለባ የሆነዉ ኢትዮጵያ ሰራዊት ለተመድ ተልዕኮ በተሰማራባቸዉ ቦታዎች ሁሉ ተመድ የሚከፍለዉን የቀን አበል ኪሳቸዉ ዉስጥ እየከተቱ ሚሊዮነሮች የሆኑትና በየዉጭ አገሩ ዉድ መኖሪያ ቤቶችንና የንግድ ተቋሞችን የሚገዙት የወያኔ ጄኔራሎች ናቸዉ። የወያኔ መከላከያ ተቋም ጉድ በዚህ ብቻ አያበቃም፤ ይህንን ወንጀለኛ ተቋም ቃላት እየደረደሩ ለመግለጽ ከመሞከር ይልቅ በጥቅሉ ወያኔ የኢትዮጵያን ህዝብ ኃብትና ንብረት እንዳሻዉ መዝረፍ እንዲችል የኃይል ሽፋን የሚሰጥ ተቋም ነዉ ማለት የሚበቃ ይመስለናል።
ወያኔና ስር የሰደደዉ ዘረኛ ስርዐቱ ከኢትዮጵያ ምድር ላይ እስካልተነቀሉ ድረስ ወያኔ ዝርፊያዉን የወያኔ መከላከያ ተቋምም የወያኔንና የደገፊዎቹን ዝርፊያ በመሳሪያ ማጀቡ አይቆምም። የወያኔን ዝርፊያ ለማስቆምና አገራችንን ከተጋረጠባት አሳሳቢ አደጋ ለመታደግ ብቸኛዉ መንገድ ወያኔን ከሥልጣን ማስወገድ ብቻ ነዉ። ግንቦት 7 የፍትህ፤የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የጀመረዉ ህዝባዊ ትግል እንደ አገር መከላያከያ አይነቶቹ ቁልፍ የአገር ተቋሞች በሚሰሯቸዉ ስራዎች ሁሉ የአገርንና የህዝብን ጥቅም እንዲያስጠብቁ ለማድረግ ነዉ። የግንቦት 7 ትግል አላማ የመከላከያ፤ የደህንነት፤ የፖሊስና የፍትህ ተቋሞች የአንድ ፓርቲ ጥቅም ማስከበሪያ መሳሪያዎች መሆናቸዉ አብቅቶ የአገርና የህዝብ አለኝታ እንዲሆኑ ነዉ፤ ሆኖም ይህንን ቅዱስ አላማ ወያኔ በስልጣን ላይ እስካለ ድረስ ተግባራዊ ማድረግ ስለማይቻል ነፃነት፤ ፍትህ፤ዲሞክራሲ፤ ሠላምና እኩልነት የናፈቀዉ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ወያኔን በፍጥነት እናስወግድ ከሚለዉ የአገር አድን አላማ ጎን እንዲሰለፍ ግንቦት 7 የትግል ጥሪዉን ያስተላልፋል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

የሸፍጥ ክርክር የሃሰት ክምር የታሪክን እውነታ አይቀይርም! ከኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚ ቴ
Ethiopian Border Affairs Committee P. O. Box 9536 Columbus, Ohio 43209 USA E-mail: ethiopianborders@gmail.com
የሸፍጥ ክርክር የሃሰት ክምር የታሪክን እውነታ አይቀይርም!
ከኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ የካቲት 15 ቀን 2006 ዓ/ም ( February 22, 2014 )
I. መግቢያ:
የካቲት 3 ቀን 2006 ዓ/ም የወያኔ/ኢሕአዴግ ሊቀ-መንበርና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ለአገር-ውስጥ
ጋዘጤኞች በሰጡት መግለጫ ላይ የኢትዮ-ሱዳን ድንበር ጉዳይን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ በድፍረት የሰጡት ምላሽ የኢትዮጵያ
ድንበር ጉዳይ ኮሚቴን ብቻ አይደለም መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ በእጅጉ ያሳዘነና ያሳፈረ ሆኖ አግኝተነዋል። በቀድሞው ጠቅላይ
ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እግር የተተኩት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የተረከቡት የመንግሥት ሥልጣንን ብቻ ሣይሆን ለኢትዮጵያ ሕዝብ
ከበሬታ-አልባነትንም በሚመስል መልክ ነው ይህንን በጣም የተምታታ፤ በተቃርኖዎች የተሞላና በእጅጉ ኃላፊነት-የጎደለው ጋዜጣዊ-
መግለጫ የሰጡት።
የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ ባደረገው ያላሰለሰ ክትትል የወያኔ/ኢሕአዴግ መንግሥት ከሱዳን
መንግሥት ጋር የሕዝብን መሠረታዊ-ሉዓላዊነት በሚዳፈርና ዘለቄታዊ ጥቅሙን ለባዕድ አሣልፎ በሚሰጥ ሁኔታ እየሸረበ ያለውን ደባና
እየፈጸመ ያለውን አሣፋሪ ድርጊት በተገቢ ጥናትና በጠራ-መረጃ ላይ ተመሥርቶ በተከታታይ ባወጣቸው መግለጫዎች እንዲሁም
በልዩ-ልዩ መገናኛ-ብዙኃን አማካይነት ለኢትዮጵያ ሕዝብ፤ ለወያኔ/ኢሕአዴግ መሪዎችና ልዩ-ልዩ ተቋማት፤ ለሱዳን መንግሥትና
ለዓለም-አቀፉ ማኅበረሰብ ጭምር ሲያሳውቅ መቆየቱ ይታወቃል። የወያኔ/ኢሕአዴግ መሪዎች ግን አሁንም በዚህ የአገር ድንበርን
በሚያክል ከባድ ጉዳይ ላይ ከዋናው ባለ-ጉዳይ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጀርባ የጀመሩትን እኩይ ተግባር እየገፉበት አንደሆነ ከራሣችው
አንደበት እየሰማን ነው።
II. የመግለጫው ዓላማ፤
የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ በሚከተሉት ምክንያቶች ከላይ የተጠቀሰውን የአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ንግግር በተመለከተ ይህንን
መግለጫ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ አግኝቶታል።
ሀ). ከማንኛውም አገርና መንግሥት መሪ በተለይም የውጭ ግንኙንትን በተመለከተ የሚሰነዘር አስተያየትም ሆነ የሚሰጥ መግለጫ
የአገር አቋም ተደርጎ የሚወሰድና በዋቢነትም የመጠቀስ መዘዝን ያዘለ በመሆኑ በዝምታ ሊታለፍም ሆነ ‘አጉል-መዘላበድ’ ተደርጎ ችላ
ሊባል የሚችል ጉዳይ ባለመሆኑ፤
ለ). በዚህ የወያኔ/ኢሕአዴግ መንግሥት ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጀርባ እየፈጸመ ባለው በአገር-ክህደት የሚያስጠይቅ፤ ሕዝብን የናቀ
የድፍረት አርምጃና ሕገ-ወጥ ድርጊት አገራችን ኢትዮጵያ አንጡራ መሬቷ ለባዕድ አሣልፎ እየተሰጠ መሆኑ ምንም ዓይነት ተቀባይነትም
ሆነ አግባብነት የሌለው ብቻ ሣይሆን የማንኛውም ኢትዮጵያዊ ጉዳይና ሁሉም በግልጥ ሊረዳው የሚገባ መሆኑን ከአሁን በፊት
በተደጋጋሚ መግልጫዎች የሰጠነበት ቢሆንም አሁንም በድጋሜ ማሳሰቡ አስፈላጊ ስለሆነ፤
ሐ). አፄ ቴዎድሮስ፤ ንጉሥ ተክለ-ኃይማኖትና አፄ ዮሐንስን የመሳሰሉ ታላላቅ መሪዎች እየታገሉና ክቡር መስዋዕትነት እየከፈሉ
አስከብረውት የቆየውንና በአካባቢው ሕዝብ የመረረ ተጋድሎ ታፍሮና ተጠብቆ የኖረውን የሱዳን ወሰን በድብቅ ስምምነት ለባዕድ
አሣልፎ ለመስጠት የሚደረግ ሕገ-ወጥ ውል ውሎ-አድሮ የሚያስከትለው መዘዝ በቀላሉ የማይታይ ከመሆኑም በላይ፤ ይህንን በመሰለ
ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጀርባ በተፈጸመ ውል ድንበር ለማካለል የሚወሰድ እርምጃ ሁለቱን እህትማማች አገሮች ወደ-አይቀሬ ጦርነት
የሚወስድና ይህም ኢትዮጵያና ሱዳን በመልካም ጉርብትና መርኅ ተከባብረው እንዳይኖሩ፤ የውስጥ ሰላማቸውንና እድገታቸውን
ወደሚያደናቅፍ ያላስፈላጊ ችግር ውስጥ ከማስገባት አልፎ ለአካባቢው ሰላምና መረጋጋት ከፍተኛ ጠንቅ እንደሚሆን ሁሉም
ሊያውቀው ስለሚገባ፤
መ). የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ የወያኔ/ኢሕአዴግ መሪዎች በሱዳን በኩል ያለውን የአገር ወሰን በተመለከተ በድብቅ
የሚያደርጉትን የክህደት ተግባር በወቅቱ ማጋለጥና ማክሸፍ ተገቢና የማንኛውም ኢትዮጵያዊ የዜግነት ግዴታ እንደሆነ በተደጋጋሚ 2

የሚያሳስበውና የሚታገለው፤ ይህ ሕገ-ወጥ እርምጃ በሌሎች አካባቢዎች ያሉ ድንበሮቻችን እንዲደፈሩና አገራችን ኢትዮጵያ አንጡራ
መሬቶቿን በተመሣሣይ ሁኔታ እንድታጣ በር-ከፋች ማስረጃ ሊሆን እንዳይችል ለማድረግም ጭምር ስለሆነ፤
ሠ). ይህንን ድብቅ ሴራ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በትክክል እንዲያውቀውና በተለይም የአገሩን ዳር-ድንበር የማስከበር ኃላፊነት
ያለበት የአገሪቱ የመከላከያ ኃይልና የአገር-ደኅንነት ክፍል አባላት የወያኔ/ኢሕአዴግ መሪዎች አሳፋሪ በሆነ መልኩ በተሳሳተ መረጃ ላይ
ተመሥርተው የአገራቸውን አንጡራ መሬት ለባዕድ አሳልፈው ለመስጠት የሚያደርጉትን የአገር-ክህደት ተግባር በትክክል ተረድተው
ከሕዝባቸው ጎን አንዲቆሙና የአገራቸውን ዘለቄታዊ-ጥቅም የማስከበር መሠረታዊ የሙያ፤ የተቋምና የዜግነት ግዴታቸውን አንዲወጡ
ማሳሰቡ አስፈላጊ በመሆኑ፤
ረ). በአገራችን የሥርዓት-ለውጥ እንዲኖር የሚታገሉ ድርጅቶች ለዚህ ዓብይ አገራዊ ጉዳይ የተባበረ ምላሽ ለመስጠት የሚያደርጉትን
እንቅስቃሴ በአገራዊ አንድነት መንፈስና በተቀናበረ ሁኔታ እንዲሆን ለማሳሰብ፤…ነው።

III. ጭብጦች፤
ሀ.) በአቶ ኃይለማርያም ደሳልኝ / ኢሕአዴግ በኩል፤
1ኛ) አቶ ኃይለማርያም በዚህ መግለጫቸው ከእሳቸው በፊት የነበሩት የወያኔ/ኢሕአዴግ ጠቅላይ-ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ግንቦት 13 ቀን
2000 ዓም የሕዝብ-ተወካዮች ምክር-ቤት ፊት ቀርበው ምንም ዓይነት ታሪካዊ ማረጋገጫ ሳይኖራቸውና ያለ-አንዳች ሃፍረት ያሉትን
በመድገም ከአፄ ምኒልክ ጀምሮ እስከ ደርግ የነበሩት የኢትዮጵያ መንግሥታት ሁሉም የሻለቃ ግዌንን መሥመር እንደተቀበሉና
እንደተስማሙ፤
2ኛ) የእሳቸውም መንግሥት ወያኔ/ኢሕአዴግ ይህንኑ የግዌን የወሰን ክለላ መሥመር እንደሚቀበል፤ በተግባር የመተርጎም ግዴታ
እንዳለባቸውና ለዚህም ዝግጁ መሆናቸውን፤
3ኛ) ይህን ተግባራዊ ለማድረግ በሚደረገው ሂደት አንድም የተፈናቀለ ኢትዮጵያዊ እንደሌለና ወደፊትም ሊኖር እንደማይችል፤
4ኛ) የሱዳንን ታጋሽነት በማወደስና የኢትዮጵያን ‘የተስፋፊነት’ አቋም በማውገዝ፤ ሃቁን በመካድና ታሪክን በማጣመም አሁን ሱዳን
ይገባኛል የምትለውና የወያኔ/ኢሕአዴግ መንግሥትም ለማስረከብ የተዘጋጀው መሬት ቀደም-ሲል በሱዳን ይዞታ ሥር የነበረና
የቀድሞው የግብፅ ፕሬዝደንት ሆስኒ ሙባራክ ኢትዮጵያን በሚጎበኙበት ወቅት በተካሄደው የግድያ ሙከራ ሳቢያ በኢትዮጵያና በሱዳን
መኻል የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ ‘ሱዳኖች የለቀቁትን መሬት ኢትዮጵውያን ገበሬዎች አልፈው ሲያርሱት የነበረውን’ አንደሆነ፤
5ኛ) በሁለቱ አገሮች መኻል ያሉ ልዩ-ልዩ የጋራ ጉዳዮችን በተመለከተ ከሁለቱም አገሮች የተሰየሙ ኮሚቴዎች በቋሚነት እየተገናኙ
ምክክር ከማድረግና ውሎችን ከመዋዋል ውጪ በአሁኑ ጊዜ የተከለለ መሬት እንደሌለ፤
6ኛ) ይህንን ኢትዮጵያ ለሱዳን መሬት አሳልፋ ሰጠች የሚለው ‘አሉባልታ’ በአገሪቱ በየአምስት ዓመት የሚደረገውን የምርጫ ወቅት
እየጠበቀ ለፖለቲካ ፍጆታ ሲባል በወያኔ/ኢሕአዴግ ላይ የሚነዛ ወሬ እንደሆነ፤…
የእሣቸውንና የመንግሥታቸውን አቋም ሲያሣውቁ፤ በአጠቃላይ የአቶ ኃይለማርያም ደሳልኝ መግለጫ ይዘት ከአሁን በፊት አቶ መለስ
ታሪክን በመከለስና ሃቁን በማድበስብስ የተናገሩትን በአዲስ መልክ በመድገም የኢትዮጵያን አንጡራ መሬት ለሱዳን አሣልፎ ለመስጠት
የወያኔ/ኢሕአዴግ መሪዎች ያላቸውን አቋምና እምነት፤ ይህንንም በተግባር ለመተርጎም የደረሱበትን ውሳኔ ይፋ ያደረገና በኢትዮጵያ
ላይ ምስክርነት የሰጠ ሆኖ አግኝተነዋል።
ለ.) በኢትዮጵያ ሕዝብ በኩል፤
1ኛ) የአውሮጳ ቅኝ-ገዥዎች ያለ-አፍሪቃውያን ተሣትፎና ይሁንታ የአፍሪቃን ምድር እንዳሻችው ሲቀራመቱ በነበረበት ወቅት ሱዳንን
ከግብፅ ጨምራ ትገዛ የነበረችው ቅኝ-ገዠዋ እንግሊዝ የኢትዮ-ሱዳን ድንበርን በተመለከተ በወቅቱ የኢትዮጵያ ንጉሠ-ነገሥት ከነበሩት
ብልኁ መሪ አፄ ምኒልክ ጋር ድርድርና ውል ማድረጋቸው የተረጋገጠ ጉዳይ ነው።
አፄ ምኒልክም ሆኑ ሌሎቹ የኢትዮጵያ መሪዎች ከእነዚህ አውሮጳውያን ጋር ውል ሲዋዋሉና ሲደራደሩ በእነዚህ ባዕዳን የተውተበተቡ
ብዙ ሴራዎችን እያከሸፉና የአገራቸውን ጥቅም ለአፍታም አሣልፈው ሳይሰጡ፤ አገራዊ ኃላፊነታቸውንና የመሪነት ግዴታዎቻቸውን
በሚገባ የሚወጡ እንደነበር በኩራት የሚዘከር ነው።
በአንድ ወቅት አፄ ዮሐንስ አራተኛ “ምጥዋን ለጣሊያኖች አልሰጠኋቸውም፤ እንግሊዞች ናቸው የሰጧቸው፤ ምጥዋ የኢትዮጵያ ነው።
እኔ በአግባቡ የኢትዮጵያ የሆነውን ማንኛውንም ግዛት የመተው ፍላጎትም ሆነ ሥልጣኑም የለኝም’’ ሲሉ እንዳረጋገጡት ሁሉ፤ በአገር-
ወዳድነታቸው የታወቁት የኢትዮጵያ መሪዎች ከፈጣሪ በታች ጠያቂ የሌለባቸውና ምንም ነገር ለማድረግ ሙሉ-ሥልጣን የነበራቸው
ቢሆንም አንኳ የሕዝብንና የአገርን ጥቅም አሣልፈው ያልሰጡ ብቻ ሣይሆን ጥንት የኢትዮጵያ ግዛቶች የነበሩና በልዩ-ልዩ ምክንያቶች 3

ከኢትዮጵያ ይዞታ ውጪ የሆኑትን ለማስመልስ ያለ-መታከት የሚጥሩ፤ በዚህ ጥረትም ሕይዎታቸውን መስዋዕት ያደርጉ እንደነበር
ይታወቃል።
አገራችን ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር ያላትን ወሰን በተመለከተ አፄ ምኒልክ ከእንግሊዝ መንግሥት ጋር የተዋዋሉት ያ ውል ግን አሁን
የኢሕአዴግ መሪዎች የሚሉትንና አጣምመው የሚያቀርቡትን ሻለቃ ግዌን የተባለ የእንግሊዝ መኮንን ያለ-ኢትዮጵያ ተሣትፎና
እውቅና፤ በራሱ ፈቃድና ዓይን-ባወጣ አድሎዓዊነት ብቻውን አሰመርኩት የሚለውን መስመር ፈጽሞ የሚመለክት እንዳልሆነ በተገቢ
ግልጥ መሆን ይኖርበታል። ‘የግዌን መስመር’ የተባለውን ይህ የተናጠል ውሳኔ አንድም የኢትዮጵያ መንግሥት ሆነ መሪ እንኳን
ሊገዛበት ሕጋዊ እውቅና የሰጠበትም ሆነ ትክክል ነው ብሎ አምኖ የተቀበለበት ጊዜ የለም። እንግዲህ የወያኔ/ኢሕአዴግ መሪዎች
በግልጥ እያምታቱ ያሉት አፄ ምኒልክ አገራቸው ኢትዮጵያ በሱዳን በኩል ያለውን ድንበሯን በተመለከተ ከእንግሊዝ ጋር ያድረጉትን
ስምምነትና ከዚያ በኋላ ግዌን ከላይ በተጠቀሰው ሁኔታ ብቻውን አካልያለሁ የሚለውንና በኢትዮጵያ በኩል ምናልባት ከአቶ መለስና
ከምትካቸው ከአቶ ኃይለማርያም የተዛባና ሃቁን ያወናገረ ምስክርነት በስተቀር ምንም ዓይነት ሕጋዊ-ተቀባይነትም ሆነ አስገዳጅነት
የሌለውን የአንድ-ወገን ውሳኔ ነው።
‘የግዌን መስመር’ የተባለውን ቅድመ-ወያኔ/ኢሕአዴግ የነበሩ የኢትዮጵያ መንግሥታት መቸውንም ያልተቀበሉት፤ ኢትዮጵያም
ልታከብረውና መቀበል ልትገደድበት የማትችል በመሆኑ፤ ይህንን በተለየ መልኩ ለማቅረብ የሚከጅሉ መሠረታዊ በሆነ የኢትዮጵያ
ብሔራዊና አገራዊ ጥቅም ላይ ከሚዘምቱ ባዕዳን ተለይተው ሊታዩ የማይችሉና በአገር-ክህደት ተግባር የሚያስጠይቃቸው እንደሆነ
ለሁሉም ግልጥ መሆን ይኖርበታል።
2ኛ) አቶ ኃይለማርያም በዚህ መግለጫቸው የተረኩት ሌላው በጣም አስገራሚና መሠረተ-ቢስ አባባል ደግሞ በኢትዮጵያና በሱዳን
መኻል እ.አ.አ. በ1996 ዓም በተፈጠረው ግጭት ሣቢያ ሱዳኖች የለቀቁትን መሬት ኢትዮጵያውያን ድንበር ዘልለው ሲያርሱ እንደነበርና
ይህ መሬት የሱዳን በመሆኑ ሊመለስላቸው እንደሚገባ መንግሥታቸው እንደሚያምንበት፤ ይህንንም ተቀብሎ በተግባር ከመፈጸም
ወደ-ኋላ እንደማይል የሚለው ህቶት ነው።
ሃቁን ገልብጦ ለመረዳት ካልተፈለገ በስተቀር እውነታው ግን የዚህ ተቃራኒ መሆኑ ግልጥ ነው። በመጀመሪያ በኢትዮጵያ የተያዘ የሱዳን
መሬት የለም። እንደሚታወቀው በአፄ ኃይለ-ሥላሴ መንግሥትም ቢሆን ኢትዮጵያ በሱዳን ወሰኗ በኩል ጎላ-ብለው የሚታዩ የጦር-
ሠፈሮች አልነበሯትም። በደርግ ጊዜም ቢሆን በዋናነት የውስጥ ተቃዋሚዎችን ለመፋለም ካልሆነ በስተቀር ለድንበር ጥበቃ የሚበቃ
ሠራዊት በዚህ የአገሪቱ መሥመር አልነበረም። ድንበሩ ተከብሮ የኖረውና በሱዳኖች በኩል ይደረጉ የነበሩ አንዳንድ ድንበር-ዘለል
መተናኮሶችን ሲከላከልና ሲያከሽፍ የኖረው የአካባቢው አገር-ወዳድ ሕዝብ እንደነበር ይታወቃል። በደርግ ጊዜም በተለይ በጎንደር
ክፍለ-አገር ባለው ኢትዮጵያና ሱዳን በሚዋሰኑበት አካባቢ ከሕዝቡ በተጨማሪ የኢዴኅ (ኢዲዩ)፤ የኢሕአፓ፤ የአገር-ወዳድ ድርጅት፤
የከፋኝ አርበኞች ድርጅት፤ ወዘተ ታጣቂዎች ይንቀሳቀሱ ስለነበር፤ አሁን የወያኔ/ኢሕአዴግ መሪዎች ‘ቀድሞ የሱዳን ይዞታ የነበረና
በኋላ ግን የኢትዮጵያ አራሾች የያዙት መሬት’ ብለው በድፍረት የሚናገሩት ከኢትዮጵያውያን ይዞታና ቁጥጥር-ውጭ ያልነበረ ነው።
ደርግ እየተሸነፈ ወያኔ/ኢሕአዴግ ወደ አዲስ አበባ ሲያመራ ቀደም-ሲል ሕዝባቸውን እያስተባበሩ ድንበራቸውን ያስከብሩ የነበሩ
የአካባቢው መሪዎች በሞት እየተለዩና ድንበር-ጠባቂዎችም የተለመደ የድንበር-ማስከበር ሥራቸውን መሥራት ያልቻሉበት ጊዜ
ስለነበር፤ እንዲሁም በአካባቢው ይንቀሳቀሱ የነበሩ ኢትዮጵያዊ ታጣቂ-ኃይሎች በልዩ-ልዩ ምክንያቶች በአካባቢው ያልነበሩበት ሁኔታ
በመከሰቱ፤ ሱዳኖች ይህንን የተፈጠረ ክፍተት ተጠቅመው ድንበር እያለፉ የኢትዮጵያን መሬት መያዝና ጦር ማስፈራቸው ይታወቃል።
እግር-በእግርም የሱዳን ገበሬዎችና ሃብታሞች ይህንኑ በሕገ-ወጥ መንገድና በጉልበት የተያዘ የኢትዮጵያ መሬት ማረስና ማሳረስ፤
ጫካውንም እንደፈለጉ ማውደምና መዝረፋቸው ግልጥ ነው። የአካባቢው ሕዝብ ይህንን የሱዳን ድፍረት ለመቋቋም ለአዲሶቹ ገዥዎች
(ለወያኔ/ኢሕአዴግ) አቤቱታ በማቅረብ ጭምር የሚችለውን ሁሉ ከማድረግ አልተቆጠበም።
“ማን ይናገር የነበረ፤ ማን ያርዳ የቀበረ” አንዲሉ ነውና ምናልባትም ይህንን ጉዳይ በትክክል ግልጥ ለማድረግ በወቅቱ የአዲሱ
መንግሥት የመከላከያ-ሚኒስትር የነበሩት አቶ ስዬ አብርሃ ግንቦት 23 ቀን 2000 ዓ/ም በወጣው ‘አዲስ ነገር’ ጋዜጣ ላይ ያሠፈሩትን
ሃቅ በዋቢነት መጥቀሱ አስፈላጊ ነው። አቶ ስዬ የተባለውን የጽሑፍ ምስክርነት የሰጡት ግንቦት 13 ቀን 2000 ዓ/ም አቶ መለስ
የሱዳንን የድንበር ጉዳይ በተመለከተ ሕዝብ-ተወካዮች ምክር-ቤት ፊት ቀርበው ለሰጡት የተዛባ ዘገባ ምላሽ ነው። አቶ ስዬ በዚህ
ጽሑፋቸው ግልጥ ያደረጉት ነገር የወያኔ/ኢሕአዴግ መሪዎች የኢትዮጵያን መሬት ለሱዳን አሣልፎ ለመስጠት በማስረጃነት
ሊጠቀሙበት የሚሹትና እንደ-ምክንያት የሚያቀርቡት አንዱ ይህ አሁን አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የደገሙትና ቀደም-ሲል አቶ መለስ
ሃቁን ገልብጠው ያቀረቡት ለሱዳን ለመስጠት የወሰኑት ‘ቀደም-ሲል በሱዳን ይዞታ ሥር የነበረውንና በኋላ በግብፅ መሪ ላይ
በተሰነዘረው የግድያ ሙከራ ሣቢያ ኢትዮጵያና ሱዳን መኻል የነበረው ግጭት በፈጠረው ክፍተት ኢትዮጵያውያን ድንበር ተሻግረው
ያርሱት የነበረውንና ድሮም የሱዳን ይዞታ የነበረውን ነው’ የሚለውን የፈጠራ ትረካ ነው። አቶ ስዬ ስለዚሁ ጉዳይ በዚህ ጽሑፋቸው
ያቀረቡትን በሰፊው እንጠቅሳለን።
 “የሱዳን መንግሥት ይህንን የጥበቃ ኬላዎች ያለመኖር ሁኔታ በመጠቀም ሠራዊቱን ወደዚህ ቀጠና
 ማስገባቱን ቀጠለ። ሱዳናውያን አራሾች የሠራዊታቸውን ኮቴ እየተከተሉ መጠጋት ጀመሩ። ባለቤት
 የሌለው መሬት አገኘን ብለው ደኑን ማጥፋት፤ የእርሻ መሬቱን እንዳሻቸው መያዝ ቀጠሉ። ይባስ
 ብለው በእርሻ ሥራ መቋቋም የጀመሩትን ኢትዮጵያውያን ገበሬዎች መተናኮልና መጋፋት ጀመሩ። 4

 ሁኔታው አየባሰበት በመሄዱ ውሱን የመከላከያ ኃይል በዚሁ አካባቢ በማስፈር ቀስ በቀስ ይህንኑ
 ማጠናከር ጀመርን። ሠራዊቱ ይህን በአራሾች ላይ የሚደርሰውን በደል እና በዓይናችን ፊት
 የሚደርሰውን ውድመት መቃወም ጀመረ። በአካባቢው የተመደበው የመከላከያ ሠራዊታችን አዛዥ
 የጽሑፍ መልእክቱን አስይዞ አቻው ወደሆነው የሱዳን ጦር አዛዥ አንድ የመላክተኛ ጓድ ይልካል።
 የተላከው ጓድ የተደረገለት አቀባበል የወዳጅ ሠራዊት አቀባበል አልነበረም። ኑ ብለው ተቀብለው
 ትጥቃችውን አስፈትተው አረዷቸው። ይህ ድፍረትና ጭካኔ እንደተፈጸመ ሠራዊታችን አይምሬ
 የአጸፋ እርምጃ ወስዶ በአካባቢው የነበረው ጦር እንደወጣ ቀረ። እኔ በኃላፊነት እስከነበርኩበት ጊዜ
 ድረስ ሱዳኖች ወደዚህ እካባቢ ተተኪ ሠራዊት አላኩም። አቶ መለስ ሠራዊታችን በ1995/1996
 አካባቢ የወሰደው ማጥቃት ብሎ የገለጸው ይህንኑ የአጸፋ እርምጃ ነው። ይህንን አካባቢ ሠራዊታችን
 በወሰደው የአጸፋ እርምጃ ምክንያት በእጃችን የገባ የእኛ ያልሆነ መሬት አድርጎ ማቅረቡ ግን
 ትክክል አይደለም። የሱዳን ወታደሮች እና እነርሱን ተከትለው የመጡት የሱዳን አራሾች ወደዚህ
 ቀጠና የመጠጋታቸው ታሪክ ከፍ ብሎ ከገለጽኩት የነገሮች አንድነት ጋር የተያያዘ ነውና ድንበር
 ሳይካለል በፊት እንደዚህ ብሎ ፍርድ መስጠት አይገባውም ነበር። አስቀድሞ በኢትዮጵያ ላይ
 እየመሰከረ ነው።”
ሲሉ ስለሁኔታው ምስክርነታቸውንና ትዝብታቸውን ለኢትዮጵያ ሕዝብ በይፋ አሳውቀዋል።

3ኛ) የወያኔ/ኢሕአዴግ መንግሥት ለሰባት ዓመታት ከኢትዮጵያ ሕዝብ ብቻ ሣይሆን እራሱ ከሚቆጣጥረው ፓርላማ ጀርባ በድብቅ
ያቋቋማቸው ‘የኢትዮጵያና የሱዳን የጋራ ድንበር ኮሚሽን’ እና ‘የኢትዮጵያና የሱዳን የፖለቲካ ኮሚቴ’ የሚባሉ ሁለት ልዩ አካሎች
መኖራቸውን ይፋ ያደረገው ይህን ድብቅ ሥራውን ማጋለጥ ከተቻለ በኋላ ብቻ ነው። የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴም ሆነ
የኢትዮጵያ ሕዝብ የወያኔ/ኢሕአዴግ መሪዎች ከሱዳን ጋር በእነዚህ ድብቅ አካሎች አማካይነት በየጊዜው ስለሚደራደራቸው
ኢትዮጵያን የሚጎዱ ውሎችና ስለሚፈጽማቸው የሕዝብን ሉዓላዊነት የሚዳፈሩ ተግባራት ማወቅ የቻለው በመንግሥት ስም
ከተቀመጠው አካል ሣይሆን ጋፍኛ ከሱዳን መንግሥት ባለሥልጣናትና ከእነሱው መገናኛ-ብዙኃን ነው። የዚህ ድብቅ ሴራ ተጠቃሚ
የሆኑት ሱዳኖች ከለጋስ የወያኔ/ኢሕአዴግ መሪዎች በየጊዜው ስለተቸሯቸው የኢትዮጵያ መሬቶች የምስራቹን ለሕዝባቸው ቢያበስሩና
በአንፃሩ ከሕዝብ ጀርባ ተደብቀው አገርን የሚጎዳ የክህደት ተግባር ላይ የተሰማሩት የወያኔ/ኢሕአዴግ መሪዎች መሰሪ ሥራቸው
እንዳይታወቅ ለመደበቅ ቢሞክሩ፤ ያ ደግሞ ሳያስቡት ይፋ ሲሆን ምንም ተቀባይነትም ይሁን ታሪካዊ እውነታ የሌላቸው የሃሰት
ማስረጃዎችን ለመደርደር ቢማስኑ ላያስገርም ይችላል። የሚያስገርመውና የሚያሳዝነው ግን የባዕዳንን ተደጋጋሚ የቀጥታ ወረራዎች
ጭምር ተቋቁማና ብዙ መስዋዕትነት ተከፍሎ ተከብራ የኖረች ኢትዮጵያ አገራችን እንመራታለን በሚሉ በራሧ ልጆች ችሮታ ድንበሯ
መደፈሩና አንጡራ መሬቷን እንድታጣ መደረጉ ነው።
እንደ ሱዳን ባለ-ሥልጣኖች ቀጥተኛ ዘገባ ከሆነ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ድንበር ለመካለል ከወያኔ/ኢሕአዴግ መንግሥት ጋር
መስማማታቸውን ብቻ ሣይሆን ቋሚ የወሰን ምልክቶችን ለማስቀመጥ ቀኖች መቆረጣቸው፤ ተግባራዊ ለማድረግ ከሚጠይቀው ወጪ
ሱዳን ሁለት-ሦስተኛውን ለመሸፈን ፈቃደኛና ዝግጁ መሆኗን፤ እንዲያውም ሥራው ከወዲሁ መጀመሩን ጭምር ያስረዳል። ይህ
እውነታ ለኢትዮጵያ ሕዝብ በተለያዩ መንገዶች ሲታወቅ ብቻ በአብዛኛው ጉዳዩን ለማስተባበል ሲባል አልፎ-አልፎ በወያኔ/ኢሕአዴግ
የውጭ-ጉዳይ መሥሪያ ቤት የሚሰጡ መግለጫዎችና አሁን አቶ ኃይለማርያም ከሚናገሯቸው የተምታቱ ንግግሮች መረዳት የሚቻለው
ቢያንስ በሱዳን በኩል የሚቀርቡ ዘገባዎችን ሃሰትነት በአስተማማኝ የሚያረጋግጡ አይደሉም። አንዲያውም እውነታውን ይበልጥ
የሚያጋልጡ ሆነው ይገኛሉ።
4ኛ) ከአሁን በፊት ኮሚቴአችን ባወጣቸው መግለጫዎች እንዳሳወቀው ሁሉ፤ አቶ መለስ ግንቦት 13 ቀን 2000 ዓ ም ፓርላማ ቀርበው
‘አንድም የተፈናቀለ ኢትዮጵያዊ የለም’ ብለው በድፍረት ሲናገሩ ልክ ከአንድ ወር በፊት (በሚያዝያ 13 ቀን) ድንበር ተሻግሮ በመጣ
የሱዳን ጦር በቋራ ወረዳ ውስጥ ነፍስ-ገበያ ከተባለ የእርሻ ሥፍራ 34 ኢትዮጵያውያን ቤት ንብረታቸው ተቃጥሎና ተዘርፎ እነሱም
ታግተው ወደ ሱዳን ተወስደው መታሰራቸው እንኳ ጥቂትም የወገናዊነት መቆርቆር ቀርቶ ሰብዓዊ ስሜት አልታየባቸውም። ይበልጥ
ስሜታቸውን የነካውና የከነከናቸው ሱዳኖች ያሳዩት ታጋሽነት (ያውም የኢትዮጵያን መሬት ለመውሰድ) እንደሆነ በአንደበታቸው
ገልጠውታል። በጣልያን ወራሪዎች የተፈጸመው ልዩ ሁኔታ እንዳለ ሆኖ፤ ምናልባትም እነ-ልዑል ዓለማየሁ ቴዎድሮስን አፍኖ
ከአገራቸው ከኢትዮጵያ ወደ-እንግሊዝ ከወሰደው በናፒር የተመራው የእንግሊዝ የባዕድ ጦር ወዲህ ኢትዮጵያዊ ዜጎች በባዕድ ወራሪ
ጦር ከአገራቸው ታፍነው ወደ-ባዕድ አገር ተወስደው የታሠሩት በዘመነ-ወያኔ/ኢሕአዴግ ብቻ ነው።
አሁንም ኢትዮጵያውያን አርሶ-አደሮች ከዘመን-ዘመን ከኢትዮጵያ ይዞታና ቀጥተኛ ቁጥጥር ውጭ ሆኖ ከማያውቀው እርሻቸው
እየተፈናቀሉና እየተነቀሉ መሆናቸው፤ ሱዳኖች በወያኔ/ኢሕአዴግ መሪዎች ሥልጣንና ችሮታ ተሰጥቶናል በሚሏቸው ሥፍራዎች
ቁጥጥራቸውን ለማጠናከር እየተጣደፉ እንደሆነ የዓይን ምስክሮች እያረጋገጡት ያለ ጉዳይ መሆኑ ሊታውቅ ይገባል።
5ኛ) ስለ-አገር ድንበር ጉዳይ በማንኛውም ጊዜ ማንሳትና የሚከሰቱ ስጋቶችን መግለጥ የማንኛውም ኢትዮጵያዊ የዜግነት ግዴታና
የፖለቲካ ድርጅቶችም መሠረታዊ ኃላፊነት መሆኑን የዘነጉት አቶ ኃይለማርያም፤ ይህንን የድንበር ጉዳይ የሚያነሱ ወገኖችን (በተለይም
የፖለቲካ ድርጅቶችን) ‘ለፖለቲካ ፍጆታ ሲባል የምርጫ ጊዜ ሲቃረብ እየተጠበቀ የሚቀርብ’ ተራ የፖለቲካ አጀንዳ አድርገው ለማሣየት 5

ዳድተዋል። ጉዳዩን በዚህ መልክ ለማቅርብ የፈለጉበት ምክንያት ግልጥ ነው። አንድም የጉዳዩን ክብደት አቅልሎ ለማሳየትና ሕዝብን
ለማደናገር ሲሆን፤ በዋናነት ግን አሁንም በተለይ ጉዳዩ በአግባቡ ያሳሰባቸውና ሕዝብን ሊያነሳሱብን ይችላሉ ብለው የሚሰጉባቸውን
ድርጅቶች ከወዲሁ ለማሸማቀቅ በማሰብ ነው። የሚገርመው ግን በአንድ አፋቸው ከሱዳን ጋር ያለውን ድብቅ ድርድር ላለፉት አሥራ-
ሦስት ዓመታት ሁለት ኮሚቴዎችን አቋቁመውና በየጊዜው እየተገናኙ ሥራቸውን እየሠሩ እንደሆነ እራሣቸው እየተናገሩ፤ እዚያው-
በዚያው ይህንን እነሱ እያደረግን ነው የሚሉትንና ያልካዱትን ከሕዝብ የተደበቀ ሥራ ‘ሕዝብ እያወቀው ይሠራ፤ የምታደርጉት የአገርን
ብሔራዊ ጥቅም የሚጻረርና ሕገ-ወጥ ነው’ የሚሉ ወገኖችን ኃላፊነት-የተሞላበት አቤቱታ አምስት ዓመት ጠብቆ ከሚደረግና ውጤቱ
አስቀድሞ ከተወሰነ የምርጫ ጨዋታ ጋር ለማያያዝ መሞከር ቢያንስ ተኣማኒነትም ሆነ ተቀባይነት የለውም።
IV. ማጠቃለያ:
የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ አሁንም ለወያኔ/ኢሕአዴግ መሪዎች ያለው መልእክት አንድ ነው። የኢትዮጵያን ሕዝብ ንቃችሁ
ከሱዳን መንግሥት ጋር በድብቅ የምታደርጉት ማንኛውም ውል ሕገ-ወጥ እንደሆነ፤ የአገርን ብሔራዊ ጥቅም አሣልፎ የሚሰጥና
እናንተንም በአገር-ክኅደት ተግባር የሚያስጠይቅ ከፍተኛ ወንጀል መሆኑን ከወዲሁ ያስታውቃል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ባልመከረበት፤
ባላወቀውና ባላመነበት ድርድር የሚደረግን ውሳኔ በለከት-የለሽ ዕብሪትና በተራ-ማምታታት ተግባራዊ ለማድረግ መሞከር አገርን ለባሰ
አደጋ ማጋለጥ እንደሆነና ለውስጥም ሆነ ለአካባቢ አለመረጋጋት ምንጭ እንደሚሆን ልትገነዘቡት ይገባል። ስለሆነም በአገርና በሕዝብ
ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት በመገንዘብ፤ የኢትዮጵያን ጥቅም አሳልፎ የሚሰጠውን ስምምነት ከመተግበር እንድትቆጠቡ እናሳስባለን።
የአገር-መከላከያ ክፍሎችና አባላት ለዚህ ዓብይ አገራዊ ጉዳይ የሚገባውን ክብደት ሰጥታችሁ ባዕዳን ድንበር ገፍተውና ተሻግረው
በሕዝባችሁ ላይ ለሚደርስ ብሶትና ሰቆቃ የሚኖርባችሁን ሙያዊና የዜግነት ግዴታ ለመወጣት ብሔራዊ ኃላፊነት አለባችሁ።
ለሥርዓት ለውጥ የቆማችሁና የምትታገሉ አገር-ወዳድና ዴሞክራት ድርጅቶች የአገር ድንበር ጉዳይ በቀላሉ የሚታይም ይሁን ለጊዚያዊ
የፖለቲካ ፍጆታ የሚመነዘር ሣይሆን መሠረታዊ የብሔራዊ ክብርና የጋራ ኅልውና መርኅ ነውና ተባብራችሁና ሕዝባዊ ኃይላችሁን
አስተባብራችሁ ይህን እኩይ ሴራ ለማክሸፍ የጋራ እንቅስቃሴዎቻችሁን እንድታጎለብቱ እናሳስባለን።
ከአሁን በፊት በተደጋጋሚ አንዳስገነዘብነው ሁሉ ይህ ጉዳይ ለወያኔ/ኢሕአዴግ መሪዎች ወይም ለተወሰኑ ክፍሎች የሚተው ሣይሆን
የሁሉም የጋራ አገራዊ ጉዳይ በመሆኑ፤ ዞሮ-ዞሮ የዚህ አሣፋሪ ድርጊት ዕዳ ከፋዩ የኢትዮጵያ ሕዝብ በመኻልህ ምንም ዓይነት የፖለቲካ
አመለካከትም፣ የጎሣ፣ የሐይማኖትም ይሁን የአካባቢ ልዩነት ሳታሣይ ወዳጅ ቀርቶ ጠላት በመሰከረልህ የተለመደ የአገር መውደድና
የአንድነት መንፈስ የጋራ ድምፅህን እንድታሰማና በጋራ እንድትቆም ወገናዊ ጥሪያችንን በአክብሮት አናቀርባለን።

በኢትዮጵያ ላይ የሚሸረብ ደባ ይከሽፋል!
የኢትዮጵያ ዳር-ድንበር በሕዝቧ ኅብረትና አንድነት ተረጋግጦ ይቀጥላል!!
ኢትዮጵያ ታፍራና ተከብራ ለዘለዓለም ትኑር!!!

የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ
source www.ethiomedia.com.

Wednesday, February 19, 2014

በሃገሪቱ የተነሰራፋው ዘረኝነት፣ የደህንነት ሥጋትና አድልዎ አውሮፕላን እንዲጠለፍ አድርጓል

ከምኒልክ ሳልሳዊ
በሃገሪቱ የተንሰራፋውን የደህንነት ስጋት በመልካም አስተዳደር እና በዘረኝነት ላይ የተመሰረተ አድልዎ ተከትሎ የተደረገው የአይሮፕላን ጠለፋ ህዝቦች በገዛ አገራቸው በደህንነት ላይ ምን ያህል ስጋት እንዳጠላበት እና በመኖር ህልውናቸው ላይ ኢትዮጵያውያን የስርአቱ ፖሊሲዎች እያሸማቀቋቸው እንደሚገኙ አለም ካለፈው ጊዘ በተሻለ እውነታውን ፍንትው አድርጎ እየመሰከረ ነው።
የሕወሓት መራሹ ጁንታ ወደ ስልጣን በጠበንጃ ሃይል ከመጣ ጀምሮ በአለም አቀፍ ደረጃ የተደነገጉ የሰብኣዊ መብት ህጎችን ካለምንም ማርቅርቅ እና ድካም ከሌሎች በመገልበጥ በወረቀት ላይ ከማስፈሩም በተጨማሪ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት በአለም ላይ የሰው አገር ህግን እና አለማቀፍ ድንጋጌን ከሃገራችን ሁኔታ ጋር ሳይገናዘቡ በስፋት በደመነፍስ ለፍጆታ የተጻፈበት ሃገር ኢትዮጵያ ብቻ ሲሆን በየትኛውም አለም ሃገራት ያልተከሰተ የአለም አቀፍ ህጎችን ግልባጭ በከፊል በህገመንግስት እንዲሁም የገዢ ፓርቲን የፖለቲካ ፕሮግራም በከፊል ደባልቆ በጋር እንደ አውራ ህግ የወጣባት ሃገር ብትኖር ኢትዮጵያ ብቻ ናት::ኢትዮጵያ በታሪኳ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ የመብቶች ሕጋዊነት በተጨበጨበለት ሁኔታ እና ይህ በማይባል ደረጃ የተደነገጉባት አገር ነች፡፡ እንግዲህ ይህ ሆኖ እያለ ነው በአገሪቱ የመብቶች ጥሰት ጉዳይ ከአገሪቱ ብሔራዊ አነታራኪ ፖለቲካዊ አጀንዳነት አልፎ ዓለም አቀፍ አጀንዳ ሆኖ ተገኝቷል፡፡
ጥላቻ በፈጠረው ፍርሃት ብቻ የሃገሪቱን ህጎች ዜጎች ለመጥለፍ እያዋሉት ነው::
የቀድሞ መንግስትን ሽንፈት ተከትሎ በኢትዮጵያ የሰብኣዊ መብት ጥሰቶች የፍፃሜ ምዕራፍ ይሆናል ተብሎ ተስፋ ተደርጎ ነበር፡፡ ነገር ግን ጭራሽ ብሶበት ቁጭ አለ፡፡ የሕወሓት ወንበሩን መቆጣጠር ተንተርሶ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በተለይም ሒዩማን ራይት ዎችና አምነስቲ ኢንተርናሽናል የወያኔን ጁንታ በሰብዓዊ መብት ጥሰት በማብጠልጠል ነበር የተቀበሉት፡፡ ባለፉት ሃያ ሁለት ዓመታት የሰብኣዊ መብት ጥያቄዎች አቤቱታ ማሰማታቸውን አላቆሙም፡፡ ጋዜጠኞችን የሃሳብ ነጻነት ከሚገድብ ጥቃት በመከላከል ላይ የተሰማሩ የመብት አስከባሪ ድርጅቶችም ወያኔ በሚፈጥረው ከባድ የሰብኣዊ መብት ጥሰት በየጊዜው መክሰስ ሥራቸው ሆኗል::የአሜሪካው ስቴት ዲፓርትመንት በየጊዜው በሚያወጣው ዓመታዊ መግለጫው ወያኔን በሰብዓዊ መብት ጥሰትና የፖለቲካ መብቶችን ማፈን ይከሰዋል፡፡ ባሁን ወቅትየእነኚህን አካላት መግለጫዎች የታወቁ ዓለም አቀፍ መገናኛ ድርጅቶች በመቀባበል ኢትዮጵያ የዜጎቿን መብቶች በመጣስና በማፈን ወደር የሌላት አገር እንደሆነች ዓለም እንዲረዳው እያደረጉ ናቸው፡፡

ኢትዮጵያ በአስከፊ ድርቅና ረሃብ ለመታወቅ እንደበቃችው ሁሉ ወያኔ የዜጎችን መብቶች በመጣስና በማፈን እንዲሁም በሰብዓዊነት ላይ በሚፈጽመው ወንጀል በዓለም ላይ ታዋቂነትን እያተረፈ ነው፡፡ ይህ ብቻ አይደለም;ወያኔ የፖለቲካ ተቀናቃኞችን መብቶች ለመጣስ ስለሚጠቀምባቸው ዘደዎች የሚቀርቡ ማስረጃዎች እና ማብራሪዎች እጅግ ዘግናኝ ናቸው፡፡የወያኔ መሪዎች የፖለቲካ ተቀናቃኖችን ለማዳከም ሲሉ ንፁኃንን ወንጀለኛ የሚያደርግ ዘዴዎችን ሥራ ላይ እንደሚያውሉ በተለያዩ ይፋዊ ሪፖርቶች ላይ ሁሉ ከነማስረጃው እየተነገረ ይገኛል::
የህ የሰብኣዊ መብጥ ጥሰት እየተባባሰ የሚሄድበት ምክንያት ወይኔ በአብዛኛው ካድሬዎች ዘንድ በስፋት ሰርጾ እንዲገባ ያደረገው የተቃዋሚዎች ጥላቻ እና እንዲሁም የተቃዋሚው ቡድን የትግል አቅጣጫው በተመሳሳይ መልኩ በጥላቻ ላይ የተመረኮዘ መሆኑ ነው::ተቃዋሚዎች የታጠቁ ሃይላት ባለመሆናቸው የመርሃቸው እንቅስቃሴ የተገደበ እና ለፖለቲካ እና ለሚዲያ ፍጆታ የዋለ ተዳፍኖ የሚገኝ ሲሆን የወያኔው ግን በታጠቁ የጸጥታ ሃይሎች እና በፖለቲካ ማጭበርበሮች ላይ ስለተመረኮዘ ካድሬዎቹ በተሰጣቸው የጥላቻ ተግዳሮት እና ወያኔያዊ ስልቶች የፈጠሩትን ጥቅማጥቅሞች ጠብቀው ለማቆየት ሲባል ጥላቻ በፈጠረው ፍርሃት ብቻ የሃገሪቱን ህጎች ዜጎች ለመጥለፍ እያዋሉት ነው::
ይህ ፍርሃት እና ጥላቻ በወያኔ ከትልቅ እስከ ትንሽ ካድሬዎች አናት ውስጥ ስር ለስር በመስደድ የፈጠረው ነገር ቢኖር ማንኛውም ዜጋ ተቃውሞ ካሰማ በወንጀለኛነት በመፈረጅ በማሳደድ በማጥፋት እረፍት ለማግኘት እና ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ ሲራወጡ የህዝብን የበላይነት አፈር ከተውታል::ማእከላዊ የወያኔ ጁንታ በዲሞክራሲ ባለመወቀጣቸው የህጎችን የበላይነት ማረጋገጥ ካለመቻሉም በተጨማሪ በህዝብ እና በዲሞክራሲ ላይ በደሎችን የሚያደርሱ ባለስልጣናት የሚጠየቁት በሃገሪቱ የበላይ ህጎች ሳይሆን በወያኔያዊ የፓርቲ መመሪያዎች በመሆኑ በጥቅም መተሳሰር በፈጠርው ዝግ መንገድ የሰብኣዊ መብት ጥሰቶች እየተብራከቱም ከመሆኑ አልፎ የእለት ተእለት ተግባራት አካል ሆነዋል:: የአይሮፕላን ጠለፋዉም ከላይ ከገለጽኩት ጉዳዮች ጋር ቁርኝት ያለውና በሃገሪቱ እየተተገበረ ያለውን የቡድን አምባገነንነት በማጋለጥ ረገድ ትልቁን ሚና ተጫውቷል።
ምንጭ ዘ-ሐበሻ

Tuesday, February 18, 2014

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የተጠለፈበትን ምክንያት ለማወቅ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች እንደቀጠሉ ነው

የካቲት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አየር መንገዱ ከአዲስ አበባ ወደ ሮም ጣሊያን በማምራት ላይ በነበረበት ጊዜ  ረዳት አብራሪው የጉዞውን አቅጣጫ በመቀየር ጄኔቭ አውሮፓላን ማረፊያ በማሳረፍ እጁን ለፖሊስ ሰጥቷል።
የኢትዮጵያ መንግስት የኮሚኒኬሽን ባለስልጣን የሆኑት ሬድዋን ሁሴን አየር መንገዱ የተጠለፈው ሱዳን በቆመበት ጊዜ በተሳፈሩ ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች ነው በማለት መጀመሪያ ላይ ለረዩተርስ መግለጫ ቢሰጡም፣ የስዊዘርላንድ ፖሊስ ግን ፈጥኖ ጠላፊው የአየር መንገዱ ረዳት አብራሪ መሆኑንና የደህንነት ስጋት እንዳለበት በመግለጽ እጁን በሰላም መስጠቱን አስታውቀዋል።
በአለም የጠለፋ ታሪክ ያልተመደ ክስተት ነው የተባለው ይህ የአውሮፕላን ጠለፋ፣ የፖለቲካ ይዘት ያለው ሳይሆን እንደማይቀር ይገመታል።
ማንነቱ ያልታወቀው ረዳት ፓይለት በ30 ዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ ሲሆን፣ ጄኔቭ አውሮፕላን ማረፊያ እንደደረሰ በመስኮት በኩል በመውጣት እጁን በሰላም ለፖሊስ ሰጥቷል። ፖሊስ እንዳስታወቀውም ጠላፊው ምንም አይነት የጦር መሳሪያ አልያዘም።
በአውሮፕላኑ ውስጥ በነበሩ ተሳፋሪዎች ላይ ምንም አይነት ጉዳትም አልደረሰም።
ጄኔቭ የሚገኘው የኢሳት ወኪል እንደዘገበው ምንም እንኳ ጄኔቫ አየር ማረፊያ ከሰአታት በሁዋላ ተራግገቶ ስራውን ለማከናወን የቻለ ቢሆንም፣ በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር እስከ ቀኑ 9 ሰአት ድረስ ተሳፋሪዎች ወደ ሮም አልተመለሱም፣ አውሮፕላኑም ባለበት ቆሞ ይታይ ነበር። ከቀኑ 9 ሰአት ከሰላሳ አካባቢ አውሮፕላኑ ለጥገና ወይም ተሰፋራዎችን ወደ ሮም ለመመለስ ሲንቀሳቀስ መታየቱን ወኪላችን ገልጾ፣ ጠላፊውን ለማግኘት የተደረገው ሙከራ በፖሊስ ጥብቅ ቁጥጥር የተነሳ ሊሳካ አልቻለም።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች በተለያዩ ጊዜያት በአስተዳደሩ እንደሚማሩ ይታወቃል። አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሀን በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየውን የሰብአዊ መብቶች ጥሰት በማንሳት ጠለፋውን ከፖለቲካ ጋር በማያያዝ ለማየት እየሞከሩ ነው።
ረዳት ፓይለቱ አላማው ጥገኝነት መጠየቅ ቢሆን ኖሮ አውሮፕላኑን ሮም ላይ ካሳረፈ በሁዋላ ጄኔቭ ገብቶ በሰላም እጁን መስጠት ይችል እንደነበር ጁኔቭ የሚገኙ አንዳንድ አስተያየት ሰጪ ይናገራሉ።  ረዳት ፓይለቱ ይህ እድል እያለው እና አውሮፕላን መጥለፍ ወንጀል መሆኑን እያወቀ እንዲህ አይነት እርምጃ ለመውሰድ የተነሳሳው አንድ ከባድ ምክንያት ቢኖረው ነው በማለት እኝሁ አስተያየት ሰጪ ገልጸዋል።
በስዊዝ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጠበቆች ረዳት ፓይለቱን ለማግኘትና ጠበቃ ቐጥረው ለመከራከር ፍላጎት እንዳላቸው ለኢሳት ገልጸዋል።
ስቱዲዮ ከመግባታችን በፊት በአውሮፕላኑ ወስጥ ተሳፍራ የነበረች አንዲት ወጣት አግኝተናል። ወጣቱዋ እንደምትለው አውሮፐላኑ የተጠለፈው ከሮም ወደ ሚላን በሚመበርበት ጊዜ ነው። ሮም ማረፉንና መንገደኞችን ማሳፈሩን ወጣቷ ተናግራለች። አቶ ሬድዋን በበኩላቸው አውሮፐላኑ ሮም ሳያርፍ ወደ ጄኔቭ መሄዱን ተናግረዋል። ወጣቱዋ አብራሪው ረጅም ና ጠይም መሆኑንሮም ላይ ሻንጣውን ማውረዱንና ፊቱ ላይ አለመረጋጋት ይታይበት እንደነበር ገልጻለች።
source ESAT news.

Sunday, February 16, 2014

‹‹ከኢትዮጵያ ጋር ከመደራደር ይልቅ ሌሎች አማራጮችን መውሰድ እንፈልጋለን›› የግብፅ የውኃ ሚኒስትር

-ግብፅ  ከኢትዮጵያ ጀርባ ቱርክ አለች ማለት ጀመረች
16 FEBRUARY 2014 ተጻፈ በ  
ባለፈው ሰኞ በአዲስ አበባ ለውይይት መጥተው ስብሰባው ተቋርጦ ወደ አገራቸው የተመለሱት የግብፅ የውኃና መስኖ ሚኒስትር መሐመድ አብዱል ሙታሊብ ካይሮ ሲደርሱ በሰጡት መግለጫ፣ ከኢትዮጵያ ጋር መደራደር እንደበቃቸው ከገለጹ በኋላ ‹‹ሌሎች አማራጮችን መውሰድ እንፈልጋለን፤›› ብለዋል፡፡
ሚኒስትሩ በደፈናው ሌሎች አማራጮችን ከማለት ውጪ ማብራሪያ አልሰጡም፡፡ ይሁን እንጂ ንግግራቸውን በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ያነበቡ ኢትዮጵያውያን ንግግሩን ፀብ አጫሪነት ነው ብለው፣ ‹‹ኢትዮጵያውያን ግድቡን እንገነባለን፣ ግብፆች ያላቸው ሌላ አማራጭ ምን እንደሆነ እናያለን፤›› በማለት በቁጣ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
‹‹የኢትዮጵያ የመንግሥት ባለሥልጣናት ግብፅን የመጉዳት ፍላጎት የለንም እያሉ ነው፡፡ ይህንን ግን በወረቀት አስቀምጡልን ብለን ስንጠይቅ አይቀበሉም፤›› ያሉት ሚኒስትሩ፣ በህዳሴው ግድብ ምክንያት በኢትዮጵያና በግብፅ መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ለማጥበብ በግብፅ በኩል የሚደረጉ ጥረቶችን ኢትዮጵያ እያደናቀፈች ነው በማለት በአገራቸው ቴሌቪዥን ወቀሳ አቅርበዋል፡፡
ከዚህ በኋላ ውጤት ለሌለው ድርድር ጊዜ ማጥፋት ተገቢ እንዳልሆነ የተናገሩት ሚኒስትሩ፣ ‹‹ሌሎች አማራጮች አሉ፣ እነርሱን ወደ መተግበር እንሸጋገራለን፤›› በማለት የአማራጮቹን ምንነት ሳያብራሩ በደፈናው አልፈዋል፡፡
በቅርቡ ኢትዮጵያን የጎበኙት የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርን በተመለከተም፣ የግብፅ የውኃና መስኖ ሚኒስትር በዚሁ መግለጫቸው ላይ አስተያየት ሰጥተውበታል፡፡
ሚኒስትሩ አብዱል ሙታሊብ፣ ‹‹ግብፅን የማይወዱ ወገኖች ከኢትዮጵያ ግድብ ጀርባ ይገኛሉ፤›› በማለት የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአዲስ አበባ ጉብኝትን ተችተዋል፡፡ የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በአዲስ አበባ በተገኙበት ወቅት ኢትዮጵያ ለምትገነባው ታላቁ የህዳሴ ግድብ ባለሙያዎችን ለመላክ ፈቃደኛ ሆነዋል ሲሉም ወቀሳ አቅርበዋል፡፡
‹‹ቱርክ፣ አታቱርክ የተባለውን ግድቧን ስትነገባ ሶሪያና ኢራቅ ተቃውሞ ነበራቸው፡፡ ቱርክ የሶሪያና የኢራቅ ተቃውሞን ቸል በማለት ሁለቱን አገሮች ለውኃ ጥም ዳርጋና ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን ጥሳ ግንባታውን አከናውናለች፡፡ አፅንኦት ሰጥቼ ማለት የምፈልገው ኢትዮጵያ ቱርክ አይደለችም፡፡ ግብፅም እንደዚሁ ሶሪያ ወይም ኢራቅ አይደለችም፤›› በማለት ዛቻ መሰል አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ 
እስካለፈው ዓርብ ምሽት ድረስ የቱርክ መንግሥት ለሚኒስትሩ አስተያየት ምላሽ አልሰጠም ነበር፡፡
የግብፅ ሚኒስትር በይፋ በአገሪቱ የቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ የተናገሩትን ተርጉመው የዘገቡ የተለያዩ ድረ ገጾችን የተመለከቱ በርካታ ኢትዮጵያውያን፣ ‹‹ሚስተር ሙታሊብ ኢትዮጵያ አሁንም ግብፅን የመጉዳት ፍላጐት የላትም፡፡ የእርስዎ ንግግር ግን የተለመደው የግብፅ ባለሥልጣናት ድንፋታ ነው፡፡ ሌሎች አማራጮች ያሉትን እስኪ እንያቸው፡፡ ከንግግርና መግባባት የተሻለ በዚህ ጉዳይ ላይ አማራጭ የለም፤›› የሚሉ አስተያየቶችን አንፀባርቀዋል፡፡
እኚሁ የግብፅ ሚኒስትር ባለፈው ሰኞ በኢትዮጵያ ተገኝተው ከኢትዮጵያ አቻቸው አቶ አለማየሁ ተገኑ ጋር ተገናኝተው የነበረ መሆኑን፣ ሚኒስትሩ ግን የህዳሴው ግድብ ግንባታ ቆሞ እንወያይ በማለታቸው ስብሰባው መቋረጡን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ 
ከዚህ ስብሰባ ማግሥት ጋዜጠኞችን በመሰብሰብ በሁለቱ አገሮች መካከል ስላለው ወቅታዊ ጉዳይ በኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ማብራርያ ተሰጥቶ ነበር፡፡ 
በዚህ ስብሰባ ላይ ከጋዜጠኞች ከተነሱ ጥያቄዎች መካከል፣ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት በተደጋጋሚ ጦርነት በዚህ ዘመን ሊሆን አይችልም በማለት ግብፅ በአማራጭነት እንደማትመርጠው እየተናገሩ ቢገኝም፣ ጦርነት ሊፈጠር ቢችልስ ሲሉ የኢትዮጵያን አቋም ጠይቀዋል፡፡ በጉዳዩ ላይ ምላሽ የሰጡት የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ሚኒስትር አቶ ሬድዋን ሁሴን፣ ‹‹አለመግባባቱን በጦርነት ለመፍታት ኢትዮጵያን መውረርና መቆጣጠር ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ ይህ ግን መሆን አይችልም፤›› በማለት ምላሽ ሰጥተው፣ ‹‹ማንኛውም አገር ጐረቤቱን ነቅነቅ ለማድረግ የሚፈልገው የጐረቤቱ እግር ወልከፍከፍ ያለ እንደሆነ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ደረጃ ግን ይህንን ለማድረግ የሚያስችል ሁኔታ የለም፤›› ሲሉ አረጋግጠዋል፡፡ 
የኢትዮጵያን ደኅንነት የበለጠ ለማረጋገጥ ቀዳዳዎችን መድፈን እንደሚገባ ያከሉት ሚኒስትሩ፣ ‹‹የጐረቤት አገሮችን ሰላምና ደኅንነት ማረጋገጥ፣ ከጐረቤቶቻችን ጋር ጥብቅ ቁርኝት መፍጠር፣ ለውጭ ኃይሎች ያደሩ የራሳችንን ሰዎች ነቅሶ ማውጣት፤›› ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ በመቀጠልም፣ ‹‹ጦርነት መክፈት ይቻላል ኢትዮጵያን ማሸነፍ ግን የማይቻል ነው፤›› ብለዋል፡፡ 
ግብፆች ኢትዮጵያን ብድር የማስከልከል እንቅስቃሴያቸውን አሁንም አጠናክረው መቀጠላቸውን የተናገሩት አቶ አለማየሁ ተገኑ በበኩላቸው፣ የህዳሴው ግድብ ግን የውጭ ኃይሎችን ዕርዳታ አይፈልግም ብለዋል፡፡   
source (ethiopianreporter.com)

ወያኔን ካላጠፋነዉ ዘረኝነቱና ዉርደቱ ይቀጥላል

ዘረኞቹ የወያኔ መሪዎች በራሳቸዉ እጅ የጻፉት ማኒፌስቶ በግልጽ እንደሚያሳየን እነዚህ ዘረኞች ጫካ ገብተዉ የትጥቅ ትግል እንዲጀምሩ ያነሳሳቸዉ በአማራ ህዝብ ላይ ያላቸዉ ጥላቻና መሰረተ ቢስ ቂም በቀል ነዉ። ይህ ጥላቻቸዉ ደግሞ አማራዉን በመግደልና ግዛቱን ሲያሻቸዉ ከራሳቸዉ ክልል ጋር በመቀላቀል አለዚያም ለጎረቤት አገሮች በመሸለም ብቻ ሊቆም ወይም ሊገታ አልቻለም። እነሆ የአማራው ህዝብ የወያኔ ዘረኞች ዋነኛ ዒላማ ሆኖ የአገዛዙን የግፍ ፅዋ ያለማቋረጥ መጋት ከጀመረ ድፍን 23 አመታት ተቆጠሩ። ፋሽስቱ ወያኔ የኢትዮጵያን ህዝብ ብሔራዊ ስሜት በማምከን ፣ የዘመናት ተገዥነቱን ለማረጋገጥ በቅድሚያ የአማራን ሕዝብ ማንነት ማጥፋት ፣ የአማራን ሕዝብ ስነ ልቦናዊ ጥንካሬ መስለብ እና አንገቱን ማስደፋት አስፈላጊ መሆኑን በጽናት ያምናል። ይህ በመሆኑም ፣ በአማራ ህዝብ ላይ በወያኔ የሚፈፀመው ግፍ እና በደል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ስር እየሰደደና እየከፋ በግልፅም በስውርም በተቀነባበረ መንገድ ቀጥሏል።
ወያኔ የኢትዮጵያን ህዝብ ብሔራዊ ስሜት በማዳከም፣ ለዘመናት ሥልጣን ላይ ለመቆየት ያገለግለኛል ብሎ ዘመቻ ከከፈተባቸው ብሄረሰቦች አንዱና ዋንኛው የሆነው የአማራ ህዝብ በራሱ ማንነት እንዲያፍርና ብሄራዊ ኩራቱ እንዲሟሽሽ ላለፉት 23 አመታት በግብር ከፋዩ ህዝባችን ገንዘብ በሚተዳደሩ የመንግሥት መገናኛዎች ሳይቀር ከፍተኛ የስነ ልቦና ዘመቻ ተካሂዶበታል። በአማራ ሥም አማራውን የወያኔ አገር የማፍረስ አጀንዳ አስፈጻሚ ለማድረግ የተሾሙበት ተላላኪዎች በህወሃት አለቆቻቸው የተሰጣቸውን ተልዕኮ ለመፈጸም በተለያዩ አጋጣሚዎች አማራውን የሚያዋርድና የሚዘልፍ አስተያየት በአደባባይ ሲሰጡ ሰምተናል አይተናል። ይህ ተግባራቸው ለአማራ ህዝብ ቅንጣት ታህል ክብርና ፍቅር ያልነበረው ዘረኛው አለቃቸው መለስ ዜናዊ ከዚህች አለም በሞት ከተሰናበተ ቦኋላም ተጠናክሮ ቀጥሎአል።
የህወሃት መሪዎች አማራው ላይ ያላቸው ጥላቻ ወደሥልጣን ከመጡ ቦኋላ የተፈጠረ ሳይሆን ገና በጫካ ትግል ላይ በነበሩበት ወቅት በጻፉት የድርጅታቸው የፖለቲካ መረሃግብር በግልጽ እንደተቀመጠው ለትግል ያነሳሳቸውም አማራ ብለው የሚጠሩት ብሄረሰብ እንወክለዋለን በሚሉት ብሄረሰብ ላይ አድርሰዋል በሚሉት የፈጠራ በደልና ቂም እንደሆነ አረጋግጠዋል። ላለፉት 23 አመታት አማራው ከሚኖርበት የራሱ ክልሉ ሳይቀር እንዲፈናቀል ተደርጎ እየደረሰበት ያለው በደል የዚህ የቆየ የወያኔ ቂም በቀል ውጤት መሆኑ ግልጽ ነው።
ሰሞኑን አለምነው መኮነን የተባለ ሆድ አደር የባንዳነት ተግባሩን በመፈጸም በአለቆቹ ፊት ግርማ ሞገስ ለማግኘት እመራዋለሁ የሚለውን የአማራ ህዝብ እጅግ በወረደና ጸያፍ በሆነ ቃላት ያን ያህል ሲዘባበትበት መደመጡ አማራውን ብቻ ሳይሆን መላውን የአገራችንን ህዝብ አስቆጥቶአል።
በእርግጥ አለምነው መኮንን አማራን በማዋረድ የመጀማሪያው የወያኔ ተላላኪ አይደለም። የህወሃቶቹን ቁንጮዎች ስድብና ዘለፋ ወደ ጎን ትተን በወያኔ የዘር ፖለቲካ አማራውን እወክለዋለው የሚለው ብአዴን ከፍተኛ አመራር እነ እነታምራት ላይኔ ተፈራ ዋልዋና በረከት ስሞን በተለያየ ወቅት ንቀትና ስድባቸውን አሰምተውናል። አለምነህ መኮንን እንደዚያ በወረደ ቃላት አማራውን ሲያዋርድ በስብሰባው አዳራሽ የነበሩ ህወሃት የፈጠራቸው የብአዴን ልጆች በሳቅ ካካታ ሲያጅቡት እንደነበረ እድሜ ለኢትዮጵያ ሳታላይት ቴለቪዥን ከአዳራሹ ሾልኮ ለህዝብ ጀሮ የደረሰው የኦዲዮ ድምጽ አጋልጦአል።
ሁላችንም፤ እንደምንገነዘበው ወያኔ የገዛ ብሄረሰባቸውን ረግጠው በመግዛት የጥፋት አላማውን እንዲያስፈጽሙለት በራሱ አምሳል ከፈጠራቸው ድርጅቶች አንዱ የሆነው ብአዴን በታሪኩ አንድም ለህዝቡ የቆመ መሪ አፍርቶ አያውቅም። ለራሳቸውና ከአብራኩ ለተገኙት ህዝብ ምንም አይነት ክብር የሌላቸው የብአዴን መሪዎች ጣሊያን አገራችንን በወረረችበት ወቅት ለሆዳቸው ሲሉ ከባዕድ ጋር ተሻርከው ህዝባቸውን ካስጨፈጨፉት ባንዳዎች የከፋ ተግባር በህዝባቸው ላይ እየፈጸሙ ነው።
ወያኔ ለም የሆነውን የአማራ ግዛት እንዳለ የኔ ነው ወደሚለው የትግራይ ከልል ሲወስድ፤ በአማር ክልል ወስጥ በቀሩት ለም ቦታዎች የህወሃት ታማኝ ካድሬዎችን ከያሉበት እያጓጉዘ ሲያሰፍር፤ የአገሬውን አርሶ አደር እያፈናቀለ ለራሱ ታማኞች ለም መሬት እየሸነሸነ ለሰፋፊ እርሻ አገልግሎት ሲያድል አማራውን እወክለዋለው የሚለው ብአዴን አንድም የተቃውሞ ድምጽ አሰምቶ አያውቅም። የብአዴን መሪዎች የወያኔን ተልዕኮ ከማስፈጸም አልፈው በሟቹ አለቃቸው በመለስ ዜናዊ ሥም እየማሉ በአገራችን ኢትዮጵያና በሚያስተዳድሩት የአማራ ህዝብና ክልል የሚፈጽሙት በደል ብዙ ነው። ልክ እንደ ብአዴን የዘረኛውን ወያኔ የጥፋት ፖሊሲ ለማስፈጸም ከሚተጉት አንዳንዶቹ አማራውን ከክልላቸው ለማጽዳት በቤኒሻንጉል፤ በቤንች ማጅና ጉራፈርዳ ወረዳ እርምጃ ሲወስዱና ንብረታቸውን ቀምተው ባዶ እጃቸውን ሲያባርሩዋቸው ብአዴን ቁጭ ብሎ ተመልካች ነበር። ከአማራ ክልል ጋር የሚዋሰነው ዳር ድንበራችን ላይ በተነሳው የባለቤትነት ጥያቄም ላይ የወሰደው አቋም በህዝብና በታሪክ ፊት ውሎ አድሮ የሚያስጠይቀው ነው።
እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ እንደሚገነዘበው ፋሽስቱ ወያኔ በአገራችንና በህዝባችን ላይ እየፈጸመው ያለው አንዱን ዘር ከሌላው ጋር የማጋጨትና በተናጠል ደግሞ እያንዳንዱን ለይቶ የማዋረድና የማጥፋት ተግባር አሁን የተጀመረ ክስተት አይደለም። የቆየና ወያኔ ህዝባችንን ከፋፍሎ ለመግዛት ከመነሻው ሲጠቀምበት የነበረ ስልት ነው። ስለዚህ ወያኔ በራሱና በተላላኪዎቹ አማካይነት ላለፉት 23 አመታት በህዝባችን ላይ እየፈጸመ ያለውና የፈጸመው ግፍ፤ ውርደትና መከራ እንዲያበቃ ሁላችንም እጅ ለ እጅ ተያይዘን መነሳት ይኖርብናል። በወያኔ ከፋፋይ አጀንዳ እርስ በርስ እየተናቆርን የጥቃት ሰለባ የመሆናችንን እንቆቅልሽ ለማስቀረት ከኛ በላይ ሃይል ያለው አይኖርም።
በተለይ ግንባር ቀደም የወያኔ ሰለባ የሆነው የአማራ ህዝብ ወጣት በጫንቃው ላይ ተፈናጠጠው የወያኔን የጥላቻና የበቀል እርምጃ የሚያስፈጽሙትን ከአብራኩ የተገኙ ባንዳዎች ላይ የጥቃት ክንዱን መሰንዘርና ለክብሩ መቆሙን ማሳየት ያለበት ጊዜው አሁን ነው።
በብአዴን ሥር የተሰባሰቡ የአማራ ተወላጆች፤ በመከላኪያ ሠራዊቱ፤ በፖሊስና በደህንነት፤ በወጣት ማህበር፤ በሠራተኛ ማህበርና በተለያየ ሙያ ማህበር ብአዴን ራሱ ያደራጃቸው ሁሉ ለክብራቸውና ለኢትዮጵያዊ ማንነታቸው ሲሉ ከትግሉ ጎን በመሰለፍ የወያኔን ዕድሜ ለማሳጠር ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የሚያካሂደውን ትግል እንዲቀላቀሉ ንቅናቄው ጥሪውን ያቀርባል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

Wednesday, February 12, 2014

ምኒልክን ብትወቅሱ ማንነታችሁን ትረሱ (ዶ/ር ኃይለማርያም ላሬቦ)

አጼ ምኒልክ
የኔልሶን ማንደላን ለቅሶና ቀብር ሳይ በጣም ተገረምሁ ብቻ ሳይሆን እፍሪቃዊ መሆኑ ራሱ አኰራኝ። ከዚህም ተነሥቼ፣
ታሪክን ወደኋላ መለስ ብዬ በኅሊናዬ መስተዋት ቃኝቼ ሳበቃ፣ ጊዜው እንደዛሬ ሁኖ ቢያመችለት ኖሮ፣ እንደሳቸው ሊለቀስ
የሚገባ ሰው በአፍሪቃ ምድር ከዚህ በፊት ታይቶ አይታወቅምን ብዬ ራሴን በራሴ ደጋግሜ ጠየቅሁ። ማንዴላ የሚደነቁት፣
በቀለሙ በመጀነንና፥ በዘመናዊ መሣርያው በመተማመን፣ በበላይነት ረግጬው ልግዛው ብሎ፣ ለብዙ ዘመናት በሥልጣን ላይ
ሁኖ ያሠቃይ የነበረውን ጨቋኙን የነጮች ግዛት ከነሥርዐቱ አሸንፈው፣ ለሀገራቸው ጥቊር ሕዝብ የድል ዋንጫ አጐናፅፈው፣
ነፃነቱንና ክብሩን ስለመለሱለት ነው። ግፈኞቹን የድሮ ጠላቶቻቸውንም እንደመበቀል ፈንታ በፍቅር ያዟቸው። ሁሉም
የደቡብ አፍሪቃ ዜጋ በጐሣና በዘር፤ በሃይማኖትና በቀለም ሳይለያይና ሳይከፋፈል፣ ታዲያ በመቻቻል፣ ባንድነትና በፍቅር
ተቀራርቦ እንዳንድ ሀገር ሕዝብ እንዲኖር አደረጉ። ለኻያ ሰባት ዓመታት በእስራት ራሳቸውን በመሠዋት፣ ጠላታቸውን
በማሸነፍ፣ ራሳቸውንና ሀገራቸውን ያኰሩ ደግና ብልህ መሪ፣ ሰውን በማንነቱና በእምነቱ ሳይሆን በሙያውና በችሎታው
የሚፈርጁ፤ ጠላትን እንኳ የሚራሩና የሚወዱ ሰው ነበሩ። ይኸንን በዐይነ ኅሊናዬ መላልሼ ካሰላሰልሁ በኋላ፣ የዓለምን
ታሪክ ደግሞ ቃኝቼ ሳበቃ አንድ እጅግ በጣም ታላቅ ሰው አገኘሁ። አፄ ምኒልክ።

አፄ ምኒልክ በሠሩት ሥራ፣ ባሳዩት ብልሃትና ደግነት፣ ከኔልሶን ማንዴላ በምንም መልክና ሚዛን ይበልጣሉ እንጂ፣ ያንሳሉ ብዬ አልገምትም። ይኸ የግሌ
ብቻ ሳይሆን ብዙ አፍሪቃውያንና የዓለም ምሁራን የሚጋሩት አስተያየት ነው።ኔልሶን የጥቊሮችን እኩልነት በአገራቸው ከማስከበር ውጭ በሌላው
ዘርፍ ብዙ አልገፉበትም። የደቡብ አፍሪቃ ጥቁር ሕዝብ በነጮች የተወረሰውን ሀብት በፍጹም መልሶ አላገኘም። ነጮቹ አሁንም እንደድሮው
በቊጥራቸው የአገሩ ሕዝብ ከመቶ ዐሥሩ እጅ እያሉ፣ ግን ከመቶው ሰማንያ እጅ በላይ የሚሆነዉን የሀገሩን ሀብት እየተቈጣጠሩ ናቸው። ይኸ
የማይካድ ሐቅ ነው። ከሁሉም የባሰ ደግሞ ያገራቸው ጥቁሮች በመጨረሻ ላይ ድል-ቢያደርጉም፣ በነጭ ተሸንፈው መገዛታቸው ራሱ በመንፈሳቸዉና
በታሪካቸው ውስጥ የማይሽር አሳዛኝ ጠባሳ ትቶባቸዋል። ስለዚህም እንደሌሎቹ ለአውሮጳውያን ቅኝ አገዛዝ እንደተዳረጉ ሕዝቦች ሁሉ የዝቅተኝነትና
የውርደት ስሜት በየሄዱበት እንደማይለያቸው ግልጥ ነው።

የአፄ ምኒልክ ሥራ ይኸንን ሁሉ ለኢትዮጵያውያን አስወግዶላቸው፣ ከፍተኛ በራስ የመተማመንና ከማንም (ፈረንጅም ጭምር) አላንስ ባይነትን፣
የልዕልናንና የኩራትን ስሜት እመንፈሳቸው ውስጥ ቀርጿል። ጆን ቦየስ የተባለ ጸሓፊ፣ የምሥራቅ አፍሪቃን የእንግሊዝ ግዛቶች ዙሮ ካየ በኋላ፣
ከኢጣልያን ወረራ በፊት ወደአዲስ አበባ ሲደርስ እጅግ የገረመው ነገር ቢኖር፣ ለመጀመርያ ጊዜ “አንድ አፍሪቃዊ ነጮችን እያዘዘ ቤት ሲያሠራቸው”
ማየቴና፣ ኢትዮጵያውያን ፈረንጆችን “ባሮች እያሉ ሲጠሩዋቸው” መስማቴ ነበር ይላል። እንዲሁም ኢጣልያ ሀገሩን ለሁለተኛ ጊዜ ሲትወርር ወደኬንያ
የሸሹትን የኢትዮጵያን ሰደተኞች፣ ቅኝ ገዢዎቹ እንግሊዞች፣ በተለመደው በዘር ተፋሰስ ድርድራቸው መሠረት፣ ከዕርከኑ ሥር ከነበሩት ከሌሎቹ
አፍሪቃዉያን ጋር ቢደረድሯቸው፣ ከፍተኛ ትርምስ ፈጠሩ። እንግሊዞች “ኢትዮጵያዉያን” የሚል ሌላ ከሌሎቹ አፍሪቃዉያን ከፍ ያለ ዕርከን ሲፈጥሩ
ብቻ ነው ሰላምና ሥርዐት የሰፈነው። ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ቢያውቅም ባያውቅም በገዛ ራሱ የመተማመንና የመንፈሳዊ ኩራት አለው ብል
አልሳሳትም። ይኸም የመንፈስ ልዕልና ስሜት የአፄ ምኒልክ የሥራ ውጤት ነውና ሁሌዬ ልመሰገኑ ይገባቸዋል። ኢትዮጵያዊ የሆነ ሁሉ ለሳቸው ተከፍሎ
የማይዘለቅ ከፍተኛ ውለታ አለበት።

አፄ ምኒልክ ኔልሶን ማንዴላን ይብለጡ እንጂ በብዙ መልክ ግን እንደሳቸው የታደሉ አልነበሩም። ማንዴላ የወረሱት በዘመናዊ መልኩ የተዋቀረ፣
አንድነቱ የጠነከረ፣ በሥልጣኔ የዳበረ፣ በዓለም መንግሥታት የታወቀ፤ ዳሩና ድንበሩ የማይደፈር መንግሥት ነው። ምኒልክ ግን ይኸ ዕድል
አልገጠማቸውም ብቻ ሳይሆን፣ መልሰው ያዋሀዱት የኢትዮጵያ መንግሥት ጥንታዊነትና አስደናቂ ታሪክ ቢኖረውም፣ ፈርሶ በመገነባት ላይ ያለ ነበር።
ለግንባታው አፄ ቴዎድሮስ መሠረቱን ጣሉ። አፄ ዮሐንስ ደግሞ ተመልሶ ከመፍረስ አዳኑት እንጂ ለግንባታው ጊዜና ዕድል ግን አላገኙለትም። እንግዴ
አሁን የሚንኖርባት በዘመናዊ መልኩ የተዋሀደችው የኢትዮጵያ ጥንታዊና አኲሪ ታሪኳ እንደተጠበቀ ሁኖ፣ በአብዛኛው የአፄ ምኒልክ እጅ ፍጡር ናት
ማለት ይቻላል።

እውነት ነው ኢትዮጵያ በብዙ ረገድ ከደቡብ አፍሪቃ ትለያለች። አንደኛ የቈዳዋ ስፋት፣ የመሬቷ ይዘትና ቅጽ፣ የሕዝቧ ባህልና ዐይነት፣ አንዳንዴ ይቀየር
እንጂ፣ ከዚህ በላይ እንዳልኩት፣ ከጥንት ዘመን የነበረች ሀገር ናት። እስከስምንተኛ ዘመን ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ፣ በግልጥ የአካላቷ ቀንድ ግዛቶቿ
የነበሩት አካባቢዎች አሁን የሉም። መናገሻዋ አክሱም በነበረችበት ወቅት፣ አሁን ጂቡትና ሱማሌ በመባል የሚታወቁት መንግሥታት ከዋኖች ግዛቶቿ
መካከል ነበሩ፤ ዛሬ ራሳቸዉን የቻሉ መንግሥታት ሁነዋል። ምናልባት የበሰለ፣ የተራቀቀና አርቆ የሚያስብ መንግሥት ሲኖራቸው፣ አንድ ቀን ወደ ጥንት
እናታቸው መመለሳቸው አይቀርም ይሆናል። እንዲሁም መሠረታዊ ግዛቷ የነበረችው የዱሯ ምድረ ባሕር፣ የቅኝ ገዢዎቿ በሰጧት ስም የሚትጠራው
የዛሬዋ ኤርትራ። የድብልቅልቅና የጨለማ ዘመን በሚባለው ከዘጠነኛ እስከዐሥራ ሁለተኛ ዘመን ድረስ በነበረው ጊዜ ውስጥ፣ የመሬቷ ቆዳ ይዘት ሆነ፣
ያስተዳደሩ ሥርዐት በግልጥ አይታወቅም። ይሁንና ከአፄ ዐምደ-ጽዮን እስከግራኝ ወረራ፣ ከዚያም በመጠኑ እስከዘመነ መሳፍንት ድረስ የነበረው የግዛቷ
መልክና ስፋት ከአሁኑ እንደሚበልጥ፣ የሕዝቧም ዐይነት ለየት እንደሚል ጥርጥር የለም።

ዳግመኛ ከደቡብ አፍሪቃ የሚለያት ዋናው ነገር ቢኖር፣ ኢትዮጵያ የተፈጠረችውና የተገነባችው ባዕዳን በሆኑ በውጭ ሀገር ወራሪዎች ሳይሆን በገዛ
ነዋሪዎቿ ትብብርና እጅ ነው። ኔልሶን ማንዴላ ሲታገሉ፣ “ነጮች ከሌላው የሰው ዘር በላይ ናቸው፥ እግዚአብሔር ዓለምን የማሠልጠን አላፊነትና አደራ
እጫንቃቸው ላይ ሰለጣለባቸው፣ ነጭ ያልሆነውን የሰው ዘር በሙሉ አንበርክኮ የመግዛት ግዴታ አለበት” የሚለው ፍልስፍናና አስተሳሰብ እንደነውር
በሚቈጠርበት ዘመን ነው። እንደገና አፄ ምኒልክ ግን በዚህ ረገድ በጣም ይለያሉ። የነጭ የበላይነት ፍልስፍናው በአሳብ ደረጃ በገነነበት ጊዜ ብቻ
ሳይሆን፣ በግብር በሰፈነበት፣ በመላው ጥቁርና ነጭ ዘር ባልሆነበት ዓለም ላይ በሰፊው በነገሠበትና፣ ምርኮውም በሆነበት ዘመን ነው ዘመናዊቷን
አጼ ምኒልክ Page 2 of 15

ኢትዮጵያን ያዋሀዷትና ሊገነቧት የበቁ። እንዲያዉም የነጭ ዘር ሕዝቡንና ሀገሩን እንደሌላው ዓለም ምርኮው ሊያደርግ ቢቃጣ፣ “የለም ሌላ ጋ ሂደህ
ተጀነን እንጂ፣ ኢትዮጵያን ሀገሬንና ሕዝቤን እንኳን አትነካብኝም” ብለው፣ ሕዝባቸውን በማስተባበር ከጐናቸው አሰልፈው፣ ነጩ ራሱ በፈጠረዉና፣
ይተማመንበት በነበረው መሣርያ ድል አድርገውት፣ ልኩን ያስገቡትና፣ የነጭ ዘር እንደሌላው የሰው ዘር መሆኑን፣ ለሱም ለራሱ ሆነ ለሌላዉም የዓለም
ሕዝብ በሙሉ ያስተማሩት፣ በዓለም ውስጥ የመጀመርያው መሪ ናቸው። ይኸንንም ከሳቸው በመማር ይሁን አብነታቸዉን በመከተል፣ ዘጠኝ ዓመት
ቈይተው ጃፓኖች ደግመውታል።

ያፄ ምኒልክ ትልቅነት የነጮችን አምባገነንንትና ጦር ማሸነፍ ብቻ አይደለም። ያገራቸው ሕዝብ ራሱ “የምኒልክ ነገር ይመስለኛል ተረት” እስከሚል ድረስ
ባስተዳደር፣ በለጋሥነት፣ ለሀገርና ለሕዝብ በሠሩት ሥራቸው ሆነ፣ ባሳዩት መርህና ፍቅር፣ በኢትዮጵያ ታሪክ ብቻ ሳይሆን፣ በዓለም ታሪክ ውስጥም
ወደር የላቸውም። በቅርቡ ልበ-ወለድ ታሪክ እየተፈጠረ፣ ሥራቸዉንና ዓላማቸውን በማጣመም፣ ክብራቸውን ስላጐደፈ፣ ምንነታቸውንም ስለገደለ፣
ቁሞ ማየቱ ተገቢ አይደለም በማለት ይህችን አጭር ጽሑፍ ለማበርከት ተገደድሁኝ። ቢትንዛዛም ረጋ ብላችሁ በጽሙና እንደምታነቧትና
እንደምትደሰቱባት፣ ዕውቀትም እንደምትቀስሙባት እተማመናለሁ።

በአገራችን “ማን ይንገር የነበረ፣ ማን ያርዳ የቀበረ” የሚባል አባባል አለ። አባባሉ ትክክል ነው። በአካል በቦታው ተገኝቶ በገዛ ዐይኑ አይቶ ከሚነግር
ሰው፣ የበለጠ ምስክርና ማስረጃ ሊኖር አይችልም። እኔም በአፄ ምኒልክ ዘመን አልኖርኩም። ግን የታሪክ ተመራማሪ እንደመሆኔ መጠን፣ በጊዜአቸውና
ከሞቱም በኋላ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ፣ ስለሳቸው በኢትዮጵያና በሌላ አገር ሰዎች የተጻፈውን ሆነ፣ እሳቸውም በሕይወታቸው ዘመን
ለአስተዳዳሪዎቻቸውና ለሌሎች የጻፉትን ጽሑፎች በሰፊው አንብቤአቸሁአለሁ። በተጨማሪም ሳይጻፍ በአፈ-ታሪክ ሰለሳቸው የሚወራዉንም
ሰምቻለሁ። የታሪክ ምሁር እንደመሆኔ መጠን፣ የተጻፈዉን በሙሉ ደጉንም መጥፎውንም በድፍኑ እንደእውነት አድርጌ አልቀበለውም። ጽሑፉ
እውነተኝነት አለው ብዬ ከመቀበሌ በፊት፣ የታሪክ ምሁራን ዉስጣዊና ውጫዊ ኀሠሣዎች የሚሉትን ትንትኖች በጽሑፉ ላይ በመጠቀም፣ እውነቱን
ከሐሰቱ፣ ድርጊቱን ከምናቡ ማበጠር ይኖርብኛል።

ኀሠሣውም፣ ደራሲው የጻፈበትን ምክንያት፣ ለመጻፍስ ምን ወይንም ማን እንዳነሣሣው፣ ወጪውን ማን እንደሸፈነለት፣ ለጽሑፉ አንባቢ ደግሞ ምን
ዐይነት መልእክት ሊያስተላልፍ እንደፈለገ፣ የጽሑፉስ ግብ ምን እንደሆነ፣ ድርጊቱ በሚፈጸምበት ጊዜ በአካል ተገኝቶ ወይንም ከሌላ ምንጭ ወስዶ ነው
የጻፈው፣ የሚሉትንና እነሱንም የመሳሰሉትን ጥያቄዎች ማንሣት ያስገድደኛል። ጥያቄዎቹም የጽሑፉን እውነተኝነት ለመገንዘብ በጥቂቱም ቢሆን
ይረዳሉ። ለምሳሌ ያህል አንድ የኢጣልያን ተወላጅ የሆነ ዘውገኛና የስዊስ ሰው ባፄ ምኒልክ ላይ ቢጽፉ፣ ኢጣልያኑ ለመጽሐፉ ንጉሡ ከሠሩት ሥራዎች
መካከል የሚመርጠው የራሱን ዓላማና እምነት የሚያራምደውንና የሚያንጸባርቀውን እንጂ የሚፃረረውን አያጐላም። ቢመርጥም ያ ጥሩ ሁኖ የሚታየው
ድርጊት ከንጉሡ የሥራ ልማድ ውጭ እንደሆነ አድርጎት ያቀርበው ይሆናል።የዘውገኛው ጣልያን ዝንባሌ ኢትዮጵያ የሚደነቅ ጥንታዊ ታሪክ
ቢኖራትም፣ አሁን ያለችው በአረመነኔትና በጨለማ ዓለም ውስጥ ተዘፍቃ ስለሆነ፣ ኢጣልያ የማሠልጠን ግዴታ ሰላለባት፣ አገሩን በውድም በግድም
መያዝና ማስተዳደር አለባት ነው። ስለዚህም በጽሑፉ የአፄ ምኒልክን ሥራ ሁሉ፣ ደጉንም ጭምር ወደማጥላላት፣ ጭካኔያቸውን ያሳያል የሚለውን ጐን
ወደማጉላት ያዘነብላል። ስዊሱ ግን ሀገሩ በቅኝ ግዛት ቅርምቻ ፍላጎት ስለሌላት፣ አሳቡ ከመላ ጐደል ቀናናነት ይኖረዋል። ስለዚህም ኢትዮጵያ ከጥቁር
አፍሪቃ የተለየች ጥንታዊት የሥልጣኔ አገር መሆኗንና፣ አፄ ምኒልክም በዘመናዊ ሥልጣኔ ከገፉት አገሮች መካከል አንዷ እንዲትሆን፣ ሌት ተቀን
የሚሠሩ ታታሪ መሪ መሆናቸዉን ማሳየት ይሻል። ስለዚህም የንጉሡን አብዛኛዉን ሥራቸዉን ሲያወድስ፣ መጥፎ ጐን ካላቸው ደግሞ፣ ሌሎችም
በሳቸው ሁናቴና ቦታ የነበሩ መሪዎች የፈጸሙት ተመሳሳይ ፣እንዲያውም የከፋ ድርጊት መኖሩን ስለሚገነዘብ፣ አደባብሶት ያልፋል ወይንም አቃልሎት
ያቀርባል። በነዚህ ሁለት አወዛጋቢ ጽሑፎች መካከል አበጥሮ እውነቱ የት እንዳለ ማወቅ የታሪክ ባለሙያ ሥራ ነው።

ደጋግሜ እንዳዳመጥኹት፣ በየቃሌው [መነጋገርያ=ፓልቶኩ]ና፣ በሌላውም ዘመናዊ መገናኛ፣ በጐጥና በጐሣ ፖሊቲካ የሚመሩት ዓላማቸውና
እምነታቸው ዘውገኛነትን ማራመድ ስለሆነ ነው መሰለኝ፣ ሰለአፄ ምኒልክ ጠንካራ ጐን በፍጹም ሊያነሡና በእምነታችውም ውስጥ ሊያንጸባርቁት
አይፈልጉም። ዐዉቆ የተኛውን ማንቃት እንደማይቻል ሁሉ፣ እነዚህም በይፋ ለተወሰነ ዓላማ የቆሙ እንደመሆናቸው፣ ምንም ዐይነት ማስረጃ
ቢቀርብላቸው ስለአፄ ምኒልክ ጥሩነት ሊቀበሉ ዝግጁ አይሆኑም። እንደፈሊጥ የሚቈጥሩት ምንጮቻቸው፣ በየቡናና በየመሸታ ቤቱ ከመሳዮቻቸው
የሚወራው ወሬና ልበወለድ ታሪክ፣ ካልሆነም በቋንቋም በባህልም ባዕድ የሆኑት ፈረንጆች ለራሳቸው አገር ጥቅምና ለእንጀራቸው ሲሉ የጻፉት
ጽሑፎች ናቸው ። እነዚህም የእምነታቸው ባርያ ስላደረጓቸው፣ ማወናበድም ሥራቸው ሁኗል፤ እውነትም ነፃ እንዳታወጣቸው ይሸሿታል፣ አይጠጓትም
ማለት ይቻላል። ስለዚህ ይኸንን ጽሑፍ እንዳነበቡ፣ እንደልማዳቸው የጥላቻቸውን ነጐድጓድ፣ የስድባቸውንና የክሳቸውን ወጨፎ እንደሚያወነጭፉብኝ
አልጠራጠርም። ከዚህ በፊት እንዳየሁት፣ ከሊቁ እስከተራው፣ ሥራቸው ከሌሎች ለይቶ ግለሰቡን በተናጠልና በስውር ማጥቃት እንጂ እንዳይጋለጡ
ፈርተው በግሁድ አያደርጉትም።

እዚህ ላይ አንድ ነገር ማንሣት እሻለሁ። በሺ ሁለት መቶ መኻል ላይ በዋሺንግቶንና በአካባቢዋ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዜና በሚያሠራጭ
ኢትዮጵያዊነት በተባለ ሬድዮ ጣቢያ ላይ በተከታታይ ስለኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁናቴዎች ሰፋፊ ቃለ-መጠይቆች እሰጥ ነበር። ስለኦሮሞ ኅብረተ-ሰብ
እውነተኛውንታሪክ ብገልጽ፣ ቈሽታቸው ያረረባቸው ዐዋቂ ነን የሚሉ ጥቂት ኦሮሞን እንወክላለን ባዮች ስድስት ግለሰቦች1
፣ የተናገርሁትን እጅግ በጣም
አፋልሰውና አከላልሰው በማጣመም ጽፈው ለሁሉም አለቆቼ በተዋረድ2
 ላኩ። ከነዚህም አንዱ ሊቅ አሰፋ ጀለታ ሲሆኑ፣ ስለኦሮሞ አንድ የምርምር

1
 . ግለሰቦቹ በቴነሲ ዩኒቬርሲቲ በኅብረተ-ሰብ ጥናት ክፍል ውስጥ መምህር ሊቅ አሰፋ ጀለታ፣ ስሟን እንኳን በትክክል መጻፍ የማትችል አድራሻዋም
ምንኔቷም ያልታወቀ ሊቅ አስናቀች ነጋሳ (የእጇ ፊርማ ግን ያንድ በጆርጃ እስቴት ዩኒቬርሲቲ ውስጥ የሚያስተምር በደምብ የማውቀው የታሪክ ሊቅ
ይመስላል)፣ እንዲሁም ሙያቸውና አድራሻቸው ያልታወቀ አቶ በቀለ ቶሎሣና አቶ አበራ ተፈራ፣ የዋሺንግቶን የኦሮሞ እርዳታ ድርጅት ሊቀ-መንበር
ንጉሤ ቢራቱና፣ ክኮሉምቡስ ኦሃዮ የኦሮሞ እርዳታ ማኅበር ሠራተኛ አቶ ጉሉማ ባልቻ ነበሩ።
2
 . እንዲሁም በተጨማሪ ለሲአይኤ፣ ለኮንግረስ ለሌሎችም እንደነየተባበሩት መንግሥታት የመሰሉ የዓለም ዐቀፍ ድርጅቶች ሬድዮ ጣቢያውን ሲከሱ
ልከዋል። Page 3 of 15

መጽሐፍ3
 የጻፉ ምሁር ናቸው። ጽሑፉም ባንድ በኢትዮጵያ ታሪክ በጣም በታወቀ እንግሊዛዊ ምሁር ታይቶ፣ “ይኸ መጽሐፍ ለቈሻሻ መጣያ ቅርጫቴ
ካልሆነ በስተቀር ሌላ ምንም ዐይነት ጥቅም የለውም” ሲል አቃቂር የጻፈበት ነው። የኔም ግንዛቤ ከዚሁ ይከፋል እንጂ አይሻልም።

ዋና ቁም ነገር፣ እነዚህ ሊቅ አሰፋ ጀለታን የመሰሉት፣ ኢትዮጵያ አገራቸው ብዙውን ጊዜ የሚበላ አጥቶ ጦሙን ከሚያድር ከተራ ድኻ ግብር በተገኘው
ሀብት፣ በነፃ አስተምራቻቸው ለወግና ለማዕርግ ካበቃቻቸው ወዲያ፣ በየቦታው እየዞሩ፣ በቅኝ ገዢዋ ኢትዮጵያ እንደደቡብ አፍሪቃ ጥቊሮች
መብታችንን ተነፍገን በጭቆና እንኖራለን እያሉ መስበካቸው ብቻ ሳይሆን፣ ብልሹ አቋማቸውን መቋቋም ሲያቅታቸው የማይታመን ውሸት ፈጥረው
አቻቸውን ከሥራ እንዲባረሩ ዘመቻ እስከማካሄድ ድረስ መዘቀጣቸው ነው። በቅርብ ጊዜም በዶቼቬለ ሬድዮ በስጠሁት ቃለ-መጠይቅ ተበሳጭተው፣
ጥቂቶች እሜይሌን ከየት እንዳገኙት አላውቅም፣ የአቋሜን ስሕተት ሊያስረዱኝ ጽፈውልኝ ነበር። በጣም የገረመኝ ነገር ቢኖር፣ ሙያቸውና
ዕውቀታቸው በምንም መልኩ ከታሪክ ትምህርት የማይገናኝ ሁኖ ሳለ፣ በታሪክ ውስጥ ገብተው ሊፈተፍቱና ሊያስተምሩኝ ይሞክራሉ። ወይ ጉድ
አልሁኝ፣ ላምነው ስላልቻልኩ። ለነዚህ ዐይነቱ ታሪክ ማለት ማንም አፈ-ጮሌ ገብቶ የሚፈተፍትበት የጥናት ዘርፍ ይመስላቸዋል። ይኸንን ዐይነት
ክብረ-ቢስነት በኤርትራውያን ምሁራን ዘንድ አስቀድመን ስላየንና ሰለለመድነው፣ ብዙዎቻችን አንገረምም ይሆናል። ግን ታሪክ ሲደገም እያዩ ዝም
ማለት አላፊነትን መርሳት ነውና እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ተቃውሞውን በግልም በወልም በሥራ የማሳየት ግዴታ ያለበት ይመስለኛል4
። እንዳልኩት ይኸ
ጽሑፌ ከነዚህ አንጃ ግራንጃ ከሚነዙ ብዙ ውርጅብኝ እንደሚያመጣብኝ ርግጠኛ ብሆንም፣ እነርሱን ፈርቶ ወይንም ለማስደሰት ተብሎ በእውነት
የተመሠረት ሐቅን ላገር ሕዝብ ከማስተማርና ከማሳወቅ ወደኋላ ማለት የተጣለብንን አላፊነትን መርሳት ስለሆነ፣ ምንም ጊዜ ወደኋላ ማፈግፈግ
አይገባም።

ወደዋናው አርእስቴ ከመመለሴ በፊት አንድ ነጥብ ላንሣ። ይኸውም በኅብረ ብሔር የቆሙትን ይመለከታል። እነዚህ አፄ ምኒልክን በተመለከተ፣
በአቋማቸው እንደጐጠኞቹና እንደመንደርተኞቹ አክራሪዎች ባይሆኑም፣ ብዙውን ጊዜ የንጉሡን ደካማውን ጐን ማየትና መቀበል ያዳግታቸዋል። አፄ
ምኒልክ፣ ምንም እንኳ ወደር የሌላቸው ታላቅ መሪ ቢሆኑም፣ ሰው ናቸዉና፣ ሰው መሆናቸው አንዳንዴ በፍጹም እስከመረሳት ስለሚደርስ መጠንቀቅ
አስፈላጊ ነው። እውነት ከሁለት ጽንፈኞች ጐን ኑሮ አያውቅም። ሁሌዬ በመኻል ላይ መሆኑን አንርሳ።

ጽሑፌ በታቻለው መጠን አፄ ምኒልክ ማን እንደሆኑ፣ የኢትዮጵያን አንድነት መልሰው እንዴት እንዳሳደሱ፣ ከዚያም አገሪቷን እንዴት እንዳስተዳደሩ
ባጭሩ ሊገልጥ ይሞክራል። ለመሆኑ አፄ ምኒልክ ማናቸው ከሚል ጥያቄ ልጀምርና ከዚያ ወደሌላው አርእስት በረድፍ በረድፉ ልሂድ። ከመጀመሬ
በፊት ግን አንድ ነገር አጥብቄ ላሳስብ። ለሱም ጄነራል ጂገማ ኬሎ ካሉት ከፍተኛ ትምህርት ካዘለ ንግግር ልነሣ።

ጀነራል ጃገማ ኬሎን ታዉቋቸው እንደሆነ አላውቅም፤ ግን ጄነራሉ ገና በዐሥራ አምስት ዕድሜያቸው አካባቢ፣ ኢጣልያን ሀገራችንን ከወረረ በኋላ፣
ሽማግሌና ሕፃን ሳይለይ ሲገድል፣ ያገሩን ሀብት ሲዘርፍ፣ ሚስት ሲደፍር፣ ያልተከለውን ዛፍ ለገበያው ሲቈርጥ፣ ያላሳደገውን ፈረስ ቀምቶ ሲጋልብ፣
ያላቀናዉን መሬት ከሕዝብ ዘርፎ ከባሕርማዶ ላመጣው ወገኑ ሲሰጥ፣ ቤቶችንና ቅዱሳት ስፍራዎችን ሲያቃጥልና ሲያረኵስ አይተው፣
ወንድሞቻቸውንና እኅቶቻቸውን አስከትለው፣ ሊዋጉ ጫካ የገቡና፣ ኋላም በዚህ አፍላ ዕድሜያቸው፣ የሦስት ሺ ዐምስት መቶ አርበኞች መሪ የነበሩ፣
በብዙ ጐራ በመዋላቸው “የበጋው መብረቅ” የሚል ስያሜ የተሰጣቸው፣ ነፃነት ከመጣ በኋላም ለጄነራልነት ማዕርግ የበቁ መሪ ነበሩ። የኦሮሞ ብሔረ-
ሰብ እንደመሆናቸው፣ የልጅነታቸው ትልቁ ሕልማቸው፣ መላልሰው እልፍ ጊዜ ስለሰሙት፣ ሺ ግዳይ እንደጣሉት እንደቅድመ አያታቸው ጎዳና ነሞ፣
ብዙ ሰው በመግደል ጀግና መሆን ነበር። ታዲያ ይኸንን የሰማ አንድ ጋዜጠኛ ጀኔራል ጃገማን፣ “ልጅ ሳለህ ሕልምህ ለምን እንደቀድሞ አያትህ ሰው
በመግደል ብቻ ተወሰነ” ብሎ ቢጠይቃቸው፣ ጃገማ በጣም ሳቁና፣ “አየህ ጐበዝ፣ በዚያን ጊዜ ከሽማግሌዎቹና ከሞግዚቴ እሰማ የነበረው የቅድመ-አያቴን
ታሪክና ጦርነቱን ብቻ ነው። ሌላው ቀርቶ ከእረኛ ጋር እንኳ አልገናኝም ነበር። በቀበሮ ጒድጓድ ሁነህ ዓሣ ነባሪ ይታይሃለን። አይታይህም። ስለዚህ
እንዳሁኑ ልጆች ሐኪም፣ መሐንዲስ፣ ፓይለት፣ ሳይንቲስት … ለመሆን ላሰብ አልችልም። ምክንያቱ ደግሞ በኔ ዘመን ይኸ አልነበረም። እንደማንኛውም
ልጅ ሕልሜና ምኞቴ ከምሰማውና ከማየው የወጣ አይደለም” ብለው መለሱ። በጣም ጥሩ መልስ።

ጃገማ እንዳሉት ሰው የቀዬው ፍጡር ነው። አሳቡም ሆነ ምኞቱ የሚቀረፀውና የሚያንፀባርቀው በአካባቢውና በጊዜው ካለው፣ ካየው፣ ከሰማው ነው።
ያንድ መሪም ሆነ ሥራው መፈረጅ ያለበት እሱ በነበረበት ጊዜና ወቅት አንፃር እንጂ ለምን በኔ ጊዜ እንደሚሠራና እንደሚታሰብ አልሠራም ወይንም
አላሰበም ማለት አይቻልም። ለምሳሌ በብዙ አውሮጳውያን ዘንድ ከወደአንድ መቶ ተኩል ዓመታት በፊት፣ ሕፃናት በክፉ ዐይን ይታዩ ስለነበር፣
አለምንም ጥያቄ በተለያየ መልክ መግደሉ የተለመደና ከፍተኛ ተቀባይነትም ያለው ነበር። የኛ ሥራ አሁን እንደጭካኔ የሚታየውን እንደዚህ ዐይነቱ
ድርጊት መኖሩን፣ ለምንስ ያደርጉ እንደነበር ማወቅና በታሪክ ሂደት በጊዜያችን የመጣዉን መሻሻል ተገንዝበን በዚያው ላይ ይበልጥ እንዲሻሻል መገንባት
እንጂ ማውገዙ ዋጋ አይኖረውም። ሰንቱንስ አውግዘን እንዘልቃለን። ማውገዝ ብቻ ከሆነማ ማንኛውም የሰው ዘር የመኖር መብት የለውም፤ ከነአካቴው
ማለቅ አለበት። እያንዳንዱ ኅብረተ-ሰብ በታሪክ የፈጸመው ግፍ ተጽፎም ተነግሮም አያልቅም። የራስን ኅብረተ-ሰብ ዐመፅ እያስተሠረዩ፣ የሌላውን
ማጋነን ግን ፍርደ-ገምድልነትም ግብዝነትም ነው። ልክ በወንጌል ውስጥ የራሳቸውን ጉድ ሳያውቁ፣ ኢየሱስ አመንዝራይቱን ሴት በድንጋይ እንድትወገር
እንደጠየቁት ምሁራንና ፈሪሳውያን እንደማለት ነው። ይሁንና ዘመን በዘመን እየተተካ ሲሄድ፣ የሰው ልጅ ገጠመኝ እየሰፋ፣ የፈጠራውም ችሎታ
እየረቀቀ፣ የራሱም ሆነ የኅብረተ-ሰቡ ባሕርይና አስተሳሰብ እየተሻሻለ ይሄዳል፤ እየሄደም ነው። ከአውሬነት ወደሰብኣዊነት፣ ከግፍ ወደፍትሕ ወዳድነት
ያመራል።

ይሁንና ብዙዉን ጊዜ መሻሻሉን ያመጡት፣ በቀዬዉና በጊዜው አስተሳሰብና ልምድ ሳይገደቡ፣ አሻግረው ማየት የቻሉ በቊጥራቸው ጭብጥ የማይሞሉ
ሰዎች ናቸው። ፈረንጆች እነዚህን “enlightened” ይሏቸዋል። በአማርኛ ቋንቋችን “ከሣቲ” እንበለው። ሰው በአካባቢው ባህልና ልማድ ስለተዘፈቀ

3
 . የመጽሐፉ አርእስት Asafa Jalata, Oromo Nationalism and the Ethiopian Discourse: The Search For Freedom
and Democracy, Red Sea Press, 1998 ነው።
4
 . ለሊቅ አሰፋ ጀለታ መልስ፣ በጠበቃ ደብዳቤ ለዩኒቬርሲትው ተጽፎ፣ ፕረዚደንቱ ተገቢውን እርምጃ እንውስዳለን ብለው መልሰዋል። Page 4 of 15

ማየት ያልቻለዉን፣ ግን የተሻለ ኑሮና አስተሳሰብ እንዲያይ የሰውን አንጐል፣ አእምሮ የሚያበራ እንደማለት ነው። ባጭሩ፣ አንድ ሰው ወይንም ሕዝብ
ከተዘጋበት የባህልና የአሳብ ዋሻ ውጭ፣ ሰፊ ዓለም እንዳለ እንዲገነዘብ አላላ ሜዳውን የሚገልጥለት፣ የሚያሳይለት እንደዚህ ዐይነቱ ከሣቲ ነው።

አፄ ምኒልክም የቀዬአቸው ውጤት ቢሆኑም፣ ያሳለፉት ሕይወትና በየጊዜው ያጋጠሟቸው ሁኔታዎች አድማሳቸውን አስፍቶ፣ ከወዲህ ባሻገር ያለውን
እውነት አይተው፣ ለሌላውም እንዲከሥቱ አብቅቷቸዋል። የኢትዮጵያን አንድነት ለማሳደስና፣ ለዘመናዊ ሥልጣኔዋ መሠረት ለመጣል፣ በዘመኑ ከነበሩት
ታላላቅ ሰዎች ማንም እንደአፄ ምኒልክ የተሟላ ስጦታ የተሰጠውም ሆነ፣ ያለው መሪ አልነበረም ብል ስሕተት አይሆንም።

አፄ ምኒልክ ባባታቸው የንጉሥ ልጅ ቢሆኑም መርሳት የማይገባን አንድ ሐቅ አለ። እናታቸው ገረድ ናት። ምናልባትም በጦርነት ተማርካ እንደጊዜው
ልማድና ባህል ካንዱ የደቡብ ብሔረ-ሰብ በባርነት የመጣች ነበረች። ስማቸውም ቢሆን፤ ንጉሡ በተወለዱ ጊዜ፣ አያታቸው የመልካቸውን አለማማር፣
ዐይነ ፈጣጣ፣ ጥርሰ ገጣጣ መሆናቸውን በመገንዘብ፣ “ምን ይልህ ሸዋ፣ ምን ይልህ ሸዋ!” ሲሉ በማፌዝና በመገረም ያወጡት ነው እንጂ፣ የኋላ ኋላ
ትንቢትና ሕልም የሰፈነበት የኢትዮጵያ ዓለም፣ በትንግርት በማሳበብ አሳምሮት፣ ከመጀመርያው የኢትዮጵያ ንጉሥ ጋር ካያያዘው ከቀዳማዊ “ምኒልክ”
ጋር ግንኙነት የለውም። የሚገርመው ደግሞ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ዘውድ ሲጭኑ ስማቸውን ሳይቀይሩ የነገሡ የመጀመርያው ንጉሠ-ነገሥት ሳይሆኑ
አይቀሩም።

ይሁንና በአፄ ቴዎድሮስ ተማርከው እስከተወሰዱበት ጊዜ ድረስ፣ ያደጉት ከቤተ-መንግሥት ተባርረው ርቀው በመኖር፣ በናታቸው ሞግዚትነት በሌላ
ሀገር ከኦሮሞኛ ተናጋሪ ልጆች ጋር እየተጯጯሁ ነበር እንጂ፣ በድሎትና በቅንጦት በቤተ-መንግሥት ውስጥ አልነበረም። አባታቸውም ቢሆን ያገቡት
ሌላ ሚስት ናት። የምኒልክን አባትነት የተቀበሉትም፣ ወደው ሳይሆን፣ በናታቸው በተጠራው ስብሰባ ላይ ተገድደው ነው ይባላል። ታዲያ አፄ ምኒልክ
የመንግሥትን ሥርዐት የተማሩት፣ እንደገዛ ልጃቸው በታላቅ ጥንቃቄ ተንከባክበው ባሳደጓቸው ባፄ ቴዎድሮስ ሥር ሁነው ነው። ካፄ ቴዎድሮስ ጋር
መኖሩ፣ የሰሜኑን ባህልና አስተሳሰብ በቅርቡ ሁነው የመቅስምና የማዋሃድ ዕድል ሰጥቷቸዋል። ኢትዮጵያንም ለብዙ ዘመናት ሰላምና ዕረፍት ነፍገውዋት
ከሚያተራምሷት ባላባቶችና መሳፍንት እጅ፣ አንድነቷን መልሶ የመገንባትንም ፍቅር ከሳቸው የቀሰሙ ይመስላል። ከተራ ሴት ተወልደው ከተራው
ሕዝብ መኻል ማደጋቸው ደግሞ፣ የዚህን መደብ ኅብረተ-ሰብ ችግሩንና በደሉን፣ ምኞቱንና ሕልሙን በቅርቡ ሁነው እንዲያዩ ረድቷቸዋል ብዬ
አምናለሁ። እንደረዳቸውም ቀጥለን እንደምናየው ሥራቸው ራሱ ይመሰክራል።

ይኸ ሁሉ የሚያመለክተን አፄ ምኒልክ በግል ኑሯቸውና፣ በትውልዳቸው ዝርያ፣ ሕይወታቸዉን የቀረጸዉን የደቡቡንና የሰሜኑን፣ የገዢውንና የተራውን
ሕዝብ ባሕርይ ከመላ ጐደል ያንጸባርቃሉ ማለት ነው። ከዚያም አልፎ ተርፎ፣ የመጨረሻ ባለቤታቸው እቴጌ ጣይቱ ከኦሮሞ አባት ከጐጃሜ እናት
ናቸው። ወላጆቿ አፋቸውን የከፈቱት የአካባቢው ሰው በሚናገረው ቋንቋ ሁኖ፣ ለነገሩ አማርኛና ኦሮምኛ ይባል እንጂ፣ በየደማቸው ውስጥ ያለው ግን
የብዙ የኢትዮጵያ ብሔረ-ሰብ ቅልቅል ነው። የምኒልክ አባቶቻቸው ራሳቸው የአካባቢው ሕዝብ ዲቃላ ናቸው። እቴጌ ጣይቱ ባባታቸው የየጁ ኦሮሞ
ልጅ ቢሆኑም፣ በታሪክ ከጠቅላላው የኢትዮጵያ ሴቶች የሚለዩበት አንድ ነገር አለ። ግዕዝ ያዉቃሉ፤ ቅኔ ይቀኛሉ፤ በገና ይጫወታሉ፤ የውጩን ዓለም
ፖለቲካ አፍተልትለው ያዉቃሉ። ቅኔአቸውን በተመለከተ ባላቸው በሞቱ ጊዜ፡ ሲያለቅሱ፣

“ነጋሪት ማስመታት፣ እምቢልታ ማስነፋት ነበር ሥራችን፤
ሰው መሆን አይቀርም ደረሰ ጊዜያችን።” ብለው የገጠሙት፣ የግጥም ዕውቀታቸው በጣም የዳበረ መሆኑን ብቻ ሳይሆን፣ እሳቸው ራሳቸው የኢትዮጵያ
ሕዝብ ምን ያህል በባህል፣ በቋንቋ፣ በሃይማኖትና በትውልድ እንደተዋሀደና እንደተሳሰረ የሚመሰክሩ ብሩህና ሕያው ምሳሌ መሆናቸውን ያሳያል።

እንግዴህ በየዘመኑ መገናኛ መሣርያ ሁሉን ነገር አንዱ አፉን በከፈተው “ብሔረ-ስብ” በሚሉት የቋንቋ መነጽር ብቻ ለሚያዩት፣ ዘመናዊቷን ኢትዮጵያን
ያዋሀዷትና፣ ነፃነቷን ሳትነፈግ እንዲታድግ፣ ሕይወታቸውን እስከመሠዋት ድረስ በአድዋ ላይ የመሯትና የታገሉላት ባልና ሚስት፣ በየትኛውም ብሔረ-
ሰብ ሥር አይጠቃለሉም። የሚያገናኛቸው ኢትዮጵያዊነትና የኢትዮጵያውያን ቋንቋ ማለትም አማርኛ ብቻ ነው። እንደሁላችን መለዮአቸው ጥቊርነትና
ዲቃላነት ነው። በመልካቸው ጥቊር፤ በዘራቸው ቅያይጥ ነበሩ ማለት ይቻላል።

በሌላ መልኩ የአፄ ምኒልክና የእቴጌ ጣይቱ ጋብቻ በሰማይ የተደረገ ነው ለማለት እንገደላለን። ሁለቱም በሀብት፣ በትምህርት፣ በባሕርይም የተለዩና
ያልተመጣጠኑ ግለሰቦች ቢሆኑም፣ አንዱ የጐደለውን ሌላው ያሟላው ነበር ብቻ ሳይሆን፣ በደማቸውና በዘር ሐረጋቸው፣ ከመላ ጐደል ከመላው
የኢትዮጵያ ብሔረ-ሰብ ጋር የተሳሰሩም ነበሩ። አፄ ምኒልክም አገሪቷን የመሩትና ያስተዳደሩት እንደአባትና እንደእናት በመንከባከብ በፍቅርና በብልሃት
እንጂ እንደጥንቱዎቹም ሆነ እንደቀደሟቸው ሁለቱ ነገሥታት (አፄ ቴዎድሮስና አፄ ዮሐንስ) በኀይልና በማስፈራራት አልነበረም። በጐናቸው የእቴጌ
ጣይቱ ዐይነት ብቁና ቻይ ጓደኛ ባይኖሩ፣ የሥራቸው ውጤት የተለየ እንደሚሆን ጥርጥር የለኝም። የኢትዮጵያን ውህደት የወጠኑት ዳግማዊ አፄ
ቴዎድሮስ፣ በቀብሯ ጊዜ “እስኪ ጠይቁልኝ ርቃ ሳትሄድ፤ እቴጌ ተዋበች ሚስትናት [= ሚስት፣ እናት] ገረድ፣ ብለው ያለቀሱላት ብልህ፣ ጀግናና ውድ
ሚስታቸው በሞት ከተለዩአቸው በኋላ፣ ይበልጥ እንዲጨክኑ አድርጓቸዋል” ይባላል። ታዲያ እቴጌይቱ ቢኖሩ ያ ሁሉ ያዋሐዱት ሰፋፊ አገሮች
ከድተውአቸው፣ በመጨረሻ ላይ ጭብጥ የማትሞላ የመቅደላ ተራራ ንጉሥ ብቻ ሁነው ባልቀሩም ነበር ይሆናል። እዚህ ላይ መነሣት ያለበት ነገር
ቢኖር፣ የኢትዮጵያን የአንድነት ሥራ የወጠነው የቋራው ካሣ ኀይሉ (ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ) ሆነ፣ አንድነቱን ግብ ያስመታው የሸዋው ምኒልክ ኀይለ
መለኮት፤ የትዳርና የሥልጣን ጓደኞቻቸው የየጁ ሴቶች ነበሩ።

ከዚህ ጠቅላላ ገለጻ ተነሥተን፣ አፄ ምኒልክ ያዋሀዱትን አገር በምን መልክ አስተዳደሩ ወደሚል ሐተታ ገብተን፣ ባጭሩ እንመልከትና ከዚያም ቀጥለን
ባላጋራዎቻቸው ወደሚሰነዝሩባቸው ወዳንዳንድ ነጥቦች እንለፍ። አፄ ምኒልክ በጦር ኀይልም ሆነ፣ “ሕዝብ በከንቱ እንዳያልቅ፣ ሀገር እንዳይጠፋ
በሰላም ግበር” የሚለውን ጥሪያቸውን ተቀብለው በፍቅር በተዋሀዱት አገሮች፣ የዘረጉት አስተዳደራቸው መዋቅር ሁለት የተጠማመሩ ግቦችን ያካተተ
ነበር ማለት ይቻላል። አንደኛው ሕዝብን በግድ ሳይሆን በፍቅርና በዘዴ መግዛት ሲሆን፣ ለዚህም በሕዝቡ ዘንድ እሱ የለመደውና የሚያውቀው ያገሩ
ባላባት ተቀባይነት ይኖረዋል ብለው ስላመኑበት፣ የተማረከዉን ገዢ መልሰው በቦታው ይሾሙ ነበር። ካልሆነም ልጁን ወይንም ሕዝቡ ተሰብስቦ
የመረጠውን ያስቀምጡ ነበር። መዋጋትንም ይመርጡት የነበረው ባላባቱ፣ በሰላም ግበር ብለው አስቀድመው ደጋግመው ለላኩት ጥሪ፣ አሻፈረኝ Page 5 of 15

ሲላቸውና፣ ሌላ አማራጭ ሲያጡ ብቻ ነበር። ሁለተኛው ዓላማ፣ ከዚህ በላይ እንደገለጽነው፣ ዘመኑ አውሮጳዉያን፣ ነጭ ያልሆነውን ዓለም
የሚቀራመቱበት ወቅት ስለነበር፣ ቅኝ ገዢዎቹ አገሩን ለመያዝ ልባቸው እንዳይዳዳ በግዙፉ በይፋ ማስታወቅ ስለሆነ፣ እነዚህ አገሩ በአፄ ምኒልክ ሥር
እንዳለና፣ ቢዳፈሩም ጦርነቱ በቀጥታ ከሳቸው ጋር መሆኑን እንዲረዱ፣ ከማዕከላዊ መንግሥት የተሾመ የታጠቀ የጥበቃ ኀይል በያገሩ ማስቀመጥ ነበር።
የውስጡ አስተዳደር ሙሉ በሙሉ በባላባቱ እጅ ስለሆነ፣ ሕዝብ ካልተበደለ በስተቀር፣ የጥበቃው ክፍል ባስተዳደሩ ጣልቃ አይገባም ነበር።

በዚህ መልክ የተዋቀረው አስተዳደር ራሱን የቻለ እንዲሆን ሲባል፣ እያንዳንዱ ባላባት ዓመታዊ ግብር ይከፍላል። ከዚህም ግብር፣ የጥበቃው ክፍል
ለራሱ የሚበቃውን ቀንሶ፣ የቀረውን ለመንግሥት ግምጃ ቤት ያስተላልፈዋል። ሁኖም ግብሩ የተጣለበት የደቡቡ ሕዝብ ከዉህደቱ በፊት፣ ራሳቸውን
በቻሉ በጥቃቅን የባላባቶች መንግሥታት ቢጤ ሥር ስለነበር፣ እንደሰሜኑ ሕዝብ ለማዕከላዊ መንግሥት ለብዙ ዘመናት ገብሮ አያውቅም። ስለዚህም
ትውፊቱ በሌለበት አካባቢ ግብር በመጣሉ፣ እንደግፍ ተቈጥሮ በመተቸት፣ ያፄ ምኒልክን ሥራ በቅኝ-ገዢነት እስከመተርጐም አድርሷል። እንዲህ
ዐይነቱ አቃቂር መሠረተ ቢስ ከመሆን አልፎ፣ በታሪክም ቢሆን በምንም መልኩ የማይደገፍ ነው። እንግሊዞች “ግብርና ሞት ሁለት አይቀሬ የመኖር ዕዳ
ናቸው” እንደሚሉ ሁሉ፣ አፄ ምኒልክ በግዛታቸው ሰላም ለማስፈር፣ ጸጥታ ለማስከበር፣ የሚወጣውን ወጪ ለመሸፈን፣ እንደማንኛውም መንግሥት
ግብር የማያስከፍሉበት ምክንያት የለም። ይልቅስ ግብሩ፣ ጊዜውንና የሕዝቡን አኗኗርና ችሎታ ያገናዘበ በመሆኑ፣ ንጉሠ ነገሥቱ ምን ያኽል አስተዋይና፣
የአገራቸውንና የሕዝባቸውን የዘለቀታ ጥቅም በደምብ የተረዱ መሆናቸውን ፍርጥ አድርጎ ያመለክታል።

ግብሩ በጠቅላላ ከሕዝቡ ዐቅም ጋር የተመጣጠነ ሁኖ፣ የክልሉን አስተዳደር ወጪ ችሎ፣ ቀሪው ለመንግሥት ግምጃ-ቤት ገቢ ያደርግ ነበር። ይኸም
ኢትዮጵያ ከውጭ አገር መንግሥታትና ከዓለም-አቀፍ አበዳሪ ድርጅቶች ገንዘብ ሳትበደር፣ ባላት ገቢዋ ብቻ ተቈጥባ፣ እጅግ በጣም ሰፊ አገር
ለማስተዳደርና፣ አንዳንድ የልማት ሥራ ለማካሄድ አበቅቷታል። አለመበደሯ ለአብዛኞቹ የእስያና የአፍሪቃ ሀገሮች ከደረሰባቸው መጥፎ ዕጣ(በተለይም
ግብፅን የገጠማት ዐይነት)፣ ማለትም አበዳሪዎቹ ክሳራቸውን ለመሸፈን በሚል ሽፋን አገሯን በዋስትና ከመያዝ አድኗታል። አካባቢው የታወቀ የተፈጥሮ
ምርት ከሌለው፣ በሰሜኑ ክፍል እንደተለመደውና ከጥንት ይሠራ እንደነበረው፣ መሬቱ ተሸንሽኖ በተወሰነ ሰው ቊጥር ይደለደልና በሰው ልክ ግብር
ይጣልበታል። በተራ ቋንቋ ገባር የሚባል ቃል ከዚህ የመነጨ ነው። ትርጒሙም “ግብር የሚከፍል” ማለት ነው።

ባህሉንና አሠራሩን ባልተረዱትና፣ ከአገራቸውና ከራሳቸው ጥቅም አንጻር በሚያዩት የፈረንጅ ጸሓፊዎች ላይ በመመርኰዝና ከታሪክ ሂደት ጋር
ካለማገናዘብ የተነሣ፣ ገባር መጥፎ ትርጒም ተስጥቶት ይገኛል። ይባስ ብሎ፣ ከፀጥታ ጥበቃው ክፍል በማያያዝ “የነፍጠኛ ሥርዐት” ብለው የሚጠሩትም
አሉ። ታሪክ ማጣመም ካልተፈለገ በስተቀር ትርጒሙ እውነቱን አያንፀባርቅም። ከጊዜው የአገሩ ምጣኔ ሀብትና የሕዝቡ ዕድገት ደረጃ፣ እንዲሁም
ከዓለም ዐቀፍ ሁናቴና የመንግሥታት ኀይል አሰላለፍ አንጻር ሲታይ፣ ምንም ብንል፣ ያኔ ከገባር የተሻለ አማራጭ ከቶውኑ አልነበረም። ቢኖር ኖሮ፣ አፄ
ምኒልክ በደስታ እንደሚቀበሉት በምንም አልጠራጠርም። ለዚህም ያኔ በመጠኑ በሥልጣኔ ደረጃ ከሌላው ክፍለ አገር ሻል ብላ ለሚትገኘው ለድሬዳዋ
ከተማ በ፳፰ ሠኔ ፲፰፻፺፰ ዓ.ም. አስተዳደርዋ እንደሌላው አካባቢ በባላባት መሆኑ ቀርቶ በመማክርት፣ ማለትም በሥራ አስኪያጅ ቡድን
እንዲትተዳደር ብለው ያወጡት ሕግ እንደማስረጃ ሊጠቀስ ይችላል። እንደዚሁም የወላይታ ባላባቶች በተራው ሕዝብ ላይ በደል ቢያበዙ፣ ሽረዋቸው
ከጥብቅ ማስጠንቀቂያ5
 ጋር በ፪ ሠኔ ፲፱፻ ዓ.ም. ያቋቊሙት የሹማምንቶች መማክርትም ሌላ ምሳሌ ነው።

የገባር ሥሪት ባሕርይ በሰሜንም በደቡብም አንድ ዐይነት ሁኖ ሳለ፣ በኻያኛው ዘመን ላይ በደቡቡ ሥርዐት ሰፊ ለውጥ ስላሳየ፣ ልዩነቱ በአካባቢው
የተከናውኑ የሥራዎች ውጤት እንጂ ከመንግሥት የታወጀ አዋጅ ወይንም የተወሰደ እርምጃ ያመጣው ፍሬ አልነበረም። የሰሜኑ ክፍል በባላባቶች
በመበጥበጡ ምንም ዐይነት የልማት ሥራ ሳይካሄድበት በቁመናው ሲቀር፣ በደቡብ የዘመናዊ እርሻ ተዘርግቶ ሲያበቃ፣ ያመጣው ሀብትና ድሎት
ባላባቱንም ሆነ የማእከላዊ መንግሥት ሹሞችን ስለተፈታተነ፣ ሁለቱ አንዳንዴ በመተባበር፣ አንዳንዴ ደግሞ በተናጠል ተራ ሕዝቡን እያባበሉ ሆነ
እያዋከቡ፣ ወይንም ኀይል በመጠቀም መሬቱን እስከመንጠቅና ጥሎላቸው እስከሚሄድ አድርሰዉታል። ለምሳሌ አሩሲዎች ለከብታቸው ግጦሽ
እስከሚያጡ ድረስ መሬታቸዉን አጥተዉት ነበር። አፄ ምኒልክና ተከታዮቻቸው ጊዜውና ዐቅማቸው በፈቀደላቸው መጠን ከሕዝቡ ጐን ሁነው
አንዳንዴ በአዋጅ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ባለሥልጣኖቹን ሽረው ሌላ በመተካት ሳይታክቱ እንደተዋጉ ሰፊ ማስረጃዎች አሉ። የወለጋው ደጃዝማች ጆቴ
በተደጋጋሚ የመንግሥት ገንዘብ ሰረቀ ሲባል ዝም ያሉት አፄ ምኒልክ፣ ድሃውን አላግባብ ዘረፈ፣ ያልሆነ ቅጣት ቀጣ ሲባል ግን ምንም ሊታገሡት
አልቻሉም። በሸዋም በአሩሲም ኦሮሞች ከመሬታቸው መነቀላቸውን እንደሰሙ በአዋጅ ተመልሰው እንዲተከሉ አድርገዋቸዋል።

ይሁንና ሕግ ቢወጣም፣ ባለሥልጣኑ ተሽሮ በሌላ ቢተካም፣ ያገሩ አባባል “ሲሾም ያልበላ፣ ሲሻር ይቈጨዋል” ነበርና እምብዛም ንጉሠ-ነገሥቱ
እንደተመኙት አልቀናላቸውም። እንኳን ያኔ በዘመናዊ ሥልጣኔ ገና መዳዳት በመጀመር ያለች ኢትዮጵያን የመሰለ አገር ይቅርና፣ በዛሬይቱ በሥልጣኔ
ከዓለም ሁሉ በመነጠቀች አሜሪቃ እንኳን ሕግን ማስፈጸም ምን ያህል አስቸጋሪ እንደሆነ ብዙዎቻችን እናውቀዋለን። አፄ ምኒልክም ምንም እንኳ ለድሃ
እጅግ ቢቈረቈሩና በአዋጅም ሆነ፣ ታማኝ ገዢ በመሾም የተሻለ አስተዳደር ሊያመጡ ቢሞክሩ፣ ጊዜውና የባለሥልጣኖቹ ወደኋላ-ቀር አስተሳሰብ
አልተባበረላቸውም። ስለዚህም እሳቸውንም ሆነ የገባርን ሥርዐት በድፍኑ ማውገዝ ታሪክን ከማጣመምና ሂደቱን ካለመረዳት የተነሣ እንጂ እውነትነት
የለውም።


5
 . ከማስጠንቀቂያው የምንረዳው ንጉሠ-ነገሥቱ ምን ያህል በባላባቶች ላይ እምነት እንዳጡ ነው። ለመማክርቱ ከሰጡት ማስጠንቀቂያ ለምሳሌ
ያህል፣ ቀጨብ ላድርግና ልጥቀስ። እናንተን “መርጬአችሁ ወላሞ ላይ መሾሜ ድሃዬን እንዲትጠብቁልኝ ነው፤… ደንብ ካደረግነው ከዓመት ግብሩና
እኔ ከማዝዘው ትእዛዝ በቀር.. ድሃው በምንም እንዳይነካ ይሁን።” እንደቀድሞቹ ሹሞች “አላግባብ ከሠራችሁና፣” ድሃው ተበላሁ ብሎ ከጮኸልኝ፣
“በገንዘብ ብቻ ሳይሆን ብዙ ቅጣት ትቀጣላችሁ”። ድሃው ከናንተም አንዱ በደለኝ፣ ገንዘብ በላብኝ ቢል፣ ተሰብስባችሁ ነገሩን አጣሩና አስጨርሱ።
ካልተቻላችሁ ግን ወደኔ ላኩልኝ። … “ከባላገሩ ግን በምንም በምንም አመካኝታችሁ የምትነኩት ገንዘብ የለም።”
 Page 6 of 15

አንዳንዶቹ ታሪክን በማጣመም ብቻ አልተገቱም። ምኒልክ የኢትዮጵያው ሂትለር ብለው እስከመስበክ ደርሰዋል። መልሰው ያቋቋሙትን የኢትዮጵያን
አንድነት ራሱን፣ ከዚህ በላይ ጨረፍ አድርገን እንዳመለከትነው፣ከቅኝ ግዛትነት ጋር የሚያመሳስሉም አሉ። እንደነዚህ ዐይነቶቹ ስለሂትለርም ሆነ
ስለምኒልክ፣ ስለቅኝ አገዛዝም ምንም የማያውቁ ብቻ ሳይሆን፣ በእሬትና በሱካር፣ በጨለማና በብርሃን መካከል ያለዉን ልዩነት እንኳን ለይተው መንገር
የማይችሉ ቅለታሞች ናቸው ከማለት በስተቀር በሌላ ልፈረጁ አይችሉም። አንባቢዬን ልብ እንድትልልኝ እያማጠንሁ፣ እስኪ በነዚህ አርእስቶች ላይ
ላትኩር።

በሂትለር ልጀምር። ብዙዎቻችን እንደምናውቀው፣ ሂትለር የቆመው የራሱ ዘር ማለትም ጀርመን የሁሉንም ሰው ዘር ጨርሶ ፈጅቶ ሌላውን እንዲተካ
ነው። ሂትለር በጀርመን ዘር አምባገንነት እንጂ በሰው ዘር እኩልነት ከቶውኑ አያምንም። የዓለምን ሕዝብ በተፋሰስ ደርድሮ ሲያበቃ፣ ጥቁሮቹን
ያስቀመጠው ከሥሩ ዕርከን ነው። በሱ አስተሳሰብ፣ እልቂታቸዉም መፈጸም ያለበት ከሥር ካለው ጀምሮ ነው፣ ማለትም ከነዚሁ አፄ ምኒልክን ከሂትለር
ጋር ከሚያመሳስሉት ኢትዮጵያውያን ራሳቸው።

ከዚህም አልፎ፣ በሂትለር ዘንድ ሁሉም ጀርመን የጠራ ስላልሆነና፣ የጀርመንን ሕዝብ ባሕርይ ስለማያንፀባርቅ፣ ጠንቀኞች ናቸው ያላቸዉን አካለ-
ስንኩሎቸን፣ ደካሞችን፣ በሽተኞችንና፣ አጭሮችንም ጭምር ፈጅቷቸዋል። እነዚህ የፈረደባቸው የመጀመርያው ድርጎው ናቸው። ችግር ባይገጥመው
ኖሮ፣ ተራው በሱ ዘንድ በደምብ ነጣ ባላሉት ጀርመኖች በሆነ። የዓለም መንግሥታት እንደነቁ፣ ተረባርበው የቀረዉን ሌላዉን እምነቱን እግብር ላይ
ከማዋሉ በፊት አጠፉት እንጂ፣ ዝም ቢባልና ዕድሉ ቢገጥመው፣ በእምነቱ መሠረት ጥቁሮቹ መጀመርያዎቹ በሆኑ ነበር። ይሁንና መንግሥታቱ
ሊያጠፉት የቻሉት፣ አጠገቡ የነበሩትን ስድስት ሚሊዮን አይሁዶችን በአሰቃቂ ሞት ከፈጀ በኋላ ነው። በቅርብ ጊዜ እንደሰማሁትና እንዳነበብሁ፡
በአገራችን በዘዉገኝነት ጽንፈኞች የሚመሩት የሂትለር አድናቂዎችም፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ባንዳንድ ብሔረ-ሰብ ላይ የፈጸሙት እልቂት፣ ልክ ይኸንኑ
ኢሰብኣዊ ዐይነት ድርጊት ሳይተካከለው አይቀርም። ግን የአሁኑ የአገራችን ሰው ከመጮህና ከመለፍለፍ አልፎ በድርጊቱ መዘገነኑን በግብር ስለማያሳይ፣
ከእነዚህ አረመኔዎች አብዛኞቹ ካገር ቤት ወጥተው እንደሌላው ንጹሓን ስደተኞች መስለው፣ ማንም ሳይነካቸው፣ በምዕራብ አገር ተንደላቅቀውና
ተንፈላስሰው እየኖሩ ናቸው። ይኸም ኢትዮጵያውያን በንግግር እንጂ በተግባር ግን ምንም ያህል የሚረቡ እንዳልሆኑ ያስረዳል።

ወደዋናው ነጥብ ልመለስ። አፄ ምኒልክ ሂትለር የቆመለትን ሁሉ የሚፃረሩ ናቸው ቢባል በፍጹም ማጋነን አይሆንም። በሰው እኩልነት የሚያምኑ
እንደመሆናቸው፣ በዘር፣ በቋንቋ፣ በሃይማኖትና በባህል የተመሠረት የማንንም ልዩነት አይደግፉም። ለሰው ሕይወት ከፍተኛ ክብር እንዳላቸው፤ ከዚህ
በላይ በተደጋጋሚ እንደተገለጸው ለድኻ እጅግ ርኅሩኅና ተቈርቋሪ መሆናቸውን ሥራቸውና ጽሑፎቻቸው በሰፊው ይገልጻሉ። ለምሳሌ ያህል ጥቂቶቹን
ከዚህ በታች አሰፍራለሁ።

በሥልጣኑ በመጀነን፣ የገዛ ሕዝቡን ያጠቃ ለነበረ የጂማ ገዢ አባ ጂፋር ሲጽፉ ያሉት፣ ፈጣሪ መርጦህ ገዢ ቢያደርግህ፣ “በሰው መጨከን አይገባም።
ለስው ቢያዝኑ ዕድሜ ይሰጣል” ነው። ጣልያኖች ከተማረኩ በኋላ፣ ዓለም እስከሚገረም፣ ጠላቶቻቸው ራሳቸው ማመን እስከሚዳያግታቸው ድረስ፣
በክብር ይዘዉአቸው ተንከባክቧቸዋል። “የሰው ደም ለምን በከንቱ ይፈሳል” በማለት ወደ አድዋ ጦርነት ላለመሄድ ፈልገው ነበር። ጣሊያኖች ግን
ልመናቸውን እንደድካምና ፍርሀት በመቊጠር፣ ደጋግመው “አለመግባባታችንን በሰላም እንፍታ” ብለው ላደረጉት ልመና በሙሉ፣ አሻፈረኝ ሲሉ ብቻ
ነው ውጊያን የመረጡት። እንደገና በአምባላጌ ከተሸነፈ በኋላ፣ በመቀሌ ውጊያ ለብዙ ቀናት በጣም ጦራቸዉን የፈጀው የጣሊያን ሠራዊት በውኻ ጥም
ሊሞት ሲል፡ በሰላም ያሳልፉን ቢሏቸው ቢማረክ፣ አፄ ምኒልክ፣ የጦር መሪዎቻቸዉን ተቃዉሞ ዝም አሰኝተው፣ ጠብታችውን እንደያዙ መጫኛና
መጋለቢያ ከብት በገንዘባቸው ካገሩ ነጋዴ ገዝተው ሰጥተውት፣ በአጃቢ ነው የሸኙት። ይኸ ብዙ ያለም የጦር ጠበብቶችን እንኳን አስደንቋቸዋል።
አንዳንዶቹ (ጣሊያኖችቹን ጭምር) ምንኛ ጅል ናቸው እስከማለትም ደርሰዋል። ጅል ግን አልነበሩም። ዘዴኛ ናቸው። ጦርነቱን በጥብቅ ይከተል
ለነበረው ዓለም፣ ምን ያህል ሰላም ፈላጊ መሆናቸዉን ብቻ ሳይሆን፣ ሥልጣኔ የሚያስፈልጋቸው ኢትዮጵያዉያን ሳይሆኑ፣ ታዲያ ባሕር አልፈው፣ ብዙ
አገር ሰንጥቀው መጥተው፣ የሰውን ልጅ በግፍ በገዛ ሀገሩ ሊጨፈጭፉ የሚፈልጉ ጣሊያኖች መሆናቸውን ሊያስረዱ ነው የፈለጉት።

ይኸንን ዐይነት ርኅራኄና ደግነት ያሳዩት በውጭ አገር ጠላት ላይ ብቻ አይደለም፣ ባገራቸዉም ሰው ላይ ጭምር ነው። የጐጃሙ ንጉሥ ተክለ-ሃይማኖት
በተሸነፉ ጊዜ በጣም ቈስለው ሰለነበር፣ እንደተማረኩ በጋቢያቸው ቊስሉን ጠርገው እንዲታከሙ አድርገው ሲያበቃ፣ አዲስ-አበባ ወሰዷቸው። እዚያም
የንጉሥነታቸዉን ማዕርግ በምንም መልክ ሳያጐሉ ተንከባከቧቸው፤ በየቀኑም ይጐበኟቸዉና አብረውዋቸው ይበሉ ነበር። የጐጃም ጦር መሪ ራስ ደረሶ
አንድ ቀን ለቀልድ፣ “አፄ ምኒልክ ቢሸነፉ ምን ባደረግህ ነበር” ብሎ ሲጠየቅ፣ “እኛማ ብናሸንፍ ኖሮ፣ ቈርራርጠን ለአሞራ ነበር የምናበላው” ነው
ያለው። መልሱ አላንዳች ክርክር፣ የአፄ ምኒክን ታላቅነት ጥርት አድርጎ ያሳያል። እንዲሁም፣ ብዙ ጦር የፈጀባቸው የወላይታው ንጉሥ ጦና ሳይማረክ
ቢሸሽ፣ አፄ ምኒልክ፣ “እንዳያመልጥ ያዙልኝ” ብለው፣ ቈስሎ እንደተያዘ፣ ከዙፋናቸው ወርደው ከተቀበሉትና፣ “እንዲያው በከንቱ ሕዝብ አስጨረስኽ”
ብለው ከወቀሱት በኋላ፣ ቊስሉን አጥበዉና፣ በጋቢያቸው ጠርገው አሳክመውት ሲያበቃ፣ ሕዝቡን ሰብስበው፣ “ከእንግዴህ የሚያስተዳድርህ ልጄ
ወዳጄ ጦና ነውና ተገዛለት፤ ዐውቆ ሳይሆን ሳያዉቅ፣ እኔን የበደለ መስሎት፣ ሕዝብ አስጨረሰ እንጂ … ቂም የለንምና መልሼ እሱን ሾሜልሃለሁ” ነው
ያሉት።

በየቦታው እንደንጉሥ ጦና ተመልሰው የተሾሙት ባላባቶች፣ በገዛ ሕዝባቸው ላይ ግፍ መሥራት አናቆምም ቢሏቸው፣ የተጻጻፉት መልእክቶቻቸው፣ አፄ
ምኒልክ ምን ያህል “ድኻዬ ተበደለ” ለሚሉት ሕዝብ እንደሚቈረቈሩ በግልጥ ያሳያል። ለምሳሌ ያህል ብቻ ሦስት ልጥቀስ። አባ ጂፋር በባርያ ንግድ
ገናና የሆነችዉን ጂማን በሥርዐት እንዲያስተዳድርና ንግዱን አንዲያቆም ቢመከር፣ የአገሩን ሰው በባርነት መሸጥ ቢያቆምም፣ ወደአገሩ በሚገባው ኦሮሞ
ላይ ግን ጭካኔውን ቀጠለ። በዚህ ሥራው የተቈጡት አፄ ምኒልክ፣ “ወዳገርህ የመጣውን ጋላ … ከእጄ ገብተህ ጭቡ አድርገህ ባርያዬ ነህና፣ አንተንም
ልበድልህ፤ ልጅህንም አምጣና እንደከብት ልሽጠው፣ ልለውጠው አትበል፤ …የሰው ባርያ የለውም፤ ሁላችንም የእግዚአብሔር ባሮች ነን።” ብለው
ገሠፁት። እንዲሁም የወለጋው ገዢ ደጃዝማች ጆቴ ደግሞ የሕዝቡን መብት እየረገጠ፣ የተገፋው እንደጊዜው ልምድ ወደጃንሆይ እንዳይሄድ ቢከለክል፡
ከአፄ ምኒልክ “የተበደለ ድኻ ከኔ ዘንድ እንዳይመጣ አትከልክል፤ ተበደልሁ ብሎ ከጮኸ ደግሞ ጭራሽ ከሹመትህ እሽራሃለሁ” የሚል የቊጣ ደብዳቤ
ደረሰለት።
 Page 7 of 15

ድኻን መበደል፣ በተለያየ መልኩ በሁሉም ግዛቶች የተስፋፋ ነው። የጐጃሙ ገዢና የአፄ ምኒልክ ከፍተኛ ባለሟላቸው የነበረው ራስ ቢትወደድ መንገሻ
አቲከም በደብዳቤ ተገሥፆ፣ የቅርብ ድኻውን ማሠቃየት እንዳቆመ፣ ንጉሥ አይደርሱብኝም በማለት፣ ያነ ሻንቅላ በመባል የሚታወቀውን ሕዝብ ባርያ
እያደረገ አጒላላ፣ አሰቃየ። አፄ ምኒልክ ነገሩን በሰላዮቻቸው እንደሰሙ፣ እየገበረ የሚኖረውን “ሻንቅላ … እንደ ከብት ሁሉ ባመት ባመቱ እየመለመልክ
ታስወጣለህ አሉ። …. ልጅህንም ስትድር የሰጠኸውን ሻንቅላም ሰምተናል። እንግዴህ ግን አንድ ሻንቅላ ተመልምሎ ካገሩ ወጣ ያሉኝ እንደሆነ፣ ሁለተኛ
እኔና አንተ መገናኛ የለንም።” ብለው የዛቻ መልእክት ላኩለት።

አፄ ምኒልክ ደግ ብቻ ሳይሆኑ ቀልደኛም ናቸው። በልጅነቴ ያነበብሁት መቼም የማልረሳ አንድ አፈ-ታሪክ አለ። በራቡ ዘመን ለማኝ እየመጣ፣
አጋፋሪዎቹ ችላ እያሉ ምንም ሳይሰጠው እየሄደ ነው የሚል ወሬ እንደሰሙ፣ አፄ ምኒልክ በግቢያቸው አንድ ደወል አሰቀሉ። ደወሉ በተደወለ ቊጥር
አስፈላጊውን የሚሰጥ ሠራተኛ ተቀጠረና ሁሉም ተደሰተ። አንዱን ቀን ግን አንድ ለማኝ ቢጤ ደውሎ ምን አስፈለገህ ቢባል፣ “ለማኝ እንኳ
አይደለሁም፤ የጃንሆይ ዘመድ ነኝና ላገኛቸው ፈልጌ ነው” ብሎ ሲመልስ፣ አፄ ምኒልክም ጉዳዩ እንደተነገራቸው አስገቡት አሉና ገባ። እያጫወቱት ራስ
ወረዳውን ቢያዩ፣ ዝምድናው አልታይ ሲላቸው ዝምድናችን በማን ነው ቢለው ቢጠይቁት፣ “ጃንሆይ፣ ባያቶቻችን በአዳምና በሔዋን ነዋ” አለ። ደግ
ቢለው አንድ ብር ሰጥተው ሲሸኙት፣ ጃንሆይ፣ እንዴት አንድ ብር ብቻ ሰጥተውኝ ይሽኙኛል ቢላቸው፣ “አዪ የተከበርክ እንግዳዬ፣ ባዳምና በሔዋን
ለሚዛመደኝ ሁሉ ቢሰጥማ ላንተ እኮ እሷም ቢትሆን አትደርስህም ነበር ” አሉ ይባላል።

አስተዳደራቸውን በተመለከተ፣ የውጭ ሀገር ጸሓፊዎች ራሳቸው አፄ ምኒልክ ኢትዮጵያን በጥበብና በፍቅር እንደሚያስተዳድሩ፣ ሕዝቡም
እንደሚወዳቸው ደጋግመው ይናገራሉ። አንድ ዊልቤ የተባለ በ1893 ዓ.ም. የደቡቡን አገር እስከሩዶልፍ ሐይቅ ድረስ ዙሮ ከጐበኘ በኋላ፣ “በዳር ሀገር
ያለው ሕዝብ በሙሉ ምኒልክ መልካም ሰው ነው ይላል፤ ምኒልክ ሁሉም ሰው በሃይማኖቱ ይደር ስላለ፣ በሕዝቡ መሀል አድልዎ ስለማያሳይና ጉልበት
ስለማይጠቀም ይወዱታል። የሚያወሩትም እንደሌሎቹ ንጉሦች ስለመሰለን ሸሽተን ነበር። በኋላ ግን ስሕተታችንን ስናዉቅ ይቅርታ ጠይቀን ተመለስን፤
… አሁን ግብራቸዉን እየገበሩ በሰላም ይኖራሉ።” ሲል ጽፏል። በቅርቡ በኢትዮጵያ ጥናት በመላው ዓለም ገናናነቱ የታወቀው ሰመ-ጥሩ ሊቀ ሊቃዉንት
ኡለንዶርፍ፣ “በምኒልክ ዘመን ያገሪቱ ክብር ከፍ አለ። የዘመናዊ አስተዳደር መሠረትም ተጣለ… ንጉሡም ያስተዳድሩ የነበሩት በዘመናዊነትና በጥበብ
ነው” ሲል ይናገራል።

እንግዴህ አፄ ምኒልክን ከሂትለር ጋር የሚያዛምዱትን ሰዎች የሚደግፋቸው ምንም ዐይነት መረጃ የላቸውም እያልኩ ነገሩ እንዳይንዛዛ በዚሁ ላብቃና
አሁን ኢትዮጵያን መልሶ የማዋሀዱን ሥራ ከቅኝ አገዛዝ ጋር የሚያመሳስሉትን ለማተት ልመለስ። ቅኝ ግዛት ማለት ባጭሩ የሌላውን አገር በኀይል
ወስዶ፣ ሀብቱን ዘርፎና ነጥቆ፣ ሕዝቡን ጨቁኖ መግዛት ማለት ሲሆን፣ ቅኝ ገዢ ያገሩን ሀብት ከመዝረፍ ውጭ ለነዋሪው ሕዝብ ደንታ የለዉም።
ይልቅስ ተገዢው ወገን ዝቅተኛ መሆኑን እንዲረዳ፣ ከገዢው ክፍል ጋር የእኩልነት ስሜት በፍጹም እንዳይሰማው፣ የራሱን ወገን ክብርንና ልዕልናን
የሚያረጋግጡ ደንቦችን ያወጣል። በአሽከርነት ሥራ ተቀጥረው ካልሆነ በስተቀር፣ በሌላ የሥራ ዘርፍም ሆነ፣ ጥሩ ገቢና ትርፋትርፍ በሚያመጣ ሙያ
እንዳይሰማሩ ያግዳል። ዋናው ዓላማ በአገሩ የራሱን ሕዝብ ለማስፈርና ለመቈጣጠር ስለሆነ፣ ባላገሩን ከለምለም መሬቱ ነቅሎት፣ ቀስ በቀስ በሰብኣዊ
መንገድ ሙቶ እንዲያልቅ ሲል በማይፈልገው ኰረኰንች መሬት ላይ ያጒረዋል።

ባጭሩ፣ የቅኝ ገዥዎች ዋና ዓላማቸው፣ ባላገሩን እንጨት ለቃሚ፣ ዉኻ ቀጂ፣ መሬት ቆፋሪ ማድረግ ነው። ባላገሩ ራሱ በከፈለው ግብርና፣ በላቡ
በሠራው መንገድም ሆነ የሕዝብ ማመላለሻ ላይ እንኳን መሄድ አይፈቀድለትም። ከተፈቀደም በንቀት “ለአገሬው ብቻ” ተብሎ በተመለከተበት በወራዳና
ብስብስ ክፍል እንጂ ፈረንጁ የሚቀመጥበት ከቶውኑ አይደፈርም።

የሴትንና የወንድን የወሲብ ዓለምንና ግንኙነትን በተመለከተ፣ ጋብቻና የርስ በርስ መቀራረብ ቀርቶ፣ ባላገሩ ፈረንጇን አትኩሮ ቢያያት እንኳ ተዳፈርኽ
ተብሎ ሊቀጣ፣ ሊገደል ይችላል። ለምሳሌ ያህል፣ የቦትስዋናው አልጋወራሽ የነበሩትና ኋላም አገሩን ከነፃነት በኋላ ለብዙ ዘመን ወደከፍተኛ ብልጽግና
የመሩት አቶ ሠረፀ ካማ፣ በተማሪነታቸው ወቅት በእንግሊዝ አገር በኦክስፎርድ ዩኒቬርሲቲ እያጠኑ እያሉ፣ ካንድ ተራ እንግሊዛዊት ጋር ሲወጡ ቢገኙ፣
[ነጭ] ተዳፍሯል ተብለው በቅጣት ትምህርታቸውን አቋርጠው ወዳገራቸው እንዲመለሱ ተገደዱ። ወደዚያ ሩቅ ሳንሄድ በጐረቤቶቻችን በኢጣልያን፣
በፈረንሳይና በእንግሊዝ ቅኝ ገዢዎች ሥር የነበሩትን ኬንያኖችንና ሱዳኖችን፣ ሱማሌዎችንና ኤርትራዉያንን ማየት ብቻ ይበቃል። በኢትዮጵያ ምድር
ላይ ኢትዮጵያውያን በነጮች ለጋብቻ ሲለመኑና በብዛትም ሲጋቡ፣ በነዚህ አገሮች ግን የሕልም እንጀራቸው እንደነበር ድፍኑ ዓለም ያውቀዋል። ሌላው
ቀርቶ ደፍረው በማየታቸው እንኳን እስከሞት ድረስ ከፍተኛ ቅጣት እንደተቀጡ የሚያሳዩ ሰፊ ማስረጃዎች አሉ።

በዚህ አንጻር ጥሬ ሰው ብቻ ነው ያፄ ምኒልክን ሥራ ከቅኝ ግዛት ጋር የሚያመሳስለው። አፄ ምኒልክ ልጆቻቸውን የዳሩት በጦር ሜዳ አሸንፈው
ላስገበሩት ባላባቶች ሲሆን፣ ባለሟሎቻቸው ደግሞ አብዛኞቹ ድል ተመትተው ምርኮኞቻቸው የነበሩ ሰዎች ናቸው። ከነዚህም አብዛኞቹ ከኢምንትነት
ተነሥተው በአገርና በዓለም ደረጃ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል። ይኸንን በመረዳት ነው አፈ-ታሪክ ፊታዉራሪ ሀብተጊዮርጊስና ደጃች ባልቻ (ታሪኩ
እንደሰው ይቀያየራል) ድል የተመቱበትን ቦታ ደርሰው፣ አንዱ ለሌላው “ይኸ እኮ የተማረክንበት ሰፈር ነው” ቢል፣ አንደኛው ቀበል አድርጎ፣
“የተማረክንበት ሳይሆን፣ የተባረክንበት ነው ብትል ይሻላል” ሲል መለሰለት የሚለው።

አንድነትን ከመፍጠራቸው በፊት፣ ከላይ እንዳየነው፣ በየቦታው ይገዛ የነበረው የባላባቶች መንግሥት፣ የራሱን ሕዝብ ከታጐረበት ክልሉ ውስጥ
እንዳይወጣ ሲያስገድድ፣ ከሌላው አካባቢ ወደሱ አገር የሚገባውን ደግሞ ብዙውን ጊዜ ለባርነት ስለሚፈለግ ተመልሶ ካገሩ እንዳይወጣ ይከለክል
ነበር። አፄ ምኒልክ የኢትዮጵያን ሕዝብ ከዚህ ሁሉ የክልል መንግሥት አሰቃቂ ጭቈናና እሰር ነፃ አስወጥተው፣ በወደደበት እንደፈለገ እንዲኖር አደረጉ።
ልማዳቸውንም አንለቅም ላሉት እንደነጂማ ዐይነቶቹ ባላባቶች ደግሞ፣ “ማንም ሰው እወደደበት ቦታ ላይ ይኖራል እንጂ … በምንም መልክ ሊትይዘው
አይገባም፤ ድኻው እወደደው፣ እተመቸው ቦታ ይደር” ብለው የሰጡት ትእዛዝ ማንኛዉም የቅኝ ገዢ ያራምድ ከነበረው መርህ ጋር በጣም ተፃርራሪ
ነበር ማለት ይቻላል።
 Page 8 of 15

ይልቅስ አፄ ምኒልክ ያደረጉት ታላቅ ሥራ ቢኖር፣ በየቦታው በነዚህ አምባገነን ባላባቶቻቸውና፣ ንጉሥ ነን ባዮች ገዢዎቻቸው ሥር፣ እንደእስረኞች
ከጠባቡ ግዛታቸው ውስጥ ታጉረው፣ በሚዘገንን ጭቈና ይማቅቁ የነበሩትን ኅብረተ-ሰቦች ነፃ አውጥተዋቸው፣ ባሰኛቸው ቦታ እንዲኖሩ፣ የመላዋን
ኢትዮጵያን ምድር ሀብታቸው ማድረጋቸው ነው። በቅርብ ጊዜ፣ አንዳንድ የጐሣ ጽንፈኞች አፄ ምኒልክ ያዋሀዷት ኢትዮጵያ “የኅብረተ-ሰቦች እስር-ቤት
ናት” እያሉ መስበክ ጀምረዋል። ታሪክን ባያውቁት ነው እንጂ እውነቱ ግን በባላባቶች ክልል ውስጥ ታስሮ የነበረውን ሕዝብ ነፃነት አቀናጀውለት፣
በፈለገበት ሄዶ እንዲኖርና፣ በሚሻው ሙያ እንዲሰማራ፣ ሕልሙን እውን እንዲያደርግ ሰፊ አገር ገንዘቡ አደርገው በእጁ ሰጥተውለታል።

አፄ ምኒልክ የሚወቀሱት ኢትዮጵያን በጦር ኀይል መልሰው አንድ ማድረጋቸው ከሆነ፣ ማንም መንግሥት አዲስም ሆነ ፈራርሶ የነበረው አንድም
ሳይቀር በሙሉ የተፈጠረው በጦር ኀይል ነው። በሕዝብ ስምምነትና ፍቅር የተቋቋመ መንግሥት በታሪክ የለም፤ ታይቶም አይታወቅም። አለ የሚል
በቅዠት ዓለም የሚኖር ብቻ ነው። ምኒልክም ሰው እንደመሆናቸው ሥራቸው የተከተለው ይኸንኑ ሕግ ነው። ከተራ ሰው የሚለዩት ባስተዋይነታቸውና
አርቆ በማየታቸው ነው።

መንግሥታት የሚቋቋሙት ደግሞ እንደሳቸው ባሉት አሻግሮና አርቆ ማየት ችሎታ ባላቸው ሰዎች ሲሆን፣ እነሱም ባንድ ታሪካዊ ተጨባጭ ሁናቴ
ተመሥርተውና፣ ጊዜውንና አጋጠምኝን በመጠቀም ነው። ለዚህም አሁን የሚናደንቃቸው መንግሥታት እንዴት አንደመጡ ማየት ይበቃል። ጥቂቶቹን
ልጥቀስ። ኀያሉና ገናናው የሮም መንግሥት ሲወድቅ፣ ፈራርሳ በተለያዩና፣ የርስ በርስ ጦርነት ዋና መለዮአቸው በሆኑ፣ የጐሣ ባላባቶችና መንግሥታት
ትገዛ የነበረችዉ ኢጣልያ፣ ጥንት በሮም እንዳንድ አገር ሁና መተዳደሯን መሠረት አድርጋ ነው፣ ከአንድ ሺ ሦስት መቶ ዘጠና አምስት ዓመታት በኋላ
እንደገና ተመልሳ የተቋቋመችው። እሥራኤል በቅዱስ መጽሐፍ ታሪክ ተመሥርታ ነው፣ በፈረሰችው በሁለት ሺ ገደማ ዓመቷ የተፈጠረችው። ጀርመን
ሦስት ሺ ከሚያክሉና ርስ በርስ ከሚፋጁ የጐሣ ባላባቶች በፈረንጅ አቈጣጠር በ1871 ዓ. ም. አንድ አገር የሆነችው ከኢምንት ተነሥታ ነው፤ ከዚያ
በፊት ጀርመን የተባለ አገር በታሪክ አልነበረም። አንድነቱን የመፍጠሩ ሥራ ለዘመናት በሰላም ቢሞከር ከንቱ ሁኖ ቀረ። በመጨረሻ ጀርመን ተዋሂዳ
ዛሬ በዓለም የሚትደነቅ አንድ ታላቅ ሀገር ለመሆን የበቃቸው፣ ያኔ የፕሩሲያ መሪ የነበረው ኦቶ ቢስማርክ፣ “በብረትና በደም” ከሚለው መፈክሩ
ተነሥቶ ከጐረቤቱ መንግሥታት ጋር ወዶ ባጫጫረው የጦርነት ኀይልና ባፋሰሰው ደም ነው።

ምኒልክ ግን አንድነቷ በተናደው በሁለት መቶ ያህል ዓመት ጊዜ ውስጥ ብቻ ነው ኢትዮጵያን መልሰው ያዋሀዷት። አጋጠመኙ የአውሮጳ አምባገነን
መንግሥታት አፍሪቃን ቅኝ ግዛታችው ለማድረግ መቀራመት ነበር። የአፄ ምኒልክ ዋና ሥጋታቸው ኢትዮጵያን የከበቧት አውሮጳውያን፣
ከአፍንጫቸውና ከሆዳቸው ባሻገር አልፈው ማሰብ የማይችሉ ባላባቶችን፣ በስጦታና በገንዘብ በማባበል፣ግዛቶቿን እየቈራረሱ እየያዙ ሰለነበር፣
ኢትዮጵያን አንድ ለማድረግ የወሰኑት ይኸንኑ ድርጊት ለማቆም ነው። ስለዚህም በባላባቶች እጅ ወድቀው የነበሩትን ግዛቶቿን መልሰው ከአንድ
ማእከላዊ መንግሥት ሥር በማድረግ ታደጓቸው። በዚህም ሥራቸው ማንኛዉም አእምሮ ያለው ኢትዮጵያዊ መኲራት ይገበዋል። እዚህ ላይ መረሳት
የሌለበት ነገር ቢኖር፣ ኢትዮጵያዉያን እንደአብዛኞቹ የዓለም አገሮች አንድነታቸው በባዕድ ተሠርቶ አልተሰጣቸውም። ምንም ጊዜ ቢሆን ራሳቸው
የታሪካቸው ሠሪዎች እንጂ ተቀባዮች ሁነው አያውቁም። ፍጡር እንደመሆናቸው መጠን ርስበርስ ቢጣሉም፣ አለመስማማታቸውን በመጠቀም
በታሪካቸውና በሀገራቸው ጣልቃ ሊገባባቸው የሞከረውን ግን ከመሪያቸው ጐን ተሰልፈው ተባብረው አጥቅተውታል።

አንዳንድ የፖለቲካ ጮሌዎች ነን ባዮች(አሁን በሥልጣን ያለውን መንግሥት ጭምር) አፄ ምኒልክ በአውሮጳውያን ኢምፔርያሊስቶች (ቄሳራዊ) ኀይሎች
ተረድተው በኢትዮጵያ ነፃ የነበሩትን አገሮችና መንግሥታት በቅኝ-ግዛትነት ያዙ እያሉ ይሰብካሉ። በጣም የሚገርመው ዛሬ አገሪቷን እየገዛ ያለው
መንግሥት ደፍሮ እንደዚህ ማለቱ ነው። ዝንጀሮ የራሷን ቂጥ ቲታ የሌላውን መልከ-ጥፉ ነው ትላለች እንደሚሉት ዐይነት ነው። አንደኛ፣ ሁሉም
እንደሚያውቀው፣ የአሁኑ መንግሥት ከጫካ ውስጥ ወጥቶ ወደአፄ ምኒልክ ቤተ-መንግሥት እየገሠገሠ ሊገባ የበቃውና፣ ድፍኑ ዓለም
እንደሚመሰክረው ሕዝቡን ረግጦ በጭካኔ እየገዛ ያለው፣ ራሱ ባመረተው መሣርያና በሠራው ጦር እንዳልሆነ የአደባባይ ምሥጢር ነው። ባይሆን አፄ
ምኒልክ፣ ጊዜውና ሁናቴው አልፈቀደላቸውም እንጂ፣ አገሪቷ በመሣርያም ቢሆን የውጭ አገር ጥገኛ ሁና እንዳትቀር የራሷን መሣርያ እንዲታመርት
ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል። ሁለተኛ፣ ኢትዮጵያ ነፃነቷንና ህልውናዋን ለመጠበቅ፣ የጥንት ግዛቶቿን ለባዕድ አሳልፋ ላለመስጠት ሲትል፣ ባሕር ጥሰው
ከመጡባት ከቄሳራውያን መንግሥታት ከፍተኛ ግብግብ ውስጥ ገባች እንጂ የማንንም መሬት አልወሰደችም። እነዚህን ግዛቶቿን መልሳ ባትይዛቸው
ኖሮ፣ በቄሳራውያኑ እጅ በወደቁና የራሷንም ህልውና ባጣች። ይኸ የሚያጠራጥር አይደለም።

አፄ ምኒልክ ያዋሀዷቸው አገሮች ከጥንት ሲወርድ ሲዋረድ እስከጥቂት መቶ ዓመታት በፊት የኢትዮጵያ ግዛቶቿ የነበሩ ስለመሆናችው ሰፊ ማስረጃ አለ።
ይልቅስ በላይ እንዳየነው፣ ከዚያም እንደሚሰፉና አሁን እውስጧ ያልተከተቱ እንዳሉ የሚደግፉ ብዙ የታሪክ ሰነዶች ይመሰክራሉ። እዚህ ለምሳሌ
ያህል፣ ላመሉ ብቻ ልጥቀስ። የጥንቱን ትተን የቅርቡን ብቻ እንኳን ብንመለከት፣ በዐሥራ ስድስተኛው ዘመን ከግራኝ ወረራ በፊት ለስድስት ዓመት
(1520-1526) በኢትዮጵያ የኖረው የፖርቱጋሉ ፍራንቸስኮ አልቫረስ በጻፈው መሠረት የኢትዮጵያ የመሬት ሰፋት ከዛሬው ይበልጣል። በሱ አባባል፣
የኢትዮጵያውያን “ግዛት ሰፊ ነው። በቀይ ባሕር ጠረፍ ካለው ከታላቁ ወደባቸው ከቢሊ ተነሥቶ፣ ወደውስጥ ለሚጓዝ፣ የአዳልን ምድር አልፎ ሐድያን
ይጨምራል። በሕንድ ውቅያኖስ ደግሞ ሞጋዲሾ ይደርሳል… በጣም ሰፊና ሀብታም አገር አላቸው።” ስለግራኝ ወረራ በአጠገቡ ሁኖ ያየውና በሰፊው
የጻፈው፣ ሺሐብ አል-ዲን ኢትዮጵያን ስለማስገበር በሚለው መጽሐፉ ይኸንን የፍራንቸስኮን ጽሑፍ ያጸድቃል። በተጨማሪ ከግራኝ ወረራ በኋላ
ስለኦሮሞ ጐሦች ፍልሰት የጻፈው ታላቁ የኢትዮጵያ ደራሲ፣ መነኲሴው አባ ባሕርይ ንብረቱን ተዘርፎ በሰበቡ አካባቢዉን ሊለቅ የተገደደው በዛሬው
ገሙ ጎፋ ይኖር እንደነበር እናዉቃለን። ገሙ ጎፋ ደግሞ አባ ባሕርይን የመሰለ ሊቅ የሚኖርባት አገር ከነበረች፣ በቀለም ትምህርት የተራቀቁ ገዳማትና
አድባራት እንደነበሯት አይጠረጠርም። ይኸም ሊሆን የሚችለው አገሩ የኢትዮጵያ ግዛት ቢሆን ነው። በነዚህ በጠቀስናቸው ሦስቱ ጸሓፊዎች መሠረት፣
የኢትዮጵያ ወሰን በምሥራቅ የባሕረ-ኤርትራ ጠረፍ ሁኖ ሞቃዲሾን፣ በምዕራብ ደግሞ ገሙ ጐፋን ያጠቀልል እንደነበር በጥያቄ ዉስጥ የሚያስገባ
የለም።

ምኒልክ እንግዴህ ከጥንት ከአክሱማውያን ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያ ግዛት እስከነበረው እስከሞቃዲሾ ድረስ ማስፋፋት ነበረባቸው። ግን ጊዜውና የነበረው
ዐቅማቸው አልፈቀደላቸዉም። ዋናው ነጥብ ግን አፄ ምኒልክ የሠሩት ሥራ፣ በግራኝ ወረራ ምክንያት ማእከላዊ መንግሥት በመድከሙ ፣ከቊጥጥሩ
ሥር የወጡትን ግን ከአክሱማውያን ዘመን ጀምሮ የኢትዮጵያ ግዛቶች የነበሩትን አገሮች፣ ከመላ ጐደል መልሰው ወደአንድነት ማምጣታቸው፣ በምንም Page 9 of 15

መልክ እንደቅኝ ግዛት ሁኖ መታየት አይችልም ነው። ከላይ የጠቀስናቸው ከሺ ዓመታት በላይ ፈርሶ ከቆየ በኋላ የተከናወነው የኢጣሊያን፣ አንዲሁም
ከኢምንት የተፈጠረው የጀርመን አንድነት፣ እንደቅኝ ግዛትነት ካልተፈረጀ፣ ከሦስቶ መቶ ዓመት በማያክል የጊዜ ገደብ ልዩነት የተፈጸመዉን የአፄ
ምኒልክን የውህደት ሥራ የቅኝ ግዛት ነው ማለት ፍርደ-ገምደልነት ብቻ ሳይሆን ዘረኝነትም በራስ-አለመተማመንም ነው ቢባል ሐሰት አይሆንም።

ማዕከላዊ መንግሥትን አድክመው ኢትዮጵያ ርስበርስ በሚበላሉና፣ ግዛቶቻቸዋንም በሚያተራምሱ ባላባቶች እንዲትከፋፈል፣ ከፍተኛ ሚና የተጫወቱት
የግራኛና የኦሮሞ ወረራ ናቸው ቢባል ስሕተት አይደለም። ግን አንድ አጥብቀን መረዳት ያለብን ነገር አለ። አሕመድ በን ኢብራሂም አል-ጋዚ (ዘ[ብሔረ]
ጋዚ) በሚል ስም የሚጠሩት ግራኝም ሆኑ ኦሮሞ ሁለቱም ኢትዮጵያውያን ናቸው። ግራኝ ካፄ ምኒልክ የሚለዩት ከአላፊውና ከጊዜያዊው የገዛ ራሳቸው
ጥቅም አልፈውና አርቀው ማየት አለመቻላቸውና፣ አገሪቷን በጥበብና በፍቅር በማስተዳደር ፈንታ የዝርፍያ፣ የንጥቂያና የግድያ ሜዳ በማድረጋቸው
ነው። አሕመድ በን ኢብራሂም አል-ጋዚ (ዘ[ብሔረ] ጋዚ) ታላቅና ጀግና ኢትዮጵያዊ የጦር መሪ መሆናቸው አይጠረጠርም። ሥልጣን የያዙት፣ ወደሩቁ
ሳንሄድ፣ ልክ በቅርብ ታሪካቸን ውስጥ እንዳየነው ሁሉ፣ እንደአፄ ቴዎድሮስና እንደአፄ ዮሐንስ፣ እጅግ በጣም ብዙ ጦር ሠራዊት ያሏቸውን
ባላንጦቻቸውን ድል በማድረግ ነው።

በዚህ ረገድ የውጭ ሊቃውንትና ሁሌዬ የእነሱን ፈር ከመከተል በስተቀር ሌላ ለየት ያለ የግላቸው አሳብ የማመንጨት ችሎታ ያጡት ብዙ የኢትዮጵያ
የታሪክ ምሁራን፣ የግራኝን ወረራ እንደሃይማኖት ጦርነት ወይንም እንደባዕድ አገር ጥቃት አድርገው ይመለከቱታል። እኔ ግን ይኸንን አስተያየት በፍጹም
አልጋራም። ሐረር የኢትዮጵያ ግዛት ከነበረና፣ እንደሌሎቹ ግዛቶች ለማዕከላዊ መንግሥት የሚገብር መሆኑ ከታወቀ፣ ጦርነቱ የሥልጣን ትግል እንጂ፣
የባዕድ ወረራ አለመሆኑ ግልጥ ነው። ከአፄ አሕመድ ጋር የተዋጉት ሰሜኖቹ ብቻ አይደሉም። ታሪካቸው እንደሚነግረን ከሆነ ሐረርም፣ ባሌም፣
አሩሲም፣ ሌሎችም እንደጉራጌ፣ ከምባታና ሐዲያም የመሳሰሉት በደቡብና በምዕራብ ያሉ አገሮች ተዋግተውዋቸዋል። ሃይማኖት እንደመሣርያና ሽፋን
ሁኖ ቢያገለግልም፣ የአፄው ዋናው ዓላማቸው ግን የተለመደው የሥልጣን ሽኩቻ ነበር።

አፄ አሕመድ በድል ያገኙትን መንግሥት “የኢትዮጵያ [የሐበሻ] መንግሥት” ብለው ማስተዳደራቸው ራሱ ጦርነቱ የሥልጣን መሆኑን
ያመለክታል፤ ከላይ እንዳልኹ አብዛኞቹ የአገራችን ታሪክ ምሁራን፣ የውጭ አገሮቹ የታሪክ ሊቃውንት ስለኢትዮጵያ የጻፉትን ፈለግ
በመከተልና፣ የተሳሳተ አመለካከታቸውን በማጠናከር፣ ክርስቲያንነትንና ኢትዮጵያዊነትን አዋሂደው ያያሉ። ሐቁ ግን እንደዚህ
አይደለም። ሥልጣኑን ክርስቲያን የሆኑት ነገሥታት ይቈጣጠሩት እንጂ፣ ኢትዮጵያ የተባለው መንግሥትና አገር ከጥንት ጀምሮ
በውስጡ የተለያየ ቋንቋና እምነት ያለውን ሕዝብ ያካተተ ነው። የነገሥታቱ ታሪክም ሆነ ግዙፉ ተጨባጭ ሁናቴ የሚያጠናክረው፣
ኢትዮጵያ በጣም ተወራራሽ እምነት፣ ባህልና ቋንቋ ባላት ሕዝብ የተጐነጐነች አገር መሆኗን ነው። በውስጧ የክርስቲያን፤ የእስልምና፣
የፈላሻና የጣዖትን እምነት የሚከታተሉት አሕዛብ ሁሌዬ እንደኖሩ ናቸው። አፄ ምኒልክም በቃላቸዉና ባስተዳደራቸው መላልሰው
በቀይ ቀለማቸው በአንበሳ ማኅተማቸው ይፋ ያደረጉት አገሪቷ የተለያየ እምነት ተከታይ ሕዝብ እንዳላት ነው።

ንጉሠ-ነገሥት አሕመድ ኢብራሂም በጦር ሜዳ ባለጀብዱ ቢሆኑም፣ ባስተዳደር ግን እንደአፄ ምኒልክ ታላቅነታቸውን ሳይሆን ምን ያህል ቅሌታምና
ደካማ መሆናቸውን ነው ያሳዩት። በጦር ሜዳ የተጐናፀፉትን ድል የተጠቀሙት፣ አገሩን በፍቅር፣ በቅንነትና በፍትሕ እንደማስተዳደር፣ ለራሳቸውና
ለተከተያዮቻቸው ብቻ የዘረፋና የግድያ ነው ያደረጉት። በየሄዱበት ታላላቅና ብርቅ የነበሩ የታሪክ ቅርሶችን አጠፉ፤ ጥንታዊነት ያላቸውን ቤተ-
ክርስቲያኖችንና ገዳማትን የኪነ-ጥበብ፣ የፍልስፍናና የምርምር ጥናቶች ከነበራቸው ብርቅ ከሆኑ ብራናዎቻቸው ጋር አቃጠሉ፤ የወርቅና የብር
ንብረቶቻቸውንና ቅርሳቸውን ዘረፉ፤ መነኮሳቱንና ካህናቱን አላንዳች ምሕረትና ርኅራኄ በጭካኔ ገደሉ። አገሪቷን ታሪክ የሌላት ድኃደግ አድርጓት
ወዳንድ ዐምስት መቶ ዓመታት ወደኋላ መለሷት። የሠሩት ተግባር ከጠላትም ሆነ፣ ከማንም የአገር መሪና የእስላም ሃይማኖት ተከታይ የሚጠበቅ
አልነበረም። በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ እንዲህ ዐይነት ያስተዳደር ብቃትና ችሎታ ያጣ፣ ቅለታምና ግፈኛ መሪ በመሆን የመጀመርያውን ቦታ ይያዙ እንጂ
በመጠኑም ቢሆን የሚመስሏቸውን አያጡም። አሁንም ቢሆን አሉ ማለት ይቻላል።

አፄ ምኒልክ ክርስቲያን ቢሆኑም፣ የሠሩት ሥራና የተከተሉት ያስተዳደር መርህ የተንተራሰሰው በሃይማኖት እምነት ላይ አይደለም፤ ፍትሕንና ቅንነትን፣
ያገርን ጥቅምና የየሕዝቡን ባህል መሠረት አድርጎ ነው። ወደኋላ ቀርነት ካለውና፣ የአገርን ጥቅም የሚፃረር ሁኖ ከታያቸው ደግሞ፣ ባህልንና እምነትን
በዘዴ የሚዋጉ ሰው ነበሩ። የወሎው ንጉሥ ኢማም መሐመድ ዓሊ (የኋላው ራስ ሚካኤል) ከገበረላቸው በኋላ፣ ታላቅ ግብር አዘጋጅተው፣ አብረው
ሲበሉ የተመለከተ፣ እንደዚህ ዐይነት ጉድ ዐይቶ የማያውቅ ሠራዊታቸው ተበሳጭቶ ቢያጒረመርም፣ “የወሎ ሰው [እግዚአብሔር] አሁን የሰጠንን አገር
አብረው የሚገዙ፣ በኋላም በርሱ ቸርነት መንግሥተ ሰማያት አብረውን የሚገቡ [ወንድሞቻችን] ናቸውና አትጥሉብኝ። … ወሎን በፍቅርና በትሕትና
እየሳብሁ አሁን ለዚህ ዓለም ግዛት፣ በኋላም በክርስቶስ ቸርነት፣ ለመንግሥተ ሰማያት ለማብቃት እንጂ ለመዝረፍና ለማጥቃት አልመጣሁም። … አሳቤ
ዘወትር በጐ ነው አትክፉኝ… አላሳፈርኳችሁምና እናንተም እንግዳዬን በመሸኘት አታሳፍሩኝ።” ብለው ነው የተበጣበጠውን ሠራዊታቸውን
አሳምነውኑት ያረጋጉት። ቈይተው ያገራቸውን ሕዝብ ይበልጥ ይግረምህ ሲሉ ደግሞ፣ ብላቴን ጌታ ኅሩይ እንደገለጹት፣ ለዚሁ “ላልተጠመቀ እስላም”
ኢማም መሐመድ ዓሊ፣ “የተጠመቀችውን ክርስቲያን” ልጃቸውን ወይዜሮ ሸዋረጋን ዳሩለት። በዚያው ልክ ደግሞ ንጉሠ-ነገሥቱ በማንም የኢትዮጵያ
ዜጋ ላይ የባዕድ እምነት ሆነ ቋንቋ በጒልበት እንዲጫንበት አይወዱም ነበር። የጅማው አባ ጅፋር በባርያ ፈንጋይነት ከገነነው ከዛንዚባር መንግሥት ጋር
ግንኙነት ፈጥሮ ሲያበቃ፣ የግዛቱ ቋንቋ ዐረብኛ፣ ነዋሪዉና መጤው ደግሞ በግድ እስላም እንዲሆን ቢያስገድድ፣ “አገሩን የዐረብ አገር ማድረግህ
እንደሆነ፣ ቊርጡን ንገረኛና፣ ውላችን ይፍረስ” ብለው ነው ያስጠነቀቁት።

ያፄ ምኒልክ መላ አስተዳደራቸው የተከተለው መርህ እንደቀድሞቹ ነገሥታት የሃይማኖትን ገለልተኝነት በመጠበቅ ነው። ይኸም ኢትዮጵያን
በክርስቲያንም ሆነ በእስላም መሪዎች ከሚተዳደሩት አገሮች በጣም ይለያታል። ለምሳሌ ያህል በዐሥራ ስድስተኛ ዘመነ ምሕረት ላይ፣ የአውሮጳ
ነገሥታት በሙሉ ሕዝባችን ነው ብለው የሚጠሩት የራሳቸውን ሃይማኖት የሚከተለውን ብቻ በመሆኑ፣ ክርስቲያኑን ሕዝብ ካቶሊክና ፕሮተስታንት
እያሉ ለያይተውት ሲያጨፋጭፉና፣ ከየሃይማኖታቸው ግዛት ሲያባርሩ፣ ከነሱ ሦስት መቶ ዓመት ቀደም ብሎ የኖረው ክርስቲያኑ የኢትዮጵያ ንጉሥ-
ነገሥት ዐምደ-ጽዮን ግን “እኔ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ የመላው እስላሞች ንጉሥ ነኝ” በማለት፣ አገሪቱ ሳታዳላ ሁሉንም እምነት አስተናጋጅ መሆኗን
ይገልጥ ነበር። Page 10 of 15


አፄ ምኒልክ፣ ከግራኝም ሆነ፣ የግራኝን አብነት በመከተል በንግሣቸው ዘመን እስላሙን ካሳደዱት ከባላንጣቸው ከአፄ ዮሐንስ በጣም ይለያሉ።
እንዲሁም ዘመናዊ መገናኛ ስልክና የባቡር ሐዲድ በሚያስገቡበት ጊዜ፣ የቤተ-ክህነት መሪዎች ቢቃወሟቸዉና፣ ሕዝቡም እንዲነሣባቸው ቢሞክሩ፣
በመኳንንቶታቸው ፊት ለጳጳሱ የሰጡት መልስ፣ እነዚህ ቅዠተኞች ሥራዬን ማደናቀፍ ካላቆሙ፣ ያለኝ ምርጫ ሃይማኖቴን መለወጤ ነው እስከማለት
ድረስ ከቤተ-ክህነቱም ከወግ-አጥባቂዎችና አክራሪዎች ጋር በጥብቅ መፋለማቸው የሳቸውም ሆነ የኢትዮጵያ ፖልቲካ ከሃይማኖት ነፃ መሆኑን
በአስተዳደራቸውም በአቋማቸዉም በግልጥ አሳይተዋል።

በቅርብ ጊዜ አበራ ቶላ የተባሉ ጸሓፊ “የኦሮሞ መስፋፋትና የምኒልክ በኀይል መያዝ ጨለማው ጐን በኢትዮጵያ6
” በሚል አርእስት አንድ ጽሑፍ
በኢትዮመዲያ” ዘግበዋል። ከመግቢያው ላይ ጠቅለል ባለ-መልኩ የሚናገሩት ታሪካዊ ድርጊቶች መጠነኛ እውነተኝነት ቢኖራቸውም፣ የኦሮሞ
መስፋፋትን ከአፄ ምኒልክ ማስገበር በማነፃፀር የሚናገሩት ሐተታ፣ ባሁን ወቅት በሰፊው የተሰራጨውን ተረት ከማስተጋባት በስተቀር፣ ጥልቀትና ቁም-
ነገረኝነት የለውም እላለሁ።

አንደኛ ኦሮሞም ሆነ ኦሮሞች የሚሉት ቃላት ራሳቸው ምን ማለት መሆናቸውን ደራሲው አብራርተው አይገልጡም። ኦሮሞ ማለት የድሮውን “ጋላ”
የሚለውን ቃል የሚተካ ከሆነ፣ ንግግሩ በሙሉ አከራካሪ ከመሆን አልፎ የጸሓፊውንም ዕውቀት ያስጠይቃል። “ጋላ” የሚለው ቃል መሠረታዊ
አመጣጡና ለመጀመርያ በጥቅም ላይ የዋለው በግዕዝ ቋንቋ ሥነ-ጽሑፍ ሲሆን፣ ትርጒሙ በተወሰነ የኑሮ ዐይነት የተሰማራ፣ ወይንም ያልተገረዘና
ክርስቲያን ያልሆነ ኅብረተ-ሰብን እንጂ፣ በቋንቋ ዝምድና የተሳሰረ፣ ወይንም በደምና በመወላለድ ያንድ ምንዝላት ወይንም ያንድ እንጅልሽ የሥጋው
ቊራጭ ያጥንቱ ፍላጭ የሆነ ሕዝብን አያመለክትም። ስለዚህም ነው ቃሉ ከግብፅ ምዕራብ ለሚኖረው በርበር፣ ለሱዳኑ ድንቃ፣ በኢትዮጵያም ውስጥ
ላሉት ለተለያዩት እንደነአፋርና፣ በኦሞ ወንዝ አካባቢ ለሚኖሩ ዐይነቶቹ ኅብረተ-ሰቦች በሙሉ ሲሰጥ የሚታየው።

ጸሓፊዎቹ “ጋላ” የሚለውን ቃል፣ እንደጠቅላላ መጠርያ ከመጠቀማቸው በፊት፣ የኅብረተ-ሰቡን ስም ጠቅሰው ሲያበቁ፣ ሁለዬ እንደመለዮው አድርገው
“የሚባል” የሚለውን ቃል ይጨምሩበታል። ለምሳሌ፣ ከግብፅ ቀጥሎ ከሚገኘው አገር (ከበስተምዕራቡ) መጥቶ በሰሜን ግብፅ ያለውን ገናናውን
የአስቄጥስን ገዳም ይዘርፍ የነበረውን የበርበርን ኅብረተሰብ ሲገልጥ፣ ጸሓፊው “በርበር” የሚባል “ጋላ” ይላል። በኢትዮጵያም ልክ እንደዚሁ “ቱለማ”
የሚባል “ጋላ”፣ “ከረዩ” የሚባል “ጋላ”፣ “ሜጫ” የሚባል “ጋላ” እያለ ነው የተለያየ የኅብረተ-ሰብን ክፍል የሚገልጠው። እነዚህ ኅብረተ-ሰቦች የሚጋሩት
ነገር የትውልድና የዘር ሳይሆን፣ ሰብአ-ትካትነትንና በዘረፋና በዘላንነት መኖርን፣ ወይንም የከረስተኑና የተገረዙ አለመሆናቸውን ነው። “በርበር፣
“ድንቃ”፣ “ሜጫ”፣ “ቱለማ” የሚሉት ቃላት የኅብረተ-ሰቡን ምንነት ሲገልጡ፣ “ጋላ” ግን የኑሯቸውን ዐይነት ነው የሚያሳየው። እነዚህ ዘላን
እንደመሆናቸው የተወሰነ መሬትና አካባቢ የላቸውም። ስለዚህም ነው ጸሓፊዎቹ ሌላውን በግብርና ተደላድሎ በተወሰነ መሬት ላይ የሚኖረውን ሕዝብ
በመሬቱ ስም፣ “የመተከል ምድር”፣ “የጋፋት ምድር” “የአማራ ምድር” ብለው ሲጠሯቸው፣ ለጋላ ሲሆን ግን የታወቀ “ምድር” የለውም ብለው በማሰብ፣
ወደ”መኖርያው” ፣ “ወደ አገሩ” ተመልሶ ሄደ የሚሉት። ለዚህም ነው ደግሞ ማዕከላዊው መንግሥት በሌላው ዐመፀኛ ነው በተባለ ሕዝብ ላይ
እስከ”ምድሩ” ድረስ ሄዶ ሲዘምትበት፣ በ”ጋላ” ላይ ግን ተመሳሳይ እርምጃ መውሰድ ይሳነው የነበረው።

ፍሬ ነገሬ “ኦሮሞ” ስለሚለው ቃል ሐተታ ሳይሆን፣ ዘውገኞች ስለዚሁ ኅብረተ-ሰብ የሚስብኩት ስብከት ልበ-ወለድና አንጃ ግራንጃ እንጂ ተጨባጭ
ማስረጃ እንደሌላቸው ለማስገንዘብ ነው። ሕዝቡ በባህልም ሆነ፣ በቋንቋና በዝርያ በፍጹም አይገናኝም። ኢትዮጵያን ከመውረሩ በፊት ሆነ፣ በአፄ
ምኒልክ መሪነት ኢትዮጵያ ተመልሳ እስከተዋሀደችበት ጊዜ ድረስ፣ አንድነት ያለው የኦሮሞ ሕዝብም ሆነ መንግሥት ከቶዉኑ አልነበረም፤ ኑሮም
አያውቅም። በኢትዮጵያ አንድነት ዋዜማ ላይ፣ ጥንት “ጋላ” በመባል የሚታወቀው ሕዝብ ራሱ፣ ዘላንነቱንና በዝርፍያ መኖሩን ትቶ በነገሥታቱ ጥረትና
በጊዜያዊ ሁናቴዎች መለወጥ፣ በየሰፈረበት ሁሉ በፍላጎቱ አካባቢውን መስሎ በግብርና መኖር ጀምሯል። በምሥራቅ፣ በደቡብ፣ በአዜብና በባሕር ያለው
የእስልምና ተከታይ ሆነ፤ በሰሜንና በምዕራብ እንደ ጐጃምና በጌምድር ባሉት አካባቢዎች የሰፈረው ደግሞ ወደኦርቶዶክስ እምነት ገባ። ኦርቶዶክስ
የሆነው ከማዕከላዊ መንግሥት ውስጥ ተዋቅሮ ከፍተኛ ሚና ሲጫወት፣ የወሎና የአዜቡ እስላም በበኩሉ ርስበርስ ጦርነት በሚፋጁ በተለያዩ ጥቃቅን
የባላባቶች መንግሥታት ቢጤ ተቋቋመ። አፄ ምኒልክ ናቸው በበርስበርስ ጦርነት ከመጨራርስ ያዳኗቸውና ሁሉንም እንደሌላው የኢትዮጵያ ኅብረተ-
ሰብ ወደውህደት አምጥተው በሰላምና በፍቅር እንዲኖር ያደረጉት።

አለቅጥ የሚደነቀው የጋዳውም ሥርዐት ቢሆን በአፍሪቃ ውስጥ በዚያ የሥልጣኔ ዕድገት ደረጃ ያሉት ብዙዎቹ ኅብረተ-ሰቦች ከመላ ጐደል የሚጋሩት
አወቃቀር ነው። ሥርዐቱ ሲመረምር አሳፍሪ እንጂ የሚደነቅ ሁኖ አይታይም። ለምን እንደዚህ እንዳልኩ ላስረዳ። የጋዳ ሥርዐት በደምሳሳው ሲታይ፣
የመዋቅሩ ቁልፍና ዋና ሊባል የሚቻለው ሉባ የተባለው ማዕርግ ወይንም ዕርከን ነው። ስለሉባነት በቅርቡ ያጠናውና በሥራ ላይ ያየው፣ አንድ የዐሥራ-
ሰባተኛ ዘመን ጸሓፊ በሚለው ከተመሠረትን፣ “ሉባነትን እስከሚያገኝ ድረስ የኅብረተ-ሰቡ አባል አይገዘርም ብቻ ሳይሆን፣ ልጅ እንኳ ቢወልድ
እንደወላጅ ሁኖ በሥነ-ሥርዐት በማሳደግ ፈንታ፣ እንደውሻ ቡችላ እውጭ ይጥለዋል። በዚህ ሹመት ላይ ባለ ጊዜ ውስጥ ሰው ካልገደለ ደግሞ፣
ጠጒሩን አይላጭም፤ የግድያ መለዮው ስለሆነ ጒቱም አያሳድግም፤ ታድያ የሞት ፍርድ እንደተፈረደበት ሰው ዘወትር እያለቀሰ፣ በሐዘን ውስጥ ተዘፍቆ
ይኖራል እንጂ።” ማንም በሠለጠነው በዛሬ ዘመን የሚኖር፣ ልብ ያለው ሰው፣ በዚህ ዐይነት ሥርዐት መኲራት ቀርቶ፣ የመደገፍ ስሜት እንኳ ቢያሳይ
ለሰው ህልውና እንደከፍተኛ ጠንቅ ሁኖ ስለሚታይ ጭንቅላቱን መመርመር፣ ከኅብረተ-ሰቡም መገለል ይኖርበታል ተብሎ ነው የሚታሰበው። በዚህ
የማይስማማ ካለ፣ እሱ ራሱ የአእምሮ ችግር እንዳለው ይቈጠራል።

እውነቱ ጋዳና ግድያ በቃላት ይለያዩ እንጂ ትርጒማቸው አንድ ነው። እጅና መዳብ ናቸው። ዝርፍያ የሥርዐቱ ዋና አንቀሳቃሽ ሞተርና ኀይል ነው።
ይኸንን ነው እንግዴህ ከዐሥራ ስድስተኛው ዘመነ ምሕረት ጀምሮ “ጋላ” የተባለው ኅብረተ-ሰብ በመላ ኢትዮጵያ ይፈጽም የነበረው። ይኸም ማለት

6
 . Abera Tola, “Ethiopia: Dark side of Oromo Expansions and Menilek Conquests,” Ethiomedia, January
4, 2014. Page 11 of 15

በምቾትና በድሎት ይኖር ወደነበረው ኅብረተ-ሰብ ሊገድልና ሊዘርፍ ይዘምታል። የተዋጋው ሕዝብ ተሽንፎ ቢገኝ፣ በጅምላ በመጨፍጨፍ፣ የነፍሰ-
ጡሮች እናቶችን ሆድ በመዘርጠጥ፣ የደሙን ጥም ለማርካትና፤ የጀብዱን ሚርጋ ለማስቈጠር ሲል ራስ በመቊረጥ፤ አባለ-ዘር በመጒመድ ያለቀው
ሕዝብ ተቈጥሮ አያልቅም። የውጭ አገርም ሆኑ የኢትዮጵያ ጸሓፊዎች “ጋላ”ን በተመለከተ የሚስማሙበት ነገር ቢኖር በነዚህ ነጥቦች ላይ ነው።

እዚህ ላይ፣ ጥቂቶቹን ብቻ ላመሉ ልጥቀስ። በዐሥራ ስድስተኛ ዘመነ-ምሕረት ሁናቴውን በቅርቡ ካዩት የኢትዮጵያ ጸሓፊዎች ልጀምር። አገሩ “በጋላ
እጅ ተመዝብሮ በረኻና ጫካ በመሆኑ ከእንስሳና ከዱር አራዊት በስተቀር ሰውም ሆነ እርሻ በፍጹም የለበትም።” ቱላማ የሚባል ጋላ መጥቶ፣
“መንፈቁን ጐጃም” ምንም ሳያስቀር ደምስሶ አጠፋው፤ ሴቶችንና ከብትን ማረከ። የገደለው ሰው ቊጥር ስፍር የለዉም። “ጋላ ጐጃምን መውረር
ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ እንደዚህ የገደለበትና የማረከበት ጊዜ ከቶውኑ የለም።” ክርስቲያኑ ብቻ አይደለም ይኸ ዐይነት ዕልቂትና ጥፋት ከጋላ
የደረሰበት። ታዲያ ያመለጠ የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ አልነበረም ቢባል ሐሰት አይሆንም። ያኔ ሻንቅላ በመባል የሚታወቀው ሕዝብ ማእከላዊው
መንግሥት በአስቸኳይ እንዲደርስለት ያቀረበው ጩኸት፣ “የከብትና የሰው ምርኮ ወሰደብን፤ ስፍር ቊጥር የሌላቸውን ጀግኖቻችንን ገደለብን፤ የቀሩት
ጀግኖቻችን የሴት ፍርሀት ይዟቸዋልና፣ ጌታችን [ንጉሥ] ሆይ እንዲትታደገን ፈጥነህ ድረስልን” ነው የሚለው። ግድያው የአረመኔነት ሳይሆን የአውሬነት
ነው። ካልሰለበ፣ ጡት ካልቈረጠ፣ ሆድ ካልዘረጠጠ፣ ቸብቸቦ ካልሰበሰበ ስሜቱ አይቀሰቀስም። እነዚህ ድርጊቶች የጀብዱነቱና የታላቅነቱ ዋና
መግለጫውና መስፈርያው ነበሩና።

እንግዴህ የዛሬው “ኦሮሞ” የትላንትናው “ጋላ” ነው ካልን፣ በዚህ ስም የሚጠራው ኅብረተ-ሰብ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ያደረሰው ጉዳትና
ጥቃት፣ የፈጸመው የሰውና የከብት ዕልቂት፣ የንብረትና የታሪክ ቅርስ ጥፋት፣ በሰው አንደበት ተገልጾ፣ በመጻሕፍት ተጽፎ አያልቅም ማለት ይቻላል።
ከግራኝ ብዝበዛ ያመለጡት ቤተ-ክርስቲያኖችና ቤተመንግሥቶች እውስጣቸው ከነበሩት የታሪክ ቅርሶችና መጻሕፍቶች ጋር ድራሻቸው ጠፍቷል።
ይኸንን እንደሰደድ እሳት ባገሩ ላይ ያደርስ የነበረውን ዕልቂት አይተው ነው እንግዴህ፣ በመጤ ሃይማኖታቸው ሰበብ ከኢትዮጵያ የተባረሩት ካቶሊኮች፣
ኦሮሞችን አምላክ ኢትዮጵያውያንን በነሱ ላይ በፈጸሙት ግፍ ተቈጥቶ ሊበቀል ሲል የላከው “የእግዚአብሔር መቅሠፍት” ነው ብለው የተረጐሙት።

እንግዴህ እንደዚህ የመሰለውን የአውሬነት ተግባር ከአፄ ምኒልክ ድርጊት ጋር ማነጻጸር ሚዛነ-ቢስነት ብቻ ሳይሆን ፍርደ-ገምደልነትም ነው ማለት
ይቻላል። ታሪክ አይደግፈውም፤ ጤናማም ሰው አያደርገዉም። ከዚያም አልፎ ተርፎ፣ ታሪክ የሚነግረን ያለው፣ ሺ ኪሎሜትር ሰንጥቆ ሄዶ የሌላውን
ኅብረተ-ሰብ መሬት ወርሮ የያዘውን ሕዝብ፣ አፄ ምኒልክ በግፍ ቅኝ ግዛት አደረጉት ማለትም እውነትን ከማፋለስና ዘበት ከመናገር በስተቀር ሌላ ቁም-
ነገር አይኖረውም።

ይኸ እንዳለ ሁኖ ከጥፋትም አንዳንድ ጥሩ ነገር አይታጣም። ኦሮሞች አገሩን በግድያና በዘረፋ ቢያራቆቱትም፣ ወንዶችንና አርጊቶችን በሚዘገንን ሁናቴ
ጨፍጭፈው ቢገድሉም፣ ሴቶችንና ልጆችን ከአገሩ ከብት ጋር ማርከው መውሰድ ልማዳቸው ነበር። ዕድለ-ቢሶቹ ሴቶች ከማራኪዎቻቸው ልጆች
ይወልዱ፣ የተማረኩትም ልጆች በተራቸው አድገው ከብሔረ-ሰቡ ጋር ይጋቡ ነበርና፣ ኦሮሞች ወደድንም ጠላንም፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ
አቀያይጠዉታል። ስለዚህ ዛሬ ማንም ሰው አፉን ከፍቶ የኔ ዘር ንጹሕ ነው ሊል በፍጹም አይችልም። የሚልም ካለ ወይ ውሸታም፤ ካልሆነ ደግሞ
ትዝብትንና ይሉኝታን የማይፈራ ውሸታምና የሚናገረውን የማያውቅ መሆን አለበት።

እንግዴህ የኢትዮጵያዊ ፍቹ በቃሉ ትርጒም መሠረት፣ “ፊቱ የጠቈረ” ብቻ ሳይሆን፣ በተጨማሪ በዘሩ “የተከለሰ ቅይጥ” መሆንንም ያመለክታል።
መለዮውም ጥቊርነትና ድቃላነት ነው። አንድ የታሪካችን ምሁር የሆነ ኢጣልያናዊ ኢትዮጵያን “የሕዝብ ሙዝዩም” ይላታል። ሐቁ ግን አገሪቷ ብቻ
ሳትሆን፣ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊም ጭምር “የሕዝብ ጥርቅማጥርቅም” ነው፤ በደሙ ውስጥ አብዛኞቹ የኢትዮጵያ ነገዶች አሉበት ማለት ይቻላል።
ለዚህም ያበቃው የማዕከላዊ መንግሥት መፍረስና የኦሮሞ ወረራ ሲሆን፣ ወረራው የኢትዮጵያን ሕዝብ አድሶታል፤ በታሪክ፣ በደም፣ በቋንቋ፣ በባህል
አስተሳስሮ እንደሰርገኛ ጤፍ ወንድማሞችና እኅትማሞች አድርጓል። ወይንም ከዚያም በተሻለ አባባል ለመግለጥ፣ የሥጋ ቊራጭ፣ ያጥንት ፍላጭ ሁኖ
ደም በደም ተቀላቅሏል፡ በዚህ መልክ የተዋሀደ ሕዝብ ነው እንግዴህ ተመልሶ ዘመናዊቷን ኢትዮጵያን በምኒልክ መሪነት ያዋሀዳት። በዚህ የተቀደሰ
ሥራ፣ በፊታውራሪነት የመሩት ደግሞ ኦሮሞቹ ራሳቸው ናቸው።

እንደዚህ ያልኩበት ምክንያት ግልጽ ነው። አፄ ምኒልክ ያደጉት ከኦሮሞች ጋር እየተጯጯሁ ሲሆን፣ አለኦሮሞች ድጋፍ፣ አለነሱ ኀይልና ሠራዊት ከአፄ
ቴዎድሮስም እጅ ማምለጥም ሆነ፣ ወዳባታቸው ግዛት ገብተው መንገሥ፣ ዘመናዊቷንም ኢትዮጵያን ማዋሀድ አጠያያቂ በሆነ። ወደደቡብ፣ ምዕራብና
ባሕር የዘመተው ሠራዊት ከጦር መሪ እስከዝርዝር ድረስ ኦሮሞ ነበር ማለት ይቻላል። እንዲህ ስል የሌሎቹን ሚና ማሳነሴ ወይንም ማጥላላቴ ሳይሆን
ከራስ ጐበና ጀምሮ እስከተራው ኦሮሞ ድረስ በኢትዮጵያ ምድር በተወሰነ አካባቢ ባገሪቷ ያንድነት ግንባታ ያደረጉትን አስተዋጽኦ ለማጉላት ነው።
እውነት ነው፣ ሌሎችም እንደየዐቅማቸው ድርሻቸውን በጋራ ተዋጥተዋል። ይኸም ቢሆን ግልጥ ነው፤ ግን ላመሉ ነካ ላድርገው።

አፄ ምኒልክ በተዋሀደች ኢትዮጵያ ላይ ለመንገሥ የበቁት የመጀመርያው ንጉሠ-ነገሥት ይሁኑ እንጂ፣ አብዛኛው የውህደት ሥራ የተከናወነው በአፄ
ዮሐንስ ሥር መሆኑን መርሳት አይገባም። በአፄ ዮሐንስ መሪነት፣ ሰሜኑን ንጉሠ-ነገሥቱ ራሳቸው፣ ምዕራቡን ንጉሥ ተክለ-ሃይማኖት፣ ከመኻል ደግሞ
ሁነው ምሥራቁን፣ ደቡብንና ምዕራቡን፣ ባሕሩንና አዜቡን ንጉሥ ምኒልክ ሁነው ነው በመተባበር የአፄ ቴዎድሮስን ያንድነት ግብ አስመቱት። እነሱም
ብቻቸውን አልነበሩም፤ እያንዳንዱ ችሎታቸውና ብቃታቸው በይፋ በጦር ሜዳ በተመሰከረላቸው ታላቅ የጦር-መሪዎች ተረድተው ነው፤ ራስ አሉላ
በሰሜን፣ ራስ ደረሶ በምዕራብ፣ ራስ ጐበና በመኻል አገር ነበሩ፣ ማለትም የትግርኛ፣ የአማርኛና የኦሮምኛ ኅብረተ-ሰብ ቋንቋ ተናጋሪ አባላት። ብዙ
ጒድለት ቢኖራቸውም፣ አፄ ዮሐንስ በዚህ ሥልጣን አደላድለው በማስተባበር ችሎታቸው፣ ንጉሥ ምኒልክ ደግሞ ተመጣጣኝ ጒልበት እያላቸው
የንጉሠ-ነገሥታቸውን ሥልጣን እንደጊዜው ልማድ አንዴም ሳይዋጓቸው በመቀበላቸው፣ መደነቅ አለባቸው።

በቅርቡ የአፄ ምኒልክን ስም የማጒደፍ ዘመቻ ያተኰረው ንጉሠ-ነገሥቱ በአሩሲ ውስጥ አኖሌ በተባለ ቦታ ፈጸሙ በተባለ ግፍ ላይ ነው። የእናቶችን
ጡት ቈረጡ፤ ብዙ ሕዝብ ጨፈጨፉ እየተባለ ይወራል። ለመታሰቢያም በቦታው ሐውልት ተሠርቷል ይባላል። እንደሚወራዉና ለኔም እንደመሰለኝ፣
የታሪኩ ምንጭ በኤርትራዊው በተስፋዬ ገብረ-አብ የተጻፈው “የቡርቃ ዝምታ” የተባለው የልበ-ወለድ ድርሰት ይመስላል። Page 12 of 15


እንግዴህ “ሞኝና ውሃ እንደወሰዱት ይሄዳል” እንደሚባለው ቅሌታም ብቻ ነው ልበ-ወለድን እንደእውነት፣ ምናብን እንደድርጊት አድርጎ የሚወስደው።
ከዚያም አልፎ ደራሲው የታሪክ ባለሙያ መሆን ይቅርና የዐሥራ-ሁለተኛ ክፍል ትምህርት እንኳን ማጠናቀቅ ያልቻለ ግለስብ ነው። በዚህ በፈጠራ
ጽሑፍ ተመሥርቶ ሐውልት የሚያሠራው ግለ-ሰብም ሆነ ባለሥልጣን በግድየሌሽነት የሕዝቡን ገንዘብ ማባከን ብቻ ሳይሆን፣ ሕዝቡን ራሱን ምን ያህል
ወደኋላ የቀረ በማሰኘት በዓለምና በታሪክ ፊት እያስገመተ ነው። ርግጠኛ ነኝ የአኖሌ ሕዝብ የሚጠጣ ንጹህ ዉሃ፣ የሚመላለስበት ዘመናዊ መንገድና
መጓጓዣ፣ በሽተኛውን የሚያስታምምበት የተደራጀ ሕክምና ቤት፣ ልጆቹን የሚያስተምርበት ማለፍያ ትምህርት-ቤትና፣ ትምህርቱንም ከጨረሰ ወዲያ
የሚሰማራበት አስተማማኝ የሥራ ዘርፍ የለውም ይሆናል። የሐውልቱ ገንዘብ በተረት ላይ በተመሠረተ ድርጊት ከሚውል፣ በእነዚህ አገልግሎቶች ላይ
ቢጠፋ፣ ሕዝቡን ምንኛ በጠቀመው፤ አሠሪውንስ ምንኛ ባስመሰገነው።

ድርጊቱ እውነት ቢሆንስ ሐውልት ለምን አስፈለገ። ኢጣልያኖች ሰንቱን አሩሲ፣ ስንቱን ኦሮሞ ጨርሰው የለ፤ ለምን ለዚሁ መታሰቢያ አልተሠራም።
እውነቱን እንነጋገር ከተባለ፣ በኢትዮጵያ ምድር ለተሠራው ግፍ ሁሉ ሐውልት እንሥራ ከተባለ ደግሞ፣ ከብዛቱ የተነሣ እንኳን ለሰው መኖርያ፣ ለእግሩ
ማሳረፍያ የሚሆን መሬት አይገኝም ይሆናል። አሩሲ ራሱ ቋንቋው ኦሮሞኛ ነው ይባል እንጂ፣ ሕዝቡ ግን ከመቶ ሰባው በትውልዱ የከምባታ፣ የሐዲያና
የጒራጌ ነው። እንግዴህ በዚህ መሬት በሌላው የተፈጸመው ሳይቈጠር፣ በኦሮሞች እጅ ብቻ ያለቀውን የነዚህን ሕዝብ ቊጥር የያንዳንዱ ቤት
ያውቀዋል። እንግዴህ ለነሱም ሐውልት ያስፈልጋቸዋላ። እኔ ራሴ የማወራው የግሌ ታሪክ አለኝ።

በሁለተኛው የኢጣልያን ወረራ ወቅት የኢትዮጵያ ጦር እንደተፈታ፣ በከምባታ ላይ የጐሦች ጦርነት በመባል የታወቀ ከፍተኛ ዘመቻ ተካሂዶ ሕፃንና
ዐዋቂ፣ ሴትና ወንድ፣ ወጣትና ሽማግሌ ሳይለይ ብዙ ሕዝብ ዐለቀ። ከብትና ንብረት ተዘረፈ። ብዙዎች ተማርከው የደረሱበት ጠፋ። ይኸ ዐይነት ሰለባና
በደል ከደረሰባቸው መካከል ቅርብ ቤተሰቦቼ ነበሩ። እናቴ ጡቷን ተቈርጣ፤ ሆዷን ተዘርጥጣ ሙታለች ተብላ እሜዳ ላይ ተጣለች። እናቷና ጫቅላ
እኅቷ ግን ተማርከው ከተወስዱ በኋላ ደብዛቸው ጠፋ። ሌላው ሕፃን ወንድሟ ግን የምርኮና የጥፋት ዕጣ ባይገጥመውም አባለ-ዘሩን ተቈርጦ በሜዳ
እንዲሞት ከተጣለ በኋላ በሕይወት ቢቀርም ወራሪዎቹ ጐሦች በያንዳንዱ ቤተ-ሰብና በመላው አገር ያደረሱት ዕልቂትና በደል በሰው አንደበት ተነግሮ
አያልቅም ብቻ ሳይሆን የሰቀቀኑ ርዝራዥ እስካሁን ድረስ በያንዳንዱ ቤተ-ሰብና ግለ-ስብ ጆሮ ውስጥ ይጮሃል። ለዚህም ዐይነቶቹ በጐሦች ለተፈጸመ
አሰቃቂ ግፍ ሐውልት ያስፈልጋል ማለት ነው።

በሥልጣን ያለው መንግሥት ከሽፍትነት ወደአፄ ምኒልክ ዙፋን ያደረስውን ዘመቻ የጀመረው ስሙን ባወረሰለት በመጀመርያ ወያኔ ትግል ላይ
ተመርኲዞ ነው ይባላል። አንዳንድ ታሪክ ጸሓፊዎች ለመጀመርያው ወያኔ መነሾው በኢትዮጵያ መንግሥት የተፈጸመው ያስተዳደር ጒድለት ነው ይላሉ።
እኔ ራሴ የሰማሁት ታሪክ ግን ከዚህ በጣም ይለያል። ያስተዳደር ጒድለት ማሳበቢያ ሊሆን ይችላል እንጂ፣ የመነሾው ጥንተ-መሠረቱ ግን የደጋ ትግሬው
ሕዝብ ከትውልድ ሲወርድ ሲዋረድ እንደመጣው ትውፊት በዘላኑ ኅብረተ-ሰብ ላይ ያካሄድ የነበረውን የዘረፋ፣ የግድያና የጥቃት ዓመታዊ ዘመቻውን
እንዲያቆም በመንግሥት ባለሥልጣኖች ስለተከለከለ ነበር። እንግዴህ ይኸ ዐይነት ዐመታዊ ዘመቻ ምን ያህል ግድያና ዕልቂት በዘላኑ ሕዝብ ላይ
ለዘመናት እንዳደረሰ እናውቃለን። ዘመቻው አባትና እናት ገድሎ ብዙዎቹን ልጆች ድኃደግ እንዳደረገ፣ የስንቶቹን እናቶች ጡት እንደቈረጠ፣ ስፍር-
ቊጥር የሌላቸውን ወንዶች እንደሰለበ፣ ከብትና ንብረት እንደዘረፈ፣ ሴቶችና ሕፃናት ማርኳቸው እንደወሰደ፤ በኅብረተ-ሰቡ ላይ ምን ያህል ሽብርና
ፍርሀት ይፈጥር እንደነበረ፣ ስንቱንስ በጋለሞታነት እንዳስቀረ መገመት አያዳግትም። አፄ ምኒልክ ባንድ ቀን በጥቂት ሰዓት ውስጥ ፈጽመዋል የሚባለው
ግፍና ጭካኔ ከዚህ በያመቱ ከሚደጋገመው ድርጊት ጋር ቢወዳደር ኢምንት ነው ማለት ይቻላል። ታዲያ ለዚህስ አረመናዊ ጭፍጨፋ ለምን ሐውልት
አያስፈልግም። በዚህ የአሳብ መስመር ከቀጠልን ደግሞ በሥልጣን ያለው መንግሥት አላንዳች ምክንያት በግፍ የጨፈጨፋቸውና ያስጨፈጨፋቸው
እልፍ አእላፋት ንጹሓን አሉ። ለነሱስ ለምን በየቀዬአቸው የመታሰቢያ ሐውልት አይሠራላቸውም።

በአሩሲ አፄ ምኒልክ ምን እንዳደረጉ ማወቅ ከተፈለገ አጥጋቢ ጽሑፍ ስላለን፣ በፈጠራና በስብከት ላይ መመሠረት አያስፈልግም። ጽሑፎቹ
የሚያስረዱት አሩሲ ምን ያህል ለአፄ ምኒልክ እጅግ ባለውለታ እንደሆነ ነው። ነገሩም እንደዚህ ነው። አገሩን ባስገበረው በቱላማ ጦር ላይ፣ ጥቂት
የአሩሲ ሰው ባንድ ባላባት ተመርቶ፣ ሌሊት ተነሥቶ ጦሩ በሠፈረበት ቦታ አደጋ ቢጥልበትና ከሺ በላይ ሠራዊት ቢፈጅበት፣ ካፄ ምኒልክ ረዳት ጦር
ተላከ። ይኸ ረዳት ጦር ሌሊቱን ሲጓዝ፣ ደግሞ እንደገና ተመልሶ አደጋ ሊጥል ከሚሄደው ከአሩሲ ሰው ጋር በድንገት በመንገድ ላይ ተገናኘና
በመካከላቸው በተፈጠረው ግጭት ብዙ ሰው ዐለቀ። የኦሮሞ ጦር እንደመሆኑ፣ በኅብረተ-ሰቡ ልማድ ጡት ቈርጦ፣ እጅ ጐምዶ ይሆናል። የጊዜው
ልማድ ስለሆነ ምንም አይገርምም፤ ሌላው ቀርቶ በአድዋ ጦርነት እንኳን ተፈጽሟል። ደጋግሜ እንዳልኩት፣ ታሪክ መዳኘት ያለበት ከጊዜው አንፃር
ነው።

የሚደነቀውና የንጉሠ-ነገሥቱ አሽማጦች የረሱት ነገር ቢኖር ግን፣ አፄ ምኒልክ እቦታው እንደደረሱ የወሰዱት እርምጃ ነው። በየትም አገር
እንደሚደረገውና እንደጊዜው ልማድ መሠረት፣ ጦራቸው የማረከውን የአሩሲን ሰው ሁሉ ባርያ አድርጎ ይዞ ቢቈይባቸው፣ ንጉሡ ከፍተኛ
ተቃውሟቸውን አሰሙ። ሠራዊታቸውን በሙሉ ሰብስበው፣ “አሩሲን ከግራኝ ወዲህ የገዛውና ያስገበረው የለም። እኛ ጥንትም የኛ [አገር] ነው ብለን
መጣንበት እንጂ ርሱ አልመጣብንም። ባለማወቁ እከላከላለሁ ብሎ ዐለቀ፤ ተጐዳም። ግን ባርያ አድርገን ልንገዛው አይገባንም፤ ወንድማችን ነውና።
የማረክኸውን የሰው ምርኮኛ ሁሉን ልቀቅልኝ። በዐዋጅ ከለመንሁህ በኋላ ወስልተህ የአሩሲን ሰው ባርያ አድርገህ የተያዝህ ከተገኘህ እጣላሃለሁ፤ ልቀቅ
ብዬሃለሁና ልቀቅ።”በማለት እንዲለቅ በአዋጅ አስገደዱትና ተለቀቀ። ባገሩም ታማኝና ብቁ ነው ብለው የሚያምኑትን አስተዳዳር ሹመው
ወደመናገሻቸው ተመለሱ።

ይኸንን የአፄ ምኒልክን ድርጊት ሌሎች የቅኝ ገዢዎች ከወሰዱት እርምጃ አንፃር እስኪ ከጥቂቶቹ ጋር እናስተያይ። ጀርመኖች የታንዛንያ ሕዝብ
ባስተዳደራቸው ግፍ አንገፍግፎት ሸፍቶ፣ አንዲት ትንሽ ምሽግ ቢጤ ሰብሮ፣ ጥቂት ሰው ቢገድልባቸው፣ ረዳት ጦር ተልኮ ሁለት መቶ ሺ ሰው በጭካኔ
ገደሉ። እንዲሁም የናምቢያ ሕዝብ በጨካኝ አስተዳደራቸው ተማርሮ በዚሁ መልክ ቢነሣባቸው፣ የተላከው ረዳት ጦር አንድም ሰው ሳይቀር እንዲገድል
ታዝዞ፣ ከመቶ ሰማንያውን እጅ አረደ። የቀረው ሊያመልጥ የቻለው ወደጐረቤት መንግሥት ሸሽቶ ብቻ ነው። እንዲሁም ፈረንሳዮች የማዳጋስካር ሕዝብ
ተበደልሁ ብሎ ቢነሣባቸው፣ ሰማንያ ሺውን አላንዳች ምሕረት ጨፈጨፉ። በጐረቤታችን ኬንያ እንግሊዞች በየቀኑ፣ “ዛሬ ሁለት መቶ ሻንቅላ ገደልን፤ Page 13 of 15

ዛሬ ደግሞ ዐምስት መቶ…” እያሉ ለቅኝ ግዛት ሚኒስትር ወደለንደን የሚልኩትን መግለጫ ያነበበ፣ ስለሰው ሕይወት ነው የሚናገሩት ወይንስ ስለወፍ
ብሎ መገረሙ አይቀርም።

የአሩሲ ዐይነቱ የስም ማጥፋት ዘመቻ በአፄ ምኒልክ ላይ ሲደረግ የመጀመርያው አይደለም፤ የመጨረሻም እንደማይሆን ርግጠኛ ነኝ። ዛሬ በሥልጣን
ላይ ያለው መንግሥት እንደገባ፣ ሊቅ ነጋሦ ጊዳዳ ከፍተኞች የኦሮሞ ባለሥልጣኖችን ሰብስበው፣አፄ ምኒልክ በጦር ኀይል አሸንፈው፣ የኦሮሞን ሕዝብ
አላንዳች ርኅራኄ የጨፈጨፉበትና ለነፃነቱ ብዙ መሥዋዕት ከፍሎ በግፍ የተገፈፈበት ወዳሉበት ቦታ ወደጨለንቆ እየደነፉና እያጕራሩ እንደሄዱ
ብዙዎቻችን ረስተን ይሆናል። እኔ በተፈጥሮዬ ከፈረንጅ ኋላ ቱስ ቱስ የሚል ሰው አልወድም። ይሁንና ሊቅ ነጋሦን ያገኘሁኋቸው ገና ተማሪ ሳለሁ
በኢጣልያን አገር በሮም ከተማ በዚህ መልክ ነው። ሁናቴው ደስ ባይለኝም፣ የታሪክ ሰው መሆናቸውን ስለማውቅ፣ ላናግራቸው ብሻ፣ ፈረንጁ
ጓደኛቸው በሥነ-ሥርዐቱ ሲያነጋግረኝ፣ እሳቸው ግን ሊቀርቡኝም ሊያነጋግሩኝም አልፈለጉም። ይልቅስ ያኔ ለሥልጣን እጩ ለነበረው መንግሥት
በመመልመል ላይ እንደነበሩ ጓዶቻቸው ሁሉ፣ እሳቸውም ኲምሽሽ ብለው ቁመው ከሩቅ በፍራቻ በስርቆሽ ማየት እንጂ ሰላም እንኳን አላሉም።
ድርጊታቸው ከቃል ይበልጥ ይናገራልና ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ስለሰውዮው ያለኝ ግምት በጣም ዝቅተኛ ነበር። የጨለንቆው ጉዳይ ሲመጣ፣ ከነጭራሹኑ
አዘቀጠው ብቻ ሳይሆን የታሪክ ዕውቀታቸው ምን ያህል አሳዛኝ እንደሆነም ተገለጠልኝ።

የጨለንቆ ውጊያ የተካሄደው ግብፆች ሐረርን ሲለቁ ከሾሙት ከአደሬው አሚር አብዱላሂ ጋር መሆኑን ማንም ያዉቃል። አሚሩ ያነ ቆቱ የተባለውን
የሐረርጌን የኦሮሞ ገበሬ በክፉኛ ጨቁኖ የሚገዛ፣ በሐረር ከተማው ሕዝብ ራሱ ብዙ በደል በመፈጸሙ በጣም የተጠላ ብቻ ሳይሆን፣ የኢጣልያን
መልእክተኞችን በጭካኔ በመግደሉ፣ አካባቢውን ይዘው የነበሩት የፈረንጆች መንግሥታት አጋጣሚውን ተጠቅመው የአሚሩን ግዛት ሊቀራመቱ
በዝግጅት ላይ ነበሩ። አፄ ምኒልክ ሐረርጌ እስከዐራት መቶ ዓመት ድረስ የኢትዮጵያ ግዛት እንደነበረ አገናዝበውት ሲያበቁ፣ አሚር አብዱላሂን በሰላም
እንዲገብር ቢጠይቁት፣ ከቱርክ የበለጠ መንግሥት የለም ካለ በኋላ፣ እርስዎ እስላም ከሆኑ እገብርልዎታለሁ ሲል፣ ሽርጥ፣ ጥምጥምና መስገጃ ምንጣፍ
ላከላቸው። ቀጥሎም ሠራዊታቸው የገና በዓል እያከበረ ተዘናግቶ ሳለ፣ በድንገት ደርሶ የመድፍ ተኲስ ከፈተባቸው። የአፄ ምኒልክ ሠራዊት ከመ ቅጽበተ
ዐይን በሚደንቅ መንገድ ተፈናጥሮ ደርሶ፣ መድፎቹን ማርኮ ቢተኲስ፣ ውጊያው ሳይታሰብ እንደጀመረ ሳይታሰብ በፍጥነት ዐለቀ። ነገሩ የተገላቢጦሽ
ሆነ እንጂ፣ ፍጻሜው ልክ የሮሜው ገናና የጦር መሪ የነበረው ጁልዩስ ቄሣር “መጣሁ፤ አየሁ፤ አሸነፍሁ” እንዳለው ቢጤ ነው። እንግዴህ በአካባቢው
የነበሩት አውሮጳውያን እንደጻፉት፣ ሐረር “የተያዘችው አለምንም ደም መፍሰስና ዝርፍያ” ነበር። እንዳይዘረፍም በየቤቱ በራፍ የአፄ ምኒልክ ዘብ ቁሞ
ይጠብቅ ነበር። አፄ ምኒልክም እንደደረሱ ሁሉም ሰው እንደባህሉና እንደሃይማኖቱ እንዲስተዳደር ማስጠንቀቂያ ሰጥተው የአሚሩን አጎቶች ሹመው
ተመለሱ። ጠፍቶ የነበረው አሚር አብዱላሂ ራሱ ከተደበቀበት ወጥቶ፣ ሐረር የኢትዮጵያ አገር መሆኑን በማሳወቅ፣ “ገብቼ ልገዛ; አገርዎን አያጥፉት”
ሲል ላከ።

እንግዴህ ሊቅ ነጋሦ ኦሮሞች ነፃነታቸውን ያጡበትና ታላቅ ዕልቂት የደረሰባቸው የሚሉት የጨለንቆ ውጊያ እውነቱ እሳቸው ከሚሉት እጅግ በጣም
የራቀ ነው። ይልቅስ አፄ ምኒልክ ኦሮሞችንና ሱማሌዎችን ከጭቈና አላቅቀውአቸው ነፃ አወጥቷቸዋል፤ ሐረርጌም ከአውሮጳ ቅኝ ግዛትነት አምልጣ፣
ከዐራት መቶ ዓመት በኋላ ከናቷ ኢትዮጵያ ጋር ተቀላቀለች። የሚያሳዝነው ግን ሊቅ ነጋሦ ጊዳዳ ተራ የታሪክ ምሁር ብቻ አይደሉም። ምርምራቸውን
ያካሄዱት በኢትዮጵያ ባሕር በወለጋ ውስጥ ባለው በሳዮ ኦሮሞ ላይ ከሺ ሰባት መቶ ሠላሳ እስከ ሺ ስምንት መቶ ሰማንያ ስድስት (1730-1880) ዓ.ም.
የጊዜ ገደባ ውስጥ ስለነበር ከማንም ይበልጥ ስለኦሮሞ ታሪክና ውህደት እንደሚያዉቁ ይጠበቅባቸዋል። የሐረርንም ጭምር። ታዲያ የሐረር ኦሮሞ
ተጨቁኖ የነበረውና ማንነቱን ያጣው፣ በአፄ ምኒልክ ሳይሆን በግብፆች ሥር መሆኑን እንኳንስ እንደሳቸው ያለው ምሁር የታሪክ ጀማሪም ያውቀዋል።
የአፄ ምኒልክ አስተዳደር አብነታዊና በሁሉም ዘንድ የተወደደ እንደነበር ሌላው ቀርቶ አውሮጳውያን ባላንጦቻቸው እንደሚመሰክሩ አይተናል።

ከዚህ በላይ ባጭሩም ቢሆን እንደተገለጸው፣ አፄ ምኒልክ ያቋቋሙት ያስተዳደር ሥርዐት በዛሬ ዘመን ሲታይ ወደፈዴሬሽንነት ይጠጋል። መሠረታዊ
መመዘኛው ባህልና ታሪክ እንዲሁም የሕዝቡ ምቾትና ልምድ ሲሆን፣ አንዳንዴ ሃይማኖትንም ቋንቋንም ጭምር የሚያስተናግድ ቢሆንም፣ በነኚህ
መለዮች ብቻ ተወስኖ እንደመንጋ ከብት ባንድጋ አያጉራቸውም። ጐጃምና በጌምድር የሚዋስኑ አገሮች ናቸው፤ በሃይማኖትና በቋንቋ አንድ ናቸው።
ሁኖም የተለየ ታሪክና ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ የራሳቸው የሆነ ያስተዳደር ትውፊት ስላላቸው ልዩነታቸውን እንደያዙ ቀጥሏል። እንደዚሁም አብዛኛው
የወለጋና የከፋ ሕዝብ በሃይማኖትም ሆነ በቋንቋ ተመሳሳይነት ቢኖራቸውም፣ በታሪክ፣ በባህልና ባስተዳደር የየግላቸው ስለነበሩ ልዩነታቸው
እንደተጠበቀ ሁኖ ተዋቅሯል። አወቃቀሩ ማናቸውም ጤናማና እውነተኛ የፈዴሬሺን ሥርዐት ያላቸው አገሮች የተከተሉት ነው ለማለት ይቻላል።
ለምሳሌ የአሜሪቃን ፈዴሬሽን የመሠረቱት ዐሥራ ሦስቱ መንግሥታት በቋንቋ፣ በትውልድ፣ በእምነትም አይለዩም። እናት አገራቸውን እንግሊዝን
አሸንፈው ነፃ በወጡ ጊዜ በዐሥራ ሦስቶቹ ፈንታ በአንድ መንግሥት ብቻ መዋቀር ሲችሉ፣ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣውን የየግላቸውን አስተዳደር
ላይለቁ ብለው በፌዴሬሽን ተቋቋሙ። ሌሎችም በሠለጠኑ አገራት ያሉት በፌዴሬሽን የተዋቀሩት መንግሥታት (ለምሳሌ ያህል እንደጀርመን ያሉት)
የተከተሉት መልክ ነው።

አፄ ምኒልክ ዘመናዊነትን ባገር ውስጥ ለማስገባት ያልነኩት የሥልጣኔ መስክ፣ ያላደረጉት ጥረት የለም። በያንዳንዱ መስክ ከፍተኛ ተቃውሞ
ገጥሟቸዋል። ግን ሁሉንም በትዕግሥትና በብልሃት በመያዝ ተወጥተው አስፈላጊ መሠረቶችን በመጣል፣ ኢትዮጵያን በዘመናዊ ሥልጣኔ ተራማጅ
ኀይሎች አንዷ እንድትሆን ለማድረግ በቅተዋል። በጣሉት መሠረት ላይ ማነጽና የተሻለች ኢትዮጵያ መገንባት የያንዳንዱ የተከታዩ ትውልድ አላፊነት
ነው።

ደጋግሜ እንደተናገርሁት፣ አፄ ምኒልክ በተለያዩ ባላባቶች ሥር ሁኖ እርስ በርሱ ይተላለቅ የነበረውን ሕዝብ፣ ባንድ ሰንደቅ ዓለማ ሥር ሰብስበው አንድ
ቤተሰብ አድርገውታል። በርስበርስ ፍጅት ፈንታ፣ ተከባብሮ፣ ተቻችሎና ተፋቅሮ እንዲኖር ለማድረግ ሲሉ ባደረጉት ድርጊት የተወሰነ መሥዋዕት
መኖሩ ርግጥና የማይካድ ነው። ሁኖም ሌሎች ብዙዎች አገሮች ለዚሁ ዓላማ ሲሉ ከከፈሉት ጋር ቢነፃፀር መሥዋዕቱ በጣም ዝቅተኛ ነው ማለት
ይቻላል። ሁኖም አንዲት እናት ሕፃኗ እንደተወለደ ምንም እንኳን አሰቃቂ ቢሆንም፣ ምጧን ረስታ በሕፃኗ ደስታ ተዉጣ እንደምትቀርና ርብርቦሿና
ትኩረቷ በሙሉ ጫቅላዋ አድጎ ለወግና ለማዕረግ እንዲደርስላት ሌት ተቀን አለዕረፍት እንደምትንከባከብ ሁሉ፣ እኛም የኢትዮጵያን ያንድነት ግብ Page 14 of 15

ለመምታት የተፈጸመውን ሥቃይና የተከፈለውን መሥዋዕት በእልልታ፣ በጸጋና በደስታ ተቀብለን፣ መሯሯጥና መሽቀዳደም ያለብን ሙጪቷን አገር
አደጋ ሳይነካት አንድ ሁነን በጥንቃቄ ገንብተን በዓለም-አቀፍ መድረክ ላይ ሳትደፈር ተከብረና ተፈርታ ከፍተኛ ሚና እንዲትጫወት ማብቃት ነው።

አንድ መረዳት የሚገባን ነገር ቢኖር፣ ከውጥኑ ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ፍጹም ሆኖ የተቈረቈረ አገር በታሪክ ውስጥ እስካሁን ድረስ አልታየም፤ ሊታይም
አይችልም። ቢሆንማ የትውልድ መተካካት ዋጋ አይኖረውም ነበር። ምክንያቱም ሥራው ሁሉ በፊተኛው ትውልድ ፍጹም ሁኖ ተሠርቶ ካለቀና
ከተላለፈ፣ ተረካቢው ትውልድ የራሱን ታሪክ የሚሠራበትን ዕድል ያጣል። አሁን በዓለም ተፈርታና ተደንቃ የሚትኖረው አሜሪቃ እንኳ እንዴት
እንደተቈረቈረች ቢናይ፣ ህልውናዋ የተጣለበት መሠረት ከልክ በላይ አሳዛኝና ግፈኛ ነበር ማለት ይቻላል። ቈርቋሪዎች አባቶች ተብለው የሚጠሩት
መሥራቾቿ በጣም ከፍ ያለና ከዚህ በፊት ባለም ታሪክ ተሰምቶ ያልተወቀ መልእክት ያዘለ መግለጫ ቢያስተጋቡም፣ በግብር ላይ የታየው ግን አነሳው
የቀረውን አብዛኛውን ሲጨቊን ነው። ሕጓ ለሁሉም ሰው የመኖር፣ ደስተኛና ነፃ የመሆን መብት ማንም የማይፈለማቸው ከእግዚአብሔር የተሰጡት
የተፈጥሮ መብቶች ናቸው ቢልም፣ ከሰው እንደማይቈጠሩ፣ ወይንም እኩል አይደሉም ተብለው ስለሚታሰቡ፣ ሕጉ ሴቶችን፣ ጥቊሮችንና፣ ያገሩን
ተወላጅ ራሳቸውን ህንዶቹን፣ እንዲሁም ድሆችንና መሃይምኖችን አያጠቃልልም ነበር። ባጭሩ የአሜሪቃ አብዮት የተባለው ሥርዐት የፈጸመው ተግባር
እግዚአብሔር መርጦ ለሥልጣን ያበቃል የሚለውን የፖሊትካ መርህ፣ የገዢው ክፍል ዋና መመዘኛው መሆን ያለበት ሀብቱ ነው በሚል ተካ፤ ሕዝባዊ
መንግሥት ወይንም ደሞክራሲም ተብሎ የተቋቋመው አስተዳደር፣ ጥንተ መሠረቱ በሀብታሙ የነጭ ወንድ ለሀብታሙ [የነጭ ወንድ] የተመረጠ
መንግሥትን እንጂ ሌላውን የአገሩን ነዋሪ ያካተተ አልነበረም። ሌሎቹ፣ በጾታ፣ በቀለምና በዘር፣ እንዲሁም በዕውቀትና በሀብት ሰበብ የተነፈጉትን
መብቶቻቸውን ያገኙት፣ የተጧጧፈ ትግል በየጐራቸውና በየፊናቸው በማካሄድ ነው። እነዚህ በየመስካቸው የተቀናጁት ድል፣ አገራቸውን እጅግ በጣም
አሻሽሎ፣ የማንም ሰው መመዘኛው ችሎታውና ምግባሩ እንጂ አስፈላጊ እስካልሆነ ድረስ ከቶውኑ በሌላ ዐይነት መለኪያ ማንም መፈረጅ የለበትም
የሚለውን አቋም የመንግሥታቸው መርህ ለማድረግ በቅተዋል።

አፄ ምኒልክ ያዋሃዷት ኢትዮጵያ አሜሪቃን ከላይ ባየናቸው ልዩነቶች ተመሥርቶ፣ ለዘመናት ከከፋፈላትና ካተራመሳት የመድሎ የአስተዳደር እንከን ነፃ
ሁና የተቋቋመች አገር መሆኗን ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ገልጫለሁ። በዘርና በጾታ፣ወይንም በቋንቋ፣ ካልሆነም በሃይማኖት ወይንም በንብረት ምክንያት
ለባርነት የተዳረገ፣ ወይንም ለሥልጣን እንዳይታጭ፣ ለወግና ለማዕርግ እንዳይበቃ የተደነገገ ሕግም፣ ኅብረተ-ሰብም፣ የኅብረተ-ሰብ መደብም
በኢትዮጵያ የለም። በዚህ ረገድ ባንረዳ ነው እንጂ አፄ ምኒልክ አንድ አድርገው ያስረከቡልን ኢትዮጵያ በጣም የተባረከች አገር ናት፤ ተረካቢዉም
ትውልድ እጅግ ዕድለኛ ነው ማለት ይቻላል። ይኸም ሁናቴ ኢትዮጵያን ከብዙ በዘመናዊ ሥልጣኔ ከገሠገሡ መንግሥታት ይለያታል።

የኢትዮጵያ ችግሯ በዘመናዊ ሥልጣኔ ወደኋላ-ቀርነትና የዘመናዊ ዕውቀት እጥረት ነው። ከመዋሃዷ በፊት ባላባቶችና ጐሦች ትርፍ ጒልበታቸውንና
ሀብታቸውን በርስበርስ ፍጅት በማዋል፣ አገሪቷን ወደጦር ሜዳነት ለውጧት ነበር። ይኸንን አፄ ምኒልክ አከተሙት። ሁላቸውንም ጠበኞች በድሮዪቷ
ኢትዮጵያ ጐጆ ሥር ሰብስበው ሲያበቃ፣ ከንግዴህ ወዲያ እያንዳንዱ ትርፍ ጒልበቱንና ሀብቱን በፈለገበት የትምህርት ገበታ ዙርያ እንዲያውል፤
በተመረቀበትም ሙያ ተሰማርቶ ያዋሀዷትን አገር በተራው እንዲያሻሽል አደራ ሰጥተው ወደማይመለሱበት ዓለም ሄዷል።

ጀነራል ጃገማ ኬሎ እንዳሉት፣ በአስተሳሰብም ሆነ በሙያ ዘርፍ ጠባብ በነበረው በጐሦችና በባላባቶች ዓለም ይኖሩ የነበሩት አባቶች የጀብድነታቸ
መለኪያና ምልክት በሚጥሉት ግዳይ በሚያስቈጥሩት ሚርጋ የተመጠነ ነበር። አሁን ግን ይኸ ዐይነት ድርጊት ያልተገራ አውሬ ብቻ ነው የሚፈጽመው።
በዛሬ ዘመን የጀብዱ ሚርጋ የሚቈጠረው እያንዳንዱ ለአገርና ለኅብረተ-ሰብ ዕድገትና ልማት በሠራው ሥራ ነው። ከዚያም አልፎ በተሰማራው የሙያ
ዘርፍ በሚያገኘው ፍልሰፋና ምርምር እኩዮቹን ሲያስከነዳና፣ ለዓለም ሕዝብ በጠቅላላ ጠቃሚ አገልግሎት ሲሰጥ ነው። አፄ ምኒልክ ይኸንን ዓላማችን
አድርገን ባገር ውስጥም ሆነ በዓለም መድረክ ላይ እንድናበረክት ዕድሉንና በሩን በሰፊው ከፍተዋል። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ እውድድሩ ሜዳ ገብቶ
ድርሻውን ለአገሩም ለዓለምም መክፈል እንዲችል መንፈሱን አደራጅተዋል፤ አገሩን አደላድለው ካበቁ በኋላ የዘመናዊ ሥልጣኔን መሠረት ጥለው
ሜዳውን አመቻችተዋል። ካርል ማርክስ እንዳለው በበግነት ስሜት እንጂ በሰብኣዊ ልቡና የማይመራውን የጐሣንና የባላባቶችን ዓለም ማድነቅም ሆነ
ከሞተበት ለማንሣት መሞከር ከታሪክ ጋር ግብግብ መያያዝ ነው። አያዋጣም፤ እንዲሁም እሳቸውን ራሳቸውን መውቀስ፣ ከሙት ጋር መሟገት ሰለሆነ
ርባን የለዉም። የራስን ድርሻ መወጣትና የተረከቡትን አሻሽሎ ማስተላለፍ ግን በታሪክ የሚጠየቅ ግዴታ ነው።

አፄ ምኒልክ የወረሷት ኢትዮጵያ በውስጥም በውጭም ጠላት ፊት ለፊት በመፋጠጥ ላይ ስለነበረች ህልውናዋ ራሱ አጠይያቂ ነበር። ሲለዩአት ግን
ህልውናዋና ነጻነቷ በመላው ዓለም የተረጋገጠ ብቻ ሳይሆን፣ በነጮች የቅኝ ግዛት ቀንበር ሥር ለነበሩት ሁሉ አለኝታቸውና የነፃነት ጨረራቸው፣
የህልውናቸው ዕርቡን ነበረች። “በልቤ ውስጥ ኢትዮጵያ ሁሌዬ ልዩ ቦታ አላት። ወደፈረንሳይና ወደእንግሊዝ፣ እንዲሁም ወደአሜሪቃ ባንድጋም ሆነ
ለየብቻቸው ሽርሽር ከመሄድ ይልቅ፣ እጅግ በጣም ይጐመጀኝ የነበረው ኢትዮጵያን የመጎብኘት ፍላጎት ነበር። ኢትዮጵያን ስጐበኝ፣ የገዛ ራሴን ጥንተ
ልደት ብቻ ሳይሆን አፍሪቃዊነቴንም ጭምር ቈፍሬ የማገኝ መስሎኝ ይታየኝ ነበር።” ሲል ኢትዮጵያን በመወደስ ኔልሶን ማንዴላ የጻፈው ስሜትና
አስተያየት በአብዛኛው ጥቊር ሕዝብ ልብ ውስጥ ያለ ነው ቢባል ሐሰት አይደለም።

ኔልሶን ማንዴላ ውዳሴውን የጻፉት አሻፈረኝ አልቀበለውም ብለው ለኻያ ሰባት ዓመት ሕይወታቸውን በእስር ቤት በመጐሳቀል የሰውበት በጐሦች
ክልልና ሥርዐት የተዋቀረ መንግሥት እምኒልክ ቤተ-መንግሥት ከመቀመጡ በፊት ነበር። ከእስር ቤቱ እንደተፈቱ መጀመርያ ላይ ከጐበኙት አገሮች
መካከል አንደኛይቷ የሚያደንቋት የአፄ ምኒልክ ኢትዮጵያ ነበረች። ዘውገኞቹ ሥልጣን ከጨበጡ በኋላ ግን በአገሪቷ ጠፈር ላይ በየጊዜው እየበረሩ
ሲያልፉም ሆነ ብዙ ዕድልና ገጠመኝ ኑሮላቸው እያለ፣ አንድ ጊዜም እንኳን አልመጡም፤ ዞር ብለውም ሊያዩ አልፈለጉም። ርግጠኛ ነኝ የወሰዱት አቋም
አፄ ምኒልክንም፣ ልክ በዘረኛው የደቡብ አፍሪቃ መንግሥት ራሳቸው እንደማቀቁ ሁሉ፣ በጐጠኛው መንግሥት ቀንበር ሥር የሚጥረውን የኢትዮጵያን
ሕዝብ ላያሳዝኑ ብለው ይሆናል። እንግዴህ ከዚህ የከፋ ኲነኔ ሊኖር አይችልም። ለአፄ ምኒልክም ሆነ እሳቸው ላዋሀዷት ኢትዮጵያ ያላቸውን
አድናቆትና ሙገሳ በሰላ አንደበታቸው፣ በወርቃማ ብዕራቸው ጽፈው ለልጅ ልጅ የሚተላለፍ ዕጹብ ድንቅ የሆነ ማስታወሻ ትተዋል። በመላ ዓለም
ታላቅነታቸው የተወደሰው ኔልሶን ማንዴላ ያከበሯቸውና ያደነቋቸው አፄ ምኒልክና ሥራቸው፣ በጥራዘ-ነጠቁና እቤተ-ክርስቲያን ውስጥ እንደገባ ውሻ
በየሄደበት በሚባረረው ቢዋረዱና ቢጠሉ በፍጹም አይደንቅም። መጠበቅም ያለበት ነው። ሥራቸው ጥርት አድርጎ የሚያሳየው ተቃራኒውን ነው። የአፄ
ምኒልክን ታላቅነትና ገናናነት፣ የአሽሟጣጮቻቸውን ከንቱነትና ብኩንነት። Page 15 of 15


***************************
+++++++++++++++++++







ኢትዮሚድያ - Ethiomedia.com
February 9, 2014